ገዳማትና አድባራት በአገልግሎት ስፋታቸውና በልማት አቅማቸው በደረጃ የሚመደቡበትና በቀጣይነት የሚያድጉበት መስፈርት ሊወጣ ነው

Sendek's coverage on A.A.D Change mgt.

 • በደረጃ ምደባው በአጥቢያዎች የተከማቸውን ከፍተኛ የአገልጋይና የሠራተኛ ቁጥር በማሠልጠንና ማብቃት ማደላደልና ማሸጋሸግ እንጂ ማፈናቀል አይኖርም ተብሏል
 • ገዳማትና አድባራት በፋይናንስ ፖሊሲው መሠረት ከዓመታዊ በጀታቸው ቀሪ ከሚኾነው ገንዘባቸው 60 በመቶውን ለልማት ተቋማት ማቋቋሚያና ማስፋፊያ ይመድባሉ፤ የልማት ፈንድ ያቋቁማሉ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት ያሉበትን ኹኔታ ተገንዝበው አገልግሎታቸውን የበለጠ በማስፋፋት ወደተሻለ የአገልግሎት ዕድገት የሚሄዱበትን አቅጣጫ ያመላክታል የተባለ የደረጃ መስፈርት ጥናት ረቂቅ ተዘጋጀ፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት ሰነዱ÷ በሀገረ ስብከቱ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋሞች ሥር የሰደደውን የመልካም አስተዳደር፣ የፋይናንስ አያያዝና የሰው ኃይል አመዳደብ ችግሮች በወሳኝ መልኩ ለመቅረፍ በቤተ ክርስቲያኒቱ ባለሞያዎች የተካሄደው የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት አካል መኾኑ ተገልጧል፡፡

አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ከሚሰጧቸው አገልግሎቶች ጋራ በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በሞያና ልምድ የተመጣጠነ የሰው ኃይል ቁጥር የማስገኘት፣ ከአገልግሎቱ ጋራ የተመጣጠነ የአገልጋዮች ክፍያ ሥርዐት የመዘርጋት፣ ከምእመኑ ፍላጎት ጋራ የተመጣጠነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስልት የመቀየስና በአጠቃላይም የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋናና መሠረታዊ ተልእኮ ከኾነው የስብከተ ወንጌልና ክህነታዊ ተግባራት አንጻር አገልግሎቷን የመምራትና ወደሚፈለገው ደረጃ ከፍ የማድረግ ዓላማ እንዳለው ተጠቅሷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የደረጃ መስፈርቱ÷ ተዋረዳዊና ጎንዮሻዊ የሞያ ልህቀት ፍኖት/ሰዋስው (career path) ባለውና ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ሀ/ስብከት በሚዘልቀው መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የሥራ መደብና የሥራ መዘርዝር መሠረት ራሳቸውን በመንፈሳዊ ቅንዓትና በፍትሐዊነት ላይ በተመረኮዘ የመወዳደር ብቃት የሚያሻሽሉበት ኹኔታ ለመፍጠር እንደሚያስችልም ተዘግቧል፡፡

የምዘና መስፈርትና ደረጃ ጥናት ረቂቁ ገዳማቱን፣ አድባራቱንና አብያተ ክርስቲያናቱን በአምስት ደረጃዎች የከፋፈለ ሲኾን አራት ዐበይትና ከሠላሳ በላይ ንኡሳን የምዘና መስፈርቶች ተለይተውበታል፡፡ በዋናነት ለተቀመጡት መስፈርቶች የተሰጣቸው አጠቃላይ ክብደት በሥራቸው ለተካተቱት ንኡሳን መስፈርቶች ተከፋፍሎ በመጨረሻ ከመቶ የሚገኘው ጠቅላላ ድምር ውጤት የአብያተ ክርስቲያናቱን ደረጃ እንደሚወስን ተመልክቷል፡፡

በዚህም መሠረት በቤተ ክርስቲያኒቱ÷ ቅዳሴ፣ ሰዓታትና ጸሎት በዘወትር፣ በሳምንትና በበዓላት የሚፈጸምበት ጊዜ፣ የአብነት ትምህርት ጉባኤያትና የተማሪዎች ብዛት፣ ስብከተ ወንጌል የሚሰጥበት ጊዜ፣ የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ኹኔታ፣ በሙዝየም፣ በጠበልና በቀብር አገልግሎት እየሰጠች ያለችው መንፈሳዊ አገልግሎት 30 ነጥብ ተሰጥቶታል፡፡

ከሙዳየ ምጽዋት፣ ከልማትና ከአገልግሎት የሚገኘው የገቢ ኹኔታ 27 ነጥብ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሙዓለ ሕፃናት፣ በጤናና በአረጋውያን መጦርያ የልማት ተቋማትና የምግባረ ሠናይ ሥራዎች 23 ነጥብ፣ በአጥቢያው በሰበካ ጉባኤ የተመዘገቡ ምእመናንን ብዛት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዞታ ሕጋዊነት፣ ስፋትና የምሥረታ ዘመን ያካተተው ሌሎች ሀብታትና ታሪክ መስፈርት 20 ነጥብ ክብደት እንደተሰጣቸው በጥናቱ ተብራርቷል፡፡

በዚህም መሠረት ከ85 – 100 ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ አንድ፣ ከ70 – 84.99 ያሉት ደረጃ ሁለት፣ ከ55 – 69.99 ያሉት ደረጃ ሦስት፣ ከ40 – 54.99 ያሉት ደረጃ አራት ሲባሉ ከተተከሉ እስከ ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የኾኑ አዲስ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ለብቻቸው በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተለይተዋል፡፡

በየደረጃ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት የተለያየ መዋቅር፣ የተለያየ የሰው ኃይል ምደባ/በቁጥርና በሞያ/ እንዲሁም የደመወዝ ስኬል የሚኖራቸው ሲኾን ይህም በየሁለት ዓመቱ በሚካሄድ ክለሳና አብያተ ክርስቲያናቱ ዐቅደው በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ዕድገታቸው በቀጣይ የምዘና መስፈርት እየተረጋገጠ እንደሚሻሻል ከቀረበው ጥናት ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንደየሥራው ስፋት የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ተፈላጊውን የትምህርት፣ የሥራ ልምድና የክሂሎት ዝግጅት ባገናዘበ አኳኋን ለየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ በሚሠራው የሰው ኃይል ትመና ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም የሚያስችላቸው የክፍያ ሥርዐት ተዘርግቷል፡፡ በተለይም ደግሞ በሀ/ስብከቱ የሚገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ትኩረት አግኝተው ተተኪዎችን ማፍራት ይችሉ ዘንድ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ በቢሮው ውስጥ ከሚሠራው ሥራ በበለጠ የካህናት ኑሮ የሚሻሻልበትን ኹኔታ ለመቅረፅ የቤተ መቅደሱ የውስጥ ክህነታዊ አገልግሎትም ቀዳሚ ቦታ ተሰጥቶታል፡፡

በሰው ኃይል ትመናው ገዳማቱና አድባራቱ ካላቸው መንፈሳዊ አገልግሎትና የልማት እንቅስቃሴ አንጻር የሚበቃቸው ያህል አገልጋይ ያገኛሉ፡፡ ቀሪው የሰው ኃይል በፋይናንስ ፖሊሲና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው እንዲሁም በልማት ሥራዎችና ምግባረ ሠናይ ተግባራት ፖሊሲና መመሪያው መሠረት÷ አብያተ ክርስቲያኒቱ ዓመታዊ በጀታቸውን ከመጠባበቂያቸው ጋራ ከያዙ በኋላ ቀሪ ከኾነው ገንዘብ ከሚመድቡት 60 በመቶ የልማት ፈንድ በሚከፍቷቸው የልማት ተቋማት የተለያዩ የክህሎት ሥልጠናዎችን በመስጠት የሚሠማራበት ሥርዐት እንደሚኖር ታውቋል፡፡

ከዚህም አኳያ ከፍተኛ የሰው ኃይል ክምችት በየአጥቢያው መኖሩ እሙን ቢኾንም አጥቢያዎች በልማት በየጊዜው ከሚፈጥሩት አቅምና በዚህም በሚስፋፉት የአገልግሎትና ምርት ተቋማት በሒደት የሚደላደል እንጂ የሚፈናቀል አገልጋይ እንደማይኖር ተገልጦአል፡፡

Advertisements

12 thoughts on “ገዳማትና አድባራት በአገልግሎት ስፋታቸውና በልማት አቅማቸው በደረጃ የሚመደቡበትና በቀጣይነት የሚያድጉበት መስፈርት ሊወጣ ነው

 1. melaku bogale December 25, 2013 at 11:38 am Reply

  temesgen, may God help us!

  • tesfahun December 30, 2013 at 7:36 pm Reply

   ለምንት አንገለጉ አሕዛብ ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ
   ሕዝብ ብርሃነኔ ገብረ ፃድቃን፣ መርከብ መኩሪያ፤
   አሕዛብ አእመረ አሸብር፡ አይነ ኩሉ ጌታነህ፡ ግርማ ባቱ፤ ያሬድ ክብረት

   ለምን የበሰበሰ ከንቱ ነገርን ይናገራሉ ለምንስ ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ለክህደት ይሰበሰባሉ፤

   መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ ሕግ መጽሐፋዊ ሕግ ጠባያዊን ሲፍጽም አድጓል
   ሕግ ጠባያዊ ቀስበቀስ ማደግ ነው ያም ማለት አምላክ ነኝና ዕለቱን ልደግ አላለም ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር እንዲል ሉቃስ 2፡51
   ሕግ መጽሐፋዊ ሕግን ሁሉ ሲፈጽም ማደግ ነው፡-
   አምላክ ሆኖ እያለ የአባቶቹን ሥርዓት ጠብቆ ማለፉ ግልጽ ነው፤ ያም ማለት ቤተ ግዝረት በመግባት ከዓመት 3 ጊዜ ለበዓል ኢየሩሳሌም መውጣት

   ወላጆቹም በየዓመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር።
   የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤
   ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።
   ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤
   ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
   ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤
   የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።
   ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።
   እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው።
   ወዘተ—- ነገር ግን ይህ ሆኖ እያለ ግን ይቀኑበት ነበር እውነቱን ነገር ሲነግራቸው ይበሳጩ ነበር እስከ ሞት ድረስ የጠሉትም ለዚህ ነበር፤ እንደ እነርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሞታል እኛም የምንፈልገውን ሁሉ እናደርጋለን ነበር አሳባቸው፤ የሞትና የሕይወት ባለቤት መሆኑን አልተገነዘቡም ነበር ምክንያቱም አንዴ ቅናት አይናቸውን አሳዉሮት ነበርና፤ ዛሬም ተረፎቸ ከአይሁድ የተረፉት እኒህ ኮሌጁን ምሽግ አድርገው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና ሥርዓት ጠብቀዉ የሚያስጠብቁትን አባቶቸ ከኮሌጁ እንዲወጡና ኮሌጅን ለኘሮቴስታንት እንዴት እንደሚያስረክቡት ዕለት ዕለት በዲያቆን ብርሃኔ ቢሮ በመሰብሰብ እየሰሩ ያሉት ሥራ በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ዛሬም በ21/ 4/ 2006 ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ አንድ ማንነቱ ያልታውቀ ሰው ይዘው ተሰብስበው አምሽተው ነበር የሚገርመው ደግሞ ዲያቆን አንድነት አሸናፊ አብሮ ተሰብስቦ ነበር፤ ቤተ ክርስቲን ስላስተማረች ምን አደረገች ለዲዳዉ ሁሉ አፍ ሆና ምንም ያልነበረዉን ሰዉ ከቁጥር አግብታ ሙሉ ሰዉ ስላደረግች ዉለታዋን መክፈል ቢቻል መልካም ነዉ ካልተቻለ ደግሞ ፍቅሩዋን ማጣጣም ነበር:

   አንድ እዉነታ አለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ ዘንድ የሞተና ሁሉም ነገር ያከተመ መስሎአቸዉ ነበር ነገር ግን በሦስተኛዉ ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ እነርሱ የከመሩት ድንጋይ በእርሱ ዘንድ ቁም ነገር አልነበረዉም ፤ ዛሬም የቤተ ክርስቲያንን አንጀራ እየበላችሁ ነገር ግን የሰይጣንን ምግባር ይዛቸዉ የይሁዳን ስንቅ አንግባችሁ የምትጓዙ፤

   ዲያቆን ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን
   ›› ግርማ ባቱ
   ›› ያሬድ ክብረት
   ›› ልዝቡ ሰይጣን አንድነት አቸናፊ
   ›› አእመረ አሸብር
   ›› አይነ ኩሉ ጌታነህ፡
   ›› መርከብ መኩሪያ፤

   ምን አልባት ቤተ ክርስቲያን አናንት በቆፈራችሁት ጉድጓድ ምትገባ መስሏችሁ ከሆነ ያጠመዳችሁ ሰይጣን አያታልላችሁ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ የታነጸችዉ በክርስቶስ ደም ነዉ፡ ስለሆነ ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፡፡

   የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሆይ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በፕሮቴስታንት እየተከበበ ነዉ፡

   ግርማ ባቱ Academic dean
   አንድነት አቸናፊ Registrar
   አይነ ኩሉ Teacher of Old Testament Commentary
   ያሬድ ክብረት Vice dean
   ብርሃኔ ገብረ ፃድቃን ወግ አይቀር ያለ አቅሙ እንኳን ለማስተማር ተማሪ ለመሆን ብቃት የሌለው Teacher of petrology

   ሰለዚህ መፍትሔዉ ምን እንደሆነ እስኪ እንወያይ

  • Anonymous December 30, 2013 at 8:27 pm Reply

   ለምንት አንገለጉ አሕዛብ ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ
   ሕዝብ ብርሃነኔ ገብረ ፃድቃን፣ መርከብ መኩሪያ፤
   አሕዛብ አእመረ አሸብር፡ አይነ ኩሉ ጌታነህ፡ ግርማ ባቱ፤ ያሬድ ክብረት

   ለምን የበሰበሰ ከንቱ ነገርን ይናገራሉ ለምንስ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለክህደት ይሰበሰባሉ፤

 2. Anonymous December 25, 2013 at 1:37 pm Reply

  Temesgen amlake

 3. በአማን ነጸረ December 25, 2013 at 1:59 pm Reply

  1. አቤት…..አቤት….አቤት…..የእናንተን ጥናት ያልዘገበው ……ቆይ….ቆይ….ማን ቀረ…..ማን ቀረ የውጭ ሚዲያዎችና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን……ከዛ ደግሞ የተሻለ ሙያዊና የፋይናንስ አደረጃጀት ያላቸው ሪፖርተርና አዲስ ፎርቹን…..የተቀሩት እነ አዲስ አድማስ፣እነ ኢትዮ ምህዳር፣እነ ሰንደቅ፣ከነፈሰበት የሚነፍሱት የግል መጽሄቶች ሁሉም እያስተጋቡት ነው፡፡ይሁን!!!ድሮም እነዚህ ፈራ ተባ እያሉ የተቃዋሚዎችን ትንፋሽ የሚያስቀጥሉ የህትመት ሚዲያዎች ጋር ያላችሁን ቁርኝት እናውቀዋለን፡፡ወሬዎች ከእናንተው በመስኮት ወጥተው ሳይከለሱ ሳይበረዙ ለየቲፎዞ ሚዲያዎቻችሁ ከተበተኑ በሁዋላ ተመልሰው እንደ ትኩስ ዜና በየብሎጎቻችሁ የሚወጡበት የቆየ አሰራር መኖሩን ከተረዳንም ቆይተናል ፡፡ ያልተቀደሰ ጋብቻ ብለነዋል!!!
  2. እነዚህ እነ እንትና በቢግ አፍሪካ ባለጉ ሲባል ስለ ህ/ሰብ የሞራል ዝቅጠት፣ታዋቂው አርቲስት ሲታሰር ስለ እስረኞች መብት፣አቦይ እንትና ሲናገሩ ስለ ጥንታዊት ኢትዮጵያ፣እነ እንትና ቪሲዲ ሲያወጡ ስለመናፍቅነት፣በጥቅምትና በግንቦት ስለ ቅ/ሲኖዶስና ስለ ተሀድሶ፣መንግስት ማህበራትን በአክራሪነት ሲከስ ስለማህበር፣እስልምናው ከረረ ሲባል ስለ አወሊያ…….ወዘተ ያለማንም ከልካይ ምንጭ እንኩዋ ሳይጠቅሱ ኪነጥበቡን ከፖለተካ፣ፖለቲካውን ከሀይማኖት እያማቱ…. እያምታቱ የሚሞነጭሩ “የአሙቁልኝ ሚዲያዎች” ከዚህ የተሻለ እንዲዘግቡ አይጠበቅም፡፡
  3. እነሱ ተባለ…..ተገለጠ…..የሚሉት ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥበት እድል ተመቻችቶ በገሀድ ከቤ/ክነት ሀላፊዎች መረጃውን አግኝተው አይደለም ፡፡መለኪያቸውም ‘ወሬው ለሀገርም ሆነ ለቤ/ክ ይጠቅማል/አይጠቅምም?’ የሚለው ሳይሆን ‘ገበያ ይስባል ወይስ አይስብም?’ ነው፡፡ በይፋ ፖሊሲ ሆኖ ከጸደቀው የመንግስት እቅድ ስንትና ስንት አማራጭ መፍትሄ የሌለው አቃቂር የሚያወጡት ቲፎዞ ሚዲያዎቻችሁ ገና ባልጸደቀው ጥናት የሚነሱ ቅሬታዎችን በማውጣት እናንተን ካስቀየሙ ነገ ማን ሊያነባቸው!! ሆሆ!!! ምንስ ቢሆን እንጀራ አይደል!!!! አልፈርድባቸውም!!!
  4. የቤ/ክ የልማት ተቁዋማት የሚባሉት ጠቅላላ ሊባል በሚችል መልኩ በጠየና እና በትምህርት ዘርፍ ያሉ በመሆናቸው አለ የተባለው በአብዛኛው ከአብነት ትምህርት ውጭ ዘመናዊ እውቀት ያልጨበጠ ትርፍ የሰው ሀይል በእነዚህ የልማት ተቁዋማት እንዴት ሊሰራ እንደሚችል መጠየቅም ለቲፎዞ ሚዲያዎች ኑክሌር-ፊዚክስ ነው!!! ‘ጥናቱ የሽግግር ጊዜ አለው/የለውም?’ ብሎ ማሰብም ነውር ነው!!!ማህበሩ ካሰመረው መስመር ማለፍ ነው!!!የማህበሩ የሆነውን ሁሉ መሬት ላይም ወድቆም ብታገኙት አንሱት ተብለናል፡፡ለጋዜጦች ገበያ ያን ያህል አማራጭ ገበያ መሆን የማይችሉት ካህናት ቅሬታ ሲያቀርቡ ግን ትኩረቱ ሁሉ የቅሬታቸው ይዘት ላይ ሳይሆን የኑሮ ደረጃቸው ላይ የሚቀርበው የሀብት ዝርዝር ነው፡፡ሚዛኑ አንድ ቢሆንም በለኪው አለማስተዋል ውጠየቱ ተለያየ!!! Double standard በኛም ልጆች ቀጥሉዋል!!!
  5. በነገራችን ላይ እዚህ ሀገር አንድ ያልተጻፈ ህግ አለ፡፡በኢቲቪ የታየና ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የተነጋገረ ሁሉ ካድሬ ነው፣ንግግሩም ፕሮፖጋንዳ ነው የሚል፡፡በተቃራኒው በግል የህትመት ሚዲያዎች የሚቀርብና በመንግስት የሚተች ሁሉ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊና የመብት ታጋይ ነው የሚል፡፡ማህበሩም በዚህ በኩል በመንግስት የሚደረግበትን መገለል በግል ሚዲያዎች አማካይነት ራሱን የቤ/ክ ትንሳኤ አብሳሪ በማድረግ እያቀረበ የሚነሱበትን የውስጥና የውጭ ጥያቄዎችን ሁሉ ለመድፈቅ እየሞከረ ነው፡፡ይህ በየፕሬሶቹ የሚወጣው ምንጭ አልባ የ99% የጥናት ድጋፍም የደፈቃው አካል ነው፡፡ lobby(ጫና) ማድረጊያ!!!
  6. ይሄውላችሁ ራሳችሁን ብቸኛ ተቆርቁዋሪ እያረጋችሁ ጥናቱን የሞትና የሽረት አታድርጉት፡፡ጥናቱ ዳግም ይታይ ማለታችንንም ለውጥ እንዳለመፈለግ አትዩት፡፡ “እንደገና ይታይ” በማለትና “አይተገበርም” በማለት መሀል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ጫጫታው በዛ እንጅ!!!ተረጋጉ፡፡አስተያየት ሰጭዎችም ገና ጥናቱን ሳታዩ ቤ/ክ አለፈላት በለውጥ ማእበል ተመታች እያላችሁ ባላያችሁት ጥናት በጭፍንነት አታጨብጭቡ!!!ክርስትና እውነት በሆነው ክርስቶስና እውነትን በሚሰብኩ ጥቂት ጻድቃንና ሰማዕታት እውነተኛ ምስክርነት የተገነባች እንጅ በድምጽ ብልጫ የቆመች ሃይማኖት አይደለችም!!!

  • Anonymous December 26, 2013 at 12:07 am Reply

   BeAman, we all know where you are going when you write it. Your intention is to distort people’s attention. Don’t waste your time. Instead, stay away and leave our church and the MK association alone.

   G G

  • Ben December 26, 2013 at 5:53 pm Reply

   የማነ አንተም እኮ ካለምንጭ ነው የምታወራው። ተባለ፥ አሉ ምናምን። አንተስ የትኛው ማስረጃህ ነው ከላይ ያለውን ሁሉ ያስፃፈህ? ቁም ነገሩ ቤተ ክርስቲያኗን ግጣችኋታል። ማር ብትሆን ልሳችሁ ጨርሳችኋታል። በየትኛው የቄስና የመነኩሴ ደሞዝ ነው ሚሊየነር የምትሆኑት? ታዲያ በደመ ነፍስ ራስህን ደጋፊ ሌላውን ተቃዋሚ ለማድረግ ብትጥር ይፈረድብሃል? አንተ በግልህ ኢቲቪ እየሰራህ ኡራኤልን ስትግጥ በአቅራቢያህ ነበርኩ። ከዛ የተሻለ መድሃኒአለም ከዛ አራዳ ጊዮርጊስ እያልክ እንደ አዲስ ቀፎ የምትዞረው አንተ ብቻ አዋቂ ስለሆንክ ነው ወይስ ማሩን ለመላስ ነው? ራስህ በሚገባ ታውቀዋለህ። ህዝቡ እንዳላየ ሲያልፋችሁ ጨርሶ አላዋቂ አደረጋችሁት እኮ። ይልቅ የሰረቃችሁትን ይዛችሁ ዞር ብትሉ ይሻላል። ካለዛ ሁላችሁም ደሞዝና ያፈራችሁት ንብረት እየተመዛዘነ መግባታችሁ ነው። እቺ ማቅ ተቃዋሚ ምናምን የተበላባት እቁብ ናት።

 4. Melaku zewdie December 27, 2013 at 7:20 am Reply

  ታህሳስ 18 ቀን 2006 ዓ.ም
  ለብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የብፁዕ ወቅዱስ ረዳት
  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
  አዲስ አበባ

  ጉዳዩ፡- የቅዱስ ሩፋኤልና ጻድቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቤ/ክ ይመለከታል

  በ2001 ዓ.ም አቶ ቦኬ ገመቹና አቶ ገመቹ ወርዶፋ የተባሉ የአካባቢው ኗሪዎች የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራበትና የአካባቢው ህብረተሰብ እንዲገለገልበት በሚል የግል መሬት ይዞታቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ኮሚቴ ተቋቁሞ መቃኞ ቤተ ክርስቲያኑ ተሰርቶ ለ4 ወራት ከተገለገለ በኋላ ቄስ ተከስተ ካሳሁን ከቀበሌ 16/18/21/22 አመራሮችና ከህብረተሰቡ እንዲሁም ከመስራች ኮሚቴ አመራር ጋር ቅራኔ ውስጥ ስለገቡ ሚያዚያ 5 ቀን 2002 ዓ.ም የቀበሌ 16/18/21/22 አስተዳደረር አመራር አፍራሽ ግብረ ኃይል በማሰማራት ቤተ ክርስቲያኑን በማፍረስ ታቦቱን ከነመንበሩ፣ ንዋየ ቅዱሳት፣ ቆርቆሮና እንጨት በመኪና ጭነው መውሰዳቸውና እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ንብረት ያልተመለሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡
  ይሁን እንጂ በ2004 ዓ.ም መቃኞ ቤተ ክርስቲያኑ እንደገና ተሰርቶ አገልግሎት ሊሰጥ በተዘጋጀበት ሁኔታ ቄስ ተከስተ ከአካባቢው ምዕመናን በተለይም ከአቶ ሚሊዮን ጋር በመደባደባቸው ለሁለተኛ ጊዜ ቤተ ክርስቲኑ በአንድ ሌሊት ፈርሶ አደረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ተቆርቋሪ አጥቶ ለብዙ ጊዜ ከቆየ በኋላ ነባሮች ምዕመናን ያሉበት አዳዲስ አባላት የተካተቱበት ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡
  ጉዳዩ ከቀድሞው ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ ጋር ደርሶ ከብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከአዲስ አበባ ም/ከንቲባና ከክ/ከተማ ኃላፊዎች ጋር ቦታው ድረስ በመምጣት ሕዝቡን ሰብስበው እርቅ እንዲወርድና ቤተ ክርስቲያኑ እንዲሰራ መመሪያ ሰጡ፡፡ በዚህም መሰረት በመስራች ኮሚቴው ጥረት መቃኞ ቤተክርስቲያኑ መሰራት ሲጀምር የአካባቢው ሕዝብ በተለይም አቶ ሚሊዮን በቄስ ተከስተ ላይ ቂም ይዘው ስለነበር ቤተ ክርስቲያኑ አይሰራም በማለታቸው ችግር ተፈጠረ፡፡ ኮሚቴውም ሕዝቡን በማግባባት አቶ ሚሊዮን የህክምና ወጭ ስላወጣ የጉዳት ካሳ 7000.00 ብር በመክፈል እርቁ ተከናወነ፡፡ ብሩን የከፈሉት የኮሚቴ አባላት ናቸው፡፡
  ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በመስራች ኮሚቴው ጥረትና ጥንካሬ ሕዝቡን በማስታረቅና በማስተባር መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም መቃኞ ቤቱ ተሰርቶ ታቦቱ ገባ፡፡
  በጥር 2005 ዓ.ም የቦሌ ክ/ከ የወረዳ 11 አመራር የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ መንግስቱ ለቄስ ተከስተ ደውለው ቤተ ክርስቲያኑ ሕጋዊ እንዲሆን ከበላይ አካላት ተፈቀደበትን ደብዳቤ እንዲያቀርቡ አለበለዚያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚፈርስ ሲያስታውቋቸው ቄስ ተከስተ በአንደበታቸው መልካም ምላሽ ባለመስጠታቸው ቤተ ክርስቲኑ በአፍራሽ ግብረ ኃኃል ሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም ለ3ኛ ጊዜ ፈረሰ፡፡
  ይሁንና ኮሚቴው እስከ አዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤትና ፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አቤቱታ በማቅረቡ በእግዚአብሔር እርዳታ ለጉዳዩ መልካም ምላሽ በማግኘቱ መቃኞ ቤቱ ለ3ኛ ጊዜ ተሰርቶ አገልግሎት እየሰጠ ቢገኝም፡-
  1ኛ. ቀደም ሲል ኮሚቴ እያለ የለም በማለት ከመስራች ኮሚቴው የድጋፍ ደብዳቤ ሳይሰጣቸው፣ በቂ ትምህርትና የማስተባበር ተሰጥኦና ችሎታ ሳይኖራቸው በፓትሪያርኩ ያልፀደቀ ለስድስት ወር ጊዜያዊ አስተዳዳሪነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል፡፡
  2ኛ. በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ብልሹነት ምክንያት ምዕመናንን “ቤተ ክርስቲያኑ ይሰራ እላችሁ ሕዝብና መንግስትን ልታጣሉ ነው” በማለት ቤተ ክርስቲያን እንዳይመጡ በማስፈራራታቸው ምክንያት በርካታ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን አይመጡም፡፡
  3ና. አከምስት ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያኑ ገና በመቃኞ እያለ በልማት ስም ከእያንዳንዱ ቄስና ዲያቆን በነፍስ ወከፍ ከ7000.00-10000.00 ብር በመቀበል (በአጠቃላ ከ500000.00 ብር በላይ የሚገመት ) ገንዘብ ለግላቸው ሰብስበዋል፡፡ይህ ገንዘብ የት እንደደረሰ አልታወቀም፡፡ መቃኞ ቤቱም ቢሆን የተሰራው በምእመናን አስተዋጽኦ ሲሆን ቄስ ተከስተ በሰበሰቡት ገንዘብ ምንም የተሰራ የልማት ስራ የለም፡፡
  4ኛ. መስራች ኮሚቴውን በማፍረስ ሰበካ ጉባኤ ባተቋቋመበትና ተቆጣጣሪ በሌለበት ሁኔታ በቤተ ክርስቲያኑ ስም ቅጽና ባጅ በማሳተምና ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በማሰራጨት መጠኑ የማይታወቅ በርካታ ገንዘብ ለግሉ ሰብስበዋል፡፡ በመሰብሰብ ላይም ይገኛሉ፡፡
  5ኛ. ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ብዙ የገንዘብና የጉልበት መስዋዕትነት የከፈሉ በነጻ የሚያገለግሉ የኮሚቴ አበላትን በማግለል ምንም አስተዋጽኦ የላበረከቱና ያልደከሙ ሚስታቸውን፣ የሚስታቸውን ወንድም ባጠቃላይ ዘመድ አዝማድ ሰብስበው በተለያዩ የስራ መደቦች በመቅጠር ቤተ ክርስቲያኑን የግል ኩባንያ ንግድ ድርጅት አድገውታል፡፡
  6ኛ. ቤተ ክርስቲያኑ ምንም የገቢ ምንጭ ሳይኖረው ከ52 በላይ ቀሳውስትና ዲያቆናት ተመድበዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ደሞዝ እንኳን በአግባቡ አይከፈልም፡፡
  7ኛ. ከንብረት ክፍልና ከእለት ገንዘብ ሰብሳቢ በስተቀር ካስተዳዳሪው ጀምሮ እስከ ተላላኪው ድረስ በሙሉ ከአንድ ብሔር የተሳሰሩ የሀገራቸው ተወላጆች ናቸው፡፡
  8ኛ. ከቤተ ክህነት እውቅና ውጭ ሰራተኞችን ቀጥረው ደሞዝ ከፍለዋል፡፡ ለምሳሌ፡-
  ሀ. ቀሲስ ሽታሁን ታደለ (ሀገረ ስብከቱ የተቃወመውን ቁጥጥርነት ሰጥቶታል)
  ለ. መዘምር ብርሐኑ ልየው (ሀገረ ስብከቱ ሳያውቀው ፀሐፊነት ሰጥቶታል)
  ሐ. ዲ/ን ፍሬው ጓድ
  መ. ቀሲስ ተስፋሁን ሰውነት
  ሠ. ቀሲስ ደገፋው ጥጋቡ
  ረ. ቀሲስ መላ መሐሪ
  ሰ. ዲ/ን ስብሐት
  9ኛ. ደሞዝ እንዲጨመር ለአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ዝርዝሩ ሲላክ የሚከተሉት ሰራተኞች ሀሰተኛ የመነሻ እርከን ተጨምሮላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
  ሀ. መ/ር ተከስተ ካሳሁን
  ለ. መ/ር ይትባረክ ታከለ
  ሐ. ዲ/ን ዋለልኝ ተገኘ
  መ. መዘምር ብርሐኑ ልየው
  10ኛ. ያለምንም ማስታወቂያና ቃለ ጉባኤ የሚከተሉት ሰራተኞችን የደረጃ ዕድገት እንዲሰጣቸውና አዲስ ቅጥር እንዲቀጠሩ ፈቅደዋል፡-
  ሀ. ዲ/ን ቀለሙ ተጻፈ (ከዲቁና ወደ ተላላኪነት)
  ለ. ፍቅሩ አበቤ
  ሐ. ይበሉ ዳኛው (የሚስቱ ወንድም)——ከተላላኪነት ወደ ንብረት ክፍል ፀሐፊነት
  መ. ባንቴ ውበቴ
  11ኛ. ቄስ ተከስተ ካሳሁን ራሳቸው ቀጣሪ ራሳቸው ደሞዝ መዳቢ በመሆን ለካህናት ዝቅ ያለ ደሞዝ ሲደለድሉ ለራሳቸው ግን ከፍ አድርገው መድበዋል፡፡
  12ኛ. ቤተ ክርስቲያኑ ድጋሜ እንዳይሰራ ክፍለ ከተማና ፖሊስ ጣቢያ ፈርመዋል፡፡ ለዚህም ከቦሌ ክ/ከተማ ክቡር ስራ አስፈጻሚ ከአቶ ዮሐንስ ዘንድ ማስረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የክፍለ ከተማ አመራሮችን “በመተት ነው የምጨርሳችሁ” በማለት አስፈራርተዋል፡፡
  13ኛ. እንደተለመደው እጅ መንሻ ጉቦ ሲሰጥ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡ ለዚህም ማስረጃ የቅዱስ ፓትሪያርኩ ልዩ ጸሐፊ አቶ ታምሩ እና መ/ጌታ ይርጋ ጌትነት እንዲሁም መ/ር ይትባረክ ሊመሰክሩ ይችላሉ፡፡
  14ኛ. ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ጥላ፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ ዘቢብ፣ እጣንና ልዩ ልዩ ንዋየ ቅድሳት በሞዴል 19 ገቢ ሳይሆን ያለምንም ቃለ ጉባኤና ውሳኔ ሸጠዋል፡፡
  15ኛ. ነሐሴ 13 ቀን 2005 ዓ.ም የገባ ወርቅና የቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት እንዲሁም መስከረም 18 ቀን 2006 ዓ.ም. የገባ ንዋየ ቅድሳት ግማሹ ሞዴል 19 የነካው ግማሹ ያልነካውን ያለምንም ውሳኔ እራሳቸው ከቀጠሩት ቁጥጥር ጋር በመሆን ሸጠዋል፡፡ ለዚህም ከንብረት ክፍሉ መረዳት ይቻላል፡፡
  16ኛ. ለቦሌ ክ/ከ ወረዳ ቤተ ክህነት ሰበካ ጉባኤ እንዲመረጥ ተጠይቆ ወረዳውም የቤተ ክርስቲኑን ጥያቄ አክብሮ እንዲያስመርጥ የተጻፈውን ደብዳቤ አፍነው እንኳንስ ለካህናትና ለአካባቢው ምእመናን ይቅርና ዋና ፀሐፊው ሳይሰማ አስመራጮችን በድብቅ አምጥተው የንስሐ ልጆቻቸውንና ወዳጆቻቸውን አስመርጠዋል፡፡
  17ኛ. ሕጋዊ ማህተም በፀሐፊው እጅ እያለ ሌላ ማህተም አስቀርጸው ሲሰሩ ተገኝተዋል፡፡ ለዚህም በሕገወጥ ማህተም የተጻፈ ደብዳቤ በማስረጃነት ተያይዟል፡፡
  18ኛ. ለሰራተኛ ደሞዝ ሳይከፈል ያለምንም ቃለ ጉባኤና ውሳኔ ለአስተዳዳሪው 300 ብር፣ ለቁጥጥሩ 200 ብር፣ ለሂሳ ሹሙ 200 ብር እንዲሁም ለሌሎቹ 150 ብርና 100 ብር እየከፈለ መሆኑና ከዐውደ ምሕረት የተሰበሰበውን ገንዘብ ቆጠራ ሲደረግ አሳማኝ ያልሆኑ ወጭዎችን አውጥቻለሁ ወዘተ… በማለት በየጊዜው ገንዘብ ይወስዳሉ፡፡
  19ኛ. የቁጥጥሩና የነገረ ፈጁ የስራ መደብ ተቃውሞ ስለቀረበበት መዘምር ብርሐኑ ልየው እንዳይመደብ በክቡር ስራ አስኪያጁ ታግዶ እያለ በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ሳይሰጥበት ቄስ ተከስተ በሕገወጥ መንገድ የቁጥጥር የሥራ መደቡን ለአቶ ብርሐኑ መድበው በወር 1060.00 ብር ደሞዝ መድበው ከፍለዋል፡፡ ይህ ሕገ ወጥ ተግባር ስለሆነ የከፈሉትን ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያኑ በደሰኝ ገቢ እንዲያደርጉና ቄስ ተከስተም በማይገባቸው ስልጣን ግለሰቡን በመጥቀም ስለፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር በሕግ እንዲጠየቁ፡፡

  ብፁዕ አባታችን! በቤተ ክርስቲያኑ ላይ ከፍተኛ ግፍና በደል እየተፈፀመ በመሆኑ እኛ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም የአካባቢው ኗሪዎችና የመስራች ኮሚቴ አባላት የምንጠይቀው ፍሬ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያኑ ለ4ኛ ጊዜ ከመፍረሱና በቤተ ክርስቲኑ ላይ ከፍተኛ ችግር ከመፈጠሩ በፊት፡-

  1ኛ. በቄስ ተከስተ ካሳሁን ምክንት ቤተ ክርስቲኑ ለአራተኛ ጊዜ ሊፈርስብን ስለሆነና በከፍተኛ ደረጃና በተደራጀ ሁኔታ እየተመዘበረ በመሆኑ ስልጣነ ክህነታቸው ተሸሮ ለስድስት ወራት የሙከራ ጊዜ በጊዜያዊነት የተሰጣቸው የአስተዳዳሪነት ስልጣን እንዲነሳና በምትኩ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ሰብሳቢ አባት እንዲመደቡልን፡፡
  2ኛ. በልማት ስም ከካህናትና ዲያቆናት የተቀበሉትንና በቅጽና በባጅ እያሳተሙ የሰበሰቡትን ገንዘብ በደረሰኝ ለቤተ ክርስቲያኑ ገቢ እንዲያደርጉ፡፡
  3ኛ. ቤተ ክርስቲያኑ የቤተሰብና ዘመድ አዝማድ የግል ንግድ ድርጅት እስከ መሆን ስለደረሰ የቀጠሯቸው ዘመድ አዝማድ ከቦታው እንዲነሱልን፡፡
  4ኛ. አዲስ አስተዳዳሪ ከተመደበልን በኋላ ሕግና ሥዓትን በጠበቀ ሁኔታ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ እንዲካሄድልን፡፡
  5ኛ. ከእሱ ጋር ተባባሪ ያልሆኑትን ካህናትንና ዲያቆናትን “ከስራ አባርራለሁ፤ ወደ ጠበልና ጽዳት ክፍል ዝቅ አደርጋለሁ፣ ወይም ወደ ሌላ ቦታ አዛውራለሁ ወዘተ….ፀሐፊውን በአስራ ሁለት ቁጥር ሚስማር መትቸዋለሁ ለእናንተም ዛሬ ቢጫ ሰጥቻችኋለሁ ነገ ቀይ እሰጣችኋለሁ” በማለት ስለዛቱ ካህናትና ዲያቆናት ከስራቸው እንዳይፈናቀሉ ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው፡፡
  6ኛ. ግለሰቡ በሙስና ወንጀል እንዲጠየቁልንና ሕጋዊና አስተዳደራዊ ርምጃ እንዲወስድባቸው ስንል በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እንጠይቃለን፡፡

  ከመንፈሳዊ ሠላምታ ጋር

  የአካባቢው ምዕመናንና ምዕመናት
  ግልባጭ፡-
  – ለቅዱስ ሲኖዶስ
  – ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት
  – ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ
  – ለቦሌ ክ/ከ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
  አዲስ አበባ

  አባሪ፡———–ገጽ ፎቶ ኮፒ

 5. H/Mariam December 27, 2013 at 7:35 am Reply

  ሕዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም

  የቦሌ ለሚ(ሰሚት) ምዕመናንና ምዕመናት
  ግልባጭ፡-
  – ለቅዱስ ሲኖዶስ
  – ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
  ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት
  – ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ
  – ለቦሌ ክ/ከ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
  አዲስ አበባ

  አባሪ፡———–ገጽ ፎቶ ኮፒ

 6. Anonymous December 27, 2013 at 10:27 am Reply

  ሐራዎች! እኔ የሚገረመኝ የምትጽፉት ሁሉ ስለገንዘብ ሌብነት እዚህች ምድር ላይ አራግፈን በአንድ አንሶላ ተጠቅልለን ለምንጣልባት ጉዳይ ብቻ ትቸከችካላችሁ፡፡ መቼ ነዉ ወንጌል ከህዝቡ ተሰረቀ ሕዝቡ ወንጌልን እንዳይማር ችሎታ ያላቸዉ ሰባክያን እየተሳደዱ ነዉ፡፡ ከወንጌል ጥማት የተነሳ ወጣቶች ወደ ሌላ ቤተ እምነት እየጎረፋ ነዉ በላችሁ የምታላቅሱትና ይህ ፀረ ወንጌልነት እንዲቆም የምትታገሉት፡፡ ያልበላንን የምታኩልንና የዲያብሎስን ዉክልና ለመወጣት መቻኮል ይዛችሁዋልና ይቅር ይበላችሁ፡፡

 7. Haymanot Ret'et December 31, 2013 at 12:33 pm Reply

  I personally would like to appreciate that you, the Hara Team have great concern over the systematic upgrade of the church. Keep on advocating.

  But the primary agenda which needs critical and carefull insight is being left aside. Currently the ‘reformationist residue’ is being given crucial devastating role. The start being conducted at Bonga is the start of the extreme danger. Once the church is under such big pressure the result will be the worst in the history. Begashaw is given podium sorrowly. You need to fight ahead…….

 8. Solomon December 31, 2013 at 1:06 pm Reply

  I do second Haymanot. Great idea and concern. Probabaly head of all concerns should be fighting the residual reformationists.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: