ሰበር ዜና – የአ/አ ገዳማትና አድባራት ሰበካ ጉባኤያት ሊቃነ መናብርት፣ ካህናት፣ ሰንበት ት/ቤቶችና ምእመናን የሀ/ስብከቱን የተቋማዊ ለውጥ ጥናት በመደገፍ ነገ እሑድ በ8፡00 ወደ መንበረ ፓትርያርኩ በሺዎች ሊተሙ ነው፤ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱ ጸድቆ እንዲተገበርና የሙሰኛ አስተዳዳሪዎችና ተቃዋሚ ነን ባዮች የሀብት ምንጭ እንዲመረመር ይጠይቃሉ

 • ‹‹ምእመናን የቤተ ክርስቲያን አባላት እንጂ አካላት አይደሉም›› ባዮቹና በተቃውሟቸው ‹‹መንግሥት እየደገፈን ነው›› ያሉት እነኃይሌ ኣብርሃ÷ ፓትርያርኩ ረዳታቸውን ‹‹እስከ ገና ድረስ ዘወር የማያደርጉ›› ከኾነ እንቅስቃሴያቸው ትጥቃዊ መልክ እንደሚኖረው በማስጠንቀቅ ዝተዋል – ‹‹ያኹኑ ሊቀ ጳጳስ የማን ረዳት ናቸው፤ የማኅበረ ቅዱሳን ናቸው ወይስ የቅዱስነትዎ? በሊቀ ጳጳሱ ፈረጅያ ሥር ተከተው ጀግና ሊቀ ጳጳስ በሠራው ሀ/ስብከት ቢሮ ተሰጥቷቸው እያረቀቁበት ስለኾነ እንዲወጡ ይደረግልን! ከአቅማችኹ በላይ ከኾነ አሳልፋችኹ ለመንግሥት ስጡ፤ ሄደን እኛ እናስለቅቀዋለን፤ ውጊያ ከመገባቱ በፊት ወረቀቱ ተቀዶ መመለስ አለበት፤ እነንቡረ እድ ኤልያስ እነአባ ሰረቀ ያርቅቁ፡፡ ታኅሣሥ ገና ላይ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ወደ ጅማቸው ብቻ ቢሄዱ፤ ይህን ከተማ አበጣብጠውታል፤ መንግሥትም ስለማይናገር ነው እንጂ እያዘነ ነው፤ ረዳትዎን ዘወር ያድርጉልን!››
 • በግፍና ነውር በተሞላው አስተዳደራቸው የተነሣ የወሊሶ ካህናትና ምእመናን ያባረሯቸው አቡነ ሳዊሮስ የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን ውሳኔ በመጋፋት ከተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎች ጋራ መቆማቸውን በይፋ አረጋግጠዋል – ‹‹በጣም ደስታ ተሰምቶኛል፤ እኔ በፊት ብቻዬን የኾንኩ ይመስለኝ ነበር፤ ግን ወደ ኋላ ከተመለሳችኁ እናንተ ናችኹ የምትመቱት፤ ቀደም ሲል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በነበሩ ሰዓት መልካም አባት ነበሩና ሲዋጉ ሲያደባድቡ የነበሩ ሰዎች እነርሱ ናቸው፤ ቅዱስ አባታችን በነርሱ ነው ተቃጥለው የሞቱት፤ እናንተ ያልተናገራችኹት ነገር የለም፤ ሙሉ ቀን ብትናገሩ ደስ ይላል፤ ንግግራችኹ ሁሉ ጥሩ ነው፤ ግን ሰዎቹ ምንድን ነው በአቋራጭ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተረክበው እንደፈለገ ሊያደርጉ ነበር፤ እናንተ ባትነቁ ኖሮ ባቋራጭ ሊረከቧት ነበር፤ ቤተ መንግሥቱንም ቤተ ክህነቱንም ተረክበው እኛን እንደ ውሻ እንጀራ ሊጥሉልን ነው፤ እንደዚህ ነው ዓላማቸው ብዙዎቻችን አልገባንም እንጂ፤ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን መልስ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህ ካልኾነ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንደሚሄድ ነው እያሳዩ ያሉት፤ ቅዱስ አባታችን፡፡ እና እንዳትመለሱ ነው አደራ የምላችኹ፡፡›› /አቡነ ሳዊሮስ የእነኃይሌን እብሪት በማሞጎስ በፓትርያርኩና በስምንት ሊቃነ ጳጳሳት ፊት ከተናገሩት/
 • ፓትርያርኩ ለአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱ ክንውን ከሰጡት አባታዊ መመሪያ በተፃራሪ በእነ ኃይሌ ኣብርሃ ለሚመራው የተቃዋሚ ነኝ ባይ ወሮበላ ስብስብ ፊት በመስጠት የሚያሳዩት የመደራደር ዝንባሌ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በተቋማዊ ለውጥ ኃይሎች ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል፤ ‹‹ተጠርቼ መጥቼ የእርስዎ ረዳት የኾንኩትና ደፋ ቀና የምለው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን ውሳኔና የቅዱስነትዎን መመሪያ ለማስከበር ነው፤ አቋምዎን በግልጽ ያሳውቁኝ!›› /ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ/
Advertisements

10 thoughts on “ሰበር ዜና – የአ/አ ገዳማትና አድባራት ሰበካ ጉባኤያት ሊቃነ መናብርት፣ ካህናት፣ ሰንበት ት/ቤቶችና ምእመናን የሀ/ስብከቱን የተቋማዊ ለውጥ ጥናት በመደገፍ ነገ እሑድ በ8፡00 ወደ መንበረ ፓትርያርኩ በሺዎች ሊተሙ ነው፤ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናቱ ጸድቆ እንዲተገበርና የሙሰኛ አስተዳዳሪዎችና ተቃዋሚ ነን ባዮች የሀብት ምንጭ እንዲመረመር ይጠይቃሉ

 1. Anonymous January 4, 2014 at 7:44 am Reply

  yigermal

 2. Habtemariam January 4, 2014 at 12:20 pm Reply

  ምንም እንኳ በአካል መገኘት ባንችልም እጅግ በጣም ብዙ ክርስቲያኖች የነጌውን ሰልፍና ዓላማውን የምንደግፍ አለነንና የፍትህ ንጉሥ እግዚአብሔር ነጌ ሰልፉን በእውነተኛ መንፈሳዊ ቅንዐት ከሚቀላቀሉ እውነተኛ ምዕመናን ጋር እንዲሆን እንጸልያለን፡፡

 3. Bahiru Bekele Shewa January 4, 2014 at 3:08 pm Reply

  “በግፍና ነውር በተሞላው አስተዳደራቸው የተነሣ የወሊሶ ካህናትና ምእመናን ያባረሯቸው አቡነ ሳዊሮስ …”
  መጠጊያ ፍለጋ ይሆን ?
  እውነተኛ መነኩሴ‘ኮ በተገፋ ቁጥር በእልህና ቁጣ ወይም በማን አለብኝነት፣ በትዕቢት ድንፋታ በየቦታው ሲያቅራሩ አላየንም፡፡ አልሰማንም፡፡ አላነበብንም፡፡ የምር አለማዊነቱና ቅሰጣው ቀርቶባቸው እንደቀደሙት አባቶች ምናለ ወደ አንዱ ገዳም መንነው ባየናቸውና፡፡ የደብረ ሊባኖሷ ውሻ ገደል ነዋሪዎች እውነተኛና ንፁህ አባት መሆናቸውን ሲረዱ እያነቡ “…አባ ፊሊጶስን ወዴት አሉ?…” እያሉ በየ በረሃው ተንከራተው ያገኟቸው ተንቤንም አይደል? ይህ መቸም ለአባ ሳዊሮስና አድናቂ ደጋፊዎቻቸው ተረት ነው፡፡እኛስ . . . በየአደባባዩ የሚያወሩት፣ የሚደሰኩሩት ሁሉ እውነት ሆኖ አሁን ተገፍተው በታደልንና አባ ሳዊሮስ ማረን ያልከው ለካ እውነት ነበር ለካስ ባልንና ባነባን፡፡ ብለን ብንመኝስ? ኪኪኪኪኪኪኪ….
  እግዚአብሄር ቤክርስቲያናችንን እና ሃገራችን ኢትዮጵያን የጠብቅ ይባርክልንም አሜን፡፡

  • Anonymous January 4, 2014 at 11:43 pm Reply

   መልካም ብልሃል ወዳጄ እግዚአብሄር ቤክርስቲያናችንን እና ሃገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅ ይባርክልንም አሜን፡፡

 4. Bahiru Bekele Shewa January 4, 2014 at 3:35 pm Reply

  “…ከአቅማችኹ በላይ ከኾነ አሳልፋችኹ ለመንግሥት ስጡ፤…” ብሎ. . . “…ሄደን እኛ እናስለቅቀዋለን…”
  ማለት ምን ማለት ነው ? ወይስ መንግታዊያኑም እነሱ ናቸው? ነው ወይስ . . . ወዴት ጠጋ. . . ጠጋ? ፡፡ እንዳለፈው ሰሞን ታጥቀናል ለማለት ነው ? “እኛም ቤት እሳት አለ፡፡” አለ ያገሬ ሰው፡፡
  ቤተክርስቲያን በእግዚአብሄር ሃይል እስከ አፍንጫው የታጠቀ እልፍ አእላፍት ጭፍሮች እንዳሏት ተስፋ እንደቆረጡና እንደነቃንባቸው ንገሩልን እባካችሁ ?

  • Anonymous January 4, 2014 at 11:41 pm Reply

   መልካም ብለሃል ወዳጄ
   እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ሰላምን ይስጠን ::

 5. sofonias eshetu January 4, 2014 at 3:53 pm Reply

  we will meet tomorrow on time please

 6. Dave January 4, 2014 at 4:41 pm Reply

  ኣንድ ቤት ውስጥ ኣይጦችና ድመቶች ኣሉ፥፥ ድመቶቹ ቤቱ እንዲጸዳ ይተጋሉ፥፥ ኣይጦቹ ግን ቤቱ እንዳይጸዳ ሌት ተቀን ይሽለኮለካሉ፥ ድመትም ኣርፋ አንድትቀመጥ ኣለበለዚያ፤ ኣንበሳ ወዳጃችን ነው አያሉ ያስፈራራሉ፤፤ ኣይጦች ቤቱ ቆሽሾ ለእንግዳም ሆነ ለቤቱ ኣባል ቢያጸይፍ ግድ የለቸውም፥ ምክንያቱም እዚህም እዚያም የሚረቃቅሙት እና የሚለክፉት እስካገኙ ድረስ፤፤

  (ኣይጦች=ሙሰኛ ኣስተዳዳሪዎች ፤፤ አንበሳ= መንግስት)

 7. Anonymous January 4, 2014 at 4:46 pm Reply

  wishing you good luck. we will see tomorrow . just wait the true will be revealed . our church will never be the sours of MK

 8. Anonymous January 6, 2014 at 7:50 pm Reply

  ሐራዎች በለውጥ መዋቅሩ ዙሪያ መዋቅሩ ተቀባይነት እንዲያገኝ እየሠራችሁ ያላችሁትን ያህል የአባ እስጢፋኖስንና የሹመኞቻቸውን ሙሰኛነት ለመጥቀስ እንኳ ያልደፈራችሁበት ምክንያቱ ምን ይሆን? መዋቅሩ ለካህናቱ ተሰጥቶ ቢወያዩበትና ካመኑበት ቢቀበሉ መልካም ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን አቡነ እስጢፋኖስ በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው የሚገኙ ሰው መሆናቸውን ግን ማስተባበል አይቻልም፡፡ ስለዚህ ታማኝ መሆናችሁ እንዲረጋገጥና ለቤተክርስቲያን ከቆማችሁ የአባ እስጢፋኖስን ሙሰኛነት አጋልጡ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: