ሰበር ዜና – የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

ኄኖክ ያሬድ

Meskel Demera Celebration at Meskel Squareየኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡

ስለ ቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንጸባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመኾኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡Meskel Demera Celebration01

የዩኔስኮ ኮሚቴው በረቡዕ ስብሰባ ውሎው  ከመስቀል ሌላ ከተለያዩ አገሮች 13 መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶችን በሰው ዘር ቅርስነት መመዝገቡንም በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ መስቀልን ጨምሮ እ.ኤ.አ. በ2013 የተመረጡትን የ14ቱ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ገጽታ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችና ፎቶዎችም በዕለቱ በድረ ገጹ ላይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡

በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን በመላ አገሪቱ በአደባባይ ደመራ የሚከበረው የመስቀል ክብረ በዓል የመጀመርያው መንፈሳዊ (ኢንታንጅብል) ባህላዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ የተመዘገበላት ኢትዮጵያ፣  ዘጠኝ  ግዙፍ (ታንጀብል) ቅርሶች ማስመዝገቧ ይታወቃል፡፡

Advertisements

7 thoughts on “ሰበር ዜና – የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

 1. Anonymous December 5, 2013 at 12:29 pm Reply

  Egiziabher yemasgen Melkam zenanaw!!!

 2. Anonymous December 5, 2013 at 7:19 pm Reply

  wonderful.This is the result of the good effort of His holiness Abune Paulos and our smart government. may the Almighty God rests in good place the soul of our beloved Patriarch Abune Paulos and He may bless our leaders.

 3. Anonymous December 5, 2013 at 8:16 pm Reply

  LeMeskel Beal kibirr – Siyansew new. Lefetari sira gin – yihem aydenkim. yeErsu wileta yeErsu deginet hulem dinkk newina. “Beliwo leEgziAbHer Girum Gibrike.” Dinkk zena new lebetekirstianachin.

 4. Gebeyehu December 6, 2013 at 1:57 am Reply

  Thanks to God ! We all Ethiipian have to celebrate this special day.

 5. Anonymous December 6, 2013 at 10:31 am Reply

  enkuan des alen

 6. Anonymous December 7, 2013 at 2:53 am Reply

  Gena sintu yaltemezegebe ale!!!

 7. Anonymous December 7, 2013 at 4:37 am Reply

  egziabhir ytemesgen yehun
  konjo zena

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: