የሃይማኖት እንከን የሌለባትና ተቆርቋሪ ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያናችን በአመራርና በአያያዝ ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ ሊገታ ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

His Holiness meglecha 11

ፎቶ- ማኅበረ ቅዱሳን

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመጀመሪያው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው ስለሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዛሬ፣ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጥዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በቅዱስነታቸው መግለጫ መሠረት ምልአተ ጉባኤው÷ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ምእመናንን ስለ መጠበቅና ማብዛት፣ የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት ተቋሞች በጥራትና አደረጃጀት በመለወጥ ከመማርና መሠልጠን አልፎ መከራን ለመቀበል የተዘጋጁ ላእካነ ወንጌልን አብቅቶ ስለማውጣት፣ ፍጹም የዕድገት ለውጥ ለማምጣት ስለሚያስችለው የፋይናንስና የመልካም አስተዳደር ጅምር ጥናት ሂደት፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የውሳኔ አሰጣጥ የቤተ ክህነት ልዩ ልዩ ክፍሎች ሓላፊዎች፣ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ ወጣቶችና ምእመናን ውክልናና ተሳትፎ ስለሚረጋገጥበትና የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት ስለሚያገኝበት አሠራር ይመክራል፤ ውሳኔም ያሳልፋል፡፡

‹‹የአክራሪነት፣ አሸባሪነትና ጽንፈኝነት›› ተግባራትን በማውገዝ የክርስቶስ መልእክት የኾነውን ሰላምና እኩልነት፣ መከባበርና መቻቻል፣ አብሮ መልማትና ማደግ ለሕዝቡ በየቀኑ ማስተማርና መስበክ እንደሚገባ የገለጹት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ችግሮችን በውይይትና በውይይት ብቻ የመፍታት ባህል መደገፍና ማጎልበት አለብን፤›› ሲሉም መክረዋል፡፡

አጀንዳዎቹ÷ በፍትሕ መንፈሳዊ በተደነገገው መሠረት የተሰበሰበው ምልአተ ጉባኤው መንፈስ ቅዱስ በሚገልጽለት መንፈሳዊ ጥበብ እየተመራ መፍትሔ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮች መፍትሔ እንዲያገኙ፣ በጥልቀት፣ በማስተዋልና የሓላፊነት መንፈስ በተላበሰ ወኔ በመወያየት ሊወስንባቸውና ለተግባራዊነታቸው ሊረባረብባቸው እንደሚገባ ምልአተ ጉባኤውን በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ፓትርያርኩ፣ መንፈስ ቅዱሳዊና ሐዋርያዊ ዐቢይ ጉባኤው በስብሰባው መጨረሻ የሚደርስበት ውሳኔና የሚያወጣው መመሪያ በውጤቱ÷ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስፋፋ፣ ማኅበረ ካህናቱንና ማኅበረ ምእመናኑን የሚያስደስት፣ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ተከታዮች ዘንድ በናፍቆት የሚጠበቀውን የለውጥና የዕድገት ጎዳና የሚከፍት እንዲኾን በመግለጽ መግለጫቸውን ደምድመዋል፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባመክፈቻጋዜጣዊ መግለጫ ዐበይት የትኩረት ነጥቦች

በድንበር የለሽ ስብከተ ወንጌል በርከት ያሉ በጎችን የማርባትና የመጠበቅ ሥራ

 • ከትንሹ የሥልጣነ ክህነት ሹም ጀምሮ እስከ ትልቁ የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ድረስ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ተልእኮ በንቃት፣ በሙሉ ዕውቀት፣ በተነሣሽነት፣ በፍጹም ፈቃደኛነት እንዲነሣሣና እንዲሰለፍ የሚጠበቀውን ያህል አልተሠራም፡፡
 • ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት ወልዳ፣ በሥጋ ወደሙ አሳድጋ፣ ወልደ ማርያም፣ ገብረ ሚካኤል ብላ የሠየመቻቸው ልጆቿ ከጉያዋ እየተነጠቁ ወደ ሌላ ካምፕ ሲወሰዱ እርስዋ የወላድ መሐን የኾነችበት፣ ያልወለዱና ያላሳደጉ ባለብዙ ቤተሰብ የኾኑበት ክሥተት እያጋጠመ ነው፡፡
 • የቅዱሳን ሐዋርያት ሥልጣን ወራሾች እንደመኾናችን ቁጥር አንድ ሥራችን በድንበር ሳይገደቡ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በሥሩ ያሉትን በጎች መጠበቅ ብቻ ሳይኾን ድንበር የለሽ ትምህርትና ስብከት በማካሄድ ከዛሬ ጀምሮ በየዓመቱ በርከት ያሉ በጎችን የማርባትና የመጠበቅ ሥራ ሊያሠራው የሚችል አሠራር መቀየስ አለበት፡፡

 

የትምህርት ተቋሞቻችንን በብዛትም በጥራትም በአደረጃጀትም በመለወጥ ትንሣኤዎቻቸውን ማብሠር፤

 • የምንሾማቸው ዲያቆናት፣ ቀሳውስትም ኾኑ ኤጲስ ቆጶሳት በተለምዶ የተሾሙ ሳይኾኑ ጌታችን እንዳደረገው የተማሩ፣ የሠለጠኑ፣ ነገሩ የገባቸውና መከራውን ለመቀበል የተዘጋጁ ሊኾኑ ይገባል፡፡
 • የአብነት ት/ቤቶቻችን፣ የካህናት ማሠልጠኛዎቻችንና የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን በብዛትም በጥራትም በአደረጃጀትም ተማሪውን በትክክል ለመለወጥና ለመቅረጽ በሚያስችል አዲስ አሠራር ማስተካከልና ማብቃት አለብን፡፡
 • ቤተ ክርስቲያናችን የሃይማኖት እንከን ሳይኖራት፣ ሞያ ሳያንሳት፣ ተቆርቋሪ ምእመናን እያሏት በአያያዝና በአመራር ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ መገታት አለበት፡፡ ይህን በወሳኝ መልኩ ለማስተካከል የትምህርት ቤቶቻችንን ትንሣኤ የሚያበሥር፣ ዕድገታቸውንና ጥራታቸውን የሚያፋጥን ጠንካራ መሠረት ዛሬ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

 

ስለ ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራርና መልካም አስተዳደር የተጀመረው ጥናት ሂደት

 • ምእመናን የሚፈለገውን ዐሥራት፣ በኵራትና ቀዳምያት በሕጉ መሠረት እየሰጡ አይደለም፤ የሚሰጡትም ስጦታ በየመንገዱ እየተንጠባጠበ ወፎች የሚለቃቅሙት ይበዛዋል፡፡ የሚፈለገውን ያህል ተደራጅተን፣ መስለን ሳይኾን ኾነን፣ በሁሉም ነገር ተዘጋጅተን ማስተማር፣ ዘመኑ በሚፈቅደው የፋይናንስ ቁጥጥርና አያያዝ መጠቀም አለብን፡፡
 • ከወገንተኝነትና አድሏዊነት በአግባቡ ያልተላቀቀው አስተዳደራችን የቤተ ክርስቲያናችንን ተሰሚነት ክፉኛ እየጎዳው ነው፡፡ በመልካ አስተዳደር ዙሪያ ጉባኤው የማፍረስ ሳይኾን የመገንባት ግብ ያለው ራእይ አንግቦ ሥር ነቀል የኾነ ፍጹም የዕድገት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለውን አሠራር መቀየስ ይገባዋል፡፡

 

በቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ አሰጣጥ የካህናትና ምእመናን ተሳትፎ ስለማረጋገጥ

 • ቅ/ሲኖዶስ በጉዳዮች ካህናትንና ምእመናንን እያሳተፈና በሐዋርያዊ ሥልጣኑ እያጸደቀ የውሳኔውን ተቀባይነትና ድጋፍ የሚያሰፋበትንና የሚያረጋግጥበትን አሠራር ይተክላል፡፡
 • የቅ/ሲኖዶስ አባላት ችግሮችን በውይይት ብቻ የመፍታት ባህል ለማጎልበት መሥራት አለባቸው፡፡Holy SynodTikmet Openiing press release
Advertisements

25 thoughts on “የሃይማኖት እንከን የሌለባትና ተቆርቋሪ ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያናችን በአመራርና በአያያዝ ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ ሊገታ ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

 1. eshetu October 22, 2013 at 1:28 pm Reply

  ምዕመናን ሁላችን በፀሎት አባቶቻችን ማገዝ አለብን

 2. Tesfaye Gebreselasie October 22, 2013 at 5:39 pm Reply

  I can’t see the Amharic full history frome my device but just I Guss it is all about one Orthodox Church in Ethiopia and all over the world where Ethiopians refuges places .this is the big news that I always praying and regretting all the time God may Bless all our church leaders and make theme creat one church like we had before !!God Bless Ethiopia!!!

 3. melketsediknewayekrstos October 22, 2013 at 7:04 pm Reply

  ቤተክርስቲያኗ ከኛ የምትጠብቀውን ሁሉ ከኛ ለመለገስ ተግተን በጋራ በመስራት ያለፉት 23ዓመታት ዘንድሮን ጨምሮ ማለት ነው በቤተክርስትያኗ ላይ እና በምእመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን ከባድ መከራ ፣በደል፣ግፍ፣ሰማዕትነት ለማስቆም በሁለመናችን ከአባቶች ጎን መቆም ይኖርብናል አምላክ ይርዳን እናንተን አባት አድርጎ የሰጠን እግዚኣብሄር ይመስገን።

 4. Anonymous October 22, 2013 at 8:27 pm Reply

  አለሁ እድሜየ ገፍቶአል የማይሉ ናቸው ና እኛ ምዕመናኖቹ ተሰላችተን የምንወዳትን ቤተክረስቲያን ጥለን ከመለየታችን በፊት በህማም ላይ ያሉትን ና እድሜአቸው የገፋውን እግዚአብሄር ረድቶዎት በጡረታ እንዲገለሉ ማድረግ ይጠበቅበዎታል ፡፡ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን ስለ ግል ጥቅማቸው ስለ ሥጋ ዘመዶቻቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ መንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራው በሚባልለት ሲኖዶስ ተሰግስገዋል ሀገረስበከቶቹን እንደግል ሀብታቸውም የሚቆጥሩ አሉ አንዳንዶቹም እድሜአቸው የገፋ በአደረባቸው ህማም ምክንያት ተንቀሳቅሰው የማያገለግሉ ነገር ግን ጡረታ መውጣት ሲገባቸው ያልወጡ በቃኝ ታምሜ

 5. Anonymous October 22, 2013 at 9:51 pm Reply

  Tkkel New ewnet New beteley ketehadesso yegelaglune Hulachenem Entseleye.

 6. Anonymous October 23, 2013 at 1:20 am Reply

  መልካም ጅምር ነው አባቶቻችንን እግዚአብሔር ይርዳቸው

 7. Anonymous October 23, 2013 at 3:29 am Reply

  dinber yalesh yewengel agelgelot endiset masebu ejig des yasenyal. entseley.

 8. Anonymous October 23, 2013 at 3:31 am Reply

  Abatachn jmarewot melkam now eskemechereshaw yetsenu hunu. Yebetekrstiyanachnn tnsae yasayen,

 9. Anonymous October 23, 2013 at 8:43 am Reply

  bemahiberu sim yetesebesebut batekalay lewegn ayhonu lebete kirsitiyan ayhonu terefe ayihud nachehu zendro yleyal seytan besew enjeralay ashiwa yemtbetnu yerasachhun enjera yemtabesilu dibki yepoletika ajenda tegaltal yketlal

 10. Yohannes October 23, 2013 at 10:52 am Reply

  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን የመሰረታት በቃሉ ነውና በትምህርትና በትምህርት ቤት ላይ ብዙ መሥራት ያስፈልጋል የሚለውን በጣም ግሩም ነው። የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የሐዋርያት ጉባኤ እንዲሆን እግዚአብሔር ይርዳን።

 11. ዮሐንስ አፈዎርቅ October 23, 2013 at 11:00 am Reply

  መልካም ጅምር ነዉ አባቶቻችን እግዚአብሐየር ይርዳቸዉ

 12. nanusha October 23, 2013 at 12:25 pm Reply

  kkkkkkkkkkk…..”ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት ወልዳ፣ በሥጋ ወደሙ አሳድጋ፣ ወልደ ማርያም፣ ገብረ ሚካኤል ብላ የሠየመቻቸው ልጆቿ ከጉያዋ እየተነጠቁ ወደ ሌላ ካምፕ ሲወሰዱ እርስዋ የወላድ መሐን የኾነችበት፣ ያልወለዱና ያላሳደጉ ባለብዙ ቤተሰብ የኾኑበት ክሥተት እያጋጠመ ነው፡፡”…..በጣም ይገርማል ውሻ ከሄደ ጅብ ይጮሃል ነው ያሉተ….ዛሬ ነው እንዴ የሚታያቹህ ወይስ አለቆቻቹህ የህዝቡን ስሜት በዚህ ውሰዱ ብለዋቹህ ነው……የተባሉት ካምፖች የዛሬ 20 ዓመት ካልነበሩበት ከሌላው ህዝበ እኩል የሚገዳደሩበትን ቁጥር ሲይዙና በትምህርት፤ ፖለቲካውና በኢኮኖሚው ቁልፍ ቦታዎችን ሲይዙና ከውስጥ አርበኞችን ሰግስገው ሁለት እግራቸውን መሬት ላይ ካቆሙ በኋላ ነው የሚነቁት…ወይስ ሌላ ተልዕኮ ለመፈፀም………ለማንኛውም በሀገር ውስጥኛ በውጭ የተማረውንና ለሃይማኖት ክብር ያለውን ውጣት ጥርግ አርገው ግዴለሹን ከተውት በኋላ ከላይ ላይ ብቻ የሚደረግ መፈራገጥ ብዙም ለውጥ ያለው አይመስለኝም ……ለውጡ ከውስጥ መጀመር አለበት የሚል ነው ሃሳቤ

  • TSEGA MARIYAM October 27, 2013 at 7:43 am Reply

   “””diyabilos zenarun cherese kesetun aragefe bête keresetiyanen gin alegodatem”””” yelekes yesedeb AFE YETESETEW DIYABELOS NEW ENA SHIMUTUN TETEN EWONET YE EGZIABEHER SEW KEHONE ENETSELEY KEGNA YEHONU BIWOTU ENKUAN YEMETALU KALEHONU GIN ENEDEWOTU YEKERALU.””””EGZIABEHER TEWAGI NEW SEMUM EGEZIABEHER NEW””””.

 13. Anonymous October 23, 2013 at 3:07 pm Reply

  ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን ስለ ግል ጥቅማቸው ስለ ሥጋ ዘመዶቻቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ መንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራው በሚባልለት ሲኖዶስ ተሰግስገዋል ሀገረስበከቶቹን እንደግል ሀብታቸውም የሚቆጥሩ አሉ አንዳንዶቹም እድሜአቸው የገፋ በአደረባቸው ህማም ምክንያት ተንቀሳቅሰው የማያገለግሉ ነገር ግን ጡረታ መውጣት ሲገባቸው ያልወጡ በቃኝ ታምሜ አለሁ እድሜየ ገፍቶአል የማይሉ ናቸው ና እኛ ምዕመናኖቹ ተሰላችተን የምንወዳትን ቤተክረስቲያን ጥለን ከመለየታችን በፊት በህማም ላይ ያሉትን ና እድሜአቸው የገፋውን እግዚአብሄር ረድቶዎት በጡረታ እንዲገለሉ ማድረግ ይጠበቅበዎታል፡፡

 14. Anonymous October 24, 2013 at 9:25 am Reply

  ጥርግ ያለ ሞኝነታቹሁን ህዝቡ ሲነቃና የመንፈሱ ጥሪን መልስ ሲያገኝ ነው የሚሄደው …ከተቻላቹህ ዘመናዊነት(የዛሬ 100 እና 200 ዓመት ለነበረ ትውልድ የሚነገር ወሬ ይዛችሁ ..እንዴት ይህን ትውልድ ለመያዝ ትሞክራላቹህ……ይህ ህዝብ ፍም እሳት ነው….ነው ያለው) እንዴት አላምዶና ተራ የአባቶችን ተረት እንዴት ቀርፎ እንደሚወጣ ስሩ

 15. Mamush October 24, 2013 at 9:51 am Reply

  These are the most critical issues of discussion,specially now a days, by the Holy Synod upon which we expect persistent decision and enforcement with out anybody’s intervention to bring change and prosperity to our CHURCH. Besides to this, ordination of new bishops has to be seriously considered not to repeat the past history mistake. Let our CHURCH first get relief from those corrupted and racist church leaders who defame the religion. Courage and determination is required in this case. The “Government” he himself must take this as a necessary step to combat corruption.

 16. Astreaye Yohanes October 24, 2013 at 12:56 pm Reply
  Hello dear blogger, I do not your address and am forced to forward this document (I do not know if it said to be article or commentary) as comment. Would you please try to post it on your blog? Astreaye   አንዴ አብዮታዊ ዴሞክራት ሌላ ጊዜ ደግሞ የአክራሪነት አቀንቃኝና ፈጻሚነት ካባ ለብሶ የመንግስቱንና የድርጅቱን ራዕይ እያደናቀፈ የሚውለው የራሳችን የታመመ ወይም የበሰበሰ አካል መስተካከል አለበት፡፡ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ይህቺ ቤተ ክርስቲያን’ኮ UNHCR ሳይቋቋም የስደተኞች ካምፕ አዘጋጅታ ስደተኞችን ስትቀበል የኖረች የዓለም ምሳሌ እንጂ ወያኔ እንደሚለው ሌሎችን የምታሳድድና ለልማት አንቅፋት የምትሆን አይደለችም፡፡ ታጋይ “ካህናት”ም ተልዕኮዉን ተቀብለው ወያኔ ስልጣን ከያዘ በኋላም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ተሰግስገው የማይነጥፈውን የእናት ቤተ ክርስቲያን ጡት ይጠባሉ፣ ሲፈልጉም ይነክሷታል፡፡ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያንን በማዳከም ዓላማቸውን ለማሳካት በታወቁ ገዳማት የስለላ ቡድኖች ተሰማርተው ስውር ደባቸውን ሲፈጽሙ ነበር፡፡ ይህንን የስለላ ቡድን አንዲመራ ተልዕኮ የተሰጠው ደግሞ የዛሬው “ወመሽ” አቶ ሰብሃት ነጋ ነበር፡፡ በቤተ ክህነት የስልጣን እርከኖች የፈለገውን የመሾምና የመሻር ተግባሩን በማኅበረ ቅዱሳንም ተግባራዊ ለማድረግ ወያኔ ብዙ ሞክሮ ነበር፡፡ መክስተ የአርዕስት 1. መግቢያ – 1 – 2. ክፍል አንድ፡ የወያኔ ዘመቻ ቅድመ 1983 – 4 – 3. ክፍል ሁለት:- የወያኔ ዘመቻ 1984 – 1990 ዓ/ም – 8 – 4. ክፍል ሦስት፡ የወያኔ ዘመቻ ከ1990 – 1997 – 10 – 5. ክፍል አራት፡ የወያኔ ዘመቻ ድኅረ 1997 – 13 – 6. ዘመቻ ወያኔ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ – 35 – 7. ማጠቃለያ – 47 – 7.1. ከሊቃነ ጳጳሳት ምን ይጠበቃል? – 47 – 7.2. ከምዕመናን ምን ይጠበቃል? – 48 – 7.3. ከሰንበት ት/ቤቶች ምን ይጠበቃል? – 49 – 7.4. ከማኅበራት ምን ይጠበቃል? – 49 – 7.5. በውጭ ሃገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምን ይጠበቃል? – 50 – 7.6. በመሪ ድርጅት ኢህአዴግ አባላት ምን ይጠበቃል? – 51 – 7.7. ከነጻ ሚዲያዎች ምን ይጠበቃል? – 52 – 7.8. ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ምን ይተበቃል? – 52 – 1. መግቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የወያኔ መንግስት አክራሪነትን አስመልክቶ በሚሰጣቸው መግለጫዎችና በሚያካሂዳቸው ኮንፈረንሶች እንዲሁም ስብሰባዎች አክራሪ የሚላቸውን ሃይሎች በስም እየጠቀሰ ለህዝቡና ለአባላቱ ያሳውቃል፡፡ በተለይ በ2006 ዓ/ም ይህንን ተግባር በግልጥና በስውር በሰፊው እንደሚያከናውነው ከተዘጋጁት ዕቅዶችና ዕቅዱን ለማስተዋወቅ ከተደረጉ ንግግሮች ለመረዳት ይቻላል፡፡ በሃገራችን የአክራሪነት ምንጩ ራሱ ወያኔ እንደሆነ በግልጥ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ያለውን ጥፋት ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ትግል ሊኖር እንደሚገባ እምናለሁ፡፡- የምንጎዳው ሁላችን ነንና! ውጤት ለማምጣት ግን አክራሪነትንና አሸባሪነትን ለማጥፋት መጀመሪያ ወያኔ ራሱን ፈትሾና ስህተቱን አርሞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ዘወር ብለን ስለ አክራሪነት በሰፊው ማጥናት የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ባይሆንም መዳሰስ ግን ይኖርብናል፡፡ የኢትዮጵያ ነገስታት በሃገሪቱ የሚኖሩ የተለያዩ እምነት ተከታዮች ተቻችለውና ተገነዛዝበው እንዲኖሩ ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ታሪክ የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡ ምናልባት እስልምና ዳብዛው ጠፍቶ እንዳይቀር ያደረገው የኢትዮጵያውያን ነገስታት ቅንነት እንደነበር ቁርዓን ሚናገረው ነው፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሉ በሙሉ የክርስትና እምነት ተከታይ የነበረባት ሃገር የሌሎች እምነት ተከታዮች መጥተው ሲሰፍሩና የራሳቸውን ቤተ እምነት ሲያቋቁሙ የከለከላቸው የለም፡፡-ለዚያውም የወቅቱ ነገስታት ኃይል በዓለም ላይ ሚዛን በሚደፋበት ሰዓት፡፡ ክርስቲያኑ የእስልምና እምነት ተከታዮችን የእምነት ተቋም ግንባታ እገዛ ሲያደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡-ምንም እንኳን የተወሰኑት አሁን ሃቁን ቢክዱትም፡፡ አልፎ አልፎ ግጭቶች እየተከሰቱ ነገስታት ርምጃ ሲወስዱ እንደነበር ደግሞ የማይካድ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ፖለቲካዊ እንጂ ሃይማኖታዊ እንዳልነበር ለመረዳት በአካል መገኘት አያስፈልግም፡፡ ሃይማኖታዊ ቢሆን ኖሮ በወቅቱ ሁሉንም ማባረር ወይንም ወደ አንድ ሃይማኖት እንዲጠቃለሉ ማድረግ የሚሳናቸው አልነበሩም፡፡ በፖለቲካው ምክንያት ርምጃ የወሰዱ ነገስታት ክርስቲያኖች ስለነበሩ ሁሉንም ወደዚህ ሃይማኖት ለማስገባት የሚከብዳቸው አልነበረም፡፡-የቤተ ክርስቲያን ፍላጎትም በኃይል ማሳመን ሳይሆን በፍላጎት ሊድን የሚወደውን መጥራት ብቻ ነው፡፡ በታሪክ የተጠቀሱት ግጭቶች (ሃይማኖትን አስመልክቶ) ተመራማሪዎች እንደሚሉት ሌሌች ለቤተክርስቲያኗ አስተዋጽዖና ታሪክ እንዲሁም ሕልውና ዕውቅና ከመንፈጋቸው የተነሳ ነው፡፡ በሃገራችን ተቻችሎና ተገነዛዝቦ የኖረው ህዝብ ለዚህ ምሳሌና ዓርዓያ ነው፡፡ ወያኔም በየመድረኩ ታሪካችን እያለ የሚደሰኩረው የቀደሙ አባቶቻችን የኖሩትን ነው፡፡ የሚያወራቸው ታሪኮችም የበፊቶቹ ነገስታት እንጂ ወያኔ ሃገሪቱን መምራት ከጀመረ በኋላ የተፈጸሙ አይደሉም፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ (ነፍሱን ይማረውና) በመድረክ ለወጣቶች እንደተናገረው በአንድ ወቅት የጀርመን ፕሬዚደንት ሃረርን በጎበኘበት ወቅት የክርስቲያኑና ሙስሊሙን ህዝብ መግባባት አይተው ይህንን የመቻቻል ባሕል ለዓለም ማስተማር ነበረባችሁ ብለው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ይሄ የመቻቻል ባህል የወያኔ መንግስት ስልጣን ከመያዙ በፊት የተገኘ ድል እንጂ የዚህ ዘመን ድል አይደለም፡፡ ተቻችሎ የኖረው ህዝብ መጣላት የጀመረው በተለይ ከ1984 ዓ/ም በኋላ መሆኑን ልብ ይሏል! አክራሪነትና አሸባሪነት ምንጩ የወያኔ መዋቅር እንደሆነ ራሱ የመሠከረውን ከዚህ በታች እንመልከት፡- እስከአሁን የተካሄዱ የፀረ-አክራሪነት እንቅስቃሴዎች የማይናቅ ውጤት ያስመዘገቡ ቢሆኑም መሰረታዊ ለውጥ አላመጡም፤….እንዲያውም የትኛውም አክራሪ ኃይል ከመዋቅር አካል (ከወያኔ መንግሰት ማለታቸውን ልብ ይሏል) “በርታ” ሳይባልና “ሽፋን ሳይሰጠው” የሚንቀሳቀስ እንደሌለ በገሐድ አማኞቹ ይገልጻሉ፡፡ የመንግስት መዋቅራችን አካል ሆነው አክራሪነቱን በድብቅም/በገሐድም የሚደገፍ አካል በፌዴራልም በክልልም ከሞላ ጐደል የሚታወቁ ናቸው፡፡ እነዚሁ አካላት በተቻላቸው ሁሉ በመድረክ ጤናማ እየመሰሉ የሚኖሩ ናቸው፡፡ የተቋማቸውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው በፀረ-አክራሪነት የሚንቀሳቀስን አካል የሚቀጡ፣ አሉባልታ እየፈጠሩ የሚያሸማቅቁ ሆን ብለው ድጋፍ የሚነፍጉና፣ በሐሰት ምስክርም ጭምር ዜጎችን የሚያሳስሩ ናቸው፡፡ የመንግስትን አቅሞች ተጠቅመው አክራሪነትን የሚያስፋፋና ከአክራሪነት እንስቅቃሴ ጋር በተለያዩ ጥቅሞች የተሳሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህን ከመዋቅር ውስጥ ይዞ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ፀረ-አክራሪነት ትግል ማካሄድ አይቻልም፡፡ “የፀረ-አክራሪነት ትግል የወቅቱ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች” የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፡፡ መጋቢት 2005 ዓ/ም በዚህ መልኩ በአሸባሪነት ቫይረስ የተበከለ ድርጅት ሌላውን አሸባሪ እያለ ለመፈረጅ አስቀድሞ ምን ሞራል ሊኖረው ይችላል? በየአካባቢው እንደምንመለከተው አሸባሪዎችን ድጋፍ በማድረግ ክርስቲያኑን የሚያስገድሉ፣ በሕግ ቁጥጥር ስር ሲውሉ ደግሞ ነጻ እንዲለቀቁ በማድረግ፣ ይህንን የሚከታታሉ የሕግ ባለሙያዎችን በማስፈራራት ውሳኔ የሚያስቀለብሱ፣ በሃሰት ምስክር እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ርምጃ የሚወስዱባቸው የወያኔ ባለስልጣናት አሸባሪ ሳይባሉ ማን አሸባሪ ሊባል ይችላል? ይህ ብቻ አይደለም በትክክል አሸባሪነትን ለመዋጋት ቆርጠው የተነሱትን እያሸማቀቀ ትግሉን የሚያደበዝዘውና የሚያኮላሸው የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣን ነኝ ባይ አይደለም እንዴ? አንዴ አብዮታዊ ዴሞክራት ሌላ ጊዜ ደግሞ የአክራሪነት አቀንቃኝና ፈጻሚነት ካባ ለብሶ የመንግስቱንና የድርጅቱን ራዕይ እያደናቀፈ የሚውለው የራሳችን የታመመ ወይም የበሰበሰ አካል መስተካከል አለበት፡፡ በጅምላ መጓዝ፤ በጅምላ መኮነን፤ ባለቤት የሌለው ፍረጃ ወዘተ… እየሆነ ይቀጥላል፡፡ ይህ አደገኛ ስርገት ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል ብቻ ሳይሆን ሕልውናችንን የሚፈታተን የጅምላ ጉዞ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በድርጅታችን ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች የተሰሩ የማጥራት ስራዎች ቢኖሩም መሰረታዊ ለውጥ ያመጣ አይደለም፡፡ “የፀረ-አክራሪነት ትግል የወቅቱ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች” የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፡፡ መጋቢት 2005 ዓ/ም ወያኔ መንግስትና ሃይማኖት ተለያይቷል፣ መንግስት በሃይማኖት፣ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚል በወረቀት ላይ ያሰፈረው ሕግ አለ፡፡ ይህ ሕግ ግን ነጮች “paper tiger” ብለው ከሚጠሩት ያለፈ አይደለም፡፡ ለይስሙላ በወረቀት ላይ ይስፈር እንጂ ጣልቃ እየገባ አሁን ላለው ሃገሪቱ ለደረሰችበት የሃይማኖት ግጭት ዋና ምክንያት ራሱ ወያኔ ነው፡፡ እንደ አቶ ተፈራ ዋልዋ አይነት ደካማ ባለስልጣናቱ በየመድረኩ አንዱን ሃይማኖት በማጥላላት ህዝብን ከህዝብ፣ የአንዱን ሃይማኖት ተከታይ ከሌላው ጋር በማጋጨት የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ ሲጋልብ የኖረው ራሱ ወያኔ እንጂ ሌላ አካል አይደለም፡፡ እንደነ ስብሃት ነጋ አይነቱ ደግሞ እስልምና በሃገሪቱ ሲጨቆን የኖረ ስለሆነ የሃይል ሚዛኑን ለማስተካከል የኦርቶዶክስን ሃይል ማዳከም በሚል ስትራቴጂ ሲደክሙ እንደኖሩ በይፋ መናገር ጀምረዋል፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያንን በዓላማ ለማዳከም፣ ብሎም ለማጥፋት የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ለመቃወምና ብሎም ለመመከት ያቻል ዘንድ ለሚመለከታቸው ሁሉ መረጃውን ለማድረስ፣ ወያኔን ደግሞ ተሳስተሃልና ተመለስ ለማለት፣ የገዢው ፓርቲ አባላትን (በቅንነት ሃገራቸውን ለሚያገለግሉት አካላት) ደግሞ እውነቱን ከሃሰቱ በመለየት ለሃገር ልማትና ሕዝቡ ሚፈልገውን ለማስፈጸም እንዲሁም ሚጋልባቸውን ወያኔን አስተውለህ ተጓዝ ለማለት እንዲያመቻቸው ግንዛቤ ለመፍጠር ይህ ጽሁፍ ድርሻ ይኖረዋል ብየ አስበባለሁ፡፡ ወያኔ በዓላማ ተሰልፎ ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ከፕሮቴስታነቱ አካላትጋር አብሮ መሥራቱን እስካለቆመና አሁን እየተከተለ ያለውን ዘግናኝና አሰቃቂ ተግባር እስካላቆመ ድረስ በእጄ የሚገኙትን ማስረጃዎች በሙሉ እውቀቱ ካላቸውና ተጨማሪ መረጃዎች ከሏቸው አካላት ጋር በመተባበር ይህንን መሰል ጽሁፍ ለኦርቶዶክሳውያን በተለያዩ ሚዲያዎችና ከተቻለም በመጽሐፍ መልክ በማዘጋጀት የድርሻየን እንደምወጣ ከወዲሁ ለማረጋገጥ እወዳለሁ፡፡ በምሠራበት መሥሪያ ቤት ባለኝ የመረጃ ቅርበት ይህንን መሠል ሥራ ለማከናወን ክፍተቱ ስለማይኖርብኝ በሚቀጥሉት ጽሑፎች በበለጠ ቤተ ክርስቲያንን በሚጠቅም መልኩ እንደማዘጋጅም እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ፡፡ ዓላማዬ ፖለቲካ ባለመሆኑ ምዕመናንም ሆነ የወያኔ ድርጅት አባላት የተደረገው ሁሉ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም በሚደረገው የወያኔ ዘመቻ በማነጣጠር እንድትረዱልኝ አሳስባለሁ፡፡ 2. ክፍል አንድ፡ የወያኔ ዘመቻ ቅድመ 1983 ከህወሀት መሥራቾች አንዱ የነበረው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ በጻፈው ታሪክ መሰል ጥራዝ ከገጽ 300 ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያበጠለጥላት እንመለከታለን፡፡ እርግጥ ይሄ አካሄድ የጥናቱ ባለቤት ፈጠራ ሳይሆን ወያኔ ይዞት የተነሳው ግብ በመሆኑ፣ አሁንም ይህንን ዓላማውን ለማስፈጸም ደፋ ቀና በማለት ላይ ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ዶ/ር አረጋዊ ካስቀመጣቸው ነጥቦች ሚከተሉት ጥቂቶቹ በጥእምርተ ጥቅስጥ ውስጥ ሆነው ቀርበዋል፡ “ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞዎቹ መንግሥታት ጋር በነበራት ቁርኝት ከገዢው መደብ ጋር የተሰናሰለ የጥቅም እና የጨቋኝነት ግንኙነት ነበራት። በነዚህ ረዥም የጭቆና ዓመታት ከተጨቆኑት መካከል ደግሞ ሙስሊሞች ይገኙበታል፡፡” በማለት ወያኔ ሲጀመር ይዞት የተነሳውን ዓለማ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶናል፡፡ “ምንም አንኳን በትግራይ ቤተ ክርስቲያኗ ከወያኔ ጋር ልትሰለፍ የምትችል ብትሆንም ሁኔታውን በጥንቃቄ መመልከት ይኖርብናል፡፡ (ድርጅታችን) የማርክሲስት አስተምህሮ የሚገፋፋው ቢሆንም ያን ያህል ሃይማኖትን የሚቃወም አይደለም (ቤተ ክርስቲያኗን መቃወሙን የሚገልጥ ነገር መቀመጡን ልብ ይሏል)፡፡ ቤተ ክርሰቲያንን በራሱ (በወያኔ) አካሄድ ለመምራት በሚደረገው ጥረት ግን እንደሚሳካ ምንም ጥርጥር አልነበረም፡፡” በግልጥ እንደተቀመጠው እስልምናን ተጨቋኝ አድርጎ በማቅረብ ቤተ ክርስቲያንን ጨቋኝ እያለ ካዳከመ በኋላ ዋናው ዓላማው ወደሆነው አጀንዳ ያመራል፡፡- ቤተ ክርስቲያንን በወያኔ ስልት ብቻ እንድትመራ ማድረግ! ጸሐፊው ቤተ ክርስቲያንን የነቀፈ መስሎት የሚከተሉትን ሃሳቦች አስፍሯል፡፡ (ከገጽ 300 እስከ 304 ያለውን የጥናት ጽሁፍ መመልከት ይቻላል) “ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ያለ ሰንደቅዓለማ በዓላትን አያከብሩም፡፡ ይሄ ደግሞ ወጥ በሆነ መንገድ በሃገሪቱ ወታደራዊ ሥርዓት ውስጥ የምንመለከተው ነው፡፡” (No church ever conducted major ceremonies without hoist the Ethiopian flag – an act also regularly observed in the Ethiopian army)፡፡ ወያኔ ለመማርም ሆነ በቀና አመለካከት ለመገንዘብ ህሊናም ጊዜም የለውም አንጂ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የቤተ ክርስቲያኗን የቃል ኪዳን አርማ የሚወክል እንጂ የፖለቲካ ምልክት አይደለም (ነገስታቱ ከሚጨምሩት ምልክት ውጪ)፡፡ የቃል ኪዳን ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሃገሪቱም ሰንደቅ ዓላማዋን ከቤተ ክርስቲያን ወስዳለች፡፡ እርግጥ ነው ቤተ ክርስቲያን በሃገራችን የመንግስትን አስተዳደር የመሠረተችና ስታጠናክር የቆየች እንደመሆኗ መጠን ነገስታቱ የሚያምኑበትን አድርገወዋል፡፡ አንድ ሉዓላዊት ሃገር የራሷ ሰንደቅ ዓላማ ሊኖራት ይገባል፣ ዓለማቀፋዊ ስርዓትም ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማ ክቡር ነው፡፡ እንኳንስ ሉዓላዊት ሃገር ድርጅቶች እንኳን ሰንደቅ ዓላማ አሏቸው፡፡ መለያቸው ነውና በእርግጥም ያከብሩታል፡፡ አቶ መለሰ ዜናዊ ሰንደቅ ዓላማ ጨርቅ ነው፣ ትርጉምም የለውም በሚል ሲያጥላላ አንደነበረ ይታወቃል፡፡ በሂደት የህዝብ ፍላጎት ስለሆነና ለሃገር አንድነትም ወሳኝ መሆኑን ሲታወቅ፣ የአንድነት ምልክት መሆኑንም የተለያዩ አካላት ሲመሰክሩና ትችት ሲሰነዝሩ “የሰንደቅዓላማ ቀን” በሚል የሃገርን ሃብት በማባከንና ህዝቡን ሥራ በማስፈታት ላይ ተጠምዶ እያየነው ነው፡፡-ቅጥ ያጣና የሃሰት ሰልፍ! ወያኔ በዶ/ር አረጋዊ በረሄ በኩል የጻፈው ሌላ ሃሳብ ደግሞ እንደ መናፍቃን የካህናትንና ደቀመዛሙርትን ስም ማጥፋት ነው፡፡ ይህንን እንደዚህ ይገልጠዋል፡፡ “Land was the most important incentive and encouraged many young men to invest time in going to church schools to become priests” (ወጣቱ ወደ አብነት ትምህርት ቤት የሚሄደውና ካህን ለመሆን የሚማረው ቤተ ክርስቲያን ይዛው ከነበረው መሬት ለመካፈል ሲል ነው) በሚል እንድምታ ካህናት ሰማያዊውን ዋጋ ፈልገው መንፈሳዊ ትምህርት መማራቸውን ሲክድና ዋጋ ሲያሳጣው ይታያል፡፡ ስለዚህም ወያኔ ዓላማውን ለማሳካት የተከተላቸው ደረጃዎች “ቤተ ክርስቲያንን ማምከን/ፍሬ ቢስ ማድረግ እና ሙስሊሞችን ማንቀሳቀስ” (neutralizing the Church and Mobilizing Muslims) የሚል ሲሆን ይህንን ዓላማውን ለማሳካት በወያኔ ድርጅት የተከናወኑ ተግባራትን ወይም የተወሰዱ ርምጃዎችን ከዚህ በታች አንመለከታለን፡፡ ሀ. የመጀመሪያው ርምጃ ቤተ ክርስቲያን ይዛው የነበረውን መሬት ሙሉ በሙሉ መቀማት፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበረሰቡ ስላልተስማማ ለካህናት እንደ ሪም ይሰጣቸው የነበረውን መሬት ለጊዜውም ቢሆን በዝምታ ማለፍ፣ ለ. ሁለተኛው ርምጃ ቤተ ክርስቲያን በማሕበረ-ኢኮኖሚው ውስጥ ያላትን ሚና በመንጠቅ ዓላማየን ያሳኩልኛል ላላቸው የመንደር ማኅበራት መስጠት (people’s assemblies) ነው፡፡ ከዚህ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን የነበራት መብትና ሃላፊነት ወደ ማኅበራቱ ተሸጋገረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም ሕዝቡን የመቀስቀስና አንድ የማድረግ እንቅስቃሴዋ እየከሰመ መጣ፣ በማስታረቅ/ግጭትን በመፍታት፣ በመንፈሳዊውና በምዕመናን ሕይወት ውስጥ የነበራትን ደረጃም እንድታጣ ተደርጓል፡፡ ሐ. በሦስተኛ ደረጃ ከ1979 (እኤአ) ጀምሮ ወያኔ በራሱ አስተምህሮ ጠልፎ ካድሬ ለማድረግና ለመማረክ ለተመረጡ አጥቢያ ካህናት ስልጠናዎች በተደጋጋሚ ሰጥቷል፡፡ ዋናው የስልጠናው ዓላማ ደግሞ የወያኔን ስልታዊ ዓላማዎች ለማሳካት ሲባል በትግራይ ያለች ቤተ ክርስቲያንን ከሲኖዶስ በመገንጠል የትግራይን ብሄርተኝነት ማጠናከር የሚል ነበር፡፡ (The underlying motive of the seminars was to isolate the church in Tigrai from the wider Ethiopian church in order to foster Tigraian nationalism along the lines of the TPLF’s strategic objective) በትግራይ የተመረጡ ወረዳዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከቅድሰት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ ነው ተብሎ በሚነገርለት ገብረ ኪዳን ደስታ ሲሆን ዓላማው የቤተ ክርሰቲያንን ኃይል (Ethiopian Church’s authority) በማዳከም በወያኔ አስተሳሰብ (TPLF minded/oriented church) የምትመራ፣ አገልግሎቷም በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲሆንና ፍጻሜውም በትግራይ ብሔርተኝነትና ማንንት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ ይላል ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፤ በትግራይ ውስጥ ያሰለጠኗቸው ካድሬ ካህናት ከቅዱስ ሲኖዶስ ለመገንጠል አንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር፡፡ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያንን በማዳከም ዓላማቸውን ለማሳካት በታወቁ ገዳማት የወያኔ የስለላ ቡድኖች ተሰማርተው ስውር ደባቸውን ሲፈጽሙ ነበር፡፡ ይህንን የስለላ ቡድን አንዲመራ ተልዕኮ የተሰጠው ደግሞ የዛሬው “ወመሽ” አቶ ሰብሃት ነጋ ነበር፡፡ በወቅቱ የወያኔ ካድሬዎች መነኮሳት መስለው (TPLF members camouflaged as monks) በገዳማት ተሰራጭተው ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በማፋለስ የወያኔን አስተሳሰብ (Ideology) በገዳማቱ ለማስረጽ ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ይህም በተወሰነ መንገድ ተሳክቶላቸዋል ማለት እችላለሁ፡፡ ከ1987 እስከ 1989 (እኤአ) ወያኔ በተቆጣጠራቸው የትግራይ ክፍሎች ባሰለጠናቸው ካድሬ ካህናት ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት በመክፈል በትግራይ አካባቢ ራሱን የቻለ ወያኔ መራሽ የቤተ ክህነት አስተዳደር መሰረተ፡፡ ይህ አስተዳደር የሚመራው ወያኔ ባዘጋጀው መተዳደሪያ ደንብ ስለነበር ሃይማኖታዊ ሳይሆን የፖለቲካ አጀንዳ የነበረውና በምድራዊ መተዳደሪያ ደንብ ሲንቀሳቀስ የነበረ ነው፡፡ የእስልምናን መስፋፋት (ለራሱ ተቀባይነትና የተወሰኑ የእምነቱን ተከታዮች ለመማረክ ሲል ብቻ ያደረገው መሆኑን መገንዘብ ይገባል) ሲናፍቅ የነበረው ወያኔ ከአባላቱ መካከል ክርስቲያን ነን ባይ ነፍጠኛ (combatants) የበረሃ አባላቱን የሙስሊም ስሞች እየለጠፈላቸው እንደነበር በዚህ የተነሳ እስልምናው በወያኔ ድርጅት ውስጥ የበለጠ ድጋፍ እንዳለውና ድጋፍ ሊያደርጉለት እንደሚችሉ አማኞችን ለማታለል ተጠቅሞበታል፡፡ ሌላው የወያኔ መንግስት ደባ ሃገሪቱን ታሪክ አልባ ማድረግ ነው፡፡ መቼም የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነሳቷ አይቀርም፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት የሃገሪቱን አስተዳደር መስመር በማስያዝ መሥርታ ለወግ ለማዕረግ ያበቃች ናትና ነው፡፡ የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ በመቀየር የ3000 ዓመት ታሪክ ሳይሆን የ20 ዓመት ታሪክ ብቻ ያላት ሃገር አድርጎ አቀረባት፡፡ ዲሞክራሲውም፣ ነጻነቱም፣ ልማቱም…ወዘተ ሁሉ ከወያኔ በችሮታ የተሰጠን ሆነi:: ነገስታቱን በሙሉ የሚያጣጥል፣ የሃገሪቱን ታሪክ ጥላሸት ቀብቶ የጻፈ፣ የሃገሩን አንድነት መሥራቾች የሚነቅፍ፣ ለሃገር አንድነትና ሉዓላዊነት ትልቁን ድርሻ የተወጣች ቤተ ክርስቲያንን እዉቅና መንሳት ሳይሆን ሰይጣናዊ አስመስሎ በሌሎች ዘንድ ጥላቻ እንዲያድርባቸው በር የከፈተና እየከፈተ ያለ፣…የበላበትን ወጭት ሰባሪ ብቸኛ ገዢ ፓርቲ ወያኔ!፡፡ በወያኔ አመለካከትና ፍረጃ (ምንም እንኳን አሁን ችግር ሲገጥመው በየሚዲያው ተቻችሎ የኖረ ህዝብ ነው እያለ ቢለፈልፍም) ዶ/ር አረጋዊ በረሄ እንደጻፈው “Ethiopia is no longer the chosen nation but a prison house of ethnic groups (ኢትዮጵያ የተመረጠች ሃገር መባሏ ቀርቶ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች እንዲሁም ጎሳዎች ሲጨቆኑባትና ሲታፈኑባት የኖረች እስርቤት)” ተባለች ፡፡ ታዲያ በዚህ መልኩ የፈረጀ መንግስት ዛሬ ኢትዮጵያውያን ተቻችለን የኖርን የዓለም ምሳሌዎች ነን በማለት ማቀንቀኑ ለምን ይሆን? ጥላሸት የቀባውን ታሪክ ለምን እንደገና አርሞ አይጽፈውም? በዚህ ቅዠት ሲመራ የነበረው ወያኔ ስልጣን በያዘ ማግስት የራሱን ካድሬዎች በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ሰበሰበ፤ የራሱን ፓትርያርክም ሾመ! በሃይማኖት ጣልቃ አልገባም የሚለው ወያኔ ጣልቃ መግባት ብቻ ሳይሆን ተዘፈዘፈበት ማለት ሳይቀል አይቀርም፡፡ ወያኔ በጫካ ውስጥ በነበረበት ሰዓት ከደርግ ቦምብ ድብደባ ለማምለጥ መጠጊያ ማድረግ የሚመርጠው አድባራትንና ገዳማትን ነበር፡፡ በተለይ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍሎች አድባራትና ገዳማት ባለውለታዎቹ ናቸው፡፡ ዛሬ መነኮሳቱን ቢያሳድዳቸውም፣ አድባራቱን ለማፍረስ ቆርጦ ቢነሳም፡፡ የዋልድባ ገዳም ለዚህ ተጠቃሽ ነው፡፡ ሟች አቶ መለስ ሲናገር እንደነበረው “ባይወዳቸውም ፈርዶበት አብዛኛውን የጫካ ጊዜውን ያሳለፈው” በገዳማት ውስጥ ተደብቆ ነበር፡፡ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የወያኔን ፖለቲካዊ ታሪክ በጻፈበት ጥናቱ ህወሐት ተከታታይ ሴሚናሮችን ለተመረጡ ካህናት በመስጠት በራሱ አመለካከት ቀርጾ ወደ ቤተ ክርስቲያን ያስገባ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1979 ሲካሄድ የነበረው ሴሚናር ዓላማ በትግራይ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ በመለየት እና በመነጠል፣ የትግራይ ብሔርተኝነትን በማጠናከር ፓርቲው ለራሱ ዓላማ እንዲሰለፉ ማድረግ ነው። በተከታታይ በተሠጡት ስልጠናዎች ሰልጣን ካህናት ቤተ ክርስቲያንን ሳይሆን የትግራይ ብሄርተኝነትን ብቻ አንግበው እንዲንቀሳቀሱ፣ አሐቲ ቤተ ክርስቲያን ብለው የሚያምኑትን ወደኋላ በመተው የወያኔን ርዕዮት እንዲከተሉ አደረጋቸው፡፡ “ታጋይ ካህናትም” ተልዕኮዉን ተቀብለው ወያኔ ስልጣን ከያዘ በኋላም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ተሰግስገው የማይነጥፈውን የእናት ቤተ ክርስቲያን ጡት ይጠባሉ፣ ሲፈልጉም ይነክሷታል፡፡ ወያኔ ሃገሪቱን ሲቆጣጠር መጀመሪያ የወሰደው ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን መድረክ ለመጠቀም እንዲመቸው መንበሯን መጨበጥ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት በሆነ ባልሆነው ሊቃነ ጳጳሳትን በማዋከብ ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስን ከመንበራቸው አነሳ፡፡ በዚህ ዙሪያ ብዙ ሲባል እሰማለሁ፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተሰባስበው ቢለምኗቸው አልፈልግም ብለው ነው፣ ታመው ስለነበረ ስላልቻሉ ነው፣ ጳጳሳቱ ተፈራርመው ከወያኔ ጋር አድመው አስወጧቸው…ወዘተ የሚል ሃሳብ ሲንጸባረቅ የምንሰማው ጉዳይ ነው፡፡ አውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ ህወሓት በጫካ ሳለ ያሰለጠናቸው ታጋይ “ካህናት” በሚፈልጉት መንገድ እንዲንቀሳቀሱ አስቀድሞም በአሜሪካ ለድርጅቱ ገንዘብ በማሰባሰብ ተግባር ላይ ተጠምደው የነበሩትን አባ ጳውሎስ በመንበሩ በማስቀመጥ ቤተ ክርስቲያንን በራሱ ምሕዋር ውስጥ እንድትንቀሳቀስ ማድረግ ነበር፡፡ ይህንን ለማሳካት ተልዕኮ የተሰጠው የዛሬው መናፍቅ የቀድሞው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ታምራት ላይ ነበር፡፡ ዛሬ በተለያዩ የፕሮቴስታንት እምነት ድርጅቶች አዳራሽ እንደሚናገረው ተልዕኮውን “በብቃት” ተወጥቷል፡፡ አቡነ መርቆርዮስም በግፍ ከመንበራቸው ተነሱ፣ አባ ጳውሎስም ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው መንበሩን ተቆናጠጡ፡፡ አቡነ መርቆርዮስ በራሳቸው ችግር ለቅቀው እንደሄዱ ለማስመሰል ብፁዓን አበዉ በግዴታና በደባ ተስማምተው ፓትርያርኩን እንዳባረሩ ተደርጎ ቃለ ጉባዔ እንዲያዝ አደረገ፣ በምትኩም አባ ጳውሎስን እንዲሾሙ ጫናው ተደርገና የተፈለገው ሁሉ ሆነ! 3. ክፍል ሁለት:- የወያኔ ዘመቻ 1984 – 1990 ዓ/ም አሁን መንበረ ስልጣኑን ተረክበዋል፣ ሃገሪቱን ተቆጣጥረዋል የቀረው አስቀድሞ በጫካ ውስጥ ሲያልሙት የነበረውን ለማስፈጸም ማንኛውንም ስልት መጠቀም ነው፡፡ ለስሙ ሕገ መንግስት ሲቀረጽ መንግስትና ሃይማኖት ተለያይተዋል፤ መንግስት በሃይማኖት፣ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚል ማታለያ ተካተተ፡፡ ስልጣኑን በተቆናጠጠ ማግስት ሊቃነ ጳጳሳትን የደርግ ደጋፊዎች ናችሁ…ወዘተ በሚል ማዋከብ ጀመረ፡፡ አካሄዱን በግልጥ ስላልተረዳነው ብዙም ትኩረት የሰጠነው ጉዳይ አልነበረም፡፡ በወቅቱ በየክፍለ ሃገሩ በነበረው የባለ ስልጣናቱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ “ሰብከት” የቤተ ክርስቲያንን ስም ማጥፋት አንዱ ስልት ነበር፡፡ አቶ ተፈራ ዋልዋ በደቡብ ሕዝቦች መድረኮች “ሲገዛህ የኖረ የሰሜን ኦርቶዶክሳዊ ነፍጠኛ ነው፣ ቤተ ክርሰቲያኗም የእነርሱ ብቻ ናት”….ወዘተ በማለት ተቀባይነትን ለማግኘት ሲጠቀምበት ነበር፡፡ “በታሪክ በርካታ ስሕተት የፈጸመች ነፍጠኛ፣ ዐፄያዊ እና ደርጋዊ” በማለት ሲፈርጃት እንደነበረ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ በሂደት በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በየሃገረ ስብከቱ ያሉ የድርጅት አባላቱን ቁጥር በመጨመር ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን የማያከብሩ ነገር ግን ሊቃነ ጳጳሳቱንና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም ምዕመናንን የሚያስፈራሩ፣ በስብከተ ወንጌል ሳይሆን ችግሮችን የፌደራል ፖሊስ በመጥራትና በማንገራገር አዳፍነው የሚያስቀሩ ግለሰቦች ቁጥራቸው ጨመረ፡፡ እነርሱን የሚቃወም ሲገኝ የወያኔ ባለስልጣናት በዓይነ ቁራኛ የሚመለከቱትና አልፎ አልፎም ጥቃት የሚያደርሱበት ሆነ፡፡ በየገዳማቱ የሚሹለከለኩ ሰላዮች፣ በየአድባራቱ የሚሾሙ ካድሬዎች፣ በስብከተ ወንጌል ስም የሚቀመጡ ካድሬዎች ተሰባስበው ቤተ ክርስቲያኗን የፖለቲካ አውድማ አደረጓት፡፡ ይህንንነ ማድረጉ ሳያንሰው ወያኔ “ቤተ ክርስቲያን የከሰሩ ፖለቲከኞች መጠራቀሚያ ናት” የሚል ነጠላ ዜማውን በየጊዜው ማሰማቱን ቀጠለበት፡፡ ለመሆኑ የከሰረ ፖለቲከኛ ማን ነው? እኔ እስከማውቀው ድረስ የተጠጋውና ካድሬዎቹን በቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ የኮለኮለው ወያኔ በመሆኑ የያዘው በሽታ ጸፍቶ እንዳናገረው እውነትም የከሰሩ ፖለቲከኞች ተጠራቅመውባታል! በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውሬ እንደተመለከትኩት የሰበካ ጉባዔ አስተዳደር ምርጫዎች አንዳንድ እኩያን በሚያደርጉት ሴራ የወረዳ ፖሊስ ጥበቃ እያደረገ የሚከናወኑ ሆነዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሰዎችም እየለመዱት የፖለቲካ ጥገኝነታቸው እየጨመረ መጣ፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ የተመሸጉ የወያኔ አባላትም ሹመቱን በሙስና ላይ ብቻ የተመሠረተ አደረጉት፡፡ መንፈሳዊነቱ ከንቱ የሆነ ሰው ይህንን ቢያደርግ የሚደንቅ አይሆንም፡፡ ፓትርያርክ ጳውሎስም ለእነዚህ ፖለቲከኞች ሽፋን በመስጠትና ለህወሓት አባላት ቅድሚያ በመስጠት (ራሱ የወያኔ ስለላ ድርጅት በ08/02/1995 ዓ/ም በጥናቱ ባቀረበው ሪፖርት) የቤተሰብ መጠራቀሚያና ለሙስና መስፋፋት አይነተኛ ቤት አደረጉት፡፡ የግላቸውን “ቤተ ክርስቲያን” እየከፈቱ በውጭ ሃገር ገንዘብ በማጋበስ የሚታወቁትን እየሰበሰቡ የራሳቸውን sphere of influence ማስፋት ጀመሩ፡፡ የፓትርያርክ ጳውሎስን ሕገወጥነት በተመለከተ በቀረበው 11 ገጽ ሪፖርት “…ለፓትርያርኩ ወዳጅነት አላቸው የሚባሉ ሊቃነ ጳጳሳት ከሦስትና አራት ብዙም ያልበለጡ ናቸው፡፡ ፓትርያርኩ ምንም ዓይነት ተቀባይነትና ከበሬታ ያጡ በመሆናቸው ህልውናቸውን የአንዳንድ መሪዎችን ስም በመጥራትና እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ላይ የተንጠላጠለ ሆኗል፡፡” በማለት በቤተ ክርስቲያን ላይ የነበረውን ሕገወጥ አሠራር ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ምንም እንኳን ሪርቱ በዚህ መልክ ቢቀርብም የተወሰደ ርምጃ ግን አልነበረም፡፡ በዚህ ሪፖርት የተካተተው ሌላው ነጥብ ደግሞ እንደሚከተለው ሰፈፍሯል፡- የመንግስት ባለስልጣናት ፓትርያርኩን ከሕግ በላይ እንዲሆኑ የተወሰነው ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዳይኖረው ማድረግና ፓትርያርኩም “ኢህአዴግ ካለ ማን ይነካኛል” እያሉ መዘባበትና ከሚያጅቧቸው ጳጳሳት ይልቅ የሚያጅሟቸው ጠመንጃዎች መብዛታቸው ሁሉንም ሰው እንደሚያሴርባቸው አድርገው በጥርጣሬ ዐይን ማየታቸውና በማንምና ማንም እምነት ማጣታቸው ሲታይ የፓትርያርኩ ህልውና ከቤተ ክርስቲያኗና ከሕግ ውጪ እንዲሆን አድርጎታል” ምንጭ፡ ለዋናው መ/ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ከ-ል.ዮ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ጉዳይ ይመለከታል፡፡ 08/02/1995 ዓ/ም፡፡ ከላይ ባየነው መልኩ የቅዱስ ሲኖዶስ ቃል ሳይሆን የግለሰቡና የግበረ አበሮቻቸው ውሳኔ ሲተላለፍ አበው ካህናት አግዚኦ….. ሲሉ ቆዩ፡፡ ለፓትርያርኩ ከህግ በላይ መሆን ዋናው ምክንያት መንግስት ለመሆኑ በግልጥ ከመቀመጡም በላይ “ኢህአዴግ ካለ ማን ይነካኛል” እያሉ ሲፈጽሟቸው የነበሩ ተግባራት ፍንትው ብለው ሲታዩ የኖሩ ናቸው፡፡ በ1994 ዓ/ም ሊቃነ ጳጳሳቱ ብሶታቸው ሲገነፍል ፓትርያርኩን ሊታገሱ ይገባል በሚል እንደራሴ እንዲሾም ወስኖ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር ሞክሮ ነበር፡፡ ውሳኔው ግን በጨለማው የቤተ ክህነትና ቤተ መንግስት ቡድኖች ሊከሽፍ ችሏል፡፡ የዚህን ዓይነት ጥያቄ ያቀረቡ ሊቃነ ጳጳሳትንም በዝውውር ስም ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ እያንገላቱ ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ማድረግ ጀመሩ፡፡ ይሄ ጉዳይ እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አባቶችን ለማሸማቀቅ ሲጠቀሙበት እንደቆዩ ግልጽ ነው፡፡ ወያኔ ሊቃነ ጳጳሳት በሚሾሙበት ወቅት የቀድሞውን ፓትርያርክ በመጠቀም የሚፈልጋቸውን ሰዎች እየመረጠ እንዲሾሙለት ሲያደርገው የነበረው እንቅስቃሴ ብዙዎችን አባቶች የተፈታተነ ነበር፡፡ እርግጥ አሁንም ይህንን ፍላጎቱን በስውር እያንጸባረቀ ነው፡፡ ወያኔ ባደረገው ስውር ደባ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከ 1990 ዓ/ም ድረስ የመናፍቃንን መስፋፋት፣ የተሃድሶ ድርጅቶችን ውስጥ ለውስጥ መስፋፋት፣ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ወያኔ መራሽ እንዲሆንና ቤተ ክህነት በቤተሰባዊ አስተዳደርና በሙስና ተጠምዳ መድረኳ ሁሉ የጉደኞች መፈንጫ ሆነባት፡፡ 4. ክፍል ሦስት፡ የወያኔ ዘመቻ ከ1990 – 1997 ከ1990 ዓ/ም ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን በመናፍቃን ላይ ተከታታይ ርምጃ በመውሰድ ሰፊ እንቅስቃሴ ያደረገችበት ጊዜ ስለሆነ ሁላችንም እናስታውሰዋለን፡፡ በወቅቱ በቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዙሪያ የተሰባሰቡ የተሃድሶ መናፍቃን ድርጅት አባላትን በማስረጃ እያጣራ ቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ ርምጃ ወስዷል፡፡ በጊዜው ርምጃ የተወሰደባቸው መናፍቃን ወያኔ የሚጓዝበትን መስመር ስለተረዱት ከቤተ ክርስቲያን የተባረርነው በፖለቲከኛው ማኅበረ ቅዱሳን ጥላቻ ነው፣ ወዘተ በማለት ለወያኔና መሰል ጁንታዎቹ ስም ማጥፋቱን ተያያዙት፡፡ አስቀድሞ ማኅበረ ቅዱሳንን በጥርጣሬ ለሚመለከተው ወያኔ ደግሞ ምክንያት ስለሆነው ለሁኔታዎች ትኩረት በመስጠት ከአባ ጳውሎስ ጋር በመሆን ስልት መቀየስ ጀመሩ፡፡ በሂደት በ1993 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተፈጠረው የአስተዳደር ችግር ከዩኒቨርሲቲው የበላይ አካላት ጋር ግጭት ተፈጠረ፡፡-አመጹም ተፋፋመ፡፡ ነገሮች ሁሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሲያመሩ ዝም ብሎ ሲመለከት የነበረው ወያኔ በተማሪዎች ላይ አላስፈላጊ ርምጃ ወሰደ፡፡ ተማሪዎች ከግቢዎች እየወጡ መጠጊያ ፍለጋ ጀመሩ፡፡ የፖሊሶች ድብደባ መፈናፈኛ ያሳጣቸው ተማሪዎች የሃይማት ተቋማትን አይደፍሩም በሚል አራት ኪሎ ወደሚገኘው መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ይገባሉ፡፡ በወቅቱ ፓትርያርኩ ከፖሊስ ሠራዊት ኃይል የድኑናል የሚል ተስፋ ነበራቸውና ተማሪዎች ያድኑን የሚል ጥሪ አስተላለፉ፡፡ ይሁን እንጂ ተቃራኒው ሆነ፡፡ በወቅቱ የአዲስ አበባ ምዕመናን ተማሪዎች በሚያሰሙትን ጩኸት እየተጨነቅን አይዟችሁ በማለት አስፈላጊውን ምግብ ስናቀርብላቸው ነበር፡፡ ምዕመናን በዚህ ተግባራቸው ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና ተችሯቸዋል፡፡ በሌሎች ቤተ እምነቶች የተጠጉ ተማሪዎች ምንም ችግር ሳይደርስባቸው ነገሩ ሲረጋጋ ወደሚፈልጉት አካባቢ ለመሄድ ቻሉ፡፡ በቅድስት ማርያም ገዳም የተጠጉት ግን በሙሉ በኦራል ተጭነው ወደ ሰንዳፋ ተወሰዱ፡፡ በዚህ ወቅት ያቋቋሙት ግቢ ጉባዔያት አባላት በመሆናቸው ማኅበረ ቅዱሳን አባቶች ተማሪዎችን አሳልፈው መስጠት አልነበረባቸውም በማለት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ ይህንን አስመልክቶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተሰገሰጉ ካድሬዎችና መናፍቃን፡- ማኅበረ ቅዱሳን ፓትርያርኩን እየተቃወመ ነው፤ መንግስትንም እንደሚቃወም ያወጣው ዘገባ ማሳያ ነው በማለት ክስ ማቅረብ ጀመሩ፡፡ ወያኔም በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከፍተኛ ዘመቻ ከፈተበት፡፡ ድሮውንም በጥርጣሬ ሲመለከቱት የነበሩ የወያኔ ሰላይና አንዳንድ ጥቅመኛ የቤተ ክሕነት ካድሬዎች ጥላቻቸው እየሰፋና ለምን ተደፈርን በማለት (የተደፈሩት ነግር ባይኖርም) ጦራቸውን መስበቅ ጀመሩ፡፡ እስከ 1997 ዓ/ም ድረስ ወያኔ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኃላፊነት ላይ ያሉ ጥቅመኛ “አባቶችን” በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የራሱን ዓላማ ብቻ እንዲያስፈጽሙ በማድረግ ላይ አተኩሮ ቆይቷል፡፡ በተለይ ቁልፍ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን የስልጣን ቦታዎች ሙያቸው የማይመጥኑት ሁሉ እንዲቀጠሩና ፖለቲካዊ አጀንዳውን ዘርግቶ ሰፊ ተግባር ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ ስልቱን ቀይሮ መጣ፡፡ አስተዳደር ሥራው ላይ ብቻ ሳይሆን ቀኖናና ዶግማዋን ለማፍረስና በራሱ Ideology የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ለማድረግና በእርሷ መድረክ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስችለውን መድረክ ለመፍጠር ቆርጦ ተነሳ፡፡ ከ1990 ጀምሮ እስከ 1997 ዓ/ም ድረስ ቤተ ክህነት በወያኔ ካድሬዎች የተወረረችበትና ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለወያኔ ዓላማ ራሳቸውን የሠጡ አካላት የተፈለፈሉበት ነበር፡፡ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ ገዳማት ችግር ሲደርስባቸው፣ አበው በግፍ ሲንገላቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ቦታዎች ሲነጠቁ ሆነ ብለው አሳልፈው የሚሰጡ ካድሬዎችና ወቸገዶች ጽ/ቤቱን ከበውት ይታዩ ነበር፡፡ በአጠቃላይ የደረሱትን ችግሮች በሚጠቁም መልኩ እንደሚከተለው አስቃኛለሁ፡፡ ለረጅም ዓመታት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ከፓትርያርክ ጳውሎስ የማይለየው ኤልያስ አብርሃን እንውሰድ፡፡ ኤልስ አብርሃ በኢህአዴግ የድርጅት አባልነቱ የታወቀ ወያኔ ያዘጋጀው ካድሬ ካህን መሆኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች የሚያውቁት ነው፡፡ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት በቆየባቸው ጊዜያት አድራጊና ፈጣሪ በመሆን ቤተ ክርስቲያን የተከፋፈለች እንድትሆን ካለው ፍላጎት የተነሳ በውጭ ያሉ አባቶች (ብጹዕ ወቅደሱ አቡነ መርቆርዩስና አብረዋቸው ያሉትን) እርቀ ሰላሙን እንዳይቀበሉት ከወያኔ በተሰጠው አፍራሽ ተልዕኮ መሠረት ሲያደናቅፍ ቆይቷል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚያካሂዳቸው ግድፈቶች ብፁዓን አበው ርምጃ እንዲወሰድበት የሚያቀርቡት ሃሳብ ሁሉ ውድቅ እየተደረገ ቆይቷል፡፡ አዲሱ ፓትርያርክ በተሸሙ ማግስት ኤልያስ አብርሃ አበቃለት ሲባል አሁንም የቅርብ አማካሪና አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ ስመለከተው ፓትርያርኩ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዳይመሩ በስውር የተቀመጠ ሰላይና ወያኔ ዓላማ አስፈጻሚ መሆኑን ለማረጋገጥ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ የሚገርመው ይህ ሰው አሁንም በውጭ ካሉ አባቶች ጋር በሚደረገው የእርቀ ሰላ ጉዳይ ዋነኛ ተደራዳሪ ሆኖ መቅረቡ ነው፡፡ ሰው እንዴት በማያምንበት ጉዳይ ስለ እርቀሰላም ሊደራደር ይችላል? ቤተ ክህነት በካድሬዎች ለመወረሯ ማሳያ የሚሆኑ ተጨማሪ ሰዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ የዋልድባ ገዳም በወያኔ የስኳር ፕጀክት ግንባታ ስም ሲታረስ፣ አባቶች እንግልት ሲደርስባቸው፣ ገዳሙም በወያኔ ሰራዊት ሲወረር ዘግይቶ ከእንቅልፉ የባነነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት አጣሪ ኮሚቴ መሳይ አሰማርቶ ነበር፡፡ የኮሚቴው አባላትም አቶ ተስፋዬ የኋላእሸት፣ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ገብረ መስቀል ነበሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገውን ሁሉ ያደርጋሉ ተብለው (ሰው ናቸው ተብሎ) ሲጠበቁ የመንግስትን አቋም ገልብጠው በሚዲያ ሲያስተላልፉ ሰማናቸው፡፡ ሃገር ያወቀውንና ፀሃይ ሞቀውን ጉዳይ እንደዚህ በማለት አስተጋቡት፡- “የምንመሰክርላችሁ ያየነውን ነው፤ ልማቱ በገዳሙ ክልል እንደማይካሄድና ገዳሙን እንደማይነካ አረጋግጠናል፤ ልማቱን እንደ ስጋት የሚያራግቡት ገዳሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግና ሕዝበ ክርስቲያኑን የማደናገር ዓላማ ያላቸው መነኰሳት ናቸው:: ይልቁንስ ግድቡ ለገዳሙ ልማት ዕድል በመሆኑ የገዳማት አስተዳደሩ በዚህ ዙሪያ መሥራት አለበት” በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካቀረቡት መግለጫ የተወሰደ በግልጥ እየታየ ያለ ሃቅን ክዶ ምዕመናንን በሃይማኖት መምራት ይቻላልን? ከዚህ በላይ ምን ክህደት አለ? በተመሳሳይ ወቅት በአሰቦት ገዳም የደረሰውን ቃጠሎ ጉዳይ ሚያጣራ የቤተ ክህነት ቡድን ተልኮ ነበር፡፡ የተላኩት አካላትም በወቅቱ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊው መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ ነበሩ፡፡ የነበረውን ሁኔታ የተለያዩ ሚዲያዎች በአግባቡ በመዘገብ አሳሳቢ መሆኑንና ሰዎች መሞታቸውን ለምዕመናን በማሳወቃችው ወያኔ ደስተኛ አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ ያልተዋጠላቸው የአጣሪ ኮሚቴ አባላት ግን “እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” በማለት የሰጡት መግለጫ ከማን ወገን እንደሆኑ ይመሠክርባቸዋል፡፡ 5. ክፍል አራት፡ የወያኔ ዘመቻ ድኅረ 1997 በምርጫ 97 ማግስት ድንጋጤ ያርበተበው ወያኔ ዜጎችን በማሰርና በመፍታት ከከተማ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? በሚል ቱባ ባለስልጣናቱን አሰማርቶ ንጹህ ዜጎችን ሲያሳድድ ነበር። በወቅቱ ለደረሰበት ሽንፈትም ምክንያት ናቸው ብሎ የለያቸው አከላት አሉ፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ጠላቶቻችን ናቸው ብለው የሚፈርጇቸውን ሁሉ የሃሰት ጥቆማ በማካሄድ በአንበሳው ጥርስ ውስጥ ያስገቡትም ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ መንፈሳዊ ማኅበራት፣ ካህናት እና ጳጳሳት የዚህ ሰለባ በመሆን እንግልት ደርሶባቸዋል፤ በእምነት አልባ የወያኔ ቱባ ባለስልጣናት ስድብና ዛቻ ተሰንዝሮባቸዋል፡፡ በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት ሕገ መንግስቱና የምርጫ ሕጉ ከሚፈቅደው ውጪ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምኅረት ሕዝቡን ካልቀሰቀስን በማለት ከአባቶቻችን ጋር ያልተገባ ውዝግብ ሲፈጥሩ የነበሩ አካላት በምርጫ ሲሸነፉ ደግሞ መልሰው እነዚህን አበው ስማቸውን ማጥፋትና ማዋከብ ጀመሩ፡፡-የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ደጋፊና አባል ናቸው እያሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሄዱባቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእስላም አሸባሪ በተነሳና ክርስቲያኖችን በገደለ ቁጥር የማስተካከያ ርምጃ መውሰድ ሲገባው በሃገሪቱ የማያባራ የአሸባሪነት ተግባራት ምንጭ የሆነው ወያኔ ቤተ ክርስቲያንን አብሮ ማዳከም ጀመረ፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አክራሪ ሙስሊሞች የጅማ ክርስቲያኖችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲጨፈጭፏቸው ዋነኛ ኢላማው የነበረች ቤተ ክርስቲያን ናት፤ በተለይ ማኅበረ ቅዱሳን፡፡ “ሊበሉ የፈለጓትን አሞራ….” እንዲሉ በወቅቱ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ በቪዲዮ ቀርፆ ያሰራጨው ማኅበረ ቅዱሳን ነው በማለት የማኅበሩን አባላት ሲያዋክብ ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳንን አሸባሪ ነው ማለት ጀመረ፡፡- ለዚህም ያግዙት ዘንድ አንዳንድ የቤተ ክህነት ካድሬዎቹን መለመለ፡፡ አስቀድሞ በራሱ ፍላጎት ሲመራቸው የነበሩትን ፓትርያርክ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ የነበረውን ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃንን እንዲሁም በየሃገረ ስብከቱ አሉኝ የሚላቸውን ካድሬዎች በማኅበሩ ላይ አዘመተ፡፡ ከ1997 ዓ/ም በኋላ የወያኔ መንግስት የአካሄድ ለውጥ አድርጓል፡፡ በተቃዋሚዎች የደረሰበትን ሽንፈት ለመቀልበስ ሲል በሃሰት ማስረጃ እጃቸው የሌለበትን ሁሉ መክሰስ ጀመረ፡፡ በተለይ እንደስጋት በሚያያት ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረገው ሁሉ የሚያስገርም ነበር፡፡ አሁን ወያኔ የሃይማኖት ተቋማትን የሚይዝበት መንገድ ተቀይሯል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ያሉ አመራሮችን በመያዝ ተወስኖ የነበረው ወያኔ ከምርጫው በኋላ እስከ ታችኛው የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ድረስ ዘልቆ በመግባት ቤተ ክርስቲያንን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ለመምራት ፈለገ፡፡ ፈልጎም አልቀረ ተግባራዊ ርምጃ መውሰድ ከጀመረ ወሎ አድሯል፡፡ አስቀድሞ ሲመሠረት ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት አልሞ የተነሳው ወያኔ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቤተ ክርስቲያንን ስም ማጥፋት፣ ያላደረገችውን አድርጋለች ማለት፣ ምዕመናን የሚፈጽሟቸውን የአምልኮ ሥርዓት ማንቋሸሽና ኋላቀር አድርጎ ማሳየት የእለት ከዕለት ተግባሩ ነው፡፡ አሉ የሚባሉና ዓለማቀፋዊ ዕውቅና ያላቸውን ቅርሶቿን ጥቁር ቀለም ለመቀባት ብዙ ርምጃ ተጉዟል፡፡ በቅብብሎሽ የሚያዙ የሚኒስተርነት ቦታዎችም ከላይ ያነሳናቸውን ነገሮች መሠረት አድርገው የሚሠሩ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ የቤተ ክርስቲያን አስተዋጽዖ ከሁሉም በላይ መሆኑ ጥያቄ የለውም፡፡ ነገር ግን ለብዙ ዓመታት ይህንን ዘርፍ የመምራቱ ኃላፊነት ከእስልምና እንዳይወጣ የሚል በሕገ መንግስቱ የተቀመጠ ይመስል በቅብብሎሽ ለእስልምና እምነት ተከታዮች ብቻ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ስልጣን መያዝ የለባቸውም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ነገር ግን ለሁሉም አግባብ አለው፡፡ ለሃገሪቱ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ አስተዋጽዖ ሊያደርጉ የሚችሉ ብርቅና ድንቅ ቅርሶችን ትቶ ምንም ትኩረት ሊስቡ የማይችሉና ለቱሪዝሙ ዘርፍ ሚዛን የሚደፋ ፋይዳ የሌላቸውን ቁሳቁሶች በዓለም ዓቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚደረገውን ሩጫ ስናየው ሆን ተብሎ የሚሠራ ሥራ እንዳለ ለመገንዘብ እንችላለን፡፡ አሊ አብዶ በአዲስ አበባ ሲፈጽመው የነበረውን ጉዳይ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ያውቀዋል፡፡ የወያኔ መንግስት አሊ አብዶ የሚፈልገውን ስላደረገለት ለበለጠ ስልጣን አበቃው፡፡ የመስጊድ ሰልፍ ልበለው፤ በከተማዋ ውስጥ ስለደረደረ አምባሳደርነትን አገኘ፡፡ ችግር ያለበት ሰው ለስልጣን ከታጨ ሌላው ምን መልካም ነገር ሊሠራ ይችላል? በጠቅላይ ቤተ ክህነት ነግሳ የነበረችውን ኤልዛቤልን (እጅጋሁ በየነ ትባላለች፤ በምግባሯ የተነሳ ግን ኤልዛቤል ተብላለች) የማያውቃት አለ ብየ ለመናገር ይከብደኛል፡፡ እጅጋየሁ ከመንግስት ተላላኪዎች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክህነት አባቶችን በመሳሪያና ደህንነት በምትላቸው ሰዎች ማስፈራራት የዕለት ከዕለት ተግባሯ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ የሌለች አንድ ሴተኛ አዳሪ ከፓትርያርክ ጳውሎስ ጋር የነበራትን የጠነከረ ግንኙነት መነሻ በአግባቡ ለመዘርዘር ቢከብደኝም ቅጥ ያጣ ነበር ብየ ለመናገር ግን እደፍራለሁ፡፡ ሥርዓት አልባ አለባበስ ከምታዘወትር ልጇ ጋር በየጊዜው በፓትርያርኩ ቤት የምትቀማጠለው እጅጋየሁ ፓትርያርኩ ለሊቃነ ጳጳሳት ከሚሰጡት ክብር በላይ ሲሰጧትና አድራጊና ፈጣሪ እንድትሆን ሲፈቅዱላት እንታዘብ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያን ሃብትና ንብረት ላይ እስከማዘዝ ደረሰች (የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ እያከራየች ወደ ኪሷ የምታስገባ ወንበዴ!)፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ በደረሰ ቁጥር ለብዙዎቻችን የኤልዛቤል ጫና ምን እንደነበርና አባቶችም በሰላም መዋላቸውን መከታተል የብዙ ሰዎች ተግባር ነበር፡፡ እጅጋየሁ በማናለብኝነት በግቢው ውስጥ እየተንጎራደደች የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎች ለማስቀየር ከግብረ አበሮቿ የጠቅላይ ቤተ ክህነት አክዓቦች ጋርና ከወያኔ ተላላኪ ደህንነቶች ጋር ብዙ ደባ ስትፈጽም ነበር፡፡ ፓትርያርኩም እንደ አማካሪ ሳይሆን የበላይ አለቃ አድርገው ስላስቀመጧት እርሷ ከምትለው መስመር ውጪ አይንቀሳቀሱም ነበር፡፡ ሽጉጥ እያወጣች ሰዎችን በማስፈራራት የምትታወቀው ኤልዛቤል ሃይ ባይ አጣች፡፡ በመጨረሻ የፓትርያርክ ጳውሎስን መልካም ያልሆኑ ተግባራት (ሙስናና የቤተሰብ አስተዳደር፣ የበጋሻውና ኤልዛቤል የሃውልት ግንባታ አስመልክቶ፣ የሥርዓተ ቤተ ክርሰቲያን ጥሰትን በተመለከተ፣ የመናፍቃንና አጽራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴን ለመግታት ፓትረያርኩ የነበራቸውን ተቃውሞ አስመልክቶ፣ ወዘተ) የተቃወሙ ሊቃነ ጳጳሳትን ማዋከብ ብሎም እስከ ማስደብደብ ደረሰች፡፡ ቤታቸው ተሰባበረ፣ በሌሊት በመንግስት ተላላኪ ደኅንነት ነን ባዮች ከቤታቸው ታፍነው ተወሰዱ፣ በየቀኑም በስልክና በአካል ማስጠንቀቂያዎች ይሰጣቸው ጀመረ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አባቶች በትዕግሰት እየተመለከቱ ሁኔታውን ለወያኔ መንግስት አቅርበው መፍትሄ ይገኛል ብለው ይጠብቁ ነበር፡፡ የመንግስት ቀኝ እጅ የነበሩት አባ ጳውሎስም የጠነሰሱትን ሴራ ያውቃሉና መልሳቸው ዝምታ ሆነ፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱን በአግባቡ አትሠሩም፣ ቤተ ክርስቲያኗን በአንድ ሰው ስህተት ችግር ላይ ጣላችኋት ወዘተ እያለ ሲወተውታቸው የነበረው ሁሉ በአባቶች ላይ መከራ ሲወርድባችው የደረሰላቸው አልነበረም፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት መከራውን ሁሉ ብቻቸውን ቻሉት፡፡ የታዘዙት የመንግስት ተላላኪዎችም የሚፈልጉትን አደረጉ፡፡- በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወያኔ አባቶቻችንን ደበደበ፤ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ተዋሕዶን ደፈራት! የሞተው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በሚሊኒየም ስም ከየአካባቢው የጠራውን ወጣት ሲያነጋግር “የራሳቸውን የፖለቲካ ዓላማ ለማራመድ የሚሞክሩ ቄሶችና ሼኮች” በማለት ካህናትን ከአክራሪ እስላም መሪዎች ጋር በመደመር በጅምላ ከነፍሰ ገዳይ ጋር ፈርጇቸዋል፡፡ ሚያዚያ 9/2004 ዓ/ም በፓርላማ ባደረገው ንግግር ጥምቀት ላይ ከነበሩት መፈክሮች አንዱ “አንድ አገር – አንድ ሃይማኖት” የሚል ነበር በማለት የቤተ ክርሰቲያንን ልጆች ሲከሳቸው ሰምተናል፡፡ ከዚህ በመነሳት የደረሰበት ድምዳሜ ደግሞ “…የክርስቲያን መንግስት እንዲኖር የሚፈልጉ እንዳሉ ያሳየናል፡፡” የሚል ነበር፡፡ ምንም እንኳን ሰውየው ከየት አምጥቶ እንደተናገረው ባይታወቅም ወጣቶቹ በጥምቀት በዓል “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅስ እንጂ “አንድ ሃገር” የሚል ጽሁፍ በቲ-ሸርቶቻቸው ጽፈው አይተን አናውቅም፡፡ በወጣቶቹ ልችሶች ላይ የተጻፈው የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል እንጂ ሟች እንደተናገረው መፈክር አይደለም፡፡ ደናቁርት መረጃ አቀባዮቹ ማየትና መስማት የተሳናቸው ሆነው አንዲት ጥምቀት የሚለውን “አንድ ሃገር” ብለው ለመተርጎም ፈልገው ካልሆነ በስተቀር እነርሱ የሚሉትን ሃሳብ ያራገበ ወጣት አልነበረም፤ ለወደፊትም ይኖራል ሚል እምነት የለኝም፡፡ የሟችን ፈለግ በመከተል የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ደግሞ የሰላም ጉባዔ በሚል በአዲስ አበባ በተጠራው ስብሰባ ባቀረበው ጥናት መሰል ዘገባ “በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል አቋራጭ የፖሊቲካ መሣርያ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ አካላት ይታያሉ” በማለት ማንም ያላሰበውን በሬ ወለደ በሚል መልኩ አቅርቦታል፡፡ ሰውየው በዓላማ ለራሱ ፕሮቴስታንት እምነት ዕቅድ ስኬት መንገድ ጠራጊ በመሆን ተግቶ የሚሠራ ስለሆነ በተናገረው ንግግር ለመፍረድ ይከብደኛል፡፡ ሰውየው ለወያኔም ለፕሮቴስታንትም ተቀጣሪ ነው፣ ምንም ተቃውሞ ቢመጣ ችግር እንደማይደርስበት
 17. Astreaye Yohanes October 24, 2013 at 1:00 pm Reply
  የሟችን ፈለግ በመከተል የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ደግሞ የሰላም ጉባዔ በሚል በአዲስ አበባ በተጠራው ስብሰባ ባቀረበው ጥናት መሰል ዘገባ “በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል አቋራጭ የፖሊቲካ መሣርያ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ አካላት ይታያሉ” በማለት ማንም ያላሰበውን በሬ ወለደ በሚል መልኩ አቅርቦታል፡፡ ሰውየው በዓላማ ለራሱ ፕሮቴስታንት እምነት ዕቅድ ስኬት መንገድ ጠራጊ በመሆን ተግቶ የሚሠራ ስለሆነ በተናገረው ንግግር ለመፍረድ ይከብደኛል፡፡ ሰውየው ለወያኔም ለፕሮቴስታንትም ተቀጣሪ ነው፣ ምንም ተቃውሞ ቢመጣ ችግር እንደማይደርስበት ስለሚያውቅ፣ ምናልባትም ይህንን በማድረጉ እንደ አሊ አብዶ ለበለጠ ስልጣን ሊታጭ እንደሚችል ስለሚያውቅ ቤተ ክርስቲያንን ማደከም ተግባሩን ለወደፊቱ በተጠናከረ መንገድ ሊቀጥልበት ይችላል፡፡ ከባለስልጣኖች ንግግር መረዳት የሚቻለው ሌሎችን ለማሳመን የግድ በሃሰት ቤተ ክርስቲያንን መክሰስና የቀደመ ዓላማቸውን ለማስፈጸም በየትኛውም አጋጣሚ እንቅስቃሴው የማይቋረጥ መሆኑን ነው፡፡ አቶ (ዛሬ አምባሳደር) አሊ አብዶ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በነበረበት ጊዜ ከስልጣን እሲኪወርድ ድረስ 98 የሚያህሉ መስጊዶች አዲስ አበባ ውስጥ እንዲሠሩ ማድረጉን ሁሉም ያውቀዋል፡፡ ዛሬም በየከተማው የሚታየው የህገ ወጥ መስጊድ ግንባታ በሁሉም ክልሎች እየቀጠለ ነው፡፡ ቱባ ባለስልጣናቱም ይህንን በመደገፍ ይታወቃሉ፡፡ የቤኒሻንጉሉ ያረጋል አይሸሽምና አሊ አብዶ በህገ ወጥ የእምነት ቦታ ግንባታ ይታወቃሉ፡፡ አቶ ጁነዲን ሳዶ ደግሞ አይን ባወጣ መልኩ የአሸባሪው ቀኝ እጅ ሆኖ ተገኘ፡፡ መስከረም 30 ቀን 2001 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ሲሆን መሐል አራዳ በሚገኘው በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድ ሙስሊም ‹‹አላህ ዋክበር፣ ሥዕል ይውረድ፣ መስጊድ ይሠራ አላህ ዋክበር›› እያለ ድመጹን እያስተጋባ ጮኸ፡፡ ምዕመናን በሆነው ነገር ተደናግጠው በጥበቃ ሰራተኞች ከቤተ መቅደስ አስወጡት ለፖሊስም አስረከቡ፡፡ ፖሊሶች ከያዙት በኋላም በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ በተደጋጋሚ ‹‹አላህ ዋክበር›› በማለት ይጮህ ነበር፡፡ ምዕመናን በራሳቸው ርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ለሃይማኖታቸው ታማኝ ስለሆኑ፣ ለሕግም ስለሚገዙ ለሚመለከተው አካል አስረከቡ እንጂ ሌላው እንደሚያስበው አላደረጉም፡፡ ይሄ መቻቻል ሳይሆን መቻል ወይም መሸከም ተብሎ ሊጠራ ይችላል እንጂ ይህንን ሕዝብ፣ በወቅቱ የነበረውን ታጋሽ ወጣት አሸባሪ ማለት ይቻላልን? ጥር 11 እና 12/ 2001 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓል የሚያከብሩ አባቶችና ምዕመናን ታቦታትን አጅበው ወደ ባሕረ ጥምቀት ሲሄዱ የእስልምና እምነት ተከታዮች የጫት ገሪባ እየበተኑ ምዕመናንን ወዳልሆነ ስሜት ውስጥ ከማስገባታቸውም በላይ ጉዳዩን ለማርገብ የተንቀሳቀሱ ፖሊሶችንም በጥይት ሩምታ ለመምታት ችለዋል፡፡ በከተማው ሙስሊሞች የሚያቀርቡትን ጥያቄ ተቀብሎ ዲሚክራሲያዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ መልስ ከመስጠት ይልቅ በቢሮው ከጸሐፊ ጋር፣ አንዲሁም ከስራ ባለደረቦቹ ጋር በሚያደርገው ግጭት የሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን “ቤተ ክርስቲያን ጨቁናችኋለች” በማለት ግጭቱ የተባባሰ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ ምንም እንኳን በአካባቢው የክርስቲያኑ ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ብዛት ስላለን ርምጃ እንውሰድ በሚል እንቅስቃሴ አላደረገም፡፡ በጎንደር ከተማ አክራሪ ሙስሊሙ ራሱን አሸባሪነት ስልጠና የሚወስድበት ቦታ አዘጋጅቶና ለዚሁም የሚረዱ ጦር መሳሪያዎችን አከማችቶ በሚመለከታቸው አካላት ቁጥጥር ሥር ሲውሉ ሕዝበ ክርስቲያኑ ድርጊቱን ሰምቶ ሁኔታውን በቅርብ ርቀት ከመከታተል ባለፈ እኔም በዚህ መልኩ መዘጋጀት ይገባኛል በሚል ወዳልሆነ ጽንፍ አልገባም፡፡ በዚሁ ዓመት በአዳዲ ማርያም ዓመታዊ ክብረ ባዓል ላይ አንድ ተልዕኮ የተሰጠው ሙስሊም ታቦታትን አጅበው ምዕመናን በሚሄዱበት መንገድ ልብሱን አንጥፎ እሰግዳለሁ በሚል ሰበብ ‹‹አላህ ዋክበር›› በማለት በዓሉን ለማስተጓጎል ጥረት ሲያደርግ ተይዞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በአጠቃላይ በ2001 ዓ/ም ከመስከረም 30 ቀን 2001 ዓ.ም እስከ ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብቻ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ከ24 የሚበልጡ ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደደረሱባት ለሚመለከታቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት አሳውቃለች፡፡ እንደሚታቀው በ1999 ዓ/ም በጅማ አካባቢ አክራሪ ሙስሊሞች አብያተ ክርስትያናትን አቃጥለዋል፣ ምዕመናንን በግፍ አርደዋል፣ ቤቶቻቸውን አቃጥለዋል፡፡ ምንም እንኳን የወያኔ እጅ እንዳለበት ቢታወቅም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁኔታውን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ከማሳወቅ ባለፈ የጉልበት ርምጃ ውስጥ መግባት አልፈለገም፡፡- ሕግ ባለበት ሃገር በዚህ መልኩ መንቀሳቀስ ለሃገር ልማት እንደማይበጅ ያውቃልና! ከዚህም በላይ በተለያዩ የሙስሊም ፀሐፍያን ቤተ ክርስቲያንን የሚያንቋሽሹ ከአንድ መቶ በላይ መጻሐፍት፣ ብዛት ያላቸው ሲዲዎችና ቪሲዲዎች ተዘጋጅተው በየክፍለ ሃገሩ በግላጭ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሲያውኩና በየሱቆቻቸው ሲሠራጩ ምዕመናን ተደፈርን በማለት ሌላ ጽንፍ ውስጥ አልገቡም፡፡ እውነታውን ለማሳየትና ምዕመናንን ለማጽናት ቁጥራቸው ከሰባት ያልበለጡ መጽሃፍትን በማስረጃ አስደግፎ በማሳተም የተወሰኑ የቤተክርስቲያን አካላት ሙከራ አድርገዋል፡፡ በተለይ ወጣቱ በዚህና በመሰለው የሃሰት ትምህርት እንዳይወሰድ እንዲሁም ለሃይማኖቱ ዘብ እንዲቆም ማኅበራትና ሰንበት ት/ቤቶች የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣት ሰፊ ነው ባይባልም የበኩላቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ ወጣቱ በተለይ በበዓላት ወቅት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እግዚአብሔርን ሲያከብር ታይቷል፡፡ በ2003 ዓ/ም በኢሉአባቦራ አክራሪ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ሲያግቱ፣ የመኖሪያ ቤታቸውን ከብቦ ሲያስጨንቃቸውና የድብደባ ወንጀል ሲፈጽምባቸው፣ የቡና እና ሌሎች ቋሚ ተክሎቻቸውን በሌሊት ሲመንጥርባቸው፣ ከብቶቻቸውን እየወሰዱ አርደው ሲበሉባቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁኔታውን ለሕግ አካላት ከማሳወቅ ባለፈ የጉልበት አጸፋ ርምጃ ውስጥ አልገባም፡፡ ሌሎችም በየክፍለ ሃገሩ የተከሰቱ ብዙ ትንኮሳዎችን ሕዝበ ክርሰቲያኑ የመቻቻልና መገነዛዘብ አስተማሪ ነውና በትዕግስ አሳልፎ በሰላም በሚኖርበት ወቅት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥር 13 ቀን 2001 ዓ.ም “አንዱ በሌላው የእምነት ሥፍራዎች ወደ መስጊድና ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባት ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን መፈፀም” በሚል መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ኦርቶዶክስና እስልምና በማለት አጫፍሮ በመገናኛ ብዙኃን ያስተላለፈው መግለጫ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን ያሳዘነ ስለነበር ቅዱሰ ሲኖዶስ ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም ያለውን ተቃውሞ ለሚመለከታቸው ሁሉ በጽሁፍ አሳውቋል፡፡ በትዕግስት የሚኖረውን ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን በአሸባሪነት እየተንቀሳቀሰ ሰውን ደም ከሚያፈስና ነፍጥ ከታጠቀ ኃይል ጋር በማመሳሰል መፈረጅ ከአንድ ሀገር እመራለሁ ከሚል አካል የሚጠበቅ አለመሆኑን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ማሳወቃቸው ይበል የሚያሰኝና የሚበረታታ አካሄድ ነው፡፡ ሙሉ መግለጫው የሚከተለውን በሚቀጥለው ገጽ ይመልከቱ፡፡ በጥምቀት በዓል ወቅት “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚል ጽሁፍ በቲ-ሸርቶቻቸው በመታየቱ ሃሳቡ ተገልብጦ አንድ ሃገር አንድ ሃይማኖት የሚል ጽሁፍ ያለበትን ልብስ ማን አዘጋጀው ፣ “ወጣቶቹን ቲ-ሸርት ያለበሱትን አጋልጡ” በማለት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፣ የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር፣ የመንግሥት ኮሚውኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዲኤታና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተገኝተው ሊቃነ ጳጳሳትን ሲያዋክቡ እንደነበር በተለያ ሚዲያዎች የተዘገበና በቅርብ ያለን ሰዎች የምናውቀው ሃቅ ነው፡፡ አስቀድሞ ሲመሠረት ጀምሮ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማዳከም ዓላማው አድርጎ ተነስቷልና ወያኔ አሁንም አጋጣሚወዎችን በመጠቀም ተግባሩን በተጠናና በተጠናከረ መንገድ እየሄደበት ነው፡፡ የወያኔ መንግስት ሃገሪቱን በአሸባሪዎች ለማስወረር የዐረብ ኢንቨስተሮችን በገፍ ወደ ሃገራችን በማስገባት፣ የአረብ ሊግ በአዲስ አበባ ከተማ ቋሚ ጽሕፈት ቤት ለማቋቋም የሚያስችለውን ስምምነት በመፈራረም፣ ሕገወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ የነበሩ አሸባሪ የመንግስት ባለስልጣናትን ወደ በለጠ ስልጣን ደረጃ በማሸጋገር ወይም ደልቷቸው እንዲኖሩ ከሃገር የሚወጡበትን መንገድና ሌሎች ሁኔታዎች በማመቻቸት ዓላማቸውን የበለጠ እንዲያሳኩ፣ በተቃራኒው ደግሞ የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ በማንቋሸሽ እንዲሁም የእርሷ ያልሆነውን በማስመስል ጥላሸት እየቀቡ ወንጀለኛ እንደሆነች በማስወራት የደርግ መንግስት እንኳን ያልፈጸመውን አስከፊና አስቀያሚ ተግባር እያከናወነ ይገኛል፡፡ እነ ዶ/ር ሽፈራው “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት የሚታየው በተለያዩ የማኅበራት አደረጃጀት ውስጥ ራሳቸውን ደብቀው በሚሠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ነው፡፡ በእነዚህ ማኅበራት ውስጥ የመሸጉ አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች በሚያሰራጯቸው የተለያዩ የኅትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የድረ ገጽ ውጤቶች በተከታታይ ሃይማኖትን ከሃይማኖት፣ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሕዝብንና መንግሥትን የሚያጋጩ ዘገባዎችን በማስተጋባት የኢፌዴሪ መንግሥት የኦርቶዶክስ ክርስትናን ያሳነሰና ተገቢውን ክብርና ጥቅም የነፈጋት አድርገው ለምእመናን ያቀርባሉ” በማለት በተደጋጋሚ ክስ ሲያቀርብና ሲዘልፍ ይሰማል፡፡ የትኞቹ ሚዲያዎች ናቸው ህዝብን ከህዝብ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ጋር የሚያጋጭ ዘገባ ያሰራጩት፣ ዘገባውንስ በትክክል ሊያሳዩን ይችላሉ? በሚገርም ሁኔታ አንድም ቀን የተላለፈው መልዕክት ይሄ ነው፣ ስህተቱም ይህንን ይመስላል ብለው ተናግረው አያውቁም፡፡ እርግጥ ነው የተለያዩ ብሎጎች የህዝቡን ብሶት እያወጡ ያስተጋባሉ፡፡ ሕዝቡን የሚያዳምጥ መሪ በሌለበት ሃገር፣ ፍትህ በሌለባት ሃገር፣ አፈና በሚበዛባት ሃገር፣ ሃይማኖትን በሚያንቋሽሽና ይህንንም ዓላማው አድርጎ በተነሳ (ወያኔ) መንግስት በምትመራ ሀገር፣ የሀገርን ታሪክ ጥላሸት በሚቀባ መንግስት በምትመራ ሃገር፣ ወዘተ ነጻ ሃሳብን ሚገልጹ ሚዲያዎችን መጠቀም ወንጀሉ ምንድን ነው? የወያኔ መንግስት በዚህ መንገድ የሚከስሳቸው ሚዲያዎች በአብዛኛው ማለት ይቻላል ለሃይማኖት ዘብ የሚቆሙ፣ የተሳሰተውን አካል የሚገስጹ እንዲሁም ለሃገር ልማትና ዕድገት ሚጠቅሙ ሃሳቦችን የሚሰነዝሩ ናቸው (በቻይና ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረተው የወያኔ ኢንፎርሜሽን መረብ ኤጀንሲ ሰለባዎች እየሆኑ ብዙዎች ዳብዛቸው ቢጠፋም)፡፡ ስማቸውን ለመጥስ ያክል ደጀ ሰላም (Deje Selam), አንዳድርገን (Andadirgen.org)፣ ቤተ ደጀኔ፣ አደባባይ፣ የኤፍሬም እሸቴ ጦማር፣ የመላኩ ዕዘዘው ብሎግ፣ የዳንኤል ዕይታዎች፣ አቤላዊነት፣ ገብርሔር ወዘተ ይገኙበታል፡፡ እነዚህን የጡመራ መድረኮች (አብዛኛዎችን) ማን እንደሚያዘጋጃቸው የማውቀው ነገር ባይኖርም የሚያስተላልፉት መልዕክት የአሸባሪነት መንፈስ እንደሌለው መመስከር ግን እችላለሁ፡፡ አልፎ አልፎ አከራካሪ የሆነ ሃሳብ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ግን ማሸበር አይደለም፤ ሃሳብን ለሃሳብ በማጋጨት ወደ በለጠ ውይይት ለማምራት በር መክፈት ነው እንጂ ህዝብን ከሕዝብ እንዲሁም ሕዝብን ከመንግስት ጋር ማጋጨት አይደለም፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸውም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲሉ የሚጽፉ አካላት በቤተ ክሰቲያን እውቅና ተሰጥቷቸው የሚንቀሳቀሱ አይደሉም፡፡ ስለዚህ ጥፋት ቢኖርባቸውም እንኳን ተጠያቂዎች የሚያዘጋጇቸው ግለሰቦች አንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወይም የመሠረተቻቸው ማኅበራት ሊሆኑ አይገባም፡፡ ምናልባት ይሄ ሁሉ ዙርያ ጥምጥም ወያኔ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ ካለው ሕልም የመነጨ ሳይሆን አይቀርም የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለማስረጃም ያህል በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ነፍስ የሌላቸውን ካድሬዎች በማደራጀት ብዙ ሲያደርግ ነበር አሁንም በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አባሎቹን እነ “አባ” ሰረቀ ብርሃንንና ነፍሳቸውን ይማርና አባ ጳውሎስን ተጠቅሞ ማኅበሩን ለማፍረስ ያደረገው ሙከራ በእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሳካለትም የሠራና እየሰራው ያለ ደባ ቀላል ሚባል አይደለም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሃገራዊ አጀንዳ ሁኖ በአሸባሪነት መፈረጁን በተደጋጋሚ በመድረኮች ስሰማና በወያኔ ጽሁፎች ላይ ሰፍሮ ስመለከት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ “ቤተ ክርስቲያንን ፍሬ አልባ ማድረግ ወይም ማቀዝቀዝ” እና “ሙስሊሞችን ማንቀሳቀስ ወይም ማነሳሳት” (neutralizing the Church and Mobilizing Muslims) ብሎ የተገለጠውን የወያኔን መነሻ ያስታውሰኛል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ባወቀ የመሠረተው ማኅበር በመሆኑ ለዚህች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቀላል የማይባሉ ተግባራትን ፈጽሟል፡፡ ሰዎች የሚኖሩበት በመሆኑ ደካማ ጎን አይኖረውም ለማለት ግን አልችልም፡፡ የአባላት ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ አባላትን የማስተዳደሩ ሥራ በራሱ አገልግሎትን የሚፈትንና በዚህም የተነሳ ሃሳብ ልዩነት ሊፈጠር እንደሚችል በተለያዩ ጥናቶች የሚታወቅና ከልምድ የምናውቀው ነው፡፡ ነገር ግን ልዩነቱ በአንድ ምህዋር ዙሪያ ነው፡፡- ቤተ ክርስቲያንን ከማገልገል አኳያ፡፡ ከዚህ ባለፈ በሌላ ምሕዋር ውስጥ ገብቶ የማኅበሩ አባል ነኝ የሚል ቢኖር ለራሱም ለቤተ ክርስቲያንም የሚበጅ አይደለም፡፡ የፖለቲካ ዓላማውን በማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት መስመር ውስጥ ለማስፈጸም የሚፈልግ ቢኖር መድረኩም አይመቸውም በሃገሪቱ ሕግ መሠረትም ወንጀል ነው፡፡ ወያኔ በተደጋጋሚ የሚያቀርበው “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የፖለቲካ አጀንቸውን በሃይማኖት ስም የሚያራምዱ ናቸው” በማለት በራሱ ቁጥጥር ስር ባሉ ሚዲያዎች ሲናገር ይደመጣል፡፡ በሕዝብ መድረኮችም ያስተጋባዋል፡፡ በአክራሪ እስልምና መስመር የተሰማሩት አክራሪዎች የሰው ደም ሲያፈሱ፣ አብያተክርስቲያናትን ሲያቃጥሉ፣ ክርስቲያኖችን ሲያሳድዱ እንዲሁም ከውጭ አሸባሪዎች ጋር ሲተባበሩ አልፎም ተርፎም በግልጥ የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፈጸም ሲጥሩ ተመልክተናል፡፡ ለመሆኑ በማኅረ ቅዱሳን ውስጥ ያሉ አሸባሪዎች ማንን ገደሉ፣ የትኛውን ቤተእምነት አቃጠሉ? ለምን ተደበቀ? ወያኔ መረጃ አለኝ እያለ ነበር፤ መረጃና ማስረጃ የተለያዩ ቢሆኑም ማስረጃውን አውጥቶ ለምን ርምጃ አይወስድም? የተቀነባበረ የሃሰት ማስረጃ ካላቀረበ በስተቀር የዚህ ዓይነት ዓላማ ያለው ኦርቶዶክሳዊ አለ ብየ አላምንም፡፡ ካለ ግን ርምጃ ቢወሰድበት ቤተ ክርስቲያን ርምጃውን የምትደግፍ ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን የምኅረት አደባባይ ብትሆንም በሃገር ሕግ መመራት አለባትና ይህንን መሰል ርምጃ ተቃውማ አትቀርብም፡፡ አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣናትን ማግኘት እድሉ ገጥሞኝ ለማወየያት ሞክሬአለሁ፡፡ አንዳንዶቹ የሚናገሩትንም አያውቁትም ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡ በውይይታችን ቤተ ክርስቲያንን በተለይም ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳንን የፈረጁበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን ይስማማሉ፡፡ ነገር ግን ወደ መድረክ ሲወጡ አንበሳነታቸው የሚታወቀው የማኅበረ የቅዱሳንን ስም በማጥፋት እንደሆነ አላውቅም ወይም የስልጣናቸው መንበር የሚጸናው በዚህ መልኩ ሲሆን ብቻ እንደሆነም አላውቅም “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት…..” በማለት የንግግራቸው “ማሳመሪያ/ማጣፈጫ” ሲያደርጉት እናደምጣለን፡፡ እርግጥ እነዚህ ሰዎች የሚናገሩት የሚያምኑበትን ነው ወይንስ የሚታዘዙትን ብቻ ነው የሚል ጥያቄ ብንጠይቅ መልሱን አንባቢ የሚፈርደው ይሆናል፡፡ ወያኔ በተለያየ ጊዜ የሚሾማቸው ባለስልጣናቱ ሌቦችና የማይታመኑ ብሎም በአሸባሪነቱ ጎራ የሚሰለፉ ናቸው፡፡ ለሃገር ባህልና ትዉፊት ደንታ የሌላቸው፣ የወገናቸውን መሬት አሳልፈው የሚሸጡ፣ እነርሱ ብቻ ትክክለኛ የሆኑ የሚመስላቸው፣ ሃገር ከሃዲዎችና ወገናቸውን አሳልፈው የሚሸጡ ናቸው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎችን በሥነ ምግባር የታነጹ፣ ሀገርንና ወገንን የሚጠቅሙ፣ ታሪካቸውን የሚጠብቁ፣ ለራሳቸውም ሆነ ለመንግስት እንዲሁም ለህዝብ ታማኝና በትህትና የሚያገለግሉ እንዲሆኑ ለማድረግ ላለፉት 20 ዓመታት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ምንም እንኳን ያስተማራቸው ሁሉ በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ ናቸው ባይባልም ከገጠር እሰከ ከተማ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ሰብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ረገድ፣ በሙያቸው በአስፈላጊው ሁሉ ከማገዝ አኳያ ቀላል የማይባል ተሳትፎ አላቸው፡፡ በተለይ መናፍቃን (ወያኔ ፈጽሞ የማይወደው ቃል ነው) ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ከንቱ ሩጫ ለመግታት ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል፤ አሁንም በመጫወት ላይ ናቸው፡፡ ይሄ ደግሞ የእስልምናን የበላይነት ለማረጋገጥ ለተነሳ ወያኔ ሊዋጥለት አልቻለም፡፡ ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቅ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ቢሆንም እንደ ቤተ ክህነት አካሄድና እንደ ምዕመናን መዘናጋት የማኅበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት አይከብድም፡፡ የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የገጠማት አስቸጋሪና ጠባሳው የማይጠፋ ፈተና በእኛ ቤተ ክርስቲያን እንዳይደርስ ብቸኛ ባይሆንም ሰፊው ድርሻ የማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን በልበ ሙሉነት መመስከር እችላለሁ፡፡ የብዙዎቻችንን ሕይወት የታደገ ማኅበር ነው፡፡ ልጆቻችን በዘመናውያን የእምነት ተቋሞች ተጠልፈው እንዳይወድቁ ያደረገውን አስተዋጽዖ እኔና ልጆቼ ብቻ የምናውቀው ነው፡፡ በሰበካ ጉባኤያት ባለኝ ሱታፌ ልጆቻቸው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በሥነ ምግባር ታንጸው ለቤተሰብ ተስፋና መካሪ የሆኑ ምዕመናን ምስክርነት ለማህበሩ መንፈሳዊ ተግባር ዋናው ማስረጃ ነው፡፡ ከ1997 ዓ/ም ምርጫ በኋላ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ የተወያየው ወያኔ ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ድርሻ የነበረው አካል ነው ብሎ የፈረጀው ማኅበረ ቅዱሳንን ነው፡፡ ከዚህ ጀምሮ የማኅበሩ አባላት “የቅንጅት” ደጋፊዎች ናችሁ እየተባሉ ወከባ ደረሰባቸው፡፡ በቤተ ክህነት የስልጣን እርከኖች የፈለገውን የመሾምና የመሻር ተግባሩን በማኅበረ ቅዱሳንም ተግባራዊ ለማድረግ ወያኔ ብዙ ሞክሮ ነበር፡፡ የሃሰት አባል በመሆን በማኅበሩ እየተመዘገቡ በስለላ ተግባር ላይ የተሰማሩት የወያኔ መንግስት ተላላኪዎችም (ሰላዮች እንበላቸው? ድንቄም ስለላ!) ያልተባለውን ተባለ በማለት በሬ ወለደ ዓይነት ዲስኩራቸውን ቀጠሉበት፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ መልኩ ለስለላ የተላኩ ነገር ግን በማኅበሩ አገልግሎት ተማርከው አሁንም በማገልገል ላይ ያሉ አባላት ቁጥራቸው ትንሽ የሚባል አይደለም፡፡ ምን ይሄ ብቻ በ2000 እና 2001 ዓ/ም አካባቢ የማህበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ጽ/ቤት ተሰማርተው ሲያዋክቡ ከነበሩት የወያኔ ተላላኪዎች መካከል በማኅበሩ ውስጥ የተባለውን ችግር ባለማግኘታቸው የስለላው ዓለም በቃን በማለት የቢሮ ቁልፍ አስረክበው (የስም ማጥፋት ስለላ ተግባርን ርማችን ነው ብለው የተውት) የወጡትን ስንመለከት ደግሞ ሁሉንም በጅምላ መፈረጅ እንደሌለብን ተገንዝቤያለሁ፡፡ ለወያኔ አንድ ነገር ማለት አፈልጋለሁ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረቱ በራሱ ለፖለቲካ የተመቸ ካለመሆኑም በተጨማሪ ከዓላማው ጋር ስለሚጋጭ ይህንን አያደርገውም፡፡- ምናልባት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ የሚታየውን ሁለት ገጽታ የተላበሰ አካሄድ በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ አናገኛለን ብላችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል፡፡ በየዕለቱ ስልካቸውን እየጠለፈ የሚያደምጣቸው የማኅበሩ ከፍተኛ አመራሮች ምናልባት የሚናገሩት መንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ ፖለቲካ አለመሆኑን ስልኩን ጠልፈው የሚያደምጡት ሁሉ ያውቁታል፡፡ መቼም የሰሙትን ገልብጠው መተርጎም ሥራቸውና በዚህ መልኩ ካላቀረቡት በስተቀር፡፡ ከሥነ ምግባር በወጣ መንገድ ቤተሰባዊ ነገራቸውን ሁሉ ሪከርድ እያደረጉ የማኅበሩን አመራሮች የሚከታተሏቸው የወያኔ ተላላኪዎች በየጊዜው የማኅበሩን መቀበሪያ ጉድጓድ ቢቆፍሩም እየገቡበት ያሉት እነማን እንደሆኑና እንደሚሆኑ ያየነውና የምናየው ይሆናል፡፡ ወያኔ የዋልድባን ገዳም በድፍረት ለስኳር ልማት ፕሮጀክት ተግባር መሬቱን ቆርሶ ሲወስድ ትልቅ ተቃዎሞ ገጥሞት እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የልማት ተቃዋሚ ባትሆንም በሚካሄዱት የሃገር ልማት ሥራዎች ውስጥ አንድ ባለድርሻ አካል በመሆኗ (ለዚያውም በራሷ መሬት ላይ ሲካሄድ) ሃሳቡን አውቃና መክራበት መሆን ይገባው ነበር፡፡ ወያኔ በአባይ ጸሃዬ ማን አለብኘነት በድፍረት ግንባታውን ጀመረ፣ የዋልድባን መሬትም አረሰው፡፡ በወቅቱ ለመነኮሳት የተሰጠው ምላሽ ደግሞ አይን ያፈጠጠና ክህደት የተሞላበት ነበር፡፡ ችግሩን በአይናችን እያየነው አላደረግንም ብለው ካዱ፡፡ የመነኮሳቱን ስም በማጥፋት ገዳማውያንን ለማዋከብ መሳሪያ በታጠቁ ወታደሮች ገዳሙ ተወረረ፡፡ በአቶ መለስ ዜናዊ ሕመም የፀለምትና ማይ ፀብሪ ፖሊሶች መነኰሳቱን ‹‹እናንተ ምትሃተኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችሁ›› በማለት ወከባውን የበለጠ አደረጉት፡፡ አባቶችን በአረመኔና ጭካኔ በተሞላበት አኳኋን እያሰቃየ በሌላ በኩል ደግሞ የማኅበራትን ስም በማጥፋት ወያኔ ያዋጣኛል የሚለውን መስመር ተከትሎ ሽምጥ ጋለበ፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ አካላት ሁኔታውን አላግባብ ሊጠቀሙበት ይፈልጉ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩን የፈጠረው አካል መፍትሄ መስጠት ቢችል ሁሉም ነገር ወዳልተፈለገ አቅጣጫ አያመራም ነበር፡፡ ወያኔ በዚህም ዋጋ ከፍሎበታል፡፡ በሚገርም ሁኔታ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ለሃገር ልማት ወሳኝ ነው ብሎ ሕግ ያወጣ መንግስት የአካባቢ ተጽዕኖ ግመገማ ሳያካሂድ፣ ዋና ባለ ድርሻ አካላት (ገዳማውያኑ) ስለ ፕሮጀክቱ ምንም መረጃ ሳይኖራቸው ገዳማቸው ሲታረስ እንዴት ዝም ይበሉ? ገዳማቸው ነፍጥ በታጠቀ የወያኔ ሠራዊት ሲረበሽ፣ የገዳሙ አርድዕት በግፍ ሲደበደቡ እንዴት ዝም ይበሉ? የሆነው ሁሉ ሆነና የወያኔ አፍ መክፈቻ ማኅበረ ቅዱሳን ነውና ሁኔታውን ያባባሰው ማኅበሩ ነው በሚል ክስ ጀመረ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በወቅቱ የነበረው አቋም የተለሳለሰ ነው የሚል ብዙ ሃሜት ነበረበት!፡፡ በርግጥም ጸጥታው መብዛቱ ብዙዎቻችንን ደስ አላሰኘም፡፡ በኋላ ባቀረበው ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ውስጥ የተካተቱት የመፍትሄ ሃሳቦችም ፍርሃት የተሞላበት ነበር፡፡ እንደ ግለስብ ቤተ ክርስቲያን የልማት ተቃዋሚ መሆን አለባት የሚል አቋም የለኝም፣ ያላትንም መሬት ቢሆን በፈቃዷ ቆርሳ በመስጠት ለህዝብ የሚጠቅም ነገር ካለ ብትሰጥ ሃጢያት አይደለም፡፡ አጉራ ዘለል ለሆነው ለወያኔ መንግስት ግን እንኳን የዋልድባን መሬት ሌላውንም ቆርሶ ለመስጠት የሚያስችል ትብብር ሊኖራት የሚችል አይመስለኝም፡፡-እንደለመደ በጉልበት ይወስደዋል እንጂ! አንዱ ሲሄድ ሌላው ሲተካ ማኅበረ ቅዱሳን በተሰማራበት ዓላማ ውጤታማ እንዳይሆን ወያኔ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ባሰማራቸው ግብረ አበሮቹና በየስልጣን እርከኑ ያስቀመጣቸው የእስልምና እና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንዲሁም ኦርቶዶክሳውያን ነን በሚሉት እነ በረከትና አቦይ ስብሃት (ወመሽ) ስድብ ውርጅብኝና ውግዘት እንዲሁም ወከባ ውስጥ ይገኛል፡፡ አሁንማ ጠቅላይ ሚኒስቴሩም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በመሆኑ እነ ዶ/ር ሽፈራው የፈለጉትን ሁሉ ለማድረግ ሁኔታዎች ተመቻቹላቸው፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር (ነፍሱን ይማረውና) በፓርላማና በተለያዩ መድረኮች ሲደሰኩር አንደነበረ፣ አባ ጳውሎስም በተለያዩ መድረኮች እንዳለሙት ሳይሆን ቀረና ተፈጥሮ የራሷን ርምጃ ወሰደች፡፡ የወያኔን የልብ ትርታ ያዳመጠው በጋሻው ደሳለኝ ደግሞ “ዝክረ ጳውሎስ ወመለስ መንፈሳዊ ጉባዔ” በሚል ስም በምዕመናን ጥረት ታግዶ ያጣውን የቤተ ክርስቲያን መድረክ ለመቆናጠጥ የሚያደርገውን ሩጫ ስንመለከት ደግሞ አቶ ኃይለ ማርያምና ዶ/ር ሽፈራው ምን ሊሠሩ እንደፈለጉ ነገሮች ግልጥ እየሆኑልን መጥተዋል፡፡ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የክልሎች የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮዎች፣ የፍትህ ቢሮዎች በየዓመቱ በሚያወጡት ዕቅዳቸው ውስጥ ቀዳሚ አጀንዳቸው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ሁሌም የሚዘገንነኝ ጉዳይ ነው፡፡ እኔ የማኅበር አባዜ የለብኝም፤ ማኅበረ ቅዱሳንንም አላመልክም፡፡ ነገር ግን ፍትህ ሲዛባ ውስጤ ይጎዳል፡፡ የዶክትር ሽፈራው ሚኒስቴር ጽ/ቤት በየጊዜው በሚያወጣቸው መግለጫዎች፣ በሚያካሂዳቸው ውስጣዊ ስብሰባዎች እንዲሁም በሚያቅዳቸው ተግባራት ማኅበረ ቅዱሳን ትልቁ አጀንዳ ነው፡፡ እነዚህ ደናቁርት በጋሻው ደሳለኝን ዋናው በጥባጭ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ነው በማለት በአንድ ወቅት ፈርጀው እንደነበረ ሳስብ ደግሞ ሚዛን የሚደፉ (substance የሌላቸው) እንዳልኖኑ እገነዘባለሁ፡፡ ለማሳያ ያህል የወያኔ መንግስት አዲሰ ራዕይ በሚለው መጽሄቱና በጸጥታ አካላት የተጻፉትን አንመልከት፡፡ በመጀመሪያ የታሪክ ምሁራን በአግባቡ ሊያስቀምጡት የሚፈለገው ነገር ወያኔ በተደጋጋሚ “ኦርቶዶክስም፣ እስልምናም መጤ ሃማኖት ናቸው” የሚል የታሪክ አላዋቂነት አነጋገሩን ማስተካከል ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መጤ አይደለችም፡፡ ሰትጠባበቀው የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀብላ፣ በትንቢቱ መሠረት ሕዝቧን አጽንታ የኖረች ቤተክርስቲያን፣ ለዚህም የተቸገሩትን ሁሉ (ኢትዮጵያውያን ባይሆኑም፡፡ – ለምሳሌ “የነብዩ” ሙሀመድን ቤተሰቦች) ስትረዳ የነበረች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የሰላምና የፍቅር አንዲሁም የመከባበር ተምሳሌት!፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን’ኮ UNHCR ሳይቋቋም የስደተኞች ካምፕ አዘጋጅታ ስደተኞችን ስትቀበል የኖረች የዓለም ምሳሌ እንጂ ወያኔ እንደሚለው ሌሎችን የምታሳድድና ለልማት አንቅፋት የምትሆን አይደለችም፡፡ የወያኔ መንግስት አስቀድሞ ሲነሳ ያለመውን ሕልም ለማስፈጸም ቤተ ክርስቲያንን በአዲስ ራዕይ መጽሄቱ እንዲህ በማለት ስሟን ያጠፋታል፣ ይወቅሳታል፣ ይከሳታል፣ ምዕመናንንም ይወነጅላል፡- “ኢትዮጵያዊነትን ከኦርቶዶክስ ክርስትና ለይቶ ማየት እንዳይችል አስተሳሰቡ ለዘመናት በተለያየ መንገዶች የተቀረጸው ዜጋ የአይሁድ እምነት ተከታዮችን ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑና ፈላሾች በሚል ስም ከመጥራት አልፈው የማታ ማታ ወደ አገራቸው እሥራኤል እንደሄዱ ሰዎች እንዲቆጥር ሲቀሰቀስ ነበረው ዜጋ፣ ሙስሊሞችን መጤ ሃይማት እንደተሸከሙ የውጭ ጠላቶችና ሰርጎ ገቦች እንዲጠራጠር ለዘመናት የተማረው ዜጋ…..” አዲስ ራዕይ መጽሄት፣ የመስከረም 2000 ዓ/ም ልዩ እትም ሃገራችን ኢትዮጵያ ከክርስትና በፊት እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሕዝብ የነበራት ሃገር ናት፡፡ ይህንን በብዙ ማስረጃዎች ማሳየት ይቻላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ40 ጊዜ በላይ ስሟ ተጠቅሶ መገኘቱ፣ በሃገሪቱ የሚገኙት የብሉይ ኪዳን መስዋዕት ማቅረቢያ ዕቃዎችና ቦታዎች፣ ከሰበዓ ሰገል አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆኑ፣ በሃገራችን ያሉ መጻሕፍት (በተለይ መጽሐፈ ሄኖክ) ፣ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረላት ንግስት ህንደኬ፣ ሌሎችም ብዙ ማስረጃዎች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔርን የሚያመልክና የክስቶስን መምጣት የሚጠባበቅ ሕዝብ የነበረባት ሀገር እንደሆነች የታሪክ አሻራዎችና ምስክሮቻችን ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን የሚጠባበቁት ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ወደምድር ሲመጣ አምሃ አቅርበው ተቀብለውታል፡፡ ሃይማኖት አልቀየሩም፡፡ የሚጠብቁትን አግኝተዋልና በተነገረው ትንቢት መሠረት ብሉይን ከሐዲስ አስማምተው ክርስትናን ይዘው ይሄው እስከዛሬ የደረሰውን ብርቅና ድንቅ ሃይማኖት፣ ትውፊት፣ ታሪክ፣ ቅርስ፣ የመቻቻል ባሕል…ወዘተ አቆዩን፡፡ ስለዚህ ወያኔም ሆነ ማንኛውም ሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጤ ሃይማኖት እንዳልሆነች ሊገነዘብ ይገባዋል፡፡ መጤ የሚባልኮ ነባርና ሌሎችን ተቀባይ ሲኖር ነው፡፡ እርሷ የተቀበለቻቸው ግን መጤ ሊባሉ ይችላሉ፡፡-ቀድሞውንም በኢትዮጵያ መሠረት የላቸውምና፡፡ በዓለም ላይ በብሉይና በሐዲስ እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሕዝብ ያላት ሃገር-ኢትዮጵያ! የቤተ ክርሰቲያንን ልጆችን አሸባሪ በማለት ሲፈርጅ የነበረው ሟች መለስ ማስረጃው “አንድ ሃገር፣ አንድ ሃይማኖት ይላሉ” ወዘተ የሚል ነበር፡፡ በዚህ ዙሪያ ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ያቀረበውን ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ ማስቀመጥ ብቻ ተገቢ ነው ብየ አምናለሁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሙስሊም አክራሪዎች ከማብራራታቸው ጎን ለጎን ደግሞ አክራሪነት በእስልምና ብቻ ያልተገታ መሆኑን ለማስረዳት በሚመስል መልኩ በክርስትናው ውስጥ በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለውን በምሳሌነት ለማንሣት በጥምቀት ወቅት ወጣቶች ይዘውት ወጡ ያሉትን መፈክር ጠቅሰዋል። “ጥምቀት ላይ ከነበሩት መፈክሮች አንዱ ‘አንድ አገር – አንድ ሃይማኖት’ የሚል ነው። …. ‘አንድ አገር – አንድ ሃይማኖት’ የሚል ሕገ መንግሥት የለንም። (መፈክሩ) … የክርስቲያን መንግሥት እንዲኖር የሚፈልጉ … እንዳሉ ያሳየናል” ብለዋል። “የዚህም መነሻው የግንዛቤ ማነሥ በመሆኑ በማስተማር የሚመለሱ ናቸው” ሲሉ አክለዋል። ቀጥለውም ይኸው አክራሪነት በክርስትናም ውስጥ እየታየ መሆኑን ለአብነትም ጥምቀት ላይ የሚታዩ መፈክሮችን ካብራሩ በኋላ አክራሪዎቹ “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ሲሉ የእስልምናው “ሰለፊ” በክርስትናው በተለይም በኦርቶዶክሱ በኩል “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው የሚል አንድምታ ያለው አጭር ነገር ግን ከባድ ኃይለ ቃል ተናግረው አልፈዋል። “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት” ያሉት ግን ምን መሆኑን በርግጥ አላብራሩም። ምናልባት ከላይ “አንድ አገር – አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ያዙ የተባሉት የጥምቀት አክባሪዎች “የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም/ናቸው” በሚል እሳቤ የተናገሩትም ይመስላል። በመጀመሪያ “አንድ ሃይማኖት” የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ ለብዙ ውይይቶች በር የሚከፍት ትልቅ ጉዳይ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት አለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው። አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ዐውድ ከተመለከትነው “ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ብ….ቻ ናት፣ ያለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሌሎቻችሁ ቦታ የላችሁም ትላላችሁ” የሚል አንድምታ እየሰጡ የሚናገሩ እና የሚጽፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ከመኖራቸው አንጻር “አንድ ሃይማኖት” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አንዳንድ ሰዎች የተሳሳተ ትርጉም እንዳለው አድርገው እየተጠቀሙበት እንዳይሆን ሥጋት አለኝ። “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ ከሃይማኖት ጋር በማይተዋወቁ ሰዎች ዓይን ከተመለከትነው መቻቻልን ለማስተናገድ ፈቃደኝነት የጎደለው አገላለጽ ሊመስል ይችላል። መቻቻል ማለት ግን መሠረታዊ የራስን ሃይማኖት አስተምህሮ መናድና መካድ ስላልሆነ መፍትሔው እርስ-በርስ መገነዛዘብና መረዳዳት ነው። የትኛውም ክርስቲያን “አንድ ሃይማኖት” ቢል የሐዋርያውን ቃል መጥቀሱ እንጂ ሌላ እምነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ጥላቻ አለው ማለት አይደለም። የጥምቀት አክባሪ ወጣቶች ቲ-ሸርቶች ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ቃል የምረዳው በዚህ መንፈስ ነው። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱት መፈክር “አንድ ሃይማኖት” ብቻ ብሎ ሳያበቃ “አንድ አገር” የሚለውን ጨምሮበት “አንድ አገር – አንድ ሃይማኖት” በሚል ተጽፎ ከሆነ አባባሉ ሌላ ትርጉም ማለትም “የክርስቲያን መንግሥት ለመመሥረት መሻት” የሚል አንድምታ ሊሰጠው ይችላል። ቲ-ሸርቶችን የለበሱ እና ባነሮችን የያዙ ወጣቶች በጥምቀት በዓላት አሁን ባለው መልክ በዓል ማክበር ከጀመሩ ገና ሁለት ወይም ሦስት ዓመታቸው ነው። በነዚህ ሁለት ወይም ሦስት ዓመታት የጥምቀት በዓላት ላይ የተነሱ እና ከተለያዩ ድረ ገጾችና ማኅበራዊ ገጾች የሰበሰብኳቸውን ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ፎቶግራፎች በድጋሚ በጥንቃቄ ለመመልከት ሞክሬያለኹ። እነዚህ በተለያዩ ካሜራዎች፣ በተለያዩ አንሺዎች፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎችና በተለያዩ ቦታዎች ከተነሡት ፎቶግራፎች ውስጥ ጠ/ሚኒስትሩ ያሉትን ዓይነት ጥቅስ ወይም ተመሳሳዩን ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም። በርግጥ መፈክሩ በነዚህ ፎቶዎች ውስጥ ባለመገኘቱ የተነገረው ነገር ስህተት ነው ማለት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ከመፈክሩ ከባድነት እና ከያዘውም ሐሳብ ጽኑዕነት አንጻር አንዱም ፎቶ አንሺ ሊያነሳው ያለመቻሉ ሁኔታ የአጋጣሚ ብቻ ነበር ለማለት አያስችልም። ስለዚህ አስቀድሞም ኅሊናዬ እንደሚነግረኝ እንዲህ የሚል ጥቅስ አልነበረምም አልተጻፈምም ለማለት እደፍራለኹ። “አንድ አገር” የሚለውን ነጥብም በተመለከተ ባለሙያዎች የበለጠ ሊያብራሩት እንደሚችሉ ባምንም በግሌ የሚሰማኝን ግን በአጭሩ ለመጠቆም እሞክራለኹ። እዚህ በምንኖርበት አገር በአሜሪካ Pledge of Allegiance የሚሉትና ቃል ኪዳናቸውን የሚያጸኑበት መሐላ (ማለትም “I pledge allegiance to the flag of the United States of America, and to the republic for which it stands, one nation under God, indivisible, with liberty and justice for all”) አላቸው። አሜሪካዊ የሆነ ሁሉ ከትንንሽ ተማሪዎች እስከ ምክር ቤት አባላት ድረስ ያውቁታል፣ በየአጋጣሚውም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይሉታል። ለአገራቸው ያላቸውንም ቃል ኪዳን ይገልፁበታል። አንድ አገር/ one nation under God ያሉት ግን የሁሉም የሆነ አገር ማለታቸው መሆኑ ግልጽ ነው። አገር የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሊሆን ይገባዋል። ኢትዮጵያን በምሳሌነት ካነሣን በአንዲቱ አገራችን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ሺህ ዓመታት በሰላም እንደኖርነው ሁሉ አሁንም ክርስቲያኑም፣ ሙስሊሙም፣ የሚያምነውም የማያምነውም “አገሬ” ብሎ ሊኖርባት ይገባል እንጂ ለዚህኛው እምነት ተከታይ “አገር” ሆና ለሌላው እምነት ተከታይ ደግሞ አገር የማትሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም። “አንድ አገር” ሲባልም ሥጋት የሚገባው ዜጋ ሊኖር አይገባም። “አንዲት አገር” ዜጎቿ ተጨፍልቀው፣ ተጠፍጥፈው የምትፈጠር አይደለችም። በሌላ ጽሑፍ እንዳነሣኹት ኢትዮጵያውያን ብዙዎች ብንሆንም አንዲት አገር ናት ያለችን። አገራችን ቀለማችንና ቋንቋችን ለየቅል ቢሆንም ሁላችን በአንድነት የምንኖርባት የጋራ ቤታችን ናት። ኢትዮጵያውያንም እንደ አሜሪካኖቹ “ከፈጣሪ በታች ያለች አንዲት አገር/ one nation under God” አለችን ብንል የሚያሳፍር አይሆንም። በእርሷ ነውና እኛም “ኢትዮጵያውያን” የተባልነው። በሃይማኖትም አንጻር ካየነው ይህቺ አገራችን ቅዱሳን በኪደተ እግራቸው የባረኳት፣ አበው በደማቸው የጠበቋት፣ እምነት እና ቋንቋ ሳንለይ የምንኖርባት ቅድስት ምድር ናት። አንድ ሃገር አንድ ሃይማኖት የሚለውን የሃሰት ክስ በተመለከተ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደሚከተለው አብራርቶታል፡፡- ‹‹አንድ አገር አንድ ሃይማኖት›› የሚለው እኮ ከራሷ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ጋራ የሚጋጭ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ አንድ ቁጥር ስምንት ላይ የሚለው ‹‹በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ በሰማርያ እስከ ዓለም ዳርቻ አስተምሩ›› ነው፡፡ አንድ አገር ውስጥ ተቀመጡ አላለም፡፡ የሚባለውን የማንቀበለው ከእኛ አስተምህሮ ጋራ ስለሚጋጭ ነው፡፡ ቢቻል ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሶማልያ፣ ታንዛንያ፣ ጋና፣ ጃማይካ ሄደን አስተምረን ክርስቲያን ማድረግ ነው የሚጠበቅብን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ የኾኑ አሜሪካውያን፣ ጃማይካውያን፣ እንግሊዛውያን፣ ጀርመናውያን አሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ እንዴት ወደ አንድ አገር መጥቅለል ይቻላል? ሊኾን አይችልም፡፡ ፈጽሞ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ጋራ የማይሄድ ነው፡፡ ሁለቱም የቤተ ክርስቲያን ልጆች በተለያየ አተያይ እንዳስረዱን እንድ ሃገር የሚባለው ነገር ቢባልም የሚያስፈረግግ አይደለም፡፡ አልተባለም እንጂ አንድ ሃገር ብለው ሌሎችን ውጡ ብለው አልተናገሩምና ስህተት የለውም፤ ነውርም አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያን ከተቋቋመችበት ዓላማ አንጻር የተባለው ስለማይመጥናት ይህንን አታራምደውም፡፡ እናም ወያኔዎች ከሚመጥናት በታች የሆነ ሃሳብ ይዛችሁ በሃሰት አትክሰሷት፡፡ በአዲስ ራዕይ መጽሔት ወያኔ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሉ ስለሚላቸው አክራሪዎች የሚናገረው ደግሞ በሚከተለው መንገድ ነው፡- “båRèìKS b@t KRSTÃN >ÍN y¸‰mdW l@§W ±ltEµ L† L† wQ¬êE mL÷C bmÃZ s!gl} öYaLÝÝ kXnz!H xNÇ yêLDÆ gÄM tdfr b¸L mLK s!‰mD yöyW nWÝÝ yêLDÆ gÄM zmÂTN ÃSö-r y¦Y¥ñT tÌM s!çN kä§ ¯dL bwYÂdU »Ä¥ mÊT §Y y¸gኝ gÄM nWÝÝ ygÄÑ mÊT wRÇ q$mt$ y¸¬wQ s!çN mNG|T kz!H mÊT W+ b²Ê¥ ¹lö §Y ySµ*R L¥T b¥µÿD §Y Yg¾LÝÝ ySµ*R L¥t$ y¸µÿdW bÈM ZQt¾ ö§ §Y s!çN yêLDÆ gÄM mÊT dGä bdU wYÂdU ï¬ãC §Y y¸g” nWÝÝ SlçnM ySµ*R L¥t$ gÄÑN b¥Ynµ h#n@¬ Xytµÿd Yg¾LÝÝ ¦q$ YH çñ úl bgÄÑ bSµ*R ¥úW mµkL ÃlWN kFt¾ ymLK› MDR L†nT bQRb# l¥ÃWq$ yKRST M:mÂN h#l# gÄM tdfr y¸lW ”L XLH yq$È S»T Yf_RÆcêL BlÖ b¥mN sð zmÒ s!µÿDbT kRàLÝÝ” xÄþS ‰:Y ¼Ml¤-n¼s¤ 2005 የስኳር ልማቱ ፕሮጀክት ከዋልድባ ገዳም ከ16 እስከ 20 ሄክታር የሚሆን መሬት መውሰዱ በተደጋጋሚ የተረጋገጠና የማይካድ ጉዳይ ነው፡፡ ቦታውን መመልከት የሚፈልግ ካለ በቴክኖሎጊ ዘመን ከgoogle earth መመልከት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ወያኔ የገዳሙን ይዞታ የማይነካ ልማት እያካሄድኩ ነው ብሎ ለማስተባበል መሞከሩ አግባብ አይደለም፡፡ በወቅቱ ነበረውን ሁኔታ በተመለከተ ይመለከተኛል ያለው ሁሉ ብዙ ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሲል ተናግሯል ለማለት አልችልም፡፡ ይሁን እንጂ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የተናገሩት ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም መለጠፍ የለበትም፡፡ እነርሱ ለቤተ ክርስቲያን ጠበቆች ናቸው ብለን መናገር አንችልም፡፡ ሁሉም የሚያስቀድመው የራሱን ፖለቲካ ስለሆነ፡፡ ስለዚህ ወያኔ እውነታውን ከመካድ ይልቅ የፈጸመውን ስህተት አምኖ ልማቱ ለምን እዚያ ቦታ ላይ ሊሆን እንደተፈለገ፣ ለምን ባለድርሻ አካላትን ሳያነጋግር መጀመር እንደፈለገ፣ ያወጣውን ህግ በመጣስ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ሳያካሂድ ትልቅ የሚባል ፕሮጀክት እንዴት አንደተጀመረ ወዘተ በመሳሰሉት ዙሪያ ገዳማውያንንና ህዝበ ክርስቲያኑን እንዲሁም በአጠቃላይ በድፍረት ለሰራው ተግባር ቤተ ክርስቲያኗን ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል፡፡ የወያኔ መንግስት በሃገራችን በእንግድነት የተቀበልናቸው አክራሪ እስልምና ቡድኖች በጅማና አካባቢዋ ሕዝበ ክርስቲያኑን በአሰቃቂ ሁኔታ ደማቸውን ሲያፈሱት ሁኔታውን ከምንም ሳይቆጥር በወቅቱ በጣም ያሳሰበው ለምን ችግሩ ተዘገበ የሚለው ነበር፡፡ ወገኖቻቸው ሲታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ፣ ከመኖሪያቸው ሲፈናቀሉ፣ በአጠቃላይ ግፍ ሲፈጸምባቸው የሚደርስላቸው ያጡ፣ የመንግስት ባለስልጣናትም ከአሸባሪዎች ጋር ተባብረው አቤቱታቸውን አንሰማም ሲሏቸው ሁኔታውን ለህዝብ ለማሳወቅ ችግሩን በጽሁፍና በቪዲዮ ማስተጋባት ጀመሩ፡፡ ይህ የሚበረታታና ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ፍትህ በሌለባት ሃገር ሰው ችግሩን በሚፈልገው መንገድ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ መብቱ ሲታፈን፣ አማራጭ ሲያጣ ሌሎች መንገዶችን መጠቀም ነበረበት፡፡ በወቅቱ የነበረውን የአሸባሪዎች ጭፍጨፋ በተለያዩ ድረ ገጾች መመልከት ይቻላል፡፡ ወያኔ ግን ችግሩን በትዕግስት የተመለከተውን ኦርቶዶክሳዊ የአጸፋ ምላሽ እንውሰድ አለ በማለት ሲከስስ ይደመጣል፡፡ የአጸፋ ርምጃ መውሰድ ቢፈልግ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ወያኔን ማማከር ባልተገባው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአጸፋ ርምጃ በመውሰድ ጽድቅ ስለማይገኝ፣ እግዚአብሔርንም በጉልበት ማገዝ ስለማይቻል (ከእግዚአብሔር በላይ ማን ጉልበት አለውና!) የዚህን አይነት ሃሳብ ያራመደ ኦርቶዶክሳዊ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በአዲስ ራዕይ መጽሄት በትዕግስት ምራቁን ዋጥ አድርጎ ተቀመጠውን ኦርቶዶክሳዊ እንዲህ በማለት ሲወርፉ ተስተውሏል፡- bxND wQT bM:‰B x!T×ùà J¥ xµÆb! báêR© SM y¸¬wq$ xK‰¶ãC bKRStEÃñC §Y Ãdrs#TN GDà m-g!à b¥DrG «KRStEÃñC Xyt=f=û nW Slz!HM xiÍW l!mlS YgÆêL´ b¸L Q¢T mNqúqS jMrW nbRÝÝ (xÄþS ‰:Y ¼Ml¤-n¼s¤ 2005) የነበረውን ችግር ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ ለሌሎች የሚዲያ አካላት ዘግበውታል፡፡ በተለይ ማኅበረ ቅዱሳን የተቋቋመለት ዓላማ መንፈሳዊ እስከሆነ ድረስ በመንፈሳዊው ጉዞ ውስጥ ያስፈልጋሉ የሚላቸውን ዜናዎች፣ ትምህርቶች…ወዘተ በጊዜው ማስተላለፍ ይጠበቅበታል፡፡ በወቅቱም ያደረገው ይህንን ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን ይህንን በማድረጉ ቪዲዮውን ቀርፆ ያሰራጨው ማኅበረ ቅዱሳን ነው በሚል የወያኔ ተላላኪዎች በተደጋጋሚ ሲከስሱትና ጽ/ቤቱንም ሲፈትሹት እንደነበር ሁሉም ያውቃል፡፡ በአጠቃላይ ወያኔ ሃይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው ብሎ በጽሑፍ ደረጃ ቢያሰፍርም በተግባር የሚያከናውነው ግልባጩን መሆኑን ያሳየናል፡፡ በጽሁፍ ደረጃ በአዲስ ራዕይ መጽሄቱ እነደሚከተለው ሰፍሮ የምናየው ሁሉ ሽፋንና ድካሙ እንዳይታወቅበት ለማድረግ የሚፈጥረው ስልት ነው፡፡ bxg‰CN bmgNÆT §Y ÃlW yXk#LnT SR›T GN b¦Y¥ñèC mµkL ÃlWN GNß#nT s§¥êE½ bmÒÒL bmGÆÆT §Y ytmsrt XNÄ!çN ÃSÒl nWÝÝ qdMT yxg‰CN g¢EãC ¦Y¥ñTN bmú¶ÃnT Xyt-qÑ HZïCN XRS bXRS s!ÃÂKs# ytÙz#bTN M:‰F b¥ÃÄGM h#n@¬ bmZUT bXMnèC mµkL bXk#LnT½ bmÒÒL bmGÆÆT §Y ytmsrt GNß#nTN b¥-ÂkR §Y Yg¾LÝÝ xÄþS ‰:Y ¼Ml¤-n¼s¤ 2005 gA 16 ወያኔ እንዳለው ሳይሆን ተቃራኒው እየተፈጸመ ለመሆኑ የተለያዩ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ እርሱ ግን ችግሩን ለመሸፈን በለመደው ስልት ሌሎችን መክሰስ ነው የጀመረው፡፡ ከነሐሴ 21 እስከ 23/2005 ዓ/ም በተካሄደው ሃገር አቀፍ “የሰላም እሴት ማጎልበቻ ጉባዔ” ላይ አቶ ስብሃት ነጋ እንዲህ ብሎ ነበር፡- መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡ ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት የሚለው አቶ ስብሃትን እንደሚወክል ከኣባ ጳውሎስ ጋር ተያይዞ ከአንዲት ሴት (ሳቤላ እንደምትባል የቅርብ አዋቂዎች ይናገራሉ) ጋር ሆኖ አባ ጳዉሎስን ከስልጣን እናወርዳለን በማለት ጳጳሳትን ለማሳሳት ካደረገው እንቅስቃሴ አንጻር ማሳየት ይቻላል፡፡ እርሱ እንደተናገረው ለምን ጣልቃ ገባችሁብን ብለው ጥያቄ ያቀረቡትን ጳጳሳት ደግሞ የወያኔ ተላላኪዎች በሌሊት ሲያዋክቡ ተስተውለዋል፡፡ ስለዚህ እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች በሁለተኛ ደረጃ ሳይሆን በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂ ሊሆኑ ያስፈልጋል፡፡ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንዲሉ “ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ” ሲል መናገሩ በእርሱ እድሜ እንደዚህ የሚዋሽ ሽማግሌ መኖሩን እስክጠራጠር ድረስ ፈትኖኛል፡፡ ይህ ቀላላም ሽማግሌ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት ዕዳ ነው፣ ብልሽቱ እንዲስተካከል አይሠራም፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክነትም እንዳለበት ይወራል። ፣ ጳጳሳቱ ለሃይማኖታቸው አይረቡም፤ ቤተ ክህነቱ ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው” (http://www.fetehe.com/sebehate142.html) ወዘተ በማለት ትችቱን ሲሰነዝር ይስተዋላል፡፡ ለመሆኑ ጣልቃ መግባት ቤተ ክርስቲያን የምትፈልገውን እርቅ ከማደናቀፍ በላይ ምን ጣልቃ ገብነት አለ? ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ የመጡትን የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን ካለ አግባብ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ ያደረገ የቤተ ክርስቲያን ጠላት “አጄ ከደሙ ንጹህ ነው” ብሎ ለመናገር ምን ሞራል አለው? በተቃራኒው ጣልቃ የሚገቡት ሌሎች ናቸው ለማለት ባስነበበን በአዲስ ራዕይ የሐምሌ-ነሐሴ 2005 መጽሔት ወያኔ እንዲህ ይለናል፡- kBi#: xb#n ÔWlÖS HLfT b“§ yx!T×ùà åRèìKS b@tKRSTÃN m¶ã–N bmr-CbT g!z@ mNG|T bz!H b¥YmlktW S‰ WS_ lmGÆT xLäkrMM”” x§sbMMÝÝ Yh#N XN©! bxND bk#L b‰úcW ±ltEµêE mSfRT yb@t KRStEÃn!t$N m¶ãC `§ðãC mëM mšR y¸fLg# t”ê¸ `YlÖC btlYM dGä bW+ y¸gß# t”ê¸ `YlÖC y‰úcWN sW xzUJtW l¥Smr_ Bz# _rT xDRgêLÝÝ…..båRèìKS b@tKRStEÃN WS_ TRMS B_B_ lmF-R åRèìKîC l@lÖC ¦Y¥ñèC mµkL GuT lmqSqS y¸äK„T ydRG ytlÆ TMKHt¾ ¦YlÖC Q¶èC ÂcWÝÝ Xnz!H yTMKHT ¦YlÖC xNÄND yXMnt$ xÆèC bU‰ ¦Y¥ñTN b±ltEµ x§¥ z#¶Ã m-q¸Ã xDRgW Xys„ lmçÂcW k97 MRÅ b“§ xNÄND bx»¶µ y¸gß# ÔÔúT QNJT bm‰W sLF §Y y¦Y¥ñT xÆTnT µÆcWN XNdlbs# kmslFM xLfW xStÆƶ çnW m¬y¬cW bqE ¥rUgÅ nWÝÝ ይህ ሁሉ ልፍለፋ ማንበብና መስማት እንዲሁም ሁሉንም ማገናዘብ የሚችል ሕዝብ የለም ከሚል ቂልነት አዕምሮ የመነጨ ነው፡፡ ከምሥረታ ጀመሮ በከፍተኛ የስለላ መረብ ቤተክርስቲያንን ሲያዳክም፣ በሰለጠኑ ካድሬዎች የቤተ ክህነቱን አስተዳደር ሲቆጣጠር ቆየው የወያኔ መንግስት አሁንም ጫናውን አጠናክሮ ለመቀጠል ሰፊ የሆነ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ በ2006 ዓ/ም ጥቅምት ወር በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ ጫና በማድረግ የራሱን ካድሬዎች ሊቃነ ጳጳሳት አድርጎ ለማስሾም ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛል፡፡ የራሱን እጩዎች መልምሎ እንዳዘጋጀ ይነገራል፡፡ በ2005 ዓ/ም መጋቢት ወር ላይ ስራውን የገመገመው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በመንፈሳዊ ኮሌጆች ለመግባትና የራሱን ካድሬዎች ለመመልመል ፍላጎት እንዳለው ሲገልጥ ነበር፡፡ ሃሳቡንም በሪፖርቱና የ2006 አቅጣጫ ብሎ ባዘጋጀው ጽሁፍ በሚከተለው መልኩ አስቀምጦታል፡- “በአጫጭር ኮርስም ይሁን በመደበኛ ፕሮግራም ከሰርቲፊኬት አንስቶ እስከ ዲግሪ ፕሮግራሞች የሚያስተምር የትምህርት ተቋም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ከእነዚህም የትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ሐይማኖታዊ ምሁራን ዘመናዊ ትምህርት ጭምር ያላቸው ስለሚሆኑ የአገራችን የሐይማኖት ተቋማትና አመራር ስለሚቆጣጠሩ በቀላሉ ለአክራሪነት የሚጋለጡበትን ሁኔታ በእጅጉ መቀነስ ይቻላል፡፡”
 18. Anonymous October 24, 2013 at 4:14 pm Reply

  “የሃይማኖት እንከን የሌለባትና” hahahaha

  • TSEGA MARIYAM October 27, 2013 at 7:35 am Reply

   men letel felek ?ene eko yemigeremegni nechochu enkuan be orthodox emenet eye tegeremu sikenu enanete gin kenesu beworesachihut ewonet meseloachihu setetalelu betam tasazenalachihu!enesus balemawok enanete gin kawokachihut behuwala lekadachihu enazenalen “kemayamen yelek hayemanotun lekade woyolet “yemilewon ayetachihu kehone gizew gena new ena beneseha temelesu.egeziabeher “””ANED GIZE LEKEDUSAN SELE TESETECH HAYEMANOY ENDETEGADELU””””yelal ena asebebet ???Amelakem bemeder lay tenedelako ayedelem kebarenet netsa yawotan Hawareyatem sele keresetos belew mekeran tekebelew new yalefut enji andem hawareya tenedelako yalefe hawareya yelem ena tsom tselot segedet fereteh kewonet ke andua hayemanot wonedeme ehete ebakachihu tedebaleku “”betekeresetiyan hule sele enanete tetseleyalech “”””SELETESEDEDU SEWOCH AND ADEREGEN EYALECH “”””NUUUUUUUUU.

 19. Anonymous October 25, 2013 at 8:16 am Reply

  እባካችሁ አሁን የጀመራችሁትን የቤተክርስቲያናችን ታሪክ እና እውነተኛነት እያጠፋ ያለውን ይህን መንግስት በመፍራት ወደኋላ እንዳትሉ፡፡ ስለ እግዚአብሔር ክብር ስትሉ የቤተክርስቲያናችን ህልውና ታደጉልን እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

 20. Anonymous October 27, 2013 at 7:14 am Reply

  DIYABELOS ZENARUN CHERESE KESETUN ARAGEFE BETE KERESETIYANEN GIN ALEGODATEM.YELEKES YE MISADEBEBET AFE YETESETEW DIYABELOS NEW ENA SEDEBUN SHIMUTUN TETEN BETSELOT ENEBERETA???”EGZIABEHER TEWAGI NEW SEMUM EGEZIABEHER NEW”DENEGEL ATELEYEN.AME……….

 21. Anonymous October 31, 2013 at 12:31 pm Reply

  It is a good start.Let us prey with them for the reality of our church dream!

 22. mega November 4, 2013 at 4:14 pm Reply

  አቤት አቤት እንዴት ነዉ ነገሩ፡ ጂብ ከሄደ ዉሻ ጮኸ እኮ ሆነ ነገሩ፡ ህዝቡ ከሲመቱ በፊት እርቁ ይቅደም እያለ ሲጮህ ሰሚ አጥቶ አሁን ስልጣንን ካመቻቹ በሁዋላ ተቆርቁዋሪ መሆን ምን ይሉታል? የከፋ የሚሆነዉ ደግሞ የዉጮቹን ባቶችን ስም እያጎደፉ እንደፓለቲካ ፓርቲ ራስን ንጹህ አድርጎ መጽሀፍ መጻፍ ምን ይሆን የሚፈይደዉ? ከመወጋገዝ እንደ ሀይማኖቱ መመሪያ በእርቅ መፍታት አይሻልም? አምላከ እስራዔል መረን ባክህ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: