ሰበር ዜና – በጋሻው ደሳለኝ በሐዋሳ የአቋራጭ ይቅርታ ሊጠይቅ ነው፤ ‹‹ውጫዊ ጫናውን በጉልሕ የሚያሳይ ነው›› /ምእመናን/

 • በዕርቀ ሰላም ሒደቱና መግለጫው ስለ በጋሻው ደሳለኝ የተጠቀሰ ነገር የለም
 • የምእመናን ተወካዮች በጋሻው ይቅርታ እንዲጠይቅ የተሰጠውን ፈቃድ ተቃውመዋል
 • በጋሻው ደሳለኝ ይቅርታ የመጠየቁን ፈቃድ እንዲያገኝ በፓትርያርኩና በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ ላይ የክልል እና ፌዴራል ግለሰብ ባለሥልጣናት ጫና መደረጉ ተጠቁሟል
Begashaw Dessalegn

በሊቃውንት ጉባኤው ለጥያቄ ተፈልጎ ያልተገኘውና በአቋራጭ ይቅርታ እንዲጠይቅ ‹የተፈቀደለት› በጋሻው ደሳለኝ

የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሲዳማና ጉጂ ቦረና አህጉረ ስብከት ልኡክ ዛሬ፣ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የዕርቀ ሰላም ስምምነት መግለጫ በሚያወጣበት በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅ/ገብርኤል ገዳም በጋሻው ደሳለኝ ‹‹ሕዝቡን ይቅርታ ለመጠየቅ›› ፈቃድ ማግኘቱ ተሰማ፡፡

በጋሻው ደሳለኝ ይቅርታ የመጠየቅ ፈቃድ ማግኘቱ የታወቀው÷ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የዕርቀ ሰላም ልኡኩ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ትላንት፣ ከቀትር በኋላ ወደ ሐዋሳ ደ/ምሕ/ቅ/ገብርኤል ገዳም ምእመናን ተወካዮች ስልክ በመደወል፣ በመግለጫው ላይ በጋሻው ምእመኑን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበትና እንደተፈቀደለት፣ የምእመናን ተወካዮቹ በዚህ እንዲስማሙና የማይስማሙ ከኾነ እርሳቸውም እንደማይገኙ ባስታወቁ ጊዜ ነው፡፡

ዋነኛው የዕርቀ ሰላም ንግግር በተደረገበት ኅዳር ፭ እና ፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በተያዘው ቃለ ጉባኤና በተዘጋጀው መግለጫ ላይ የበጋሻው ስም እንኳ እንዳልተነሣ የሚጠቅሱት የምእመናን ተወካዮች፣ የዕርቀ ሰላም ስምምነቱ የሐዋሳ ችግር ብቻ የተዘረዘረበትና የከተማውን ምእመናን ብቻ የሚመለከት እንደኾነ ለብፁዕ ዋና ጸሐፊው ለማስረዳት ቢሞክሩም ብፁዕነታቸው በአቋማቸው በመጽናታቸው ተቀባይነት እንዳላገኙ ተገልጦአል፡፡

የምእመናን ተወካዮቹ ተቃውሞ፣ ግለሰቡ በዕርቀ ሰላም ስምምነት ውስጥ አለመጠቀሱ ብቻ ሳይኾን የሐዋሳ ከተማ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ነዋሪ ምእመን አለመኾኑና ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ሃይማኖትንና ክርስቲያናዊ ትውፊትን በመፃረር በተናገራቸውና በጻፋቸው ሕጸጾች የበደለው የሐዋሳን ብቻ ሳይኾን ቤተ ክርስቲያንንና በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መኾኑን፣ ስለዚህም ከፍተኛ በደሉ በታኅሣሥ ወር ፳፻፬ ዓ.ም. በተቋቋመው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ጉባኤ አባላት ጥምር ጉባኤ ጉዳዩ የተያዘ መኾኑን የሚጠቅስ ጭምር ነው፡፡

በዛሬው የዕርቀ ሰላም መግለጫ በጋሻው የተፈቀደለት የአቋራጭ ይቅርታ ዕድል ተቀባይነት እንደሌለውና ግለሰቡ እንደለመደው ለጥያቄ የሚፈለግበትን ጉዳይ ለማዘናጋትና ለመሸፈን ሊጠቀምበት ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው የምእመናኑ ተወካዮቹ ይገልጻሉ፡፡ የበጋሻው ጉዳይ በሒያጅና በአማላጅ የማይፈታ ሃይማኖታዊ ከመኾኑም አንጻር በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንና የግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. ቅ/ሲኖዶስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ‹‹ለጥያቄ ቀርቦና ጉዳዩ ተጣርቶ እንዲቀርብ›› ሲል በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ቀኖናዊ አካሄዱን ጠብቆ እንዲታይ በጥብቅ አሳስበዋል፡፡Holy Synod on Begashaw

ብፁዕ ዋና ጸሐፊው የበጋሻው ጉዳይ ሃይማኖታዊ መኾኑንና በተያዘው መንገድ ማለቅ እንዳለበት ከዕርቀ ሰላሙ ሒደት መጀመሪያ አንሥቶ ደጋግመው ሲናገሩ እንደነበር ያስታወሱ የዜናው ምንጮች፣ አኹን በድንገት የተሰማው የአቋም ለውጥ በሒደቱ ምልክቱን ሲታዘቡት የቆዩት ውጫዊ ተጽዕኖ ጉልሕ ማሳያ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ ‹‹የሐዋሳ ጉዳይ በዕርቅ ማለቅ እንዳለበት ከመንግሥት በተጠቆመው መሠረት›› የሚሉ አገላለጾች በዕርቀ ሰላም መግለጫው ውስጥ መታዘባቸውን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡

ይህም ኾኖ ጉዳዩን በዕርቅ ለመጨረስ ሁለቱም ወገኖች በተስማሙበት መሠረት ለኅዳር ወር መጨረሻ ቀጠሮ ከተያዘና ቀጠሮውና ጅምሩ የቋሚ ሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ ሳለ፣ በጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት ካልተያዘ በሚል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተደጋጋሚ መወትወታቸው በምልአተ ጉባኤው አባላት ዘንድ በበጎ አልታየም፡፡

የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች እንደሚሉት÷ ‹‹ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ይነሡ፣ የሐዋሳ ደ/ምሕ/ቅ/ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤትና ልማት ኮሚቴ ፈርሶ እንደ አዲስ ይቋቋም›› በማለት የሚጠይቁ 30 ግለሰቦች በስብሰባው ሰሞን ከሐዋሳ፣ ክብረ መንግሥትና ነገሌ ቦረና ከተሞች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋራ መገናኘታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን በቢሯቸው ማነጋገራቸው ተገልጦአል፡፡ ግለሰቦቹም በፓትርያርኩ አመልካችነት የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ወደ ደቡብ ኮርያ – ሴዑል በሄዱበት አጋጣሚ በምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ላይ ተገኝተው ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

ይህም ሁሉ ኾኖ ምልአተ ጉባኤው ጉዳዩ በአጀንዳ ተይዞ እንወስንበት የሚለውን ሐሳብ በከፍተኛ ድምፅ ውድቅ በማድረግ፣ ‹‹ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለያዙት የዕርቀ ሰላም ጥረት ሌሎችን ጨምረን የዕርቀ ሰላም ስምምነቱን ያወርዱ›› በሚል ሁለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በተጨማሪነት ሠይሟል፤ ስምምነቱንና ዕርቀ ሰላሙን አስፈጽመው የመጨረሻ የዕርቁን ሰነድም ለምልአተ ጉባኤው እንዲያቀርቡ ብቻ ነበር ውሳኔው፡፡

ለበጋሻው የተሰጠው በአቋራጭ ይቅርታ የመጠየቅ ፈቃድ በአንድ በኩል ወትሮም ሒደቱን ይተቹ የነበሩ ወገኖች የሚያነሡትን ጥርጣሬ የሚያጠናክር እንደኾነ አስተያየት እየተሰጠ ነው፡፡ በሌላም በኩል ከዕርቀ ሰላሙ በኋላ በሚኖሩ የስምምነቱ አፈጻጸሞችና አገልግሎት ላይም ሊኖረን የሚገባውን ንቁና ያልተቋረጠ ክትትል በእጅጉ አስፈላጊ ያደርገዋል፡፡

Advertisements

39 thoughts on “ሰበር ዜና – በጋሻው ደሳለኝ በሐዋሳ የአቋራጭ ይቅርታ ሊጠይቅ ነው፤ ‹‹ውጫዊ ጫናውን በጉልሕ የሚያሳይ ነው›› /ምእመናን/

 1. ብርክቲ December 8, 2013 at 6:33 am Reply

  ሀራዎች
  አሸናፊ መኮንን የተባለው ግለሰብ በቅርቡ በቅዱስ አትናቴዎስ ስም ቸርች መክፈቱን ሰምተናል። ይህ ነገር እውነት ነው ወይ? እውነት ከሆነ ቤተክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ል ሊኖራት የሚገባው አቋም ምንድን ነው? እስካሁንስ ድረስ የሱን መጽሐፍ በቤተክርስቲያን አካባቢ እየሸጡ የሚገኙ እበላ ባይ ግለሰቦች ላይ ቤተክርስቲያን ልትወስድ የሚገባት እርምጃ ምንድር ነው። የዚህን የሌሎችን በሰውየው ዙርያ ማወቅ የሚገባንን ነገር ለጥንቃቄ አንዲሆን አሳውቁን።

  • ሚሚ December 8, 2013 at 9:40 am Reply

   ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል !
   አሸናፊን በግፍ ያባረራችሁት እናንተ አይደላችሁም እንዴ፤ ስታወግዙት ለንሰሐ እንኳን መች ጊዜ ሰጣችሁት፡፡ ታዲያ አሁን ለምን ትጮሃላችሁ ? ገና በጋሻውም የራሱን ቤተ ክርስቲያን ይከፍታል፡፡
   እነዚህ ሰዎች ከጌታ የተሰጣቸውን ጸጋ / መክሊት አትርፈው መመለስ ይጠበቅባቸዋል፤ ስለዚህ በመጽሐፍም፣ መንገድ ላይም ፣ዛፍ ጥላ ስርም፣ ቤተ ክርስቲያንም እየዞሩ የምስራቹን ቃል ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡
   በጋሻው፣ ያሬድ፣ አሸናፊ……ወዘተ ጠላት በቅናት ተነሳስቶ ቢያሳድዳችሁም፤ እናንተ ግን አደራ የማስተማር ስራችሁን አታቋርጡ፡፡
   ፈሪሳውያን ጌታን በቅንአት ተነሳስተው እንዳሳደዱትና እንደገደሉት ሁሉ፣ ዛሬም ታሪክ መልሶ መላልሶ እራሱን እየደገመ ነው፡፡
   በበጋሻው ደሳለኝ ላይ ያቀረባችሁት ነገር ሁሉ እንኳን ለውግዘት ለክስም የሚያበቃ አይደለም፤………..ቅንአት

   • Anonymous December 8, 2013 at 1:16 pm

    አንቺ መናፍቅ ከሆንሽ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ እዛው አዳራሽ ብትሄጅ አይሻልም ::

   • Anonymous December 9, 2013 at 5:17 am

    @ሚሚ በመጀመሪያ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የማይቀና ምእመን እንዲኖረን አያስፈለግም “የቤትህ ቅንአት በልታኛለች ” እንዳለ ቅዱስ መጽሃፍ አንቺም ወይ ክርስትናን መማር አለዛም በሚያገባሽ ጉዳይ ብቻ አስያየት መስጠት ነው :: አጠቃለው ከቤተክርስቲያን ተወግዘው ወደአንቺ አዳራሽ ሲመጡ ትወያያለሽ እዚህ ቦታሽ አይደለም::

   • girma December 10, 2013 at 5:21 am

    ለማያውቅሽ ታጠኚ ሚሚ……

   • Chrstian December 10, 2013 at 1:55 pm

    If the they have the plan to establish their own church,why they stick on EOTC.

 2. ዘነበ December 8, 2013 at 12:49 pm Reply

  መቼ ነዉ ግን ይህን መነቋቆራችንን ምናቆመዉ? ዓለም ያዉ ቤተክርስቲያን ያዉ፤ ታዲያ የት ይኬድ? ማን ያስታርቀን? ማን ልብ ይስጠን? እንዴትስ አምልኮ ተጠናክሮ አንድነታችን ይቀጥል? ምናለ ይህን መወነጃጀል ብናቆመዉ? ስንት አገር የተቸገረችበት እየተስፋፋ ስማችን እየጠፋ ያለ ጉዳይ እያለ አሁን በእርቅ ጉዳይ, በፍቅር ጉዳይ, በስምምነት እንፍጠር ጉዳይ፣ በልመለስ ጉዳይ፣ ጊዜያችንን እናጥፋ? ለምንድነዉ እንደዓለማዊ ጉዳዪች ፀጉር መሰንጠቅን እንተወዉ፣ አረ ጎበዝ ነገሮችን በበጎ መልኩም እንያቸዉ፤ አረ ከትርምሳችን እንመለስ፡ ከእኛ በላይ እኮ ስለቤተክርስቲያን የሚቆረቆር አምላክ አለን፡፡ ኦ አንተ ይቅር በለን፡፡

 3. Anonymous December 8, 2013 at 1:13 pm Reply

  የተፈራው ደረሰ መናፍቃንን መልሶ ወደ ቤተክርስቲያን መሰግሰግ ሆነና አረፈው::ግን የአባቶቻችን ሸፍጥም አሳዛኝ እየሆነ መጥቷል እግዚአብሔር ለአባቶቻችን መልካሙን መንገድ እንዲከተሉ ይርዳቸው

 4. Anonymous December 8, 2013 at 1:46 pm Reply

  ታዲያ እነዚህ አባቶች ነገ መናፍቅ ጳጳስ ለምሳሌ ሰረቀን…እንዲሁም ሌሎች መናፍቃንን ላለመሾማቸው ምን ዋስትና አለን ? የሚያሳዝን ግዜ ላይ ደረስን ::

 5. Getachew December 8, 2013 at 10:42 pm Reply

  Merejachun bertubet gin ebakachu alu alu.. yemeslal..eyetebale neaw..sintktik..shukshukk.. melkam yemimeslewnm endeminm bilachu qebaqeba kaladeregachut yeBetekrstean dehninet yemaytebek weynm chigir yalebet enkuan endemaygelets yemtasibu atmselu… Seawu gira yemiagaba mereja tifategnawn mayet gira eskigeba atadrgu bakachu…ebakachu sileBetekrstean! Chigrwan yabsewalna… Sititsifu bizu yemtasibubet aymeslm! Sile Egziabhear Bet sayhon be abzagnaw tilacha ena poletica poletica yemimesil atsatsaf yetaybetal. Love!

 6. Anonymous December 8, 2013 at 11:26 pm Reply

  ሃራዎች የፃፍኩትን በምትፈልጉት መሰረት ቀይራችሁ ማቅረብ ጀመራችሁ ምነው ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ መናፍቅ አይደለም ለማለት ነው ምነው ፈራችሁ የ አሁኑ ሹመት ውስጥ መካተቱን እኮ ይታወቃል ::

 7. Anonymous December 9, 2013 at 5:09 am Reply

  ይቅርታ ምን ማለት ነው ??? ማንን ነው ይቅርታ የሚጠይቀው ??? የ ሃይማኖት ህጸጽ በይቅርታ የሚታለፍ አይደለም እባካችሁ የሃዋሳ ምእመናን በርቱ …..ለእንደዚህ አይነት ቀልድ ቦታ አትስጡ

  • Anonymous December 9, 2013 at 9:30 am Reply

   This is not the responsibility of the people of Hawassa. The Hawassa people done their best and identified the protesters of the church. Now it is the responsiblity of every body to fight againist the church enemies. Every body has the right to oppose what is going on.

 8. ክነፈርግብ December 9, 2013 at 6:48 am Reply

  ኁሉም ራሱን ይመርምር፡፡ምንጫቸው ባልታወቀ ቆርጦ ቀጥል ቪሲዲዎች የእነዚህ ልጆች ሞራል ምን ያህል እንደተነካ አይተናል፡፡የግል ስልካቸውን እስከመጥለፍ የደረሰ የመብት ጥሰት በጠራራ ፀሀይ ተፈጽሞባቸው በዚያው ላይ ራሳቸውን ለመከላከል እንኩዋ እድል በማይሰጥው የኢንተርኔት ዓለም የደረሰባቸው ወከባ እጅጉን ልብ ይሰብር ነበር፡፡

  አንዳንድ ወንድሞች አንድ ሰሞን በግልጽ ራሳቸውን ተሀድሶ ብለው የለዩ 5ት መነኮሳትን(እነ አባ ዮናስ) ጉድ ቀርጸው በማሳየታቸው የበዛ ምስጋና እና ታዋቂነት ተችሩዋቸዋል፡፡

  ታዲያ አሁን የልጅ ነገር ሆነና ይቺን ምስጋና ደጋገሞ ለማግኘትና እኛ ባንኖር ኖሮ ኦርቶዶክስ አልቆላት ነበር ለማስባል በሚመስል መልኩ ግዳይ ለመጣል ሲጥሩ አጥብቀው በጭፍን ይተኩሳሉ፡፡እነበጋሻው በዚህ የጭፍን ተኩስ ከቆሰሉት መሀል ናቸው፡፡

  ደግነቱ ቆስለውም እንደ ቀድሞዎቹ መነኮሳት አሰፍስፎ ሲጠብቃቸው በነበረው ጠላት(መናፍቃን) እጅ አልወደቁም፡፡አባቶችም ይህን የልጆቹን ጽናትና አንዳንድ ሊታረሙ የሚችሉ ካለማወቅ ብቻ የመጡ የምግባር ህጸጾችን አይተው ይመስለኛል ግማሽ መንገድ ሄደው “ለስሂት መኑ ይሌብዋ!!” ብለው ለእርቅ የተቀበሉዋቸው፡፡

  ታዲያ የሃይማኖታችን የበላይ ቅዱስ ሶኖዶስ ያመነበትንና ብጹአን ጳጳሳት የተሳተፉበትን የእርቅ ሂደት የምንኮንን እኛ እነማን ነን??የምን ከጳጳሱ በላይ አማኝ ነኝ ማለት ነው??የሚጨበጥ ማስረጃ ካለ አባቶችም በሩን የሚዘጉ አይመስለኝም፡፡ስለዚህ ማስረጃው ያለው ያለፉት 2 አመታት ካልበቁት አሁንም ያቅርብ!!እንጅ ካፈርኩ አይመልሰኝ ብሎ ልጆቹን የማሳደድ ዘመቻ በዚሁ ቢያበቃ መልካም ይመስለኛል፡፡አልዕሉ አልባቢክሙ….ነስሁ…ባለማስተዋል በምንወረውረው ድንጋይ ብዙ የዋሃን በጎች በርግገዋል!!!

  አስተውሉ!! ወትሮም እነዚህን ልጆች ደጋግሞ መናፍቅ እያለ ሊለያቸው የፈለገ የኢንተርኔቱ ዓለም እንጅ ቅዱስ ሲኖዶስ አይደለም!!ስለዚህ ይመከራሉ ይገሰጻሉ እንጅ የምን ቀኖና ነው!!

  እረ ተው!! ማንም ተራ አማኝ የጠረጠረውን ሰው ሁሉ ከመሬት እየተነሳ ከሲኖዶስ ቀድሞ መናፍቅ የሚልበት ስርዓት ከማን ያገኘነው ነው?? እንዲህ ከቀጠለስ እርስ በርስ መናፍቅ..መናፍቅ ስንባባል መኖራችን አይደል፡፡ይሄ እኮ በሌላ ቁዋንቁዋ የሃይማኖታችንን መርህ የጣሰ ሃይማኖታዊ ህግ አልባነት(anarchism) ነው፡፡መንግስት እንኩዋ ግለሰቦችንም ሆነ ድርጅቶችን አሸባሪ ከማለቱ በፊት ቀድሞ በፓርላማ ስያሜውን ያጸድቃል፡፡የኛ ፓርላማ ደግሞ ሲኖዶስ ነው ስለዚህ ሲኖዶሱ በመናፍቅነት ከማውገዙ እየቀደምን ፍርድ ባንሰጥ!!

  ብሎጎችም ግለሰቦችን መናፍቁ…ተሃድሶው…ሙሰኛው…ቅጥረኛው…ዘማዊው… እያሉ ቀድመው ደምድመው ከመጥራት ቢያንስ “በመናፍቅነት የሚጠረጠረው(ለሱም ማስረጃ ካለ)” የሚሉ የለዘቡ አገላለጾችን ቢጠቀሙ እኛንም ከውዥንብር ያድኑናል ተጠርጣሪውም ደንብሮ ከመሄዱ በፊት የንስሀ ጊዜ ያገኛል!!!
  እናስተውል!!

 9. Mieraf December 9, 2013 at 6:50 am Reply

  መንግስት እጁን በቤተክርስቲያን ጉዳይ እጁን ጣልቃ ማስገባት እስካልተወ ድረስ አሁንም ተሃድሶ መስፋፋቱ እና የቤተክርስቲያናችን ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ እማይቀር ነው……..የተሀድሶዎች እንቅስቃሴ እጁ ሰፊ እና አስፈሪ ነው ከምንግዜውም በላይ የምንመካበት እግዚአብሄር እንዲያስበን ተግተን ነው መጸለይ ያለብን

  • ሚሚ December 9, 2013 at 3:12 pm Reply

   @ Mieraf
   ተሃድሶ ዛሬ አልተጀመረም ፤ ከ2000 ዓመታት በፊት ከኢየሩሳሌም ጉባዔ ጀምሮ የነበረ ነው፤ የመጀመሪያውን ተሃድሶ ያደረጉት ሐዋርያት ናቸው (ሐዋ.ስራ 15፡1 )፡፡ ስለዚህ ተሃድሶን አትፍሪ፣ ተሃድሶ መቀስ ነው ግንዱን መቁረጥ አይችልም፤ ተሃድሶ መቁረጥ የሚችለው ቅርንጫፉንና ትርፍ ነገሮችን (ተረት ተረቱን) ብቻ ነው ፡፡
   በተረፈ በጸሎትሽ በርቺ
   ቻው የኔ ማር

   • Chrstian December 10, 2013 at 2:15 pm

    Mimi be tewahido esat tibelalachihu….tehadisowoch….2000 mini ametachihu hawariyat ema kidistitun emnet meseretu lezelalemum sitabera tinoralech!

 10. kasa December 9, 2013 at 7:19 am Reply

  ‹‹ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ይነሡ፣ የሐዋሳ ደ/ምሕ/ቅ/ገብርኤል ሰበካ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤትና ልማት ኮሚቴ ፈርሶ እንደ አዲስ ይቋቋም›› በማለት የሚጠይቁ 30 ግለሰቦች በስብሰባው ሰሞን ከሐዋሳ፣ ክብረ መንግሥትና ነገሌ ቦረና ከተሞች ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ከትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋራ መገናኘታቸውን ተከትሎ ሚኒስትሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን በቢሯቸው ማነጋገራቸው ተገልጦአል፡፡ቂቂቂቂ 30 ሰዎች!! አንቺ መናፍቅ ከሆንሽ እዚህ ምን ታደርጊያለሽ እዛው አዳራሽ ብትሄጅ አይሻልም ::

 11. Bigi December 9, 2013 at 7:19 am Reply

  Wugzet endih rkash hone?? Menfes qdus wede ewnet yimrachu!!

  • ሚሚ December 9, 2013 at 2:12 pm Reply

   @ Bigi
   “እርጉም ተረጋግሞ ያልቃል” ሲባል አልሰማህም
   አባታችን ኖህ ከረገመን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስንረጋገም እየኖርን ነው፡፡

 12. Anonymous December 9, 2013 at 9:59 am Reply

  It is a big SHAME!

 13. Wogderes December 9, 2013 at 10:56 am Reply

  በዚህ የእርቅ ስነ ስረዓት ላይ በአጋጣሚ ተሳተፌ ነበር፡፡ አጠቃለይ ድባቡ እጅግ ደስ የሚል ነበር፡፡ ከቤተ ክርስቲያን በምንም ምክንያት ይሁን የወጣ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመለስ ማየት በጣም ደስ ይላል፡፡ ይሁን እንጂ በእርቅ፤ ሂደት ውስጥ መግባት ያልነበረበት ጉዳይ የአቶ በጋሻው ጉዳይ ነው፡፡

  አቶ በጋሻው ከቤተክርስቲያን የወጣው በአዋሳ ህዝብ ላይ ድንጋይ ወርወሮ ፈንክቶ ወይንም ተፈንክቶ ሳይሆን በተለያዩ የሀገራችን ክፍችሎ ላይ የቤተክርሰቲያኒቱ ያልሆነ ትምህርት በማስተሩ መራ ተገኝቶበት የሚመለከተው የቤተ ክርስቲያኒቱ ህዝብ አገደው እንጂ፡፡ ታዲያ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያውቀውን ጉዳይ እዚያ ነበሩ አባቻችንን ለምን በዚህ መልክ አደረጉት፡፡

  እጅግ አዝናለሁ፡ ጥፋኛ በጥፋቱ ሳይጠየቅ ወይንም ጥፋቱን ሳያስተካክል ዝም ብሎ አድበስብሶ ማለፉ ማን ሊጠቅምን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን፤ አባቶችን ታራቂውን፡፡ ከሁሉም በላይ ግለሰቡ የአዋሳ ህዝብን እንዲወክል ማን ፈቀደለት፡፡ በይቅርታ አጠያየቅ ሂደቱም ግለሰቡ ታላላቅ አባቶች ባላጠፉት እኔ ጥፋተኛ ነኝ ሲሉ እርሱ አሁን ቶሎ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቲ ገብቶ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ህዝብ ሞልቶ ስለ ማስተማሩ ተናገረ እንጂ ስለ ጥፋተኘቱ አልነበረም፡፡

  ለሁሉም እኔ እርቁን ጥሩ ነበር እያልኩ ግን በይቅርታ መታለፍ ማይገባውን የክደት ትምህርት ያስተማረን ግለሰብ እዚህ ውስጥ መቀላቀሉ፤ ትሩሙ ስልገባኝ የሚመለከተው አካል አሁን ጉዳዩን በድንብ ቢያየው እላለሁ፡፡

 14. simegne December 9, 2013 at 11:34 am Reply

  በርግጥ ልብና ኩለሉላሊትን መርማሪ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የነበጋሻው የይቅርታ ጉዳይ ታጥቦ ጭቃ ሆኖ የቀረሩትን ምዕመነናን የማውጣት አላማ እንዳይኖረው እሰጋለሁ፡፡ ፈጣሪ ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን እኛንም የቤቱ ተክሎች ያድርገን አሜን፡፡

 15. kahn December 9, 2013 at 1:16 pm Reply

  1. የክልልና የፌደራል ባለስልጣናት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር መቼ፣በምን ቦታና ሁኔታ እንደተገናኙ፣ከተገናኙም በሁዋላ በእርግጥም ስለጉዳዩ ስለመወያየታቸው የማስረዳት ግዴታ ነበረባችሁ፡፡ግን አላደረጋችሁትም፡፡ይሁን፡፡ለመሆኑ እነዚህ ባለስልጣናት በፕሮቴስታንትነት የሚጠረጠሩ እንደመሆናቸው መጠን ከእርቁ የሚያገኙት ጥቅም ምንድን ነው??እርቁ እኮ ለአንድነት እንጅ ኢኦተቤክ ከድርሻዋ ቆርሳ ለመናፍቃን አክሲዮን የምትሸጥበት አይደለም፡፡ልጆቹ “በፕሮቴስታንቶች ፈንድ ይደረጋሉ” ስትሉ ትቆዩና መልሳችሁ ደግሞ አሁን እንታረቅ ያሉት “የቪሲዲ ገበያ ስለቀዘቀዘባቸው ነው” ትላላችሁ፡፡የተምታታ ነገር፡፡ፈንድ ከተደረጉ ለቪሲዲ ሽያጭ ምን አስጨነቃቸው??ሀቁ ግን አለው ነገር የሚለው መዝሙር ሲዲ እንኩዋ ከ80ሺህ ኮፒ በላይ በመሸጥ የ2005 ዓ.ም ባለሪከርድ መሆኑና የዘርፌም መዝሙር ለ50 ሺህ በላይ ታትሞ ወደ ገበያ መውጣቱ ነው፡፡ (በዘርፌ መዝሙር ውስጥ ባለው የይዘት ስብጥር ግን እኔም ደስተኛ አለመሆኔን መግለጽ እወዳለሁ፡፡)

  2. የሀዋሳው ሁከት የተፈጠረው በነበጋሻው ምክንያት ነው እየተባለ ጉዳዩ ለእርቅ ሲቀርብ እነሱ “የሀዋሳ ምእመናን ስላልሆኑ ለእርቅ አይቀርቡም” ማለት ምንድን ነው??ይሄ በሌላ አነጋገር የአዲስ አበባ መኪና ሀዋሳ ላይ የከተማውን ነዋሪ ቢገጭ ባለመኪናው አዲስ አበቤ ስለሆነ በሀዋሳ ትራፊክ አይጠየቅም እንደማለት ነው፡፡የአካባቢ ምእመን መሆን የሚጠየቀው ለአጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አባልነት ምርጫ እንጅ ቂምና በቀል ለማስቀረት በሚደረግ እርቅ አይመስለኝም፡፡

  3. ቁማር የሚለው ቃል ለሃይማኖት ማስተማሪያነት ያውም በፈጣሪና በፍጡር መሃል ሲቀርብ ለአእምሮ ይከብዳል፡፡ቢሆንም በኑፋቄ ደረጃ አላየውም፡፡ምክንያት(1)የምሳሌው ሚስጥር ሲፈታ አሸናፊ የተባለው ጌታ ስለሆነ፣(2)ፈታኙ ዲያብሎስ ጌታን ከልደቱ እስከ ስቅለቱ በነበረው የስጋ ወራት እንደ እሩቅ ብእሲ(ተራ ሰው) ይፈትነው እንደነበር በቅ/መጽሀፍ ከመጻፉም በላይ ቅ/ያሬድም ይህንኑ የዲያብሎስ የተሸናፊነት ኑዛዜ ትምህርተ-ህቡዓት በተሰኘው ድርሰቱ “መኑ ውእቱ ዘነኪር እምህግየ…….መኑ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ……መኑ ውእቱ ዘበብዝሀ ብርሀኑ ለጽልመት ዐዖሮ”(ነፍስን ከስጋ ከምለይበት ህግ የተለየ፣በብርሀኑ ማዕበል ጨለማን የሚያሳውር ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ማን ነው??) እያለ በዲያሎግ መልኩ ይገልጸዋል፡፡ በጋሻው ደግሞ እነዚህ አገላለጾች ለዘመኑ ወጣት አይገቡም ብሎ አስቦ ወጣቱ በሚያውቀው ቁማር ወርዶ ለማስረዳት ሞከረ፡፡(3)እንዲህ አይነት የየዘመኑ ምሳሌዎችን ተጠቅሞ ማስተማር ከጥንትም የነበረ ሲሆን አሁንም በቅኔ ቤት በሰፊው ይሰራበታል፡፡ግእዝ የምትረዱ እስኪ ዝክረ ሊቃውንትን(በመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ የተጻፈ) እዩ፡፡ አማርኛ ብቻ የምትችሉ ደግሞ የአለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊን መጽሀፍ አንብቡ፡፡ ወይም የቅኔ መምህራንን ጠይቁ፡፡ቅኔው ሲፈታ ሚስጥሩ የተቃና ሆኖ ይገኝ እንጅ በቅኔ ቤቶቻችን ብዙ አይነት ምሳሌዎችን ለመጠቀም ሊቃውነት የደራሲነት መብታቸው ነው፡፡

  ለምሳሌ፡
  ጉባኤ-ቃና፡(1) ቅርብት ይእቲ መንግስተ-ሰማይ ሀዳስ፣
  አምጣነ በጽሀ በእግር አሀቲ ተ/ሃይማኖት ሀንካስ፡፡
  ትርጉም፡ ቅርብ ናት አዲሱዋ የሰማይ መንግስት፣
  አንካሳው ተክልየ ባንዱ እግሩ ገባት፡፡

  (2) ዘማ መቅበርት ለወልደ ነጎድጉዋድ ትቤሎ፣
  እመ ትጸልአኒ አንተ ዘያፈቅረኒ ሀሎ፡፡

  ትርጉም፡ አለች(ው) ዮሀንስን ዘማዋ መቃብር፣
  አንተ ብትጠላኝ አለኝ የሚያፈቅር፡፡
  ሚስጥሩ፡ ዮሀንስ ሳይቀበር አርጉዋል ነው፡፡

  ሆኖም የቅኔ ደቀመዛሙርት በጣም የወጣ ምሳሌ መስለው ሲገኙ ምሳሌው ጸያፍ ነው ይባልና በመምህሩ ይታረማል እንጅ ተማሪው አይወገዝም፡፡አፉን እየጠበቅን ካወገዝነውማ ፈጠራውም ውሃ በላው!!!ልጁም በሰቀቀን ቅኔውን መቁጠር ተወው!!!ስለዚህ በበጋሻው ላይ የተነሳው ቁማርን የተመለከተ ክስ በአባቶች እርማት የሚታለፍ እንጅ ውግዘት የሚያስመጣ አይመስለኝም፡፡ቢያንስ በምንም መልኩ ይህን የቁማር ምሳሌ ያነበበ ሰው መጨረሻው መናፍቅነት ይሆናል የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ አንችልም፡፡

  • Anonymous December 9, 2013 at 11:59 pm Reply

   ደስ የሚል ትንታኔ ነው ።

  • Anonymous December 11, 2013 at 3:08 pm Reply

   hmmmmmmmmm

 16. feyisaaaa December 9, 2013 at 2:01 pm Reply

  Egzeabher lhulachinm mastawolin yisiten Amen!!!!!!

 17. Annonyname December 9, 2013 at 2:08 pm Reply

  የዚች አገር ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ የመንግስት አካላቱ ለዘመናት ሲፈልጉት የነበረውን ሥልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ አሁን ድብቅ ሴራቸውን መሥራት ጀመሩ፡፡ ዱሮም ዓላማቸውን ፖለቲካ አልነበረም፤በስህተት ስብከታቸው መውሰድ ያልቻሉትን ምዕመን ለመውሰድ፤ለዚህም ተቀዳሚ ተግባራቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቷን መናድ፣ሊቃውንቷን ማሳደድ፣ ከዚያም ምዕመኑን እርቃኑን ካስቀሩ በኋላ ወደ ፈለጉት አቅጣጫ መንዳት ነው፡፡ እባካችሁ ወገኖቼ ምዕመናንና እንዲሁም ቀና መንፈስና ሃይማት ያላችሁ አባቶች ይህንን እኩይ ተግባራቸውን በፅኑ እንዋጋው፡፡ ይህንን ስናደረግ ምንአልባትም የሥጋ ሞትን ፈርተን ወደ ኋላችን አንበል፡፡ ወገኔ እስከ መቼ ነው ዝምታው? በዚህ የምንገደልው ግድያ ለክብር ያበቃናል፡፡ ፈርታችሁ ይሆን? አይዞን!! አንድ ቀን እውነቱን ተናግረን እንገደል!! እንሙት!! ፈጣሪ ሆይ የእኛን በደል ሳትመለከት የቸርነት ሥራህን ስራልን፡፡

 18. ወ/ሮ ዘርፌ December 9, 2013 at 3:58 pm Reply

  ወንድሞቼ/ እህቶቼ ይህችን መዝሙር በህብረት እንዘምር

  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፤
  ቅዱስ ሲኖዶሱም እውነት መሰከረ፤
  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣
  በጋሻው ደሳለኝ ስራውን ጀመረ፤
  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣
  ከሳሽ ማህበርም በስራው አፈረ፤
  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣
  ስራ አስኪያጁም ከሐዋሳ ተጫረ ፤
  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣
  የልዩነት መንፈስ ከእኛ ላይ በረረ፤
  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣
  የተዋህዶ ልጆች አንድነት በሰረ፤
  እሰይ ስለቴ ሰመረ፣ እሰይ ስለቴ ሰመረ፣
  እልልልልልልልልልልልልልልልልልልል

  • Anonymous December 9, 2013 at 5:56 pm Reply

   አንቺ መናፍቅ ምን ልትሰሪ መጣሽ እዛው አዳራሽ አትሄጅም

 19. Anonymous December 9, 2013 at 5:01 pm Reply

  አብ ያልተከለው ግንድ ሁሉ አይጸድቅም፡፡

 20. Tewodros December 10, 2013 at 12:22 am Reply

  Wesagn ena feraj YeEgziabhearn fekad bemigeba yemaywk sim bicha yehone TEKORKUARI bezzzzza!

  Sinodosun sayhon agelgaun siltan yesete tiwld! meferaredun telemamednew! dirketachin yeKirstosin fekad alemawek new, yetgnaw tsadk weynm semaet Abat endastemaren gira yegebal! astemariachin man yehon? Abatoch gudaun keyazut, Kemenfes Kidus gar yemiserubetn enante! Egna! adebabay lay mindinen?? Mereja kalen lemin anakeblachewm??? manim ke computer jerba yetsafewns eyanebebn lemn ech! Enlalaen, enferaredalen, enaweraln?? Abatochn atakalu!? Sinodosun atakalu!?

  betekrsteanuan lenege adega atamechachwat…alemawi aydelechm ! Ye alemawi agelalets, akahed, mikikir,….ersuan letelat be andim belela menged metekmia yadergatal enji ayaterflatm,…yemiaterflat Amlakwa befekedew menged, bota,… mikikir, weyeyt, akahed new:: Egziabhearn endalamenew anhun,emnetachinin enastaws! sasibew ende Betekrsteanachn lijochwa/ agelgayochwa bedemenefs beye diregetsu! be adebabay erkanwa yemizekzeklat..telatm hone yetelat telat yemiakdilat! Yemisalekbat Betekrstean YALE AYMESLEGNIM! ebakachu yebkan! yegid 1000 mehonina mot ena seyf edejachn mekom alebet astewy ena tenkara kirstean lemehon?! ebakachu mengedh tikikil new ye ene akahed be ante keyrlgn enbelew Egziabhearn????! hulachinm bintegna Ersu metebek yemaychalew anhun?? enamnalen awo! Emnetachhin sira yemaygeltsew protestantawi ye lib maninetnachinin enastewlew! meamen yehone Betekrsteanun yemiwed Betekrsteanu yehedal! Eziam sile Betekrsteanu yegeletsiletal Higawi ena Keteregagetelet ye Betekrstean minch yalewn guday yesemal, TETEYAKINET balew agelgay, kifil:: halafinetachinin Ende Egzeabhear Fekad ena ORTHODOXAWINET enweta!!!? lemin yeBetekrsteanitu wana dihre getsochin anketatelm, antebkim? lemsale ye Mahibere Kidusan wana d. gets lay antebabekim???? lemins yeBetekrsteanituan guday be tikiklegna menged angeltsim, aniketatelm? Alemawi silehonin, alemawkachin, yegil ena wegentegninetachin, weregninetachin, yetelat agelgaynetachin…, min yehon??

  Egziabhearm ye kedemu abatochim yehin aynet yeKinat agelgilot alastemarunm Mengedun enketel! bedelu tezergifo ligeletibet yemigeb arios enkuan binor ende alem sayhon ende Egziabhear akahed, agelalets bicha neaw Bayhon Egziabhear Menfes Kidus yelelebet, sirawm dikam ena tifat BICHA yehonal:: akuhuanachinin enastekakil?! Yemnargebegibewn lemaketatel diabilos zewetr yeseral, Sirachinin Mesrat Bemigeban ena ende Kirstnachin sile nefs/ nefsoch gidetachnin ensra::

 21. አእነንቀቁ December 10, 2013 at 7:33 am Reply

  ማን ይሆን ለምዕመኑ የሚያስበው?

  በተለያዩ ጊዜያት በአዋሳና በዙሪያዋ ያሉትን ሰባኪያን ተብዮች የተነሳ ህዝቡና ቤተ ክርስቲያን በብዙ ሲተራመሱ ቆይተው፤ መቋጫ አገኝ ሲባል በማን ስህተት እንደሆነ አይታወቅም ሌላ ጽንፍ ይዞ የመከራከሪያና መለያያ ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ ባለብሎጎችም፤ ጥሩ ርዕስ ያገኙ ይመስለኛል፤ ለራሳቸው ግብዓት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ በመካከል ያለው ምዕመን የፈረደበት ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በጸጥታ ከአምላኩ ጋር መነጋገር አልቻለም፡፡ እነዚህ አይነት ድርጊቶች ምዕመኑን ዋዘኛ ፈዘኛ፤ ቤተ ክርሰቲያን ያለ እየመሰለው ግን ልቡ የሸፈተ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

  እኔ የሚገርመኝ አባቶች ናቸው፤ ማንን ነው የሚፈሩት? ሞትን፤ ስድብን፤ ባለስልጣንን፤ እውነትን አውጥተው እስካልተናገሩ፤ በጋራ ለወሰኑት ውሳኔ በግል ቁርጠኛ መሆን፤ ካልቻሉ ሲኖዶሱ መንፈስ ቅዱስ ይመራዋል ሚለውን እውነታ በእነርሱ ማየት ካልቻልን፤ የአባትነት ደንቡስ የቱ ጋ ነው፡፡ አንዳንዴ የይልማ መዝሙር የእቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሳ የሚለው፤ በእውነት ዘመኑን የዋጀ ነው፤እላለሁ፡፡ አቡን ጴጥሮስ ለሀገሬና ለሃይማቴ ብለው ስጋቸውን አሳልፈው ለሞት ሰጡ፤ ሌሎችም እንደዚሁ፤ ታዲያ የዛሬ የእኛ አባቶች ምን ነካቸው? ጥፋተኛ ነው ያሉትን አካል ጥፋቱን ሳያስተካክል፤ ግባ በለው ማለታቸው፡፡

  ሰባኪያው ትክክለኛ ከነበረ እኛ ተሳስተን ነው ብለው በግልጽ ይቅርታ መጠየቅ ካባቸው ይጠይቁ ያኔ ምዕመኑም መናፍቁ ማን እንደሆነ ማወቅ ይችላል ብዬ አሳባለሁ፡፡ ባለ ብሎጎችም ጉዳዮችን ማረገባችን ትታችሁ እባካችሁ ግራ የገባውን ምዕመን አስታውሉና ትክክለኛውን መረጃ፤ስጡን፡፡

 22. Anonymous December 12, 2013 at 10:13 am Reply

  This post by itself is rather NON-SENSE

 23. Anonymous December 13, 2013 at 6:11 am Reply

  በጣም ያሳዝናል በጋሻው ደሳለኝ ስለቤተክርስትያን ቀኖናና ስርዓት ትምህርት ገና ያልገባውና በድምጽ ብቻ የእግዚአብሔር መንግስት የሚወርስ የሚመሰለው በትዕቢት የተወጠረ በመሆኑ እንደገና በቤተክርስትያን ስርዓት መታነጽ ስላለበት ከሰንበት ት/ቤት ገብቶ መማር ያለበት መሆኑን ያሳየበት የዕርቅ መድረክ ነበር፡፡

 24. Anonymous December 13, 2013 at 2:33 pm Reply

  we should understand the way how to approach all protestantism system in our church …. EOTC SHOULD not accept those betrayers who plays their agenda in side the temple

 25. Anonymous December 23, 2013 at 12:55 pm Reply

  Come to your senses man! Your gods (the missionaries) in the Western world fed into your poor soul the poison of hatred towards your own history and values including religion and culture in the name of Christianity. The funny thing is those same people who pretended to have preached to you our Lord Christ have long changed their churches into night clubs, museums, art galleries…. Remember they sent their satanic spies as missionaries to Ethiopia to “evangelize” the already EVANGELIZED. Their main MISSION however was to sow seeds of division and hatred among us the sons and daughters of Ethiopia so that we will fall prey to their long term agenda of breaking our pride and make us ready for them to use us as they wish. Please use your intellect, come to your heart and rejoin with the original, apostolic, absolutely true church that is the ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH. This church belonged to your fathers and mothers and yourself although you betray it now. Don’t ever continue collaborating with the enemies of Ethiopia who always work hard to destroy her history, including her ancient true church.let strugle them whom support their mission.

 26. kasa December 23, 2013 at 12:56 pm Reply

  Come to your senses man! Your gods (the missionaries) in the Western world fed into your poor soul the poison of hatred towards your own history and values including religion and culture in the name of Christianity. The funny thing is those same people who pretended to have preached to you our Lord Christ have long changed their churches into night clubs, museums, art galleries…. Remember they sent their satanic spies as missionaries to Ethiopia to “evangelize” the already EVANGELIZED. Their main MISSION however was to sow seeds of division and hatred among us the sons and daughters of Ethiopia so that we will fall prey to their long term agenda of breaking our pride and make us ready for them to use us as they wish. Please use your intellect, come to your heart and rejoin with the original, apostolic, absolutely true church that is the ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH. This church belonged to your fathers and mothers and yourself although you betray it now. Don’t ever continue collaborating with the enemies of Ethiopia who always work hard to destroy her history, including her ancient true church.

 27. Hi there, its pleasant article about media print, we all be familiar with media is
  a enormous source of data.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: