‹‹እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጡ ተቃዋሚዎች ከ‹‹ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ጋራ በየዕለቱ እየተገናኘን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሰን ሕንፃውን እንረከበዋለን›› እያሉ ነው – ‹‹ከእናንተ ጋራ መሣርያችኹ ቢኖርና በመሣርያችኹ ብትመኩም ከእኛ ጋራ ደግሞ እግዚአብሔር አለ፤ አንፈራም፤ ከዚህ በኋላ ለውጡ ወደኋላ አይመለስም፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/

Akaki Kality Qirqos Lideta subcities

የአቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ ቂርቆስና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ገዳማትና አድባራት ልኡካን በጥናታዊ ውይይቱ ወቅት (ፎቶ: አዲስ አበባ ሀ/ስብከት)

 • የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመሸጥ የሚታወቁት የ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባዮቹ ዋነኛ አስተባባሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ፣ በቅርቡ በ1.3 ሚልዮን ብር በገዙትና ለቻይና ተቋራጭ ባከራዩት ሲኖ ትራክ መኪና ብቻ በወር ብር 70,000 ገቢ ያገኛሉ፤ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ለውጥ ለማምጣት የተነሡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተንገላቱበት የግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም. ጥቃት የተሳተፉትና ሞዴል ፴ በማቃጠል የሚታወሱት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች ጋራ ስልታዊ ግንኙነት መጀመራቸው የሚነገርላቸውና ለአፃዌ ኆኅትነት እንኳ ሳይበቁ በደ/ምሕረት ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እልቅና ለመሾም ‹‹መቶ ሺሕ ብር እከፍላለኹ›› በሚል ልጆቻቸውን ለረኀብ የዳረጉት መልአከ ብሥራት መልአከ አበባው (ብይዱ ይመር)ስ እነማን ናቸው?

*         *        *

 • የካህናቱን፣ የሊቃውንቱን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የምእመናን ተወካዮችን ከ92 – 97 በመቶ ድጋፍ ያረጋገጠው የአ/አ ሀ/ስብከት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናታዊ ውይይት ዛሬ ይጠናቀቃል፤ የጥናቱን ትግበራ የሚቆጣጠር በአፈጻጸምም እየተከታተለ የሚያርምና የሚያስተካክል ራሱን የቻለ አካል እንዲቋቋም ተሳታፊዎቹ በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡
 • ‹‹ይህ መዋቅር አደረጃጀት ስለ መታሰቡ፣ ቅንብር ስለ መደረጉ በቤቱ ስም አመሰግናለሁ፡፡ አባታችን የልማት አርበኛ ናቸው፡፡ በየመንደሩ ያለው አሉባልታ ይህ ነው አይባልም፤ እዚህ ስናየው ግን የተለየ ነው፡፡ የጥናት ዘገባው ቀጥሎ እንድናየው እንጂ ሁከት አያስፈልግም፡፡ ጀርባዬም ፊቴም አንድ ከኾነ በሕግ ለመተዳደር ምን ያስፈራኛል? አስቀድሞ ይህ እንዲህ ይኾናል እያሉ መደንበር ምን ያስመለክታል? ወጡም ሊጡም እያሉ ያሉት ጉዳቸው እንዳይጋለጥ ነው ይህ ኹሉ ጭፋሮ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና ለመጠበቅ ከፍተኛ ሓላፊነት ያለበት ቅ/ሲኖዶስ ይውጣ ያለውን ሕግ መደገፍ ተገቢ ነው!!›› /የደብር አስተዳዳሪ/
 • ‹‹አንድ ድጓ ከዲግሪ ጋራ ይወዳደራል ካላችኹ መቼ ነው እውን ኾኖ የምናየው? እውን ይኾናል ወይ? አምስት እንትን የምንላቸው ካልኾኑ በቀር ይህን የሚቃወም አይኖርምና ቶሎ ይተግበር፡፡ ብፁዕ አባታችን ከዚህ የበለጠ ምን ይጠበቃል? ይሄ ነገር ቶሎ የማይተገበር ከኾነና ወደ ኋላ የምታዘገዩት ከኾነ የልብ ልብ እንዲያገኙ ታደርጓቸዋላችኹ፤ እናንተም ተጠያቂዎች ትኾናላችኹ፡፡›› /የመምህራን ተወካይ/
 • ‹‹የማይነካው ተነካ፤ የዘመናት ጸሎቴ ነበር፤ ፍጻሜውም ዛሬ ዛሬ. . .ይለኛል፤ እንግዲህ ጸሎተ ስምዖንን ነው የምጸልየው፤ ጌታዬ የቤተ ክርስቲያንን መዳን አሳይተኸኛልና ባሪያኽን አሰናብተኝ እለዋለኹ፡፡›› /የምእመናን ተወካይ/

ተጨማሪ መረጃውን ይከታተሉ

Advertisements

34 thoughts on “‹‹እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል›› ያሉ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጡ ተቃዋሚዎች ከ‹‹ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ጋራ በየዕለቱ እየተገናኘን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሰን ሕንፃውን እንረከበዋለን›› እያሉ ነው – ‹‹ከእናንተ ጋራ መሣርያችኹ ቢኖርና በመሣርያችኹ ብትመኩም ከእኛ ጋራ ደግሞ እግዚአብሔር አለ፤ አንፈራም፤ ከዚህ በኋላ ለውጡ ወደኋላ አይመለስም፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሉቃስ/

 1. Anonymous December 23, 2013 at 7:55 am Reply

  Temesgen Amlak hoy!!

 2. Eshetu Haile December 23, 2013 at 9:08 am Reply

  You are doing good. Be strong for the realization of the progressive change.

  • ሐ/ጊዮርጊስ December 23, 2013 at 10:11 am Reply

   በርቱ!

 3. ሐ/ጊዮርጊስ December 23, 2013 at 10:07 am Reply

  የትኛዉም ለዉጥ የራሱ ተግዳሮቶች ይኖሩታል፡፡ ተግዳሮት የግድ ነዉ፡፡ ብጹአን አባቶቻችን እርፍ ይዞ ወደፊት እንጂ ወደሓላ አይባልም፡፡ለዘመናት ስንመኘዉ የነበርነዉን የለዉጥ ጭላንጭል በእናንተ ቆራጥ አመራር በማየታችን ደስታችን ወደር የለዉም፡፡እባካችሁ ከዳር አድርሱት!

 4. ፍቅርተ ድንግል December 23, 2013 at 10:35 am Reply

  ማንም ምን ይበል ፈጣሪ ሥራውን እየሰራ ነው ፍጻሜን እንዲያሳምረው መጸለይ ነው

 5. Anonymous December 23, 2013 at 11:34 am Reply

  የ ቀደምት አባቶቻችንን ጥንካሬ ን ፅናት በዚህ ዘመን ልናይ ነው መሰለኝ ? እግዚአብሔር ከቤተክርስቲያን ተለይቶ ስለማያውቅ ዛሬ መናፈቃንንና የውስጥ አርበኞቻቸውን ጠራርጎ የሚያስወጣበት ዘመን ደርሷል ::አባቶቻችንን እግዚአብሔር ይርዳቸው ምዕመኑም በፀሎት መትጋት አለበት ::

 6. Musietselim December 23, 2013 at 12:50 pm Reply

  May God be with you our fathers!

 7. በአማን ነጸረ December 23, 2013 at 1:16 pm Reply

  1. እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል……….ያሉ……..
  ማህበረ-ቅዱሳንን አፍርሰን ህንጻውን እንረከበዋለን…….እያሉ…..
  ከዚህ በሁዋላ ወደሁዋላ አንመለስም…………………ተባሉ….
  ያሉ + እያሉ + ተባሉ=አሉባልታ፡፡ማስረጃ የለማ!!!
  2. እነዚህ በሙሰኝነት ምትከሱዋቸው ሰዎች ሙሰኛ መሆናቸው ብቻ የግድ የሚናገሩትን ነገር ሀሰት ያደርገዋል ብላችሁ እንዳትሳሳቱ፡፡ እመኑኝ!!! ለውጡን ከሚደግፈው ይልቅ የሚቃወመው እንደሚበዛ ለማወቅ ከፈለጋችሁ በቀላሉ በአ/አ አጥቢያ አ/ክርስቲያናት ከሚገኙ ካህናት ውስጥ ዝምብላችሁ በተለያየ መንገድ 10ሩን ጠይቁዋቸው፡፡ ቢያንስ 7ቱ እንደሚቃወሙት ትረዳላችሁ፡፡ በገሀድ የማይናገሩት እናንተ ስማቸውን እንደጠቀሳችሁዋቸው ሰዎች በገንዘብ አቅም ስላልዳበሩ ለእንጀራቸው በመፍራትና የእናንተን ጭፍን ማሳደድ በመሰቀቅ እንጅ አብዛኞቹ ጥናቱን ተቃውመው ፈርመዋል፡፡ይቺ እንግዲህ እኔ በሳምፕሊንግ ሜተድ የሰራሁዋት ሚጢጢ ጥናት መሆኑዋ ነው!!!
  3. ወደምትከሱዋቸው ሰዎች ስመለስ: እነዚህ ሰዎች ለአመታት በመሀከላችን ሲኖሩ አንድም ቀን እንኩዋ ስለሙሰኛነታቸው ሳትነግሩን ከርማችሁ ዛሬ የእናንተ ተቃዋሚ ሆነው ሲቀርቡ ንብረታቸውን ማስቆጠር መጀመራችሁ ወትሮውንም ‘ማህበሩ የቤ/ክንን ጥቅም የሚለካው በራሱ ጥቅም ልክ አድርጎ ነው’ ስንል የምናማችሁን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ለቤ/ክ ብታስቡማ ስርቆት እንደተፈጸመ ወዲያውኑ የሰውና ሰነድ ማስረጃ ሳይጠፋ ታጋልጡ ነበር፡፡ ሆኖም የእናንተ አላማ ጳጳሳትንም ሆነ አለቆችን የገበናቸው እስረኛ በማድረግ አፋቸውን በማፈንና ጥቂቶች ከዚህ አፈናችሁ ሲያፈነግጡም ገመናቸውን በአደባባይ በማስጣት መቀጣጫ አድርጎ እንደልብ በቤ/ክ ለመናኘት ነው፡፡ ለእውነተኛ ለውጥ ቢሆንማ እስከ ጉድፋቸው በጉያችሁ የተደበቁትንም ገሀድ ታወጡአቸው ነበር!!!መ/መንክራት ሀይሌ እኮ እናንተ እንምትስሉት ጭራቅ ግለሰብ ሳይሆን በየሄደበት ስሙ በተግባር ሰውነት የሚነሳ ነው፡፡ ጠይቁ ፉሪ ሃና – ደብሩን ከአመታት ጉስቁልና ኑሮ እንዳወጣው ይነግሩዋችሁዋል፣ጠይቁ ብሄረ ጽጌ ማርያም – ለሀያ አመታት ህንጻ ቤ/ክ አቁመው ለግላቸው ሀብት ሲያካብቱ የኖሩ ባላባት ነን ባይ ትምክህተኞችን አስወግዶ የቤ/ክኑን ህንጻ አራት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በማስፈጸም ለሰፊው የቤ/ክ ይዞታ ካርታውን አስወጥቶ በክብር መሄዱን ይነግሩዋችሁዋል፣መሀል ከተማ ተቀምጦ የረባ ልማት ላልነበረው ብ/ገብርኤል ባጭር ጊዜ ያማረ የት/ቤት ህንጻ ማስገንባቱንም እንዳትረሱት!!!አውቃችሁ ብትረሱትም ስራው ይናገራል!!! “ህንጻ ወውሉድ የዐብዩ ስመ” ነውና!!!
  4. በጳጳሳት እንግልት የተሳተፉ፣ከፕሮቴስታንት ብሎግ ጋር የሚገናኙ፣፻ሺህ ብር ጉቦ የከፈሉ፣ሞዴል፴ ያቃጠሉ፣ለአጻዌ ሆህትነት የማይበቁ የምትሉዋቸው ሰዎች በሲኖዶስ ታምኖባቸው የተሾሙ አባቶች እንጅ መንግስት ቤ/ክ ላይ የጫናቸው የመ/ት እንደራሴዎች አይደሉም፡፡ በተለይ የጉቦውንና ደረሰኝ ቃጠሎውን ጉዳይ ለህግ ማቅረብ ሲገባችሁ ባለማቅረባችሁ ‘የወንጀልን ድርጊት አይቶ ባለመጠቆም’ ራሳችሁም መከሰስ አለባችሁ፡፡ለማንኛውም የአባቶቻችን የብቃት መመዘኛ ማህበር የመደገፍና ያለመደገፍ ጉዳይ ነው ካልተባለ በቀር ‘ሊቀ ሊቃውንት’ የሚል ማዕረግ ይዘው ግዕዝ የማይሰሙ የእናንተ ደጋፊ አለቆች እንዳሉም እናውቃለን ፡፡ስናውቅ አንተላለቅ!!!

 8. Anonymous December 23, 2013 at 1:29 pm Reply

  WE ,ALL SUNDAY SCHOOL,START TO HELP THIS STRUCTURAL REFORM.

 9. Anonymous December 23, 2013 at 2:06 pm Reply

  God be with us.

 10. Anonymous December 23, 2013 at 2:17 pm Reply

  Ebakachehu Band lebe honene Enetselie. Legeziabhere Hulu Yechalalena.

 11. ሐ/ጊዮርጊስ December 23, 2013 at 2:18 pm Reply

  መልካም ስራ ስሰራ ሰይጣን በእጥፍ ፈተና፡ ዉሸት ያበዛል፡፡ ነገሮች የፖለቲካ ይዘት ያላቸዉ አድርጎም ያቀርባል፡፡ ዋነኛዉ የሰይጣን ቀኝ እጅ በመሆን በዚህ ዘመን የሚሰራዉ ደግሞ የአባሰላማ ብሎግ ነዉ፤፤ለቤተክርስቲያን ዉድቀት ከምን ጊዜም በላይ ተግቶ ይሰራል፡፡አባቶችንም ያዋርዳል፡፡ ሰይጣን ቅዱሳንን ለመሳደብ በአባ ሰላማ ብሎግ በኩል አፉን ከፍተል፤፤ ማስተዋል ይገባል፡፡

 12. WOLET MARIAM December 23, 2013 at 2:25 pm Reply

  Hulune Lemichel Amlakachen Besome Beselot enelemenew Ymeneshawn melkam neger hulu yaderglenal. EMEBETACHNEM KELEGUA KEWEDAGEWA TAMALDEN. LeAbatochachnem Bertatune Yestelen.

 13. Mesfin T/wold December 23, 2013 at 2:55 pm Reply

  May the Almighty GOD be wtih ours Holy fathers

 14. Birhen Mezgebu December 23, 2013 at 4:39 pm Reply

  beru egziyabhar yagzashuwa

 15. Birhen Mezgebu December 23, 2013 at 4:41 pm Reply

  yabatochachin amilak yrdachihu

 16. Ambachew December 23, 2013 at 4:53 pm Reply

  ‹‹ ከዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ጋራ በየዕለቱ እየተገናኘን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳንን አፍርሰን ሕንፃውን እንረከበዋለን፤ እስከ አፍንጫችን ታጥቀናል፤… ›› የሚሉት ሰዎች እነማን ናቸው? ብሎ መጠየቅ የዋሕነት ነው፡፡ ማንነታቸውን ከግብራቸው/ከሥራቸው ማወቅ ቀላል ስለሆነ፡፡

  ነገር ግን እነዚህ ሰዎች አንድም የመንግስት ባለሥልጣናትን ተገን አድርገው ማስፈራራታቸው፣ ለመንግስትም፣ ለራሳቸውም አሉታዊ ጎኑ ይበረታል፡፡ ያሉት እውነት ከሆነ መንግስት በራሱ ጊዜ በሚሊዮን ከሚቆጠር አማኝ ጋር እየተጣላ ስለሆነ ራሱንና ሥልጣን የሰጣቸውን ሰዎች ማየት አለበት፡፡ ውሸት ከሆነ ደግሞ እነዚህን ሙሰኞች፣ ምግባረ ብልሹዎችና የለውጥ አደናቃፊዎች አፍ መዝጋት አለበት፡፡ ይህ የሚታወቀው ደግሞ ለለውጡ እውቅና በመስጠትና በሃሳብም ሆነ በተግባር በመደገፍ ነው፡፡

  ሐራ ዘተዋህዶም ስለ ለውጡ ተቃዋሚዎች አብዝቶ ከመዘገብ መቆጠብና ስለ አደረጃጀት ለውጡ፣ ስለአጠቃላይ ጥናቱ ዘገባ በማቅረብ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩት ምዕመናን የግንዛቤ ማሳደግ ሥራ መስራት የተሻለ ነው፡፡ ምናልባት ሌላ የከፋ አሉታዊ ጎን ከሌለው ማለቴ ነው፡፡

 17. Anonymous December 23, 2013 at 7:20 pm Reply

  “ይሄይስ ተአምኖ በእግዚአብሔር እምተአምኖ በሰብእ” ነውና ነገሩ ለሁሉም ሁኔታውን በእርጋታ መመልከት መልካም ነው። የሰውማ ነገር የሰው ነው ዛሬ ታይቶ ነገ የሚጠፋ ስለዚህ ብዙ አያስጨንቅም። የዚች ቤተ ክርስቲያን አማኞች ሁሉ ነገራችንን ወደ እግዚአብሔር ማመልከት ብቻ ነው የሚጠበቀውና ሁላችንም በያለንበት ለበጎ ነገር እንትጋ። የተሰናከሉትም ወገኖች መልካሙን ልብ እግዚአብሔር መልሶላቸው ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ ነገርን እንዲያስቡ ፈቃዱ ይሁን።

 18. Anonymous December 23, 2013 at 8:47 pm Reply

  This is a good beginning: we are not done. we have to expect more and more challenges from different parties against the reform; since manys who live milking the treasure of the church are shouting. And, there are people who have anti-church strategy obviously oppose the reform. However, as we are Christians, we have to show our support by praying, creating a know -how about the reform to every member of the church.

 19. Anonymous December 24, 2013 at 5:50 am Reply

  መች ይሁን ቤተክርስትያን እረፍትዋ ……ያውም በገዛ ልጅዋ ……..በእውነት ያሳፍራል ምን አይነት ጊዜ ላይ ደረሰን ጎበዝ……….እንዴ ኑሮ ባይደላን ለምንድነው በእምነታችን እማንጽናናው……..ቤተክርስትያን ጥብቅ የሆነ አመራር ባሁን ሰዓት ያስፈልጋታል…….ከየትኛው እምነት የተሻለ ሀብት አላት…..ግን ይባክንባታል……ለምን…….ምን ያህል እድሜ ለምንኖረው ነው ይህ ሁሉ…….አሁስን ይብቃን ጌታ ሆይ፡፡

 20. ተቋማዊ ለውጡን መቃወም ለምን? December 24, 2013 at 7:26 am Reply

  @በአማን ነጸረ
  የማኅበረ ቅዱሳንን ሕንጻ አንወርሰዋለን “አሉ”። ሲል አማርኛው አሉባልታ አደለመ ተናገሩ ማለት ነው።አሉባልታ ለመሆን “እያሉ ነው አሉ” ተብሎ ከተጻፈ ነው።
  ወይስ የተቀዳ የተጸፈ ማስረጃ ነው የምትፈልገው?ከተሃድሶ ብሎግ ሂድና ፈለግ አታጣውም አታች አድርገውልኻል።
  ካህናት ለውጡን ተቃውመዋል ብለኻል።ለምን ተቃወሙ?
  ሲወያዩበት ምን እንከን አገኙበት?ልታብራራልን ትችላለህ(ያው መቃወማቸውን ካወቅህ ይህንንም ምክንያት ማወቅ አለብህ)
  እነዚህ በገንዘብና በአቅም የበለጸጉት ደፍረው መቃወም ጀመሩ ካልከን ጎሽ አንተው መሰከርክ።በአቅምና በገንዘብ የበለጸገው ቢቃወም ምን ይገርማል(ከደከመው የቤተክርስቲያን አስተዳደር ተጠቃሚ ነበርና ይቃወመዋል)።
  ካህናት የለውጡን ፋይዳ ተረድተው፤ ገብቶአቸው ግን ለውጡን ስለማይፈልጉት ተቃወሙት ብትል ማን ያምንሃል።
  ተቃውሞ ሊኖር ይቻላል። በተለያየ ምክንያት
  1- ባለመረዳት
  2- ለውጥ በራሱ ተቃውሞ እንደሚገጥመው የሚጠበቅ ስለሆነ(ከዘልማዳዊ(ባህላዊ) አሰራር መውጣት ያለመፈለግ ዳተኝነታችን)
  3- ተቋማዊ ለውጡ ጥቅምን(አላግባብ የሚገኝ) ስለሚያሳጣ
  4- ሐሳውያን በተራ ቁጥር ሦስት የተጠቀሱት በሚነዙት ወሬ
  ነገር ግነ በቅንነት ሊነቀፍ የሚገባ ነገር እንዳለው አውቀው የሚያርሙ የሚተቹ ካሉ እንደደጋፊ እንጂ ተቃዋሚ አይታዩም።

  አንተ ለምሳሌ መ/መንክራት ኃይሌን አወድሰህ ተቃውሞው ልክ ነው ልትለን ሞክራኻል።እስቲ ሌላ የሚያውቃቸው ምን ይለናል?።
  እኔ ደግሞ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራን(ከተቃዋሚዎቹ አንዱን አለቃ) ጠቅሼ ቤተክርስቲያንን እንዴት እንዳዳከሟት አስረድቼ የተቃውሞዋቸው ዓላማ ልተነትንልህ እችላለሁ።
  እስከዛሬ ሳትነግሩን ላልከው እንከዛሬ ያስለቅሱን የነበሩትና ብዙ የተነገረባቸውን ዛሬ ነው አንተ ማንበብ የጀመርከው?
  በነገራችን ላይ እነኚህ አሁን የሚጮኹት አለቆች በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ሥር የሰደዱ ቤተክርስቲያኗን ያሽመደመዱ እንደነበር መዘንጋት የለበትም።
  ግንባታ ትቆጥራለህ።
  ሰው፣ሥርዓት፣ሃይማኖት እያጠፉ ልማት(ግንባት?) መሥራት አቡነ ጳውሎስም ተክነውበት ነበር።

  “የወንጀልን ድርጊት አይቶ ባለመጠቆም” አልክ
  አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ማንን ለማን እንክሰስ?
  አሁን በር ተዘጋብን እያሉ ወደመንግስት እየጮኹ ያሉት በር ዘጊ የነበሩ ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማደከሟ ተጠያቂ የሚሆኑ ናቸው።

 21. ቀለመወርቅ December 24, 2013 at 7:57 am Reply

  1. በእምነታቸው ጥብቅ የሆኑ ሰዎችን አደንቃለሁ!!! አኔም አቅሜ በፈቀደ ሁሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ስርአትን እንደ አንድ ተራ ምእመንም ሆነ እንደ ማህበረ-ምእመናን አባልነቴ ለማስፈጸም እተጋለሁ ፡፡ዘመናዊ ትምህርት የቀመሱ ሰዎች ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በቤተ-እግዚአብሄር ሲያገለግሉ ሳይ ልቤ በሀሴት ይሞላል፡፡
  2. እኔን ቅር የሚለኝና አንዳንዴም ዘመናዊ ት/ት መስጫ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎቻችንን የት/ት አሰጣጥ ምታዘበው አባል የሆኑበት ማህበር ተነካ በተባለ ቁጥር ሃይማኖት እንደተነካ ተደርጎ የሚቀርብን ዜና መቼ፣የት፣እንዴት፣ማን፣ለምን በሚሉ መሰረታዊ የሀቅ ማጣሪያዎች ግርዱን ከገለባ ሳይለዩ ዘለው ከዚህ በፊት የማያውቁዋቸውን ግለሰቦች ያውም አባቶችን በልዩ ልዩ ስም በአንድ ድምጽ ሆነው የሚያወግዙ የከፍተኛ ተቁዋማት ምሁራንን ሳይ ነው፡፡
  3. አሁን የቀረበው በዳግም እይታ ሊከለስ ሊሻሻል የሚችል የአስተዳደር ጥናት ሆኖ ሳለ ልክ ትምህርተ-ሃይማኖት ይመስል ጥናቱን የመቀበልና ያለመቀበል ጉዳይ የሀጥአንና የጻድቃን፣የአረማዊና የክርስቲያን፣የምእመንና የመናፍቅ፣የሀቀኛ እና የሙሰኛ መለያ እንደሆነ ተደርጎ ይሄ ሁሉ ዘመናዊ ምሁር ከዚህ የተለየ ድምጽ ላለመስማት ጆሮውን ሲይዝ ሳይ አዝናለሁ!!!ተቁዋማቱን እጠይቃለሁ!!!
  4. የት/ት ተቁዋሞቻችን ለግሬድ ብቻ የሚጨነቁ ደረቅ አካውንታንት፣ደረቅ ኢንጅነር፣ደረቅ ማኔጀር፣ደረቅ ሎየር፣ደረቅ አስተማሪ፣……ወዘተ ከማፍራት በቀር ተማሪዎቹ ከሚያጠኑት የት/ት አይነት ውጭ የሆነና ምሉእ ስብእናቸውን በመገንባት ምክንያታዊ ዜጋ(reasonable person) ሆነው የሚወጡበት ተጨማሪ ንባብ የሚያነቡበት መንገድ ስላልተመቻቸ ከተመረቁበት የት/ት አይነት ውጭ ባለ አስተሳሰባቸው (ህ/ሰቡ ለምሁራን ባለው የቀደመ አስተሳሰብ ትልቅ ቦታ ቢሰጣቸውም) ከመሀይምናኑ የማይሻሉ ስለመሆናቸው በየሄድንበት እያየናቸው ነው ፡፡
  5. የማህበረ-ቅዱሳንንና የአባላቱን ሁኔታ ሳይም በቃ ይህቺ ሀገር በምሁር የተመሰረተ ማህበር አይውጣልሽ ተብላ ተረግማለች እላለሁ፡፡ ልጆቹ ያላቸውን ቅንነትና አገልግሎት፣በአንድነት ሆኖ ስለ ርእትእት ሃይማኖት መቆርቆር ካህናትን በመፈረጅና ግለሰቦችን በማሳደድ ወቅትም ያለ አንዳች ማቅማማትና ማወላወል ልክ እንደ ትምህርተ-ሃይማኖት ተቀብለው ስለሚያስተጋቡት በመሀሉ ብዙ እውነቶች በቡድን ውሸቶች እንዳይደፈጠጡ እፈራለሁ፡፡
  6. ልጆቹ ከተመረቁበት ትምህርት በዘለለ የተሻለ ምክንያታዊ ሰው ሊያደርግ የሚችል የት/ት ብቃት እንደሌላቸው ስታዘብና በመንፈሳዊ ትምህርትም በሰ/ት/ቤት ደረጃ ሊታይ የሚችል መሰረታዊ የትምህርተ ሃይማኖት ኮርስ ከመውሰድ ውጭ ያን ያህል በአብነት ት/ት ቤት ደረጃም ሆነ በቲዎሎጅ ደረጃ ሊታይ የሚችል ዝግጅት ሳይኖራቸው ይሄን ያህል የሃይማኖቱን አስተዳደር በመሰረታዊነት ሊቀይር የሚችል ጥናት ብቻቸውን እንዲያጠኑ መተዋቸውና እነሱም ብቻቸውን ለማጥናት ድፍረቱን ማግኘታቸው ያስደንቀኛል!!!
  7. በተለይ የእኛ አባላት ስለሆኑ በሚል ብቻ የጥናቱን ሂደትም ሆነ ይዘት ሳያዩ በጭፍን ሌሎች ጥናቱን አይተው የተቃወሙትን ግለሰቦች የሚያሳድዱ ቡድናዊ ግለሰቦች ሳይ “ልጅ ወለድኩ ይበል አባቴ“ በሚል ጸጋየ ገብረ መድህን ትውልዱን ነቅፎ የተቸበት ግጥም ትዝ ይለኛል፡፡የለውጡ አደናቃፊ የሚሉዋቸውን በጸጥታ ሀይል ሲያስፈራሩ ቆይተው መልሰው ደግሞ “እረ ሰዎቹ እስከ አፍንጫቸው ታጥቀዋል“ በሚል “ሀይል የእግዚአብሄር ነው“ እያሉ ከሎጂኩም ከፈጣሪም ሳይሆኑ ሲቀሩ አይ የኔ ትውልድ እላለሁ!!!ደግነቱ “ኢየሀድጋ ለሀገር ዘእንበለ አሀዱ ብእሲ“ የሚለው አምላካዊ ቃል አለና ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ራሱ ባለቤቱ ይጠብቃታል፡፡

 22. Anonymous December 24, 2013 at 8:30 am Reply

  በእምነታቸው ጥብቅ የሆኑ ሰዎችን አደንቃለሁ!!!

 23. Anonymous December 24, 2013 at 8:54 am Reply

  lewtu aydenaqefm!!!!

 24. ያለው December 24, 2013 at 9:28 am Reply

  ለነገሩ እንደነ መልአከ ብሥራት መልአከ አበባው (አቶ ይመር) አይነት ለትምህርት ያልታደሉ ለነገር ፤ለውሸት እና ለሌብነት የፈጠኑ በርካታ ጠንቅዋዮች በየ ደብሩ ተሰግስገዋል በይበልጥም እርሱ በሚኖርበት በሰዓሊተ ምህረት ቤ/ክ አካባቢ ያሉት ጸሀፊ እና ሂሳብ ሹም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሄር ለቤተክርስቲያናችን መልካሙን ሁሉ ያምጣልን

 25. Anonymous December 24, 2013 at 10:11 am Reply

  አይ በተክርስቲያን ወልዶ መና ሆንሽ ግን እነዚ ሰዎች እምነት አላቸው አግዚአብሔርን ያውቃሉ ??????????

 26. tesfaye December 24, 2013 at 10:13 am Reply

  አይ በተክርስቲያን ወልዶ መና ሆንሽ ግን እነዚ ሰዎች እምነት አላቸው አግዚአብሔርን ያውቃሉ ??????????

 27. Anonymous December 24, 2013 at 11:27 am Reply

  Dear Dn. Yemane Zemenfeskidus,

  I know you are writing this message. I was fallowing your comments starting from the first Hara report and I was there at the discussion hall when you present your complains on the “mewaker tinat ” at Addis Ababa diocese representing my Sunday school.

  First of all I really appreciate your courage to air out your complains at the hall ( even if you made it in the absence of Abune Estifanos and you didn’t appear in the second session). On the other hand your bald criticism that the study is totally immaterial and representing yourself as a fan of the 40 years old “Kale Awadi” was totally unexpected from you ( at least you are educated) unless you did it deliberately. It is obvious that you and your family ( your father, sister and sister husband) are benefiting a lot from this church. I quietly know the church is your ” Cash Cow” where you are getting money …..

  My big brother please come back to your heart!!! am sure that you quietly know your grievance. Moreover, you know who መ/መንክራት ሀይሌ is and what he was doing at least in Bisrate Gebreil. Let me remind you one thing.. As far as I know .. he is the one who took 4.5 Million birr loan from the bank in the name of the church and took it all for himself (nothing left to the church).And so on ..

  So my bro pls pls pls .. let us think about our church. Our fathers had left for us many many spiritual treasures but think about yourself. what are you doing for the church? …

  Forgive me if I make wrong
  Egziabher Amlak Lehulachinem Libuna Yisten Amen

 28. Anonymous December 24, 2013 at 4:58 pm Reply

  please be sustain and strive to get real picture of the church. it was clear that we were beaten by the previous leader of the church but still God is with Us

 29. በአማን ነጸረ December 24, 2013 at 4:59 pm Reply

  @ተቁዋማዊ ለውጡን መቃወም ለምን?
  1. አሉ…..እያሉ……ተባሉ….የሚሉ አገላለጾች ማን፣መቼ፣የት፣እንዴት፣በምን ሁኔታ እንዳላቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ አሁንም እለሀለሁ አሉባልታ ናቸው፡፡ተቀባይነት ያለው ማስረጃ የሚባለው በአይኔ አየሁ፣በጆሮየ ሰማሁ፣በምላሴ ቀመስኩ…ወዘተ በማለት በ5ቱ የስሜት ህዋሳት ሊረጋገጥ ሲችል እንጅ ከእንትና ሰማሁ በሚል ከ3ኛ ወገን ስለመሰማቱ እንኩዋ ምንጭ ያልተጠቀሰለት “ማስረጃማ” የስሚ-ስሚ የሚል የወሬ ማእረግ ስለማግኘቱም እጠራጠራለሁ፡፡እንግዲህ ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ጥቅሥ ለሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በሃይማኖት አስተዳደር ዙሪያ ለሚነዙ ወሬዎችም ያገለግላል ካልክ አላውቅም!!!ደግሞ ተሀድሶ የሚለውን ቃል ላንተ ያልተስማማ ሀሳብ በሰነዘረ ላይ ሁሉ አትለጥፈው፡፡ትስታለህ!!!እንዳልሆንኩ ፻፻፻፻፻፻፻፻፻፻፻፻፻ ጊዜ ስለምነግርህ!!!በአስተዳደር አይደለም. አባቶቻችን በዜማና በትርጉዋሜ እንኩዋ ልዩነታቸውን የላይ ቤትና የታች ቤት፣ቆሜና ቤተልሄም፣ተክሌና ጎንደሬ ወይም ፋኖ አቁዋቁዋም እያሉ የዜማ እና የትርጉዋሜ አካሄድ ልዩነታቸውን እንደ ሀይማኖት ልዩነት ሳቆጥሩ ተከባብረው ኑረዋል፡፡እናንተ ግን የእነሱን አሰረ-ፍኖት ስላልተከተላችሁ ገና ጸድቆ ባልወጣ ጥናት ተሀድሶ ካልሆነ በቀር እኛን የሚቃወም የለም ብላችሁ ራሳችሁን የሀጥዕ እና የጻድቅ መለኪያ በማድረግ ከጉልላቱ በላይ ወጣችሁ!!!እናም ጥያቄ ያነሳውን ሁሉ ትፈርጃላችሁ!!ገፍቶ ለማስወጣት እንጅ ማርኮ ለማምጣት አልታደላችሁማ!!!ይመስገነውና የውግዘት ስልጣን አልተሰጣችሁም እንጅ ቢሰጣችሁ ኖሮ የማህበሩን ስም በመልካም ያልጠራ ሁሉ ከዚህ በመለስ ይወገዝ ሳትሉ ትቀራላችሁ!!!
  2. ‘ካህናቱ ለምን ተቃወሙ??’ ላልከው: ስላልተሳተፉበት፣የሰው ሀይል ይቀነሳል ስለተባሉ፣ጥናቱ የማህበሩን የመደብ ጥቅም ለማስከበር የታለመ ነው የሚል ጥርጣሬ፣ጥናቱ በቃለ-ዐዋዲው ማይታወቁ አዳዲስ የስራ መደቦችን ፈጥሮ ቃለአዋዲውን በገቢር መሻሩ፣ሙሉጥናቱን ለማየት ስላልተፈቀዳቸው፣100ሺህ ገጽ ያለውን ጥናት በሁለት ቀን ስልጠና ካልተቀበላችሁ ስለተባሉ፣ሁሉም የጥናቱ አቅራቢዎች ‘አቶ’ መሆናቸው፣…..ወዘተ እልሀለሁ፡፡አንተ የጠቀስካቸው የተቃውሞ ም/ቶች በአጥኝዎችም ቢሆን ቀድሞ ታስቦባቸው በተገቢ ዝግጅት ሊመለሱ ሚችሉ ነበሩ፡፡ምን ያደርጋል ቤቱ የፍረጃ እንጅ የማስረጃ ቤት እንዲሆን የሚሰሩ ምሁራንን አላገኘም ወይም ማግኘት አይፈልግም፡፡በመሰረቱ ለውጥ የተፈጥሮም የዘመናዊ ኑሮም ህግ መሆኑ እውነት ነው፡፡ለውጦች ሁሉ መልካም ብቻ እንደሆኑ አለማሰብም ትክክል ነው፡፡ይሄ የለውጥ ጥናት ቢያንስ ከላይ የተጠቀሱት ጉድለቶች አሉበትና እስኪ ይፈተሽ ብሎ መጠየቅን እንደለውጥ አደናቃፊነት መቁጠር ግን ትክክል አይደለም!!!ጥናቱን ተችተው ለአብነት ስማቸው በበጎ የተነሳ ግለሰቦች አለመኖራቸውም የጉዳዩን በሆታ መዋጥ ያሳያል፡፡
  3. እኔ ጉዳየ ከተቃዋሚዎቹ ሳይሆን ከተቃውሞ ነጥባቸው ነው፡፡የተቀዋሚዎቹ በሙስና መጠርጠር የሚናገሩትን ሀቅ ሀሰት አያደርገውም፡፡እደግመዋለሁ፡፡የሰዎቹ በሙስና መጠርጠር ብቻ ዛሬ ሚናገሩትን እውነት ውሸት አያደርገውም፡፡አለቀ፡፡
  4. ሙት ወቃሽ ባንሆን ደስ ይለኛል፡፡አቡነ ጳውሎስ እኮ መናፍቃኑ መቀበሪያ አጥተው ሲጮሁ እሳቸው ግን ለሚመሩዋቸው 120 የአ.አ አብያተ ክርስቲያናት ካርታና ይዞታ ያስወጡ፣የካህን ደሞዝ ከ60 ብር ወደ 2ሺህ ብር አድርሰው በየእለቱ “እግዚኦ አእርፍ ነፍሰ አቡነ ጳውሎስ” እየተባሉ በፍቅር የሚነሱ፣አንተም እንዳመንከው በልማት ዘመኑን የዋጁ፣ባስከፈቱዋቸው መንፈሳዊ ኮሌጆች ለቁጥር የሚያታክቱ ወጣት ሰባክያንን በማፍራት ሃይማኖታችን ለመታደግ የደከሙ፣በዐለምአቀፋዊ ሰውነታቸው ሀይማኖታችንን በየሄዱበት ያስተዋወቁ፣ ለሃይማኖቱ ባይተዋር ሆኖ ለኖረው ከሰሜን ኢ/ያ ውጭ የሆነ ህዝብ ከራሱ ብሄረሰብ ቁዋንቁዋውን የሚናገር ሰባኪ እየመለመሉ እስከ ጵጰስና ያበቁ ድንቅ የቤ/ክ አባት ነበሩ፡፡የሳቸው ጥፋት ተደርጎ ሁሌ የሚደሰኮረው ለመንግስት ይወግናሉ በሚል ነው፡፡ነገር ግን የእሳቸው ለመንግስት መወገን ለቤ/ክ ካጎደለባት ይልቅ ያተረፈላት እንደሚበልጥ በቅርብ ጊዜ እንረዳዋለን፡፡
  5. በጽሁፍህ መ/መንክራት ሀይሌን እንደማታውቀው እየገለጽክ ዝቅ ብለህ ደግሞ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ቤ/ክ ሲያሽመደምድ እንደነበረ በመግለጽ የሌሎችን ፍረጃ ተከትለህ በማታውቀው ሰው ላይ ራስህን በምስክርነት በመቁጠርህ ሰማእተ-ሀሰትን ቀስፎ ሶስናን ያዳናት ሊቀ መላእክት ሰይፉን ከማንሳቱ በፊት ይህን በደልህን ለመምህረ-ንስሀ በመንገር ቀኖና ተቀበልበት!!!
  6. “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ስላልከው”….ግዴለህም ሞክር ፡፡ማስረጃ ካለ እንኩዋን ተራ ካህን እነ ገብረዋህድ፣መላኩ ፈንታ፣የደህንነት ሀላፊው ወልደስላሴ ሳይቀር ለፍርድ እየቀረቡ ነው፡፡የስርዐቱን ዳኞች ወገናዊነት ለማረጋገጥ ፍርድ ቤት ድረስ መሄድ አያሻኝም ካልክ ግን ስርዐቱን በማህበር ስም በቤ/ክ በመጠለል ሳይሆን ፓርቲ መስርተህ መርተህ ጣልና ፍትህ አትረፍርፍልን!!!ያንጊዜ እኛም “እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉስ” እያልን ስምህን በመዝሙረ ዳዊት እናነሳዋለን!!!ያለበለዚያ አንድ መኖሪያ ቤት ያለው ግለሰብ ቤቱን እያገለባበጠ በመሸጥ ብቻ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አትርፎ በሚቆጥርባት አ.አ ተቀምጦ ጥፋተኝነታቸው በፍርድ ቤት ያልተረጋገጠ ግለሰቦችን ገና ለገና መኪና አላቸው፣ቤት ሰርተዋል በሚል በየኢንተርኔቱ ስማቸውን መቦጨቅ ከረከቦት ዙሪያ ወሬ ያለፈ ትርጉም የሌለው በነፋስ የሚበን አሉባልታ ነው የሚሆነው፡፡ወንድማችን ዲ/ዳንኤል ክብረት የስድቦቻችንን ወደየብሎጎቹ፣ፌስቡክ፣ፓልቶክ መሰደድ በማስመልከት የጻፋት ጥሩ ጽሁፍ ነበረች፡፡ እባክህ ፈልገህ አንብባትማ!!!!እሱዋ በቃ ተግሳጽ በእንተ ጦማር ወጦማሪ/ት ነች!!!

 30. Anonymous December 24, 2013 at 5:00 pm Reply

  Do not be frustrated by the so called intruder

 31. Mitiku December 24, 2013 at 8:34 pm Reply

  Dingle direshelen

 32. Anonymous December 25, 2013 at 5:57 am Reply

  Dear Dn. Yemane Zemenfeskidus(በአማን ነጸረ)

  I know you are writing this message. I was fallowing your comments starting from the first Hara report and I was there at the discussion hall when you present your complains on the “mewaker tinat ” at Addis Ababa diocese representing my Sunday school.

  First of all I really appreciate your courage to air out your complains at the hall ( even if you made it in the absence of Abune Estifanos and you didn’t appear in the second session). On the other hand your bald criticism that the study is totally immaterial and representing yourself as a fan of the 40 years old “Kale Awadi” was totally unexpected from you ( at least you are educated) unless you did it deliberately. It is obvious that you and your family ( your father, sister and sister husband) are benefiting a lot from this church. I quietly know the church is your ” Cash Cow” where you are getting money …..

  My big brother please come back to your heart!!! am sure that you quietly know your grievance. Moreover, you know who መ/መንክራት ሀይሌ is and what he was doing at least in Bisrate Gebreil. Let me remind you one thing.. As far as I know .. he is the one who took 4.5 Million birr loan from the bank in the name of the church and took it all for himself (nothing left to the church).And so on ..

  So my bro pls pls pls .. let us think about our church. Our fathers had left for us many many spiritual treasures but think about yourself. what are you doing for the church? …

  Forgive me if I make wrong
  Egziabher Amlak Lehulachinem Libuna Yisten Amen

 33. Anonymous June 30, 2016 at 9:51 am Reply

  ድንቅ ነው ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: