ፓትርያርኩ የሀ/ስብከቱ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናት ‹ተቃዋሚዎች› ንግግር ግብረ ገብነት የጎደለው ሕገ ወጥ እንደኾነና የለውጥ ሒደቱ መሥመሩን እንደማይለቅ አረጋገጡ

 • ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልጅነት በግብረ ገብነት መነጋገር ነው እንጂ ሕገ ወጥ ንግግር ተቀባይነት የለውም፤ ይኼ የአሁኑ የእናንተ የረጋ አቀራረብ ነው፤ ያስመሰግናል፤ ቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለው አስተዳደር እንዲኖራት ነው የኹላችን ጥረት፤ ወደኋላ የምንመለስበት ምንም ምክንያት አይኖርም፤ መሥመሩን አይለቅም›› /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ/
 • ‹‹የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ያስጠናውን ተወያይተንበታል፤ የታሰበው የአደረጃጀትና የአሠራር ማሻሻያ የሚያነቃቃ፣ አንገታችንን አቅንተን እንድንሔድና በቤተ ክርስቲያናችን እንድንኮራ የሚያደርገን ነው፤ ቤተ ክርስቲያናችን መልካም አስተዳደር ለማስፈን በመነሣሣቷ ደስተኞች መኾናችን ዕወቁልን፤ እኛን እንደወከሉ መስለው እዚኽ የመጡት እኛን አይወክሉም፤ ጥናቱ በእኛ ዘመንና በቅዱስነትዎ ጊዜ መተግበር አለበት፡፡›› /የምእመናን ተወካይ የኾኑ የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር/
 • ‹‹በመዋቅርና አሠራር ለውጥ ረቂቅ ላይ ውይይት ሲካሔድ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በዝቷል ያላችኹትን ቀንሱ፣ የጎደለበትን ጨምሩ ብለዋል፤ ሀ/ስብከቱ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን የጠበቀና የዘመኑን ሥልጣኔ የዋጀ አደረጃጀትና አሠራር ለመዘርጋት መነሣቱ ያስመሰግነዋል እንጂ አያስነቅፈውም፤ የበዛው ተቀንሶ፣ የጎደለው ተሟልቶ በብፁዕ ሊቀ ጳጳሳችን መሪነት እንድንሠራበት ይደረግ…፤››
 • ‹‹…ከእኛ በላይ ያሉት አባቶች እየተሰደቡ እኛን የሚሰማን አይኖርም፤ ትውልዱ መካሪ አባትና አርኣያ ካጣ የሥነ ምግባር ጉድለት ይስፋፋል፤ ሠርተው የሚያሠሩንን አባቶቻችንን አጥተን ሌላ አባት ልናገኝ አንችልም፤ የስም ማጥፋት ዘመቻውና ውንጀላው እንዲቆም ቅዱስነትዎ መመሪያ ቢሰጡልን፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያልቅ ነገር ካለ ይለቅ፤ አስተዳዳሪዎች እየተለያየን ሳይኾን በአንድ ላይ ኾነን ፊት ለፊት እንነጋገር፤ የተነጋገርነውም እዚኹ ይቅር፤ በኢንተርኔት የመናፍቅ መጫወቻ አንኹን፡፡›› /የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ተወካይ የኾኑ የጃቲ መካነ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ/

 

Advertisements

6 thoughts on “ፓትርያርኩ የሀ/ስብከቱ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናት ‹ተቃዋሚዎች› ንግግር ግብረ ገብነት የጎደለው ሕገ ወጥ እንደኾነና የለውጥ ሒደቱ መሥመሩን እንደማይለቅ አረጋገጡ

 1. Rodase January 11, 2014 at 9:27 am Reply

  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚታየውን የአሰስተደዳደረር ብልሹ አሰራር (ሙሰኝነት፣ ምዝበራ፣ ጎሰኝነት፣አድሎ…) ከሥር መሰረቱ ለመንቀል የተጠናው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአሰራርና የአደረጃጀት የጥናት ሰነድ
  1. እነማን ተቃወሙት?
  2. ቅድመ ታሪካቸው ምንድን ነው?
  3. ለምን ተቃወሙት?

  1. እነማን ተቃወሙት?
  – ኤልያስ አብርሃ ‹‹”ንቡረ ዕድ”››/በቤተ ክህነት መዋቅር ቋሚ የሥራ መደብ የለውም፣ ዋና ስውር ተግባሩ የጸረ-ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የውስጥ የጠላት ምሽግና ጉዳይ አስፈጻሚ ነው፡፡ በአንዳንድ ጉዳዮች እና አጀንዳዎች ዙሪያ በስውር ‹‹”በመንግስት”›› ይደገፋል/፡፡
  – ሳውሮስ ‹‹”ጳጳስ”›› /የወሊሶ፣ የግልም ሆነ የዕምነት ሥነ-ምግባር የሌለው፣ የተሀድሶ ዕምነት አራማጅ፣ የቤ/ክ የዕምነት “አባቶች” በዘመናችን ምን ያህል የምዕመናን እረኚነታቸውን እንደዘነጉ አብይ ምሳሌ ሆኖ የሚቀርብ፣ የዘመኑ ይሁዳ ተምሳሌት መገለጫ/፡፡
  – ዘካርያስ ሐዲስ ‹‹”ሊቀ ትሁሃን”››/የኮተቤ ቅዱስ ሚካኤል “አስተዳዳሪ”/
  – ዕዝራ ‹‹”ሊቀ ሊቃውንት”››
  – ሰረቀ ‹‹”አባ“›› /የፕሮቴስታንት ዕምነት ተከታይ፣ የተሀድሶ የውስጥ ክንፍ ዋና አደራጅ፣ ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምሮ የተሳሳተ ነው በሚል በቅፅል ስም መጽሀፍ ያሳተመ፣ ሽጉጥ ታጣቂ…/፡፡
  – ኃይሌ አብርሃ ‹‹”መልአከ ገነት”››/ከብስራተ ገብርኤል ሚሊዮኖችን የዘረፈ፣ አሁን አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ “አስተዳዳሪ” ሆኖ የተሾመ/-… እንዲሁም ሌሎች ስድስት ግለሰቦች፡፡

  2. የተቃወሙት ግለሰቦች ቅድመ ታሪካቸው ምንድን ነው?

  – የጸረ-ኦርቶዶክስ፣ የጸረ-ኢትዮጵያ ተሀድሶ መስራቾችና ጉዳይ አስፈጻሚዎች የነበሩ፣ አሁንም በዚህ ድርጊታቸው ላይ የሚገኙ፡፡
  ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸው ተሀድሶዎች እና ጉዳያቸው ሳይጠናቀቅ በአቋራጭ አዲስ የአካሄድ ስልት የቀየሱ ግለሰቦች፡፡
  የኢትዮጵያ ቤ/ክ ለሁለት (‹‹አ/አ ሲኖዶስ እና አሜሪካ ሲኖዶስ››) በመባል እንድትከፈል ያደረጉ፤ የ2005 ዓ.ም. የዕርቅ ሂደቱን ያደናቀፉ፡፡ በዋናነት ኤልያስ አብርሃ!፣ ሰረቀ፣ ሳውሮስ… የዚህ ተልዕኮ አስፈጻሚ የነበሩ፡፡
  – ከደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ከ 30 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ በጠራራ ጸሃይ የዘረፉ (አሁን አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ ሆነው ለሌላ ዝርፊያ ዘመቻ የጀመሩ)፣ህዝብ ያሰራውን የቤተክርስቲያን ህንጻ ለመናፍቅ ያስረከቡ፡፡-የድሬደዋ ሀ/ስብከት አብያተክርስቲያናት ህንጻ ስራ ዘራፊዎቸ የነበሩ፡፡
  – ከልደታ ማርያም ቤ/ክ ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ በጠራራ ጸሃይ የዘረፉ፤ ጉዳያቸው አሁን በፍትህ ሚኒስቴር ተመርምሮ በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ፡፡
  – ከቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ ለቁጥር የሚያዳግት የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት የዘረፉ፣ ያዘረፉ፡፡ የዝርፊያ ሀብታቸውን እስከ ደ/አፍሪካ ድረስ መላክ የጀመሩ፡፡ የቤተክርስቲያን የገቢ እና የወጪ ህገወጥ የገንዘብ ሞዴል ሪሲቶች፣ ማህተሞች፣ ቲተሮች… በማተም፣ በማሰራጨት፣ ገቢውንም በመሰብሰብ የተሰማሩ፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ ካዛንችስ ዑራኤል ህንጻ ላይ አሁን ሄዶ ይህን ህገወጥ ህትመት መግዣት ይቻላል፡፡
  – የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የቁልቢ ቅ/ገብርኤል፣ የሳህሊተ ምህረት ቅ/ማርያም ገዳማት፣ ቤ/ክ ሀብትና ንብረት ምዝበራና ዝርፊያ ፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች፤-ሽጉጥ ታጣቂዎች፣-ዘረኞች፣- በ3 ሺህ ብር ደመወዝ የሲኖ ትራክ ገልባጭ፣የዶልፊን፣…ባለሀብቶች፣-የሳምንት ዕቁብ ጣዮች…
  ከላይ የተዘረዘሩት አባይን በጭልፋ እንደሚባለው ለአብነት የቀረበ ሴጣናዊ ቅድመ ታሪኮቻቸው ሲሆን በአጠቃላይ የእነዚህ ግለሰቦች እና መሰሎቻቸው ቅድመ ታሪክ የሚያጠነጥነው፡- በተሀድሶ ምንፍቅና አገልግሎት፣ የሰው ነፍስ በማጥፋት፣ በአደባባይ ዝርፊያ፣ በሙስና፣ በሙዳይ ምጽዋት ገልባጭነት፣ በዘረኚነት… ነው፡፡
  የንስሃ ህይወት ይስጣቸው!

  3. ከላይ የተዘረዘሩት ኃይሎችና መሰሎቻቸው የአሰራር፣ የአደረጃጀት ለውጡን ለምን ተቃወሙት?
  ከጀርባቸው ያነገቡት ዕውነታ !!

  ቤተክርስቲያን ጠንካራ የአስተዳደር መዋቅር፣ ግልጸኚነት እና ተጠያቂነት ያለው የፋይናንስ አሰራር፣ በዕቅድ የሚመራ የካህናት፣ የምዕመናን፣ የሰ/ት/ቤት፣ የማህበራት… የልማት አገልግሎት ብትዘረጋ እስከ አሁን ሲዘርፉት፣ ሲያዘርፉት፣ ሲጨፍሩበት፣ ምንፍቅናን ሲዘሩበነት … የነበረው በር ክርችም ብሎ ሊዘጋ ሆነ፡፡ ለዚህ መፍትሄው ደግሞ አሁን እንደመረጡት መቃወም፣ ማደናቀፍ፣ ፓሮፓጋንዳ መንዛት…ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ይህ የመጀመሪያው ስልታቸው ግቡን ካልመታ ይህንን የቤ/ክ ጉዳይ ወደ ፓለቲካ አጀንዳ በመቀየር የቤተክርስቲያን ቀናተኛ አገልጋዮቿን፣ ምዕመኖቿን… ከጸረ-ኦርቶዶክስ ‹‹የመንግስት›› ሹማምንት ጋር ማጋጨት፣ ማበጣበጥ… ነው፡፡
  ይህም ካልተሳካ ደግሞ አልሞተ ባይ ተጋዳይ በሽጉጦቻቸው እራስን አጥቶ ጠፊ ሆኖ መሰለፍ በአንደበታቸው የሚናገሩት የመጨረሻው የስልቶቻቸው ማስፈጸሚያ አማራጭ አድርገው ቀርበዋል፡፡ የይሁዳ መጨረሻ እራሱን ዛፍ ላይ ሰቅሎ ማጥፋት ነበርና፡፡
  ታዲያ በዚህ የቤተክርስቲያን መዳከማ ዋና ተጠቃሚው የሰረቀ የውስጥና የውጭ የጸረ-ኦርቶዶክ ፣ ተሀድሶ ቡድን እንዳይሆን ከእኛ ኦርቶዶክሳዊ የተዋህዶ ልጆች ምን ይጠበቃል? ጊዜው አሁን ነው!!!

 2. Anonymous January 11, 2014 at 1:46 pm Reply

  የሳቸውም አካሄድ በ መሠሪዎቹ ኤልያስ አብርሃ ና ሰረቀ እንዳይበላሽ ተግተን ልንጠብቅ ይገባል:: መናፍቃንና የወያኔ ተላላኪዎች ከቤተክርስቲያን ተጠራርገው የሚወጡበት ሰዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ መረጋገጥ አለበት መቸም መናፍቅ ሁልግዜ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ባይጠፋም ::

  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንንና ሀገራችንን ኢትዮጵያን ስለ እመቤታችን ስለገባው ቃል ኪዳን ሲል ይጠብቅልን ::

 3. Annonyname January 14, 2014 at 2:24 pm Reply

  የቤተ ክርስቲያናችን ችግር የዕኛ የጓዳችን ችግር ችግር ነው ብለን ምዕመናን በሙሉ የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ዘራፊዎቹን በማጋለጥ፣ መረጃዎችን በማስረጃ አስደግፈን በማቅረብ እነርሱ በታጠቁት ሽጉጥ እስከምንሞት ድረስ መታገል አለብን፡፡ ምዕመናን በፀሎትና በፆምም ልንተጋ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፣ለአገልጋይ አባቶቻችን ኃይልና ብርታቱን ይስጥልን፡፡

 4. Redae Tewelemedhn Gebremaryam January 14, 2014 at 8:40 pm Reply

  The person who has written a comment above about Abaserekebrihan Weldesamual is the one who is the exact copy of “Diablose” because we know who is Abasereke?
  Abaserekebrihan is the one who is stand always with the truth , he is a wise,the educated one and stand always against the corrupter.He has repeatedly written a letter to the holy “Synodose” to exist peace between the two “Synodose” and also has contributed a great role to Ethiopian orthodox tewahido church when he was in USA.Now he is the head of the Ethiopian orthodox “tewahido” church learning and training center. Therefore,you and “Mahibere setan” must learn from him………………….

 5. Sisay Wondimu January 16, 2014 at 12:06 pm Reply

  If u are truth lover, u have not to state your objection on the specific statement in a way u object all the statement.

 6. Sisay Wondimu January 16, 2014 at 12:18 pm Reply

  We all the Orthodox Tewahido Christians’ who loves the administrative renaissance of our Church have to be on the side of the drafted regulation “denb”.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: