የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሻረው! በርካታ ሚልዮን የምእመናን ገንዘብ የተመዘበረበት የድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታና ሒሳብ በብቁ እና ገለልተኛ ባለሞያዎች እንዲመረመር ቅ/ሲኖዶሱ ያስተላለፈውን ውሳኔ ልዩ ጽ/ቤቱ እንዲዘገይ አዘዘ

???????????????????????????????

በውል ከተያዘው ገንዘብ ውጭ ከ8 ሚልዮን በላይ ብር የወጣበትና ሥራው ሳይጠናቀቅ በ6 ዓመት የዘገየው የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግድግዳ ተሰነጣጥቋል፤ ዋናው መካከለኛ ጉልላት እንዳይወድቅ ያሰጋል

 • የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ገቢና ወጪ ኦዲት እስከ ግንባታው ፍጻሜ መዘግየቱ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ተፈጻሚነት አዳጋች እንደሚያደርገውና የግንባታው ሒደት ምርመራም ከግንባታው መጠናቀቅ በኋላ እንዲኾን መታዘዙ የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ እንደሚያሥነሳ የገለጹ ምእመናን፣ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ያስተላለፈውን ትእዛዝ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡
 • የኦዲት ምርመራው እንዲዘገይ ከድሬዳዋና ምዕራብ ሐረርጌ ሊቀ ጳጳስ ጋራ እንደተስማሙ አስመስለው ለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ያስረዱት ብርሃኔ መሐሪ፣ በአድራሻ ለፓትርያርኩ በግልባጭ ደግሞ ለድሬዳዋ ሀ/ስብከት ጽ/ቤትና ለሳባ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በጻፉት ይዘቱ የተለያየ ደብዳቤ÷ ‹‹ማን እንደሚመራው የማይታወቅ ሲኖዶስ ግራና ቀኙን ሳያጣራ በግብር ይውጣ ያስተላለፈው ነው›› በሚል ቋሚ ሲኖዶሱ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ያስተላለፈውን ውሳኔ ማጣጣላቸው ተዘግቧል፡፡
 • የደብሩን የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ በብቸኝነት የሚያዝዙበት መዝባሪው ብርሃኔ መሐሪ፣ በብፁዕ አቡነ ገሪማ የበላይ ሓላፊነት የሚመራው የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ከፓትርያርኩ እንደተሰጠው በተገለጸ መመሪያ መሠረት የኦዲት ምርመራውን እስከ ግንባታው ፍጻሜ በማዘግየቱ ዝርፊያውን ያጋለጡ ተሟጋች ምእመናን ‹‹ምንም አታመጡም›› በሚል እየተሳለቁባቸው ነው፤ የደብሩ አስተዳዳሪንም ‹‹በአቋም ወደ እኛ የማትመጣ ከኾነ እናበርሃለን›› ሲሉ ዝተውባቸዋል፡፡
Lique Tiguhan Birhane Mehari00

የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ትእዛዝ ያስተጓጎሉት ‹ሊቀ ትጉሃን› ብርሃኔ መሐሪ
‹‹ምንም አታመጡም!››

