የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ካህናቱንና ምእመናኑን እያነጋገረ ነው

 • ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዲያገልግሉ ብቻ ሳይሆን በትምህርትና በተግባራዊ ልምምድ ለከፍተኛ ክብርና ማዕርግ እንዲበቁም ትሠራለች
 • ገዳማት እና አድባራት የልማት ፈንድ ያቋቁማሉ

/ምንጭ፡- ኢትዮ – ምኅዳር፤ ቅጽ 02 ቁጥር 51፤ ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 23 ቀን 2006 ዓ.ም./

Addis Abeba diosces facebook profile picበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን ለሀ/ስብከቱ ባለድርሻ አካላት ለውይይት ያቀረበው የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነድ ካህናቱንና ምእመናኑን እያነጋገረ ነው፡፡ የጥናት ሰነዱን እንደማይቀበሉት የሚገልጹ ወገኖች፡- ‹‹ጥናቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያልተሳተፉበትና በውይይት ያልዳበረ በመኾኑ በገለልተኛና ልምድ ባላቸው ምሁራን ይሰናዳ፤ ከነባሩ ሕገ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዐዋዲ ጋራ የሚጋጭና የሚጣረስ ነው፤›› ይላሉ፡፡

ጥናቱ ‹‹ነባሩን ሠራተኛ በማፈናቀል በስመ ዲግሪና ዲፕሎማ ዕውቀት የሌለውን በመዋቅሩ ውስጥ በመሰግሰግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር ያለመ ነው፤›› የሚሉት እኒሁ ወገኖች፣ ‹‹የአጥኚው አካል ማንነት በግልጽ አይታወቅም፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ሥልጣን ያለውን የፓትርያርኩን ሥልጣን ይጋፋል፤›› የሚሉ ተቃውሞዎችን በመዘርዘር አቤቱታቸውን ለፓትርያርኩና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አቅርበዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ በአደረጃጀትና አሠራር ትግበራው በሚመጣው ለውጥ ተጠቃሚ የኾኑትን ካህናትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደማይወክሉ ለኢትዮ – ምኅዳር የተናገሩ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች በበኩላቸው፣ የተጀመረው የለውጥ ሒደት በሐቅ ላይ ባልተመሠረተ፣ ቅንነት በጎደለውና ደረጃውን ባልጠበቀ የአቋም መግለጫ ወደኋላ እንደማይመለስ በመግለጽ ተቃውሞውን አስተባብለዋል፡፡

የጥናቱ መነሻ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በመልካም አስተዳደር፣ በፋይናንስ አያያዝና በሰው ኃይል አመዳደብ የሕግ የበላይነትን አክብሮ እንዲሠራ የተሰጠው ውሳኔ መኾኑን ሓላፊዎቹ አስታውሰዋል፤ጥናቱን ያካሄደው የባለሞያ ቡድንም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በኾኑት አቡነ እስጢፋኖስ መዋቀሩንና ሥራውን ከመጀመሩ በፊትም በፓትርያርኩ ፊት ቀርቦ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አልፎ ለሌሎች አህጉረ ስብከትም የሚያገልግል የአሠራር ጥናት በማድረግ አደረጃጀቶችንና መመሪያዎችን እንዲያዘጋጅ አባታዊ መመሪያ መቀበሉን ገልጸዋል፡፡

His Holiness meglecha 11

‹‹ጥናቱን ለአዲስ አበባ ብቻ ሳይኾን ለሁሉም አህጉረ ስብከት እንዲኾን አድርጋችኹ አቅርቡ››
(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ለባለሞያዎች ከሰጡት አባታዊ መመሪያ)
‹‹የአደረጃጀትና አሠራር ሰነዱን ለትግበራ እንዲያመቻችኹ አጥኑት፤ ለውጡ ወደኋላ አይመለስም››
(ቅዱስነታቸው ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ለጥናታዊ ውይይት ተሳታፊዎች ከሰጡት ቃለ ምዕዳን)

ሀገረ ስብከቱ በአንድ ሀገረ ስብከትና በአንድ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ በሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ከተወሰነ በኋላ ከሐምሌ 2005 ዓ.ም. እስከ መስከረም 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ለሦስት ወራት የተመራበትንና ቋሚ ሲኖዶስ ያጸደቀውን ጊዜያዊ መዋቅር የሠራው የባለሞያ ቡድኑ፣ በፓትርያርኩ አባታዊ መመሪያ ላይ ተመሥርቶ በረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው የቅርብ ክትትል እየተደረገለት በቀጣይ ባከናወነው ጥናት÷ ክህነታዊ አገልግሎትንና ስብከተ ወንጌልን ማዕከል ያደረገ፣ ወጥነት ያለው የሰው ሀብት አስተዳደርና ዘመኑን የዋጀ የፋይናንስ አሠራር ለመዘርጋትና በልማት ራስን ለመቻል የሚያበቃ 13 ጥራዞች ያሉት ሀገረ ስብከት አቀፍ መዋቅርና አደረጃጀት ሰነድ አርቅቆ ጥቅምት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ለሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ ማቅረቡ ተገልጦአል፡፡

ጥናቱ በባለሞያ ቡድኑ ገለጻ ታግዞ በስላይድ የቀረበለት የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ሰነዱ ወደ ታች ወርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ዳብሮ በሚገባ ተጠንቶና ተስተካክሎ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብና ቋሚ ሲኖዶሱም ዐይቶና ተመልክቶ በሥራ ላይ እንዲያውለው ይኹንታና የአፈጻጸም አቅጣጫ እንደሰጠበት ተጠቅሷል፡፡

በዚህም መሠረት ቁጥራቸው ከ2700 በላይ የኾኑ የሀ/ስብከቱ የአስተዳደር ሓላፊዎች፣ የሰባት ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሥራ መሪዎች፣ የ169 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የአስተዳደር ሠራተኞች፣ የካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤቶችና ምእመናን ተወካዮች ከኅዳር 17 – ታኅሣሥ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. በተለያዩ ዙሮች በንቃት እንደተወያዩበት ሓላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡ የውይይት መድረኮቹ፣ ‹‹ጥናቱ በይዘቱ እንዲዳብርና በአቀራረቡ እንዲስተካከል ግብአት የሚኾኑ ትችቶችና አስተያየቶች የተገኙበት አሳታፊ ብቻ ሳይሆን ሳይዘገይ ጸድቆ እንዲተገበር ብዙኃኑ አገልጋይና ሠራተኛ በአማካይ እስከ 96 በመቶ ድጋፍ በመስጠት ግፊት ያደረገበትም ነበር፤›› ብለዋል፡፡

his grace abune estifanos

‹‹ጥናቱን ቀን ከሌት ሠርተው ከዚኽ ላደረሱት ኹሉ÷ የእያንዳንዳችኹን ዋጋ አምላከ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ይሰጣችኋል፡፡ በ1500 ገጽ ላይ የኹላችኁም ስማችኹ ተጽፏል፡፡ ሰው ዛሬ ቢያመሰግን ነገ ሌላ የሚል ነውና በአንደበታችኹ ስንነቀፍ ደስ ይለናል እንዳላችኹት በልባችኁም ደስ ይበላችኹ፡፡ በጥናቱ ደስ ያላላቸው ካሉ በአስተሳሰብ ልዩነት ሊኾን ይችላል፤ ሳይገባቸው ቀርቶም ሊኾን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር፣ ይህ ኹሉ ጩኸት ለቤተ ክርስቲያን ካልኾነ ለምን ሲባል ኖሯል? እኔስ ብኾን ከዐሥር ዓመት በላይ የደከምኹበት ሀ/ስብከት እያለ እዚህ ምን አደርጋለኹ? ሙሉ ቀን እዚኽ የምቆመው ምን ለማግኘት ነው? በእውነት እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው ነው የምለው፡፡
እንደ ጨለማው ዘመን፣ እንደ ወርቃማው ዘመን ኹሉ ይህም የእኛም ዘመን በወደፊቱ ትውልድ ስም ይወጣለታል፡፡ ዘመኑን ሳንሠራበት ካለፍን በነፍስም በሥጋም እንጎዳለን፤ ዐፅማችን እንኳ አያርፍም፡፡ አሁን ስማቸውን እየጠራን ያለነው በዘመናቸው ገድላቸውን ፈጽመው ያለፉ አባቶቻችንን ነው፡፡ እኛ የተቀመጥነው በእኒህ በዘመናቸው ሥራ ሠርተው ባለፉት አባቶቻችን ወንበር ነውና ከባድ አደራ ነው ያለብን፡፡
ዛሬ ለችግራችን መፍትሔ ይምጣ በሚባልበት ጊዜ መድኃኒት እንደገባበት ባሕር የምንገላበጠው ለምንድን ነው? በስታቲስትክሱ ሌሎች በስንት ነው ያደጉት? በየክልሉ የእኛ በምን ያህል ቀነሰ? በሕዝብ ቆጠራውኮ በትልቁ ጎድለን የተገኘነው ስንት ሊቃውንት አሉ በተባለበት በአዲስ አበባ ነው፡፡ ይኼን ሁሉ ምእመን ባጣንበት አዲስ አበባ ሊቅ ነኝ ማለት በራሱ ያሳፍራል፡፡ ቀጣይ ቆጠራ ይካሄዳል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያስወረሩት፣ ምእመኑን ያስነጠቁት በዚህ ዘመን የነበሩ አባቶች ናቸው ተብለን በመቃብር እንኳ ዐፅማችን አያርፍም፡፡ አሁን በተመቻቸ ሜዳ ላይ ነው ያለነውና ልናስተውል ይገባል፡፡ እኛ ሰላም ኾነን፣ ፍቅር ኾነን ምእመኑን ስንመራው በእምነቱ ኮርቶ አንገቱን ቀና አድርጎ ይራመዳል፡፡
አባቶች፣ እባካችኁ ማስተዋል ይኑረን፤ እኛ ርስ በርስ ስንነቃቀፍ ስንት ሰው ይሄዳል መሰላችኁ? ለምን አንመካከርም? ማንምኮ ፍጹም የለም፤ እንዴ! ለቤተ ክርስቲያናችንኮ ጠላት የኾናት እኛው ነን፡፡ አሁንም በገዳማቱ ቅዱሳን አልጠፉም፡፡ አባቶቻችን ይህችን ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ከነዘርፈ ብዙ ሀብቷ ያስረከቡን ደመወዝ የሚያስብላቸው ሳይኖር አንጀታቸውን በጠፍር አስረው እያረሱ፣ ቅባ ኑግ እያበሩ ቀድሰው ነውና ዐፅማቸው ይወቅሰናል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድናት፤ እኛም እንዳን፡፡››
/በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ለየዙሩ የጥናታዊ ውይይት ተሳታፊ ገዳማትና አድባራት ልኡካን የሰጡት ቃለ ምዕዳን/

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑም ይኹን በቃለ ዐዋዲ ደንቡ፣ የሁሉም አህጉረ ስብከት ማዕከል የኾነው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው ልዩ ደንብና መመሪያ እንደሚተዳደር መደንገጉን የጠቀሱት ሓላፊዎቹ የጥናት ሰነዱን በሲኖዶሱ አባላት እየታየ ከሚገኘው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ጋራም ለማገናዘብ ጥረት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህም ኹሉ አኳያ የቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻ ወሳኝ አካል የኾነው ሲኖዶሱ በምልአተ ጉባኤ ስብሰባው ባስተላለፈው ውሳኔና የውሳኔው አስፈጻሚ የኾኑት ፓትርያርኩ በሰጡት መመሪያ መሠረት÷ ዕውቅና ባለው፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች በተውጣጣና ቤተ ክርስቲያኒቱን በጥልቀት በሚያውቅ የባለሞያ ቡድን አዲስ የአደረጃጀትና የአሠራር ጥናት ሰነድ መዘጋጀቱ የሚጥሰው ሕግና ደንብ የለም በማለት የሕግና ደንብ ጥሰት እንዳለ የተሰነዘረውን ተቃውሞ ተከራክረዋል፡፡

የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጡ ‹‹ነባሩን ሠራተኛ በማፈናቀል በስመ ዲግሪና ዲፕሎማ ዕውቀት የሌለውን በመዋቅሩ ውስጥ በመሰግሰግ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር ያለመ ነው፤›› ስለሚለው ተቃውሞ ኢትዮ – ምኅዳር የጠየቃቸው የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎች÷ ‹‹በጥናቱ የሀ/ስብከቱ የመዋቅር፣ አደረጃጀትና አሠራር ችግሮች መነሻ ተደርገዋል፤ ዋና ተልዕኮውና መሠረታዊ ተልዕኮውን የሚደግፉ ተግባራት በዝርዝር ተለይተዋል፤ መዋቅሩ ከዚህ አንጻር ያሠራል ወይስ አያሠራም በሚል አመቺነቱና እንከኑ ተገምግሞ በስምምነት የሚወሰን ነው፤›› ብለዋል፡፡

በሰነዱ የሚታየው ተቋማዊ መዋቅር የመጨረሻ መልክ ከመያዙ በፊት ብዙ አማራጮች እየቀረቡ መፈተሹን ያስረዱት ሓላፊዎቹ ለውይይት የቀረበው መዋቅር የቤተ ክርስቲያናችን ዋነኛ ተልዕኮ የኾነው ሐዋርያ አገልግሎትዋ እየሰፋ እንዲሄድ፣ የተሻለ የልማት ዕድል ተፈጥሮ የበለጠ ገቢ በማግኘት ሐዋርያዊ አገልግሎትዋን ለማስፋፋትና ለማጠናከር እንዲቻል የተመቻቸበት በመኾኑ ከፍተኛ የአገልጋይ ቁጥር ለማቀፍ እንደሚያበቃ የተናገሩት ሓላፊዎቹ÷ ያለውን አገልጋይ በሥልጠና የማብቃት፣ በትምህርት ራሱን እንዲያሳድግ የማበረታታት፣ የመደልደልና የማሸጋሸግ ሥራ ይሠራል እንጂ ትርፍ ነው ተብሎ የሚፈናቀል ሰው አይኖርም ብለዋል፡፡

ሀ/ስብከቱ በጥቅምት ወር መጨረሻ ባካሄደው የሦስት ወራት የጊዜያዊ መዋቅሩ አፈጻጸም ግምገማ በየገዳማቱና አድባራቱ ካለው ከፍተኛ የሰው ኃይል ክምችት አንጻር በተለያየ ምክንያት ከሥራ ተፈናቅለው ካልተመደቡ ሠራተኞች በስተቀር ላልተወሰነ ጊዜ የአዲስ ሠራተኛ ቅጥር እንዲቆም መወሰኑም በሥራ ላይ ያለውን አገልጋይ ሰፊ የሥራ ዕድል በሚፈጥረው በአዲሱ ተቋማዊ መዋቅር አደረጃጀትና የሥራ መደብ ዝርዝር መሠረት በመለስተኛ ሥልጠና ጭምር እያበቁ ለመደልደል ምቹ ኹኔታ ይፈጥራል የሚል እምነት እንዳለ ሓላፊዎቹ በምላሻቸው ጠቅሰዋል፡፡

የሀ/ስብከቱ ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በአገልግሎት ስፋትና በልማት አቅም እርስ በርስ እየተወዳደሩ ወደ ደረጃ አንድ የሚያድጉበት አምስት ደረጃዎችና ደረጃዎቹ የሚለዩባቸው መመዘኛዎች መዘጋጀታቸው ተገልጧል፤ አምስቱም ደረጃዎች የየራሳቸው መዋቅር፣ በሞያና በቁጥር የተለያየ የሰው ኃይል ምደባና የደመወዝ ስኬል ያላቸው ሲኾን ቤተ ክርስቲያኑ እንደሚገኝበት ደረጃና እንደሚሰጠው የአገልግሎት ስፋት የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ትመና የቤተ ክህነቱን ትምህርት ከዘመናዊው ትምህርት ጋራ በአቻ ንጽጽር በመመዘን ተገቢው ትኩረትና ደረጃ እንዲሰጠው ተደርጎ መሠራቱም ተመልክቷል፡፡

‹‹የሰው ኃይል ትመናው÷ ሥራና ሠራተኛ በማገናኘት የሥራን ጥራት ከማሳደግ አንጻር የአገልጋዩ ዝቅተኛ የትምህርት፣ የሥራ ልምድና የክሂሎት ዝግጅት የታየበት ነው፤ የደመወዝ ስኬል ጥናቱ÷ ከቢሮ ሥራ ይልቅ ለካህናቱ የቤተ መቅደስ አገልግሎት ቅድሚያ በመስጠት የካህናቱን ኑሮ ለማሻሻል፣ ሊቃውንቱ ትኩረት አግኝተው ተተኪ ለማፍራት እንዲችሉ በልዩ ኹኔታ የሚበረታቱበት ነው፤›› ይላሉ ለኢትዮ – ምኅዳር አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የባለሞያ ቡድኑ አባል፡፡

ባለሞያው አያይዘውም ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንዲያገልግሉ ብቻ ሳይሆን በትምህርትና በተግባራዊ ልምምድ ለከፍተኛ ክብርም እንዲበቁ እንደምትሠራ ገልጸዋል፤ ከዚህም አንጻር ልዩ ተሰጥኦና ላቅ ያለ ችሎታ ያላቸው አገልጋዮች ወደ ታችና ወደ ጎን ለተሻለ ዕድል የሚበቁበትና የሚበረታቱበት የደረጃ ዕድገት፣ የዝውውርና ሹመት፣ የክፍያና ምዘና፣ የጤና ክብካቤ ሽፋንና የጡረታ ዋስትና ሥርዐት የሚወሰንበት የአገልጋዮች ማስተዳደርያ ፖሊሲ፣ መመሪያና ዕቅድ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ለየዘርፉ የተጠኑት የሥራ ማኑዋሎች መለስተኛ ክሂል (semi-skilled) ያለው አገልጋይ በቀላል ሥልጠና ሊተገብራቸው የሚችላቸው ናቸው፤›› ያሉት ባለሞያው፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ የለውጥ አመራር ዕቅድና በአገልጋዩ አቅም መካከል የሚታዩ ክፍተቶች በየጊዜው እየተለዩ የሚሞሉባቸው የአቅም ግንባታዎች(የሥልጠና) ዐይነቶች ከማስፈጸሚያ መመሪያው ጋራ በሥልጠናና የሰው ሀብት ልማት ፖሊሲው በዝርዝር መቀመጣቸውን አብራርተዋል፡፡

የገዳማትና አድባራት የልማት ፈንድ

በተያያዘ ዜና÷ የሀ/ስብከቱ ገዳማትና አድባራት ልማትን በማስፋፋት ሐዋርያዊ አገልግሎትን በዘላቂነት ለማከናወን የሚያስችል ሀብትና ንብረት የሚያፈሩበት የልማት ፈንድ ሊያቋቁሙ መኾኑን የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በሰበካ ጉባኤ ከሚሰበስቡት አስተዋፅኦ ጋራ በልማት መስኮች ለሚያገኙት ገቢ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን ለኢትዮ ምኅዳር ያስታወቁት የሀ/ስብከቱ ምንጮች÷ ገዳማትና አድባራት በአንድ የበጀት ዓመት መጨረሻ ለመደበኛ አገልግሎት ከሚመደበው በጀትና መጠባበቂያው ከሚተርፈው ገንዘብ ስድሳ በመቶውን (60%) የልማት ፈንድ እንዲያቋቁሙበት የሚያስችል ጥናት በሀገረ ስብከቱ የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ ረቂቅ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡

እንደምንጮቹ ገለጻ በጥናቱ መሠረት፣ ሀገረ ስብከቱና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ካለው የተጣራ የባንክ ሒሳብ ተቀማጭ ገንዘብና የአጭር ጊዜ ተሰብሳቢ ገንዘብ ውስጥ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት መደበኛ ወጭዎችን ለመሸፈን የሚያስፈልገውን ገንዘብ መጠባበቂያ አድርገው ካስቀመጡ በኋላ ከሚተርፈው ዓመታዊ ቀሪ ገንዘብ ውስጥ ስድሳ በመቶውን የልማት ፈንድ እንዲያቋቁሙበት ታስቧል፡፡

የልማት ፈንዱ÷ የልማት ተቋማትን በማቋቋምና በማስፋፋት የካህናትንና ሊቃውንትን የኑሮ ኹኔታ የማሻሻልና አብያተ ክርስቲያናቱን ከልመና የማውጣት፣ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን በዘላቂነት ከመደገፍ ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የምግባረ ሠናይ ድርጅቶች በቋሚ የገንዘብ ምንጭነት በማገልገል የምግባረ ሠናይ ተግባራትን በስፋት የማከናወን በአጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋነኛ ተልእኮ የኾነውን ሐዋርያዊ አገልግሎት በከተማና በገጠር የማስፋፋትና የማጠናከር አስፈላጊነት እንዳለው የሀ/ስብከቱ ሌላው የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ሰነድ አካል የኾነው የልማት ሥራዎችና የምግባረ ሠናይ ተግባራት ፖሊሲና መመሪያ ረቂቅ ያስረዳል፡፡

ፖሊሲው ለልማት ተቋማቱ ባስቀመጣቸው መርሖዎች መሠረት÷ በተቋማቱ ምሥረታና ማስፋፋት ወቅት ለቤተ ክርስቲያን ምስጢራዊ አገልግሎት እንደ ግብዓት የሚያገልግሉ ዕቃዎችን ለማምረትና ለማከፋፈል ቅድሚያ መሰጠት ይገባዋል፡፡ ተቋማቱ የሚያመርቷቸውና የሚያከፋፍሏቸው ንዋያተ ቅድሳት፣ የኅትመት ውጤቶች፣ የምስል ወድምፅ ሥራዎችና የመሳሰሉት ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማና ሥርዐት፣ ከማኅበረሰቡ ኢትዮጵያዊ ማንነትና ትውፊት አንጻር ታሳቢ መደረጋቸው መፈተሽና መረጋገጥ እንደሚኖርበትም ተመልክቷል፡፡

ፖሊሲው ‹‹የተፈቀዱ›› የሚላቸው የልማት ተቋማት ለብዝኃ ሕይወት አዎንታዊ አስተዋፅኦ ሊኖራቸው እንደሚገባ፣ በዕውቀቱ የበለጸገ፣ በሥነ ምግባሩ የታነጸ ትውልድ ለማፍራት ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንደሚያስፈልጋቸው በመርሖው አስቀምጧል፡፡ ከተቋማቱ ዝርዝር ውስጥም፡- ኮሌጆችና ማሠልጠኛዎች፣ ማተሚያ ቤቶች፣ የጉዞና አስጎብኚ ድርጅት በማቋቋም የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት መስጠት፣ ክሊኒኮችንና ፋርማሲዎችን በማቋቋም የሕክምና አገልግሎት መስጠትና መድኃኒቶችን ማከፋፈል፣ የግንባታ ቁሳቁሶችን ማቅረብ፣ ለአገልግሎትና ኪራይ የሚውሉ ሕንጻዎችን መገንባትና ማከራየት፣ ከውጭ የሚገቡ ንዋያተ ቅድሳትን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የውጭ ምንዛሬ ማዳንና ሥርዐትና ትውፊት የጠበቁ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት፣ የግብርና ውጤቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ፣ የፋይናንስ ተቋም አክስዮን፣ የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድና ቦንድ መግዛት የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

ገዳማትና አድባራት በራሳቸው አልያም በመቀናጀት ተቋማቱን መመሥረት እንደሚችሉ በመርሖው የተገለጸ ሲኾን ቅንጅቱም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያኒቱ ከሌሎች አጥቢያዎች ጋራ፣ አጥቢያዎች ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጋራ እንዲሁም ሀ/ስብከቱና አጥቢያዎቹ ከሌሎች አህጉረ ስብከትና አጥቢያዎቻቸው ጋራ ሊከናወን የሚችልበት የፕሮጀክት አጸዳደቅና አተገባበር ሥርዐት መካተቱ ተገልጧል፡፡ የልማት ተቋማቱ የሚተዳደሩት በቦርድ ሲኾን የቦርዱ ተጠሪነትም ላቋቋማቸው አካል (በአጥቢያ ደረጃ ከኾነ ለአጥቢያው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ) እንደኾነ ታውቋል፡፡

በልማት ፈንዱ የሚቋቋሙና የሚስፋፉ ተቋማት፣ ካህናትና ሊቃውንት ከመደበኛ ተግባራቸው  በተጨማሪ እንደየዝንባሌያቸው በተለያዩ ክሂሎች እየሠለጠኑ እንዲሠማሩ በማስቻል የሥራ ዕድል እንደሚፈጠሩላቸው፣ በአገልግሎታቸውም እንዲበረቱ ተገቢውን በማሟላት አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉላቸው ታምኖባቸዋል፡፡ የልማት ተቋማቱ ወደፊት ሀገረ ስብከቱ ከምእመናን አሰፋፈር አኳያ እንደአስፈላጊነታቸው እያየ ከሚተክላቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጋራም አንጻራዊ መስፋፋት እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በቁጥር 169 ለሚደርሱት የመዲናዪቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሰራጨው ቅጽ እየሰበሰበው የሚገኘው የአገልጋዮች ጠቅላላ መረጃ÷ ገዳማቱና አድባራቱ ልዩ ልዩ ክህሎት ያላቸው አገልጋዮች እንዳሉባቸው በምንጮቹ መረጃ ተመልክቷል፡፡ ይህም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በየደረጃቸው ከተዘረጋላቸው ተቋማዊ መዋቅርና አደረጃጀት አኳያ የተሠራላቸው የሥራ መደቦች መዘርዝር መንፈሳዊ ዕውቀትን ከዘመናዊው ሞያ ጋራ በአቻ ንጽጽር በማስቀመጥ ከሚያቅፈው በርካታ የሰው ኃይል በተጨማሪ በሒደት አገልጋዮችን በብዛት ለማፍራትና ለማሰማራት ያስችላል የሚል እምነት እንደተጣለበት ተዘግቧል፡፡

Advertisements

23 thoughts on “የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት ካህናቱንና ምእመናኑን እያነጋገረ ነው

 1. በአማን ነጸረ December 31, 2013 at 2:42 pm Reply

  ይቅርታ!!!በ3 ወር ያውም በትርፍ ጊዜ በተሰራ ስራ 1ሺህ ገጽ ያለው ጥናት ተሰራ የሚል ፕሮፖጋንዳ ለማመን ይከብደኛል!!!እንኩዋን ጥናትን ያህል ነገር ዝምብሎ ስድ ጽሁፍ ቢጻፍም በ3 ወራት ብቻ 1ሺህ ገጽ ማድረስ የሚቻል አይመስለኝም!!
  ቀድሞ ተዘጋጅቶ ነበር!!ልክ አቡነ ጳውሎስ ሲያልፉ ከማህበረ ቅዱሳን መሳቢያ ውስጥ ተመዘዘ!!!እንደ ቁራን ከሰማይ ወረደ ካላላችሁን በቀር ሀቁ ይኸው ነው!!

  • Kinfe silase December 31, 2013 at 6:19 pm Reply

   wanaw 90% yebetekristiyan lijoch tesmamitewal, 10% endant yalu silehone bizum aydenkim! Le andand tikimegnoch yebetekristiyan lewut lemin endemayasdesitachew aygbagnim. Le negeru mahibere kidusan yekdusan mesebsebiya silehone leboch aywodutim, ewunet enezih 90% tinatun yetekebelut mahibere kidusan nachew ketebale 90% Orthodox mahibere kidusan nachew malet new. Zilezih ye bizuhanu yawatalina saymeshibih tekelakel!

 2. Habtemariam December 31, 2013 at 3:06 pm Reply

  ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡ የተጀመረው ለዘመናት ስንናፍቀው የነበረው አሰራር ከዳር ደርሶ እንድናይ እግዚአብሔር በዚህ ሥራ ውስጥ የያሉትን ሁሉ ያበርታነን፡፡ አሜን

 3. Anonymous December 31, 2013 at 4:24 pm Reply

  ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡ የተጀመረው ለዘመናት ስንናፍቀው የነበረው አሰራር ከዳር ደርሶ እንድናይ እግዚአብሔር በዚህ ሥራ ውስጥ የያሉትን ሁሉ ያበርታነን፡፡ አሜን
  Please make it your next task to do the same for the All Africa Diocese – administered by Abuna Yacob . We kept quiet for quite sometime now hoping that the Addis Synod would do something about it after hearing our grievances aired on the same web some months ago. Please send delegation to hear even more shocking news about the Diocese.

 4. SISAY TEKLAY December 31, 2013 at 4:49 pm Reply

  ከዳር እንዲደርስ የሁላችንም ፀሎት ያስፈልጋል።

 5. Weldegebriel December 31, 2013 at 4:57 pm Reply

  ቤተ ክርስትያን ካላት የስንት ዘመን እምነትና እውቀት ይህን የመሰለ የኣሰራር ሰንሰለት ለማቅረብ እንዲያውም ዘገየች፣ የኛ ተራ በስሩ ሁነን ኣክብረን እንድንጠቀምበት ነው።
  ኣማረ ነጸረ የሊቃውንቱ ክህሎት ማስተዋል ኣልቻልክም፣ በቃላቸው እየጠቀሱ የሚያስታውሱ ሊቃውንት ሦስት ወር ሲበዛባቸው ነው፣ ችግሩ ከኛ ጋር ያደገ ያየነው ያሰለቸን ሰለሆነ፣ መፍትሄው ለመሻት ምንም መከራከርም ኣያስፈልገውም። የውጪው ኣካል ኣሁን ይቅር ብሎ ተቀብሎ እንደ ለንደኑ ሰላም ማስቀደም ኣለባቸው። እናት ቤተ ክርስትያን ኣንዲት እስዋ ባቻ ነች፣ ኣማራጭ ኣልነበራትም ኣይኖራትም መከለስ ካልሆነ በስቀር። የነ ኢዛና ካለብ ቅዱስ ያሬድ።።።። ሃገር ተከብራ ትኑር።
  ወልደገብርኤል

 6. Anonymous December 31, 2013 at 5:38 pm Reply

  ወደድንም ጠላንም መዋቅሩ በምእመናን እና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶቸና ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ በኾኑ ካህናት መስዋዕትነት ይተገበራል፤ ሙስና…ግን….;;;;;;;;;////;;;;;;;;;

 7. Alem Mq December 31, 2013 at 5:51 pm Reply

  I think whether it’s from heaven or earth, if we found its inline with the cannon and valuable enough to the church we should use it. And if we see some of the contents, they are not so special that require years to prepare, what the church has to do are clearly known by default and already in the hearts and dreams of even ordinary people (non-professionals). so, its not hard to prepare such a plan in short period.

  For example, የጉዞና አስጎብኚ ድርጅት በማቋቋም የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት መስጠት. Didn’t you dream this before when you see huge tourist attractions that the church has? I always do.

  Let God help us!

 8. Anonymous December 31, 2013 at 7:43 pm Reply

  በአማን ነፀረ፣ ችግርህ ከጥናቱ ነው ወይስ ከአጥኝው ነው ወይስ ከገጽ ብዛት ?? ከግል ጥላቻ ወጣ እንበል ጎበዝ:: “በ3 ወር ያውም በትርፍ ጊዜ በተሰራ ስራ”?? አይደለም 3ወር 30 ዓመት ቢሰራ ፋይዳ ያለው ስራ የማይሰራ፡ ነገር ሲጠመዝዝ የሚሮር ሞልቷል በቤተ ክህነቱ::

  ቀድሞ ይዘጋጅ አሁን ይዘጋጅ፡1ሺ ገጽ ይሁን 100 በይዘቱ ላይ መነጋገሩ መልካም ይመስኛል::

 9. Anonymous December 31, 2013 at 8:48 pm Reply

  ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር፡ የተጀመረው ለዘመናት ስንናፍቀው የነበረው አሰራር ከዳር ደርሶ እንድናይ እግዚአብሔር በዚህ ሥራ ውስጥ የያሉትን ሁሉ ያበርታነን፡፡ አሜን

 10. Anonymous January 1, 2014 at 4:14 am Reply

  God thank you for your blessing. If we can be kind to each other and pay attention to our mother Churche’s message we can all be bless to live in peace, harmony, and love; there are too much that we can learn from each other as well. Just open your heart to the Church and close to beleka beleka zena. Stay away from kilil mentality you are human better than that, don’t loss your humanity, leave the other to God.

 11. Anonymous January 1, 2014 at 8:07 am Reply

  የእግዚአብሔር ልጆች ነን ነካችሁ! የቤተክርስቲያን ለውጥን አትፈልጉምን? እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!!

 12. Anonymous January 1, 2014 at 8:13 am Reply

  የእግዚአብሔር ልጆች ምን ነካችሁ? የቤተክርስቲያንንን መለወጠጥ አትፈልጉምን? እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን!!

 13. Anonymous January 1, 2014 at 8:20 am Reply

  የእግዚአብሔር ልጆች ምን ነካችሁ? የቤተክርስቲያንን ለውጥ አትፈልጉምን? እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን!!

 14. በአማን ነጸረ January 1, 2014 at 9:29 am Reply

  ወድ ሀራውያን ሁላችሁም ሊባል በሚችል መልኩ አዲሱን የመዋቅር ጥናት ሳታነቡት ከባህር ዳር እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ያላችሁ ሁሉ እንደው በደፈናው ያላያችሁትን ጥናት ይተግበር….ይተግበር….እያላችሁ ግፊት ስታደርጉ ሳይ እና ቆይ ….ይመርመር የምንል እንደኔ አይነት ግለሰቦችን በልዩ-ልዩ ስም ስትወነጅሉ ስመለከት ወደፊት ቤ/ክ ‘ከቡድንና ከቡድን አባቶች’ በሚሉ ቲፎzo ተኮር ትውልድ እጅ ውስጥ እንዳትገባ እፈራለሁ!!!
  የሩቆችስ ይቅር!!!
  እስኪ የቅርቦቹ በቃለ-ዐዋዲው አንቀጽ 13 “የሰበካው ቤ/ክ አስተዳዳሪ ስልጣንና ተግባር” በሚል የተቀመጡትን ድንጋጌዎችና በአዲሱ ጥናት ለሰው ሀይል አስተዳደር የተሰጠውን ስልጣን አነጻጽሩት. በዚሁ ቃለ-ዐዋዲ አንቀጽ 17 የተዘረዘሩትን “የዋና ጸሀፊ ስልጣንና ተግባራትን”ም እንደዚሁ!!አዲሱ ጥናት እነዚህን በቃለ-ዐዋዲው የተቀመጡ ስልጣንና ተግባራት ለልዩ-ልዩ አዳዲስና ነባር የስራ ክፍሎች ደልድሉዋቸዋል!!!ይሁን!!!ጥሩ!!!
  ችግሩ፡ ይሄ ሁሉ እየሆነ ያለው ቃለዐዋዲው ባልተሸሻለበት ነው-መቼም ከ2እስከ4ሺህ ዘመን የሚቆጠርለትን መጽሀፍ የምትጠቀም ቤ/ክ የዛሬ 15 አመት ተሻሽሎ የጸደቀ ቃለዐዋዲ ‘ያለፈበት ነው’ አትሉንምና ቢያንስ እሱ እስኪሻሻል ጠብቁ!!!ቃለዐዋዲ በመመሪያ አይጣሥም!!!ስለ hierarchy of law ጠይቁ!!
  “ማህበራችን ጥናት በጉንጩ ነው” ያላችሁኝን ወንድሞች ጥናት እንዲህ ማጣቀሻ መጻህፍት ሳይጠቀስለትና ሊቃውንት ሳይሳተፉበት ሊሰራ እንደሚችል በማስረዳት፣ ‘1ሺህ ገጽ ያለው ጥናት እኮ ከባድ አይደለም እንኩዋን በ3 ወር በ30 ቀናት ይደርሳል’ በማለት 1ሺህ ገጽ ጥናቱን አንብባችሁ ገብቱዋችሁ እኔ ግን ባየው….. ባየው ሊገባኝ ያልቻለው ደፍኖብኝ መሆኑን በመንገር ሂሴን እንድውጥ ስለረዳችሁኝ አመሰግናለሁ!!!መካሪ አያሳጣን!!!!!!!!

  • Anonymous January 1, 2014 at 8:28 pm Reply

   ወዳጄ አንተ ቀዳዳው ቋት እንዳይዳፈን ነው ጥረትህ። ቃለ አዋዲው በጥናቱ መሰረት የማይቀየርበት ምንም ምክንያት የለም። ደሞ እሱን ጠብቃችሁ ስትሰሩ አይደል እንዴ? መቼም ቃለ አዋዲው ስረቁ ይላል አትለኝም አይደል?
   ጥናቱን ስለመመርመር ላነሳኸው፦
   ለዛ መስሎኝ ውይይቱ ያስፈለገው። እዛ መግለፅ ያቃተህን በየባለስልጣኑ ቢሮ የሚያሯሩጣችሁ እንደለመዳችሁት በአቋራጭ ለማሰናከል ነው።

   በአንተ አጨራረስ፤ ሩጫህ ከግል ጥቅምህ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያኗ መጠናከር ስለሆነ ምስጋና ይድረስህ።

 15. frewoyni January 1, 2014 at 12:07 pm Reply

  beaman netsere ahunm chigirih ke tinatu sayihon ke mehaber new eski alfeh asib ebakih

 16. Anonymous January 2, 2014 at 3:33 am Reply

  በአማን ነጸረ:ሂስማ በጣም ጠቃሚ ነው:: ሂስ እንዲሰጥበትማ ነው የከረመው:: የኔ ነጥብ እከሌ ስላጠናው ትክክል አይደለም የሚለው ነው የማይስማማኝ:: ‘ከቡድንና ከቡድን አባቶች’ ነው ያልከው? ይቺማ ያንተ ግንዛቤ ናት:: እርስ በርሱ የሚጣላ አተያየት ነው እሰጠህ ያለኅው ወንድሜ::

 17. Mamush January 2, 2014 at 8:13 am Reply

  I do not know the reason why everybody is in a sort of resistance to this promising change. Why? Do not you appreciate the change that protects our CHURCH from those people who are always restless to snatch its money and property just for the sake of accumulating EARTHLY wealth rather than working for the boarder less baptism & spread of the Holy Gospel all over the world? Do you still want our CHURCH to continue to be in a state of poverty? Do those ‘minority’ priests be starved while others built their house and buy modern vehicles? Do we still continue to go along the streets to beg for money while we have much more enough in the CHURCH? Think over it and be constructive if you all are concerned about the CHURCH. We all know that those who lost their advantage, are irritated, frustrated and intended to create chaos.

 18. Mamush January 2, 2014 at 8:22 am Reply

  ‹‹ጥናቱን ቀን ከሌት ሠርተው ከዚኽ ላደረሱት ኹሉ÷ የእያንዳንዳችኹን ዋጋ አምላከ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ይሰጣችኋል፡፡ በ1500 ገጽ ላይ የኹላችኁም ስማችኹ ተጽፏል፡፡ ሰው ዛሬ ቢያመሰግን ነገ ሌላ የሚል ነውና በአንደበታችኹ ስንነቀፍ ደስ ይለናል እንዳላችኹት በልባችኁም ደስ ይበላችኹ፡፡ በጥናቱ ደስ ያላላቸው ካሉ በአስተሳሰብ ልዩነት ሊኾን ይችላል፤ ሳይገባቸው ቀርቶም ሊኾን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር፣ ይህ ኹሉ ጩኸት ለቤተ ክርስቲያን ካልኾነ ለምን ሲባል ኖሯል? እኔስ ብኾን ከዐሥር ዓመት በላይ የደከምኹበት ሀ/ስብከት እያለ እዚህ ምን አደርጋለኹ? ሙሉ ቀን እዚኽ የምቆመው ምን ለማግኘት ነው? በእውነት እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው ነው የምለው፡፡
  እንደ ጨለማው ዘመን፣ እንደ ወርቃማው ዘመን ኹሉ ይህም የእኛም ዘመን በወደፊቱ ትውልድ ስም ይወጣለታል፡፡ ዘመኑን ሳንሠራበት ካለፍን በነፍስም በሥጋም እንጎዳለን፤ ዐፅማችን እንኳ አያርፍም፡፡ አሁን ስማቸውን እየጠራን ያለነው በዘመናቸው ገድላቸውን ፈጽመው ያለፉ አባቶቻችንን ነው፡፡ እኛ የተቀመጥነው በእኒህ በዘመናቸው ሥራ ሠርተው ባለፉት አባቶቻችን ወንበር ነውና ከባድ አደራ ነው ያለብን፡፡
  ዛሬ ለችግራችን መፍትሔ ይምጣ በሚባልበት ጊዜ መድኃኒት እንደገባበት ባሕር የምንገላበጠው ለምንድን ነው? በስታቲስትክሱ ሌሎች በስንት ነው ያደጉት? በየክልሉ የእኛ በምን ያህል ቀነሰ? በሕዝብ ቆጠራውኮ በትልቁ ጎድለን የተገኘነው ስንት ሊቃውንት አሉ በተባለበት በአዲስ አበባ ነው፡፡ ይኼን ሁሉ ምእመን ባጣንበት አዲስ አበባ ሊቅ ነኝ ማለት በራሱ ያሳፍራል፡፡ ቀጣይ ቆጠራ ይካሄዳል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያስወረሩት፣ ምእመኑን ያስነጠቁት በዚህ ዘመን የነበሩ አባቶች ናቸው ተብለን በመቃብር እንኳ ዐፅማችን አያርፍም፡፡ አሁን በተመቻቸ ሜዳ ላይ ነው ያለነውና ልናስተውል ይገባል፡፡ እኛ ሰላም ኾነን፣ ፍቅር ኾነን ምእመኑን ስንመራው በእምነቱ ኮርቶ አንገቱን ቀና አድርጎ ይራመዳል፡፡
  አባቶች፣ እባካችኁ ማስተዋል ይኑረን፤ እኛ ርስ በርስ ስንነቃቀፍ ስንት ሰው ይሄዳል መሰላችኁ? ለምን አንመካከርም? ማንምኮ ፍጹም የለም፤ እንዴ! ለቤተ ክርስቲያናችንኮ ጠላት የኾናት እኛው ነን፡፡ አሁንም በገዳማቱ ቅዱሳን አልጠፉም፡፡ አባቶቻችን ይህችን ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ከነዘርፈ ብዙ ሀብቷ ያስረከቡን ደመወዝ የሚያስብላቸው ሳይኖር አንጀታቸውን በጠፍር አስረው እያረሱ፣ ቅባ ኑግ እያበሩ ቀድሰው ነውና ዐፅማቸው ይወቅሰናል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድናት፤ እኛም እንዳን፡፡››
  /በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ለየዙሩ የጥናታዊ ውይይት ተሳታፊ ገዳማትና አድባራት ልኡካን የሰጡት ቃለ ምዕዳን/
  The CHURCH needs a courageous person like you.

 19. Anonymous January 2, 2014 at 9:54 am Reply

  @ በአማን ነጸረ
  አንዲ ሺ ገጽ በ3 ወር እንዴት ብለሃል?በኮሚቴ እንደተከናወነና
  ያጥኚውን (ረቂቅ አዘጋጁን)ብዛትከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ድረ ገጽ ተመልከት።
  አቡነ ጳውሎስ ሲሞቱ ከMK መሳቢያ ወጣ ብለኸናል ግሩም አንተ ባልከውም እኮ ችግር የለውም።ተዘጋጅቶ የነበረው እንደገና ተከልሶ ሊቀርብ ይችላል?እዚህች ላይ አንድ ምስጢር አረጋገጥክልን በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ችግር መኖሩን(ሙስናው፣ዝምድናው፣ምንፍቅናው የደከመ አሰራሩ ሁሉ)። ያኔ መዋቅራዊ ለውጡን አንዳይመጣ ይፈለግ ነበር።አንተም ትፈልግ ነበር?
  በቲፎዞ ብለሃል እና ከበጎ ነገር ጋርማ እንተባበራለን።መተባበራችን የማሻሻያ/ማረሚያ ሐሳብ ከማቅረብ አያግደንም።አንተ አለህ አደል ከተቃዋሚ ጋር የምትተባበር።
  መነሻህ ራሱ ለምን ማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጀው እንጂ ያዘጋጀው ለቤተክርስቲያን ካለው ፋይዳ አንጻር አትመዝነውም።
  ለቤተክርስቲያን በጎ አስተዳደር እያንዳንዱ ምዕመናንም ድርሻ አላቸ ይቅርና በተደራጀ በታቀደና በተማረ የሰው ኃይሌ የሚመሩ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ፤እንደ ማኅበረ ቅዱሳንን ያሉ ማኅበራት።ሊቃውንቱ ሊመሩት ሊያርሙት ይችላሉ።ከመነሻው ሐሳቡ በሲኖዶስ ይሁንታ ካላገኘ አይጸድቅም አይተገበርም።ሲኖዶስ ደግሞ የሊቃውንቱ ብጹዓን ጳጳሳት ምልዓተ ጉባኤ መሆኑን ትጠራጠራለህ?

 20. Haymanot Ret'et January 2, 2014 at 12:36 pm Reply

  Guys please Do not keep on focusing on rudimentary issues! The reformationists are now widely being spread in a very traumatic manner. The issue of structural administration is very silly as compared to the previaling agenda.

  Please do not try to waste our time by focusing on petty issues. First should come the integrity and existance of the church. It is the later now being challenged by few blind bishops, fantu woldie (who is acting as a widow) and those usual trashes. While the biggest problem is knocking at the doors of the mother church, we must not try to widely open our doors for their looting purpose.

 21. Beko January 6, 2014 at 5:47 pm Reply

  ወንድሞቼ የመዋቅራዊ ለውጡ የሀዘቦችን የመስማት የማወቅ የቋንቋ የመረዳት ሁኔታ ያካተተ ይሁን አይሁን ስላናበብኩት አስተያየት መስጠት አልችልም፡፡ ሆኖም እንደክርስቲያን ሁልጊዜ የማዝንበት ነገርን ማንሳት እፈልጋልሁ፡፡
  እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በክርስትና ወደ 2000 አመታት ታሪክ አላት፡፡ በግልጽ አሁን ድረስ እንደሚታየው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወንጌል በበቂ ሁኔታ ያልደረሰበት ቦታ ይገኛል (እንደምሳሌ ሙርሲ፡ቦዲ… ጅንካን አልፋችሁ ብትሄዱ) ፡፡ እንደኔ እምነት ይህች ቅድስት ቤ/ክ ብዙ ምእመን ሊጠፉባት/ልታጣ የቻለችው አንዱ ምክንያት በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የወንጌል ት/ት አማርኛ ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገ በመሆኑ እንደሆን ይሰማኛል፡፡ እስቲ ጎንደር ተወልዶ ላደገ ህጻን እንዴት በሲዳምኛ፡ በኦሮምኛ …… ልታስተምረው ትችላለህ? መቼም ወንጌል ከሰማ ስማ አይባልም። ለምሳሌ በራሴ ምሳሌ ብጠቅስ ፡ ያደኩት ከተማ በአማርኛ ተጽእኖ ውስጥ ስለሆነ አማርኛን ለማወቅ ችያለሁ፡ አከባቢውም ለክርስትና የተጋለጠ ስለሆነ ክርስትናን ለማወቅና ለመረዳት ችያለሁ። ገጠር ያደገው ወንድሜ ግን ሙስሊም ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ውስጤ ይብላላ ነበር። እንደ አንድ ምክንያት ያቀረብኩት የቋንቋ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ በሙስሊምና በፕሮቴስታንት ብንመለከት ሁለቱም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚያስትምሩት እንደየአከባቢው ቋንቋ ነው። ቢቀር ቢቀር በትርጉም ያስተምራሉ። ለዚህም ነው ብዙ ተከታይ ያገኙት። በቅርቡ ለስራ ወደ ገጠር በሄድኩ ጊዜ የተመለከትኩት ይሀንኑ ነው። የኛ ቤ/ክ ናት አማርኛ ለሚሰሙት ብቻ በአማርኛ ወንጌል ሲሰበክ ያየሁት። ይህ በጣም አሳዝኖኛል። አሁን ስራ ላይ ይዋል የምትሉት ጽሁፍ የቋንቋን ጉዳይ የተለየ ምእራፍ ሰጥትት ካላየው በኢትዮጵያ ውስጥ ወደፊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለአማራና ለአማርኛ ተናጋሪዎች ብቻ የተተወ ይሆናል።
  እንደኔ እምነት ይህ የምትሉት ጽሁፍ ውስጥ እንኳን ባይካተት ጊዚ ሳይሰጠው መምህራንን መዘምራንን ቀሳውስጥን ከተላያይ ቋንቋ ተናጋሪ የማብቃት ስራ መጀመር አለበት እላለሁ ፡ ይህንን ጉዳይ ለማስፈጸምም የተለየ ማእከል መቋቋም አለበት ። ቤ/ክርስቲያኗ በታሪክ የተላልፉላት መጽሃፍት ወደ ተለያየ ቋንቋ መተርጎም መቻል አለበት፡ ሌላም ሌላም…… ብዙ ስራ መሰራት አለበት። እንደፖለቲከኛ ሳይሆን እንደ አንድ ክርስቲያን የቋንቋን ጉዳይ ከተመለከታችሁት ቋንቋ ባለማውቁ ወንጌልን አለማወቁ ያስለቅሳል። ስላልተሰራብት ነው እንጂ ቢሰራበት ለሌሎች አፍሪካ ጥቁር ህዝቦችን መድርስ ይቻል ነበር ነገር ግን….። በዚህ ጉዳይ ብዙ ማለት ቢቻልም በዚሁ ላብቃ ……. ምናልባት የዚህ ጽሁፍ አንባቢ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከትህ/ታችሁ ከሆነ በእግዚአብሔር ስም ጉዳዩን በማጥናት አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወስዱ ጠይቃልሁ። እግዚአብሔር ከዕናንተ ጋር ይሁን!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: