ፓትርያርኩ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በሙስና ላይ እንዲዘምቱ አዘዙ

  • በቤተ ክርስቲያናችን ሸፍጥና ጉቦ ተንሰራፍቷል›› /ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
  • ሰንበት ት/ቤቶቹ የአማሳኝ አስተዳዳሪዎችን ዶሴ ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፩፤ ቅዳሜ ጥር ፲ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

His Holiness Patriartch Abune Mathias

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በተንሰራፋውና ለዕድገቷ መሰናክል ኾኖ በተደነቀረው ሙስናና ሸፍጥ ላይ በተጠናከረ ኃይል በመዝመት የተጀመረውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ከዳር እንዲያደርሱ አዘዙ፡፡

Dn Yonas Isayas of A.A.D SSD Unity reading the position paper

የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር ተወካይ ዲያቆን ዮናስ ኢሳይያስ ለፓትርያርኩ የፁረ ሙስና እንቅስቃሴ፣ ለአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተግባራዊነት የሰንበት ት/ቤቶቹን የድጋፍ መግለጫ ሲያሰማ

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ቅዱስነትዎ በይፋ የገለጹትንና እንዲስተካከል አበክረው ማሳሰቢያ የሰጡበትን የቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ችግር ለማረም በሚደረገው ጥረት ኹሉ በግንባር ቀደምነት መሰለፍ የእኛም የወላጆቻችንም ጽኑ አቋም እንደኾነና በታዘዝንበት መሥመር ኹሉ ለመሰለፍ ዝግጁዎች መኾናችንን ለቅዱስነትዎ በላቀ አክብሮትና ትሕትና ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ 

 

አቡነ ማትያስ ትእዛዙን የሰጡት ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን በሥር ነቀል እርማት ለማስተካከል ያስተላለፉትን መግለጫ ለመደገፍና የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት የኾነው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ያዘጋጀው የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት ተግባራዊ እንዲኾን ለመጠየቅ ከትላንት በስቲያ ኀሙስ፣ ጥር 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ለተሰበሰቡት በሺሕ ለሚቆጠሩ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በሰጡት መመሪያ፣ ቃለ ምዕዳንና የበዓለ ጥምቀት ቡራኬ ነው፡፡

ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት 160 ገዳማትና አድባራት የተሰበሰቡት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በሀ/ስብከቱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር አማካይነት ባወጡት መግለጫ፣ ፓትርያርኩ ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን በማውገዝ ለማስተካከል አበክረው ሥራ በመጀመራቸው ምስጋናቸው አቅርበዋል፡፡ ብዙኃን የሰንበት ት/ቤት አባላት አይነኬ ኾኖ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያስተቻት የቆየውን ሙስናና ብልሹ አስተዳደር እስከ እስር ደርሰው ሲታገሉት እንደቆዩም ተናግረዋል፡፡

የሙስናና ብልሹ አስተዳደር ተጠቂ እየኾኑ በማደጋቸው አስከፊነቱን በሚገባ እንደሚያውቁ በመግለጫቸው ያተቱት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶቹ፣ ፓትርያርኩ በየጊዜው ያስተላለፏቸውን መመሪያዎች በመከታተልና የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤትና በየክፍለ ከተማቸው በመወያየት ችግሩ ከመሠረቱ እንደሚወገድና በዘመናቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ትንሣኤ እንደቀረበ መገንዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

ሙስናንና ብልሹ አስተዳደርን ለማረም የሚካሔደው እንቅስቃሴ በእነርሱም በወላጆቻቸውም ጽኑ እምነት እንደተያዘበት የጠቀሱት ወጣቶቹ፣ ጥረቱን ከግቡ ለማድረስ ከፓትርያርኩ ጎን ቆመው በታዘዙበት መሥመር ለመሰለፍ ዝግጁዎች መኾናቸውን አስታውቀዋል፡፡

Sunday School Students of Holy Trinity Cathedral headind to Jan Meda,2004E.CTimket

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ወደ ጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀት ሲያመሩ

‹‹የፀረ ሙስና እንቅስቃሴውን እንደግፋለን ብላችኁኛል፤ እኔም እንደምትደግፉኝ አምናለኹ፤›› በማለት ተስፋቸውን የገለጹት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በበኩላቸው÷ ‹‹ዘመኑ የእምነት ጉድለትና የኑፋቄ ነው፤ ሐቅ፣ መልካም አስተዳደር፣ እውነተኝነትና ሓላፊነት ጠፍቷል፤ በቤተ ክርስቲያናችን ሸፍጥና ጉቦ ተንሰራፍቷል፤›› ሲሉ አምርረው ተናግረዋል፡፡ ስለ ሙስናና ብክነት ከሚሰጧቸው ተደጋጋሚ መግለጫዎች ጋራ ተያይዞ ‹‹ኹላችንም ሌቦች ተብለናል›› የሚል ቅሬታ ያቀረቡላቸው ወገኖች መኖራቸውን ያልሸሸጉት አቡነ ማትያስ፣ ‹‹የሚያመው ያመው ይኾናል፤ ኹላችኁም አማሳኞች ናችኹ የሚል አልወጣኝም፤ የሚያማስኑ እንዳሉ ግን ሐቅ ነው፤›› ሲሉ የችግሩ አስከፊነት ሊካድ እንደማይገባው አረጋግጠዋል፡፡

ሙስና ማለት ጥፋት ነው ሲሉ የቃሉን ትክክለኛ ንባብና ገላጭነት ያብራሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹በቤተ ክርስቲያን ያለው የሙስና ሙስና›› መኾኑን በመግለጽ በፀረ ሙስና ቅስቀሳው የሰንበት ት/ቤት ወጣቶቹ በይበልጥ እንዲዘምቱበት አሳስበዋቸዋል፡- ‹‹ተይዞ ባለው የፀረ ሙስና ቅስቀሳ እናንት የሰንበት ት/ቤት አባላት በይበልጥ ብትዘምቱበት፤ በተጠናከረ ኃይል ይህን ብትረዱኝና ከዳር ብናደርሰው አመሰግናችኋለኹ፡፡››

በተያያዘ ዜና÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ እንቅስቃሴ የሚበዙት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የጽ/ቤት ሠራተኞች፣ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንደሚደግፉት እየተገለጸ ቢሰነብትም ‹‹ምእመናን በእኛ ሕግ ምን ያገባቸዋል፤›› የሚሉ አንዳንድ አስተዳዳሪዎች ቅሬታቸውን ለፓትርያርኩ ማቅረባቸውን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡

እንደምንጮቹ መረጃ፣ ቅሬታ አቅራቢ አስተዳዳሪዎቹ የመዋቅር ለውጡን የሚቃወሙ ሲኾኑ ከእነርሱም መካከል ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጡ በተከታታይ የተካሔዱት የድጋፍ መግለጫ ስብሰባዎች ምእመናኑን በእነርሱ ላይ ኾነ ተብሎ ለማነሣሣት የታለሙ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ሰንበት ት/ቤቶቹ ከፓትርያርኩ ጋራ ባካሔዱት ውይይት ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን በግልጽ በመቃወማቸውና በማጋለጣቸው ያሳሰሯቸውና ያስደበደቧቸው አስተዳዳሪዎች እንዳሉ ተገልጧል፡፡

የሰንበት ት/ቤት ወጣቶቹ የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት ለግል ጥቅም በማዋልና ለባዕድ አሳልፎ በመስጠት አላግባብ በልጽገዋል የሚሏቸውን አማሳኝ አስተዳዳሪዎች ዶሴ ለፓትርያርኩ ለማቅረብ፣ እንደ ሕጉ አግባብም ለፀረ ሙስና ኮሚሽን ለማመልከትም ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ከአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራር አባላት ተጠቁሟል፡፡

YeTimket Lijoch

ዉሉደ ጥምቀት

የቤተ ክርስቲያኒቱ የጥቅምት ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ÷ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት ዕንከን ሳይኖርባት፣ ሞያ ሳያንሳትና ተቆርቋሪ ምእመናን እያሏት በመልካም አስተዳደርና በፋይናንስ አያያዝ ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ መገታት እንዳለበት የገለጸ ሲኾን የቤተ ክርስቲያኒቱን የአገልግሎት አፈጻጸም እሴቶችና መርሖዎች የሚገልጸው መሪ ዕቅድ ከገመገመ በኋላ ሙስናና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ በሚያስችል አኳኋን ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት መመሪያ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

7 thoughts on “ፓትርያርኩ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በሙስና ላይ እንዲዘምቱ አዘዙ

  1. Anonymous January 18, 2014 at 1:09 pm Reply

    Musena ena bileshu aserar ba betekristiyan yejemerewu amlakachen eyesus kiristos sisekel naw. yihenenem yejemerut Tsehaft ferisawuyan ena Yihuda nachewu. silezih ahunem musena ena bilishu aserar ka betekristiyan yamitefawu wereket lay bamiweta mameriya sayhon majameriya ba agelgayu lib wuset yekristos fiker yigeba. kaziya bahuala 1500 gatse mameriya sayhon 1 mesmer tsihuf baki nawu. amlak betekristiyaninen(AMANYUN) YITEBK.

    • Annonyname January 20, 2014 at 6:44 am Reply

      መመሪያ አጥር ነው፡፡ ሌባ እንደፈለገው ሊገባበት አይችልም፡፡ በብርሃን የተመላ መንገድም ነው፤ጥሩ አገልጋዮች ይጓዙበታል፤ይመሩበታል፤ያዩበታል፤ ሰው ደግሞ ሕግን ሲጠብቅ ራሱ ሕጉ እርሱን ይተብቀዋል፡፡ ሰው ሕግን ከጠበቀ ከእግዚብሔር ጋር ይኖራል፡፡ የእግዚበሔር ቤተ መቅደስነቱ ይፀናል፡፡ እየተሰራ ያለው ሥራ መልካም ጅምር ነው፡፡ ፍፃሜውን ያሳምርልን፡፡የእግዚአብሄር ልጆች በርቱ፣ እንበርታ፤ለአባቶቻችን ዕድሜና ፀጋውን ጥበቡን ይስጥልን፡፡

  2. Anonymous January 18, 2014 at 5:11 pm Reply

    keminutu serra bteguadagn mussena yemikelakel denbna yetsda hayle yasfelegal.Yetebalew yewnet kehone yemoker.

  3. Anonymous January 21, 2014 at 7:54 am Reply

    denb yasfelgal.geta hign yesera hulu hizb yesu fikir slelew aydelem.metazebia endihon new.silezih ahunm tolo bilo yitsdek.
    zelealem

  4. Anonymous January 22, 2014 at 7:16 am Reply

    ሙስናን በአንዴ ማጥፋት አይቻልም መቀነስ እንጂ በሂደት ይጠፋል በርቱ

  5. Anonymous January 23, 2014 at 7:03 am Reply

    seber zena aba haile abriha ye giorgis bet kirisitiyan astedadari sport bemiserabet jim bet ke andua ye ayin fikir yizotal bezihim mikiniyat sport bemiserut ayine yemil sim wetoletal.wedefit yemifeterewin eyetektatelin bemereja asidegifen lemakireb emokiralehu

  6. Anonymous January 23, 2014 at 8:59 am Reply

    ከጂም ከወጡ በሁዋላስ…..
    ሰው የሚጻፈውን ከማይጻፈው መለየት ተሳነው!!
    እረ ሀራ ሼም ነው!!ዲያሪ(የእለት ውሎ ማስታወሻ)ሳይቀር በአስተያየት ስም ታወጣላችሁ እንዴ!!ይደብራል!!አሁንስ መዝቀጥ ጀመራችሁ!!
    በሞቴ የዐይን ፍቅርን በብሎግ ላይ ማስረዳት የሚቻለው እንዴት ነው??
    ኤጭ!!!አሁንስ መንደሬነት በዛ!!ከካራን ውጡ!!!privacy ምናምን የሚባሉ መብቶች በአስተያየት ስም ሲጣሱ እያዩ ለሃይማኖታችን በአርበኝነት ስለቆምን ነው ማለት ያስተዛዝባል!!ከሃይማኖተኛነታችን በፊት ሰው እንሁን!!!የኛውን ሰው ቀርቶ የሌላ ሃይማኖት ተከታይም ቢሆን እንዲህ ዝምብሎ በሜዳ መዘርጠጥ ነውር ነው!!!

Leave a reply to Anonymous Cancel reply