 • መዝባሪው ብርሃኔ መሐሪ ከጥቅመኞቹ የሕንፃው ተቋራጭ ኤፍሬም ተስፋዬ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ ኢንጅነር ሰሎሞን ካሳዬ ጋራ በመኾን በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤቱ እንዲተላለፍ ያደረጉት ለሙስናና አማሳኞች ሽፋን የሚሰጠው ትእዛዝ፣ የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አሳዝኗል፤ የከተማውን ምእመናን አበሳጭቷል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ምእመናኑን ዛሬ በጉዳዩ ላይ እንደሚያወያዩ ተጠቁሟል፡፡
 • ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ÷ ከሀ/ስብከቱ፣ ከደብሩ ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ት/ቤት በተውጣጡ ተወካዮች አማካይነት የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ የገቢና ወጪ ሒሳብ ኦዲትና የግንባታ ሒደቱ ምርመራ ቋሚ ሲኖዶስ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ለማስፈጸም ብቁና ገለልተኛ ባለሞያዎች የሚመረጡባቸውን አግባቦች በማዘጋጀት ላይ የነበሩ ሲኾን የምርመራ ሪፖርቶቹ እስከ ሚያዝያ ፲፱/፳፻፮ ዓ.ም. ተጠናቅቆ እንዲቀርብ ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡
 • የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ማስፈጸም ያለበት የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ከመዝባሪዎች ጋራ የመከረበትን ትእዛዝ ሳይኾን የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ መኾን እንደሚገባው ያሳሰቡት የደብሩ ምእመናን፣ ትእዛዙ ‹‹የፓትርያርኩ ፀረ ሙስና አቋም በተግባር የተፈተነበት ነው፤›› ብለዋል፡፡
 • የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በአድራሻ ለሀ/ስብከቱ በግልባጭ ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ ትእዛዙን ያስተላለፈበት ደብዳቤ ትላንት በደብሩ አስተዳዳሪ በንባብ በተሰማበትና የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ ፓትርያርኩ የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ መሻር እንደማይችሉ የገለጹት ምእመናኑ እንዳስጠነቀቁት÷ የኦዲት ምርመራው በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት የማይፈጸም ከኾነ በደብሩ ሕንፃ ግንባታ ስም የሚካሔዱ ማንኛውንም የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴዎች በማገድ ለመንግሥት አቤት ይላሉ፡፡

*                         *                       *

 

 • በጥቅምት ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ዊነር ኮንስትራክሽን ከተባለው ደረጃው ከማይታወቅ የአቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ተቋራጭ ጋራ በተያዘ ውል፣ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ በ2 ዓመት ጊዜና በ2‚984‚562.51 ሚልዮን ብር ወጪ መጠናቀቅ ነበረበት፡፡ ከውለታ ጊዜው ውጭ ለ6 ዓመታት የዘገየውና 8 ሚልዮን ብር የፈጀው የግንባታ ሒደት ግን ከ70 – 80 በመቶ ብቻ እንደተፈጸመ ነው የተመለከተው፡፡
 • የግንባታ ፈቃድ ባለውና ደረጃው በተለየ መሐንዲስ ቁጥጥር ተደርጎበት የማያውቀው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ÷ ሥራው ከዲዛየኑ ውጭ ስለመከናወኑ፣ ምእመናን በዐይነት የሚያበረክቷቸው አስተዋፅኦዎች (ቆርቆሮ፣ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ አሸዋ) በአግባቡ ተተምነው ገብተው ወጪ እንደማይደረጉ፣ በዓመት ሁለት ጊዜ ለቅ/ገብርኤል ክብረ በዓል በግንባታው ስም የሚሰበሰበው ከፍተኛ ገቢ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴውን በብቸኝነት ከሚቆጣጠሩትና የግል ኢንቨስትመንታቸውን በማጧጧፍ ላይ ካሉት ብርሃኔ መሐሪ በቀር በሚመለከተው አካል በትክክል እንደማይታወቅ በኅዳር ወር ፳፻፭ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተሠየመው አጣሪ ልኡክ ለቅ/ሲኖዶሱ ባቀረበው ሪፖርት ተረጋግጧል፡፡

Lique Tiguhan Birhane Mehari03

 • ቋሚ ሲኖዶሱ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ገቢና ወጪ እንዲሁም የግንባታው ሒደት በብቁና ገለልተኛ ባለሞያዎች እንዲመረመር መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ያስተላለፈው ውሳኔ፣ ለሦስተኛ ጊዜ የተሠየመው የጠቅ/ቤ/ክህነቱ አጣሪ ልኡክ ባቀረበለት ሰፊ ሪፖርት ላይ የተመሠረተ ኾኖ ሳለ፣ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ ከግንባታው ፍጻሜ በፊት እንዳይካሔድ ማዘዙ በርግጥም የፓትርያርኩ የፀረ ሙስና አቋም ከኹኔታዎች ጋራ እንደሚጋሽብ የሚያመላክትና በመግለጫዎች የሚናገሩለትን ቆራጥነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መኾኑ አይቀርም፡፡ 

   

 • የድሬዳዋ ሀ/ስብከትን ከአዲስ አበባ ኾነው ለሁለት ዓመታት የመሩትና በሕንፃው ግንባታ ዙሪያ ሲቀርቡ ለቆዩት የምእመናን ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ያሉት የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ የሚጋፋውን የኦዲት ምርመራ የሚያዘገየውን ትእዛዝ በፊርማቸው ወጪ ያደረጉት በፓትርያርኩ መመሪያ ነው ቢባልም ወቀሳንና ተጠያቂነትን የሚያስቀርላቸው አይኾንም፡፡ – ‹‹ብፁዕ አባታችን፣ በድሬዳዋ ሳባ ደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እየተፈጸመ የሚገኘው ከባድ ወንጀል ሕዝበ ክርስቲያኑን እያስቆጣ ከመምጣቱም ባሻገር ብፁዕ አባታችን ይህን እየሰሙና እያወቁ ምነው ዝም አሉ ብሎ ሕዝቡ እንዲያስብ አድርጎታል፡፡… የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ጅምር ሥራ አልቆ ማየት እንፈልጋለን፡፡ የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ በአስቸኳይ ሕዝቡ በሚመርጣቸው የኮሚቴ አባላት ይተካልን፡፡ ይህ የማይደረግ ከኾነና ኹኔታው ባለበት ከቀጠለ ለሚፈጠረው ችግር ሓላፊነቱን የማንወስድ መኾኑን እናሳውቃለን፡፡›› /የደብሩን ወቅታዊ ጉዳይ ለማሳወቅ ምእመናኑ በኅዳር ፳፻፬ ዓ.ም. ለብፁዕ አቡነ ገሪማ ከጻፉት አቤቱታ የተወሰደ/

Holy Synod decision on D.D.St.Geb bld. AuditHoly Synod decision on D.D.St.Geb bld. Audit01

Advertisements

6 thoughts on “የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሻረው! በርካታ ሚልዮን የምእመናን ገንዘብ የተመዘበረበት የድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታና ሒሳብ በብቁ እና ገለልተኛ ባለሞያዎች እንዲመረመር ቅ/ሲኖዶሱ ያስተላለፈውን ውሳኔ ልዩ ጽ/ቤቱ እንዲዘገይ አዘዘ

 1. yohan January 23, 2014 at 8:17 pm Reply

  eskemche new endew lewune yemimot abat yemnnafkew ?

  • Anonymous February 14, 2014 at 11:05 am Reply

   I read I, two more times, the people of Ethiopia in this case the Orthodox Church followers, they don’t understand what the definition of <>. Because they did not understand the will of GOD, written in the bible, the translates must be<> and chosen by almighty GOD. it is simple logic that, our churches are business organization, intended to raise money to the<> groups of priests go officials in the name of GOD terrifying the followers of the church drawing the designee of <>,the depth, width and how fire full and cold over all the internity of hell . if the followers of the church give their money to the church they are granted to haven where there is no suffering and pain and no death this is a game between the wise and the fools citizen of certain country to our case ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH FOLLOWERS. O my fellow countrymen, how long are you going being fool and allowing yourself be full.

 2. DADI January 24, 2014 at 7:39 am Reply

  መቆርቆር ጥሩ ነው፡፡ግንባታው ለምን በጊዜው እና በተቆረጠለት ጊዜ አንዳልተጠናቀቀ ማብራሪያ መጠየቅም ተገቢነት አለው፡፡ግን ደግሞ…..
  1. የፓትርያርኩ ጽ/ቤት ኦዲት እንዲዘገይ ያዘዘው በምን ምክንያት እንደሆነ ሳያጣሩ ደርሶ ፓ/ኩ ተፈትነው ወደቁ ለማለት መፍጠን ችኩል ያሰኛል፡፡ የልማት ኮሚቴውና የተቁዋራጩ መከራከሪያ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በእንድ ወገን በቀረበ መረጃ ብቻ መደምደሚያ ላይ መድረስም ይቸግረናል፡፡ የግንባታ ውሉን ሙሉ ይዘት ሳይመረምሩ ውሳኔ ላይ መድረስም ተገቢ አይሆንም፡፡
  2. የግንባታ ውል በባህርዩ እርግጠኝነት የሚጎድለው ነው፡፡ ለመነሻ ያህል ካልሆነ በቀር በዚህ ጊዜ በዚህ ዋጋ ያልቃል ማለት ያስቸግራል፡፡በየአካባቢያችን ያሉ ህንጻዎችና መንገዶች መቼ ያልቃሉ ተብሎ መቼ እንዳለቁ ማየት ነው፡፡
  3. ለምሳሌ፡አሁን በቀረበው ጉዳይ ውሉ የተደረገው በ1998ዓ.ም ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የነዳጅ፣የብረት፣የሲሚንቶ፣የውጭ ምንዛሬ፣የጉልበት ሰራተኛ ዋጋ ምን ያህል እንደተለዋወጠ እናውቃለን፡፡ በብዙ የግንባታ ውሎች ደግሞ የዋጋ ማስተካከያ አይደረግም የሚል አንቀጽ (no refund or adjustment for price escalation) በውሉ ውስጥ ካልገባ በቀር ለነዚህ የዋጋ ለውጦች ሀላፊነቱ የተቁዋራጩ ሳይሆን የውል ሰጭው ነው፡፡ በዚህ ላይ በውል ሰጭው ክፍል ማለትም በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር አካባቢስ ለተቁዋራጩ ስራ አመቺ ሁኔታ ተፍጥሮ ነበር፣ክፍያዎችስ በጊዜው ይፈጸሙለት ነበር፣የግንባታውን ይዞታስ በወቅቱ ነው አመቺ አድርጎ ያስረከበው ለሚሉት ጥያቄዎች የሚቀርበው መልስ ጥፋተኛውን በመለየት ረገድ ዐቢይ አስተዋጽኦ አለው፡፡
  4. በተቁዋራጩ በኩልም በቂ የፋይናንስና የሰው ሀይል መድቦ ሲሰራ ነበር፣በእሱ ቸልተኝነት ምክንያት ስራው እንዳይጉዋተት በቂ ጥረት አድርጉዋል፣ከአማካሪ መሀንዲሱና ከአሰሪው ክፍል ማስጠንቀቂያ ደርሶታል፣ላልተሰራ ስራ ክፍያ ጠይቁዋል፣እና የመሳሰሉት ከአንድ ተቁዋራጭ የሚጠበቁ ግዴታዎች በሙሉም ሆነ በከፊል ስላለመሙዋላታቸው ሳናረጋግጥ ተቁዋራጩን ተጠያቂ ማድረግ ይከብዳል፡፡
  5. ስለዚህ እንደኔ የቀረበው ዘገባ ትክክል አይደለም ባልልም የጉዳዩን ሙሉ ስእል የሚሰጥ ግን አይመስለኝም፡፡ ባጭሩ በዘገባው የፓ/ኩ ጽ/ቤት በምን መነሻ የማዘግየቱን ውሳኔ እንደሰጠ፣የልማት ኮሚቴው ውሳኔውን ለማሰጠት ያቀረበው አቤቱታ ይዘት ምን እንደሆነ፣ተቁዋራጩና የግንባታው አማካሪ መሀንዲስ ምን አይነት መልስ እንደሰጡ ሳይታወቅ በአንድ ወገን በቀረበ መረጃ ብቻ እንዲህ ነው እንዲያ ነው እያሉ የግለሰቦችን ስም ወደ መዘርዘር መግባት አንድም ኢ-ፍትሀዊ ነው እንዲያም ሲል ሳይሞቅ ፈላ ያሰኛል!!!

  • haratewahido January 24, 2014 at 7:52 pm Reply

   Dear Samuel, please refer to previous reports for all your concerns. Tnxs.

 3. Anonymous January 28, 2014 at 1:37 pm Reply

  benatachuu ye abbatochin sim atatfu beteley ahun abune gerima min yawkalu shimagilee nachew sim atfi selefii

 4. Anonymous February 3, 2014 at 7:48 pm Reply

  የሃራ ተዋህዶ ባልተቤቶች ከንቱዎች ናቸሁ አባት ሚባል ቀርቶ የሚመስል እን ቤተክርስቲያኒቱ የሌላት መሆኑን ሁለም አማንኝ ተገንዝቦ ያለበት ዘመን መሆኑን ብታዉቁ ኖሮ ጽሁፋችንን ባልደመሰሳችሁት ነበር በሉ እናንተን ወንበዴዎቹ ጳጳሳት ለስርየት ያብቁአችሁ እኛ ግን ሽፍታን አባት አንልም

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: