የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናታዊ ውይይት በጥብቅ ሥነ ሥርዐታዊ ኹኔታ ውስጥ ይካሄዳል፤ ለካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት አመራሮች እና የምእመናን ተወካዮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

A.A Diosces Head Office

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት (ፎቶ: ሀገረ ስብከት)

 • ጥናቱ – እያንዳንዳቸው ከ30 – 296 ገጾች ያሏቸውን 13 የመዋቅር (የሀ/ስብከቱ ልዩ መተዳደርያ ደንብ)፣ የፖሊሲና ማኑዋል አርእስተ ጉዳዮችን ያካተተ በርካታ ጥራዞች ሰነድ መኾኑ ተገልጦአል፡፡
 • ከእነርሱም መካከል ከሚሻሻለው ቃለ ዐዋዲ ጋራ እንደሚጣጣም የሚጠበቀውን የሀ/ስብከቱን ልዩ መተዳደርያ ደንብ (መዋቅር) ጨምሮ፡- የሰው ሀብት አስተዳደር፤ የሰው ኃይል ልማት፤ የፋይናንስ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን፤ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ፤ የግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር፤ የኢንቨስትመንትና ምግባረ ሠናይ፤ የቅርስና ቱሪዝም፤ የመንፈሳዊ ፍትሕ፣ የአስተዳደር እና የሥራ ክርክር ጉዳዮች ችሎቶችን የተመለከቱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ዝርዝር አሠራሮች ይገኙበታል፡፡
 • ዛሬ፣ ኅዳር ፲፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በሀ/ስብከቱ አዳራሽ እንደሚጀመር የሚጠበቀው ጥናታዊ ውይይቱ በአምስት ጠቅላላት ዙሮች የሚካሄድ ሲኾን ከብር 160,000 በላይ የማስፈጸሚያ በጀት ተመድቦለታል፡፡
 • በዛሬው የመጀመሪያ ዙር ጥናታዊ ውይይት ላይ በተጋባዥነት ከሚሳተፉት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ዋና ሓላፊዎች ጋራ የሀ/ስብከቱ የዋና ክፍል እና የክፍል ሓላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጆችና የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ሓላፊዎች እንዲሁም በቀጣይ አራት ዙሮች በ40፣ በ40 ምድብ የተከፈሉ የ166 አድባራትና ገዳማት ሠራተኞችና አገልጋዮች ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ በተሳታፊዎች ውክልና ረገድ የለውጥ አመራሩ ማኅበራዊ መሠረቶችና ዋነኛ ፈጻሚዎች ለኾኑት ካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት አመራሮችና የምእመናን ተወካዮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡
 • ጥናታዊ ውይይቱ የለውጥ አመራር ፖሊሲዎቹንና ማኑዋሎቹን በማስተዋወቅ (ኦሬንቴሽን)፣ በማሥረጽ እና በተሳታፊዎች ውይይት በማዳበር ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያው በጥናታዊ ውይይት መርሐ ግብሩ በሚገኘው የብዙኀኑ ሠራተኛና አገልጋይ አስተያየት ከዳበረና መሠረተ ሰፊ ግንዛቤ ከተያዘበት በኋላ የጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ ጸድቆ ለአህጉረ ስብከት ኹሉ በሞዴልነት የሚጠቀስ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የሥራ ሰነድ ይኾናል፡፡
 • ለሦስት ወራት የቆየውና በሓላፊው፣ ሠራተኛውና አገልጋዩ ላይ የማይናቅ የለውጥ ዜናና የተነሣሽነት ንቅናቄ እንዳሰማና እንደፈጠረ የሚታመነው የሽግግር ወቅት በተፈጸመበት ማግሥት የሚጀመረው የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናታዊ ውይይት÷ የሠልጣኞች ተጨባጭ አቅምና ለለውጡ ያላቸው ዝግጁነት በግልጽ መድረክ የሚፈተንበት፣ ጥቅመኛ አሉባልተኛውና የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ቅጥረኛው ከሐቀኛ ሠራተኛውና ቀናዒ ኦርቶዶክሳዊው የሚለይበት ኹነኛ ወቅት እንደሚኾን ተመልክቷል፡፡ ህም እያንዳንዱ ሠልጣኝ ለጥናታዊ ውይይቱ ያለውን የተሳትፎ አግባብነት በጥብቅ ሥነ ሥርዓታዊ ቁጥጥር ከማረጋገጥ ጀምሮ በጥናታዊ ውይይት ተሳትፎውና ተሳትፎውን ተከትሎ በአቻ ግመታ በተወሰደ የቤተ ክርስቲያንና የዘመናዊ ትምህርት ዝግጅት፣ ሞያዊ ልምድ እና በአገልግሎት አፈጻጸም ምዘና ሥርዐት በሚካሄምደባዎች እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡
 • ከምንም ዐይነት ክፍያ ነጻ በኾነ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮና ሥርዐት በማገናዘብ የተሠራው ይኸው የለውጥ አመራር ጥናት ቤተ ክርስቲያናችንን ከብር ሦስት ሚልዮን ያላነሰ ወጪ እንደሚያድን ተገምቷል፡፡
 • ካለፈው ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ በገዳማውያን ጸሎት ጭምር እየታገዘ ጥናቱን በታታሪነት ሲያካሂድ የቆየው የባለሞያ ቡድኑ ከሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት የተውጣጡትን ጨምሮ ዘጠኝ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች በአባልነት የሚገኙበት መኾኑ ታውቋል፡፡

የጥናቱንና የጥናታዊ ውይይቱን ተጨማሪ መረጃዎች ይከታተሉ

Advertisements

8 thoughts on “የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአፈጻጸም አቅጣጫ የሰጠበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የለውጥ አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ጥናታዊ ውይይት በጥብቅ ሥነ ሥርዐታዊ ኹኔታ ውስጥ ይካሄዳል፤ ለካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የሰንበት ት/ቤት አመራሮች እና የምእመናን ተወካዮች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

 1. Anonymous November 26, 2013 at 8:57 am Reply

  endezih aynet aserar new mayet yemnnafqewu.Egziabher yasayen.

 2. Anonymous November 26, 2013 at 10:10 am Reply

  ቃለ ህይወት ያሰማልን!

 3. Anonymous November 26, 2013 at 10:16 am Reply

  good job.

 4. Fekadu Gashaw November 26, 2013 at 11:46 am Reply

  Ye EgziAbHer terad’o ayileyachew.

 5. Anonymous November 26, 2013 at 2:48 pm Reply

  መልካም ጅምር ነው እግዚአብሔር ለአባቶቻችንና ለቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የሚተጉትን እድሜ ይስጥልን ::

 6. demessie tefera November 27, 2013 at 5:04 am Reply

  Great job! I think it is a time of rennaissence for EOTC.

 7. Annonyname November 27, 2013 at 6:02 am Reply

  ይበል፣ይሁን የሚያሰኝ ጅምር ነው ፡፡እግዚአብሔር ፍፃሜውን ያሳምርልን፡፡ ለሰራተኞቹም መንፈሳዊ ብርታትንና ብልሀትን ይስጥልን፡፡

 8. Melaku November 27, 2013 at 11:57 am Reply

  May God ends this great Proposal!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: