ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ተጽዕኖ አልባ መሪ›› ተባሉ: አዲስ ጉዳይ መጽሔት

Addis Guday cover storyዛሬ፣ መስከረም ፲፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ለንባብ የበቃው አዲስ ጉዳይ ሳምንታዊ መጽሔት የ፳፻፭ ዓ.ም የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ የዓመቱ ምርጦች እየተባለ በሌሎች ኅትመቶች ከወጡት ተቋማትና ግለሰቦች በተለየ አኳኋን በ፳፻፭ ዓ.ም ‹‹ተጽዕኖ አልባ መሪዎች ነበሩ›› ያላቸውን አምስት ግለሰቦችና አንድ ተቋም ለይቷል፡፡

መጽሔቱ ለልየታው የተጠቀመው÷ ግለሰቦቹና ተቋሙ ካለባቸው ሰፊ ሓላፊነት፣ ከተቀመጡበት ወሳኝ ቦታና ከሚጠበቅባቸው ውጤት በተቃራኒ በተገመገሙ ጥቅልና ቀጥተኛ መመዘኛዎች  እንደኾነ በመግቢያው አመልክቷል፡፡ እንደ መጽሔቱ መመዘኛ ተጽዕኖ አልባ ነበሩ የተባሉት መሪዎች፣ በተለይ የሃይማኖት አባቶቹ፣ ባሳለፍነው ፳፻፭ ዓ.ም ኢትዮጵያ ባለፈችባቸው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሂደቶች ውስጥ ጉልሕ ሚና ሊኖራቸው ይገባ ነበር፡፡

ነገር ግን፣ ተጽዕኗቸው ጎልቶ አለመውጣት ብቻ ሳይኾን ጭራሹን ከሚጠበቀው በጣም በአነስተኛ ደረጃ እንኳ ያልነበረ መኾኑን በግምገማው አትቷል፡፡ በጥቅልና ቀጥተኛ መመዘኛና በመመዘኛው ላይ ተመሥርቶ በተደረገው ግምገማ በዓመቱ ‹‹ተጽዕኖ አልባ መሪ›› ነበሩ ከተባሉት ውስጥ ው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ይገኙበታል፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን በወቅቱ ከሚያስፈልጋት አስተዳደራዊ አንድነት፣ ተቋማዊ ለውጥ እና የዕቅበተ ሃይማኖት ተግባራት አንጻር ምዘናው ለሐራውያን ማንጸርያና መወያያ ሊኾን ይችላል በሚል በመጽሔቱ በቀረበበት መልኩ አስተናግደነዋል – ይመልከቱት፤ ይወያዩበት፡፡

*                              *                              *

His Holiness in Dire Dawa

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

የሃይማኖት አባቶች በአገራችን ውስጥ ለሚከሠቱ ችግሮች ሰላማዊ መፍትሔ ለማስገኘት የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ነገር ግን የሃይማኖት አባቶች በሚፈለግባቸው መጠን ቀርቶ በተወሰነ ደረጃ እንኳ ይህን የሞራል፣ የዜግነት ይኹን የሃይማኖት ድርሻቸውን ሲወጡ አይታይም፡፡ ይህ በመኾኑም ዘንድሮም በተለይ የሁሉም ሃይማኖት አባቶች ከሚመሩት ምእመን ብዛት አንጻር ተጽዕኖ አልባ ኾነው ከርመዋል፡፡

በተለይ በርካታ ምእመናንን በሥራቸው በማቀፍ የሚታወቁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ኾነ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ሊኖራቸውን የሚገባውን ሚና በአግባቡ መወጣት አልቻሉም፡፡ ይልቁንም ባለፈው ዓመት ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፮ ፓትርያርክ ኾነው የተመረጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በእርግጥ የሥራ ዘመናቸው ለምዘናው አነስተኛ ቢኾንም፣ አቡኑ የቤተ ክርስቲያኗን የውስጥ ችግር ኾነ በአገሪቱ ውስጥ የሚታዩትን በርካታ ችግሮች ለማስወገድ የሚያስችልና የሚገባ ርምጃ ወስደዋል ለማለት ይቸግራል፡፡

በርግጥ በ፳፻፭ ዓ.ም ፓትርያርኩ ለማከናወን የሚጠበቅባቸው ሥራም ከፍተኛ የኾነበት ምክንያት፣ ቤተ ክህነቱ በእጅጉ መስተካከል የሚገባቸው በርካታ ክፍተቶች ያሉበት በመኾኑ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ለሁለት የተከፈለው ሲኖዶስና በዚህ ምክንያት በየሀገሩ በጎጥና በፖሊቲካ አመለካከት ተከፋፍሎ የሚያመልከው ምእመን ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ሥር የሰደደ ችግር በአጭር ጊዜ አክሞ ማዳን ባይቻልም ፓትርያርኩ ግን ቢያንስ አንድ ፈጣን የሰላምና ዕርቅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ የሚል ግምት ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር የእምነት መከባበርን በመስበክ ሀገሪቱ በተሻለ ደረጃ መግባባት የሰፈነባት እንድትኾን ለማድረግ ይጥራሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር፡፡

በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሚወሳው፣ ቤተ ክህነቷ ከመንግሥትና ከፖሊቲካው ጋራ በእጅጉ ተጣብቃ በአብዛኛው አካሄዷ የመንግሥትን የፖሊቲካ ዓላማ ማስፈጸም የኾነበት ጊዜ እንዲያበቃ የብዙ ምእመናንም ፍላጎት ነበር፡፡ ነገር ግን አቡነ ማትያስ የቀየሩትም ኾነ ሊቀይሩት ያቀዱት ነገር ለጊዜው ያለ አይመስልም፡፡ ፓትርያርኩ እንኳን የፖሊቲካው ጉዳይ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን የሃይማኖት[አስተምህሮ] ሽኩቻ ለመፍታት የአባትነታቸውን ድርሻ በሚገባ አልተወጡም፡፡ እነ እገሌ ተሐድሶ[መናፍቅ] ናቸው እየተባለ የተፈጠረውን የመከፋፈል ችግር ለመፍታት እንዲሁም በእምነቱ ተከታዮች መካከል ያለውን የመፈራረጅ ክፉ ልማድ ለማስቀረት በፍጥነት አልሠሩም የሚል ወቀሳ ከወዲሁ እየቀረበባቸው ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር ፓትርያርኩ በሀገር ጉዳይ ላይ እንደ ሃይማኖት መሪ ጣልቃ ሊገቡበት የሚገባ በርካታ ዐቢይ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ በመንግሥትና በሙስሊም ማኅበረሰቡ መካከል የተከሠተው ችግር በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ የሃይማኖት አባቶች በቀዳሚነት ሓላፊነቱን መውሰድ ይችሉ ነበር፡፡ በዚህ ባለንበት ዘመን የሕዝቦች መብት ሲነካና አለመግባባት ተፈጥሮ የአገሪቱ ሰላም ስጋት ላይ ሲወድቅ በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ያለ አባት ጣልቃ ገብቶ ችግሩን ማርገብ ከሓላፊነቶቹ አንዱ ይኾናል፡፡ አቡነ ማትያስም ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ባላት ሥፍራና ሌሎች የሃይማኖት አባቶችን የማስተባበር ድርሻ ተጠቅመው ከመንግሥት ጋራ መደራደርና ችግሩን በአስታራቂነት ለመፍታት ሰፊ ጥረት ማድረግ ይችሉ ነበር፡፡ ጉዳዩ የእምነት መመሳሰልን የሚሻ ሳይኾን ሰላምን ለማስፈን የሚደረግ መንፈሳዊ ሓላፊነት ብቻ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ ፓትርያርኩ ወደ ማረሚያ ቤት ጎራ ብለው የታሰረ ሲጠይቁና ሲያጽናኑም አላየንም፡፡ በማረሚያ ቤቶች ኾነው መጽናናትን የሚሹ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ከአንድ የሃይማኖት አባት የሚጠበቅ መንፈሳዊ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንግሥትን ምሕረት ጠይቀው የተከለከሉ አልያም መንግሥት እልህ የተጋባባቸው ዜጎችም አሉ፡፡ ቢያንስ የነዚህን ዜጎች ጉዳይ እንደ ሃይማኖት አባት መጠን አቤት ማለት ይችሉ ነበር፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ግን ከቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ተልእኮ ውጭ በኾኑ የመንግሥት የፖሊቲካ ስብሰባዎች ላይ ቀዳሚ ተሳታፊ እንድትኾን እየተደረገች፣ ምእመኑም እያዘነ ነው፤ ጸሎተ ቅዳሴን እስከ ማስተጓጎል የደረሰ የፖሊቲካ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡ አቡኑ ከ፳፻፮ ዓ.ም የዘመን መለወጫ ቡራኬያቸው ከንግግራቸው አብዛኛው የመንግሥት የዕለት ተዕለት ንግግሮች የታከሉበት ነበር፡፡ እንደ ሃይማኖት አባት ስለ ሰላም፣ ስለ መፈቃቀር፣ ጠብን ስለማስወገድ፣ ስለ መከባበር. . .ወዘተ መስበክ ሲገባ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት የኾኑ ይመስል ስለ መልካም አስተዳደር መስበክ ከእርሳቸው የማይጠበቅ እንደኾነ ብዙዎች ይነቅፋሉ፡፡

በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሣ ባለፈው ዓመት ፓትርያርኩ የወራት የሥራ ላይ ቆይታ የነበራቸው ቢኾንም ከ፳፻፭ ዓ.ም ተጽዕኖ አልባ መሪዎች መካከል አንዱ ኾነው መካተታቸው ግድ ኾኗል፡፡

Advertisements

18 thoughts on “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ተጽዕኖ አልባ መሪ›› ተባሉ: አዲስ ጉዳይ መጽሔት

 1. መስቀል ክብራ September 28, 2013 at 11:17 pm Reply

  ይድረስ ለመጽሔቱ አዘጋጆች

  ቅዱስነታቸው ወደ መንበር ከመጡበት ጊዜ አንጻር ሊያከናውኑት እንደማችሉ ካመናችሁ መተው ነበር የነበረባችሁ:: ለምን ለትችት ቸኮላችሁ? ገበያ መር የሕትመት ሥራ ትሠራላችሁ ብዬ አልገምትም:: ይሁን እንጂ እንዲያከናውኗቸው ጥቆማ በመስጠት የመሪነት ሚና መጫወት ስለፈለጋችሁ ጎትታችሁ ጨመራችኋቸው:: ተሞ ኛችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ከዚህ በኋላ ሚድያውን የምትመራ እንጂ ሚድያ የሚመራት ቤተ ክርስቲያን አትሆንም:: ያንንም ቢሆን በግልጽ ቢያከናውኗቸው ብሎ መጠቆምም ይቻል ነበር:: ተጽእኖ መፍጠር የቅዱስነታቸው ግብ ሊሆን አይችልም:: ለዚያ የሚሠሩና የሚጠበቅባቸውም በርካቶች ስለአሉ ስለነዚያ መተንተን ይቻል ይመስለኛል:: እንደ መንግሥት የግድ አንዱን ቤተ እምነት አንስታችሁ ሌላውን ሳትነኩ ብታልፉ ሚዛናዊ አይሆንም ብላችሁ ያሰባችሁ ይመስላል:: ጊዜ ፋታ ስጧቸው ትደርሱበታላችሁ ለትችቱ:: የሚል አስተያየት አለኝ::

 2. geezonline September 28, 2013 at 11:40 pm Reply

  አባውን ተጽዕኖ አልባ መሪ ማለት ፍጹም ዐሰት ነው!

  ደግሞ “… ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር።” ይባላል እንዴ? ረ ስለግዚሓር! ማነው ተስፋ የጣለባቸው? እያወቅነው? የተጣለባቸው ተስፋ ሳይኾን ሐላፊነት ነው። ጣዩም እነአቶ አባይ እንጂ ምእመናን አይደሉም። ሐላፊነቱም ባለጉልበቶቹ ብያ (already) ሽባ ያደረጓትን ቤተ ክሲያን፤ ስርኗን ተመንገጭሊዋ አጣብቆ በመሸበብ የሚጭኗትን ኹሉ አንዳች ሳትተነፍስ እንድትሸከም ማድረግ ነው። ይኸንንም እያከናወኑ አሉ። ከዚኽ የበለጠ ምን ተጽዕኖ (ጭነት) ይፍጠሩ??? [“ተጽዕነ” ማለት “ተጫነ… ጸዋሪ(ተሸካሚ) ኾነ ማለት ነው’ኮ!]

 3. nitsuh miskire September 29, 2013 at 1:20 am Reply

  Do not cheat us. There is no difference between so called church leaders and political leaders. The leaders of the the Church is assigned by the political party. Do you expect him to work on contrary to his assignment? How can he conduct peace and unity whereby himself is part of the problem? He is doing his home work right. Do not blame him for not doing what is not his job. .

  • Anonymous December 13, 2013 at 6:58 am Reply

   this didn’t happen,will not happen.the church assignes political leaders ,no cherch leader is asssigned pilitically in ehiopia stil now and it will no thappen forever.

 4. gorgori September 29, 2013 at 10:18 am Reply

  አባቶቻችን ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን አይሾሙም፡፡ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዓላማቸው ተጽዕኖ መፍጠር እንጂ መንፈሳዊ ሕልምና ርዕይ አይኖራቸውም፡፡ ቅዱስነታቸው አሁን ከሊቃነ ጳጳሳትና ሌሎች አጋር አካላት ጋር የጀመሯቸው ሥራዎች አሉ፡፡ ሙሰኞችን ለመዋጋት፣ በቤተ ክርስቲያኗ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ በተለይ የአዲስ አበባን አድባራትና ገዳማት ሃብትና ንብረት በአግባቡ ማስተዳደር የሚቻልበትን መንገድ በጥናት አስደግፎ ለመሥራት እንቅስቃሴው ደስ የሚልና ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጅምር ሥራዎች ግባቸውን እንዲመቱ እገዛ ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡

  አስቀድሞ ከነበረን ጥርጣሬ አንጻር ፍረጃ የምንጀምር ከሆነ ለቤተ ክርስቲያን ጸር ሆነን እየተንቀሳቀስን መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ በዕውነትም እስከ አሁን ባየነው አስቀድመን እንደጠረጠርናች ሆነው አላገኘናቸውም፡፡ የበከተ የቤተ ክህነት ሠራተኛ ይዘው በአንድ ጊዜ ለውጥ ካላመጡ፣ የመንግስትን አካላት በሙሉ አሳምነው በሃገሪቱ ድምጻቸው ተሰሚነት ያለው አባት መሆን ይገባቸዋል ማለት ከባድ ነው፡፡ እንኳንስና በኃይማኖታዊው አገልግሎት በፖለቲካው አካሄድም ከባድ ይመስለኛል፡፡

  እናም ወገኖች መነጽራችንን ጎላ እናድርግ፡፡ ለመፈረጅ መቸኮል የልጅነት/ያለመብሰል ጠባይ ነው፡፡ እንእኔ ግን ቅዱስነታቸው የበለጠ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ሁላችንም በየአቅማችን በሥራ በመሠማራት እንዲሁም በጸሎት ማገዝ ይገባናል ባይ ነኝ፡፡
  መንፈሳዊ አባት ተጽዕኖ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን ፈልጎ ሳይሆን ራሱ ሥራዉ በሂደት ተጽዕኖ እየፈጠረ ሲሄድ መሆን ይገባዋል፡፡

 5. Deborah September 29, 2013 at 3:12 pm Reply

  @geezonline….Thank you for writing the truth…no need of further comments.GOD bless you.

  • gorgori September 30, 2013 at 7:50 am Reply

   የዕውነት መለኪያው ምን እንደሆነ ካላወቅነው መውደቅ እንደሚመጣ ማወቅ ይገባናል፡፡ እውነትም የምትነገረው ውጤት ለማምጣት በምንችልበት ሁኔታ መሆን አለበት ይመስለኛል፡፡ እርግጥ እንደየአረዳዳችን ሊለያይ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ቅዱስነታቸውን ለመተቸት ጊዜው ገና ነው፡፡

   • geezonline September 30, 2013 at 5:17 pm

    “…ጊዜው ገና ነው?” ርግጥ ነው እንደ ቀዳሚኣቸው ሃያ ዓመት እስቲሞላቸው መጠበቅ አለብን ብሎ ለሚያስብ ገና ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ይቀራል። ወዳጄ ጎርጎሪ፦ አእምሮ ግዕዛንኽን በሚገባ እየተጠቀምኸው መኾንኽን አጠራጠርኸኝ። “ወጽድቅ ታግዕዘክሙ” ይላልና፤ የእውነት ውጤት ነጻነት ነው። እናም ለእውነት ፍቀድላት፤ ነጻ እንድታወጣኽ…

 6. Anonymous September 30, 2013 at 9:24 am Reply

  please i have comment to addis guday & other pessimist ………… ABUNE MATIAS GENA SERA EYEJEMRU NEW so how can we compare with GERMA W/GIORGIS le 12 amet seltan lay kale sew gar becha abatachen gize yesetachew …………..

 7. Misa September 30, 2013 at 9:30 am Reply

  አዲስ ጉዳይ የቸኮለ መሰለኝ!!!!!!!!!!! ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሰዎቿ በፈጠሩት በርካታ ችግሮች ባለችበት ወቅትና ይህንም ለማስተካከል የሚወስደው ጊዜ ከባድ ሆኖ ባለበት ወቅት ይህ መባሉ ትንሽ ቅር ብሎኛል፡፡
  ሁለተኛ ከአክራሪነት ጋር በተያያዘ የአክራራሪዎች ዓላማና አጀንዳ ምን እንደሆነ እየታወቀ ይህን ከማውገዝና ከማስተማር የዘለለ ሚና እንዲኖራቸው አንፈቅድም!!!

 8. Mengaw September 30, 2013 at 11:10 am Reply

  በጣም የምትገርሙ ቅንጣት ያህል ክርስቲያናዊ ተግባር የሌላቹና ክርስቲያናዊ ተግባር የማታቁ. ማን ይሙት አሁን ስለ ሰላምና ስለ መልካም አስተዳደር መናገራቸውና ያን በማስተካከል ለመጅመር መሞከራቸው ነው ከመንግስተ ጋራ እንደወገኑ ያስቆጠረባቸው አይ እናንተ ዘረጆች . . . እግዚአብሔር ልቡና ይስጣቹ

  • Mengaw September 30, 2013 at 11:12 am Reply

   በጣም የምትገርሙ ቅንጣት ያህል ክርስቲያናዊ ተግባር የሌላቹ; ማን ይሙት አሁን ስለ ሰላምና ስለ መልካም አስተዳደር መናገራቸውና ያን በማስተካከል ለመጅመር መሞከራቸው ነው ከመንግስተ ጋራ እንደወገኑ ያስቆጠረባቸው አይ እናንተ ዘረጆች . . . እግዚአብሔር ልቡና ይስጣቹ

 9. Anonymous September 30, 2013 at 6:38 pm Reply

  I think it is not the right time to comment on the performance of our holly father. He already started some activities and planed lots. I am unclear about the difference between free medias and your blog. Please talk a lot about the stability of our church and the nation at large.

 10. Jordan September 30, 2013 at 8:40 pm Reply

  Ye emiategib injera ke mitadu yastawikal new negeru

 11. Anonymous October 1, 2013 at 4:26 pm Reply

  Who is this guy? Pls don’t lesson this jerk.

 12. Anonymous October 7, 2013 at 9:56 am Reply

  ቢደርስ ለአዲስ ጉዳይ ዝግጅት ክፍል
  እባካችሁ ገና ለገና የአንባቢን ትኩረት ለመሳብና ሕትመታችሁ እንዲሸጥላችሁ ብቻ ለዘለፋና ለትችት ብሎም ለጥላቻ አትፍጠኑ!!

 13. ደጉ ሳምራዊ October 7, 2013 at 9:58 am Reply

  ቢደርስ ለአዲስ ጉዳይ ዝግጅት ክፍል
  እባካችሁ ገና ለገና የአንባቢን ትኩረት ለመሳብና ሕትመታችሁ እንዲሸጥላችሁ ብቻ ለዘለፋና ለትችት ብሎም ለጥላቻ አትፍጠኑ!!

 14. BEKELE ABEBE KUMA October 9, 2013 at 2:21 pm Reply

  ቢደርስ ለአዲስ ጉዳይ ዝግጅት ክፍል
  እባካችሁ ገና ለገና የአንባቢን ትኩረት ለመሳብና ሕትመታችሁ እንዲሸጥላችሁ ብቻ ለዘለፋና ለትችት ብሎም ለጥላቻ አትፍጠኑ!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: