የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን ለማረም የፓትርያርኩን ትእዛዝ በተጠንቀቅ ቆመው በመጠባበቅ እንዳሉና በታዘዙበት መሥመር ለመሰለፍ ዝግጁ መኾናቸውን ገለጹ

 

Sunday school Timket Mezemeran

 • የቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ችግር ለማረም በሚደረገው ጥረት ኹሉ በግንባር ቀደምነት መሰለፍ የእኛም የወላጆቻችንም ጽኑ አቋም ነው፡፡
 • አያሌ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን እስከ መታሰር ደርሰው እየታገሉት ነው፡፡
 • ፓትርያርኩ ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን ለማረም የሚያደርጉት ጥረት ታሪክ የሚዘግበውና መዘገብም ያለበት እውነት ነው፡፡
 • ሰንበት ት/ቤቶች የጨቅላ አእምሮዎችና የሥራ ፈቶች መጠራቀሚያ ሳይኾን ካህናትና ዲያቆናት፣ የሥነ መለኰት ምሁራን፣ ኢንጅነሮች፣ ዶክተሮች፣ አካውንታንቶች፣ የሕግ ባለሞያዎችና የትምህርት ባለሞያዎች በአጠቃላይ እምነት የሚጣልባቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ያሉበት ኹለገብ ተቋም ነው፡፡

*                              *                            *

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም

ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

አዲስ አበባ 

የቅዱስነትዎ የአባትነት ቡራኬ ይድረሰን እያልን እኛ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት አመራሮችና አባላት ኹላችንም ከኹሉ አስቀድመን የልጅነት ፍቅራችንንና ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡ ፍቅራችንን የምንገልጽበትና ምስጋናችንን የምናቀርብበት ምክንያትም ቅዱስነትዎ ለዚኽ ታላቅ ተልእኮ ከተሾሙበት ማግሥት አንሥቶ፡-

 1. በርካታ የሰንበት ት/ቤት አባላት እስከ መታሰር ደርሰው ሲታገሉት የቆዩትንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከመንሰራፋቱ የተነሣ አይነኬ ኾኖ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን እያስተቻት ያለውን ሙስናና ብልሹ አስተዳደር በማውገዝዎና ለማስተካከልም አበክረው ሥራ በመጀመርዎ፤
 2. ሰንበት ት/ቤቶች ሲያበረክቱት የቆዩትን አገልግሎት በተጠናከረ መንገድ መቀጠል ይችሉ ዘንድ ያዘጋጁትን የአንድነት መዋቅር ዕውቅና እንዲያገኝና የሚተዳደርበት ሰነድ እንዲያገኝ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋራ በመኾን መፍቀድዎ፤
 3. በሢመተ ፕትርክናዎ የመጀመሪያ ዘመን በአጭር ጊዜ በየአህጉረ ስብከቱ በመዘዋወር አብያተ ክርስቲያን ያሉበትን ኹኔታ በአካል እየተገኙ በመመልከትዎና ተገቢውን ምክርና መመሪያ በመስጠትዎ ነው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ይህ ያቀረብነው ምስጋና ታሪክ የሚዘግበውንና መዘገብም ያለበትን እውነታ ለማስቀመጥ እንጂ ለከንቱ ውዳሴ ወይም ደግሞ ለሌላ የተለየ ዓላማ እንዳላቀረብነው እንደሚገነዘቡልን ርግጠኞች ነን፤ ምክንያቱም በከንቱ ውዳሴ የቀረበን ምስጋና ቅዱስነትዎ እንደማይቀበሉት እናውቃለን፤ እኛም እንዲኽ ዐይነት ምስጋና የማቅረብ ልማድ እንደሌለንና ወደፊትም እንደማይኖረን በቀላሉ የሚገመት ጉዳይ ነውና፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ቅዱስነትዎ በይፋ የገለጹትንና እንዲስተካከል አበክረው ማሳሰቢያ የሰጡበትን የቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ ችግር ለማረም በሚደረገው ጥረት ኹሉ በግንባር ቀደምነት መሰለፍ የእኛም የወላጆቻችንም ጽኑ አቋም እንደኾነና በታዘዝንበት መሥመር ኹሉ ለመሰለፍ ዝግጁዎች መኾናችንን ለቅዱስነትዎ በላቀ አክብሮትና ትሕትና ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ እኛ የሰንበት ት/ቤት አባላት ብዙዎች እንደሚገምቱን፣ ሕፃናትና ሥራ ፈቶች ሳንኾን ወይም ሰንበት ት/ቤቶች የጨቅላ አእምሮዎችና የሥራ ፈቶች መጠራቀሚያ ሳይኾን ካህናትና ዲያቆናት፣ የሥነ መለኰት ምሁራን፣ ኢንጅነሮች፣ ዶክተሮች፣ አካውንታንቶች፣ የሕግ ባለሞያዎችና የትምህርት ባለሞያዎች በአጠቃላይ እምነት የሚጣልባቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ያሉበት ኹለገብ ተቋም ነው፡፡

ሰንበት ት/ቤትን የመሠረቱልን አባቶች ክብር ይግባቸውና በረከታቸውም ይደርብንና ሞያ፣ ዕውቀትና ሀብት ብቻም አይደለም ቅን ታዛዥነትና ሐቀኝነትም የዚኽ ኹለገብ ተቋም ፍሬዎች ናቸው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ የጀመሩትን የፀረ ሙስናና ብልሹ አስተዳደር የማረም ዘመቻ ከግብ ለማድረስ ሰንበት ት/ቤቶች በተጠንቀቅ ቆመው የእርስዎን ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ በድጋሚ ልናረጋግጥልዎት እንወዳለን፡፡

የቤተ ክርስቲያን አምላክ ዕድሜና ጤና ይስጥልን፡፡

የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

ጥር ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.

Advertisements

10 thoughts on “የአ/አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ሙስናና ብልሹ አስተዳደርን ለማረም የፓትርያርኩን ትእዛዝ በተጠንቀቅ ቆመው በመጠባበቅ እንዳሉና በታዘዙበት መሥመር ለመሰለፍ ዝግጁ መኾናቸውን ገለጹ

 1. Anonymous January 16, 2014 at 8:23 pm Reply

  እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል መናፍቃንና ደጋፊዎቻቸው እንዲሁም ወያኔ ጉድ ፈላባቸው

  • Annonyname January 17, 2014 at 7:25 am Reply

   ከወያኔ ጋር ፀብ የለንም፣ በርሱም ላይ ጉድ ልናፈላ አልተነሳንም፤ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ነው የሚያነጋግረን፤ስለዚህ አስተያየት ሰጪዎች ለሰራተኞቹ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችን እንለግስ፡፡ ምንአልባትም ፖለቲካን ሽፋን አድርገው ቤተ ክርስቲያንን የሚወጉ ግለሰቦችን ከሆነ እነርሱን ከመንግስት ጋር እንዋጋቸዋለን፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ የህዝብ መንግስት ነው፡፡

 2. WOLETE MARIAM January 17, 2014 at 2:42 am Reply

  Gena Bezu Ale Yedendel Ferie Getachen Medhanitachen Eyesus Kirestorse YeEthiopian Ortodox Tewahedo Betechristianen Tensai Yasayen. Labatachenem Mulu Tenanena Edmen Yestelen. Yabatochachen Amlak Bewnet Yewnetegoch Abatoch Amlak Ayleyen. Amen. EleleleleleleleleleleleleleleleleleleleleleleellllllllllEWNET NEW Elelelelelelelelelel

 3. Anonymous January 17, 2014 at 8:28 am Reply

  Ere endew wed egame wed alenbet hager bemeta yemeyasfelgwen meswatent enkfelalen
  setu besedet berun zegto yetkemet ale bertu

 4. በአማን ነጸረ January 17, 2014 at 11:59 am Reply

  ስለቃለ-ዐዋዲያችን ያለፈበት መሆን ብዙ ተባለ.ሰ/ተማሪዎቻችንም አዲሱ ጥናት በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩን እየተማጸኑ ነው፡፡እስኪ ከተሰረዘም፣ከተሻሻለም፣የሚጨመርበት ከኆነም ነባሩን ህግ እንደመነሻ ማየት አይከፋምና እንየው፡፡በ1991ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የወጣው ቃለ-ዐዋዲ ስለ ሰ/ት/ቤት የሚደነግገውን አንቀጽ 21 እንዳለ ላስቀምጠው፡፡እውነት ይሄ ህግ አያሰራም?እስካሁንስ ሰ/ት/ቤቶቻችን በትክክል ሲተገብሩት ነበር?እውነት የሚባለውን ያህል ሁዋላቀር ነው?አንድ ምእመን እንዳሉት አርጅቱዋል?ማሻሻያ ነው ወይስ ጭራሽ መቀየር ነው የሚያሥፈልገው? የሚለውን እዩና ፍረዱ!!!ይሄው……
  አንቀጽ 21
  የሰንበት ት/ቤት ክፍል ስራና ሀላፊነት
  ስለ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች በቅ/ሲኖዶስ ፈቃድ የሚወጣውን ደንብና መመሪያ እየተከታተለ የሰበካው ሰ/ት/ቤት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
  1. የሰ/ት/ቤትን በሰበካው ቤ/ክ ያቁዋቁማል፣ያደራጃል፣በሰበካው ከ4 እስከ 30 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙትን ህጻናትና ወጣቶች የሰ/ት/ቤት አባላት እንዲሆኑና ዲያቆናት በመማር ቀሳውስትና መምህራን በማስተማር በሰ/ት/ቤቱ እንዲሳተፉ ያደርጋል፣
  2. ለህጻናትና ለወጣቶች እንደየእድሜያቸው ክልል በመከፈቃፈል በማእከል ደረጃ በሚወጣው ስርዐተ-ትምህርት መሰረት ት/ት መሰጠቱን ያከታተላል፣
  3. በሰንበትና በሌሎችም አበይት በዐላትና አመቺ ቀናት የእለትና የዘወትር መርሀግብር በማውጣት የቤ/ክ ህግና ስርዐት ፣የሃይማኖት ት/ት፣የቅዳሴ ተሰጥኦና የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እንዲሰጥ ያደርጋል፣
  4. ህጻናትና ወጣቶች ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እንዳይወጡ የቤ/ክ ህግና ስርዐት እንዲያውቁና እንዲያከብሩ፣ግብረ-ገብ እንዲሆኑ ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር በቅርብ እየተከታተለ ያስተምራል፣ይመክራል፣ይቆጣጠራል፣
  5. ለምዕመናን ት/ትን የሚሰጡ መንፈሳዊ መዝሙራትን እንዲያጠኑ የእለትና የዘወትር መርሀግብር ያዘጋጃል፣
  6. ወጣቶች መንፈሳዊ እውቀታቸው እንዲዳብር ስእሎችና ልዩ ልዩ የመማሪያ መሳሪያዎች የሚገኙበት ቤ/መጻህፍትን ያቁዋቁማል፣
  7. ከሰ/ተማሪዎች በበዐላትም ሆነ በአጋጣሚ ጊዜ በትያትር መልክ የሚቀርበው መንፈሳዊ ዝግጅት በቅድሚያ ለሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ቀርቦ ከተመረመረና ከተጠና በሁዋላ ሲፈቀድ በስራ ላይ እንዲውል ያደረጋል፣አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣
  8. የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች በትያትርም ሆነ በማናቸውም ሁኔታ የሚሰበስቡት ገንዘብ ለአጥቢያው ሰ/ጉባኤ ገንዘብ ቤት ገቢ ይሆናል፣ለሚያስፈልጋቸው ወጪ ጥናቱ ለአስተዳደር ጉባኤ ቀርቦ ሲፈቀድ በስራ ላይ እንዲውል ያደረጋል፣
  9. ቀሳውስት የንስሐ ልጆቻቸው ልጆች በሰ/ት/ቤት ተመዝግበው መንፈሳዊውን ት/ት እንዲከታተሉ ወላጆችም ልጆቻቸው በሰ/ት/ቤት ተመዝግበው መንፈሳዊውን እውቀት እንዲቀስሙ ማድረግ ክርስቲያናዊ ግዴታቸው መሆኑን ያሳውቃል፣
  10. የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች መንፈሳዊውን በዐል በሚያከብሩበት ጊዜ የቤ/ክርስቲያናችንን ስርዐትና ባህል በተከተለ ሁኔታ የመለያ ልብስ (ዩኒፎርም)እንዲዘጋጅላቸው ያደርጋል፣
  11. በሰ/ጉባኤ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ አካል ካልታወቀና በጽሁፍ ካልተፈቀደ በስተቀር በሰ/ት/ቤት ስም የአዳር መርሀግብር እንዳይደረግ በጥብቅ ይቆጣጠራል፣
  12. ከስብከተ ወንጌልና ከመንፈሳዊ ት/ቤቶች ክፍሎች ጋር በመተባበር መምህራንን እየጋበዘ ለሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ብቃትና ጥራት ያለው ት/ት እንዲሰጣቸው ያደርጋል፡፡

  ክቡር አንባቢ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መርሆዎችን ሰ/ት/ቤቶቻችን በትክክል ተልእኮዋቸውን እንዳይወጡ እንቅፋት ነበሩ ብለው ያምናሉ???መፍትሄውስ ይህን ህግ ወደ ትግባር ለማውረድ የሚረዳ ጥናት መቅረጽ ወይስ መርሆዎቹን የያዘውን ቃለ-ዐዋዲ እንዳለፈበት አድርጎ ማጣጣል???እባካችሁ እንቅስቃሴያችን በእውቀት የታገዘ ይሁን፡፡ያለንን በወጉ ይዘን በእሱ መሰረትነት አስፋፍቶ አሻሽሎ መስራት እንጅ የሃይማኖት መሪዎችን መቀያየር እየጠበቁ እንደ አዲስ ቤተ-ሰሪ ወከባ ማብዛት ረብ የለውም!!!
  በእኔ እምነት ቅዱስ አባታችን ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ጉዳዩ በሊቃውንት ጉባኤ በመታየቱ ቤ/ክ የምታገኘው እንጅ የምታጣው ጥቅም የለም፡፡እነሱ ሳያዩት አያሌ አጀንዳዎችን ከ15 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በሚያየው ሲኖዶስ አቅርቦ በግርግር ለማስጸደቅ መሞከርም ከቅን ልቦና የመነጨ ሀሳብ አይመስልም!!!ስለዚህ የሊቃውንት ጉባኤው በቂ ጊዜና ጥሞና ወስዶ እንዲያየው መደረጉ አግባብ ነው!!!
  እኛ አጥኚው አለመታወቁ አግባብ አልነበረም ስንል ወድቆም ይገኝ ዋናው ጠቀሜታው ነው ብላችሁ አልነበር!!ታዲያ አሁን ደርሶ እነ እንትና እንዳይገቡ እነ እገሌ ይግቡ ማለትን ምን አመጣው??እነሱንም በስራቸው ገምግሙዋቸዋ!!ለመስፈርታችሁ ታማኝ ሁኑ!!
  ታማኝ ልብ ይስጠን!!!!ይቆየን!!!

 5. Anonymous January 17, 2014 at 12:13 pm Reply

  Yebetekristiyan ganzab MK sizerf noro ahun silemusena mawurat ayaskedem. betekristiyan beraswa gize hulun tastekakelalech.

 6. berhan January 17, 2014 at 1:04 pm Reply

  ሶፎንያስ ጥር 09 2006 January 17, 2014
  ክብር ምስጋና ለመደሀኔ ዓለም ይግባዉ ሰንበት ት/ቤት ሁላችን ያደግንባት ከዉስጦም በዩንቨርስቲ የማይገኘዉን ብዙ ትምህርት የቀሰምንባት ነች ስለዚ ለዛሬዉ ማንነታችን መሰረት ናት እና በርቱ ተበራቱ አብረናቹ እንፋለማለን ከጎናቹ ነን በማንኛዉም ነገር አለንላቹ

 7. fekadeselassie January 17, 2014 at 4:00 pm Reply

  Bertu wondmochichin ena ehtochachin egziabher kegonachihu yikum!!!

 8. Anonymous January 28, 2014 at 11:27 am Reply

  betami dessi yemilnewu bertu ayzachu………….

 9. ሀይሌ March 12, 2014 at 3:40 pm Reply

  ያብዬን ወደ እምዬ ይሏል ይህ ነው !!!
  በሳሊተምህረት ካቴድራል የተሰራፋው የክህደትና የዘረፋ የህግ ወጥ መሬት ንግድ የኪራይ ሰብሳቢነት እውን መንግስትና ህግ ባለበት ሀገር እየተፈፀመ ነው ?
  በሚል ርዕስ የተፃፈውን የሀሰት ድራማና ተራ የስም ማጥፋት ሙከራን ብሎጉን የከፈተ ሁሉ አንብቦ በሁኔታው የሚናደድ የሚገረምና የሚቆጭና በአርምሞ ሁኔታውን የሚከታተል እንደሚኖር እሙን ነው ፡፡ ፀሐፊውና አበሮቹ ለድራማው የመረጡት ርዕስ በብልጣ-ብልጥነት የአንባቢንና የአድማጭ አእምሮ አገኝ ይሆናል የሚል የተስፋ ጉዞ መሆኑ ያመለክታል ፡፡ ጽሁፉ ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን እንደሚሆን አንባቢዎቼ እንዲገነዝቡልኝ ትረካው የውሸት ክምር ስለመሆኑም ላስረዳ ፡፡

  1. ክህደትና ዘረፋ ፡- ፀሀፊው ክህደትና ዘረፋ ያሉትን በሁለት መንገዱ በአጭር በአጭሩ እንየው፡፡
  ሀ/ በእርግጥም በሳሊተምህረት ይዞታ ላይ መኖሪያ ቤት ሠርተው የነበሩ የእኛ ነው በማለት በህግ ክርክር የከፈቱ ካህናት አባቶች እንደነበሩ አይካድም አነዚህን አገልጋይ አባቶችንም በሽምግልና አካሄዳቸው ትክክል እንዳልሆነና ወደ ውስጣቸው ተመልክተው ቦታው የእነሱ እንዳልሆነ አምነው እንዲቀበሉ ብዙ ሙከራዎች ተደርጎ መቀበል ባለመቻላቸው ጉዳዩ ረዥም ጊዜን ይውሰድ አንጂ ቤተክርስቲያኗ በህግ ይዞታዋ ተረጋግጦ ካርታዋን ተረክባለች ፡፡
  ለ/ የሰንበቴ ማህበራትን ለመናገር አስበው ከሆነም ፀሀፊውና አበሮቻቸው የኦ/ተዋህዶ እምነታቸው ካልተሸረሸረ በስተቀር በመላእክት ፃድቃን ሰማእታት ስም ሰንበቴ ማህበር ማቋቋም በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከአባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በአማኞቹ ዘንድ ያለ የነበረ ወደፊትም የሚኖር የቤተክርስቲያኒቱ ትውፊት ሆኖ ሳለ በሳሊተ ምህረት ካቴድራልም ያለው ከሌሎቹ አብያተክርስቲያን የተለየ እንዳልሆነም ሊሰመርበት ይገባል የተለየም አይደለምና ፡፡ እርግጥም ነው በቤተክርስቲያኒቱ ጥላ ስር የተቋቋሙ የሰንበቴ ማሀበራት አባላት የቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ፤ በሥራቸውም ሆነ በዕድሜአቸው ለአንቱታ የበቁ በህይወት ዘመናቸውም ሳያወላወሉ በያዙት ሃይማኖት የቆዩ ክህደትን ዘረፋንና ሙሰኝነትን የሚቃወሙ ምእመናንና ምአመናት ስብስብ በመሆናቸው በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የሚፈጸሙትን የመልካም አስተዳደር ፤ የሙስናና በልማት ሰበብ የሚፈፀመውን አይን ያወጣ ምዝበራን በመቃወማቸው እንብላ ባዮቹ የዚህ ጽሁፍ ፀሀፊውና አበሮቻቸው ፤ አናስበላም በሚሉ ምእመናን መካካል የተፈጠረውን ትንንቅ አቅጣጫ ለማስቀየር የቤተክርስቲያኗን አባቶችን ሁሉ ያሳሳተ መረጃ በመንገር ፉካ ነጋዴዎች ጥቅመኞች የሚል ሥም በመስጠትና ጥላሸት በመቀባት ብዙ መንገድ ተጉዛችኋል ፊት ለፊት በሚቀርቡ መረጃዎች ግን ማሸነፍ እንደማትችሉ ስትረዱት ከቁብ ሊገባ በማይችል የመናፍቃን ድረ ገጽ ያሰፈራችሁት ጽሁፍ የራሳቸሁን ማንነትና ሓይማኖታዊ ምንፍቅናና ጉዞአቸሁን ጭምር ያጋለጣችሁበትና ተስፋ የቆረጣችሁበት ጽሁፍ ሆኖ አግኝተነዋል ፡፡ ሀሰት ምንግዜም በቻዋን መቆም ስለማትችል በዙ ድሪቶ ያሻታልና ድሪቶአቸሁን አልብሳችሁ ቁመና ልትሰጧት ጣራችሁ ዕውነት ለጊዜው ብቻዋን የቆመች መስሏችሁ እየገፋችኋት ብትሆኑም ዕውነት የእግዚአብሔር ቃል ናትና ማሸነፏ አይቀሬ ነው ፡፡ ዕውነቱ መቼም ቢሆን ይወጣል ጊዜ ቢፈጅም ! እናንተም እርቃናችሁን ትቆማላችሁ ! ይህ ሁሉ መንፈራገጥ ከምንም የመጣ ሳይሆን በዐውደምህረቱና በየክብረ በዓላቱ ድምጽ ማጉያውን አንቃችሁ እየተፈራረቃችሁ “ሀሰት ሲደጋገም ዕውነት የመስላል የሚለውን የግብዞች አባባል ተጠቅማችሁ ” ለምዕመኑ የነዛችሁት ፐሮፓጋንዳ እርቃኑን ሲቀር እንጋለጣለን በሚል ካለባችሁ ስጋት የመነጨና ለቤተክርስቲያኗ ተቆርቋሪ መስሎ ለመታየት ከላይ የጠቀሳችሁትን ርእስ በመምረጥ የማደናገሪያ ስልት ይሆነናል ያላችሁትን መንገድ መረጣችሁ ፡፡ በእውነት ለእውነት የቆማችሁ ቢሆንማ ከ20ሺ የማያንሰው የአጥቢው ምእመን በሰንበቴ ያልታቀፈ በመሆኑና ቃለ ዐዋዲውም የአጥቢያው ምዕመን ሥልጣንና ተግባርን በግልጽ የአስቀመጠና በየ6ወሩ ምዕመኑ ሪፖርት በማዳመጥ በመልካም አስተዳደሩ ፤ በልማቱ ፤ በገንዘብ አሰባሰቡና አወጣጡ ላይ ተችቶ አቅጣጫ የሚሰጥ ሆኖ ሣለ በ3 ዓመት ከ10 ወራት ቆይታ አንድም ቀን ጉዳዩን ወደ ህዝብ አቅርቦ መፍትሄ እንዲያገኝ ወይም የአጥቢያው ምእመንን በማነቀሳቀስ መቋጫ እንዲኖረው ሳይደረግና በቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ውስጥም የተማከለ አስተዳደር እንዳይኖር ከካህናት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላትን የእናንተን ብልሹ አካሄድ እንዳይጋለጥባችሁ ስም አውጥታችሁላቸውና ጥላሸት ቀብታችሁ 2ቱን የካህናት ተወካዮች ከቦታው እንዲቀየሩ አስደረጋችሁ 2ቱ የህዝብ ተወካዮችም ምዝበራ ሲካሄድ ዓይናችን እያየ አንቀጥልም በማለት ራሳቸውን አገለሉ ፀሀፊውና አበሮቻቸው በአመቻቹት ጎዳና ከህደትና ዘረፋውን ተያያዙት ያብዬን ወደእምዬ የሏል ይህ ነው ፡
  2. ህገወጥ የመሬት ንግድ ፡- አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ካልሆነ በቀር እንኳን የዞታዋን በህግ ያስከበረችንና ማረጋገጫ ካርታ ያላትን የቤተክርሰቲያን ይዞታ መሸጥ ቀርቶ የራስንም ለመሸጥ በክ/ከተማው የመሬት አስተዳደር በኩል በካዳሰተር ካልተረጋገጠ እንደማይቻል እየታወቀ አባባሉ ትኩረትን ለመሳብ ተብሎም ከሆነ ጊዜው ያለፈበት ነውና የማይመስል መናገሩ ትዝብት ላይ ይጥላችኋል፡፡
  3. ኪራይ ሰብሳቢነትንም በተመለከተ፡- መንግሥትም ህግም በአገሪቱ ላይ ስለመኖሩማ ሉአላዊት አገር ስለሆነች እኛ ሳንጠራጠር አለ እንላለን !! ልትጠራጠሩም አይገባም በህገ ወጥ መንገድ እየመዘበሩና በአቋራጭ ለመክበር የሞከሩ የመንግስት ባለስልጣናትንም ሆነ ተላላኪዎቻቸውን ሳይቀር ለፍርድ አደባባይ አቅርቦ መኖሪያቸውን ቃሊቲ ያደረጉ ለመኖራቸው አላወቃችሁም !! መንግስት በኃይማኖት ኃይማኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለው የኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 11 /3 የጠቀመው እናንተኑ ጸሀፊውንና አበሮቹን ነው ባይሆንማ በአሁኑ ሰአት ቤታችሁ የት እንደምትሆኑ ለእናንተም ግልጽ ነበር ፡፡ የቅድስት ሳሊተ ምህረትን ምልጃና እርዳታ ፈልጎ የሚመጣው ምዕመናንና ምዕመናት በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩት ሳይቀሩ እናቶች መቀነታቸውን ፈትተው አባቶች ኪሳቸውን ዳብሰው በገንዘብም ሆነ በዓይነት እያለቀሱ ያቀረቡትን መባ ሙዳየ ምጽዋቱ ሲዘረገፍ በማዳበሪያ እየሞላ በሸክም የተሰበሰበው ወደ ባንክ ሲሄድ ቀሎ በካኪ ኮሮጆ ወይም በፌስታል ተይዞ ባልገባም ነበር ከእናታችሁ መቀነት መስረቁ ሳያነስ በይዞታዋ ዙሪያ ያከራያችኋቸውን የብሎኬት አምራቾች ጉቦ ካልሰጣችሁ ውላችሁ እይታደስም በማለት ያንገላታችኋቸው ተከራዮች ምን ያህል እንደሚታዘቧችሁ እንደሚያቀሏችሁ አስባችሁት ተውቃለችሁ !! ሰሚ ካለ ሀቁ ይወጣል ለነገሩ ኅሊናውን የሸጠ ሰው ምን ይለኛልን የማያወቅ ገንዘብን አምላኩ ያደረገ ይህን ያስባል ማለት የዋህነት ነው ፡፡ ለዚህም ነው በቡድን በመደራጀት እያደረጋችሁት ያለው ወደር የሌለው ብዝበዛ እንድታቆሙ በዕውነት ስለዕውነት የሚታገሏችሁን ምዕመናንና ምዕመናት ላይ ስም የለጠፋችሁባቸው ፡፡ ሀሰትን በድሪቶዋ ለመሸፋፈን የተደረገ በመሆኑ ዕውነት ብቻዋን ሆና እንደምታሸንፍ ለደቂቃ የሚጠራጠር ልቦና የለምና ጊዜ ይርዘም እንጂ መሸነፋችሁ እውነትና አይቀሬም ነው ፡፡
  ዕውነቱ ግን ይህነው !!!!
  የሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ባጥቢያዋ ምዕመናንና ምዕመናት ጥያቄ በሟች አቡነ ተክለሃይማኖት ፕትርክና ዘመን በአባታችን ፈቃድ በወቅቱ የገበሬ ማህበር ክልል ስለነበረ ማህበሩ 2ዐ ሄክታር መሬት በዓዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት መድቦና የወቅቱ የአቃቂ ወረዳ መሬት አስተዳደር ፈቅዶ የተተከለች መሆኑ አይዘነጋም ፡፡
  የአጥቢያ ምዕመናትና ምዕመናን ተባብረው መቃኞ ቤተክርስቲያን ሰርተውና ታቦተ ሕጉን አስገብተው መገልግል መጀመራ ቸውም እውነት ነው ፡፡ በወቅቱ በነበረው ውስን አቅም አንድ አነስተኛ ሕንፃ ቤተክርስቲያን በይድረስ ይድረስ በመስራት መሰረቱን በብር 38 ሺ ተጀምሮ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ ከቦታው ስፋትና አቀማመጥ አኳያ የተጀመረው መሰረት ላእላይ አካሉን መሸከም የማይችልና ጠባብም በመሆኑ እንዲፈርስ ተደርጎ የአጥቢያዋ ምእመናንና ምእመናት እንደ አንድ ሰው ሆነው ሕብረት በመፍጠር 54 ሺ ብር ይዘው ተነስተው በ 9. 7ሚሊዮን ብር ይህንን አሳይ መሲዎቹ ስዕሉ ላይ ያወጡትን ካቴድራል ሰርተው ግንባት 21 ቀን 1997 ዓ/ም አስመርቀው ለአገልግሎት አብቅተዋል ሂሳቡም በየዓመቱ ኦዲት ተደርጎ የመጨረሻው የኦዲት ሪፖርት አ/አ ሀገር ስብከት ጽ/ቤት አውቆት የሰጠው ምስጋናና የኦዲት ሪፖርቱ በሕዝቡ እጅ ይገኛል ፡፡
  በግንባታው ሂደት አሰራሮች ግልጽና አሳታፊ እንደነበረ ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ሁሉ የተመለከተው የተሳተ ፈበትና ያደነቀው ስራ ነው ፡፡ ይህ ወሮበላ የወጣቶች ቡድን ከሳሪስ አቦ ተዛውረው የመጡ ሦስት ግለሰቦችና ከአጥቢያዋ ምዕመናን ሀቀኛ መስለው በሰበካ ጉባዔ ተመራጭነት ሾልከው ከገቡ በኋላ ለይስሙላ ሕዝቡ እንዲያምናቸው ከሳሪስ አቦ በሕዝብ ጩኽት የተባርረውን ቡድን ለጊዜው ከኮነኑትና ዝውውሩንም የተቃወሙ ከመሰሉ በኋላ ለዘረፋ የሚያመቻቸውን ስልት በጋራ ቀይሰው አንዳንድ ቁልፍ ቦታ ላይ ያሉ አባቶችን ለማሳመን የሚቻላቸውን ሁሉ ካደረጉ በኋላ ከሕንፃ ግንባታው የተረፈውን 3.8 ሚሊዮን ብርና በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የተሰበሰበውን የአሁኑ ጊዜ የቤተክርስቲያኗ ተገልጋይ ሕዝብ 25 ሺ በላይ በመሆኑና ገቢዋ ስላደገ በትንሹ በወር 1 ሚሊዮን ቢታሰብ በእነሱ የቆይታ ዘመን ሲሰላ በጠቅላላው ከ 3ዐ ሚሊዮን ብር በላይ በጥቃቅን ብልጭልጭ የልማት ስራዎች ስም ተገንነት ለግል ጥቅማቸው የዋሉ ወጣት ዘራፊዎች ናቸው ፡፡
  ስማቸውም
  • ዲያቆን ታምራት ውቤ የሰበካ ጉባዔ ተመራጭ
  • ዲያቆን አቤል አሰፋ ሰንበት ት/ቤቱን የወከለ የሰበካ ጉባዔ ተመራጭ
  • ዲያቆን ሩፋኤል የማነብርሃን ፀሃፊ /ከሳሪስ አቦ የተባረረ
  • ዲያቆን ዘርዓብሩክ አብርሃ ሂ/ ሹም /ከሳሪስ አቦ የተባረረ
  • ዲያቆን ፍፁም የማነብርሃን ም/ፀሃፊ /ከሳሪስ አቦ የተባረረ ፡፡ ይህ ማፋያ የወጣቶች ቡድን ነው ዛሬ ቤተክርስ ቲያኗን የተከሏትንና ሕንጻ ቤተክርስቲያኑን ገንብቶ ለአገልግሎት ያበቁትን ትክክለኛ ምዕመናን ስም እያጠፋ ያለው፡፡
  ምእመናንና ምእመናት እንደማንኛውም ሌሎች አድባራትና ገዳማት በቤተክርስቲያኗ ፊቃድና መመሪያ መሰረት የሰንበቴ ማሕበራት ማቋቋማቸውና መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በትውፊቱ መሰረት ማራመዳቸው እውነት ነው በአጭር አነጋገር ፋካ ሻጭና ነጋዴ ሰንበቴም ሆነ ግለሰብ የለም ትልቁ ነጥብ ምእመናትና ምእመናን የቤተክርስቲናያኗን ሀብትና ንብረት ያለምእመናን ተሳትፎ ሲዘርፏት ዝም ብሎ ማየት አለመፈለጋቸው ነው ፡፡ ይህ ከሚገለጽበት አንድ መንገድ ምንም ስራና ሞያ የሌላቸው እነዚህ ወጣቶች ባሁለትና ሦስተ መኪና ባለቤት ሲሆኑ በተለይ ዲያቆን አቤል አሰፋ የአዳዲስ መኪና አስመጪ ሆኖ በሚሊዮኖች ብር ጨዋታ ውስጥ መግባቱ ነው ፡፡ የማይገናኙ ነገሮችን እያገናኙ የእውነት ጠብታ ያልነካውን ድርሰት የሚደርሰው የበፊት ልምዱና ስራውን ስለምናውቅ ይሄው አቤል አሰፋ ኑሮው ሲለውጥ ከየት አመጣኽው ሲባል የአባቴን ሽጉጥ ሸጬ ነው ብሎ ምክንያት ለመስጠትም ሞክሯል ሽጉጥ ሸጦ መኪና አስመጪና ሻጭ መሆን እንዴት የቻላል ፡፡ ይሄው ይህን የውሸት ክምር ያነበበ ሀሉ እንዲገነዘብ የምፈልገው በጥቅሉ
  1. የቤተክርስቲየኗ ይዞታ ለሌላ ሦስተኛ ወገን ያከፋፈለ ሰንበቴ ማኅ በር የለምም ሊኖርም አይችልም
  2. በሰንበቴ ማኅበር ውስጥ ያጥቢያዋ ምእመናን እንጂ መናፍቃን የሉም መናፍቃኑ ኃይማኖታቸውም የመላእክት የጻደቃን ሰማእታት ምልጃን ስለማያምኑበት በማህበሩም ሊሰባሰቡ አይችሉም እያንዳንዱም አባል የቤተክርሰቲኗ ደብተር ያለው የንስሀ አባቶች ያሏቸው ናቸው
  3. ፋካ የሸጠም ሆነ ያጫረተ የለም የራሱንም አባላት ድርሻ አለሟላምና
  4. የተሰሩ ፋካዎች በወቅቱ የቤተክርስቲያኗ ሰበካ ጉባዔ ፈቅዶና ፈረሞ በሰጠው ቦታ ላይ የተገነቡ ስለሆኑ አንደሌላ አድባራት ሰንበቴ ማህበሮች የሚመሩና የሚተዳደሩ ከመሆኑ በቀር የተለየ መመሪያ ሊወጣላቸው አይችልም አይገባምም፡፡ ዘራፊው የወጣቶች ቡድን ይህን የሚለው ሕዝቡን በመከፋፈል በእርሱ ላይ ያለውን አትኩሮት ለመቀነስና በሰንበቴ የተሰ ባሰበው አማኝ ምዝበራውን በጋራ ለመቃወም እንደሚችሉና በነርሱ መዘውር ውስጥ እንደማያስገቧቸው በማመን ከፍርሀት ያመነጩት መሆኑ ነው፡፡
  • የሰንበቴ አገልግሉት የሚሰበሰብ ገንዘብ ለአባላት አይከፋፈልም
  • ከሰንበቴ አባላትም የደህንነት አባል ነኝ ያለ ግለሰብም የለም ቢኖርም ባለው የስራ ኃላፊነት አለአግባብ ተጠቅሞበት ከሆነ በማስረጃ በህግ መጠየቅ ሲቻል ………ያለበት ዝላይ አይችልም ከሆነ ሥጋቱ ቢኖር አይደንቅም
  • ከርታው እንዲገኝ የታገለው ቦታውን የተረከበው የአጥቢያዋ ምእመናን እንጂ ትላንት ተጠራርተው የተሰበሰቡ የዘራፊ ቡድን አባላት አይደሉም ፡፡ የግል ባለይዞታነት መብት አለን የሚሉትና የሚከራከሩ ግለሰቦች ከሰንበቴም ሆነ ከአጥ ቢያው ምእመናን የአገልግሎት ጥያቄ ጋር ግንኙነት የለውም
  • ሕንፃ ኮሚቴ ለሰንበቴዎች ቦታ ሰፍሮ የሰጠው በወቅቱ ከነበረው የሰበካ ጉባዔውና አስተዳዳሪው የተፈቀ ደውንና በንዑስ ኮሚቴነቱ ታዞ ተመርቶለት ነው ዛሬ የዘራፊው ቡድን እየሰበሰበ በአጥቢየዉ ምእመናን ላይ ሴራና ደባ የሚሸርብበት ቢሮ ሁሉ ታቹ ፋካ ሆኖ በተመሳሳይ መንገድ የተሰራው ነው ፡፡
  • ጰጰሳት በተገኙበት ተካሄደ የተባለው የሰበባካ ጉባዔው ምርጫ በአጥቢያዋ ምእመናን የተካሄደ ሳይሆን ከጎሮ ገብርኤል ከኢምፔሪያል ማርያም ከየካ ሚካኤል ከአያት አቡዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ በተሰበሰቡት የሰን በት ትምህርተ ቤት አባላት የተካሄደ ስለሆነ እነዚህ 5ቱ ዘራፊ ወጣቶች በቀየሱትና አውቀውመ ሆነ ሳያ ውቁ በተሳሳቱ ጰጰሳት አስተባባሪነት የተካሄደ ስለሆነ በርግጥም ይቺን ቤተክርስቲያን የተከሏትንና ሕንፃዋን የገነቡትን ምእመናን የማይወክል አሻንጉሊት የሰበካ ጉባዔ ነው፡፡
  • ከቃለ አዋዲ ውጭ የሰበካ ጉባዔ ተመራጭ መሆን የሚፈልግ ምእመን የለም በቤተክርስቲየኗ ቀርቶ በአለማዊ መድረክ የማይሰራ ምርጫ የተካሄደው በሳሊተምህረት ቤተክርስቲያን ብቻ ነው በጥቅሉ ያጥቢየዋ ምእመናን ከዚህ ወሮበላ ቡድን ጋር መቆየትም ሆነ መደራደር ስለማይፈልግ በአንድነት ታግሎ ቤተክርስቲየኗን ከማጽዳት ውጪ የፖለቲካም ሆነ የሌላ ዓላማ ስለሌለው የሚመለከታችሁ መንግስታዊመ ሆነ መንፈሳዊ የአስተዳደር አካላት በዚሁ ግንዛቤ መሰረት ከእውነቱ ጋር በጽናት እድትቆሙ በአግዚአብሔር ስም እየጠየቅን ይህ ተስፋ የቆረጠ የዘራፊ ቡድን ምንም ጻፈ ምንመ ምእመናኑ ከእውነት መስመሩ ንቅንቅ የማይል መሆኑን እንገለጻለን፡፡
  • ከቃለ አዋዲ ውጭ የሰበካ ጉባዔ ተመራጭ መሆን የሚፈልግ ምእመን የለም በቤተክርስቲየኗ ቀርቶ በአለማዊ መድረክ የማይሰራ ምርጫ የተካሄደው በሳሊተምህረት ቤተክርስቲያን ብቻ ነው በጥቅሉ ያጥቢየዋ ምእመናን ከዚህ ወሮበላ ቡድን ጋር መቆየትም ሆነ መደራደር ስለማይፈልግ በአንድነት ታግሎ ቤተክርስቲየኗን ከማጽዳት ውጪ የፖለቲካም ሆነ የሌላ ዓላማ ስለሌለው የሚመለከታችሁ መንግስታዊመ ሆነ መንፈሳዊ የአስተዳደር አካላት በዚሁ ግንዛቤ መሰረት ከእውነቱ ጋር በጽናት እድትቆሙ በአግዚአብሔር ስም እየጠየቅን ይህ ተስፋ የቆረጠ የዘራፊ ቡድን ምንም ጻፈ ምንመ ምእመናኑ ከእውነት መስመሩ ንቅንቅ የማይል መሆኑን እንገለጻለን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: