የፓርላማ ተመራጩ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ

Kesis Belay Mekonen00

ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና አማካሪ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ፡፡

በዛሬው ዕለት የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው የተሾሙት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ÷ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ከ፲፱፻፺፫ – ፲፱፻፺፭ ዓ.ም. ሦስት ዓመታት ውስጥ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በመኾን አብረዋቸው ሠርተዋል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ፣ በቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት፣ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በከፍተኛ የአስተዳደር ሓላፊነት/ዲንነት በመሥራት በርካታ ተሞክሮዎች እንዳሏቸው የተገለጸው ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ፣ በትምህርት ዝግጅታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡

በዚኹ ሞያቸው የማማከርና የፍ/ቤት ክርክር ጉዳዮች በሚከናወንበት በመንበረ ፓትርያርኩ የሕግ አገልግሎት መምሪያ እየሠሩ ያሉት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ፣ በሪፍት ቫሊ ኮሌጅም በማታው መርሐ ግብር እንደሚያስተምሩ ተገልጦአል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በንግድ አስተዳደር የድኅረ ምረቃ ትምህርታቸውን (ኤም.ቢ.ኤ) በተልእኮ በመከታተል ላይ እንዳሉ ተዘግቧል፡፡ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ የሠለጠኑበትና ሥራ የጀመሩበት ሞያ በጤና ረዳትነት እንደነበርም ታውቋል፡፡ ተሿሚው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ኦሕዴድ/ኢሕአዴግን በመወከል የፓርላማ ተመራጭ ናቸው፡፡

20 thoughts on “የፓርላማ ተመራጩ ሊቀ አእላፍ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ

 1. Ben November 28, 2013 at 8:39 pm Reply

  ወይ አንቺ ቤተክርስቲያ እንዲህ ባለቤት እንድሌለው ቤት የሁሉም መጫወቻ ትሆኝ??

  በላይ መኰንን ማለት ትላንት ለአክራሪው ጴንጤ ለዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም “. . .የተጠሩበት ሐዋርያዊ አገልግሎት የበለጠ የሚፈጽሙበትና የሚያስፈጽሙበት ዘመን እንዲኾንልዎ ምኞቴን ስገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው” ብሎ የፃፈው? ወይ አንቺ ሀገር::

  በላይ መኰንን ማለት:

  አንድ ሰው መርጦ የማይወለድበትን የትውልድ ማንነት የጠብና ክፍፍል መንሥኤ የማድረግ ጎጠኝነት እና ‹ፖለቲከኝነት› በዋና ዲኑ በቀሲስ በላይ ላይም እንደሚታይ ምንጮቹ ይመሰክራሉ፡፡ የቡድን ጥቅምን ከማሳደድ፣ ኦርቶዶክሳዊነትን ከማዋረድ፣ የመናፍቃን ተልእኮን በውስጥ አርበኝነት ከማስፈጸም ጋራ በተያያዘ በቅዱስ ሲኖዶስ ሳይቀር ጉዳያቸው ለታዩትና በዚህ የጡመራ መድረክ ስማቸው ደጋግሞ ከሚነሣ ግለሰቦች ጋራ በተያያዘ ቀሲስ በላይ ባላቸው የሕግ ሙያና ፖለቲካዊ ትስስር ዋነኛው አጋር፣ ሽፋን ሰጪ ኾነው መቀጠላቸውን በቁጭት ይናገራሉ፡፡

  በዕሥራ ምእቱ በዓል አከባበር የቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ “ሰማዕት ዘእንበለ ደም” በተባሉበት መድረክ አባ ገዳው ያበረከቱላቸውንና በሺሕዎች ተመልካቾቻቸው ፊት ያከናነቧቸውን የቡልኮ ሸማ ስጦታ መቀበላቸው ብዙዎች ቅዱስነታቸው ለእምነቶች መከባበር እና መቻቻል እንደሚሠሩ ለማስረዳት ታላቅ አጋጣሚ አድርገው እንደሚጠቅሱላቸው ለ80ኛ ቀን መታሰቢያቸው ከወጣውና የሐዘንተኞች አስተያየት ሰፍሮበት ከነበረው መዝገብ ተመልክተናል፡፡ የአባ ገዳውን ስጦታ ክዋኔ ከኋላ ላስተባበሩት ቀሲስ በላይ ግን ያ አጋጣሚ “ተመልከቱ÷ አባ ጳውሎስን ቡልኮ አስለበስኳቸው!” በሚል ተሣልቆ የተወጠነ እንደነበር በራሳቸው ቃል እያስካኩ ሲናገሩ ያደመጧቸው ምንጮች ያስታውሳሉ፡፡

  እስኪ አምላክ ያስበን::

 2. Anonymous November 29, 2013 at 1:36 am Reply

  ይቺ ቤተክርስቲያን መቸም የመናፍቃንና የወያኔ መፈንጫ ሆናለች ያሳዝናል ::እግዚአብሔር መልካም ግዜን ያምጣልን::
  http://www.dejeselam.org/2012/11/blog-post_8.html

 3. Anonymous November 29, 2013 at 1:37 am Reply
 4. TEGEHAS November 29, 2013 at 8:58 am Reply

  ሊቀ አእላፍ WELCOME TO THE HELL!!!አባቶች ሹመት ሺ-ሞት ነው ይላሉ
  ያቀፈ መስሎ ከሚያፍነው ማህበር ሴራና ከዘመነኛ-መሰል ግዕዝ-ጠቃሽ ሚሽኖች ወጥመድ ሰውሩዎት ለቤተክርስቲያናችን የሚገባውን አመራር ለመስጠት እንዲያበቃዎት እንጸልያለን!!!
  ሹመት ያዳብር!!!!!!!!

 5. Anonymous November 29, 2013 at 10:58 am Reply

  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነትን ለአንድ ለማይረባ ለወያኔ አሽከር አቶ በላይ መኮነን መሰጠቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ያበቃለት ስለመሆኑ ምልክት ነው፡፡

 6. Anonymous November 29, 2013 at 11:56 am Reply

  KEMANEME AYANESUME MEKNENTE ASETYAYTE SCHIWOCE YESTSUTE KETCHAL KENBI ASETYAYETE MESETSE NWE ENJI………

 7. kk November 29, 2013 at 12:09 pm Reply

  Like A’elaf, I hope you will not mix your politics with the church affairs … let me remind you the concept of so called “secular state”. … metne lezich ager, metne lezich betekrestian!!!

 8. Senait November 29, 2013 at 12:10 pm Reply

  Hodam…degimo tadenankutalachuh ende

 9. Anonymous November 29, 2013 at 7:55 pm Reply

  dont judge peoples without knowing them. pls my people

 10. liqu November 29, 2013 at 7:55 pm Reply

  ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን በትምህርት ደረጃቸው የተሻሉ በክህነታቻውም በአንዲት የትዳር አጋር ጸንተው የሚኖሩ ናቸው!! ገባህህህህህህ

 11. Anonymous November 30, 2013 at 2:48 am Reply

  my friend! even you know him/her/ we do not have to judge. because the holy bible says ” do not judge you will be judged” Matthew 7:1-

 12. elias November 30, 2013 at 4:26 am Reply

  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅነትን ለአንድ ለማይረባ ለወያኔ አሽከር አቶ በላይ መኮነን መሰጠቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ያበቃለት ስለመሆኑ ምልክት ነው፡፡wey gud nibured yohannis atse naod 4th grade temari kalteshome sibal endalneber ahun le kesis belay aa diocese yansachewal?mechem tsinfegninte milikitu yihe new yegid ante yemitifelegew sew meqemet alebet?

 13. Anonymous November 30, 2013 at 5:09 pm Reply

  ሃራ ተዋህዶ የማህበረ ቅዱሳን ልሳኖች ጉደኞች ናችሁ በብሎጉ ላይ እኮ የመሰለንንና የምናውቀውን ለመጻፍ መብታችን ነው እናንት ውሾች በድፍረት የጻፍነውን መልዕክት እየቆራረጣችሁ የራሳችሁን ሀሳብ እየቀጠላችሁ መጻፋችሁ የብልግናችሁ መገለጫ መሆኑን ልታውቁ ይገባል ሳሙኤል ስለ ሊቀ አእላፍ ያልተናገረውን አልጻፍንም የናንተ አባል በመሆኑ አስተያየታችንን ቆራረጣችሁት ይህ የሸፍጥ ሥራ ነው ከዚህ በተረፈ ሀሳባችንን አናቀርብም፤፤

 14. Anonymous November 30, 2013 at 6:28 pm Reply

  church is not only for the tigres or amharas our church belong to all of us bei from walayta, oromo, or keffa

 15. Anonymous November 30, 2013 at 6:29 pm Reply

  አንድ የሀሳብ ልውውጥ ሲደረግ አስተማሪ ሊሆን ውይም እርምት ሊደረግ በሚያስችል መልኩ ቢቀርብ መልካም ይሆናል። በአለፉት ሃያ ዓመታት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የታየው ሁኔታ ከምንጊዜውም የከፋ ቢሆንም ለወደፊቱ እንዴት ሊታረም ይችላል የሚል በድረ ገጹ ላይ ቢስተናገድ የበለጠ በአስተማሪነቱ በሳል ሀሳብ ሰጪዎችን ሊያሳትፍ ይችል ነበረ ። ነገር ግን በድህረ ገጹ ላይ በአብዛኛው የሚነበበው የሰው በደል በመሆኑ የሚሰጠውም አስተያየት በአብዛኛው ስነ ስርአት የጎደለው እንኳን በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ሊነገር ይቅርና በመንደር የሚወራ አይደለም።

  ምን አልባት እኔ እንደሚመስለኝ የድህረ ገጹ አዘጋጆች እንዲህ ዓይነቱ ካልተነገረ የተመልካቹን ልብ አይማርክም ከሚል ተነስተው ከሆነ ግን ጊዜው ነውና በወቅቱ የሚጻፉም ሆነ የሚነበቡትም ነገሮች የሰውን አስተሳሰብ ለመቆጣጣር እንዲያመችና ተምልካች ለማሰባሰብ ብቻ ለገቢያ የሚቀርቡት ጋዜጦችም ለገቢ ምንጭነቱ ብቻ ታስቦ በመሆኑ በዚህ መልኩም ከሆነ ይህም ትክክለኝነት አለው ማለት ሳይሆን ሰው የሚፈጥረው ችግር ስለሆነና ይህንንም ለማረም የአአምሮ ብስለትን የሚጠይቅ በመሆኑ በጊዜው ሁሉም ራሱን ተቆጣጥሮ አስተያየቱንም ሆነ አመለካከቱን በአግባቡ ሊያስነብብ የሚችልበት ወቅት ወደፊት ይኖራል ብዬ በእርግጠኝነት ማለት ባልችልም ሁሉም ጊዜውን ጠብቆ እንደሚስተካከል ግን መገመት ይቻላል።

  የድረ ገጹ ሚና መሆን የሚገባው እርገጠኛ የሆኑትን መረጃዎች አንዱን አንስቶ አንዱን ጥሎ ሳይሆን ያለውን ሁኔታ በማአከላዊነት ቢያቀርብ ለአስተያየ ሰጪው መሰናክል ከመሆን ይልቅ የገንቢ አስተያየቶ መፍለቂያ ስለሚይደርገው አሠራሩንም ያጠናክረዋል እንጂ አያዳክመውምና የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በተመለከተ በተቻለ መጠን ስርዓት በአለው መልክ ቢሆን መልካም ነው እላለሁ።

 16. haile melkot January 2, 2014 at 11:43 am Reply

  Those of you who appointed this Devil Kingdom (E.P.R.D.F) servant will be punished by him and by his bosses in near future. Because you preferred the servant of Devil kingdom instead of the servant of God kingdom. His aim is known. All things is registered and even some of fornication and false witness has been seen and listened in TV and Radio.

 17. korabanchi April 4, 2016 at 4:44 pm Reply

  በድንብ ብሉ ስለተ ባሉ ይብሉ ሃይ ባይ የሌለው ገብስ ውፍ ይጨርስዋል

 18. […] ኾነ የክልል ሲኖዶስ የማቋቋም ዓላማ እንደሌላቸው የገለጹት እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በበኩላቸው፣ በክልል ደረጃ የአህጉረ ስብከትን ጉዳይ […]

 19. […] ኾነ የክልል ሲኖዶስ የማቋቋም ዓላማ እንደሌላቸው የገለጹት እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በበኩላቸው፣ በክልል ደረጃ የአህጉረ ስብከትን ጉዳይ […]

 20. […] ኾነ የክልል ሲኖዶስ የማቋቋም ዓላማ እንደሌላቸው የገለጹት እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በበኩላቸው፣ በክልል ደረጃ የአህጉረ ስብከትን ጉዳይ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: