ሙሰኛው የቅ/ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪ አባ ገ/ኢየሱስ መኰንን ሢመተ ጵጵስናን በገንዘብ ለመግዛት መንቀሳቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል

Komos Aba Gebre Eyesus Mekonen

 • ‹‹የሰባት ወይራ ሆቴልን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዳይወስድብን ለመለመን›› በሚል በደብሩ አስተዳደር ያስወሰኑትን ግማሽ ሚልዮን ብር፣ ሢመተ ጵጵስናውን ይቃወማሉ የሚባሉ አባቶችን የማግባባት አቅማቸውን እንደሚያጠናክሩበት ጠቁመዋል፡፡
 • ከቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በተፃራሪ በሥልጣን ላይ የቆዩትና በአስተዳዳሪው ውሳኔ እስከ 7000 ብር በወር የሚከፈላቸው አብዛኞቹ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላት እና የጽ/ቤቱ ሠራተኞች፣ በአስተዳዳሪው የግማሽ ሚልዮን ብር ጥያቄ እንዲስማሙ በ‹ጥቅማቸው› መገደዳቸው ታውቋል፡፡ ከአስተዳደሩ ሠራተኞች የሚበዙት ከገቢያቸው በላይ ከደብሩ በሚያካብቱት ሕገ ወጥ ጥቅም በከተማው ሕንጻዎችንና መኖርያ ቤቶች ግንባታ በማካሄድ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡
 • አስተዳዳሪው አባ ገ/ኢየሱስ÷ ጉዳዩ በፍ/ቤት የተያዘውንና ደብሩ የይዞታ መብቱን በሕግ ለማረጋገጥ የተቃረበብትን የሰባት ወይራ ሆቴል ባለቤትነት፣ ባለፈው ዓመት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በድብቅ በጻፉት ደብዳቤ የተረከቡኝ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡ ድርጊቱ፣ የደብሩ አለቃ ሢመተ ጵጵስናን በስምዖናዊ መንገድ ለማግኘት የሚያግባቡበት ገጸ በረከት አካል እንደኾነ ታምኖበታል፡፡
 • በ1965 ዓ.ም ከልዕልት ኂሩት ደስታ (የደጃዝማች ደስታ ዳምጠው ልጅ) ለቅ/ላሊበላ ደብር በስጦታ የተበረከተው የሰባት ወይራ ሆቴል በሙሰኛውና ዐምባገነኑ አስተዳዳሪ ፍቅረ ሢመት የተነሣ ሕጋዊ ባለቤትነቱ በድብቅ ተላልፎ መሰጠቱ ሳይበቃ፣ ‹‹ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዳይወስድብን መለመኛ/መያዣ›› በሚል የደብሩ አስተዳደር ብር 500,000 እንዲያጸድቅ በአለቃው መገደዱ በከተማው ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ቊጣ ቀስቅሷል፤ ሥር የሰደደውና ሃይ ባይ ያጣው የአለቃው ዘራፊነትና ዐምባገነንት በቁጣ ለተሞሉትና ለተመረሩት ምእመናን ጥቃት እንዳይዳርጋቸውም ተሰግቷል፡፡
 • ምእመናኑ ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ወደ ወልድያ ተጉዘው ለሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል፡፡ አስተዳዳሪው ከሓላፊነታቸው ተነሥተው በሕግም እንዲጠየቁ ያመለከቱት ምእመናኑ፣ ያለከልካይ የሚታዘዝበት የደብሩ የሒሳብ ቋቶች እንዲታገዱም ጨምረው እየጠየቁ መኾናቸው ተዘግቧ፡፡ባለፈው ዓመት ከነሐሴ ፲፭ – ፲፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም የአሸንድዬ በዓል በተከበረበት ወቅት ለክብረ በዓሉ ከሀ/ስብከቱ በመጡ ልኡካን በይምርሐ ሆቴል ላይ ድንገተኛ ኦዲት በተካሄደበት ወቅት ብር 260‚000 ጉድለት መገኘቱ ተዘግቧል፡፡ ጉድለቱን ባመነው የሆቴሉ አስተዳደር ላይ ሀ/ስብከቱ ጥፋቱን የሚገልጽ ደብዳቤ የጻፈ ሲኾን ይህንኑ የሀ/ስብከቱን የቁጥጥር ርምጃ የደብሩ አስተዳዳሪ መቃወማቸው ተገልጧል፡፡በሌላ በኩል ከመጋቢት ወር፣ ፳፻፭ .ም ጀምሮ ለ800 ለደብሩ ካህናት የተወሰነው የደመወዝ ጭማሪ ተግባራዊ የተደረገው ከሚያዝያ ወር ወዲህ መኾኑ የተነገረ ሲኾን ድምሩ ብር 270‚000 የሚኾነው የሁሉም ካህናት የመጋቢት ወር ጭማሪ፣ ከተመረቀ ሦስት ዓመት ላስቆጠረው የይምርሓ ሆቴል ማስመረቂያ በሚል ሰበብ ለአስተዳዳሪው የግል ጥቅም መዋሉ ተገልጧል፡፡
 • ዘግይተው ከሥፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በኹኔታው ክፉኛ ማዘናቸው የተጠቀሰው የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ‹‹የሰባት ወይራ ሆቴል ጉዳይ የእርስዎም የጠቅላይ ቤተ ክህነትም ጉዳይ ሳይኾን የላሊበላ ሕዝብ ጉዳይ ነው፤›› በማለት ግማሽ ሚልዮን ብር ወጪ እንዲደረግ በግዳጅ የተላለፈው ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለውና ውድቅ እንዲደረግ የደብሩን አስተዳዳሪ ማሳሰባቸው ተሰምቷል፡፡ ወደ ወልዲያ አምርተው አቤቱታቸውን ለማቅረብ በምእመኑ የተመረጡት ተወካዮች ወደ ሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት መሄዳቸው ቀርቶ ነገ እሑድ፣ መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ወደ ላሊበላ ከሚላከውና የሀ/ስብከቱን ጸሐፊ ከሚያካትተው ልኡክ ጋራ እንደሚነጋገሩም ተጠቅሷል፡፡
 • ላለፉት ስምንት ዓመታት በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን የውቅር አብያተ መቅደሱን ሀብት ያለቦታው በማፍለስ፣ ክብካቤ እንዳይደረግላቸው በመከላከል፣ በአብያተ መቅደሱ ዙሪያ የሚገኙና በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ኾነ ብለው በቃጠሎ አደጋ እንዲጠፉ በማድረግ፣ የደብሩን ድጎማ እንዲያገኙ በሀ/ስብከቱ ለታዘዛላቸው ቤተ ጉባኤያት ደቀ መዛሙርት ድጋፍ በመንፈግና በማዳከም፣ የአብያተ መቅደሱን አገልጋዮች ሐሰተኛ ሰነድ እየፈጠሩ ከሥራ በማፈናቀልና በማንገላታት ከባድ ክሥ የቀረበባቸውን አስተዳዳሪ ከቦታው ለማስወገድ ወቅቱ አኹን እንደኾነ ታምኖበታል፡፡
 • ከዚሁ ጋራ ተያይዞ ለአስተዳዳሪው መረጃዎችን በመስጠት፣ በሕግ የሚጠየቁባቸውን ጉዳዮች በማድበስበስ አላግባብ የሚተባበሯቸው የከተማው የፖሊስ አዛዥና የዞኑ አስተዳዳሪ ተገቢው እርምት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
Advertisements

12 thoughts on “ሙሰኛው የቅ/ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪ አባ ገ/ኢየሱስ መኰንን ሢመተ ጵጵስናን በገንዘብ ለመግዛት መንቀሳቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል

  • Anonymous September 28, 2013 at 8:12 am Reply

   What is the criteria to be a bishop contraption will not

 1. Anonymous September 28, 2013 at 3:08 pm Reply

  መድኃንያለም መጨረሻውን ያሳምርልን እንጂ የሰዎቹማ ደግፋ ቀና ማለት ቤተ ክርስትያንን እስከማፈረስ ድረስ የገፋ ነው::
  በእውነት ይህ ካህን ነኝ ባይ ጳጳስ ቢሆን ምን ለመፈጠረ አስቦ ነው?ቤተክርስትያንን ለማፍረስስ ይህን ያህል መድከም ለምን አስፈለገ እንደማትፈርስ እንደው ይታወቃል ::ቢያንስ እንኩዋን ህሊና ያላቸው ለሃይማኖታቸው የቆሙ ጳጳሳትም እንዳሉ መገንዘብ ነበረበት ሁሉም ጳጳሳት በገንዘብ የሚደለሉ መሰለው እንዴ?

  መናፈቅ ካህን ማለት ይህንን ነው :;መወገድ ካለባቸው አሁን መወገድ አለባቸው ::

  እግዚአብሔር ሀገራችንንና ቤተክርስትያናችንን ከጠላት ዲያብሎስና ከተላላኪዎቹ ይጠብቅ ::

 2. Anonymous September 28, 2013 at 4:25 pm Reply

  This is a Dirty criticisim from a bull !!!!!!!!!!!!!!!! This is back bitting

 3. Anonymous September 28, 2013 at 4:28 pm Reply

  As a person, Aba might have some drawbacks but what you are writing is TOTALLY FALSE. Please be reasonable and write geniune things.

 4. anonymous September 28, 2013 at 6:58 pm Reply

  Who ever writing this is a total lyre. I have seen in my eyes. Let me ask. What was there before he came? How much was the salary of priests and clergies now and then? Who build bet Abraham hotel? Who fought to take over the museum to be under church administration? Who established a center where poor people will get shelter, food and clothing? Please don’t criticize blindly. What is the difference whether sebat woyera hotel belongs to lalibela deber or betekehnet as far as we believe in one (ahati) orthodox church. He is a father of change. At least he showed how change can happen. About his personal life leave it to him and god. If he really want to be corrupt, he would have chosen to remain there in stead of ‘bribing’ to be a bishop where he will get nothing.

 5. Hailemariam September 29, 2013 at 3:02 am Reply

  Let God give him heart ! this is unwiseness. How such a big priest want to buy the gift of Alimght God PiPisina? Didn’t he read the Holiy Bible in Act that Giyaz called the desciple if God Jesuse and asked them to sell him their Silitane Kihinet and healing pow as a result of that what happend to him. This man would sell the church if he becomes PaPas. He is Devil and he is drunk of money and blinded of money and never think of church and never listend to the words of God,and never become the sheep heard because he will eat them therefore, he should go before he causes non reversable destruction to our church and distance the Orthodox believer away from the church.
  Engiz Abher Dingayun Ynakebalilinal
  Amen

 6. Anonymous October 1, 2013 at 1:08 am Reply

  ሀራዎች እባካችሁ አስተውሉ
  ይህ አባት እንደማንኛውም ሰው ደካማ እና ጠንካራ ጎን ይኖራቸዋል በአንድ ወቅት ለጉብኝት በቦታው በተገኘሁበት ጊዜ በርካታ በጎ ሥራዎችን ለገዳሙ እንደሠሩና ብዙ ለውጥ እንዳመጡ ሰምቻለሁ እናንተ ግን አንድም በጎ ነገር አልጠቀሳችሁም ፅሑፋችሁ ጠቀለል ተደርጎ ሲታይ በጥላቻ የተሞላና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው፡፡ ከመመካከላችሁም የግል ጥላቻ ያለው ግለሰብ እንዳለ በግልፅ ያሳያል፡፡ እኔን እያሳሰበኝ የመጣው ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ይህን መሰል ፀሑፋችሁን ሳነብ እጠረጠራችኋለሁ ለመሆኑ የብሎጋችሁ ዓላማ ምንድን ነው? ጳጳስነት በሙስና ይገኛል ብሎ መፃፍ ተሿሚውን ብቻ ሳይሆን ሲኖዱሱንም መሳደብና ማጥላላት ነው አኝህ አባት ነገ ጳጳስ ሆነው ቢሾሙ በምዕመናን ልብ ውስጥ ለመፍጠር በምትሞክሩት አሉታዊ ምስል በሄዱበት ሀገረ ስብክት ሁሉ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው፣ እሳቸውም ሲኖዱሱም/ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኗ/ ሙሰኛ ናት ለማለት ለማሰኘት፣ ሰድባችሁ ለሰዳቢ
  አባ ገብረኢሱስን ብቻ ነው የተሳደብነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ገና አልበሰላችሁም ማለት ነው አባ ገ/ኢየሱስን፣ የላሊበላን ገዳም፣ ሀገረስብከቱን፣ ሲኖዱሱን፣ ቤተክርስቲያኒቱን
  ስለዚህ እባካችሁ በእውነት ለቤተክርስቲያን የምትቆረቆሩ ከሆነ እያሰተዋላችሁ ፃፉ፣ የግል ጥላቻችሁን አታንፀባርቁ፣ እኛ ምዕመናኑ ደግሞ በቤተክርስቲያናችን አባቶች ላይ እምነት እንዳይኖረንና ጥላቻ እንዲያድርብን አትትጉ አባካችሁ እንዲህ ዓይነቱን ፅሑፍ አትድገሙት ማንንም አያንፅምና ይልቅስ የብዙ ሰዎችን ልብ ያቆስላል

 7. Anonymous October 3, 2013 at 1:47 pm Reply

  አባ ገ/ኢየሱስ መኮነን የልማት አርበኛ የቅዱስ ላሊበላ ደብርን የገቢ ምንጭ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደጉ አገልጋይ ካህናቶቹን የኑሮ ደረጃ ና ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደጉ በሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ጽ/ቤት ግንባታ ላይ ከደብሩ በጀት በብድር ና በልገሳ በከፍተኛ ሁኔታ እገዛ ያደረጉ የልማት ጀግና ናቸው በዚህም ተግባራቸው በሀገር ና በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ ና የተረዳ ጉዳይ ነው የሀገረስብከቱም ሊቀጳጳስ እና ሰራተኞች ከአንድ መሰሪ እና ተንኮለኛ ሰው በስተቀር ስለ ጠንካራ የስራ ተግባራቸው የሚያደንቁአቸው ና የሚመሰክሩላቸው ድንቅ አባት ናቸው በሀገረስብከቱ ውስጥ የተሰጠውን የስራ ኃላፊነት ከተገቢ በላይ በመጠቀም የፈጠራ እና የሀሰት ወሬ እየፈበረከ የሀገረስብከቱን ሰራተኞች አንገት በማስደፋት ከስራአስኪያጁ በላይ በማን አለብኝነት እራሱን የኮፈሰው በሙያው እዚህ ግባ የማይባለው ግለሰብ ከአባ ገ/ኢየሱስ እጅ ጠበታ ሳንቲም ማግኘት ባለመቻሉ ለረጅም ጊዜአቶች በሀሰት እና በፈጠራ ወሬ ሲያሳድዳቸው የቆየ መሆኑን የምናውቀው ጉዳይ ስለሆነ የዚህን ከንቱ ሰው ተንኮል እግዚአብሄር ያጋልጠው እያልን መምህር አባ ገ/ኢየሱሰ መኮነን ይበርቱ እግዚአብሄር አይለየወት ለማለት እንዳወዳለን፡፡

 8. Anonymous October 17, 2013 at 7:52 am Reply

  btekekele amenalhu qoshasha melekuse new amenalhu seqelaete yeferedebete !!!!

 9. Anonymous November 5, 2013 at 2:14 pm Reply

  twe Turu Aydlme

 10. Anonymous November 11, 2013 at 7:12 am Reply

  mene Besalam Hager Selamin Besbek.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: