ፓትርያርኩ÷ አቡነ ጢሞቴዎስን በመደገፍ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ ሻሩ

 • ቋሚ ሲኖዶሱ የሚያጤነውን የአካዳሚክና አስተዳደር ዲኖች ሹመት አጽድቀዋል
 • የመምህራኑ የመብራትና ውኃ አገልግሎት ከተቋረጠ አንድ ወር ሊሞላው ነው
 • ደመወዛቸው እንደታገደ ነ
 • ከቅ/ሲኖዶሱ ቁጥጥር የወጡት አቡነ ጢሞቴዎስ ‹‹በውንብድና›› እየተተቹ ነው
 • ሙስናን መዋጋት በተግባራዊ ርምጃ ወይስ በቃላዊ ዕወጃ!?

ከሥልጣናቸው ተገልለው እንዲቆዩ በተወሰነባቸው ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እየተመራ ያለው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር÷ በሕንጻ እድሳት አመካኝቶ በኮሌጁ ቅጽር የሚኖሩ መምህራን ቤቶቻቸውን ለቀው እንዲወጡ ያስተላለፈው ትእዛዝና ቤቶቹን ካለቀቃችኹ በሚል በመምህራኑ ደመወዝ ላይ የጣለው እገዳ ውድቅ ተደርጎ፣ መምህራኑ÷ በመኖርያ ቤቶቹ መገልገላቸውን እንዲቀጥሉ፣ የታገደው ደመወዛቸው እንዲለቀቅና በቀጣይም በአግባቡ እንዲከፍል በቋሚ ቅ/ሲኖዶስ የታዘዘበት ውሳኔ በፓትርያርኩ ተሻረ፡፡

ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የጻፉት ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ስለ ኮሌጁ በተላለፉ ውሳኔዎች ላይ ‹‹አስተዳደራዊ እርምት መውሰድ›› ማስፈለጉን ይገልጻል፡፡

ፓትርያርኩ ራሳቸው በሰብሳቢነት በመሩት የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔ የተላለፈባቸው ኮሌጁን የተመለከቱ አጀንዳዎች፣ ‹‹ሐቀኝነት የጎደላቸው›› እና ‹‹በቃል ብቻ የቀረቡ›› እንደነበሩ ደብዳቤው ተችቷል፤ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ መሠረት በማድረግም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ለኮሌጁ የተጻፈውና የኮሌጁ አስተዳደር ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና የወሰዳቸው አስተዳደራዊ ርምጃዎች ውድቅ የተደረገበት ደብዳቤ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተሻረ መኾኑን አስታውቋል፡፡

Teachers of the Holy Trinity Theological College

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህራን በከፊል

‹‹የተጠናከረ ማስረጃ እስኪቀርብ›› በሚል በፓትርያርኩ በተወሰደ ‹‹አስተዳደራዊ እርምት›› የተሻሩት የቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔዎች በደብዳቤው ላይ በግልጽ ተዘርዝረው ባይጠቀሱም÷ በዋናነት በቋሚ ሲኖዶሱ አባላት የእምነት ርቱዕነት ጥያቄ የተነሣባቸው አዲሶቹ የአስተዳደርና አካዳሚክ ዲኖች ሹመት እንዲጤን የተደረሰበትን ስምምነት እንደሚመለከት ተገልጧል፡፡ ከዚህም ጋራ መምህራኑ የኮሌጁን መኖርያ ቤት ለመልቀቅ እንዳይገደዱና በምትኩ በአስተዳደሩ የተቆረጠባቸው የመብራትና ውኃ አገልግሎት እንዲሟላላቸውና የታገደባቸው የነሐሴ ወር ደመወዝ ተለቆላቸው በቀጣይም በአግባቡ እንዲከፈላቸው የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚያካትት ተዘግቧል፡፡

የኮሌጁ አስተዳደር÷ ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በመሻር በጽ/ቤታቸው በኩል የጻፉትንና በዋና ሥራ አስኪያጁ የተመራለትን ደብዳቤ በመጠቀም መምህራኑና ሠራተኞቹ እስከ ኻያ ዓመት ያህል የቆዩበትን የኮሌጁን መኖርያ ቤቶች ያለአንዳች የኪራይ አበል ለቀው እንዲወጡ፣ ለቀው የማይወጡ ከኾነ በደመወዛቸው ላይ የተጣለው እገዳ እንደሚቀጥል መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በድጋሚ በቅጽር ግቢው በለጠፈው ማስታወቂያ ማሳሰቡ ታውቋል፡፡

ማሳሰቢያው÷ ከቅ/ሲኖዶስ ተጠያቂነት ውጭ የኾነውና ከፓትርያርኩ ጋራ ባላቸው ግላዊ ግንኙነት መደገፉን የቀጠለው የአቡነ ጢሞቴዎስ የጉልበት አስተዳደር አስከፊ መገለጫ ነው ያሉት መምህራኑ እንደ ማሳሰቢያው ቃል ከቤታቸው አልወጡም፤ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ፴ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ጀምሮ በአስተዳደሩ የተቆረጠባቸው የመብራትና የውኃ አገልግሎት እንደተስተጓጎለ አንደኛ ወሩን ሊያስቆጥር ተቃርቧል፡፡

በአካላዊ የመስማትና ማየት ችሎታ ውስንነትና በአስተዳደራቸው አስከፊ ብልሹነት ምክንያት ለ14 ዓመታት በኮሌጁ ከነበራቸው የበላይ ሓላፊነት ሥልጣን በቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ የተገለሉት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ÷ ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ በቀጥታ በመፃረር የጻፉትን የመሻርያ ደብዳቤ፣ ከሥልጣናቸው ከተገለሉ በኋላ አላግባብ ለወሰዷቸው የቅጥር፣ ዝውውርና ስንብት ርምጃዎች ሕጋዊ ልባስ ለመስጠትም ጭምር እየተጠቀሙበት እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

በፓትርያርኩ ተግባር በእጅጉ ማዘናቸው የተገለጸው የቋሚ ሲኖዶስ አባላት የመምህራኑ የማያቋርጥ አቤቱታ እየቀረበላቸው መኾኑ ተነግሯል፡፡ አባላቱ አቡነ ጢሞቴዎስን በተመለከቱ ጉዳዮች ልዩ ጥንቃቄ በሚያደርጉት ርእሰ መንበር አቡነ ማትያስ አኳኋን መመረራቸውንና አቡነ ጢሞቴዎስንም በውንብድና አስተዳደር በመተቸት ላይ እንደሚገኙም ተዘግቧል፡፡

ኹኔታው እንደ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ርእሰ አንቀጽ አባባል፣ ሙስናን መዋጋት በተግባራዊ ርምጃ ወይስ በቃላዊ ዕወጃ የሚያሰኝ ነው፡፡

Advertisements

17 thoughts on “ፓትርያርኩ÷ አቡነ ጢሞቴዎስን በመደገፍ የቋሚ ሲኖዶሱን ውሳኔ ሻሩ

 1. Anonymous October 2, 2013 at 12:30 am Reply

  ወይ ጉድ ዘንድሮ

 2. Anonymous October 2, 2013 at 7:56 am Reply

  lememeheranu ena leserategochu yedengel lig geta yawkal kuami senodos yalu abatochin gen adenkalehu ferd siyakenu ayichalhu gin min yadergal ferd yemiyatamimu degmo alu asteyayet mestet yemifelegew neger binor abatoch beandenet bemetebaber musenan zereghneten lelochinem chigeroch mewagat yenorebachewal musena beeweja weyes bermeja

 3. Anonymous October 2, 2013 at 7:58 am Reply

  yasasinal yequami senodos abalatin adenkalhu ahunim lewinet bertu

 4. Anonymous October 2, 2013 at 9:08 am Reply

  “ሐቀኝነት የጎደላቸው” ለተባሉ ጉዳዮች ውሳኔ የሰጡ አባቶችስ በተዘዋዋሪ ምን ተባሉ ማለት ነው ፣ ከሀቅ የተፋቱ ወይስ ሃቅ የሆነና ያልሆነ የማይለዩ?

 5. tt October 2, 2013 at 9:11 am Reply

  ‹‹ሐቀኝነት የጎደላቸው››ለተባሉ ጉዳዮች ውሳኔ የሰጡ አባቶችስ በተዘዋዋሪ ምን ተባሉ ማለት ነው ፣ ከሀቅ የተፋቱ ወይስ ሃቅ የሆነና ያልሆነ የማይለዩ?

 6. Anonymous October 2, 2013 at 10:50 am Reply

  ብዙሃኑ ተስማምተው ያሳለፉትን ውሳኔ መሻር አምባገነንነት አይሆንም? ይህ የሚሆን ከሆነ ታዲያ ሲኖዶሱ ለምን አስፈለገ? የሀይማኖት መሪዎች እንዲህ ከሆኑ የሌሎቹ ታዲያ ምን ይደንቀናል? በጣም ያሳዝናል!

 7. Anonymous October 2, 2013 at 11:35 am Reply

  it is very difficult to manage the church that not to be a mediator. I have to see that the patriarch could not administer the Holy Synod.Because he decide with the holy synod ,at the same time to refute the decision of the holy synod. moreover, he has a great relationship with abba timotiwos to have hidden relation more than 18 years. Due to this relation the patriarch couldnot do together with the holysynod. This is not good behavior .finally I appreciate The holy synods fathers to have strong relationship. May our Lord God to give us peace.

 8. Mengaw October 2, 2013 at 11:37 am Reply

  ይህ ልዩነት ተፈጥሮ ከሆነ ያሳዝናል ግን እናንተን እንዴት ለመናቹ ይህ ኮሌጅ የመናፍቃን መፍለቅያ ነው ይዘጋ ስትሉት እንዳልነበር አሁን የናንተ አባላት እየበዙበት ሲሄዱ የፃድቃን ከተማ/መንደር/ ትሉት ጀመር መ/ር አንዱዓለም የካቶሊክ ትምህርት አንደሚያስተምር እያውቅነው አሁን ታመሰግኑታላቹ ያም ሆነ ይህ የአባቶች መከፋፈል ለቤ/ን አይጠቅምም

  • Anonymous October 2, 2013 at 1:36 pm Reply

   አንተ ቱልቱላ ለምን የካቶሊክ ሲያስተምር ዝም አልክ ?

 9. Anonymous October 2, 2013 at 12:23 pm Reply

  besidesteghaw patriarich yeastedader lewt yimetal teblo bitasebem lewt limeta alchalem endewem yebase neger yemigermew kuami senodos yewesenewin wesane abba pawlos shirew enkuan ayawkum yemasfetsem chiger lalhone besteker yahunu gin ejig sinodosun ymitsarer neger gena kewedihu bemesrat lay nachew. yemigermew bezuhanun yesinodos abalatin tetem kabba tiomtiwos ena kaaba estifanos gar becha mesrat yichal yihon?patriariku sishomu yetenagerutin eresu ende sinodosu berasu litemamen yigebal yalutin tadiya minew gena keenchichu yesinodosun wesane berasachew sharut.tadeya abba pawlosin ande keyerusalem andem keamerica minew seyawegzu noru. Abba pawlos rest in peace erso yishalun neber.

 10. Anonymous October 2, 2013 at 5:09 pm Reply

  mn elalew church yeglesb nat

 11. Anonymous October 3, 2013 at 11:50 am Reply

  is it religious blog or church politics I cant get any useful teachings which saves our sole since the time I encounter it I am sorry u have to change the name to other which fits with it. thank u I will search other religious( o.tewahedo)
  blogs

 12. Anonymous October 4, 2013 at 7:09 am Reply

  ewuru ena eke bete kirstiyanin nkeberat

 13. Anonymous October 4, 2013 at 10:04 am Reply

  ሐራ ደሞ በዚ ብቅ አልሽ ስም: አርፋቹ አትቀመጡም

 14. Anonymous October 9, 2013 at 3:29 pm Reply

  Geta Hoy: Lebetkiristiyan Yetamene Meri Setat.

 15. MAREW GETU August 3, 2014 at 5:32 pm Reply

  GETA HOY ANTE TAWUKALEH+ MELISIHIN LEMETEBEK TIGISTIN SITEN!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: