ቤተ ክርስቲያን ለሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሽ ወገኖች 2 ሚልዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ ሰጠች

 • ‹‹ስደተኞችን በእንግድነት ተቀብለን እየተከባከብን አኑረናል፤ ሸኝተናል፡፡ እኛ ስደተኞች ኾነን እየተደበደብንና እየተገደልን መገኘት የለብንም፤ አይገባንም›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሳዑዲ ዓረቢያ በመመለስ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚኾን የሁለት ሚልዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ አበረከተች፡፡

MK feeding the Saudi returness00

የሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሽ ወገኖች በቦሌ የስደተኞች ጊዜያዊ መቀበያ ጣቢያ (ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን)

ትላንት፣ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀትር በፊት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በተጠራ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው÷ ረዳኤ ምንዱባን ምስካየ ኅዙናን ቤተ ክርስቲያን ከስደት ተመላሽ የኾኑ ወገኖች ተመልሰው እንዲቋቋሙና ሕይወታቸው በተረጋጋ ኹኔታ እንዲቀጥል፣ ከመጸለይና ከማስተማር ባሻገር የሰብአዊ ርኅራኄ ተግባሩ በመዲናይቱ አዲስ አበባ ሳይወሰን በየአህጉረ ስብከቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ታደርጋለች፡፡

ተመላሾቹን በቦሌ የስደተኞች ጊዜያዊ መቀበያ ጣቢያ ተገኘተው ማጽናናታቸውን የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የተቻለውን ያህል ረድኤት ከስደት ተመላሽ ለኾኑ ወገኖች መፈጸም እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

MK feeding the Saudi returnees

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን – ረዳኤ ምንዱባን ምስካየ ኅዙናን (ፎቶ: ማኅበረ ቅዱሳን)

የጉባኤው ተሳታፊዎች ለኾኑ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችና ድርጅቶች ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት 169 አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና የጽ/ቤት ሠራተኞች ቅዱስነታቸው እንደተናገሩት፣ ‹‹ባለን አቅም ለወገኖቻችን ቀዳሚ ደራሾች መኾን አለብን፡፡ እኛ ከዚህ እንደተቀበልናቸው ወደየቤታቸው ሲመለሱ ደግሞ አህጉረ ስብከት ሊቀበሏቸውና ሊደግፏቸው ያስፈልጋል፡፡ ስደተኞችን በእንግድነት ተቀብለን እየተከባከብን አኑረናል፤ ሸኝተናል፡፡ እኛ በሰው ሀገር ስደተኞች ኾነን እየተደበደብንና እየተገደልን መገኘት የለብንም፤ አይገባንም፡፡››

ለየሳዑዲ ዓረቢያ ከስደት ተመላሽ ወገኖች በትላንትናው ዕለት የተደረገው የሁለት ሚልዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ፡- ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ብር 500,000፣ ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ብር 200,000፣ ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ብር 1.3 ሚልዮን አስተዋፅኦ የተሰበሰበ መኾኑ ተገልጦአል፡፡

አዲሱ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን ምደባም በተገለጸበት በዚኹ ጉባኤ ላይ÷ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችና ሊባኖስ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ ተገኝተዋል፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃ፣ 87 ሺሕ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ የተቻለ ሲኾን ከተመለሱት ያላነሱ ወገኖች በመካከለኛው ምሥራቅ የተለያዩ አገሮች በከፍተኛ ችግር ላይ እንዳሉ እየተዘገበ ይገኛል፡፡ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና በጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤትና በሀ/ስብከቱ አድባራትና ገዳማት እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን እየተደረጉ ያሉት በአቀባበል የመርዳትና በዘላቂነት የማቋቋም ተግባር በሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችን አካላት፣ ገባሬ ሠናይ ድርጅቶችና ዜጎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

Advertisements

6 thoughts on “ቤተ ክርስቲያን ለሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሽ ወገኖች 2 ሚልዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ ሰጠች

 1. Anonymous December 4, 2013 at 9:35 am Reply

  Melkam jmr now. Betekrstiyanachn hulem qedami engi teketay mehon yelebatm.

 2. Anonymous December 4, 2013 at 10:31 am Reply

  Of course the deed is plausible. It is nice to get involved in such social activities, which is the least what the church should do. But I don’t like the way you wanted to advocate for MK. In whatever MK is involved you are there as a shadow.

  I have read some of the comments given under one monk blasphemy, which redundantly urged you to say something about the Hawassa current issue. But You kept silent and you seem worried on minor things like this one. Do you mean that you are deaf about the Protestantism devastation? I wish God may help you to the deepest insight!
  Why are you choosing to be ignorant of the hot thing? Do you think since you didn’t speak the Mighty God’s work will be hidden. No way dear, better to think once again.

 3. Anonymous December 4, 2013 at 10:34 am Reply

  Shame on you guys, you are still silent about the Hawassa thing? Can I guess you are standing by the side of the wicked yared and begashaw? Else you would have said something.

 4. sami December 4, 2013 at 11:20 am Reply

  yemidegef ena melkam hasab new !!!!

 5. Anonymous December 4, 2013 at 6:36 pm Reply

  this is not a new thing. our beloved church has been doing like this for a long time. and this is very good job and this part of her mission. let me say just one word. do you think MK is out of the church? ” በጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤትና በሀ/ስብከቱ አድባራትና ገዳማት እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን” what do mean by this? I believe that you are always trying to promote mk.

 6. ሃይማኖት ርትተት December 5, 2013 at 5:04 am Reply

  እንግዲህ ንስሐ እንግባ!
  አዩ የእኔን ሀሳብ የሚጋሩ ብዙዎች ብቅ እያሉ ነው፡፡ ባለፈው አንድ መነኩሴን በሚያብጠለጥለው “ጽሑፍ” ወደ አወዛጋቢው የአዋሳ ዕርቅ መሰል ግድምድም እንዲመለከቱ ተጋብዘው ነበር፡፡ ዛሬም እንዳሸለቡ ቀጥለዋል፡፡ ሰዎቹ እሁድ በአዋሳ ቅዱስ ገብርዔል ገዳም ብቅ ይላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በጋሻው ቀፈቱን ለብሶ ያሬድም ተንኮሉን! ይህ ካስደሰተዎት እንግዲህ ምን እላለሁ?
  ሰው ከእባብ ጋራ እንዴት ይደራደራል? በዘበቱበት ሕዝብ ፊትስ እንዴት ቂጥጥ ብለው ይቆማሉ፡፡ አዋሳ ላይ እንዲህ ሆነ ማለትስ በሌላው ዘንድ ያለው ተጽእኖ ምንድን ነው? ወዴት እያመራን ነው? የእንጨት ሽበት የተባሉ አባቶች ጎን እንዴት መቆም ተፈቀደ? የበጋሻው ሙሻዙር ያሬድ በእባብነት አደራዳሪ እና ተፈራራሚ ሆኖ እንዴት…….ኧረ ያማማማማማማል!
  ነው ወይንስ እነርሱ ሲገቡ እኛ እንድንወጣ? ጉድ በል! የተፋለሰው የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት፣ ጌታችንን ቁማር ተጫዋች አድርጎ ያውም ከዲያብሎስ ጋር የቀለደው ከሃዲ (ለአቅመ መናፍቅ እንኳ የማይበቃ) እንዲህ እንደቀልድ ዘው ብሎ እንዲገባ ሆሳዕና እያሉ ማጎብደድ….አይሞከርም፡፡ ብታርፉ ደግ ነው በሉልኝ፡፡ የቤተክርሰቲያን አምላክ ይፋረዳችኋል፡፡ እናንተም ታፍራላችሁ!
  በእርግጥ የአዋሳ ምእመናን ተወካዮች ብዙ ደክመዋል፡፡ ድካማቸው ግን እንዲህ እንዲያልቅ አልነበረም፡፡ የወጡትን ምእመናን ወደቤታቸው መመለስ ይገባል፡፡ እርሱ በመሆኑም ደስተኛ ነኝ፡፡ ግን ከእነርሱ ጋር በእነርሱ ተከልለው ሊገቡ ያሰፈሰፉት ዉሉደ ከይሲ ደጅ ሰላሙን መሻገር የለባቸውም፡፡ ሰዎቹ እንዲመለሱ ጥረት አድርገዋል መባሉ ብቻ ምሕረት ሊሆንላቸው በጭራሽ አይገባም፡፡ ከሰዎቹ መካከልም እነማን ለምን ተልእኮ እንደሚመጡ በጥንቃቄ መመርመር ይኖርበታልና፡፡
  ጫቱን እየቃመ ከዚችም ከዚያችም በየዳንስ ቤቱ ምድረ አዲሰ አበባን ሲወላከፍባት የሚኖረው ያሬድ ምን በጎ ነገር ይሰራል ተብሎ ነው? ከበለስ ወይን ይለቀማልን? ይቆየን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: