ለወራት ያለአስተዳዳሪ የቆየው የካርቱም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በችግር ላይ ነው

 • አስተዳደሩና ማኅበረሰቡ የመረጣቸው አስተዳዳሪ ምደባ እንዲወሰንለት ጠይቋል
 • ሊቀ ጳጳሱ ለምደባ ያቀረቧቸው ስድስት ሠራተኞች ማንነት እያጠያየቀ ነው
 • ቋሚ ሲኖዶስ በአህጉረ ስብከቱ አስተዳደር ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን እየመረመረ ነው
 • ለደቡብ አፍሪካ የቅዱስ ያሬድ ገዳም ከአ/አ አድባራት የተሰበሰበውና በሊቀ ጳጳሱ የግል አካውንት ተልኮ የነበረው አራት ሚልዮን ብር ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል

ላለፉት ሦስት ወራት ያለአስተዳዳሪ የቆየው በምድረ ሱዳን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቱ እየተበደለ መኾኑን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ፤ በደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና በኦርቶዶክሳዊው ማኅበረሰብ ሙሉ ስምምነት በቀድሞው አስተዳዳሪ ቦታ እንዲተኩ የተመረጡት አባት ምደባ እንዲጸድቅለትም ጠየቀ፡፡

የደብሩ አስተዳደር በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ለመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የላከው ደብዳቤ እንደሚገልጸው፣ ከሐምሌ ፳/፳፻፩ ዓ.ም ጀምሮ ደብሩን ለአራት ዓመታት በእልቅና ያገለገሉት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ይርሳው ከሐምሌ ወር ፳፻፭ ዓ.ም ከቦታው ተቀይረው ወደ ኢትዮጵያ በመመለሳቸው ደብሩን ከውጭ አካላት ጋራ የሚያገናኙት አገልግሎቶቹ እየተበደሉ ይገኛሉ፡፡

በምድረ ሱዳን የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምእመናን በተለይ ከሱዳን የሃይማኖት ሚኒስቴር፣ ፍርድ ቤት፣ የኢትዮጵያ ኤምባሲና መሰል አካላት ጋራ የሚከናወኑ የማኅበረሰቡን ጉዳዮች ምትክ አስተዳዳሪ ባለመመደቡ ለማስፈጸም መቸገሩን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አስታውቆ፣ በቀድሞው አለቃ ፈንታ ‹‹ማኅበረሰቡ የተቀበላቸውና ለአገልግሎቱ ብቁ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸው›› አባት ምደባ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲያገኝ በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥያቄ እልባት እንዲሰጠው የፓትርያርኩን መልካም ፈቃድ ጠይቋል፡፡

Sudan Debre Selam Medhanialem Church request to the Patriarchምደባቸው በፓትርያርኩ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲያገኝ የደብሩ አስተዳደር የጠየቀላቸው አባ ገብረ ኢየሱስ አየለ፣ ላለፉት ሦስት ዓመታት የካርቱም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን በግብዝና በማገልገል ላይ ያሉ መኾናቸው ተገልጧል፡፡

በምድረ ሱዳን የተበተነውን ስደተኛ ኢትዮጵያዊ በማሰባሰብና ለንስሐ የሚያበቃ ትምህርተ ወንጌል በማስተማር፣ ከዐጸደ ሕፃናት ጀምሮ በመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ (እስከ ስምንተኛ ክፍል) ዘመናዊ ትምህርት የሚሰጥበትን ት/ቤት ወደ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ በማሳደግ፣ በገዳሪፍ የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርኩ ታውቆ በማእከላዊነት እንዲተዳደር ምእመኑን በማስተማርና በማሳመን በሰበካ ጉባኤው መተባበር የተደረገውን ጥረትና የተገኘውን ውጤት አስጠብቆና አጠናክሮ ለማስቀጥል ወሳኝ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተመልክቷል፡፡

በሌላ በኩል ከደብሩ ጋራ ያላቸው የሥራ ግንኙነት የታወከው የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ በካርቱም ደ/ሰ/መድኃኔዓለም የጸሐፊነት መደብ ጨምሮ በኬንያና በጅቡቲ አብያተ ክርስቲያን የስድስት አገልጋዮች ቅጥር እንዲጸድቅላቸው ለመንበረ ፓትርያርኩ ጥያቄ ማቅረባቸው ተጠቁሟል፡፡ ምደባቸው እንዲጸድቅ ከተጠየቀላቸው ስድስት አገልጋዮች መካከል፣ ሊቀ ጳጳሱ ቀድሞ በግል መፍቀዳቸው በሚፈጽሙት የአዲስ አገልጋዮች ቅጥር ሰበብ የግል ጥቅም ይሰበስቡበታል የሚባለውን የአዲስ አበባ ኔትወርክ ያንቀሳቅሳሉ የሚባሉት ቀሲስ ግሩም ታዬ እንደሚገኙበትና በካርቱም ደ/ሰ/መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በጸሐፊነት ሊያስመድቧቸው ማቀዳቸው ተነግሯል፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ቀሲስ ግሩምን በጸሐፊነት ለመመደብ ያላቸውን ፍላጎት ቀደም ብሎ በኢንፎርሜሽን ደረጃ ሲከታተለው ቆይቷል የተባለው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምደባቸውን በጽኑ እንደሚቃወም ባለፈው ዓመት ሐምሌ አጋማሽ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጻፈው ደብዳቤ ማሳሰቡ ተዘግቧል፡፡ ‹‹የካህኑን ሕይወትና ሥነ ምግባር ጠንቅቄ ዐውቃለኹ›› ያለው የደብሩ ጽ/ቤት፣ ሰበካ ጉባኤው በጉዳዩ ላይ መክሮ ያስተላለፈውን ውሳኔ ባስታወቀበት በዚያ ደብዳቤው፣ ቀሲስ ግሩም ታዬ ‹‹ከቦታውና ከኅብረተሰቡ ጋራ ተመጣጥነው መሄድ የማይችሉ ናቸው›› ሲል ነው የሊቀ ጳጳሱን የምደባ ዕቅድ ውድቅ ያደረገው፡፡ ከዚህ በመነሣት በኬንያና በጅቡቲ አብያተ ክርስቲያን ምደባቸው እንዲጸድቅ ሊቀ ጳጳሱ ዝርዝራቸውን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጽ/ቤት ያቀረቧቸው የተቀሩት አገልጋዮች ማንነት በሚገባ ሊጤን እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡

በጥቅመኝነት፣ ወገንተኝነትና ብቃት ማነስ ክፉኛ ከሚተቸው የሊቀ ጳጳሱ አስተዳደርና ከማጥመቅና ሌሎች ኢክርስቲያናዊ ተግባራት ጋራ ተያይዘው ሲጎርፉ የቆዩ አቤቱታዎችንና መረጃዎችን ማጠናቀሩ የተገለጸው የፓትርያርኩ ጽ/ቤት፣ ጉዳዩን በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል ለቋሚ ሲኖዶስ በአጀንዳነት ማቅረቡ ተገልጧል፡፡

በአጀንዳው÷ የሊቀ ጳጳሱ አስተዳደራዊ ድክመት በአህጉረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅራዊ አንድነት ከማስጠበቅ፣ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ከማስፋፋትና ከማጠናከር አንጻር የደቀነው ስጋት በቀዳሚነት እንደሚመረመር ይጠበቃል፡፡ መንበረ ጵጵስናው በሚገኘበት ደቡብ አፍሪካ ለተቋቋመው የቅዱስ ያሬድ ገዳም ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ተሰብስቦ በሊቀ ጳጳሱ የግል አካውንት መላኩ የተገለጸው አራት ሚልዮን ብር አጠቃቀም ደግሞ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ተመልክቷል፡፡

4 thoughts on “ለወራት ያለአስተዳዳሪ የቆየው የካርቱም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በችግር ላይ ነው

 1. Anonymous September 19, 2013 at 12:50 am Reply

  እንዲህ ቤተክርስቲያን በሌቦች ትከበብ ?

  እግዚአብሔር መልካም ግዜ ያምጣልን ::

 2. Anonymous September 19, 2013 at 1:34 am Reply

  God help us

 3. fbi September 19, 2013 at 1:44 am Reply

  Do u know who Aba Gebereselase Yeresaw is? He is one of the most disgusting church father…Ye bezu sew eneba Yalebete be church birr begezaw delala weregna yehonu sewochen teketelchu yehan post maderegachu yasaferal ask about him and search it. Pls Sudan yale christian mechem bihon yehan aynetun asetedadari ayefelegem!

 4. Anonymous September 19, 2013 at 7:07 am Reply

  Why you left the nomination & the decision for the approipriate authority???

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: