የመንግሥትን የአክራሪነት ፍረጃ ተከትሎ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ለውጥ የሚቃወሙ ጥቅመኞች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚሰነዝሩት ውንጀላ ተጠናክሯል፤ ማኅበሩ ክሥ ለመመሥረት እየተዘጋጀ ነው

Aba sawiros

 • ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው፣ መልአ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ እና መልአከ ገነት አባ ዮናስ ታደሰ ዋነኛ ተጠያቂዎች ይኾናሉ ተብሏል፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የዐፄ ምኒልክ ሥርዐት እንዲመለስና የዐፄ ምኒልክ ባንዴራ እንዲሰቀል የሚፈልጉ ናቸው›› ብለው በመንግሥታዊ ስብሰባ ላይ በይፋ በመክሰስ ርምጃ እንዲወስድበት የጠየቁት የወሊሶ ሀ/ስብከት ሥ/አስኪያጅ መልአከ ገነት አባ አፈ ወርቅ፣ በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ‹‹አጥቢያዎች ፐርሰንት እንዳይከፍሉ ሕዝቡን ይከፋፍልብናል፤ ወጣቶችን ያደራጅብናል›› በሚል መሠረተ ቢስ ክሥ በቅ/ሲኖዶስ እንዲታገድ ጠይቀዋል፡፡
 • የደቡብ ምዕራብ ሸዋ – ወሊሶ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጳጳስነት ይኹን በሥራ አስኪያጅነት ለመምራት ችሎታውም ሥነ ምግባሩም እንደሌላቸው ተቃውሞ የቀረበባቸው አቡነ ሳዊሮስ እና መልአከ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ ለ፴፪ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ባቀረቡት ‹ሪፖርት›፣ የአስተዳደራቸውን ብልሹነት የተቃወሟቸውን አገልጋዮችና ምእመናን ‹‹ሥራ ዐጦች እና ተራ ዱርዮዎች›› በማለት ዘልፈዋል፡፡
 • ምግባረ ብልሹው ሥራ አስኪያጅ በነሐሴ ወር ፳፻፭ ዓ.ም. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የጸጥታ ቢሮ በአዳማ ከተማ ባዘጋጀውና ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት በተሳተፉበት ‹‹የፀረ አክራሪነት›› ስብሰባ÷ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት የተማረው ትውልድ በትምህርትም ኾነ በሥራ ምክንያት በሄደበት በሰንበት ት/ቤትና በሰበካ ጉባኤ ታቅፎ በገንዘቡ፣ በዕውቀቱና በጉልበቱ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግል የሚያከናውነውን አገልግሎት በጣልቃ ገብነት ከሰዋል፡፡ የስብሰባው መሪም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ of tooltoota ነው፤›› ሲሉ በግልጽ ተባብረዋቸዋል፡፡
 • የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ባዘጋጁት ‹‹አገር አቀፍ የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ላይ÷ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት የሚያከናውነውን አገልግሎት ከተቀበረ ፈንጂ ጋራ ያመሳሰሉት መልአከ ገነት አባ ዮናስ ታደሰ፣ በጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀ/ስብከት የሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቀሲስ ነበሩ፡፡
 • የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊ የኾኑት መልአከ ገነት አባ ዮናስ፣ የአባ አፈ ወርቅ ዮሐንስን የውንጀላ ሪፖርት ‹‹ወንድ! ያበጠው ይፈንዳ!›› በማለት ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ በከፍተኛ ስሜት ሲደግፉ ተስተውለዋል፡፡ አባ ዮናስ በከምባታ ሃድያ ስልጢና ጉራጌ ዞኖች አህጉረ ስብከት የሦስት አብያተ ክርስቲያናትን አስተዳደር ከወረዳ ቤተ ክህነቱ ጋራ ደራርበው የሚመሩ፣ በጠበኛነትና ከሙስሊም ሴቶች ጋራ ሳይቀር ዝሙት በመፈጸማቸው የሙስሊም አዛውንቶች ስሞታና ክሥ ያቀረቡባቸው ቆሞስ ነኝ ባይ ስመ መነኩሴ ናቸው፡፡
 • መሰላቸው መልአከ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ ደግሞ በምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት የአምቦ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት በተካሄደ የኦዲት ምርመራ በከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት በተነሣ አለመግባባት ከተወገዱ በኋላ በቀድሞው ፓትርያርክ ትእዛዝ የሆሮ ጉድሩ (ሻምቡ) ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የተሾሙ፣ በሻምቡ ብልሹ አሠራራቸውንና ምግባራቸውን ያጋለጡ ቀናዒ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችንና የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን በአሸባሪነት በመክሰስ ስም ዝርዝራቸውን ጠቅሰው ለመንግሥት የከሰሱ፣ ይህንኑ ተግባራቸውን በ፳፻፬ ዓ.ም. በተካሄደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በሪፖርት እንዲያቀርቡ በቀድሞው ፓትርያርክ ትእዛዝ መበረታታቸውን የገለጹና በማቅረባቸውም የተሸለሙ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹው አባ አፈ ወርቅ በኢጃጂ እና ሻምቡ ከተሞች እንዲሁም በሰበታ ቤተ ደናግል ሴት መነኩሲትን በዝሙት በማሳሳት በወለዷቸው ልጆች ምንኵስናቸውን ያዋረዱ፣ እንደ አባ ዮናስም የኦሕዴድም የኦነግም የአባልነት መታወቂያዎች ይዘው ንግዳዊ ፖሊቲካ በማራመድ የሚታወቁ ናቸው፡፡
 • በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት÷ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በተገበረው የሽግግር መዋቅርና ለቀጣይ የለውጥ አመራር ባካሄደው የመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር የአሠራር ጥናት የማኅበረ ቅዱሳን ሞያተኞች ግንባር ቀደም ተሳትፎ በማድረጋቸው ሕገ ወጥ ጥቅማቸው የሚነካባቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳደር ሓላፊዎች የመንግሥትን የአክራሪነት ውንጀላ አመካኝተው ማኅበሩን ለማሸማቀቅ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ነው፤ ፴፪ውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በቅሰቀሳ መድረክነት እየተጠቀሙ ነው፡፡
 • በግንቦት ፳፻፭ ዓ.ም. የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የተጠናው የለው አመራር መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አልፎ ለመላው አህጉረ ስብከት በመነሻ ሞዴልነት የሚጠቀስ እንደኾነ ፓትርያርኩም ረዳት ሊቀ ጳጳሳቸውም መስክረዋል፤ በትውፊታዊውም ይኹን በዘመናዊ ትምህርት ደክመው ተጨባጭ ሞያዊ ክሂል ያላቸው ባለሞያ ሠራተኞችና አገልጋይ ካህናት ሁሉ ትክክለኛ ቦታቸውን የሚያገኙበት፣ አቅማቸውን በቀጣይነት የሚያሳድጉበትና ጥቅማቸውን የሚያረጋግጡበት፣ የምእመናን ገንዘባቸው ከዘረፋ ተጠብቆ በአግባቡ የሚለማበት መኾኑን በመጥቀስ አመስግነዋል፡፡

 • ወቅቱ ሀ/ስብከቱ ጥናቱን (የለውጥ አመራር አስተሳሰብና ተግባሩን) መላው የሀ/ስብከቱ ሠራተኞች፣ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምእመናን በሚገናኙበት የጋራ መድረክ በማቅረብ ጥልቅ ግንዛቤ ለመፍጠርና ለማዳበር የሚዘጋጅበት ነው፡፡ ይህ ኾኖ ሳለ የሀ/ስብከቱየሙስና ኔትወርክ ተቆጣጥረው የኖሩ የጥቂት አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በለውጥ ስም ካህናቱን በማግለልና ቀውስ በመፍጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቆጣጠር ነው›› በሚል ሂደቱን በሚያደናቅፍ አሉታዊ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ (blackmailing strategy) ተጠምደው ይገኛሉ፤ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በማወቅም ይኹን ባለማወቅ የሠሯቸውን አስተዳደራዊ ስሕተቶች በመለጠጥ እንዲሁም የመንግሥትን ‹‹የፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴ›› አጀንዳ በመጠቀም ማኅበረ ቅዱሳንን በጽንፈኛነት ለማስመታት ‹‹የፀረ አክራሪነት ሰልፍና ስብሰባ›› ለመጥራት ተዘጋጅተዋል፡፡
 • የቀድሞው የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩትና ዛሬም በሕገ ቤተ ክርስቲያን ባልተደገፈውና አስፈላጊነትም በሌለው ‹‹የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት›› ስም በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ከትመው የጥፋትና ድለላ (ለጵጵስና ለሚቋምጡ ቆሞሳት) ተግባራቸውን በሚያጧጡፉት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ይታገዛሉ፡፡ ከእኒህ ቀንደኛ የሙስና ጌቶች የኾኑ የአድባራት አስተዳዳሪዎች መካከል÷ ቀድሞ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል አሁን የደብረ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ መንክራት ኃይሌ ኣብርሃ፣ የሲ.ኤም.ሲ፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል አብያተ ክርስቲያን፣ የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን አለቆች ይገኙበታል፡፡

 • ከኀምሳው አህጉረ ስብከት የሚበዙት ማኅበረ ቅዱሳን በተቋማዊ ለውጥ አመራር፣ በቅዱሳት መካናትና አብነት ት/ቤቶች ድጋፍና ክብካቤ፣ በስብከተ ወንጌል መስፋፋትና መጠናከር ያደረገውን አስተዋፅኦ በሪፖርታቸው በማካተት እየገለጹ ባለበት ኹኔታ፣ እንደ መልአከ ገነት አባ ዮሐንስ አፈ ወርቅና መሰሎቻቸው የሚያቀርቡት የውንጀላ ሪፖርት ለአንዳንድ ጥቅመኛ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳደር ሓላፊዎች የቅስቀሳ መሣርያነት መዋሉ የአጠቃላይ ጉባኤውን ተሳታፊዎች እያስቆጣ ነው፤ የስብሰባ አመራሩም እያጠያየቀ ነው፡፡
Advertisements

23 thoughts on “የመንግሥትን የአክራሪነት ፍረጃ ተከትሎ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ለውጥ የሚቃወሙ ጥቅመኞች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚሰነዝሩት ውንጀላ ተጠናክሯል፤ ማኅበሩ ክሥ ለመመሥረት እየተዘጋጀ ነው

 1. geezonline October 16, 2013 at 3:57 am Reply

  “…በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ…” በነፍስ ግድያ? በነፍስ ግድያ? በነፍስ ግድያ?… ደግሞ “ወንጀሎች” ስትሉ ግድያው የብዙ እንጂ የአንድ ነፍስ ብቻ እንዳይደለ ያመለክታል። እንዴት ይዘገንናል!!! እንዴት የሰቀጥጣል!!! እጅግ አሳጥሮ፤ እጅግ አጨማድዶ፤ ቁንጫ እሚያሳክል ከዚኽ የባሰ ምን አለ!!!

  “እናንተስ እንዲኽ ያለውን ገመና ማውጣታችኍ ለምን ነው?” ብየ ልጠይቃችኍ ሳስብ፤ ከውስጤ አንድ ድምፅ ሰማኍ፦ “ማበራቸው ተነካኣ!” የሚል።

  አዬ ኢትዮጵያ፤ አዬ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን! በዚኽ ዘመን ለእናንተ የሚቆም ማን ይኾን???

 2. Anonymous October 16, 2013 at 5:02 am Reply

  Mahiberu ye egziabher new yinoral yashenfal

 3. melaku bogale October 16, 2013 at 6:09 am Reply

  belu enantem qetlu egnam Egziabher eskale dres betekrstiyanen enageleglalen! sayigebachihu weyim leloch yalgebachew mertowachihu yihonal blen slemnasb sle enante entselyalen! abatochachen men honachihu gen? ere yasafral nekso le nekash setachihun eko. ya lebotaw yaletfatachin tweqsun??? yasaznal alemn nqachihual snl lealm sibseba kesesachihun. yihun and qen yigebachihual, mahiberu ye agelglot enji ye lela alemehonun tredutalachihu. yemengst alamam slalgebachihu enji enantenm endih slalchihu ayishomem ayakebrem egnanm matfat ayichlem. gen eski asbut ke ena entna gar tesebsbachihu slebetekrstiyan teru meftehie tamtalachihu blen antebkim. lemangnawem gubayeachinen be menfeskidus merinet enji be ….lela sew merten betekrstiyanen slemantekim asbubet. yet mechie lemn endet lema menblen … ennager blachihu asbu!!!!! tanash wendamachihu

 4. mulushewa October 16, 2013 at 8:28 am Reply

  ዉድ የሐራ ጸሀፊ
  1. እውነት በተጸውኦ ስምህ ቢሆን ይህን ጽሁፍ ታወጣው ነበር???
  2. ለምን ቀድመህ አልነገርከንም ወይስ ሰዎቹ ማህበሩን እስካልነኩ ድረስ በቤ/ክርስቲያን ውስጥ እንደፈለጉ ቢሆኑ ላንተ ግድ አይሰጥህም???
  3. አሁንስ ዕዚህ ከመለጠፍ ለምን ለሲኖዶስ አታቀርቡትም???
  4. ጽሁፉን አሁን ማውጣት አላማው ምንድን ነው???
  5. አድርገዋልስ ቢባል የተከሳሾችን ሀጢዓት መዘርዘር በማህበሩ ላይ ያቀረቡትን ክስ ሀሰት ያደርገዋል???
  6. በዚህ ዐይነት ግለሰቦችን ዒላማ ያደረገ ዒሞራላዊ መከላከል ማህበሩ ተጠቃሚ ይሆናል???
  7. በሌሎች ላይ በእናንተው የሚቀርበው ካህናትን በማጣጣል ምእመኑ በካህናት ላይ አመኔታ እንዲያጣ አድርገዋል የሚል ክስ ለእናንተ ሲሆን እንዴት ነው የሚተረጎመው???
  8. ክስ ክስ ትላላችሁ ለመሆኑ ማህበሩ ራሱን ችሎ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል የህግ ሰውነት(legal personality) አለውን???
  9. ስጋውያን ተቁዋማት አንኩዋ የመላእክት ስብስብ አይደለንም እያሉ ማህበሩ ግን አንድም ቀን ስለአባላቱ (ያውም የበዙት ወጣቶች ሁነው) አንዳንድ ድክመቶች እንኩዋ ለመናገር ለምን አንደበቱ ይያዛል???
  10. ማህበሩ እና ሀራ ብሎግ ያላቸው ግንኙነት ምንድን ነው???
  11. ባላችሁ መረጃ ማህበሩ የሃራ ዘገባዎች ይገልጹኛል ብሎ ያምናል???
  የግቢ ጉባኤን ይጠብቅልን!!!!!

 5. Anonymous October 16, 2013 at 8:54 am Reply

  በዚህ አይነት ከመናፍቃኖች በምን ተሸላላችሁ? እባካችሁ አሁንኑ አጥፉት፡፡

 6. Anonymous October 16, 2013 at 9:20 am Reply

  አሁንስ በቤ/ክ ውስጥ ያለው ውግያ የጨበጣ ደረጃ ላይ የደረሰ መሰለኝ፡፡…ያሳዝናል፡ ያሳዝናል፡ ያሳዝናል፡….ከዚህ ውጪ ምንም ማለት አልችልም፡፡

 7. Anonymous October 16, 2013 at 9:47 am Reply

  little bit personal attack, after all I will no more trust any monk living in Addis and other little towns.

 8. Anonymous October 16, 2013 at 12:27 pm Reply

  ይህ ክአናተ ኣይጠበቅም ። ክፍን በ ክፉ ምመለስ የለብንም
  ስለ አውነት ቢዙ ፈተና ይደርስባቹሃል ግን ክፍን በ ክፉ ምመለስ የለባቹም የ ኣባቶቹን ገመና መድረክ ላይ ማውጣት ግን ኣሳፋሪ ነው
  ህማኖታችንም አንዲ ኣታስምርም
  ለሁላቺም ልብ ይስጠን

 9. ms October 16, 2013 at 12:56 pm Reply

  ማሕበሩ ኣክራሪ ኣይደለም ሰው ሲገድል እስካሁን ኣላየሁትም ነገር ግን ኣንድ መካድ የሌለበት ሓቅ ኣለ! ማኅበሩ ከሃይማኖታዊ ተልእኮው ይልቅ ፖሎቲከኝነቱ ያመዝናል ኣብዛኛው ኣመራሩ የትምክህተኛው ኀይል ኣቀንቃኞችና ደጋፊዎች ናቸው! ግን ለምን? ቤተክርስትያኒቱ እኮ የትምክህተኛውም የጠባቡም መድረክ መሆን የለባትም! ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠው ኣደራና መመርያ ቸል ብሎታል! ለቤተ ክርስትያኒቱ ብዙ ኣገልግሎት ሊሰጥ እየቻለ በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ መዘባረቅ ቢያቆም ኖሮ እንዴት መልካም ነበር! ኣባላት ሆይ ማኅበራችሁን ኣስተካክሉ! ኣሁንም ግዜው ገና ነው ኣልረፈደም! እኔ በግሌ በማኅበሩ ኣገልግሎት የምደግፈው ነገር ቢኖርም እንደዚህ በፖሎቲከኞች በቀላሉ የሚጠለፍ ከሆነ ምን ግን ይደረጋል! ኣዬዬዬዬ!!!!!

  • Anonymous June 1, 2014 at 9:01 am Reply

   Dear ms can u tell us any politics done by by Mk…Please tell us one. You should be evidence based…otherwise u will like ur TPLF comrades

 10. KAHN October 16, 2013 at 1:46 pm Reply

  ሂዳችሁ ሂዳችሁ አበሳውን ሁሉ የአንድ ብሄር ተወላጆች ላይ እየደፈደፋችሁ እንዴት ተቁዋማዊ ለውጥ እንደሚመጣ እሱ ይወቀው. የሃይሌ በደል ምንድን ነው የብሄረ ጽጌ ማርያምን ህንጻ አሰፈጽሞ ለብ/ገብርኤል ባጭር ጊዜ ዘመናዊ ት/ቤት ማሰራቱና በየሄደበት ለካህናት ኑሮ መሻሻል መስራቱ ነው ?? የጸጋየስ ሰ/ት/ቤቶች ኦዲት መደረግ አለባቸው ማለቱና ዘረኝነት የሌለበት መሆኑ ነው?? የኤልያስስ ተምሮ መገኘቱ ነው?? ምናልባት የእነዚህ ሁሉ ዋና በደል እናንተ በተወለዳችሁበት አካባቢ አለመወለዳቸው ይሆን????????
  ይሄ የምትሉት ተቁዋማዊ ለውጥ እውነት በናንተ የተጠና ከሆነ የገርመኛል. ሲኖዶስም በማህበሩ የሚቀርቡለትን ጥናቶች የማህበሩ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ስለመሆን አለመሆናቸው በጥልቀት ሊያጠነው ይገባል ማለት ነው.እንዲያውም አሁን ካለው የማህበሩ ቡድን ጠቀስ እና ቢዝነስ ተኮር እንቅስቃሴ አንጻር ቅ/ሲኖዶስ ማህበሩ ነጻ የሆነ የማማከር አገልግሎት ይሰጠኛል ብሎ ባይጠብቅ ይሻላል.
  ተቁዋማዊ ለውጥ ይምጣ ከተባለ ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ገለልተኛ ሙያተኞችን አስጠንቶ በጥናቱ ላይ ሲኖዶስ ከመከረ በሁዋላ ከህገጋተ-ቤ/ክ አንጻር የራሱን አስተያየት ጨምሮበት ተግባራዊ ቢያደርግ ይሻላል. ያለበለዚያ ማህበሩ የቤ/ክህነቱ አካል ሆኖ እያለ እና ለችግሩ መወሳሰብም የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለበት እየታማ ገለልተኛ መፍትሄ እንዲያቀርብ መጠበቅ የዋህነት ነው. ለዚህም ነው አሁን አሁን የካህትን እሮሮ ከማዳመጥ ይልቅ ከአፍቃሬ ማህበሩ ሰ/ተማሪዎች ጋር ሆነው በትምክህት እየተሽከረከሩ ካህናትን የሚያስለቅሱ የማህበሩ አጎብዳጅ አለቆች የበዙት. ሂዱ ጎፋ ገብርኤልና ላፍቶ ሚካኤል
  ለመሆኑ የምትሉት ተቁዋማዊ ለውጥ መቼ በተደረገ ጥናት ነው ሞዴል ይሆናል የተባለው. ለውጡ የሙስናውን ኪስ እና ሰንሰለት እንዲሁም የካህናትን ለቅሶ በይግባኝ ውጣ ውረድ ከማራዘም በቀር ያየነው ለውጥ የለም. ጳጳሳትንና ትልልቅ ባለስልጣናትን እስከመቆጣጠር የደረሱ አለቆች አንድ የክ/ከ/ቤ/ክህነት ሃላፊ መቆጣጠር ያቅታቸዋል ማለት ዘበት ነው. እያየን ያለውም ይኸው ስለሆነ ተፈትኖ የወደቀውን ጥናት አቡዋራ ለማራገፍ መጣራችሁ አይገባኝም.
  አሁን ባለው ሁኔታ ማህበሩ በግቢ ጉባኤና በይፋዊ ሚዲያው አካባቢ የሚሰራው ስራ ለቤ/ክርስቲያኑዋ ጠቃሚ መሆኑ፣ገዳማትንና የቆሎ ት/ቤቶችን ለመርዳት የሚያደርገው በጎ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑ እንዳለ ሆኖ በሌሎች ጉዳዮች ግን ከቤ/ክ ህጋዊ መዋቅር ቀድሞ አለሁ አለሁ ማለቱን እንዲያቆም ከቅ/ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ ሊሰጠው ይገባል(በመንግስት ቁዋንቁዋ ቀይ መስመር ይባላል መሰለኝ). እዩኝ እዩኝ ያለች ማሽላ እጣዋ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ!!!!!

 11. Anonymous October 16, 2013 at 2:08 pm Reply

  በተለያዩ መድረኮች ክስ ሲቀርብበት ማህበሩ ለምን ምላሽ አይስጥም? MK is represented in this meeting. why are the representatives not defending themselves? If not we continue to suspect there is something behind

 12. wabel October 16, 2013 at 2:26 pm Reply

  Koye yalegebaje negere kepapasate selemeindenewen yaltegeba or yalbesele semytawint yemitayew. Minm bihon minm biyatefa abate yegesesale enji byesebsebaw seme ayatefam.Erre ABATOCH SELEMENGAW HEZEB ASEBUUUU

 13. wabel October 16, 2013 at 2:29 pm Reply

  KOYE ABATOCH SELEHEZBU KALTECHENKU HALAFINTACHEW MINDEN NEWE???
  Drgmo KISE YeDIYABLOS ENDEHONE ALNEGERACHHUNM?Ere yezich bytekeresetiyanen hazen anabzabat!

 14. Anonymous October 16, 2013 at 6:39 pm Reply

  ይኽቺ ምድረ መናፍቅ መንጫጫት ጀመረች አሁን ሳዊሮስ ዛላውን ሲያዩት መንፈሳዊ አባት ይመስላል; መከስስ ብቻ ሳይሆን የበከተ ታሪኩ ገና ገና ገና መች ተነካና ይሄ ጎረምሳ መግቢያውን ይፈልግ ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊ አባቶች ቦታ እንጅ የወጠጤ መፈንጫ አይደለችም

 15. yedingel October 16, 2013 at 8:36 pm Reply

  Is it really will make you happy exposing some one’s sin(if it is true) this what you guys are doing. I think you guys are menafikan. You believe in money also. Please remove this post from facebook.

 16. Yonatan October 17, 2013 at 12:34 am Reply

  I think this document is distributed by other religious follower, until i get exact information i don’t believe. please all orthodox religious follower don’t hate our religious.
  I am sorry!!!!!!!!!!!!!

 17. amage October 18, 2013 at 6:32 am Reply

  enene yemegrmge manwe tikikle? manwe lebtekirstyane yemeyasibilati? mikiniyatumi enanitem ewnete lebetkirstyane ena lehayimanotachu ketkorkorachu edzhi ayinte abatochin bicha sayihoni hayimanotachinin chmiro yemesdibi neger manim bemeyaywe page laye post madirge balitegeba ensu atiftwe lehoni yichilali gin ensun mastemarina memles yalbin bezhi mengedi ayimeslgim ega tesadiben lesdabe hayimanotachinin bansetwe tiru new! slzhi manwe tikikle?
  hulachme ersachun mermiru wedswe kemhedachu befte!

 18. Endale Seifu October 18, 2013 at 7:50 am Reply

  I think all the allegations are true! There have always been enemies of the Church! Not alone Mahibere-Kidusan, Our Lord Jesus Christ received sufferings, persecutions and crucifixion. There are followers of Demon, which is the father of false, hatred. I think, God knows, it is orchestrated by those whose evil deeds were disclosed. They may be getting funds from protestant camps. We know who you are. Mahibere-Kidusan was founded by the will of God. What Mahibere-Kidusan doing is clear and it is for the Church. But, the enemies of Mahibere-Kidusan are children of demon and Jews. May God rebuke you, devil!
  Endale Seifu

 19. Boru Dub October 18, 2013 at 12:58 pm Reply

  I think like yonatan if not “mahibre qdusal” also don’t have a right to post like this information because it expose unwanted information for public. Every body have a problem including “mahibre qdusan” that not mean acceptable but it should be reported only for intended people/representative only. Egziyabhere betkrestiynachnena Ethiopian yetbqat.

 20. ms February 6, 2014 at 1:36 pm Reply

  ወይኔ ሓራዎች ስታስጠሉሉሉሉሉ!!!!!!!!!! ደባሪዎች! ኣሁን እናንተ የቤተክርስትያን ወገኖች ልትባሉ ነውን የሆናችሁ ወሮበላዎች ነገር ናችሁ በእውነት!

  • Anonymous January 14, 2016 at 9:09 am Reply

   Bilu bilu yidekmalu enji mahberu endehone egziabher yitebkewal sintegna mukerachew new……..ahe ahe alu emama …..wegebachewun asrew …..azenkulachu MK foreever,!!!!!!!

 21. Tiruwork Abera February 11, 2016 at 7:39 am Reply

  Egziwo Abetu Amelak Hoye Ewnetegna Fered Beante Zend Bicha New Yalew! Yehechin Bedemhe Yemeseretkatn Betekrstiyan Tebike! Lehulum Lebona Setachew! Anete Yemibejewn Ameta!!! Abetu Yemiserutn Ayawekum Ena Yeker Belachew Lehulum Lebonana Masetawal Setachew! Misekinun Me emenun Tebik!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: