ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትን የአ/አ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናት በመድረክ ለመሞገት አቅም ያነሳቸውና ውይይቱን ለማደናቀፍ ሲያሤሩ የቆዩ ጥቅመኛ የአጥቢያ አለቆችና የአስተዳደር ሠራተኞች በቦሌ ላሊበላ ሆቴል ኅቡእ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው፤ ሤረኞቹ ‹‹ይደግፉናል›› በሚል የሚነግዱባቸው አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸውን ከሤራው እንዲያገሉና ለቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዲቆሙ ይጠየቃሉ!

YeHibue Sebseba Metriyaw

ይህ የኅቡእ ስብሰባ አስተባባሪዎቹ በድብቅ ያሰራጩት ጥሪ ነው፡፡ የስብሰባው ቦታ ከቦሌ ላሊበላ ሆቴል ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተለውጧል፡፡ ይህም የኾነው በሀ/ስብከቱ ፈቃድ እንቅስቃሴውን በቅርበት የሚከታተለው የጸጥታ አካል ኅቡእ ስብሰባውን እንደደረሰበት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ጸሐፊ መ/ር ሰሎሞን በቀለ አማካይነት ለዋነኞቹ አስተባባሪዎች መረጃ እንዲደርስ ከተደረገ በኋላ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡
መ/ር ሰሎሞን በቀለ ጥናቱን ለሚሠራው ቡድን በረዳትነት ከተመደቡ በኋላ በተሰጣቸው ሓላፊነት አጋጣሚ የሚያገኟቸውን መረጃዎች ‹‹እንዲህ ታስቧል፤ እንዲህ ሊደረግ ነው›› እያሉ በማዛባት ሐሰተኛና የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት ለለውጡ አደናቃፊዎች ‹የውስጥ ሰው› ኾነው የሚንቀሳቀሱ እንደኾኑ ተገልጦአል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር ባካሄደው የመጀመሪያ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተሳትፎ እንዲዳብርና በቋሚ ሲኖዶሱ አማካይነት በሥራ ላይ እንዲውል በመወሰን በሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናታዊ ውይይት ለማወክ አፍራሽ ተግባራትን ሲያራምዱ የቆዩ ጥቅመኛ የአድባራት አለቆች፣ ጸሐፊዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች ኅቡእ ስብሰባ መጥራታቸው ተሰማ፡፡

Holy Synod direction on the A.A Change mgt.

ምልአተ ጉባኤው ስለ አ/አ ሀ/ስብከት የአስተዳደር መዋቅር ጥናት ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲፈጸም የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ያዘዘበት ደብዳቤ

በቅ/ሲኖዶሱ የምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መግለጫ መሠረት÷ በብዙኃን ተሳትፎና ውይይት ለመዳበርና የበለጠ ለመስተካከል ክፍት የኾነውን የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ረቂቅ በመድረክ ከመሞገት ይልቅ በአሉባልታዎችና አሻጥሮች ለማሰናከል የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ የቆዩት የለውጡ ተቃዋሚዎች÷ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በኅቡእ የጠሩትን ስብሰባ ለማካሄድ ያቀዱት የገዳማቱና አድባራቱ በርካታ ልኡካን በረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤትና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች አስተባባሪነት ተከታታይ ዙር ውይይቶችን እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

የሀ/ስብከቱ የመዋቅር፣ አደረጃጀትና የሥነ ምግባር ችግሮች ለቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ተልእኮ መጠናከርና መስፋፋት ትኩረት በሰጠ አኳኋን እንዲስተካከሉ፤ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ሰብአዊ፣ ፋይናንሳዊና ቁሳዊ ሀብቶቿ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ታስቦ በቅ/ሲኖዶሱ ዕውቅናና ይኹንታ የተዘረጋውን አሳታፊ መድረክ በመርገጥ በኅቡእ የተጠራውን ስብሰባ በዋናነት ያስተባበሩ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ተለይተው መታወቃቸው ተገልጦአል፡፡

ኹኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ሐራዊ ምንጮቹ እንደጠቆሙት፣ በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኅቡእ ይካሄዳል የተባለውን ስብሰባ በዋናነት በማስተባበር ረገድ ከተዘረዘሩት 15 ግለሰቦች መካከል በቀዳሚነት የተጠቀሱት፡-

 • የየካ ደብረ ሣህል ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
 • የገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣
 • የኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
 • የሳሪስ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አስተዳዳሪ፣
 • የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣
 • የጉለሌ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
 • የአፍሪቃ ኅብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ፣
 • የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት
 • የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
 • የቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
 • የአውግስታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ፤
 • የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ጸሐፊና ሒሳብ ሹም፤
 • የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ጸሐፊ ናቸው፡፡

ከእኒህና ከመሰሏቸው ግለሰቦች አብዛኞች፡- ከገቢያቸው በላይ በልዩ ልዩ የዝርፊያ ስልቶች ባጋበሱት የምእመናን ገንዘብ ከአንድ በላይ መኖርያ ቤቶች የሠሩ፤ የኪራይና ንግድ ቤቶች፤ የጭነት፣ የሕዝብ ማመላለሻና የቤት መኪኖች፣ ድልብ የባንክ ተቀማጭ፣ በቤተ ክርስቲያን የሥራ ሰዓት የግል ሥራ እየሠሩ ገቢ የሚያገኙበት ቢዝነስ ያላቸው፣ አንዳንዶቹም በሕገ ወጥ የጦር መሣርያ ይዞታና በተለያዩ ሥነ ምግባራዊ ችግሮች የተከሰሱና የተቀጡ መኾኑ ታውቋል፡፡ የተቋማዊ ለውጥ ሒደቱን የሚቃወሙትም እኒህን ሕገ ወጥ ጥቅሞች የሚያስጠብቁባቸው ክፍተቶች÷ መተግበሩ አይቀሬ በኾነው የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ እንዳይስተካከል ለመከላከል መኾኑ ተነግሯል፡፡

ከኅቡእ ስብሰባው አስተባባሪዎች መካከል ለሁለት፣ ለሁለት ቀናት በየክፍላተ ከተማቸው የተካሔደውን ጥናታዊ ውይይት አሟልተው ያልተከታተሉ፣ ካለባቸው ሓላፊነት አኳያ መገኘትና ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ሲገባቸው ጨርሶ ያልተገኙ፤ በፈንታው ሐሰተኛና የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ከሚቀርበው ርእሰ ጉዳይ ጋራ ጨርሶ የማይገጥምና ለርእሰ ጉዳዩ መዳበር አንዳችም አስተዋፅኦ የሌለውን የአሉባልታ ጥያቄ በማንሣት አቅጣጫ ለማሳት አበክረው የሚንቀሳቀሱ እንዳሉባቸው ተጠቅሷል፡፡

እኒህ አካላት የሚነዟቸው አሉባልታዎች ሊሸፍኗቸው/ሊከላከሏቸው የሚፈልጓቸውን ጥቅሞችም የሚያመላክቱ እንደኾኑ ግንዛቤ የተወሰደ ሲኾን ከእነርሱም መካከል፡-

 • አስተዳዳሪዎች ወደ ግብዝና ወርዳችኋል፤ ሥልጣን የላችኹም
 • ጸሐፊ ሥልጣንና ማኅተም ልትነጠቅ ነው፤ ወደ ድጋፍ ሰጪነት ወርድኻል፤ ድራሽኽ ጠፍቷል
 • ቁጥጥር ሥራኽ በኮሚቴ ተወሰደብኽ፤ ማኅበረ ቅዱሳን የራሱን ሰዎች ሰግስጎና ሰንጎ ሊይዝኽ ነው
 • የድጋፍ ሰጪ መዋቅሩ በመስፈርየማኔጅመንት ምሩቅ ስለሚጠይቅ ማኅበረ ቅዱሳን የራሱን ሞያተኞች ሊያስቀምጥበት ያዘጋጀው መዋቅር ነው፤ 
 • በየአጥቢያው 20፣ 20 ካህናት ብቻ ነው የሚያስፈልጉት ተብሏል፤ ካህን ሆይ፣ መበተንኽ ነው፤
 • በየአጥቢያው በቅዳሴ ላይ የአባ እስጢፋኖስን ስም አንጠራም፤
 • ጥናቱን ለምን ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ያጠናዋል፤

የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

እስከ አሁን በአራት ተከታታይ ዙሮች በተደረጉት ጥናታዊ ውይይቶች፣ አብዛኛው ተሳታፊ ለውጡ ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አመራርና አስተዳደር ትንሣኤ መኾኑን እየመሰከረ፣ በየዙሩ ከጥናታዊ ውይይቱ በፊትና በኋላ በሚሰበሰብ አስተያየት ከአጠቃላይ ተሳታፊው ከ92 – 95 በመቶ የሚኾነው ረቂቁ በአስቸኳይ ጸድቆ መተግበር እንዳለበት ድጋፉን እየገለጸ፤ በመድረኩ ላይ የሚነሡ ከርእሰ ጉዳይ ያፈነገጡ የቅስቀሳ መሰል አስተያየቶችንም ርስ በርሱ እየተጋገለባቸው መኾኑ ሲታይ፣ በኅቡእ ተሰብሳቢዎቹ የለውጡን ሒደት ጋት ያህል ሊመልሱት እንደማይችሉ የብዙዎች እምነት ነው፡፡

*                 *                 *

አሁን ዘግይቶ በተሰማ መረጃ መሠረት÷ በደብረ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ገነት (ቀድሞ መልአከ መንክራት) ኃይሌ ኣብርሃ ሰብሳቢነት፣ በደብሩ ጸሐፊ ዲያቆን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጸሐፊነት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በኅቡእ መደረጉ የተገለጸው ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

ስድስት አስተዳዳሪዎችንና አምስት ጸሐፊዎችን ጨምሮ 15 ያህል ተሰብሳቢዎች እንደተገኙበት የተነገረው ይኸው ኅቡእ ስብሰባ የተጠናቀቀው በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ‹አቤቱታውን› ለቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለማቅረብ በመስማማት ነው ተብሏል፡፡

በሌሎች ምንጮች ጥቆማ ደግሞ ስምምነቱ በዕለቱ÷ ነጭ በጥቁር የለበሱ ኻያ ኻያ ሰዎችን ከየአድባራቱ አደራጅቶ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገናኘት በቀድሞው ፓትርያርክ መቃብር ዙሪያ ማልቀስንና የለውጥ ሒደቱን የሚቃወም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠትን እንደሚያካትት ተመልክቷል፡፡

ማረሚያ፡- ኅቡእ ስብሰባው በቦሌ ላሊበላ ሆቴል እንደተጠራ በርእሱ የተጠቀሰው መረጃ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተብሎ እንዲስተካከል ከይቅርታ ጋራ እንጠይቃለን፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ

 

Advertisements

14 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበትን የአ/አ ሀ/ስብከት የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናት በመድረክ ለመሞገት አቅም ያነሳቸውና ውይይቱን ለማደናቀፍ ሲያሤሩ የቆዩ ጥቅመኛ የአጥቢያ አለቆችና የአስተዳደር ሠራተኞች በቦሌ ላሊበላ ሆቴል ኅቡእ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው፤ ሤረኞቹ ‹‹ይደግፉናል›› በሚል የሚነግዱባቸው አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ራሳቸውን ከሤራው እንዲያገሉና ለቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዲቆሙ ይጠየቃሉ!

 1. Anonymous December 14, 2013 at 12:53 pm Reply

  ወይ መድኃኒያለም የዚች ቤተክርስቲያን መከራ መቼ ይሆን የሚቆመው ?እንዲህ የወያኔ ስርዓት መጫወቻ ትሁን ?እግዚአብሔር የራቀ ቢመስልም ፍርዱ ግን አይዘገይም ::

 2. didimos December 14, 2013 at 1:57 pm Reply

  yetim aydersum midire leba zerafi hula

 3. Tsione December 15, 2013 at 1:02 am Reply

  Aye Embete Dengle Weladite Amlak Ebakesh Betekristianachenen ena Tewahedo Hymantachenen Tetebekilen. Telashen Tiyben. Bemlgashe Ateleyen. Ebakacheuh wogenochachen SELEBETEKRISTIAN BLACHEHU ” AMESTUNE YEMEBETACHEN HAZENAT” EYASEBEN ENSELEYE. Ke Tute Nekashoch Egeziabehere Yeseweren. ETHIOPIAN ENA ORTODOXES TEWAHEDO EMENETACHENEN EGZIABHERE LEZELALEM YANURELEN.

 4. MISTRU ZELEKE December 15, 2013 at 7:52 am Reply

  እኔ የማዝነው የክርስቶስን ወንጌል በጀሯቸው ሰምተው ነገርግን እንደ ይሁዳ ኮሮጆአቸውን ለመሙላት ብቻ በሚሯሯጡ ካህናትናት ቤተ ክርስቲያን እስከመቸ ታስራ የምትኖረው?
  ግን ለውጡ አይቀርም!

 5. sami December 15, 2013 at 1:03 pm Reply

  haile ye arada giyorgisu aleqa: betekiristiyanuan abetabito zerfo sheto lememot new bisrate gebrielin ye15 million br eda tilobat new yetebarerew ye 6 kifil temari yebetekiristiyan timihirt yelelew denqoro dilib mehayim esu new wanaw asadami begize niqubet

 6. sami December 15, 2013 at 1:13 pm Reply

  off course ato HAILE is the one who lead the mob i know him very well he is a chief theaf he have two G+2 house at sendafa &lafito and two car dolfin& minibuse

 7. Anonymous December 15, 2013 at 2:09 pm Reply

  YIHE HULU WENJEL YALEBACHEWUN SEWOCH ASTEDADARI ADRGO QOYTO AHUN BEHASAB SIGACHU WENJELACHEWUN MABZAT MIN YIBALAL…… LEBAN YESHOME IRASUM LEBA NEW…. BETEKRSTIANACHIN YELEBOCH/YEWENBEDEWOCH WASHA HONALECH….RASU CHIRSTOS YATSDAT INJI

 8. mengesha December 16, 2013 at 6:41 am Reply

  If the corrupted people are collaborated they can’t create a truth!!

 9. Anonymous December 16, 2013 at 10:39 am Reply

  abo church yalut abat kahnatn sikeseksu neber. Mahiber Kidusan l 1 dber 3 kahn bca ybkal eyal nw ltbarru nw eyalu bzu kahnat bsnbet tmhrt bet bmmtat sitykun nber . wre mhonun ena tkkl endalhon asrdtnal. Genzeb endefelgu yemibelubet aserar endmiker geltenlacwal. Betam cenkuacwal . teru asrar lewut egnam neflgaln > yga satdadari sbktwngelun ln bgasaw bdun eystu ymiyascgru na lmahber kdusan mtfo smet yalacw nacw endi madrgacw aydnkm bgnzeb ytsomu slhon Daniel saris abo mktl sbasabi>

 10. Anonymous December 17, 2013 at 4:26 am Reply

  Ygrmal !! lzeshbatkrstyan ymeyznlat man ihon hulum yrasun tkem lmastbke irotal. ysaznal. !!!!!!!!!!!!!

 11. daniel December 17, 2013 at 8:35 am Reply

  wededum telum lewitu memitatu gid new betekiristiyanua eko aleqech uuuuuuuuuu yemengist yaleh hizibu tilo tefa kazinaw bado qere

 12. mezgebu December 17, 2013 at 9:00 am Reply

  1. ጥናት አቀረባችሁ፡፡ጥናቱ በገቢር ከመተርጎሙ በፊት በጥናቱ ላይ ተቹበት ብላችሁ ሰው ጠራችሁ፡፡የተጠሩት 2 ቀን ብቻ ተችቶ መለያያቱ አላረካቸውም፡፡ስለዚህ ተመሳሳይ ስሜት የተሰማቸው ተጠራርተው የቅሬታ ነጥባቸውን በዝርዝር ተወያዩ፡፡ ይህንኑ ቅሬታቸውን ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ተስማሙ፡፡መብታቸው ነው!! ምርጫቸውን አክብሩላቸው እንጅ!!!ወይስ፡
  -አለቆችና ጸሀፊዎች ስለ ቤ/ክ መዋቅር ለመወያየት አይፈቀድላቸውም??
  -እናንተ ይሄን ያህል ዘመን ስለ ቤ/ክ ያገባናል እያላችሁ ስትሰበሰቡ ፈቃድ እየጠየቃችሁ ነበርን??
  -ጥንቱኑ እነዚህን አካላት በጥናቱ ወቅት ሳታሳትፉ ለውጥ በሚል ብቻ ከላይ ወደ ታች እየጫናችሁ እንዴት እልል ብለው እንዲቀበሉዋችሁ ትጠብቃላችሁ??
  -ለመሀላ አንድ ሰው(ሰለሞን) ከካህናት ወገን መሀላችሁ ቢገባ ቤ/ክ እንደገባ ከልብ(ውሻ) ይሄን ያህል ማሳደድ የጤና ነው ??
  -በጥናቱ ከተማመናችሁ 15 እና 20 ሰው ተሰበሰበ ብላችሁ ለምን ሀገር ይያዝ ትላላችሁ??
  -ቅሬታቸውን ለፓትርያርኩ ለማቅረብ ማቀዳቸው እንዴት የቤ/ክርስቲያኑዋን መዋቅርና የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ እንደሚቃረን ተደርጎ ይወሰዳል???
  -ከእናንተ በጸጥታ ሀይል ማስፈራራትና ከእነሱ ለፓ/ኩ አቤት እንላለን አካሄድ ለቤ/ክ ስርዐት የትኛው ይቀርባል??
  2.በአንድ በኩል “መተግበሩ አይቀሬ ነው……አንድም ጋት ወደ ሁዋላ አይመለስ” ትላላችሁ ፡፡ እንደ ራዕየ-ዮሀንስ ፍጻሜ ንባብ “በዚህ ጥናት የጨመረ….የቀነሰ……”የሚል የግዝት ቃል ታስቀመጣላችሁ ፡፡ከድጋፍ ውጭ ለምን ሌላ ድምጽ ተሰምቶ!!!ትቆጣላችሁ!!!በሌላ በኩል ለተሰብሳቢዎች ቤ/ክ አበል እየከፈለች ‘አይጨመርበት…. አይቀነስበት’ በተባለው ጥናት ላይ ጉንጭ-አልፋ ውይይት ይደረጋል፡፡ግራ የሚያጋባ ነገር!!እረ የዚህ ውይይት ዓላማ ምንድን ነው??
  3. ጥናቱ ከተሰብሳቢው ያገኘው ይሁንታ ከ 92% እስከ 95% ይደርሳል የሚለው መነሻ የሌለው መደምደሚያም ከፓርቲያችን የወሰዳችሁት በጎ ያልሆነ ልምድ ነውና ወይ አስወግዱት ወይ አጠጋጉና አንደኛውን 99.6% አድርጋችሁት ተመሳሰሉ፡፡
  4.ጥናቱ ከሊቃውንት ተሳትፎ የራቀ መሆኑ ካመጣቸው ችግሮች አንዱ ዘመናዊ ት/ት ላልቀመሱ አገልጋዮች አስተያየት እንኩዋ ለመስጠታ በሚያስችል ቁዋንቁዋ አለመቅረቡ ነው፡፡
  -ሌላው ችግር በቃለ-ዐዋዲው የማይታወቁ አዳዲስ የስራ መደቦችን በመፍጠር ሉዐላውይውን ቃለ-ዐዋዲ በመመሪያ የመጣስ አካሄድ መከተሉ ነው፡፡ ቢያንስ ጥናቱ የተሸሻለውን ቃለ-ዐዋዲ መጽደቅ ተከትሎ ቢመጣ የተሻለ ይሆን ነበር፡፡
  -ማህበረ-ቅዱሳን አሁን በካህናት ዘንድ ካለው የቀዘቀዘ ተቀባይነት አንጻር ጥናቱን እሱ ከሚያካሂደው ይልቅ ሊቃውንት በአማካሪነት ተሰይመው ገለልተኛ አካል ቢያጠናው ሁሉም በምሉዕ ልብ ሊቀበለው ይችል ነበር ፡፡አሁን ግን ሁሉም ከጥናቱ ይልቅ አጥኚውን ጠላና ለግራቀኙ አስቸገረ፡፡
  5.አንዳንድ የዋሃን ወንድሞች ካህናቱ ማህበረ-ቅዱሳንን እንዲህ የጠመዱት ‘የተማረ ሰው ስለማይወዱ’ ነው ይላሉ፡፡ እኔ ግን እላለሁ፡ የተማረ ሰው በቅጡ ካልተያዘ ምክንያታዊ ስሜት ከመያዝ ይልቅ ስሜቱን ምክንያታዊ በማድረግ የሚያደርሰውን ጥፋት ከ1960ዎቹ ወጣት ምሁራን እንቅስቃሴ በላይ ምስክር የለም ፡፡ማህበሩ ከተማ-ቀመስ አጽራረ ቤ/ክንን በመታገል ያደረገውን አስተዋጽኦ ማንም አይክደውም!!! ሆኖም፡
  – አበሳዎችን ሁሉ አባቶቹ ላይ እያላከከ አያቶቹን እየዘከረ መሄዱና ያኛው ትውልድ ራሱን ብቸኛ የሀገር ተቆርቁዋሪ አድርጎ አገሪቱዋን እንዳጎሳቆላት ሁሉ ማህበሩም ቤ/ክ ያለመሪ ስለቀረች ብቸኛ መድህኑዋ እሱ(ማህበሩ)ብቻ እንደሆነ በገደምዳሜ ለማስረዳት እየሞከረ ነው፡፡
  -የደርግን ውርጅብኝ ተቁዋቁሞ በይለፍ-ወረቀት እየተንቀሳቀሰ በሰራው ስራ ዛሬ ደመወዙን ከ60 ብር ወደ 3000ብር ያደረሰው ይኸው እነሱ ሂሳብ አያውቅም እያሉ የሚያቃልሉት ካህን መሆኑን ይረሱታል፡፡ልክ ያኛው ትውልድ አባቶቹ በሰሩት ዩኒቨርሲቲ እየተማረ፣እነሱ ያስመጡትን አውሮፕላን እየጠለፈ፣ መልሶ ሁዋላቀር እንደሚላቸው
  -የሀገሩን አበው ተራምዶ በአቡነ ሺኖዳ ፍቅር የወደቀው ማህበር በሌኒን ፍቅር እንደወደቁት ቀደምቶቹ በአብዮት(revolution) እንጅ በሂደታዊ ለውጥ(evolution) የሚያምን አይመስልም፡፡
  -ልክ ያኛው ትውልድ በcrocodile ህቡዕ መዋቅሩ አጀንዳዎችንና ተመራጮቹን ከለየ በሁዋላ በአደባባይ የይስሙላ ምርጫ እንደሚያስጸድቀው ሁሉ የኛም ማህበር ከሰበካ ጉባኤ ምርጫ እስከ መዋቅር ጥናት ድረስ በህቡእ እየመከረ በገሀድ የተቃወሙትን በአንጃነት ይፈርጃል፣ስጋቸውን ቢያቅተው መንፈሳቸውን ይገድላል፡፡እናም በ1960ዎቹ ‘ማርክስ ይሳሳታል??’ ብሎ መጠየቅ ነውር የሆነውን ያህል ዛሬም ማህበር ይሳሳታል ብሎ መናገር የኑፋቄ ያህል ተቆጠረ፡፡አባት ልጁን ለመገሰጽ የሚሳቀቅበት ዘመን ደረሰ፡፡
  -ያኛው ትውልድ ብቸኛው መስመሬ ኮሙኒዝም ነው ብሎ ወጣት ምሁራንን ሁሉ በአንድ መስመር አሰልፎ ተፎካካሪ ሀሳቦችን እንደደፈቀው የኛዎቹም ከማህበሩ ያላበረ ከቤ/ክ ያላበረ ያህል እየቆጠሩ ካህን ቁጣውን በአርምሞ እንዲውጣት ይጫኑታል፡፡ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ አብዛኞቹ ምሁራን የማህበሩ አባላት ምክንያታዊ የሆነ አካሄድንና አማኒ(ሃይማኖተኛ) መሆንን ለይተው ባለማወቅ ማህበሩ ተነካ በተባለ ቁጥር በቡድን ሆ…የሚሉ መሆናቸው ነው፡፡
  -እነዛ ‘ፊውዳሉቹ ዘግተው እየበሉ ባይበዘብዙዋት ኢ/ያ ሀብታም ሀገር ነበረች’ በማለት ከምርት(production) ይልቅ ማን ምን በላ የሚለውን በላተኝነት (consumption)ለፍፈው ሁሉም እኩል የሚራብበት ስርዐት እንዳመጡ ሁሉ እናንተም የቤ/ክ ገቢ እንዴት ይደግ ከማለት ይልቅ አለቃ እና ጸሀፊ በዘበዘን እያላችሁ አመራርን ከምዕመን በመለየት ተጠምዳችሁዋል፡፡
  ስደመድም፡ ካለፉት እንማር እንጅ ስህተታቸውን አንድገም!!
  ልክ ያኛው ትውልድ በሀገር ፍቅር ያበደ የመሆኑን ያህል የሀገሩን ነባራዊ ሁኔታ ባለማገናዘቡና የአባቶቹን ውለታ በመዘንጋት ፋጻሜው እንዳላማረ ሁሉ አፍቃሬ ማህበረ-ቅዱሳንም ለቤ/ክ ያላችሁን ፍቅርና ለኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት ያላችሁ ቀናኢነት አባቶችን በማክበርና በተለይ ባለፉት 60 አመታት የኢትዮጵያ ቤ/ክ’ንን ከግብጽ ጥገኝነት በማላቀቅ አርቅቀው በፓርላማ ባስጸደቁት ቃለ-ዐዋዲ መነሻነት በተመሰረቱ ሰ/ጉባያት እና ሰ/ት/ቤቶች ረዳትነት ርስት ባጣንበት ወቅት ርስት ፈጥረው ለዚህ ያበቁንን አባቶች አክብሩ፡፡

 13. Anonymous December 18, 2013 at 5:41 am Reply

  እናንተ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስና ለመበጣበጥ የተቋቋማችሁ የዲያብሎስ ወገን ናችሁ የአባቶችን ትውፊት የምትንዱ ያጠፋ ካላ በግልጽ ላራሱ ብቻ መምከር የሚለውን ሕግ የተላለፋችሁ ፀረ ኦርቶዶክስ ናችሁ

 14. Anonymous December 18, 2013 at 10:44 am Reply

  kelay yetesetew merreja betam tekami ena wesagn new. gin betam yemaznew kelay ketetekesut zirzir wests minim tesatfo saynorachew list tedergew besirachew lay kefetegna chana enedefeter yetegededu sewoch alu. ena harawoch ebakachu kemereja gar biteseru…ewenet new yemilachu betam azegnalew. ebakachu ahunim kemereja gar bitiseru melkam new!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: