የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ያነጋግራሉ

Sunday school Mezemeran

 • የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ በቅ/ሲኖዶስ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲኾን የሚጠይቁት የሰንበት /ቤት ወጣቶች፣ ከአንድ ሚልዮን በላይ አጠቃላይ ብዛት ያላቸውን የሀ/ስብከቱን ወጣቶች የሚወሉና 160 ሰንበት /ቤቶች የተውጣጡ ናቸው፡፡
 • በሀ/ስብከቱ፣ በክፍላተ ከተሞች ቤተ ክህነት /ቤቶችና በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መዋቅርና አደረጃጀት ውስጥ ሰንበት /ቤቶችን በማደራጀትና በማጠናከር ተልእኳቸውን እንዲወጡ ማድረግ ከዋነኛ ዓላማዎችና ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡
 • የቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ የማፋጠን፣ የቤተክርስቲያንን ኦርቶዶክሳዊ ማንነትና አስተዳደራዊ አንድነት የመጠበቅ፣ አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን የመከላከልና ሞያዊ አስተዋፅኦን ለቤተ ክርስቲያን የማበርከት ድርሻ ያላቸውየአያሌ ተሰጥኦዎች ባለቤት የኾኑ ሰንበት /ቤት ወጣቶች በአባቶች እግር ላቸው የተተኪነት ሚና ተጨባጭና ቀጣይ እንዲኾን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናቱ ዋስትና ነው፡፡
 • የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነዱ በፋይናንስ ፖሊሲውና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ÷ የቤተ ክርስቲያናችን የገንዘብ አያያዝና አሠራር ግልጽነትና ተቀባይነት ያለው እንዲኾን ማድረጉ መሠረታዊ ተልእኮዋን ለማጠናከር ከሚኖረው አጠቃላይ ፋይዳ ባሻገር በዋና ዓላማና ተግባር ደረጃ ያስቀመጠው የሰንበት /ቤቶች አገልግሎት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሙዓለ ንዋይ ምደባ (budgeting/financial arrangements) በቂ የፋይናንስና በጀት ድልድል እንዲያገኝያስችላል፡፡
 • ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት /ቤቶች ሀገር አቀፍ አንድነት ምሥረታበ፳፻፬ ዓ.ም. የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚጠቁመው 65 ዓመታትን ባስቆጠረው የዘመኑ የሰንበት /ቤቶች አሠራር የታቀፈውና ከ15 – 30 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኘው በብዙ ሚልዮን የሚገመት ወጣት 70% የምእመኑን አጠቃላይ ድምፅ ይወክላል፡፡

YeTimket Lijoch BeSera Lay 

 • የዛሬው ውይይት፣ ይኸው ወጣት የበጎ ፈቃድ አገልጋይ በብቁ አመራር እየታገዘ ዐውቆትና ተገንዝቦት በቅድመ ግንባር የሚያስፈጽመውና በደጀንነት የሚደግፈው የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ኃያልነቱን የሚያረጋግጥበት ነው የሚኾነው፡፡ የተቋማዊ ለውጥ ንቅናቄው የሰላ  እና የነቃ ጫፍ ነውና የማይሻገረውና የማይጠራርገው ዕንቅፋት አይኖርም!!
Advertisements

8 thoughts on “የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች የአደረጃጀትና አሠራር ለውጡን በመደገፍ ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ያነጋግራሉ

 1. በአማን ነጸረ January 16, 2014 at 3:09 pm Reply

  በአሁን ዘመን ከምን ጊዜውም በላይ ኦርቶዶክሳዊ መንፈስ የተላበሱ የፌስቡክ መልእክቶችንና የፕሮፋይል ምስሎችን ያየ ሰው ሁሉም ጠቅሎ ሃይማኖተኛ ሆነ እንዴ ማለቱ አይቀርም፡፡እንኮራለን!! ይህ እንግዲህ በግለሰብ ደረጃ ነው፡፡በብሎግ እና በዌብሳይት ደረጃስ ለዚህ ቴክኖሎጅ መራሽ ትውልድ የሚመጥን በቂ፣ሀቀኛ እና ከኢኦተቤክ አስተምህሮዎች ጋር የሚራመድ የመረጃ ግብአት እየቀረበለት ነው??? አይመስለኝም!!መጀመሪያ ያሉት ኦርቶዶክሳዊ ጦማሮችና ድረ-ገጾች ውስን ከመሆናቸውም በላይ እነሱም ቢሆኑ ግብታዊነት ከተጫነው ቀናኢነት ባለፈ በቂ የመንፈሳዊ ት/ት ዝግጅት ባላቸው እና ግብረ-ገብነት በተላበሱ ግለሰቦች የሚመሩ አይመስሉም፡፡ይህ ጉድለት ያመጣው ጣጣ ብዙ ነው፡፡ልዘርዝረው፡
  1. ወንጀልን እንደ ወንጌል መስበክ፡
  ሀ. ለኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት ክብርና ህላዌ እዋጋለሁ ለሚል መንፈሳዊ ወታደር፣ለአንድነቱዋ እቆማለሁ ለሚል ቀናኢ አማኝ የጦር ሜዳ ውሎ ስንቁና ትጥቁ ሊሆን የሚገባው ቃለ እግዚአብሄር ነው፡፡ወንጌል እና የኢኦተቤክ የምትቀበላቸው ቅዱሳት መጻህፍት ናቸው፡፡እየሆነ ያለው ግን የካህናትን፣የጳጳሳትን፣የሰባክያንና የልዩ ልዩ አገልጋዮችን ወንጀል ኮምፒዩተር ስር ተደቅኖ በስማ በለው መዘርዘር ነው፡፡ይህን አይነት ስራ ቅዱስ ዳዊት በመዝ 49 ቁ 20 “ትነብር ወተሀምዮ ለእሁከ ወአንበርከ እቅፍተ ለወልደ እምከ-ተቀምጠህ ወንድምህነ አማኸው ለእናትህም ልጅ እንቅፋት አኖርህ” ሲል ይኮንነዋል፡፡ ድርጊቱ የጠላትን ወታደር ሊማርክ ቀርቶ ያለውን ኦርቶዶክሳዊ ሰራዊትም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው፡፡
  ለ. አስቡት እስኪ!!አሁን በሀራ እና በአንድ አድርገን ብሎጎች የሚወጡ ዘገባዎችን ያነበበ መናፍቅ ‘ምነው ከቀደመው ሃይማኖቴ ባልወጣሁ’ ብሎ ልቡ ይጸጸታል፡፡እውን ዘገባዎቻችን ያለነውን የሚያጽናኑ የራቁትን የሚያቀርቡ ናቸው፡፡አይመስለኝም!!!ክርስትና በይቅር ባይነት፣በማስተማር፣በማጽናናት እንጅ ጠርገን እናስወጣለን፣ድራሻቸውን እናጠፋለን እየተባለ ሀጢአትንና ሀጢአተኛውን አንድ ላይ እየጨፈለቁ ምርኮ የሚገኝባት እምነት አይደለችም፡፡አባቶቻችንም እንዲህ አይነት በየአደባባዩ በኢአማንያን ፊት ገመና በማስጣት የአማኞችን ቁጥር ማብዛት የሚቻልበት አብነት አላኖሩልንም፡፡መጽሀፉም ይናገራል…………… “ሀሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ እንደተወለዱ ህጻናት ተንኮል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ”(2ኛ ፔጥ 2ቁ1)
  ሐ. ብሎጎቻችን ምን ያህል ፀጋ እግዚአብሄር እንደራቃቸው ለማወቅ ከዚህ ንባብ በሁዋላ ዝምብላችሁ ሁለት ሶስት ዘገባዎቻቸውን እዩ፡፡ተጀምሮ እስኪጨረስ እንደ አለማዊ ጋዜጣ ስመ እ/ሄር ለመሀላ አይጠራባቸውም፡፡ይሄ ደግሞ አንዳንድ ፖለቲከኞች እንኩዋ በንግግራቸው መደምደሚያ “እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ” ሲሉ ከሚያቀርቡት መጣጥፍ በታችም ብሎጎቻችን ከመንፈሳዊነት እንደወረዱ የሚያመላክት ነው፡፡ወንጀል መስበክ ወንጌል ቢሆን ኖሮ ንፍሱዋን ይማረውና ከዚህ ዓለም የተለየችው ደጀሰላም የዘረዘረቻቸውና ከኢንተርኔትም አልፈው በህትመትና በኤሌክትሮኒክስ ዐለማዊ ሚዲያዎች ሳይቀር የተስተጋቡት ወንጀሎችና ወንጀለኞች በሺህ ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጠፉ በጎቻችንን ይመልሱልን ነበር!!ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም፡፡በሀሜትና በሹክሹክታ የሚጠበቅ ሃይማኖት የለም!!!!አዎ የለም!!!
  መ. የተሀድሶውን ጎራ በዚህ መልኩ እሾህን በእሾህ በሆነ አካሄድ ካልሆነ በቀር መመከት አይቻልም ካላችሁም ተሳስታችሁዋል፡፡እነሱ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ለመምታት ነው የሚሞክሩት፡፡ወዲህ የአባቶችን ገመና ያሰጣሉ ያክሉና የእነሱ የአንድ ፓስተር ተብየ ኢንተርፕርነር ንብረት የሆነ ቸርች የአስተዳደር እጅና እግር ሳይኖረው ለኛ አዛኝ መስለው ይህ ሁሉ የሆነው ቤ/ክ ስላልታደሰች ነው ሲሉ በቁስሉ ላይ እንጨት ይሰዳሉ፡፡ግባቸውም አንድ ነው፡፡መንጋውን ከእረኛው መለየት፡፡ታዲያ ለዚህ ስልታቸው የመልስ ምት ሊሆን የሚገባው (1)በመ/ቅዱስ እውቀት ታንጸን መገኘት,(2)እነሱ ያሞገሱትን እየሰደብን ‘ውሻ ነከሰኝ ብሎ እንደመንከስ’ አይነት አካሄድ መከተል ሳይሆን በማስረጃና በምክንያት የተደገፈ መልስ ማስቀመጥ፡፡ከዛ ውጭ እነሱ ያጥላሉትን ማቀፍ ያሞገሱትን ማጥላላት የሀቁን ሚዛን ወደ ቡድናዊነት ስለሚያወርደው እውነት ከቲፎዞነት ትምታታብናለች፡፡
  ሠ. በነገራችን ላይ በየተሀድሶ ብሎጉ የሚወጡት ሀተታዎችም ቢሆኑ ኦርቶዶክሳውያንን ለማናደድ እንጅ ለመማረክ የሚጻፉ አይመስሉም፡፡በጥላቻ መንፈስ ነው የሚጻፉት፡፡እልሀቸውን በቁንጽል የግእዝ ጥቅሶች ሊወጡ ነው የሚሞክሩት፡፡ጥሩ ነው!!!በየሰፈራችን እየተቅለሰለሱ ጌታን እናስተዋውቃችሁ የሚሉን አፈ-ቅቤዎች ሶፍትዌራቸው ምን እንደሚመስል እያየንባቸው ነው!!!አፋቸውና ልባቸው ምን ያህል እንደሚራራቅ በሚደረድሩዋቸው የስድብ አይነቶች እያየን ነው!!!
  ረ. ወደ ርእሴ ስመለስ፡በየኢንተርኔቱ በአባቶችና በአገልጋዮች ላይ የሚለጠፉት ክሶች ቢያንስ ለሚመለከተው አካል ከመቅረባቸው በፊት ይፋ ባይደረጉ፣ተከሳሾቹ የማስተባበል እድል ስለሌላቸውና አንባቢውም ይህን ያልተስተባበለ ክስ እንደወረደ ተቀብሎ ግለሰቦችን ወደመፈረጅ ስለሚገባ ማስረጃዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ቢደረግ፣ መጽሀፉም በ1ኛጢሞ5-19 “ሁለት ወይም ከሶስት ምስክር በቀር በሽማግሌ(ካህን)ላይ ክስ አትቀበል” እንደሚል ብናስተውል፣አንባብያንም ለሚቀርቡ ክሶች በቂ ማጣራት ሳናደርግ ‘ወይኔ ቤ/ክ’ እያልን በችኮላ ለስም ማጥፋቱ ተባባሪ ለመሆን ባንፋጠን፣ትችቶች ሁሉ ለመጥረግና ለማሳደድ ሳይሆን ለመመለስና ለማነጽ ቢሆኑ፣ከቡድናዊ አጀንዳ(motive)ሳይሆን ከቤ/ክ ጥቅም ብቻ ተነስተን ብንጽፍ፣ በተለይ በተለይ ባለቤቶቻቸው በማይታወቁ ብሎጎች የሚወጡ የውንጀላ ዘገባዎች ብሎገሩን እንደ ይፋዊ ሚዲያ ማስተባበያ እንዲያወጣ በህግ ለማስገደድ የሚቻልበት መንገድ ስለሌለና ክሱ የቀረበበት በስተመጨረሻ ንጹህ ሆኖ ቢገኝ እንኩዋ ስሙን መመለስ ስለማይችል የሚደርስበት የመንፈስ ስብራት በምንም መልኩ ሊካስ አይችልም፡፡ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊ ብሎገሮች እናስተውል!!!በእናንተ ሊደርስ የማትፈልጉትን የስም ማጥፋት ወንጀል እንደ ወንጌል አትስበኩት፡፡
  2. ወደላይ ማዳጥ
  ሀ. ይህን ርእስ ከአቡነ ቴዎፍሎስ ንግግር ነው የተዋስኩት፡፡አቡነ ቴዎፍሎስ የመጀመሪያው ኢ/ዊ ፓትርያርክ የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ እንደራሴ በነበሩበት ወቅት አንድ ሰው ይመጣና ሀይለ-ቃል እየተጠቀመ አቡነ ባስልዮስን ማጥላላት ማናናቅ ማማረር ይጀምራል፡፡በዚህ ጊዜ አቡነ ቴዎፍሎስ ‘እንዴት አባታችንን እንዲህ ትናገራለህ’ ብለው ሲገስጹት ‘አባታችን ይቅርታ አድርጉልኝ የማይባለውን ያልኩት አድጦኝ ነው’ ይላል፡፡እሳቸውም መልሰው “ታዲያ ሰው ወደታች እንጅ ወደላይ ያድጠዋል” በማለት አባቶችን አንጋጦ መዝለፍ እንደማይገባ ገስጸው ሸኙት ይባላል፡፡አባቶቻችን እንዲህ ነበሩ፡፡እኛስ???
  ለ. እኛማ፡በየዋህነት ልቡን ሰብሮ፣በጋቢው ስር መባውን ይዞ የሚመጣውን ቅን ምዕመን መሪዎችህ እንዲህ ናቸው……አልተማሩም፣ተሀድሶ ናቸው፣ሙሰኞች፣ጥቅመኞች፣አያት እንጅ አባትስ የለህም፣መባህ መና ቀረ እያልን ተስፋ እናስቆርጣለን፡፡እረኛውን ከመንጋው እንለያለን፡፡በመቶ እንኩዋ ሊቆጠሩ የማይችሉ የጥቂት የከተማ ካህናትን ያልተገባ ምግባር እያጋነን በማውራት ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ ለዕለት ኑሮዋቸው እያረሱ በትሩፋት የሚያገለግሉ ካህናትን በስመካህን አብረን እንወቅጣለን፡፡ያድጠናል!! የህዝቡን ጆሮ ተስፋ በሚሰጡ ሳይሆን በሚያስቆርጡ የወሬ ቅኝቶች እንቃኛለን፡፡ተሳክቶልናል!!!ያለምንም ማስረጃ የቀረበን አባቶቹን የሚነቅፍና የሚያጥላላ ዘገባ ያለማወላወል እንደ ት/ሃይማኖት ተቀብሎ የሚያሳድድና በጭፍን ዘመቻ የሚከፍት ኤቢሲዲ የቆጠረ አማኝ እየፈጠርን ነው-በተሰራለት ድጥ ሽቅብ የሚንሸራተት!!
  ሐ. እናስተውል!!!ጠንካራ የሃይማኖት ተቁዋም የሚኖረን ቅን መሪዎች ሲኖሩን ነው፡፡ቅን መሪ የሚፈጠረው ደግሞ ከየቅዱሳን አበው ገድል እንደምናነበው ከቅን ምዕመን ነው፡፡ቅን ምዕመን የሚፈጠረውም ስለበላይ አመራር ያልተገቡ ተግባራት እየለፈፉ ስለ ምዕመኑ መብት በማውራት ብቻ ሳይሆን ምዕመኑ በአንጻረ ቤተክርስቲያን ያለበትንም ግዴታ እየተወጣ አባቶቹ በምግባርና በሃይማኖት እንዲበረቱ በማገዝ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር በማስተማር ነው፡፡
  መ. ግዴላችሁም!!አባቶቻችን ቢስቱ እንኩዋ ሀጢአታቸውን በማስተጋባት ሳይሆን በቅንነት ቀርቦ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዲታረሙ የተቻለንን ያህል ከመሞከራችን በፊት አሳልፈን አንስጣቸው፡፡ይህን ርእስ በአንድ እውነተኛ ገጠመኝ ልዝጋው፡፡አንድ እብሮ አደጌ መነኩሴ የነገሩኝ ነው፡፡እኚህ መነኩሴ ስጋዊ ፍላጎታቸው በጣም በርትቶ ይፈታተናቸውና ሰባተኛ መርካቶ ወደሚገኝ ሴተኛ አዳሪ ሰፈር ጨለማውን ተገን አድርገው ይገባሉ፡፡የዝሙት ስራ የምትሰራው እህት ለመሳለም ስትቀርብ ለፈቃደ-ስጋ ጠየቁዋት፡፡እሱዋም፡ ‘አባ እኔ የክርስቲያን ልጅ ነኝ ያውም የቄስና የመነኩሴ ዘር፣ዛሬ ኑሮ አስገድዶኝ እዚህ የሀጢአት ስራ ውስጥ ብገባም እስዎን አሰናክየ ሁለት ጊዜ ፈጣሪየን አልበድለውም’ ፡፡አባ መልሰው ‘ያልሽውን ልክፈል’ ቢሉም የዘማዊቱዋ ሴት መልስ ‘ለምን ሚሊዮን አይከፍሉኝም አላደርገውም’ የሚል ነበር፡፡መነኩሴው ይሄን የነገሩኝ በጸጸት ውስጥ ሆነው ነው፡፡ዘማዊ ከተባለችው አለማዊ ሴት ማነሳቸው ምን ያህል ስሜታቸውን እንደጎዳው ከፊታቸው አንብቤያለሁ፡፡አዎ ይቺ ሴት አባን ለማስተማር አንጉዋጦ መሳደብ አላስፈለጋትም፣ኢንተርኔት ላይ ታሪካቸውን አላስለጠፈችውም፣ሙከራቸውን ጽፋ ሙዳየ-ምጽዋት ውስጥ አልከተተችም፣እስዎ የሃይማኖት አባት አይደሉም እንዴ ብላም አፉዋን አድጦት የጽርፈት ቃል አልተናገረችም፡፡ቃሉዋ አጭር ነው!!!አላሰናክልዎትም!!!!
  ለአባቶቻችን መሰናክል ከመሆን እና አንጋጦ ታላላቆችን ከማቃለል ይሰውረን!!!ይቆየን!!!

  • tesfahun January 17, 2014 at 2:35 am Reply

   Aemre Ashebir atsheber ayzoh zemenu alkobihal

  • Annonyname January 17, 2014 at 7:00 am Reply

   አቡነ ባስልዮስና እነዚህ ሰዎች በጣም ይለያያሉ፤ አባታችንንም እነርሱንም በስራቸው ለይተን እናውቃቸዋልን፡፡ አርዮስም ሊቅ ነበር እኮ ወዳጄ!! እርሱን ያወገዙና ክፉ ስራውን ያጋለጡ አባቶችንም ሽቅብ አዳጣቸው ይሉኝ ይሆን?እራሱን የብርሃን መልአክ አስመስሎ አከአንድ ቅዱስ አባት ጋር ወዳጅነት የመሰረተ ሰይጣን ከቅዱሱ አባት ጋር ፀሎት ሲሳተፍ ሁል ጊዜ የፀሎቱ ኃይል ያቃጥለው ስለነበር አንድ ወቅት ‹‹ አረ በፍቅር በስመ አብ ይቅር አለ ይባላል፡፡›› እርሶንም በዚህ አይን አይቼዎታለሁ፡፡ አሁን እያጠፉና ስርዓተ ቤተክርስቲያንን ዶግማንና ቀኖናዋን እየጣሱ ያሉ ግለሰቦች የአባትነት ክብርም ደረጃንም የሚያሟሉ አይደሉም፡፡ምንአልባት አባት ያሰኛቸው ለምዳቸው ካልሆነ በስተቀር፡፡አርዮሳውያን ናቸው፡፡ ለሆዳቸው ያደሩ ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ናቸው፡፡ ይህንንም የገዛ ግብራቸው ገልጦባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እውነትን እያወቁ የሚያጠፉ፣አላመ ይዘው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የገቡ ናቸውና እኔ እርሶ ባዩበት አይን አላያቸውም፡፡ ብሎጎችም ትክክል ናቸው ብዬ አምናለሁ፡፡ያለስርዓት የሚጓዙትንም መገሰፅ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ በጭፍን አልተፈረጁም፣መረጃዎች በበቂ ማስረጃዎች ተደግፈው ቀርበዋል፡፡ ይህንን ሀሳብም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጤናማ አእምሮ ያለው ሁሉ ይደግፈዋል፡፡ ኃበነ እግዚኦ አእይንተ አእምሮ፡፡

  • Anonymous January 18, 2015 at 5:26 pm Reply

   amen

 2. Anonymous January 16, 2014 at 8:17 pm Reply

  Dear brothers and sisters in Christ,,

  If you know, could you please tell me where the truth is ? and who is the one who stands with it? the groub with his grace Abba Estifanos or the other groub who are stand againest to Mk.and Abune Estifanos? Are you going with the truth ?or going againest it?
  dear my brothers and sisters who follow the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church,
  we have to stop accusing each other and if we have any different , we to discuss on our difference by closing our door ,otherwise, our mother church will be distroyed because of us.
  ask yourself, saying that, Am I really the follower of the mother church? and am i the honenst?
  please understand this, the enemy the church is working hard day and night to distroy us.
  let retern to the Lord of lords and KIng of kimgs Jesus Christ, and we have to repent from
  our sin
  may the Almighty God opens our internal ear to hear His divine word.
  faithfully,
  M.R. Demoz Tasew.

  • tesfahun January 17, 2014 at 2:36 am Reply

   kelay new tiezazu silezih temelesu nisiha gibu

 3. Fekadu Gashaw January 17, 2014 at 1:15 am Reply

  “BeAman Netsere” yetebalew asteyayet sechi – 1. mussegnoch saygaletu
  betekrstianachinin sigtu endinoru yemisha wana yemussegnoch tebeqa
  yimeslal. Be ‘Wongel yisebk’ shifan enesu endayinekubetna endaygaletu
  yemisha dibk teleko yalew sew yimesilal.
  2. Betekrstianachinin eyetefetatenat yalew ye tehadiso-menafikan seram
  endaygalet yemisha yetehadisoawuyan swur tebeqa yimeslal. Ebakh wendme
  ‘fikir,kibir,wengel mesbek…’ yemilutn yetekedesu kalat
  lewonjelegnoch gashanet atitekemibachew? B/krstianin lemaferares
  yemiseru yetifat arbegnoch sirachewn magalet b/krstianin magelgel new.

 4. በአማን ነጸረ January 17, 2014 at 3:42 pm Reply

  እዝች ጋ እኔ ልግባ
  3. ስለግዝት ዘበከንቱ
  ሀ. “ግዝት ማለት አንድ ምዕመን ከሃይማኖት ወጥቶ ከበጎ ምግባር አድጦ ሲገኝ ከህዝበ-ክርስቲያን እንዲለይ በስልጣነ-ክህነት የሚፈጸም መንፈሳዊ ቅጣት ነው፡፡” ይላል በ1988ዓ.ም በትንሳኤ ዘጉባኤ የታተመ መርሀ-ጽድቅ ባህለ-ሃይማኖት የተሰኘ የቤተክርስቲያናችን መጽሀፍ በገጽ-157፡፡ይኸው መጽሀፍ “…ደርሶ ማውገዝና መገዘት ግን አይገባም፡፡ምክንያቱም ሰውን ከእግዚአብሄር አንድነት ለይቶ እስከ(ፍጻሜ)ለሌለው ዘመናት የሚያርቀው ስለሆነ ይላል፡፡” እንደዚህ መጽሀፍ ከግዝት በፊት፡
  (1)ምዕመኑ ከሃይማኖት መውጣቱ መረጋገጥ አለበት፣
  (2)ወደ ሃይማቱ ለመመለስ የተደረገ ተደጋጋሚ የግለሰብና የጉባኤ ጥረት አለመሳካቱ ይረጋገጣል፣
  (3)ካልተመለሰ ስልጣነ-ክህነት ባላቸው አባቶች(ቅ/ሲኖዶስ)ተወግዞ ከቤ/ክ ይለያል፡፡
  ከዚህ ቀን ጀምሮም መናፍቅ ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡ልክ የእኛ ሲኖዶስ ግንቦት15ቀን2004ዓ.ም እንዳደረገው ማለት ነው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ የሚደረግ ግዝት ካለ ግዝት ዘበከንቱ ሲባል ገዛቹም ወፈ-ገዝት ይባላል፡፡
  ለ. ስለሆነም ምዕመናን የእምነት ህጸጽ አለበት ስለምንለው ሰው ማስረጃ ካለን ማስረጃችንን ይዘን ወደ ቅ/ሲኖዶስ በመሄድ ተጠርጣሪው መናፍቅ ባይወገዝ እንኩዋ ምንፍቅናውን እንዳያስፋፋ ለጊዜው በአባቶች ተመርምሮ ለጉባኤ እስኪቀርብ ድረስ እንዲታገድ ማስደረግ እንጅ በየኢንተርኔቱ በመለጠፍ፣ዶክመንተሪ በመስራት፣እሱን መናፍቅ ያላለ ራሱ መናፍቅ ነው እያሉ ባልተሰጠ የክህነት ስልጣን በማውገዝ ሰዶ ማሳደድ የቤ/ክ ስርዓት አይደለም፡፡ እነ አርዮስ፣እነ መቅዶንዮስ፣እነ ንስጥሮስ እና የመሳሰሉ መናፍቃንም ተወግዘው የተለዩት በዚህ መልኩ እንጅ በህዝብ ድምጽ፣መናፍቅነታቸውን ህዝቡ ሁሉ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያውቀዋል እየተባለ አይደለም፡፡ይቺን ይቺን እዛው ለሪፈረንደም፣ለምርጫ እና ለመሳሰሉት አለማዊ ተግባራት እንጠቀማት!!!
  ሐ. የአሁን ዘመን ኢንተርኔት መራሽ ውግዘቶች በስልጣነ-ክህነት ሳይሆን በቡድናዊ አደረጃጀት የሚተላለፉ ከመሆናቸውም በላይ ተጠርጣሪ መናፍቁ ከሃይማኖቱ ስለመውጣቱ ለማረጋገጥ ለነ አርዮስ የተሰጠው እድል እንኩዋ አይሰጠውም፡፡ ከውግዘት አዝማቾቹ በኩል ራስ መክሮ ለመመለስ ይቅርና አባቶች መክረው፣ገስጸው የመለሱትን ለመቀበል እንኩዋ ያለው ዝግጁነት የሚያሳፍር ነው ፡፡ለእነሱ የጌታ 99ኙን በጎች ትቶ የጠፋውን ለመፈለግ ስለመሄዱ መስማት አሰልቺ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ ‘አንድ ሳር ቢመዘዝ ጎጆ ቤት አያፈስም’ በሚለው ተረት መደበቅ ይፈልጋሉ፡፡
  መ. ሁሉም ምእመን እየተነሳ የሚገዝትበት ህገወጥ ድርጊት በቤ/ክ ላይ የሚያመጣው መረን የመልቀቅ አካሄድ እስከየት እንደሆነም መገመት የቻሉ አልመሰለኝም፡፡ አውጋዦቹ ማእከላዊውን የቅ/ሶኖዶስ ውሳኔ ሳይጠብቁ በየግላቸው የሚያስተላልፉት ውግዘት በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝበት አካሄድ ባለመኖሩ በህዝቡ ውስጥ እየፈጠሩ ያሉትን ውዥንብር ለመረዳትም ገና ዐይነ-ልቦናቸው አልበራም፡፡ውግዘት ተቁዋማዊ እንጅ ግለሰባዊ አይደለም፡፡ስለሆነም ‘ያንተን አላውቅም ለእኔ ግን መናፍቅ ነው’ የሚለውን አጉል አባባል ለማስወገድ የቅ/ሲኖዶስ ማእከላዊ አሰራርን እንከተል፡፡ቤቱ የስርዐት ቤት ነው፡፡እንደነ እንትና ቸርች ማንም እየተነሳ የዐይኑ ቀለም ያላማረውን ሁሉ በየፊናው በመናፍቅነት የሚፈርጅበት አይደለም፡፡
  ለሁሉም ዐይነልቦናችንን ያብራልን!!!ይቆየን!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: