ፓትርያርኩ÷ ሰንበት ት/ቤቶች በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀላቸው የውስጥ መመሪያ ደንብ መሠረት እያገለገሉ አማሳኞችን እንዲያጋልጡና ሙስናን በተጠናከረ ኃይል እንዲዘምቱበት አሳሰቡ

Sunday School student applausing his holiness anti-corruption effort

 • በሰንበት ት/ቤቶቹ የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ÷ የፓትርያርኩ ፀረ ሙስና መግለጫዎች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናት ተግባራዊነትና የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ የሚያሻው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

*           *          *

 • የድጋፍ መግለጫ ስብሰባውን ለማሰናከል የሞከሩት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ፣ ሰንበት ት/ቤቶቹ ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጡ ድጋፋቸውን ለመግለጽና ስለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ በቅድሚያ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን ማማከር እንደሚገባቸው በመጥቀስ ከአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራሮች ጋራ ተሟግተዋል፡፡
 • ዋና ሓላፊው፣ የአንድነት አመራሮቹን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የሚከፍላችኹ የማኅበረ ቅዱሳን ቅጥረኞች›› በሚል እየዘለፉ በመሟገታቸው የገሠጿቸው የመምሪያው ምክትል ሓላፊና የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ÷ ሰንበት ት/ቤቶቹ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን የተወያዩበት እስከኾነ ድረስ በመረጃና ዕውቀት ላይ ተመሥርተው መደገፍ ይኹን መቃወም መብታቸው መኾኑን ገልጸዋል፤ ስብሰባው በተፈላጊ አጀንዳዎች ላይ እንዳያተኩር ዋና ሓላፊው በግራ አጋቢ ንግግሮች ያደረጉት የመርሐ ግብር ማጣበብ ሙከራም ሳይሳካላቸው ብርቱ ትችት አትርፈው ወጥተዋል፡፡

*           *          *

 • በተሰጥኦዋቸው፣ በሞያቸውና በጉልበታቸው በሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከምንም ዐይነት ተጽዕኖ ነጻ ኾነው የተሳሳተውን ነገር በማጋለጣቸው አንዳንድ አለቆችና ጸሐፊዎች ለፖሊስ በሚጽፉት ደብዳቤ ብቻ ጉዳዩ ሳይጣራ ድብደባና እስር የተፈጸመባቸው የሰንበት ት/ቤት አባላት እንዳሉ ተገልጧል፡፡ በጽ/ቤት ደብዳቤ ብቻ ብልሹ አሠራርን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ የሰንበት ት/ቤት አባላትን ማሳሰርና ማስደብደብ እንደ እንጀራ ልጅ መመልከትና ፍትሐዊ ባለመኾኑ እንዲቆም ቅዱስነታቸው መመሪያ እንዲሰጡበት ተጠይቋል፡፡
 • የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ በአማሳኝ አስተዳዳሪዎች ላይ ማስረጃ ያጠናቀረበትን ሰነድ ለፓትርያርኩና ለፀረ ሙስና ኮሚሽን እንደሚያቀርብ ተሰምቷል፡፡
 • ሰንበት ት/ቤቶች በአዲስ አበባ በዓለ ጥምቀት በሚከበርባቸው 46 የባሕረ ጥምቀት ሥፍራዎችና የታቦት ማደርያዎች የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ‹ተቃዋሚዎች› እንደሚያሰራጩ ያስወሯቸውን ኅትመቶች በመቆጣጠር በዓሉን በተለመደው ድምቀትና ሰላማዊነት እንደሚያከብሩ ገልጸዋል፡፡

*           *          *

 • እስከ ኻያ ሚልዮን የሚደርሰው ኦርቶዶክሳዊ የሰንበት /ቤት ወጣት ወጥ የኾነ ራእይና ተልእኮ እንዲኖረው በተዘጋጀው የውስጠ ደንብ መመሪያ መሠረት ሰንበት /ቤቶች÷ ወጣቶችን ከቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ሥርዐትና የክርስቲያናዊ ማንነት መገለጫ ከኾኑት ማኅበራዊ ግንኙነትና አኗኗር፣ ጠባይና ሥነ ምግባር የሚያስወጡ የየዘመናቱን ክርስቲያናዊ ለውጦች በመከታተል በክርስቲያናዊ ትምህርት መታገልና ወጣቶችን ከመነጠቅ የመጠበቅ፣ እንዲሁም ይህን ተጋድሎ ማስጠበቅ የሚችልና ለመጭው ትውልድ ጽኑ የኾነ ተቋማዊ መሠረት መጣሉን የማረጋገጥ ተልእኮ ይኖራቸዋል፡፡
 • ቤተ ክርስቲያን በአጥቢያም ኾነ ከዚያ ከፍ ባለ የአስተዳደር መዋቅር በምታከናውናቸው ሐዋርያ አገልግሎቶች ተሳታፊ እንዲኾኑ የማስቻል መርሕ አላቸው፡፡ ቃለ ዐዋዲውን መሠረት አድርጎ በተዘጋጀውና በቅ/ሲኖዶሱ በጸደቀው በዚኹ የሰንበት /ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤያት የውስጥ ደንብ መመሪያ በሚሰጣቸው መብት፣ የሰንበት /ቤት ወጣቶቹ ቤተ ክርስቲያኒቷ የምትፈልገውን እንዲያሟሉበት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አሳስበዋል፡፡

*           *          *

 His Holiness Abune Mathias and His Grace Abune Markos

 • ‹‹በየደጁ ሙስናን ተዋጉ! ዲያቆንም ቄስም መነኩሴም ይኹን ሌባ ሰው ሲገኝ ማጋለጥ ነው! ይኼ ፕሮቶኮል የለውም፡፡ ቢቻል እጅ ከፍንጅ ይዞ ድረሱልኝ ማለት ነው፡፡ በከተማው ያለው ሌባ ያው እዚኹ ያለው የእምነቱ ተከታይ ነው፡፡ ከሌላ የመጣ የለም፡፡ እምነቱን ሳያውቀው ያመነ ነው፡፡ ሰው ካመነ በኋላ ይሰርቃል እንዴ!›› /ብፁዕ አቡነ ማርቆስ/
 • ‹‹የታሰሩት፣ የተደበደቡት የሰንበት ት/ቤት አባላት ምንድን ነው ያደረጉት? የት ነው የታሰሩት? ማነው የሚያሳስራችሁ? ለምንስ ተጽዕኖ ይደርስባችኋል? ምክንያቱ መጠናት አለበት፤ ምክንያቱ ተጠንቶ ከነማስረጃው ቢቀርብልን ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድ ውሳኔ ትሰጣለችኮ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆቿን ዝም ብላ አሳልፋ አትሰጥም፡፡ በጥናት ቢቀርብልን የበጀ ይኾናል፡፡››
 • ‹‹የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታምንባችኹ የቤተ ክርስቲያኒቱ ታማኞች መኾናችኁን ያረጋገጣችኹ ልጆቻችን ናችኹ፡፡ እናንተ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አለኝታዎች ናችኹ፡፡ ዘመኑ የእምነት ጉድለትና የኑፋቄ ነው፡፡ ምሳሌው ጥሩ ባይኾንም እሾኽን በእሾኽ እንደሚባለው አሉ ለምትሏቸው መናፍቃን መልስ የምትሰጡ እናንተ ናችኹ፡፡ እምነት የሚያቃውስ፣ ሥርዐትና ትውፊት የሚያፋልስ ካለ በማስረጃ ተረጋግጦ ሲቀርብ ቤተ ክርስቲያኒቱ መልስ መስጠት አለባት፡፡ ፀረ ሙስናውን እንደግፋለን ብላችኁኛል፤ እኔም እንደምትደግፉኝ አምናለኹ፡፡ ሐቅ፣ መልካም አስተዳደር፣ እውነተኝነትና ሓላፊነት ጠፍቷል፤ የሚያሳዝን ኹኔታ ነው ያለው፡፡ ተይዞ ባለው የፀረ ሙስና ቅስቀሳ እናንት የሰንበት ት/ቤት አባላት በይበልጥ ብትዘምቱበት፤ በተጠናከረ ኃይል ይህን ብትረዱኝና ከዳር ብናደርሰው አመሰግናችኋለኹ፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
Advertisements

6 thoughts on “ፓትርያርኩ÷ ሰንበት ት/ቤቶች በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀላቸው የውስጥ መመሪያ ደንብ መሠረት እያገለገሉ አማሳኞችን እንዲያጋልጡና ሙስናን በተጠናከረ ኃይል እንዲዘምቱበት አሳሰቡ

 1. abebe January 18, 2014 at 12:58 am Reply

  egziabher yrdachhu qurt yebetekrstiyan ljoch.

 2. Getachew Abebe January 18, 2014 at 1:41 am Reply

  አባታችን እድሜ ይስጥልን። “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ…”

  • Fekadu January 18, 2014 at 1:58 am Reply

   Enegnih yelewutu amasagnoch (tekawamiwoch nen bayoch) beTimket be’al lay libetinut yasebutn yetifat tsihuf hulum krstian liketatelew ena likotaterew yigebal!

   • Fekadu January 20, 2014 at 11:59 pm

    Tikikl!

 3. maru January 18, 2014 at 1:46 am Reply

  Temesgen

 4. Anonymous February 25, 2015 at 4:20 pm Reply

  tiru new

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: