የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባና የመሻሻል ጅምሮቹ

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ÷ በጉባኤው አዘጋጆችና ተሳታፊዎች የተለመደ አነጋገር÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእግር እስከ ራሷ በአንድ አዳራሽ የምትገኝበት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ዓመታዊ ስብሰባው÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ነው፡፡

ይኸውም ቤተ ክርስቲያናችን በውጭ እና በሀገር ውስጥ ካሏት የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መንፈሳውያን አስተዳደር ጉባኤያት ተመርጠው የተወከሉ ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ በየአህጉረ ስብከቱ በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የተመደቡት ሊቃነ ጳጳሳት በጉባኤው አባልነት በአንድነት የሚገናኙበት መድረክ በመኾኑ ነው፡፡ በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ቃለ ዐዋዲ ደንብ አንቀጽ ፵፯ መሠረት የጉባኤው ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሲኾኑ ዓመታዊ ስብሰባውን በዋናነት የሚመሩት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ደግሞ የአጠቃላይ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር ናቸው፡፡

Lique Maemeran Fantahun Muche

ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ
የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ
የቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ ሀብቶች ምእመናን መኾናቸው በውል የታመነ ነው፡፡ ዋናው ትኩረታችን ከገንዘብ ይልቅ በገንዘብ ባለቤቶች ምእመናን ላይ መኾን ይኖርበታል፡፡ አህጉረ ስብከት ሰውን በማልማት በኩል ተግተው ሊሠሩ ይገባል፡፡

ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ተጀምሮ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከተጀመረበት ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. አንሥቶ ለ፴፪ ጊዜ የተደረገ ነው፡፡ የማደራጃ መምሪያው ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ እንደሚገልጹት፣ የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ቀጥሎ የሚታይ ነው፡፡

ይኸውም ከመላው ዓለም የሚሰባሰቡ የቤተ ክርስቲያናችን ሓላፊዎችና ተወካዮች በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ተወያይተው የውሳኔ ሐሳብ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀርቡበታል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤም ከአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የቀረቡለትን የውሳኔ ሐሳቦች የሚሻሻሉትን አሻሽሎ ካጸደቀ በኋላ የዓመቱ የአህጉረ ስብከት የሥራ መመሪያ ይኾናል፡፡ ስለዚህም ዐቢይ ጉባኤው÷ ‹‹በዓመቱ ውስጥ የተሠሩ ሥራዎች የምንገመግምበት፣ አንዱ ሀ/ስብከት ከሌላው የሚማርበት፣ ከድክመታችን ተምረን ጠንካራ ጎናችንን አጎልብተን ለቀጣይ ሥራ የምንዘጋጅበት ነው፡፡››

የመምሪያው ሓላፊ ይህን ይበሉ እንጂ የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ለግምገማ፣ ለመማማርና ለቀጣይ ሥራ በሚያነቃና በሚያተጋ ደረጃ እየተካሄደ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ የስብሰባው ሂደት ከውይይት ይልቅ ሪፖርቶችን ማድመጥ ይጫነዋል፡፡ ኀምሳ አህጉረ ስብከት፣ መመሪያዎችና ድርጅቶች በአማካይ ለዐሥር ደቂቃ በማራቶን ይሉት ንግግር የሚያቀርቧቸውን ሪፖርቶች ማዳመጥ የአጠቃላይ ጉባኤውን ተሳታፊዎች አያፈዝም፣ አያደነግዝም ማለት አይቻልም፡፡

አንዳንድ ሪፖርቶች የያዟቸው ሐቆች አጠያያቂነት እንደተጠበቀ ኾኖ በሪፖርቶቹ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ጉዳዮች መርጦና ሌሎች አንገብጋቢ አጀንዳዎችን ለይቶመወያየት በቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ችግሮች ላይ ጠንካራና ጥልቅ አቋም ለመያዝ ዓመታዊ ስብሰባው የሚሰጠውንም ዕድል አለመጠቀምም ነውና እንዲታሰብበት አበክረው የሚያሳስቡ ድምፆች በተደጋጋሚ ተሰምተዋል፡፡

Participants of the 32nd SGGA 02

የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ
በመሪነት ውስጥ ኃይልና ሥልጣን (power and authority) መሟላት አለበት፤. . . መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ሠርከ ኅብስት ችለው ለምን የአቅም ግንባታ ሥልጠና አይሰጡም?. . .የሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ ሲጸድቅ የጡረተኞች ኹኔታ ግን ተዘንግቷል፤ የጡረታን ገንዘብ አህጉረ ስብከት እንዲያስተዳድሩት ሥልጣን ቢሰጣቸው?

በዚህ ረገድ የወቅቱ የሰበካ ጉባኤው ማደራጃ መምሪያ አመራር ዘንድሮ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የያዘው፣ በአጠቃላይ ጉባኤው አራተኛ ቀን ውሎ÷ ነገ፣ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.÷ የሚጀመረውና በዘመናዊ ሥራ አመራር፤ በዕቅድ፣ ክትትል፣ ቁጥጥርና ግምገማ፣ በአነስተኛና ከፍተኛ ሥራ ፈጠራ እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት ላይ የሚያተኩሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ወቅቱን እየዋጁ መቀጠል ያለባቸው ናቸው፡፡ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም የመነጋገርያ ርእሶችን መርጦ የጉባኤውን አባላት በቡድን በመክፈል ማወያየትና የውይይቱን ውጤት በመድረክ አቅርቦ የጋራ አቋምና ግንዛቤ መጨበጥ መበረታታት ያለበት ነው፡፡ በዚህም መሠረት ከነገ በስቲያ ዐርብ በአጠቃላይ ጉባኤው አምስተኛ ቀን ውሎ በ12 ቡድኖች ተከፍሎ በሚካሄደው የቡድን ውይይት፡-

 • የቤተ ክርስቲያናችን የስብከተ ወንጌል ተግዳሮቶች፣
 • የምእመናን ምዝገ ለቤተ ክርስቲያን ዕድገትና ልማት ያለው ጠቀሜታ፣
 • ማእከላዊ የፋይናንስ አስተዳደር ለቤተ ክርስቲያን ያለው ጠቀሜታና ጉዳት፣
 • የተቀናጀ የልማት እንቅስቃሴ ለቤተ ክርስቲያን ዕድገትና ለካህናት ኑሮ መሻሻል፣
 • የዕቅድ፣ ክትትል፣ ግምገማና ቁጥጥር አገልግሎት ጠቀሜታና የማድረጊያ መንገዶች፣
 • ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሐዊነት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር እንዴት ተግባራዊ ይደረግ፣
 • የወጥ ሥርዐተ ትምህርት አስፈላጊነት ለሰንበት ት/ቤቶች፣
 • ወጥ ሥርዐተ ትምህርት ለአብነት ት/ቤቶች፣ ብሔረሰቦችን ለአብነት ትምህርት ማብቃት፣
 • ለቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ት/ቤቶች ወጥ ሥርዐተ ትምህርትና የሰው ኃይል አደረጃጀት
 • ቅርሶችን ከዘረፋና ጉዳት ማዳን፣ የቤተ ክርስቲያንን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
 • በገዳማዊ ሕይወትና በምንኵስና አሰጣጥ ያሉ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣
 • መንፈሳዊ ኮሌጆችንና የካህናት ማሠልጠኛዎችን እንዴት እናስፋፋ

የሚሉ አርእስተ ጉዳዮች መካተታቸው ታላቅ ርምጃና መሻሻል ነው፡፡ ቁም ነገሩ አንዳንዶቹ ርእሰ ጉዳዮች በቀጥታ ይኹን በተዘዋዋሪ በድጋሚ የተነሡ እንደመኾናቸው በሂደት የደረሱበትን ደረጃ ከመገምገም ይልቅ ከአምናው በተመሳሳይ አኳኋን መቅረባቸው በአፈጻጸም በኩል ድክመት እንዳለ፣ ይህም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የአስተሳሰብ ለውጥ መጀመር እንዳለበት አመልካች ነው፡፡

His Grace Abune Elsa on 32 SGGA

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ለሥራ ሁሉ ሂደት አለው፤ ለመልካም አስተዳደርም ጅመራ አለው፡፡ ጥያቄ ያስፈራን ነበር፡፡ በዚህ ዓመታዊ ስብሰባ ግን አጠቃላይ ጉባኤው ጥያቄ ይቅርብለት መባሉ የመልካም አስተዳደሩ ፊደሉ (ጅምሩ) ነውና በዚሁ ይቀጥል፡፡

የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊ እንዳሉት፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ቀጥሎ ባለው ሥልጣኑ ሪፖርት አድምጦ፣ የአቋም መግለጫ አውጥቶና የጋራ ውሳኔ አሳልፎ ከመለያየት ባሻገር የመግለጫውን ተሰሚነትና የውሳኔውን ተፈጻሚነት የሚያረጋግጥበትና የሚቆጣጠርበት ኃይልና ችሎታ (በርግጥም ለቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ግብአት ስለመኾናቸው) እንዲኖረው ሊደረግ ይገባል፡፡

ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ባቀረቡት የ፳፻፭ ዓ.ም. በጀት ዓመት ሪፖርት በጥያቄና አስተያየት ተጀምሮ በአጭሩ በተቋጨው ውይይት የመልካም አስተዳደርና የሀብት ብክነት ችግሮች ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንደሚነሡና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጎልተው እንደሚታዩ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መነገሩና መታመኑ የለውጡ ተስፋ ነው፡፡ ለውጡ በተስፋና በተወሰነ መልኩም በጅምር ላይ ብቻ ያለ መኾኑ ደግሞ የዐቢይ ጉባኤው ተሳታፊዎች በምሳሌነት የጠቀሷቸው (የቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሻሻል፣ ለተወካዮች ምክር ቤት የተመራው የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ ሕግ፣ የማእከላዊ በጀት አስተዳደር፣ የአብነት ት/ቤቶች ድጎማ) የመሳሰሉት እንዲጓተቱና በሚያመረቃ ደረጃ እንዳይፈጸሙ ምክንያት መኾናቸው ሊያሳስብ ይገባል፡፡

Wag Himera Hagere Sibket 32nd SGGA

የዋግ ኽምራ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የምናወጣው ሕግ በመንግሥት በኩል ታውቆ ጉዳያችንን ማስፈጸም አልተቻለም፡፡ ለምን እንዲሠራ አይደረግም? ፖሊስና ፍርድ ቤት ከሃይማኖት አያገባንም ብለው እምቢ ይላሉ፡፡. . .በጀት በማእከላዊነት ይግባ ተብሎ በየዓመቱ ይነገራል፤ ዛሬም ተነግሯል፤ ነገር ግን በጀታችን ማእከላዊ ኾኖ እኩል መኾን አልተቻለም፡፡

የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ አዘጋጆች ለ፴፪ው ዓመታዊ ስብሰባ ባስተላለፉት መልእክት፣ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ተደራጅተው የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር በሚመሩበት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ዋናው ትኩረት ከገንዘብ ይልቅ የገንዘቡ ባለቤቶች የኾኑ ምእመናንን በብዛትና በጥራት ማፍራት ላይ ሊኾን ይገባል፡፡ ‹‹የጊዜው ኹኔታ ፈቅዶልን እኛም በትጋት ሠርተን የቤተ ክርስቲያን ገቢ በብዙ እንዲያፈራ አድርገናል፡፡ ይህ እሰኘየኹ የሚያሰኝ ቢኾንም በምእመናን በኩልስ ትርፍ ተገኝቷል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሊመለስ የሚገባው ነው፡፡ ምእመናንን በማብዛት በኩል የተሠራው ሥራ አመርቂ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡ ክርስቶስ በአደራ የሰጠንን በጎች ከተኩላ መጠበቅና እንዲበዙ ማድረግ ክህነታዊ ግዴታችንና ሥራችን ነው፡፡ የምእመናን ቁጥር እየቀነሰ ከዓመት ዓመት ገቢያችን አድጓል ብንል ቤታችንን በድቡሽት ላይ የሠራን ያስመስልብናል፡፡

በገቢ በኩል ቤተ ክርስቲያን ከሰበካ ጉባኤ አስተዋፅኦ ይልቅ በልማት ማደግ እንዳለባት ታምኖ እንቅስቃሴዎች ከተጀመሩ ቆይተዋል፡፡ ሥራዎች በተደራጀ መልኩ ባይከናወኑም ይደጉ ሊባሉ የሚችሉ የልማት ሥራዎች በቤተ ክርስቲያን ዐጸድ እየታዩ ናቸው፡፡ አሁንም ግን ጥላ ዘቅዝቆና ሥዕለ አድኅኖ ይዞ በመንገድ ላይ ከመለመን አልዳንም፡፡ ይህን ለማስቀረት አህጉረ ስብከት ሰውን በማልማት በኩል ተግተው ሊሠሩ ይገባል፡፡ ለዚህም በመሻሻል ጅምርና ሂደት ላይ ከሚገኘው የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ የሚሰነቁት መረጃዎችና ግንዛቤዎች፣ ተመክሮዎችና ውሳኔዎች ትልቅ አቅሞች እንደሚኾኑ ይታመናል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባና የመሻሻል ጅምሮቹ

 1. zelalem October 17, 2013 at 12:01 pm Reply

  ይህ መንግስት በቤተክርስያን ላይ የከፈተው ዘመቻ ማንታገስበት ደረጃ ደርሶል

 2. Anonymous October 19, 2013 at 4:09 am Reply

  The first enemy of the church are those who working for the destruction of the church having external network with government and other religions only for their own interest.Tsetse are the real enemies of the church. No excuse for their untruthfulness.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: