ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተመደበ

  • የለውጥ አመራር ሂደቱን የሚያስቀጥል ዋና ሥራ አስኪያጅ ይፈለጋል
NebureEd Aba Yohannes Gebra Hiwot

ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በጊዜያዊነት የሚመሩ ሓላፊ ተመደቡ፡፡ ሓላፊነታቸውን በድንገት ለቀው ወደ አሜሪካ ባቀኑት መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት ምትክ የተመደቡት ጊዜያዊ ሓላፊ የክህነትና መንፈሳዊ ፍትሕ ዋና ክፍል ሓላፊ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት ናቸው፡፡

የንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት ጊዜያዊ ሓላፊነት እስከ ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ሲኾን በዚህ ከኻያ ቀናት ላልበለጠው ጊዜ በሚቆየው ሓላፊነታቸው መደበኛና ዕለታዊ ቢሯዊ ተግባራትን ብቻ ሲያከናውኑ እንደሚቆዩ ተገልጧል፡

ወዲያውም በሽግግር መዋቅርና አደረጃጀት የተጀመረውንና በዘላቂነት የሚቀጥለውን የለውጥ አመራር ሂደት ይዞ ለመጓዝ ብቃት ያላቸው ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በግልጽ አሠራር ለመመደብ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚቆይ ተመልክቷል፡፡

በለውጥ አመራር መዋቅሩና አደረጃጀቱ መሠረት የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ ተልእኮ በኾኑት በክህነታዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ሲያተኮር፣ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ደግሞ የድጋፍ ሰጪ ክፍሎችን/ሥራዎችን በበላይነት የሚያስተባብር፣ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ያለው ከፍተኛ ባለሞያ እንደኾነ ‹‹አዲስ አበባ በለውጥ አመራር ያብባል ገና›› በተሰኘው ሰፊ ዘገባችን ማስነበባችን ይታወሳል፡፡

ለተገለጹት ጥቂት ቀናት ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ የመመደብን አስፈላጊነት የተጠየቁት የዜናው ምንጮች ስለ ኹኔታው ሲያስረዱ÷ የቀድሞው ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት ስለ አሜሪካ ጉዟቸው ቀድመው ሳያሳውቁና ለጽ/ቤቱ የዝግጅት ጊዜ ሳይሰጡ በድንገት ተነሥተው መሄዳቸው፣ ወቅቱ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ሰሞን የነበረ መኾኑንና ዋና ሥራ አስኪያጁ ሲለቅ በፍጥነት የሚተካ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳይመደብ መቆየቱን በምክንያትነት ዘርዝረዋል፡፡

በጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡት ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት ከኅዳር ፩ ቀን እስከ ግንቦት መጨረሻ ፳፻፭ ዓ.ም.  በቆየው በአራቱ የአህጉረ ስብከቱ መዋቅር ወቅት ሁከትና አቤቱታ ከተዘወተረባቸው አህጉረ ስብከት አንዱ የነበረውን የደቡብ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት በሥራ አስያጅነት መርተዋል፡፡


Advertisements

2 thoughts on “ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተመደበ

  1. Mamush November 8, 2013 at 1:29 pm Reply

    Be honest for your church

  2. ተካልኝ ከበደ November 8, 2017 at 2:49 am Reply

    አሳትፉኝ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: