የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥን በመደገፍ ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የድጋፍ ስብሰባ ለመጪው ሳምንት ዐርብ ተላለፈ፤ የድጋፍ መግለጫ የኾነውን ስብሰባ በሦስት ምዕራፎች በመክፈል በከፍተኛ ዝግጅት ለማካሔድ ዝግጅቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል

 • በሦስት ምዕራፎች በተከፋፈለው የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ መርሐ ግብር÷ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የአብነት መምህራንና ሰባክያነ ወንጌል በመጀመሪያው ምዕራፍ፤ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት ሊቃነ መናብርትና ምእመናን በሁለተኛው ምዕራፍ፤ ሰንበት ት/ቤቶች በሦስተኛው ምዕራፍ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ ተገናኝተው እንዲወያዩ ዕቅድ ተይዟል፡፡
 • የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የአብነት መምህራንና ሰባክያነ ወንጌል በምልአት ወጥተው የሚሳተፉበት የመጀመሪያው ምዕራፍ የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ መርሐ ግብር በመጪው ሳምንት ዐርብ፣ ጥር ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡00 በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ ለማካሔድ የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ቀጠሮ መያዙ ተገልጧል፡፡
 • ለዛሬው መርሐ ግብር መስተጓጎል ተጠያቂ የተደረጉት የፓትርያርኩ አቡነ ቀሲስ እና የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊ እርስ በርሳቸው እየተወነጃጀሉ ነው፡፡ ከሙሰኞች ጋራ የተሳሰሩት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቁ አራማጆች እንደሚመኙት ሳይኾን የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነዱን በቀረበበት አኳኋን በአረጋጋጭነት (maker – checker) ለመገምገም በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ የተቋቋመው ‹‹የሊቃውንት ጉባኤ›› አባል መኾናቸው የተገለጸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ሁለቱንም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ረዳቶች እንቅስቃሴ እንደሚዘውሩና ከባድ ተጽዕኖ እየፈጠሩባቸው እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡
 • ከአቡነ ቀሲሱ ጋራ እየተወዛገቡ የሚገኙት የልዩ ጽ/ቤቱ ሓላፊ አቶ ታምሩ አበራ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በዛሬው የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ መርሐ ግብር እንደተያዘላቸው የስብሰባው አስተባባሪ ለኾኑ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ዐርብ ምሽት አረጋግጠውላቸው ነበር፡፡
 • የፓትርያርኩን ዕለታዊ መርሐ ግብር ዐውቀውና ከቅዱስነታቸው ጋራ በመማከር አዘጋጅተው  አፈጻጸሙን የመከታተል ሓላፊነት ያለባቸው አቶ ታምሩ በትላንትናው ምሽት ለስብሰባው አስተባባሪዎች ፓትርያርኩ በዛሬው የድጋፍ መግለጫ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እንደማይችሉ የገለጹላቸው ምክንያት፣ ‹‹ቅዳሜና እሑድ እኔ ፕሮግራም ላስይዛቸው አልችልም፤ ረስቼ ነው እሺ ያልኋችኹ፤ እኔ ፕሮግራም ላስይዝ የምችለው ከሰኞ እስከ ዐርብ ድረስ ብቻ ነው፤›› የሚል ነው፡፡
 • በግልጽ በሚታይባቸው የንቁህነትና የትጋት ውስንነት (inaction) ፓትርያርኩ አርቀዋቸዋል የሚባሉት አቶ ታምሩ ከዕንቅልፍ ማብዛት ጋራ ተያይዞ በፓትርያርኩ ላይ በሚሰነዘረው ትችትም ተጠያቂ ተደርገዋል፤ ወደ ፓትርያርኩ በወቅቱ መቅረብ የሚገባቸውን ጉዳዮች ‹‹ይቀብራል፤ ያገኘ ኹሉ ያታልለዋል›› በሚል የጠቅ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ጭምር የሚያማርሯቸው የጽ/ቤት ሓላፊው በጥቃቅን ጉቦኝነትም ይታማሉ፡፡
 • የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ካህናትንና ሊቃውንትን ለማይወክሉ ሙሰኛ የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ተቃዋሚ ነን ባዮች ዕለቱኑ የተመቻቸላቸው የውይይት መርሐ ግብር፣ የለውጥ ማዕበል ለመፍጠር ለተዘጋጁት ብዙኃን አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያት ሊቃነ መናብርት፣ ካህናት፣ መምህራን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ ሰንበት ት/ቤቶችና ምእመናን ያልተመቻችበትና አድልዎ የተደረገበት ምክንያት፣ ከዚኹ የጽ/ቤት ሓላፊው የጥቅም ሰለባነትና ለተቃዋሚዎቹ ኅቡእ አመራር እንደሚሰጡ ከሚጠረጠሩት ንቡረ እድ ኤልያስ ተጽዕኖ የተለየ ባይኾንም ከተደጋጋሚ መግለጫዎች ባለፈ በተጨባጭ የመፈተኛ ጊዜው የተቃረበው የፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥ የማምጣት የተግባር ዝግጁነትና ቆራጥነትም ከጥያቄ የራቀ አይኾንም፡፡
 • የአደረጃጀትና አሠራር ሰነዱ የመጀመሪያ ዙር ጥናታዊ ውይይት ተሳታፊ የነበሩት ንቡረ እድ ኤልያስ ይፋ ባልኾነ የሥራ ድርሻ በአማካሪነት ስም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ተጠግተው እንደዛሬው ባለው የፓትርያርኩ መርሐ ግብርና በሚይዟቸው ወሳኝ አቋሞች ላይ ይፈጥሩታል የሚባለው አሉታዊ ተጽዕኖ ርግጥ ከኾነ፣ በጥናታዊ ውይይቱ ወቅት ስለአደረጃጀትና አሠራር ሰነዱ ከሰጡት ገንቢ ሐሳብ ጋራ የሚጋጭና የንቡረ እዱን መሠሪነት የሚያረጋግጥ ነው – ‹‹ዛሬ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን ነው፤ በሕይወቴ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ከትክክለኛ መፍትሔ ጋራ እንዲህ ተስማምቶ ሲቀርብ አይቼ አላውቅም፤ ማስተካከያ ቢኖር እንኳ ኢምንት ነው፤ ጥናቱን የሠሩት ባለሞያዎች ከተለያዩ ልምዶቻቸው ተነሥተው ቀምረውታል፤ በውይይት ጊዜ ማባከን የለብንም፤ ወደ ሥራ ገብተን ተግባራዊ ማድረግ አለብን፤ ጥናቱ መተግበር ያለበት በጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ነው፡፡››
 • ተቋማዊ ለውጥ አመራር ለቤተ ክህነታችን ወቅታዊና አንገብጋቢ ለመኾኑ በድርቡ ከተሠመረባቸው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ መግለጫዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል – ‹‹የፀረ ሙስና ዐቢይ ኮሚቴ፣ የአስተዳደር መሻሻል ዐቢይ ኮሚቴ፣ የፋይናንስ አያያዝ ዐቢይ ኮሚቴ የማቋቋም ሦስት መሠረታዊ ርምጃዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን ጤናማ ሒደት የሚወስኑ እጅግ አስፈላጊ ርምጃዎች ናቸው፡፡ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲኾን ቅዱስ ሲኖዶስ ቆራጥ ውሳኔ ሊሰጠበት ይገባል፡፡ ሥር ሰዶ የሚታየው አሳፋሪና አሳዛኝ ብልሹ አሠራር ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደምትወድቅ በግልጽ እየታየ ነው፡፡ እኛ በአመራር ላይ ያለነውን ሰዎች ይህ ብልሹ አስተዳደር እንደሚያስወቅሰንና እንደሚያስፈርድብን ልንገነዘብ ይገባል፡፡ ሥር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ቆራጥነትን ይጠይቃል፡፡ በአጭር ጊዜ የተፈለገውን ለውጥ ለማምጣት የሚያዳግት ቢኾንም የለውጡን መሠረት ግን በአስቸኳይ ማስቀመጥና አቅጣጫውን መቀየስ እጅግ አስፈላጊ መኾኑ ሊሠመርበት ይገባል፡፡›› /ግንቦት ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ መክፈቻ ከተናገሩት/፤ ‹‹በፋይናንስ አያያዝና በመልካም አስተዳደር ዙሪያም ይህ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥበብና ማስተዋል ያልተለየው፣ የማፍረስ ሳይኾን የመገንባት ግብ ያለው ራእይ አንግቦ ሥር ነቀል የኾነ ፍጹም የዕድገት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለውን አሠራር መቀየስ ይገባዋል፡፡›› /ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ መክፈቻ ከተናገሩት/
Advertisements

5 thoughts on “የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥን በመደገፍ ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የድጋፍ ስብሰባ ለመጪው ሳምንት ዐርብ ተላለፈ፤ የድጋፍ መግለጫ የኾነውን ስብሰባ በሦስት ምዕራፎች በመክፈል በከፍተኛ ዝግጅት ለማካሔድ ዝግጅቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል

 1. Anonymous January 5, 2014 at 2:53 pm Reply

  we know who the enemy is. Ato Teamru enough is enough. as you know know nothing about this church.and you are the ambassador of MK.
  dear brothers and sisters in Christ,
  please get an attention on this matter.

  • Anonymous January 5, 2014 at 4:52 pm Reply

   ውሻ መናፍቅ ዝም ብለህ ተቀመጥ

 2. Anonymous January 7, 2014 at 12:27 pm Reply

  what ever the case we want the change and it is a must. It is time for our fathers who truly serve God and us. May God be with our true fathers and pay to those who love money than our church. U get enough till now not only to urself but also to ur relatives and grand children.

 3. MK January 8, 2014 at 1:49 pm Reply

  Dear Hara Group, All have to know that our church is normally led by the holy sprite. what is first expected from anyone who want to serve the church I believe is spiritual life.
  Abatochahchen betekereseteyanen yemeruat be tehetena, beyewahenet new. Ahun yalew huneta gen Elehe yetemolabet, ke menefesawinet yelek alemawi tekemena keber yemitasebebet new. le manegnawem betekereseteyanen hulem Amlak yetebekatal.

 4. Anonymous January 8, 2014 at 2:40 pm Reply

  ማንም ከሜዳ እየተነሳ ቅን የቤተክርስትያን ልጆች የሚሰሩትን ሥራ ማደናቀፍ አይችልም ምድረ የመናፈቅ ስብስብ ከቤተክርስቲያን ራስ ላይ ተጠራርገው እስኪጠፉ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል ::እግዚአብሔር በክህነት ስም የተሰበሰቡ አፍቃሬ ወያኔ: መናፈቃንና የተሃድሶ አቀንቃኞችን ጠራርጎ ያፅዳልን ::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: