ፓትርያርኩ: ወደ ኋላ ለማይመለሰው የተቋማዊ ለውጥ አደረጃጀትና አሠራር አገልጋዩ የለውጥ ሐዋርያ እንዲኾን አሳሰቡ፤ የሥራ ጊዜያቸው ያበቃውን ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ ‹‹በዘላቂነት እናስቀጥላለን›› በሚል ጥቅመኝነት የተሳሰሩ ጎጠኛና ሙሰኛ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎች በፓትርያርኩና በረዳት ሊቀ ጳጳሱ መካከል ክፍተት ለመፍጠር እያሤሩ ነው

???????????????????????????????

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጥናታዊ የውይይት መርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ቃለ ምዕዳን በሰጡበት ወቅት (ፎቶ: የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት)

 • የለውጡ ቀንደኛ ተገዳዳሪዎች፣ ‹‹በውጭ ጠላቶች ነበርን፤ ዛሬ የሰማነውና ያየነው ጥናት ግን መልካም ኾኖ አግኝተነዋል፤›› ሲሉ ራሳቸውን ሒስ አድርገዋል፤ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ የተወለደችው ዛሬ ነው፤›› ሲሉም የመዋቅርና አሠራር መመሪያ ጥናቱን አድንቀዋል፤ ጥናታዊ ውይይቱ በላቀ የለውጥ መነሣሣት ለሁለተኛ ቀን እየካሄደ ይገኛል፡

**          **        **

 • ትላንት፣ ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የተቋማዊ ለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ላይ ከፍተኛ አመራሩን በማስቀደም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የመጀመሪያ ዙር የጥናታዊ ውይይት መርሐ ግብር ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
 • የመጀመሪያ ዙር ጥናታዊ ውይይ÷ የሀ/ስብከቱ ዘጠኝ ዋና ክፍሎችና የክፍሎች ሓላፊዎች፣ የሰባቱ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ሥራ አስኪያጆችና የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ሓላፊዎች፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅና የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎች በአጠቃላይ 70 ተሳታፊዎች የተካፈሉበት ነው፡፡
 • ከ13 በላይ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ጥናት ረቂቅ ሰነዶች ተሳታፊዎችን ባስደመመ የባለሞያዎች ገለጻ ለውይይቱ ተመጥነው በቀረቡበትና ከፍተኛ የለውጥ መነሣሣትና ዝግጁነት እንደታየበት በተዘገበው መርሐ ግብር ላይ አስተያየት የሰጡት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ የተወለደችው ዛሬ ነው፤›› ሲሉ መጋቤ ካህናቱ ሊቀ ማእምራን ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም ደግሞ ‹‹በውጭ ስለ ለውጡ ስንሰማ ጠላቶች ነበርን፤ በውስጥ ዛሬ ገብተን ያየነውና የሰማነው ግን መልካም ኾኖ አግኝተነዋል፤›› ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
 • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ረዳት ሊቀ ጳጳሱ÷ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምቱ ምልአተ ጉባኤው ለተቋማዊ ለውጥ ጥናቱ ከፍተኛ ድጋፍና ይኹንታ በመስጠት የምልአተ ጉባኤውን ተከታይ ስብሰባ ሳይጠብቅ በብዙኃኑ ሠራተኛና አገልጋይ አሳታፊነት ከዳበረ በኋላ በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቆ እንዲተገበር የሰጠውን አቅጣጫ ለማስፈጸም የሚያሳዩት ቁርጠኝነት፣ የለውጥ ሂደቱ ተግዳሮት እንደኾኑ በስፋት የሚነገርባቸው ግለሰቦች በጥናታዊ ውይይቱ ላይ ላንጸበረቁትና በሂደት መረጋገጥ ለሚገባው አዎንታዊ ሐሳባቸውና አቋማቸው ግፊት ሳይኾንባቸው እንዳልቀረ ተጠቁሟል፡፡
 • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጥናታዊ ውይይቱን ሲከፍቱ በሰጡት ቃለ ምዕዳን፣ ከላይ እስከ ታች ባለው የሥራ ሓላፊነት ላይ የሚገኝ ሁሉም ሓላፊና አገልጋይ ለአዲሱ አደረጃጀትና አሠራር ግንባር ቀደም የለውጥ ሐዋርያ በመኾን ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ይጠበቅበታል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ የጥናታዊ ውይይቱን አስፈላጊነት ሲገልጹም፣ ‹‹ሁላችንም አገልጋዮች ዘመኑን የዋጀ የለውጥ ሰው ለመኾንና ለውጡን አምኖ ለመቀበል፣ የቤተ ክርስቲያናችንን ሀብቷንና ንብረቷን በሕጋዊ አሠራር ተቆጣጥረን በአግባቡ በሥራ ላይ ለማዋል እንዲቻል›› መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ውጤቱም የቤተ ክርስቲያናችንን ስም ያስጠፋውን የመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር ጉድለት በታማኝነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት መርሕ ከሥር መሠረቱ ነቅለን በማስወገድ ታሪካዊነቷንና ሉዐላዊነቷን ማስከበር፣ የቀደመ ክብሯን ማስመለስ እንደኾነ የሀ/ስብከቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡
 • በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳትና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በተጀመረው የጥናታዊ ውይይመርሐ ግብር ቀዳማይ ዙር ከሚካፈሉት 70 ተሰብሳቢዎች ቀጥሎ÷ ኅዳር 27 እና 28 ታኅሣሥ 5 እና 6፤ ታኅሣሥ 12 እና 13 በሚኖሩት ተከታታይ አራት ዙሮች ከ166 ገዳማትና አድባራት ከእያንዳንዳቸው የተውጣጡ 16፣ 16 ተወያዮች በአጠቃላይ 2656 የአጥቢያ አለቆች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤቶች አመራሮችና የምእመናን ተወካዮች እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡
 • የጥናታዊ ውይይቱ የመጀመሪያው ዙር 70 ተሳታፊዎች በትላንት ውሏቸው፣ የባለሞያዎች ገለጻ በተደመጠባቸውና በአጠቃላይ ጥያቄዎች ላይ የተመሠረቱ ማብራሪያዎች በተሰጡባቸው የጥናት ሰነዶች ረቂቅ ላይ በአራት ቡድኖች ተከፍለው ተወያይተዋል፡፡ በትላንቱ የባለሞያዎች ገለጻና የተሳታፊዎች የቡድን ውይይት የተሸፈኑት ጉዳዮች፡- የጥናቱ አጠቃላይ ሥራዎች፣ የአደረጃጀት ጉዳይ ረቂቅ ሰነድ፣ የአብያተ ክርስቲያን ደረጃ አሰጣጥ ረቂቅ ሰነድ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ረቂቅ ሰነድ መኾናቸውን ለውይይቱ የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ÷ በፋይናንስ መመሪያ ረቂቅ ሰነድ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ረቂቅ ሰነድ፣ በልማት መመሪያ ረቂቅ ሰነድ፣ በዕቅድና ሪፖርት መመሪያ ረቂቅ ሰነድ፣ በቁጥጥር መመሪያ ረቂቅ ሰነድ እና በሥልጠና መመሪያ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይቱ ቀጥሎ እንደሚውል በመርሐ ግብሩ ላይ ተመልክቷል፡፡
 • ለተሳታፊዎች የቡድን ውይይት ከጥናት ሰነዶቹ ተለይተው የተጠቀሱ አጀንዳዎች÷ ለሰው ኃይል አስተዳደር፣ ለሥነ ሥርዐት(ሥነ ምግባር)ና የፍትሕ ሥርዐት እንዲሁም ለአብያተ ክርስቲያን ደረጃዎችን የመወሰን አስፈላጊነትና ለደረጃዎቹ መስፈርቶች ትኩረት የተሰጠባቸውን ነጥቦች የያዙ ናቸው፡፡ የመወያያ ነጥቦቹን በየራሳቸው ለማመልከት ያህል÷ የአገልጋዮች ቅጥር ሥርዐት፤ የአገልጋዮች ዝውውር ሥርዐት፤ የአገልጋዮች የጡረታና ጤና ክብካቤ ሽፋን፣ ጥቅምና ጫና፤ የአገልግሎት አፈጻጸም ምዘና ሥርዐት፣ የሥነ ሥርዐት አጠባበቅና የፍትሕ ሥርዐት፤ የአብያተ ክርስቲያን ደረጃዎችን የመወሰን አስፈላጊነትና ጥቅም፤ አብያተ ክርስቲያንን በደረጃ ለመለየት የተወሰዱ መስፈርቶች የሚሉ ናቸው፡፡
 • በአገልጋዮች የቅጥር ሥርዐት፣ ‹‹ቅጥር የመፈጸም ሥልጣን የትና በማን ይፈጸም?›› በሚል የመነሻ ጥያቄ የአገልጋዮች ቅጥር፡- ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፣ ከክፍላተ ከተማ ወይም ከሀ/ስብከት በየትኛው ደረጃ ቢፈጸም ብቁና ውጤታማ ሊኾን እንደሚችል ይጠይቃል፡፡ ይህም ቢሮክራሲያዊ ውጣ ውረድንና ሙስናን ከመቀነስ፣ ኢኮኖሚያዊ(አዋጭ) አሠራርን ከማስፈን፣ ብቁ ተወዳዳሪዎችን ከማግኘት፣ አቅምና የመወሰን ድርሻን ከማሳደግ (ለምሳሌ፡- በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ደረጃ ቢፈጸም) አንጻር በተሳታፊዎቹ በጋራ ከተገመገመ በኋላ አመራጭ ሐሳብ እንደሚቀርብበት ተመልክቷል፡፡
 • በዚህ ረገድ ሀ/ስብከቱ ስለ ሦስት ወራቱ የሽግግር ወቅት አፈጻጸም ያካሄደው ግምገማ እንደሚያመለክተው፣ የአዲስ ሠራተኛ ቅጥር ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ ይህም አሁን በየገዳማቱና አድባራቱ ያለው የሰው ኃይል ክምችት እጅግ ከፍተኛ ከመኾኑ አንጻር ነው የሚለው የግምገማው ሪፖርት፣ በተለያየ ምክንያት ከሥራ ተፈናቅለው ምደባ ያላገኙትንና ከዝውውር አኳያም ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙ ሠራተኞችን ብቻ እንደሚያስተናግድ ይገልጻል፡፡ ይኸው የሠራተኛ ዝውውርና ምደባም ቢኾን በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች መካከል በሽሚያ በሚመስል መልኩ ሲፈጸም እንደነበር፣ ከዚህም የተነሣ በአንድ የሥራ ቦታ ሁለት ሰው እስከ መላክ የተደረሰበት አጋጣሚ ተፈጥሮ እንደነበር ሪፖርቱ ዘርዝሯል፡፡
 • ሀ/ስብከቱ÷ የቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ተልእኮ ከኾነው የስብከተ ወንጌልና የልማት ሥራዎች ይልቅ የሠራተኛ ምደባና ዝውውርን ከክፍለ ከተማ ጋራ እየተሻማ ይፈጽም የነበረበት ምክንያት፣ ‹‹የሽግግር ወቅት የመዋቅርና የሰው ኃይል አደረጃጀቱ የአፈጻጸም መመሪያ ስላልተዘጋጀለትና ወደ ታች ወርዶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ሳይደረግበት በቀጥታ ሥራ ላይ በመዋሉ›› መኾኑን በግምገማዊ ውይይቱ ወቅት ተገልጾአል፡፡ ይህን ምክንያት የሚቃወሙ ወገኖች በበኩላቸው፣ ለሽግግር ወቅቱ የሚያገልግል የትግበራ ስልት በጋራ አውጥቶ መንቀሳቀሱ የሁለቱም አካላት ድርሻ እንደነበርና ይህም የተባለውን ‹‹የሽሚያ ምደባና ዝውውር›› ያስቀር እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡ እንዲህ ዐይነቱ ምላሽም የለውጡን ውጤት ከወዲሁ ዐውቀው የሚቀርባቸውን ሕወጥ ጥቅም ለመከላከል በሂደቱ ላይ ዕንቅፋት ከሚፈጥሩ አካላት መደመጡ አስገራሚ እንደሚያደርገው ያስረዳሉ፡፡
 • በትላንቱ ውይይት፣ የአገልጋዮች ዝውውር ሥርዐት በማንና እንዴት መፈጸም እንዳለበት በሁለተኛ ደረጃ ተለይቶ የተጠቀሰው የቡድን መወያያ ነጥብና በጋራ የሚደረስበት ጥናታዊ ስምምነት ለዚህ ውልውል መፍትሔ እንደሚያበጅ ይጠበቃል፡፡ በመፍትሔው ምላሽ ከሚያገኙትና ግንዛቤ ከሚያዝባቸው የመወያያ ነጥቡ ዝርዝር መጠይቆች መካከል፡- ዝውውር በአገልጋዩ ፈቃደኝነት ብቻ ወይስ ፈቃደኝነቱ ባይኖርም የሚፈጸም መኾን አለበት? ዝውውር ያልፈለጉትን አገልጋይ የመግፊያ መሣርያና አጥፊ አገልጋዮች ወደማይታወቁበት ቦታ የሚደቁበት አሠራር መኾን አይገባውም የሚሉት ይገኙበታል፡፡
 • ይህን ተከትሎ ስለ አገልጋዮች የጡረታና ጤና ክብካቤ ሽፋን ጥቅምና ጫና የተቀመጠው የቡድን መወያያ ነጥብ፣ የጡረታ አስተዳደር ሥርዐትን የሚመለከት ሲኾን የጡረታ መዋጮ በምን መልኩ ይሰብሰብ? እንዴት ይተዳደር? ለሚሉ ዝርዝር መጠይቆች ግንዛቤ የተፈጠረበትና አማራጭ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበት ነው፡፡ በጥናቱ ረቂቅ ላይ የጡረታ መዋጮ መጠን የአገልጋዩ ድርሻ 5% እና የቤተ ክርስቲያን ድርሻ 10% እንደኾነ ተመልክቷል፡፡ ከዚኹ ጋራ በተያያዘ በለውጡ ሕገ ወጥ ጥቅምን በመከላከልና ተገቢ ጥቅምን በመጨመር በሚጎለብተው ተቋማዊ አቅም በመጠቀም አገልጋዮች በአገልግሎት ዘመናቸው ነጻ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባቸው የሚጠቅሰው ሐሳብም ተያይዞ ቀርቧል፡፡
 • የአገልግሎት አፈጻጸም ምዘና ሥርዐት በማንና እንዴት ይካሄድ? የሚለው አራተኛው የቡድን መወያያ ነጥብ በሰው ኃይል አስተዳደር ሥር የሚካተት ሲኾን ምዘና በቅርብ ሓላፊ ብቻ ወይስ በቡድን? መመዘኛ ነጥቦቹ በሥነ ምግባር ላይ ያተኩሩ ወይስ በአገልግሎት ስፍራ ላይ በሚታይ አፈጻጸም ብቻ፣ የሚሉት መጠይቆች በቅጥር፣ ዝውውርና ዕድገት ወቅት ስለሚኖረው የምዘና መስፈርትና አፈጻጸም የጋራ ግንዛቤ የተያዘባቸው ናቸው፡፡ ከእኒህም ጋራ የቅጥር ኮሚቴ አደረጃጀት፣ የማስታወቂያ አወጣጥ መልኮች፣ የዝውውርና ዕድገት ዐይነትና አፈጻጸም፣ የሹመት አሰጣጥ፣ ስንብት በምን መልኩ እንደሚፈጸም የተሠራ ሥርዐት ተካቶበታል፡፡
 • የባለሞያዎች ቡድኑ በብዙ እንደ ደከመባቸው ከተገለጹት ጥናቶች መካከል የሥነ ሥርዐት አጠባበቅና የፍትሕ ሥርዐት ሰነድ ረቂቁ ተጠቃሽ ነው፡፡ ከዚህ ጥናት÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሥነ ሥርዐትና ፍትሕ ጉባኤ ከሚደነግገው አኳያ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቶቻችን እንደተቋም አለመጠናከር በስፋት ከሚታየው የመልካም አስተዳደርና የሥነ ምግባር ጉድለት ጋራ ተያይዞ ዓለሙ የሚዳኝባቸውን ፍርድ ቤቶች ላጣበቡ ጉዳዮቻችን የሚኖረው ፍቱንነት ይጠበቃል፡፡ ለቡድን ውይይት መነሻነት በተሰራጨው ሰነድ ላይ እንደተጠቆመውም፣ በሥነ ሥርዐት አጠባበቅና የፍትሕ ሥርዐት ላይ የሚደረገው ውይይት አጠቃላይ ፋይዳ፡- ጠንካራና ብቁ የቤተ ክርስቲያን አመራር ስለ መፍጠር፣ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለውን አገልጋይ ስለማነፅ፣ ጠንካራ የሥነ ሥርዐት ማስጠበቂያ ስልትና ትክክለኛ ፍትሕ በቤተ ክርስቲያን መድረክ ማፍራትና መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶቻችን ማጠናከር ስለሚቻልባቸው አግባቦች በመምከር ጠንካራ አማራጮችን ማውጣት ነው፡፡
 • የሥነ ሥርዐት አጠባበቅ÷ የሥነ ሥርዐት ርምጃ(ቅጣት) ዐይነቶችን፣ ቅጣት እንዴት እንደሚነሣ፣ ይግባኝ እንዴት እንደሚጠየቅ ያትታል፡፡ የቤተ ክርስቲያናችንን የሥርዐት መጻሕፍት (በተለይ መጽሐፈ ዲድስቅልያን) ዋነኛ የሥነ ምግባር ደንብ ማዘጋጃ ምንጩ በማድረግ የተጠቀመው ጥናቱ÷ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው አገልጋዮች የሚጠየቁበትን፣ ሦስት ደረጃዎች ያሏቸው የቅሬታ አቀራረብ ሥርዐቶችና በይርጋ ስለሚቆዩ ጉዳዮች የተካተተበት መኾኑ ተገልጦአል፡፡
 • የፍትሕ ተቋማቱ÷ የመንፈሳዊ ፍትሕ ችሎት፣ የአስተዳደር ጉዳዮች ችሎት እና የሥራ ክርክር ጉዳዮች ችሎት በሚል ይዋቀራሉ፡፡ በዚህም ሉዐላዊት ቤተ ክርስቲያናችን በመደበኛ ፍርድ ቤት የማይታዩ፡- ሥልጣነ ክህነትን፣ የጋብቻ ውልን፣ ውክልና ማጽደቅንና የሥራ ክርክርን የተመለከቱ የራሷን ጉዳዮች በራሷ ችሎቶች ለማስተናገድና ውሳኔአቸውንም ለማስፈጸም የሚያስችል መዋቅራዊ አቅም እንደምትፈጥር፣ ዕሴቶቻቸውንም እንደምታጎለብት ይታመናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ በ፳፻፬ ዓ.ም. ለተወካዮች ምክር ቤት ቢመራም መጽደቁ በእጅጉ ስለዘገየው የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስፈጸሚያ ሕግ ማስታወስ ተገቢነት ይኖረዋል፡፡
 • የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በአንድ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የሚመሩትን አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሳያካትት 166 (በሀ/ስብከቱ የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሪፖርት መሠረት ደግሞ 155) አድባራትና ገዳማት እንዳሉት ተገልጦአል፡፡ ለቡድን ውይይት በቀረበው የመወያያ ነጥብ ላይ እንደተጠቆመው፣ ገዳማቱና አድባራቱ በአምስት ደረጃዎች ተለይተዋል፤ በአምስቱ ደረጃዎች ገዳማቱና አድባራቱ አንዳቸው ከሌላቸው እንደ ደረጃቸው የተለዩባቸውና የተካከየምዘና መስፈርቶች ተቀምጠውላቸዋል፡፡ የገዳማቱና አድባራቱ ታሪካዊነትና ቅርሳዊነት፣ የገነቧቸው ማኅበራዊና የልማት ተቋማት፣ የሚሰጡት አገልግሎት ስፋትና የገቢያቸው መጠን በደረጃ ለመለየት በዝርዝር ከተቀመጡት መስፈርቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡
 • ከዚህም አንጻር የአድባራቱና ገዳማቱ አደረጃጀት፣ አደረጃጀቱ የሚጠይቀው የሰው ኃይል ብዛትና ብቃት ከተዛማጅ ጥቅሞቹ ጋራ የተለያየ ነው፡፡ ይኸውም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ ያላቸውን ዘርፈ ብዙ አቅምና የሚበረክቷቸውን አገልግሎቶች በሚገባ ለማወቅ ከማስቻሉም በላይ በቅጥር፣ ዕድገትና ዝውውር ረገድ አገልጋዩ በየደረጃው በሚያሳየው ሞያዊ ልህቀትና ብቃት (career/vocation path) የመሻሻል ተስፋውን ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለበት ሥርዐታዊ መንገድ እንደሚያጎለብትለት ይታመናል፡፡
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያንም በቃለ ዐዋዲ ደንቡም እንደተደነገገው፣ የአህጉረ ስብከት ኹሉ ማዕከልና መዲና የኾነው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የሚተዳደረው ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው ልዩ ደንብና መመሪያ ነው፡፡ ለሦስት ወራቱ የሽግግር ወቅት ከተዘጋጀው መዋቅርና አደረጃጀት በተሻለ ኹኔታ ጊዜ ተወስዶበት የተሠራው ዐይነተኛው የሀ/ስብከቱ መዋቅርና አደረጃጀት በጥናታዊ ውይይቱ ላይ በግንባር ቀደም ከቀረቡትና ተሳታፊው በከፍተኛ የለውጥ መነሣሣት ከተወያየባቸው ዳጎስ ያሉ የጥናት ረቂቆች ዐብዩ ነው፡፡
 • በ134 ገጾች የተዘጋጀውና በመሻሻል ላይ ከሚገኙት ሕገ ቤተ ክርስቲያንና የቃለ ዐዋዲ ድንጋጌ ጋራ ያለው መጣጣም ጥንቃቄ የሚደረግበት የሀ/ስብከቱ ልዩ መተዳደርያ ደንብ፣ ከዚህ ቀደም በስፋት ባቀረብነው ዘገባ እንደተጠቆመው÷ የቤተ ክርስቲያናችን መሠረታዊ ተልእኮ ለኾኑት የክህነትና ስብከተ ወንጌል ተግባራት ቅድሚያ (70%) የተሰጠበት፣ መሠረታዊውን ተልእኮ የሚያጠናክረው የድጋፍ ሰጭ ተግባር (30%) ደግሞ ትክክለኛው ሰው በትክክለኛው ቦታ ተቀምጦ ብቃት ባለው ባለሞያ የሚመራበትና የሚሠራበት እንደኾነ በባለሞያዎች ማብራሪያ ተገልጾአል፡፡ ይህም የለውጥ አመራር መዋቅሩ÷ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር (የፋይናንስ እና የሰው ኃይል ስምሪቱን፣ የክትትልና ቁጥጥር አግባቡን) አስቀድሞ ከነበረው የተገላቢጦሽ አመለካከትና አሠራር ፍጹም የተለየና ውጤታማ እንደሚያደርገው ታምኖበታል፡፡
 • በመዋቅሩ መሠረት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተጠሪ የኾኑት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ የሀ/ስብከቱን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና የአስተዳደር ጉባኤ በርእሰ መንበርነት ይመራሉ፡፡ ለወትሮው የአንድ – ሰው – መዋቅር ኾኖ ለከፋ ሙስና ተጋልጦ የቆየው የኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት በተገቢው የሰው ኃይል ተዋቅሮ ቀጥተኛ ተጠሪነቱ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የቁጥጥር(ኦዲትና ኢንስፔክሽን) አገልግሎት እንዲኾን ተደርጓል፡፡ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍሎችና ቀጥተኛ ተጠሪ የኾኑለት የሀ/ስብከቱ ኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት፣ ከረዳት ሊቀ ጳጳሱና በየደረጃው ካሉ አካላት ጋራ ያላቸው ግንኙነት የሥራ ብቻ መኾኑ የቁጥጥር አቅማቸውንና እንደሚያጠናክርላቸውና እንደ ተቆጣጣሪ አካል መጠን ከአላስፈላጊ ጫና እንደሚጠብቃቸው ይታመናል፡፡
 • በአዲሱ የሀ/ስብከቱ አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያከናወኑ ተግባራት፡- ዋና ተግባር እና ደጋፊ ተግባር በሚል  በግልጽ ለሁለ የተከፈሉ ሲኾን ዋና ተግባሩን በበላይነት የሚያስተባብረው የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲኾን ደጋፊ ተግባራቱን ደግሞ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ያስተባብረዋል፡፡ ተጠሪነቱ ለረዳት ሊቀ ጳጳሱ የኾነው የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ጋራ የሥራ ግንኙነት ይኖረዋል፤ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁን የሰባቱ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ሥራ አስኪያጆችበአስተዳደራዊ ግንኙነት በበላይነት ይመራል፡፡
 • የክህነት ሥልጣን፣ ከፍተኛ ግብረ ገብነት፣ ከአስተዳደር/ሥራ አመራር ጋራ ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው የትምህርት ዝግጅትና የአገልግሎት ልምድ መሠረታዊ መስፈርት በኾነበት የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥር የሚመሩትና ዋነኛ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ዋና ክፍሎች፡- የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዋና ክፍል፣ የክህነትና ፍትሕ ጉዳይ ዋና ክፍል፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃና ማኅበራት ጉዳይ ዋና ክፍል፣ የቅርስና ቱሪዝም ዋና ክፍል፣ የሰንበት ት/ቤቶች ጉዳይ ዋና ክፍል ናቸው፡፡
 • መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ዕውቀትና በተለይ ደግሞ ከአስተደደርና ፋይናንስ ጋራ ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያለው ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅትና ሞያዊ ልምድ የግድ በኾነበት በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ሥር የተዋቀሩትና ደጋፊ ተግባራት የሚከናወኑባቸው ዋና ክፍሎች ደግሞ፡- የሰው ሀብትና አስተዳደር ዋና ክፍል፣ የፋይናንስና በጀት ዋና ክፍል፣ የልማትና ምግባረ ሠናይ ዋና ክፍል፣ የዶክመንቴሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዋና ክፍል፣ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ሪፖርት ዋና ክፍል ናቸው፡፡ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ በሀ/ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ስብሰባዎች የጸሐፊነት ድርሻም የሚኖረው ሲኾን ከዕውቀት/ሞያ የተፋታ የሹመኝነት ባህል የወለደውና በቤተ ክህነታችን ልዩ ኹኔታ የከፋ ሙስና መናኸርያ የኾነው የጸሐፊነት ሥልጣንና ተግባር ከእንግዲህ በሀ/ስብከት ይኹን በመላው የበታች መዋቅሮች እንደማይኖር አመላካች ኾኗል፡፡
 • ከዚሁ ጋራ በተያያዘ በሽግግሩ ወቅት የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት በድንገት ሓላፊነታቸውን ለቀው ወደ አሜሪካ በማቅናታቸውና በቦታው ክፍተት በመፈጠሩ መደበኛ ሓላፊ እስኪመደብ ድረስ በሽግግር መዋቅሩ የክህነትና ፍትሕ ጉዳዮች ዋና ክፍል ሓላፊ የኾኑት ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅነት መመደባቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚፈጽሟቸው ተግባራት፣ ተጀምረው በእንጥልጥል የቀሩ ሥራዎችንና በዕለታዊ ተግባራት ላይ ከመፈረም የዘለሉ አይደሉም፡፡ ተቆጥረው ተሰፍረው የተሰጧቸውን ተግባራት በሚያከናውኑበት ጊዜያዊ ሓላፊነት ላይ የሚቆዩትም ከጥቅምት ፳፭ – ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ብቻ እንደኾነ በረዳት ሊቀ ጳጳሱ ተፈርሞ የተሰጣቸው ደብዳቤም ያረጋግጣል፡፡ Letter of assignment to NebureEd Aba Yohannes as acting G.Manager of A.A
 • በዚያው ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው፣ ወቅቱ ሀ/ስብከቱ ያካሄደውን የተቋማዊ ለውጥ ጥናት በማገባደድ ወደ ትግበራ ለመግባት ሰፊ ዝግጅት የሚያደርግበት በመኾኑ ለተቋማዊ ለውጥ አመራሩ ተገቢና ትክክለኛ ሓላፊ በአስቸኳይ ሊቀመጥበት ግድ ይላል፡፡ ይህም ለቦታው ተለይቶ በተዘረዘረው የተሟላ የትምህርት ዝግጅት፣ ውጤታማ የሥራ ክንውን ሬከርድና ምስጉን ሥነ ምግባራዊ ልምድ መሠረት ለውጡን ይዞ ለመጓዝና በትክክል ለማስፈጸም የሚችል ዋና ሥራ አስኪያጅን በወቅቱ የማስቀመጥ ጥያቄ እንጂ በምንም ዐይነት ከተወላጅነትና የጎጥ ልዩነት ጋራ ሊገናኝ አይችልም፤ አይገባውምም!!
Advertisements

12 thoughts on “ፓትርያርኩ: ወደ ኋላ ለማይመለሰው የተቋማዊ ለውጥ አደረጃጀትና አሠራር አገልጋዩ የለውጥ ሐዋርያ እንዲኾን አሳሰቡ፤ የሥራ ጊዜያቸው ያበቃውን ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ ‹‹በዘላቂነት እናስቀጥላለን›› በሚል ጥቅመኝነት የተሳሰሩ ጎጠኛና ሙሰኛ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎች በፓትርያርኩና በረዳት ሊቀ ጳጳሱ መካከል ክፍተት ለመፍጠር እያሤሩ ነው

 1. TEGEHAS November 27, 2013 at 11:21 am Reply

  ስራ አስኪያጁ ይቀጥሉ የሚሉት በዘርና በጥቅመኝነት የተሳሰሩ ብቻ ናቸው አላችሁን፡፡አይቀጥሉ የሚሉቱስ ጻድቃን መሆናቸው ነው???መቼ ነው ይህ በዘረኝነት የታወረ የአንድ ብሄር አባላትን የማሳደድ(ትግራይ-ፎቢያ) እርምጃችሁ የሚቆመው??አባ ጳውሎስ፣አባ ሰረቀ፣ንቡረ ዕድ ኤልያስ አሁን ደግሞ ንቡረ ዕድ ዮሀንስ ሁሉም የእናንተ ሰለባዎች ናቸው፡፡ተው….ተው…ይህ አጉል ወንበር ደልዳይነት ይቅርባችሁ፡፡እንደ እናንተ ቢሆን እኮ በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲቀመጥ የተፈለገውም አቡነ ማትያስ እንዳልነበሩ እናውቃለን፡፡ዛሬ ሰልፋችሁን አስተካክላችሁ ለእሳቸው ተቆራቁዋሪ ሆናችሁ ቀረባችሁ!!!

  የለውጡ ተገዳዳሪዎች ግለ ሂስ አደረጉ ትላላችሁ፡፡ወትሮስ ጥናቱ ማህበረ ቅዱሳን በገዳማውያን ጸሎት ታግዞ የሰራው የብጽአት ስራ ነው ተብሎ እየተወደሰና እንደ አማሌቃውን መጽሀፍ(ቁራን)ከሰማይ ነው የወረደው ሊባል ትንሽ ቀርቶት ምኑን የተማመነ ሰው ነው ለውጡን የሚተች!!!ማን ነው ስሙ በየኢንተርኔቱ ጎጠኛ፣ሙሰኛ ሲባል ማየት የሚፈልግ!!እንዴ!! ማህበሩ ካጠናው እኮ በቃ እንደ 11ኛው የሙሴ ህግ ቆጥሮ መቀበል ነው፡፡ሆሆ..!!

  በነገራችን ላይ እባካችሁ ሰራተኛን ከደሞዝ(ከአገልግሎት አላልኩም) የማገድና የማሰናበት ስልጣን የረዳት ሊቀጳጳሱ ብቻ እንዲሆን ጩሁ፡፡በተለይ የመንፈሳዊ አገልግሎት ዘርፍ ሰራተኞች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ስለማይታይ የአድባራት አለቆችና የክ/ከ/ሀገረ ስብከት ስ/አስኪያጆች እየተመሳጠሩ በሚጥሉት እገዳና ስንብት ለወራት በየእለቱ በሀገረ ስብከቱ በር ላይ ፀሀይ ሲመታቸው ውለው ያላንዳች መፍትሄ ከአራት ኪሎ ዝለው ሲመለሱ ላያቸው አንጀት ይበላሉ፡፡their job security should be beyond ጭቃ ሹም መሰል አለቆች!!

  ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስም በየዋህነትና በቅንነት ጉዳዮችን በየዓውደ ምህረቱ በመገኘት ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት ጥሩ ቢሆንም አካሄዱን የድሮውን “አፈርሳታ” በሚመስል መልኩ ስለሚመሩት ሂደቱ በአፈ-ጮሌ አለቆችና በቲፎዞዎቻቸው እየተጠለፈ በመድረክ የመናገር ልምድ የሌላቸው ምስኪን ካህናት ሰለባ እየሆኑበት ነውና ጉዳዮችን በሰከነ መንፈስ የግራቀኙን አቤቱታ ተረጋግተው በሚሰሙበት በቢሮዋቸው ቢያደርጉት ጥሩ ይመስለኛል፡፡

  • agew November 27, 2013 at 4:26 pm Reply

   ወንድሜ መቼም ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆነና ትግሬን ማብጠልጠል ብትል አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ እናንተስ ብትሆኑ እግራችሁ አዲስ አበባ ከረገጠ ጀምሮ ማህበረ ቅዱሳን አላምጣችሁ ልትውጡት ያልባዘናችሁበት ቀን አለን፡፡ በእርግጥ ማኅበሩ እንኳን ምን እንደሆነ ውስጥ ገብተህ ሳታየው አትቀርም፡፡ ለዚህ አሉባልታ እንዲመቻችሁ ብላች አይደለም እንዴ “ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ አንድም ትግሬ የለም፡፡ በሙሉ የሸዋ ስብስብ ነው” እያላችሁ የምታስወሩት፡፡ የአቡነ ማትያስን ምርጫስ ቢሆን አንተ ነህ ያስመረጥካቸው ማለት ነው፡፡ ለመሆኑ የማኅበሩን ሚና በምርጫው ወቅት እንዴት ብለህ ፈረጅከው፡፡ ለነገሩ ማህበሩ ጥሩ ቢሰራም አላማችሁ የተወሰነን ክፍል ጭቃ መቀባት ነውና እንደማይጥምህ (ለአንተና ለመሰሎችህ) ግልጽ ነው፡፡ ስማቸውን የጠቀስካቸው ሰዎች ከማኅበሩ ጋር የማይስማሙት በአስተሳሰብና አሰራር እንጂ ትገሬ በመሆናቸው ነው ብለህ ማውራትህ እግዜር ይቅር ይበልህ እንጂ ሌላምን ይባላል

   • TEGEHAS November 28, 2013 at 2:52 pm

    “የአቦን መገበሪያ የበላ ሳይጠይቁት ይለፈልፋል” አሉ ፡፡
    አሁን ሸዋና-ትግሬ ማለትን ምን አመጣው???
    እኔ ለማለት የፈለኩት፡
    -አንዳንዴ እንኩዋ ቢሆን እሺ ግን ሁሌ በዘረኝነትና በጥቅመኝነት የሚከሰሱት የአንድ ብሄር አባላት ብቻ ናቸው፡፡ይሄ ደግሞ ተገልብጦ ሲነበብ የከሳሾችንም ዘረኝነት የሚያሳይ ነው፡፡ስለዚህ ለኔ ሌሎችን ፈርጀን ጨርሰን እራሳችንን ብቻ ቅዱስ አድርጎ ማስቀመጥ ኢ-ቀጥተኛ ሆነ እንጅ ሌላ ስም የለውም፡፡ዘረኝነት/ጎጠኝነት ነው!!!ስህተትን በስህተት ለማረም መሞከር ነው!!!
    -እንዳልከው ይቅር ይበለኝና ማህበሩ ግን ሁሌም ሲከፋ የማየው ሀላፊዎች ከክልል-1 ሲመጡ ብቻ ነው፡፡ከአንድ ግለሰብ ጋር ብቻ ቢሆን ጥሩ፡፡ግን ይደጋገማል፡፡ለዚህም ነው መጠርጠሬ!!!
    -ውሰድ በዘገባው የተነሱትን አባ ዮሐንስን, እሳቸውን ለማስቀጠል የሚጥሩ ሁሉ ወይ ጎጠኛ ወይ ጥቅመኛ ናቸው፡፡አለቀ!!!ግለሰቡ ምን ተማሩ፣ምን ሰሩ፣መንፈሳዊ ህይወታቸውስ፣…..ይሄ ሁሉ አይጠየቅም፡፡ በቃ እንትን ከሆኑ ጎጠኝነት አያጣቸውም ተብሎ ተደምድሙዋል፡፡what a prejudice!!!
    -ሌሎቹን ነጥቦች አንተም አሉባልታ ናቸው ስላልካቸው ለአሉባልታ መልስ በመስጠት አልደክምም፡፡በፓትርያርኩ ምርጫ ዙሪያ አብዛኞቹ የማህበረ-ቅዱሳን አባለት ደስተኛ እንዳልነበሩ ለማወቅ ከፈለክ ግን በየአፍቃሬ-ማህበሩ ብሎጎች(ኦፊሻሉን አላልኩም፡፡እሱማ ያስመታላ!!) በጊዜው ፖስት ተደርገው የነበሩ ዘገባዎችን ተመልከት፡፡አንዳቸውም ስለ እሳቸው መልካም ነገር ተናግረው አግኝተህ በዚህ ብሎግ ፖስት ብታደርግልኝ ስለበደሌ በምጾመው ገና ጾም ላይ በየእለቱ አንድ ሰዓት ጨምሬ እጾማለሁ፡፡ቃሌ ነው!!!

 2. Anonymous November 27, 2013 at 1:53 pm Reply

  kkkkkkkk beteqilay betekihinet sint yememirya halafi tigre endale tawiqaleh? ke 23 memirya 21 tigre eko new lemayawiquh ahunis yetigere yawim yedonqoro sibisib beza

 3. Anonymous November 27, 2013 at 5:23 pm Reply

  ጥናት አቅራቢዎች እነማን እንደሆኑ መጥቀስ የፈራችሁ ይመስላል።

 4. Anonymous November 27, 2013 at 9:33 pm Reply

  we do know very well the dream of MK. Dream of MK is a dream of Shiwa. let me tell you this, we are very sure. the Shuwanisim dream of Mk.will never come true. enough is enough. You have to understand. you have nothing to be proud of yourself. everything that you have is from Tigray. Without Tigray, there is no Ethiopia. So, you have to respect the people of Tigray just like you.

 5. Kebede November 27, 2013 at 10:42 pm Reply

  ከ23ቱ የምሪያ ኃላፊዎች 21ዱ ትግሬዎች ናቸው ? ይህ ምን ያህል እውነትነት አለው?

 6. Anonymous November 28, 2013 at 4:12 am Reply

  በአሁኑ ጊዜ ተቺ አልቸገረም ወሬኛም ሞልቶአል በሥራ ግን የሚታየው ሰው በጣም ጥቂት ነው። መቺም በዚህ ዘመን የምንገኝ በስም ኢትዮጵያውያን መልካሙን ነገር እንኳ ለመቀበል በፍጹም እያቃተን ነው። የአንድ ሰው ትክክለኛነቱ የሚመዘነው በቀላሉ መልካሙን ከመጥፎው እንዲለይበት የተሰጠውን አእምሮ በአግባቡ ሲጠቀምበት ነው። ከዚህ ውጪ ከሆነ ግን ጤናማ መሆኑ ያጠራጥራል። በተለይ ምቀኝነት ምንጊዜም የማይለየን በስም ኢትዮጵያውያን ነገር ሁሉ ስለተምታታብን የምንሰጠው አስተያየት ከተራ ምቅኝነት የመነጨ እንጂ አንድም ለእርምት የሚያበቃ በሳል አስተያየት በአብዛኛው ድረ ገጾች አይነበብም። ይህ ራሱ የችሎታም ማነስ ተጨምሮበት ለህገርም ትልቅ የትውልድ ኪሣራ ነው ለማለት ይቻላል።

 7. Anonymous November 28, 2013 at 6:43 am Reply

  በኦርቶዶክስ ዉስጥ ያለዉን ችግር ለማስዎገድ የተጀመረዉ የመዎያያ መድረክ የሚያበረታታነዉ፡፡ስለዚህ ዎደፊትም የታሰቡት መድረኮች ተጠናክረዉ መቀጠል አለባቸዉ፡፡

 8. Anonymous November 28, 2013 at 9:46 am Reply

  ይገርማል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሰሜን(በተለይ የትግሬ)ያደረጋት ማንው አማራ ደቡብ እና ኦሮሚያ ሌሎችስ ድርሻ የላቸውም ያሳዝናል

 9. Anonymous November 28, 2013 at 5:26 pm Reply

  werewu yiweral sirawun man yisrawu

 10. Melaku November 28, 2013 at 6:55 pm Reply

  kale Hiyiwot Yasemalin!!!!!!!!!!!!!! lela min enilalen!!!!

  የቤ/ንን ለውጥ ያማይፈልጉ ሰዎች የሚነሱትን የተስፋ የመቁረጥ አስተሳሰቦች ቦታ አንስጥ፡፡ አበው እንደሚሉት አውቆ የተኘውን ብቀሰቅሱት ይሰመም ነው ብህሉ!፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: