ሰበር ዜና – ለደመወዝ ጭማሪ ጥናት ድጋፍ ለማግኘት በሚል በተጭበረበረ መንገድ የተሰበሰበ የካህናት ፊርማ የአ/አ ሀ/ስብከት የአስተዳደር መዋቅር ጥናት መቃወሚያ ኾኖ ለፓትርያርኩ ቀረበ፤ በጥናታዊ ውይይቱ ገና ያልተሳተፉ ሙሰኛ አለቆችና ሠራተኞች የተቃውሞው አካል መኾናቸው በተቋማዊ ለውጡ ላይ ያላቸው ጥያቄ በጥላቻና ጥቅመኝነት ላይ ብቻ መመሥረቱን አረጋግጧል

 • ሀ/ስብከቱ ከኑሮ ውድነት አንጻር በአጥቢያዎች ተሳትፎ እያስጠናው የሚገኘው ጊዜያዊ የደመወዝ ጭማሪ ማስተከከያ ጥናት በመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ ረቂቅ ውስጥ ካለው የአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት፣ የሥራ መደብ ግምገማ፣ የአገልጋዮች ጥቅምና ጫና ጥናት ጋራ አንዳችም ግንኙነት የለውም፡

 • ለፊርማ አቤቱታው የቀረቡት ጥያቄዎች ይዘት ‹ተቃዋሚዎቹ›÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከቃለ ዐዋዲ ደንቡ ጋራ ያለውን ልዩነትና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ላይ ያለውን ተፈጻሚነት በቅጡ ለይተው እንደማያወቁ፣ ስለ ለውጥ አመራር መዋቅርና አደረጃጀት ጥናት ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ፣ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በካህናትና ምእመናን አንድነት የተዋቀረ መኾኑንና ምእመናንም ድርሻ እንዳላቸው የማይቀበል፣ በፍትሕ ሥርዐት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ጉዳዮች በራሷ ተቋማት ለመዳኘት ያላትን ሉዓላዊነት የማያምንና ኦርቶዶክሳዊ ውግንና የጎደለው፣ የለውጡ ከፍተኛ ተጠቃሚዎች የሚኾኑት ካህናትና ሊቃውንት በተወሰነላቸው የተሳትፎ ቁጥር ልክ በጥናታዊ ውይይቱ እንዳይሳተፉ በጥቅመኛ አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች አፈና መፈጸሙ፣ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዕውቅና የሰጠውን የባለሞያ ቡድን ‹‹ኅቡእ አካል›› በማለትና የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትን ጥናቱን ‹‹የኅቡእ አካሉ የግል ፍላጎት ነው›› የሚል ዐመፀኝነት፣ በፓትርያርኩና በረዳት ሊቀ ጳጳሳቸው መካከል ቅራኔ ፈጥሮ የተቋማዊ ለውጥ ሂደቱን በመቆጣጠርና በማክሸፍ ሕገ ወጥ ጥቅምን ለመከላከል ያለመ መኾኑ የተጋለጠበት ነው፡

 • በወጣው የክፍላተ ከተሞች መርሐ ግብር መሠረት በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ሳይሳተፉ ጥናቱን ከተቃወሙትና ካህናትን በግዳጅ ለተቃውሞ ከሚያነሣሡት አስተዳዳሪዎች መካከል ጥቅመኛው የአፍሪቃ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ብሥራት መልአክ አበባው ይገኝበታል፡፡ በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ካህናት፣ ሊቃውንትና ሠራተኞች ስም በጸሐፊው ሊቀ ትጉሃን ሲሳይ ገብረ ማርያም የተሰበሰበው የተቃውሞ ፊርማ ገዳሙን እንደማይወክል ሊቀ ሊቃውንቱ አባ ኃይለ መስቀል ውቤ ለሀ/ስብከቱ በደብዳቤ ያስታወቁ ሲኾን የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል አስተዳዳሪም ዋና ጸሐፊው፣ ዋና ተቆጣጣሪውና ሒሳብ  ሹሙ በካህናቱ ስም አሰባሰብን ያሉትን ፊርማ በመቃወም ጥናታዊ ውይይቱን በጉጉት እንደሚጠብቁት ለጽ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡

YeEne Meleak Abebaw Tekawumo01

 • ከካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት አመራሮችና ምእመናን ተወጣጥተው በጥናታዊ ውይይቱ እንዲሳተፉ ለተጠሩ 16 ልኡካን በአግባቡ ጥሪውን ሳያስተላልፉ የአስተዳደር ሠራተኞችን ብቻ ይዘው ከተገኙትና በአጥኚው ቡድን ውስጥ ‹‹ካህናትና ሊቃውንት አልተካከተቱም›› በሚል ራሳቸውን በግንባር ቀደምነት ተቃዋሚ ካደረጉ የአጥቢያ አስተዳደሮች መካከል፡- ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ (5 ተሳታፊዎች ብቻ የላከ)፣ ድል በር መድኃኔዓለም (1 ተሳታፊ ብቻ የላከ)፣ ደብረ ቢታንያ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት(6 የቢሮ ሠራተኞች ብቻ የላከ)፣ መሪ ሎቄ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (4 የቢሮ ሠራተኞች ብቻ የላከ) መኾኑ ተረጋግጧል

 • የቅዳሜው የጥቂት ጥቅመኞች ኅቡእ ስብሰባ በሀ/ስብከቱና ኹኔታውን በቅርበት በሚከታተለው የፖሊስና የደኅንነት አካሉ መታወቁን ተከትሎ ተሰብሳቢዎች አንዳቸው ሌላቸውን በማጋለጥ ትርምስ ላይ ናቸው፤ ካህናቱና ሊቃውንቱም ባልተሳተፉበትና በማያውቁት ጥያቄ በአስተዳደር ሓላፊዎቹ እየተዋከቡ ‹የቅሬታ ፊርማቸውን› መስጠታቸውን ለሀ/ስብከቱ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

 • በጥናት ላይ ለተመሠረተውና ወደኋላ ለማይመለሰው የሀ/ስብከቱ የተቋማዊ ለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ጥናት ተግባራዊነት አገልጋዩ የለውጥ ሐዋርያ እንዲኾን ያሳሰቡትና የለውጥ ተቃዋሚዎቹ ቅሬታ› የቀረበላቸው ፓትርያርኩ የሚሰጡት ወሳኝ ምላሽ ዛሬ ይጠበቃል፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ

Advertisements

13 thoughts on “ሰበር ዜና – ለደመወዝ ጭማሪ ጥናት ድጋፍ ለማግኘት በሚል በተጭበረበረ መንገድ የተሰበሰበ የካህናት ፊርማ የአ/አ ሀ/ስብከት የአስተዳደር መዋቅር ጥናት መቃወሚያ ኾኖ ለፓትርያርኩ ቀረበ፤ በጥናታዊ ውይይቱ ገና ያልተሳተፉ ሙሰኛ አለቆችና ሠራተኞች የተቃውሞው አካል መኾናቸው በተቋማዊ ለውጡ ላይ ያላቸው ጥያቄ በጥላቻና ጥቅመኝነት ላይ ብቻ መመሥረቱን አረጋግጧል

 1. melaku bogale December 18, 2013 at 8:43 am Reply

  bertuln abatachin yihe tqmegninet meweged alebet!

 2. fiqir December 18, 2013 at 8:52 am Reply

  it is true we are in behind of the new change !!!!!! we will see! Maranatha

 3. sisay g/maryam December 18, 2013 at 8:55 am Reply

  tiqimachinin silemineka atibiqen eniqawemalen

 4. Haymanot Rete't December 18, 2013 at 11:45 am Reply

  Do you know solomon of the bole is the friend of ‘kesis’ solomon? The later is orchastrating to things. Now a days I see him in every anthi-church movemnets, like the hawassa case. He was there, though not clear how he was called there. He must be warned, if not the sword of God will very soon come upon him.

  Dear Hara, btw I want to thank you for you have said something about the hawassa case, although toooooooooo late. You also have seen the response.

 5. girma December 18, 2013 at 11:49 am Reply

  betam yemigermew, Yelebana Yezerafi sibisib asgerami new. Bicha enkuanim aquamachewin ayenew!

 6. Anonymous December 19, 2013 at 6:57 am Reply

  Lebinet amel kehonebachew negem silemytewut lebetehiristiyanachin hiliwuna sinil liniqawemachewu yigebal, leban Yemiserkibet ijun lemaser lewutu wesagn new!!!!

 7. mezgebu December 19, 2013 at 10:16 am Reply

  ምንም እንኩዋ ዘገባዎቻችሁ ብዙ ጊዜ ወገናዊነት ይነበብባቸዋል የሚል ቅሬታ ቢኖረኝም በአስተያየት መስጫችሁ ላይ የሁሉንም ወገን አስተያየት በሚዛናዊነት የሚያስተናግድ መድረክ ከፍታችሁ ወደ ተሀድሶ ብሎጎች ሳንቀላውጥ በውስጥ ጉዳያችን በአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ጥላ ስር ሆነን የየራሳችንን አስተያየት እንድንሰጥ ያደረጋችሁንን ሀራውያን አመስግኘ ትችቴን ልቀጥል!!!
  ፍታህ ሊተ እግዚኦ ወተበቀል በቀልየ…………
  1. ‘ጊዜያዊ የደሞዝ ጭማሪ ማስተካከያ ጥናት ላይ የተደረገ ፊርማ ለጥናቱ መቃወሚያ ዋለ’ አላችሁ፡፡አባባላችሁ እውነት አይመስለኝም፡፡
  ም/ቱም (1) የደሞዝ ጭማሪው በጥቅምቱ ሲኖዶስ ጸድቆ ከሳምንት በፊት ለተግባራዊነት ወደየአድባራትና ገዳማት ተልኩዋል፡፡ስለዚህ በጸደቀ ደሞዝ ፊርማ የሚሰበስብ የለም፡፡(2)እናንተው በዘገባችሁ ላይ ለማሳያነት ያወጣችሁት የከርቸሌ ሚካኤል አገልጋዮች የፈረሙበት ሰነድም በራስጌው በሰፈረው ጽሁፍ “አዲስ በተዘጋጀው መዋቅራዊ አስተዳደር ቃለ-አዋዲውን የሚጥስና የማይገናኝ በመሆኑ ያልተቀበልነውና ያላጸደቅነው መሆኑን የሚገልጽ ፊርማ” ተብሎ በግልጽ አማርኛ ሰፍሩዋል፡፡ፈራሚዎች ይህን ፊት ለፊት የሚታይ መግለጫ እያነበቡ ፈርመዋል፡፡ስለዚህ ቢያንስ የራሳችሁን ማስረጃ የሚጣረስ ዘገባ አታውጡ፡፡በነገራችን ላይ የተቃዋሚዎች ቁጥር ከ15 አይበልጥም እንዳላላችሁ ሁሉ ራሳችሁ ባቀረባችሁት ማስረጃ እንኩዋ ከአንድ አጥቢያ ብቻ ከ15 በላይ ጥናቱ ላይ ጥያቄ ያነሱ ግለሰቦች እንዳሉ ስላረጋግጣችሁልን እናመሰግናለን፡፡ስለ 95% ድጋፍ ለመጻፍ ደግሞ ታህሳስ 9/2006ዓ.ም በቤ/ክህነት የስብሰባ አዳራሽ ከትሞ የነበረውን በመቶ የሚቆጠር ቅሬታ አሰሚ ዝርዝር ብታወጡልን!!!
  2. ቅሬታ አቅራቢዎችን ‘ህገ ቤ/ክ ከቃለአዋዲው ያለውን ልዩነትና በአ/አ/ሀ/ስብከት ያለውን ተፈጻሚነት በቅጡ የማያውቁ’ ብላችሁዋል፡፡እንዴ!!!በመጀመሪያ ቃለ-ዐዋዲው በራሱም የህገ-ቤ/ክ የበላይ ህግ መሆኑን ተረዱ፡፡ህገ-ቤ/ክ ሌላ ቃለ-አዋዲው ሌላ የሆነ አታስመስሉ፡፡ባጭሩ የቅሬታ አቅራቢዎቹ አቤቱታ በጥናት ስም ከህገጋተ ቤ/ክ ሁሉ የበላይ የሆነው ቃለ-ዐዋዲ የሚቃረን መመሪያ መውጣት የለበትም ነው፡፡እናንተ ባጠናነው ጥናት የተካተቱት እንደ የሰው ሀይል አይነት የስራ ክፍሎች በቃለ-ዐዋዲውም ነበሩ ካላችሁ አንቀጽ ጥቀሱና እንከራከር!!!አ/አ/ሀ/ስብከትንም ከቃለ-ዐዋዲው ውጭ የሚተዳደር አታስመስሉት፡፡
  3. ‘ስለ ለውጥ አመራር ያላቸው ግንዛቤ የተሳሳተ ነው’ የምትሉት ለስህተቱ መፈጠር ተጠያቂዎቹን እነማንን አድርጋችሁ ነው???በየኢንተርኔቱ ለምን ቅሬታ ተነሳብን ብሎ ከመጮህ ቅሬታቸውን የሚመጥን መልስ መስጠትና ግንዛቤያቸውን ማስተካከል የአጥኚው አካል ድርሻ መስሎኝ!!!
  4. ‘ሰዎቹ ምዕመናን በቤ/ክ ያላቸውን ድርሻ ስለማይቀበሉ ነው’ ጥናቱን የሚቃወሙት ብላችሁዋል፡፡መጀመሪያ ነገር ጥናቱ ከመቅረቡ በፊት መሰለኝ ቤ/ክ ምዕመናንን በሰ/ጉባኤነትና በልማት ኮሚቴ እያሳተፈች ቀጥተኛ ውሳኔ ሰጭ እንዲሆኑ ያደረገች፡፡በጥናቱ የምዕመናን ተሳትፎ ከዚህ በተሻለ መልኩ ስለመስፈሩም አልነገራችሁንም፡፡ስለዚህ በምዕመን ስም ለማስፈራራት አትሞክሩ!!!እንግዲህ በአሜሪካ የሚታየውን የምዕመናን ተወካይ ተብየ የኢህአፓ እና ኢሰፓ አባላት የቀፈደዱት፣አምባገነንና ጎጠኛ የቦርድ አስተዳደር በኢ/ያ ቤ/ክ ማስፈን ከፈለጋችሁ አላውቅም፡፡
  5. ‘ቤ/ክ በራሱዋ ለመዳኘት ያላትን መብት የሚያስከብረውን ጥናት ተቃውመዋል’ ስላላችሁትም ወትሮም ከጥናቱ በፊት ያልጠነከረና ያልዳበረ ይሁን እንጅ የክህነት ጉዳዮችን የሚያይ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አለን፡፡አሁንም ይሕ ፍርድ ቤት በቢሮ ደረጃ ሰው ተመድቦለት ስላለ ጥናታችሁ ልክ አዲስ ግኝት እንዳመጣ ሆኖ ባይቀርብ ጥሩ ነውያለውንና የነበረውን የሚቃወም አልተነሳም፡፡የሚመጣውን መጠርጠር ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ያውም ለኢትዮጵያዊ!!!በዚሁም ላይ ለካህን!!!
  6. ‘አጥኚው በሲኖዶስ ትእዛዝ ተቁዋቁሞ ሳለ እንደ ህቡዕ አካል ታይቱዋል’ ትላላችሁ ግን እኮ ሲኖዶሱ ‘የትም ፍጩት ጥናቱን አምጡት’ ብሎ አይመስለኝም ትእዛዙን የሰጠው፡፡ቢያንስ የአ.አ አገላጋዮችን አታሳትፉ አላላችሁም፡፡እናንተ ግን አዲስ አበባ ለይ የሚተገበረውን ጥናት በገዳማውያን ጸሎት ለመታገዝ በሚል በሂደቱ የሚመለከታቸውን የአ.አ አገልጋዮች ሳታሳትፉ ድንገት ጥናታችንን ፈጸምን ብላችሁ ብቅ አላችሁ፡፡እና በአ.አ አገልጋዮች ፊት ህቡእ ብትባሉ ምን ይደንቃል??ስታጠኑት አላዩአችሁ!!!
  7. አሁንም በጥናቱ ሂደትና ውጠየት ላይ ያሉኝ ቅሬታዎች፡
  – በጥናቱ የአሀት አብያተ-ክርስቲያናት ልምዶች አለመታየታቸው፣
  – ጥናቱ ከቤ/ክ ነባራዊ ሁኔታ ይልቅ ከአለማዊ ተቁዋማት መነሳቱ፣
  – የቅሬታ አቀራረብ ስርዐት ያልተዘረጋለት መሆኑ፣
  – ቢያንስ የተጠቃለለ የጥናቱ ይዘት እንኩዋ ለሚመለከታቸው እንዲደርስ ሳይደረግ እንደ ስብከት ከመድረክ ብቻ የሚደመጥ መሆኑ፣
  – አጥኚዎቹ በምንም መልኩ ጥናቱን ለማሻሻል ዝግጁነት የሌላቸው ሆነው መቅረባቸው፣
  – ለትግበራ ብቻ በጥድፊያ መራወጥ መብዛቱ የጠየና አለመምሰሉ፣
  – በምክክሩ ወቅት ከመድረክ በኩል ተቃራኒ የሆኑ ሀሳቦችን የማፈን አዝማሚያ፣
  – ቃለ-ዐዋዲው ባልተሸሻለበት ጥናቱ በቃለ-ዐዋዲው የማይታወቁ ትልልቅና አዳዲስ የስራ መደቦችን ፈጥሮ የበታቹ መመሪያ የበላዩን ቃለ-ዐዋዲ በተግባር መሻሩ፣
  – የአጥኝዎች አመራረጥ ግልጽነት የጎደለው መሆኑ፣በተለይ በጎ ስራው እንዳለ ሆኖ አሁን አሁን አንዱ የቤ/ክ ችግር አካል እየሆነ ለመጣው ማህበረ-ቅዱሳን በምን መመዘኛ ጥናቱ እንደተሰጠ አለመታወቁ፣
  – በጥናቱ ሂደት የካህናት ተሳትፎ የለም በሚያስብል ደረጃ መሆኑ፣
  – ወዘተ………..

 8. Anonymous December 19, 2013 at 11:55 am Reply

  ebakachu legilesboch sayhon lbytekrstiyanwa enasib ezaw menegager sichal endezih aynete were bemidia eyawetu minm yemayawkewn memen gira magat lemin asfelege minalebt tekerarbo menegager bichal yemenafikan msakia banhon ebakachu enantem endezih aynet were be enternet batawetu yebet krstiyanwan kiber bintebk yiblagn legna enji byte krstiyan raswa kirstos new manm bihon litekembat enji litekmat aychlm yhen enreda

 9. በእምነት መጽደቅ December 20, 2013 at 5:47 am Reply

  መናፍቅ እኮ በጌታ በኢየሱስ የሚያፍር የሱ ደም ብቻ ከሃጢአት የሚያነጻ መሆኑን የሚጠራጠር ማለት ነዉ ይህ ምንፍቅና በቤተክርስቲያናችን ነግሶ መኖሩን ጸሐይ የሞቀዉ ጉዳይና መሳቂያ መሳለቂያ ሆነን መኖራችን ምን ምስጢር አለዉና ነዉ አሁን ይህ ይደበቅ ያ አይነገር የሚባለዉ ሰይጣን እንዲህ አድርጎ የሚያምሳችሁ እኮ በወንጌሉ ላይ ስላመጻችሁና ኢየሱስ የሚለዉን ስም ያነሳዉን ስታስወግዙና ስታድኑ ሲመቻችሁ ስትደበድቡና ስትገድሉ ስማችሁ ከመናፍቅ በላይ የአርዮስ ልጆች መባል ይገባችሁዋል! ክብሩን ሁሉ ለጌታችን ኢየሱሰ በመስጠት ንሰሐ መግባት ስላለፈለጋችሁ ልባችሁን እልከኛ በማድረጋች ነዉ ገና ምኑ ተይዞ! ጌታ በክብሩ እንደማይደራደር ታያላችሁ! እሱ ብቻ ጌታና መድሐኒት መሆኑን ለማስታወቅ የንሰሐ ጊዜ ቢሰጣችሁም መንበዛበዙን ቀጠላችሁበት ሐራ ይህንን አታወጪዉም ግን የራስሽ አዘጋጆች ካነበቡትና አንድ ወይም ሁለት ነፍስ ቢድንበት ብዬ ነዉ እግዚአብሔር አገራችንን ይባርክ

  • hiruy December 20, 2013 at 12:26 pm Reply

   1. ወንድሜ “መጽደቅ በእምነት” በስድብና በማጣጣል እንኩዋን ሌላ ሰው ራስህንም የምታድን አይመስለኝም፡፡ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማወቅም በላይ ከልደቱ እስከ ትንሳኤው ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ በአልም አድርጋ ለዘመናት ጌታን አክብራ ያስከበረችውን ቅድስት ተዋህዶ ለመንቀፍ መብት የለህም፡፡አሁን እየተወያየን ያለነውም በምን መልኩ ብንመራት ነው “እንደ እብድ ጨርቅ እየተበጣጠሱ” በየጊዜው ከሚበዙ አዳዲስ ሀይማኖቶች በተሻለ መልኩ አንድነታችንና ጥንካሬያችንን የበለጠ አሳድገን የምንቀጥለው በሚል እንጅ በሀይማኖት ተከፋፍለን አይምሰልህ፡፡ጉዳዩ አይመለከትህም፡፡ምክንያቱም ይህ የእኛ የኦርቶዶክሳውያን የውስጥ ጉዳይ ነው!!!
   2. የኢየሱስ ስም ስለተጠራ ብቻ መዳን በሽበሽ ይሆናል፣ሰላምም ይሰፍናል ካልክ መጀመሪያ እስኪ በየፍርድ ቤቱ ተነታርከው…..ተጨቃጭቀው….ተቁዋስለው….በስተመጨረሻ ለሁለት የተከፈሉትንና በኢቲቪ ለበዐል እንኩዋን አደረሳችሁ ለማለት እንኩዋ አንድ መሆን ያቃታቸውን ኢየሱሳውያን ነን ባዮቹን የኢ/ያ ወንጌላውያን ህብረትና የአ/አ ወንጌላውያን ህብረትን አስታርቅ፡፡እሱን ስትጨርስ ደግሞ ልሳን በሚል ሲንተባተቡና ተወዳዳሪ ያለው ይመስል ኢየሱስ 1ኛ፣1ኛየ ኢየሱስ እያሉ ዘለው ሲያዘልሉህ ውለው ያለማንም ሀይባይ የመባዕ ከረጢቱን ለብቻቸው ይዘው እብስ የሚሉትን ነቢያት ነን ባዮች ታምራት ገለታ መሰል ዘመናዊ ጠንቁዋይ ፓስተሮችን አስተካክል፡፡
   3. የበለጠ ጊዜ ካገኘህ ደግሞ አሜሪካ ላሉ ለዘመናት የጥቁርና ነጭ በሚል አዳራሻቸውን ለያይተው ዘረኝነትን በይፋ በመስበክ የመብት ታጋዩ ሉተር ኪንግ ሳይቀር ወደ እስልምና እንዲሄድ የገፉትንና ሰሞኑን ወንድና ወንድ በየቸርቾቻቸው ማጋባት ጀምረው የካቶሊክ ቤ/ክ ይህን ድርጊታቸውን ስለተቃወመች በሁዋላቀርነት ለሚፈርጁዋት የሀይማኖት መሰሎችህ ፀልይ፡፡
   4. እንጅ የአዲስ ኪዳኑን በግ የሃይማኖት አባትህ ሉተር ሳይወለድ ገና በ34 ዓ.ም ከሐዋርያው ፊልጶስ የተቀበለችውን የኢ/ያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ‘በተረፈ-አርዮሳዊነት’ ለማብጠልጠል የሞራል ብቃት የለህም፡፡ለነገሩ ዘመን አመጣሽ የሆነ ነገር ሁሉ ትክክል ለሚመስለው ግልብ ስልጡንነት የያዘ ሰው እና ‘አብርሃም አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት’ የሚለውን ደረቅ ምንባብ በማየት የአብርሃም ጽድቅ ይስሀቅን ለመስዋእትነት በማቅረብ በምጋባር የተረጋገጠ መሆኑን ዘንግቶ ‘በእምነት ብቻ እጸድቃለሁ’ ከሚል ምግባር አልባ ራሱን አጽዳቂ ከዚህ የተሻለ ነገር አይጠበቅም፡፡
   5. እኛ ግን ጌታ ሆይ….ጌታ ሆይ….በማለት ብቻ መንግስቱን እንደማንወርስ ባለቤቱ የነገረንን በማመንና ሐዋርያው ያዕቆብም ምግባር የሌለው ሃይማኖት ሙት መሆኑን የገለጸበትን መልእክት ተረድተን ምግባር ከሃይማኖት የምታስተምረንን አብ የመሰረታት፣ወልድ በደሙ ያነጻት፣መንፈስቅዱስ ፈጽሞ በእለተ-ጰራቅሊጦስ ያጸናትን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስንከተል አንገታችንን ቀና ብለን ነው!!!ማተባችን እስኪታይ!!!

 10. Anonymous December 23, 2013 at 6:57 pm Reply

  በአውሮፓ አቆጣጠር 14/12/2013 ለተላለፈው ላስመሳዩ የኢንተርኔት አሉባልታ የተሰጠ መልስ
  ዛሬ ባወራችሁት ውሸት ውስጥ ብዙ ሰዎች ወይም አሥራ ሁለት የደብር አስተዳዳሪዎች እና ፀሐፊዎች ተካተውበታል፡፡ ዘወትር ስንቃቸውና መሸፈኛቸው ማታለልና ውሸት አሉባልታ የሆነው ስሙ የማይወክላቸው የቅዱሳን ስብስብ የተባሉት እነዚህ በቤተ ክርስቲያን አባቶች ወይም በማኅበረ ጻድቃን፣ በማኅበረ ቅዱሳን ስም ተንደርድረው የሚቀላምዱት በአሁኑ ጊዜ ሞኝ ሰው ይገኛል ብለው ከሆነ ስሕተታቸው ደረቅ ወንዝ አያሻግርም፡፡ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት እንደተባለው ሁሉ ይህ ሁሉ ምክንያትና ጋጋታ ድብቅ አላማን ለማስፈጸም ይመስልባችኋል፡፡ ስብሰባ ተሰበሰቡ ተብሎ የተነዛው ወሬ አልተሰበሰቡም እንጂ የመንግሥት አዋጅና ደንብ እንዲሁም ሉአላዊው የሀገሪቱ መተዳደሪያ ሕገ-መንግሥት የማይቃረን ከሆነ መብታቸው ነው፡፡ ለመሆኑ የሀገረ ስብከቱ መዋቅር አደረጃጀትና የሥነ ምግባር ደንብ የሚባለው ለሀገሪቱ እኔ አውቅልሃለሁ የሚለው አንባገነናዊ ሥርዓት ከረሳቸው 40 ዓመታት ተቆጥረዋል አልሰሙም ማለት ነው፡፡ ለማንም ኢትዮጵያዊ በሕግ ፊት እኩል ነው ይላል ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምሑራን ለቀሳውስትና ዲያቆናት ይነፍጋል ይሕ ሕግ ይነፈጋል ቢባል ኢትዮጵያዊ አይደለም ማለት ነው፡፡
  ስለዚህ በውይይቱ ላይ ከ92-95% የሚሆነው ሕጉን ደግፎታል ተብሎ የተለቀቀው ውሸት እንኳን 95% ሊደግፈው ይቅርና 5% እንኳን አልደገፈውም ነገር ግን በካህናቱ መካከል በማህበሩ የተዘጋጁ ቲፎዞዎች በቁጥር ሁለት ሦስት የሚሆኑ ሲደግፉ ለማየት ተችሏል፡፡ ይህን ቁጥር በብዙ እጥፍ አግንኖ ማቅረብ በእውነት ራስን ትዝብት ላይ ከመጣል ውጭ የሚያስገኘው ፋይዳ አይኖርም፡፡
  ሀቁን ለመናገር ግን
  1.ኛ የማህበሩ ፍላጎት የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብና ሕዝቡን በመያዝ በዚህ በቤተ ክርስቲያን ትክሻ ተራምዶ በትረ መንግሥት ለመጨበጥ እንደሆነ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ መንግሥት የተያያዘውን የሰላምና የልማት ስትራቴጅ በመቃዎም በሕዝበ ክርስቲያኑና በካህናት ላይ መለያየትን እንዲሁም ጥላቻን ለመፍጠር የምታደርጉት የኢንተርኔት አሉባልታ በአንዳንድ ቦታዎች የምንሰማው የፌስቡክ ጦርነት ምንጩ ከእናንተ የሆነ ያስመስልባችኋል፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረኝ በእውነት እናንተ እንደ ስማችሁ የቅዱሳን ማኅበር ከሆናችሁ ገሕገ ቤተ ክርስቲን ከአባቶቻችን ትውፊትና ቀኖና በመውጣት የቤተ ክርሰቲያኗን ራስ ሲኖዶስን የሚመሩ በትምሕርት፣ በሃይማኖት እና በአስተዳደር ተመርጠው በፈቃደ እግዚአብሔር የተሸሙ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የኢሱስ ክርስቶስን ሥላጣነ ክህነት የያዙ ቀሳውስትን በኢንተርኔት ላይ እንዲህ ናቸው እንዲያ ናቸው እያላችሁ ስም የምታጠፉት ከምን የመነጨ ነው; ወንድምህን በአደባባይ ውቀሰው የሚል ሕግ ከየት አገኛችሁት; ይህ አዝማማያችሁ ይህ አዝማማያችሁ እውነትም እነዚህ ሰዎች ፀረ ቤተ ክርስቲያን ናቸው ያሰኛችኋል፡፡ 2ኛ. የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሙሰኞች እያላችሁ ትሳደባላችሁ እውነት ሙሰኛው ማን ነው? በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላት ሰብስባችሁ ከአባላት መዋጮ ሌላ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ አስራት እያስከፈላችሁ ኪሳችሁን የምታደልቡ እናንተን ምን እንበላችሁ? አስራት ለቤተ ክርስቲያን መከፈል ሲገባው በሥልጣናችሁ አባሎቻችሁን አስራት በማስከፈል የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በተዘዋዋሪ መንገድ ትዘርፋላችሁ፡፡ ለዚህም ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውና በቤተክርስቲኗ ኦዲተሮች ያልተረጋገጠ ገንዘብ ታደልባላችሁ፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በርካታ ሱቆቻችሁ፣ ምግብ ቤቶቻችሁ፣ ትምህርት ቤታችሁና አሁን ያሰራችሁት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ሕንፃ ምስክሮች ናቸው፡፡ ታዲያ በየትኛው ጎናችሁ ነው ሐቀኞች እና የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪዎች የምትሆኑት እናንተ መስሏችሁ ነው እንጂ የካህናት ልዕልና በምድራውያን ሰዎች የሚተች ሳይሆን ‹‹ ወለእመቦ ተስናን ምስለ ቢጹ ለይትዋቀስ በኀበ ቅዱሳን ወአኮ በኀበ ጸዓልያን ወአማፅያን፡፡ ወኢተአምሩኑ ከመ ቅዱሳን ይኴንንዎሙ ለዓለም ወእመሰኬ ትኴንንዎሙ ለዓለም ኢይደልዎክሙኑ ትኰንኑ ዘንተ ትሑተ ምኵናነ ወኢተአምሩኑ ከመ መላእክት ጥቀ ንኴንን ሕድጉሰ ዘዝዓለም ›› ይላል 1ኛ ቆሮ 6፡1-4 ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማዕ ነው፡፡
  3ኛ. ሒሳብ ሒሳብ ትላላችሁ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በደንብ አላወቃችኋቸውም እንጂ የሒሳብ ምንጩ አቡሻኽር መሆኑንና የዚህ ሒሳብ ባለቤቶች ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው፡፡ እንኳንስ የዘመኑን አካውንቲንግ ወይም የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ቀርቶ አቡሻኽርን ያህል ውስብስብ ሒሳብ የሚፈቱ ሊቃውንትን ነው እየሰደባችሁ ያላችሁት አሁንም ቢሆን በቤተ ክርስቲያን ክፍፍልና ግጭት መፍጠራችሁን ትታችሁ ወደ ሰላምና መረጋጋት ተመለሱ እያልኩ የሚመለከተው አካልም ይህ አካሄድ የሰላም አይመስልምና በንቃት ይከታተለው እላለሁ፡፡ ክብርና ምስጋና ለፈጣሪ ይሁን አሜን፡፡

 11. በረሀ December 23, 2013 at 7:12 pm Reply

  በአውሮፓ አቆጣጠር 14/12/2013 ለተላለፈው ላስመሳዩ የኢንተርኔት አሉባልታ የተሰጠ መልስ
  ዛሬ ባወራችሁት ውሸት ውስጥ ብዙ ሰዎች ወይም አሥራ ሁለት የደብር አስተዳዳሪዎች እና ፀሐፊዎች ተካተውበታል፡፡ ዘወትር ስንቃቸውና መሸፈኛቸው ማታለልና ውሸት አሉባልታ የሆነው ስሙ የማይወክላቸው የቅዱሳን ስብስብ የተባሉት እነዚህ በቤተ ክርስቲያን አባቶች ወይም በማኅበረ ጻድቃን፣ በማኅበረ ቅዱሳን ስም ተንደርድረው የሚቀላምዱት በአሁኑ ጊዜ ሞኝ ሰው ይገኛል ብለው ከሆነ ስሕተታቸው ደረቅ ወንዝ አያሻግርም፡፡ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት እንደተባለው ሁሉ ይህ ሁሉ ምክንያትና ጋጋታ ድብቅ አላማን ለማስፈጸም ይመስልባችኋል፡፡ ስብሰባ ተሰበሰቡ ተብሎ የተነዛው ወሬ አልተሰበሰቡም እንጂ የመንግሥት አዋጅና ደንብ እንዲሁም ሉአላዊው የሀገሪቱ መተዳደሪያ ሕገ-መንግሥት የማይቃረን ከሆነ መብታቸው ነው፡፡ ለመሆኑ የሀገረ ስብከቱ መዋቅር አደረጃጀትና የሥነ ምግባር ደንብ የሚባለው ለሀገሪቱ እኔ አውቅልሃለሁ የሚለው አንባገነናዊ ሥርዓት ከረሳቸው 40 ዓመታት ተቆጥረዋል አልሰሙም ማለት ነው፡፡ ለማንም ኢትዮጵያዊ በሕግ ፊት እኩል ነው ይላል ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምሑራን ለቀሳውስትና ዲያቆናት ይነፍጋል ይሕ ሕግ ይነፈጋል ቢባል ኢትዮጵያዊ አይደለም ማለት ነው፡፡
  ስለዚህ በውይይቱ ላይ ከ92-95% የሚሆነው ሕጉን ደግፎታል ተብሎ የተለቀቀው ውሸት እንኳን 95% ሊደግፈው ይቅርና 5% እንኳን አልደገፈውም ነገር ግን በካህናቱ መካከል በማህበሩ የተዘጋጁ ቲፎዞዎች በቁጥር ሁለት ሦስት የሚሆኑ ሲደግፉ ለማየት ተችሏል፡፡ ይህን ቁጥር በብዙ እጥፍ አግንኖ ማቅረብ በእውነት ራስን ትዝብት ላይ ከመጣል ውጭ የሚያስገኘው ፋይዳ አይኖርም፡፡
  ሀቁን ለመናገር ግን
  1.ኛ የማህበሩ ፍላጎት የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዘብና ሕዝቡን በመያዝ በዚህ በቤተ ክርስቲያን ትክሻ ተራምዶ በትረ መንግሥት ለመጨበጥ እንደሆነ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ መንግሥት የተያያዘውን የሰላምና የልማት ስትራቴጅ በመቃዎም በሕዝበ ክርስቲያኑና በካህናት ላይ መለያየትን እንዲሁም ጥላቻን ለመፍጠር የምታደርጉት የኢንተርኔት አሉባልታ በአንዳንድ ቦታዎች የምንሰማው የፌስቡክ ጦርነት ምንጩ ከእናንተ የሆነ ያስመስልባችኋል፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረኝ በእውነት እናንተ እንደ ስማችሁ የቅዱሳን ማኅበር ከሆናችሁ ገሕገ ቤተ ክርስቲን ከአባቶቻችን ትውፊትና ቀኖና በመውጣት የቤተ ክርሰቲያኗን ራስ ሲኖዶስን የሚመሩ በትምሕርት፣ በሃይማኖት እና በአስተዳደር ተመርጠው በፈቃደ እግዚአብሔር የተሸሙ ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የኢሱስ ክርስቶስን ሥላጣነ ክህነት የያዙ ቀሳውስትን በኢንተርኔት ላይ እንዲህ ናቸው እንዲያ ናቸው እያላችሁ ስም የምታጠፉት ከምን የመነጨ ነው; ወንድምህን በአደባባይ ውቀሰው የሚል ሕግ ከየት አገኛችሁት?

  ይህ አዝማማያችሁ እውነትም እነዚህ ሰዎች ፀረ ቤተ ክርስቲያን ናቸው ያሰኛችኋል፡፡ 2ኛ. የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ሙሰኞች እያላችሁ ትሳደባላችሁ እውነት ሙሰኛው ማን ነው? በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላት ሰብስባችሁ ከአባላት መዋጮ ሌላ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ አስራት እያስከፈላችሁ ኪሳችሁን የምታደልቡ እናንተን ምን እንበላችሁ? አስራት ለቤተ ክርስቲያን መከፈል ሲገባው በሥልጣናችሁ አባሎቻችሁን አስራት በማስከፈል የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በተዘዋዋሪ መንገድ ትዘርፋላችሁ፡፡ ለዚህም ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውና በቤተክርስቲኗ ኦዲተሮች ያልተረጋገጠ ገንዘብ ታደልባላችሁ፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በርካታ ሱቆቻችሁ፣ ምግብ ቤቶቻችሁ፣ ትምህርት ቤታችሁና አሁን ያሰራችሁት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ሕንፃ ምስክሮች ናቸው፡፡ ታዲያ በየትኛው ጎናችሁ ነው ሐቀኞች እና የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪዎች የምትሆኑት እናንተ መስሏችሁ ነው እንጂ የካህናት ልዕልና በምድራውያን ሰዎች የሚተች ሳይሆን ‹‹ ወለእመቦ ተስናን ምስለ ቢጹ ለይትዋቀስ በኀበ ቅዱሳን ወአኮ በኀበ ጸዓልያን ወአማፅያን፡፡ ወኢተአምሩኑ ከመ ቅዱሳን ይኴንንዎሙ ለዓለም ወእመሰኬ ትኴንንዎሙ ለዓለም ኢይደልዎክሙኑ ትኰንኑ ዘንተ ትሑተ ምኵናነ ወኢተአምሩኑ ከመ መላእክት ጥቀ ንኴንን ሕድጉሰ ዘዝዓለም ›› ይላል 1ኛ ቆሮ 6፡1-4 ዘቦ እዝን ሰሚዓ ለይስማዕ ነው፡፡
  3ኛ. ሒሳብ ሒሳብ ትላላችሁ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን በደንብ አላወቃችኋቸውም እንጂ የሒሳብ ምንጩ አቡሻኽር መሆኑንና የዚህ ሒሳብ ባለቤቶች ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው፡፡ እንኳንስ የዘመኑን አካውንቲንግ ወይም የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ቀርቶ አቡሻኽርን ያህል ውስብስብ ሒሳብ የሚፈቱ ሊቃውንትን ነው እየሰደባችሁ ያላችሁት አሁንም ቢሆን በቤተ ክርስቲያን ክፍፍልና ግጭት መፍጠራችሁን ትታችሁ ወደ ሰላምና መረጋጋት ተመለሱ እያልኩ የሚመለከተው አካልም ይህ አካሄድ የሰላም አይመስልምና በንቃት ይከታተለው እላለሁ፡፡ ክብርና ምስጋና ለፈጣሪ ይሁን አሜን፡፡

 12. Anonymous January 6, 2014 at 1:59 pm Reply

  ቤተ ክርስቲናችን ስንዱ እመቤት ናት፡፡ትዉፊቱን፤ዶግማዉንናቀኖናዋን ያልሳተ ዘመኑን የዋጀ አዲስ አሰራር(የስራ መመሪያ) ያስፈልጋታል።በተረፈ ማንንም በደፈናዉ አንተች።የቤተ ክርስቲያን ሰርጎገቦችን(ተሃድሶ መናፍቃንን) ድብቅ ሴራ ስላጋለጠ የተጋላጨች ባለማዎቅ ወገን የሆናችሁና የተጋለጠችሁ ስለ ማህበረ ቅዱሳን የማታዉቁ በሙሉ ተስተካከሉ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: