በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

 • መነኰሳቱ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው
 • አስተዳደሩ ለመነኰሳቱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አልፈቀደም
 • ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ብትውሉ አታድሩም!›› /ጥቃት ፈጻሚዎቹ/

Haro Wonchi Monasteryበደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ወንጪ ወረዳ ሐሮ ወንጪ ቀበሌ በሚገኘው የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ምሽት 5፡00 ላይ ወደ ገዳሙ ቅጽር በተወረወረው ቦምብ ነው፡፡

በገዳሙ የኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ታቦታት መኖራቸውን የገለጹት የገዳሙ አበምኔት መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ኣብርሃ፣ የተወረወረው ቦምብ በገዳሙ ቅጽር ውስጥ ቢፈነዳም በመነኰሳቱ ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል – ‹‹ቢፈነዳም እርሱ ሊቀ መልአኩ በተኣምሩ አንከባሎት ከልሎናልና ጉዳት አላደረሰብንም፡፡››

የአንድነት ገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 17/2005 በቀን ፭/፲፫/፳፻፭ ለሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ለወንጪ ወረዳ መስተዳደርና ፖሊስ ጽ/ቤት በጻፈው የድረሱልን ጥሪ÷ ከዚህ ቀደም የገዳሙን ይዞታ በመጋፋት፣ መነኰሳቱና መናንያኑ ገዳሙን ለቀው እንዲሄዱ ተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ በማሰማት የሚታወቁ 18 ግለሰቦችን በስም ለይቶ በመዘርዘር በጥቃቱ አድራሽነት እንደሚጠረጥራቸውና በቁጥጥር ሥር ውለው ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል፡፡ በስም ከተዘረዘሩት 18 ግለሰቦች መካከል ጌቱ ታደሰ እና መኰንን ካሳ የተባሉ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የኾኑ የቀበሌው ነዋሪዎች በዋና አስተባባሪነት ተጠቅሰዋል፡፡Haro Gedam Appeal

ደብዳቤው ‹‹ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› ሲል የገለጻቸውና በቡድን የሚንቀሳቀሱት እኒህ አካላት፣ በገዳሙና በገዳማውያኑ ላይ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ የተለያዩ ጥቃቶችን  በማድረስ ንብረት ማውደማቸውንና መነኰሳቱን ማሳደዳቸውን ጠቅሷል፡፡ ‹‹ለቀበሌው ብዙ ጊዜ አመልክተናል፤ ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ በመጻፉ መፍትሔ ሳናገኝ እስከ አሁን አለን›› በማለት ከግለሰቦቹ ጥቃት ባሻገር አስተዳደራዊ በደልም እየተፈጸመ እንደሚገኝ ደብዳቤው አጋልጧል፡፡

የወረዳውና ቀበሌው ባለሥልጣናት በተገኙበት ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከነዋሪው ጋራ በተደረገ ውይይት ሕዝቡ በቡድን እየተንቀሳቀሱ በገዳሙ ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ግለሰቦችን የጠቆመ ቢኾንም ተገቢው ርምጃ ባለመወሰዱ÷ ግለሰቦቹ ገዳሙ በሚገለገልበት የውኃ ታንከርና የሶላር ቴክኖሎጂ ላይ ባደረሱት ጉዳት ሲስተሙ ለብልሽት ተደርጓል፤ መነኰሳቱ በሱባኤ ላይ ባሉበት ቀን ለቀን ወደ ገዳሙ ክልል ገብተው በይዞታው ላይ ችግኝ ከመትከል፣ የገዳሙ መውጫና መግቢያ በኾነ ቦታ ላይ አጥር ከማጠር አልተከለከሉም፤ ገዳማውያኑንም ‹‹ከዚህ ቦታ ባትመጡ ይሻል ነበር፤ ለዛሬ ብቻ ነው የምትኖሩት፤ ብትውሉ አታድሩም›› እያሉ በስልክና በአካል በተደጋጋሚ ዛቻና ስድብ ከማስፈራራት አልታቀቡም፡፡

‹‹በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዕለቱ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚሰነዘርብን ጥቃት በዘመናዊ የጦር መሣርያ ጭምር የታገዘና በቀጣይም እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያሳያል፤ በጨለማ  የሚሠሩትን በገሃድ ቀጥለዋል፤›› ያለው የገዳሙ አስተዳደር÷ ነሐሴ ፲፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡40 ዘመናዊ የጦር መሣርያ ታጥቀው ወደ መናንያኑ መኖርያ የመጡት ግለሰቦቹ በመናንያኑ መኖርያዎች ላይ የድንጋይ ውርጅበኝ ማዝነባቸውን፣ ጥይት መተኰሳቸውን፣ ገዳሙን በጥበቃ እንዲያገለግሉ የተቀጠሩ የአካባቢው ተወላጆች ሥራቸውን እንዲተዉ ያልተሳካ ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውሷል፡፡

ገዳሙ ይዞታውን በሕግ ያረጋገጠበት ደብተር እንዳለው የጠቀሰው አስተዳደሩ፡- የሹራብ ሽመና፣ የማር ምርት፣ የዶሮና እንስሳት ርባታን ጨምሮ ራሱን የሚያግዝበት በርካታ የልማት ጅምሮችና ዕቅዶች ቢኖሩትም ፍትሕ እያጡ በሚሰደዱት መነኰሳት ምክንያት ጥረቱ እየተሰናከለ ነው፤ በገዳሙ ምሥረታ ከነበሩት 15 መነኰሳት መካከልም ጸንተው የቀሩት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

ወረዳው በተለይ ከ፳፻፬ ዓ.ም ጀምሮ ከገዳሙ ለሚቀርቡለት አቤቱታዎች ሁልጊዜ ተስፋ ይሰጠናል እንጂ የተጨበጠ ነገር አላስገኘልንም፤ ትኩረትም አይሰጠውም ያለው አስተዳደሩ÷ ‹‹በሰሜንም በደቡብም በምሥራቅም በምዕራብም ያለው ሕዝበ ክርስቲያን ይህን እንዲሰማን እንፈልጋለን፤ እምነታችንን አጽንተን ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን እንሥራ አልን እንጂ የማንንም እምነት አልነካንም፤ ወገን ይድረስልን፤ የድረሱልን ጥሪ ነው የምናስተላልፈው፤›› በማለት የመነኰሳቱንና የመናንያኑን ተማኅፅኖ አሰምቷል፤መንግሥት ለሃይማኖታችንና ለገዳማችን ልማት የማይተኙልንን ፀረ ሃይማኖት የኾኑ ግለሰቦች›› በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲያውልና ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድባቸውም ጠይቋል፡፡

የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ጥቃቱ በተፈጸመባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ መረጃው እንዲደርሰው ሲደረግ የቆየ በመኾኑ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከሚለው ቸልተኝነቱ ተላቆ ገዳማውያኑ አስፈላጊውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እገዛ እንዲያገኙ ፈጥኖ መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡

የሐሮ ወንጪ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም መቋቋም በ፲፱፻፺፪ ዓ.ም መልአከ ሰላም አባ ገብረ ማርያም ኣብርሃ በተባሉ መነኮስ የተጀመረ ሲኾን የተገደመው ደግሞ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሀ/ስብከቱን (ደቡብ ምዕራብ ሸዋን) ከምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት ጋራ ደርበው በሚያስተዳድሩበት በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. እንደኾነ የገዳሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

*                        *                      *

መንሥኤው አክራሪነት ይኹን ጥቅመኝነት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በበርካታ መንገዶች እየተፈጸመ ለሚገኘው ግልጽ ጥቃትና አስተዳደራዊ በደል የወንጪ ሐሮ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አንድነት ገዳም ልዩ አይደለም፡፡ ለመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴ እና ፴፩ መደበኛ ስብሰባ የቀረቡ የ፳፻፬ ዓ.ም. እና ፳፻፭ ዓ.ም. የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች እንደሚያስረዱት÷ እምነታችኹን ለውጡ እያሉ ማወክ፤ የማንነት/ባህል ወረራ፣ የጠብ አጫሪነት፣ የቅርስ ዝርፊያና የታቀደ ቃጠሎ አለመገታት፣ ማስረጃ በሌለው የይገባናል ጥያቄ ይዞታን መንጠቅ፣ ለሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሥራና ለልማት የቦታ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠት፣ በፍትሕ አካል የተሰጠን ውሳኔ ፖሊስ አለማስፈጸም በየጊዜው እየገጠሙን ያሉ ችግሮቻችን ናቸው፡፡

‹‹የልዩ እምነት ተከታይ የኾኑ ባለሥልጣናት በመንግሥት ስም በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርጉት ተጽዕኖና አድልዎ›› በዓመቱ ካጋጠሙ ችግሮች መካከል በዋናነት ያስቀመጠው የ፳፻፭ ዓ.ም. የአጠቃላይ ጉባኤው ሪፖርት፣ በሲዳማ ሀ/ስብከት ሥር የወንዶ ገነት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር ፕሮቴስታንቶች በግድ እየተቀበሩበት መቸገሩን ይጠቅሳል፡፡ ይኹንና ቤተ ክርስቲያን ከሥር ፍ/ቤት እስከ ሰበር ድረስ ተከራክራ መብቷን ብታስከብርም የፍርድ ውሳኔ የሚያስፈጽም አካል በመጥፋቱ ጉዳዩ ወደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሄድ ወይም የክልሉ ፖሊስ ባለመፈጸሙ በሕግ እንዲጠየቅ አለመደረጉን ሪፖርቱ ገልጧል፡፡ በደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ሲጠየቅ በጎ ምላሽ አልተገኘም፤ የልማት ቦታም ያለሊዝ ሊፈቀድ አልቻለም፡፡ በምዕራብ ሸዋ ሀ/ስብከት አራት አብያተ ክርስቲያን በመናፍቃን ተዘርፈው እስከ አሁን የፍርድ ቤት ውሳኔ አላገኙም፡፡

በመንበረ ፓትርያርክ ደረጃ የተጠቃለለው የ፳፻፬ ዓ.ም. የአህጉረ ስብከት ሪፖርት ደግሞ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በሀዲያና ሥልጢ አህጉረ ስብከት የቤተ ክርስቲያን ይዞታ በሌሎች እንደተነጠቀና የመንግሥት ሓላፊዎች ለቤተ ክርስቲያን ፍትሕ እንደነፈጉ፣ ለልማት ሥራ፣ ለግንባታ ፈቃድ መስተዳድሮቹ በቂ ትብብር እንደማያደርጉ ይገልጻል፡፡ በደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት የሦስት አብያተ ክርስቲያን ምእመናን ሰፈር በኢአማንያን በመቃጠሉ ምእመናን አካባቢያቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡

በደቡብ ምሥራቅ መቐለ ሀ/ስብከት ከካህናት ይኹን ከምእመናን ወገን የቅ/ሲኖዶስ መመሪያ ተላልፈውና የቃለ ዐዋዲ ድንጋጌ ጥሰው ሲገኙ ለሚሰጣቸው የቅጣት ውሳኔ አፈጻጸም ፖሊስ ከፍ/ቤት ትእዛዝ ካልተሰጠኝ አላስፈጽምም ብሏል፡፡ በጅማ ሀ/ስብከት እምነታችሁን ለውጡ እያሉ ምእመናንን ማወክ፣ በሰሜን ወሎ እና በመተከል አህጉረ ስብከት የፕሮቴስታንቶች ትንኮሳና የባህል ወረራ፣ የተሐድሶ መናፍቃን በጥቅም ያስከዷቸው ‹ካህናት› ተመልሰው የአገልግሎት ዕንቅፋት መፍጠራቸው በሪፖርቱ ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡

በየአህጉረ ስብከቱ በገዳም፣ ደብርና ገጠር ሥሪት የሚገኙ አብያተ ክርስቲያን ይዞታቸውን በባለቤትነት መታወቂያ ካርታ ለማረጋገጥ የሚያደርጉት ጥረትና ያስገኙት ውጤት የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡ ይዞታን በባለቤትነት መታወቂያ ካርታ ማረጋገጡ አብያተ ክርስቲያኑ ከሰበካ ጉባኤ ዓመታዊ አስተዋፅኦ፣ ከሙዳይ ምጽዋትና ስእለት ገቢዎች ባሻገር ማኅበረ – ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸውና መንፈሳዊ አገልግሎቱን የሚያጠናክሩ የራስ አገዝ ልማት እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡

ይኹንና በአንዳንድ አጋጣሚ በጉልሕ እንደሚስተዋለው፣ በመንግሥት መዋቅር ባሉና የእነርሱን ብልሹ አሠራር ተገን ባደረጉ ግለሰቦችና ቡድኖች በየጊዜው የሚፈጸመውን ግልጽ ጥቃትና አስተዳደራዊ አድልዎ ለመግታትና በብቃት ለመመከት ቅ/ሲኖዶስ በጥብቅ ሊመክርበትና የሚመለከተውን የመንግሥት አካልም በማትጋት የአገልጋዮችንና ምእመናንን መብት ሊያስከብር ይገባል፡፡

በሰላምና ልማት ጉዳዮች ላይ አብሮ መሥራት፣ የዜጎችን ሰላም፣ ደኅንነት፣ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ማረጋገጥ የመንግሥት ግዴታ እንደኾነ በፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴ ዙሪያ የመንግሥትን አቋምና አቅጣጫ የሚያትቱ ጽሑፎች ይገልጻሉ፤ መንግሥታዊ አገልግሎትን የሚሰጥ ማንኛውም ሓላፊ ይኹን ሠራተኛ ተግባሩን ከራሱም እምነት ጭምር ገለልተኛ በኾነና በእኩልነት መንገድ መካሄዱን ማረጋገጥ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡ ሓላፊዎቹና ሠራተኞቹ ገለልተኝነትን ለድርድር ከሚያቀርቡ ስሕተቶች መጽዳታቸውን፣ የአንዱ ወይም የሌላው እምነት ውግንና እንዳላቸውና አድልዎ ለመፈጸም የተዘጋጁ ከሚያስመስሏቸው አቀራረቦች ራሳቸውን መጠበቃቸውን፣ የሕዝቡን ከፍተኛ አመኔታ ባተረፈ አኳኋን ሥራቸውን ማከናወናቸውን ማረጋገጥም ይገባቸዋል፡፡

YeDebre Tabor Metmeke Melkot Debir

በአንድነት ገዳሙ ሥር የሚተዳደረው የደብረ ታቦር መጥመቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት መዘምራን

በተጨባጭ ሃይማኖታዊ ውግንና የሚያሳዩ አመራሮች እንዲሁም ከጥንቃቄ ጉድለት የሃይማኖት አድልዎ እንዳለ አስመስለው የሚያሳዩ ድርጊቶች/ዝንባሌዎች በአፋጣኝ መስተካከል እንደሚኖርባቸው የሚያሳስቡት ጽሑፎቹ፣ ‹‹ካልተስተካከሉም ከመንግሥት ሓላፊነት ተነሥተው የሃይማኖት መምህርነትን ወደሚቀጥሉበት አቅጣጫ ማመላከት ይገባል› በማለት የመንግሥትን አቋም ያስቀምጣሉ፡፡

በቀበሌ ይኹን በወረዳ የመስተዳድሩ አንዳንድ ባለሥልጣናት አይዞህ ባይነትና ሽፋን ያላቸው የሚመስሉትና የሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ንብረትን በተደጋጋሚ ከማውደምና መነኰሳቱን ከማሳደድ አልፈው የቦምብ ጥቃት ለማድረስ የተደፋፈሩት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የኾኑ ግለሰቦች፣ መንግሥት በጽሑፉ ያተተውን የፀረ አክራሪነት አቋምና እንቅስቃሴ በግልጽ የሚፃረሩ ናቸው፤ ግለሰቦቹን በድብቅም በገሃድም የሚደግፏቸው ባለሥልጣናትም ከጥቃት አድራሾቹ ጋራ ‹‹ዘይትና ሞተር ኾነው የሚሠሩ››፣ ዋጋ የሚያስከፍሉ እንጂ በአስተዳደር ሓላፊነታቸው የሰላምና መረጋጋት ምንጭ ሊኾኑ አይችሉም፡፡

ስለዚህም አፋጣኝ የማስተካከያ ርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ችግሩ በየደረጃውና በወቅቱ እልባት እንዲሰጠው ከማድረግ ባሻገር ተቋማዊ ህልውናዋንና ነጻነቷን በሚያስከብር አኳኋን መሠረታዊ መፍትሔ እንዲያገኝ በከፍተኛ አመራሯ አማካይነት መንቀሳቀስ ይገባታል፡፡ ሳይዘገይ ዛሬውኑ!

Advertisements

23 thoughts on “በሐሮ ወንጪ ቅ/ገብርኤል አንድነት ገዳም ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ

 1. Me September 17, 2013 at 2:00 am Reply

  ውድ የሐራ ተዋህዶ አዘጋጆች: መልካም ፈቃዳችሁ ከሆነ ይህንን ጉዳይ ተከታትላችሁ መንግስት የሚወስደውን እርምጃ አሳውቁን:: በጣም ከበቂ በላይ መረጃ ያለ በመሆኑ እርምጃ ለመውሰድ የቀናት ጊዜ በቂ ነው:: ገዳማውያኑ ስም አስቀድመው ከማሳወቃቸውና የቀበሌውና የወረዳው ሰዎች ከማወቃቸውም በላይ በስልክ ዛቻ አድርገውባቸዋል:: የስልክ ንግግር ደግሞ የተመዘገበ እጅ ከፍንጅ የሆነ መረጃ ነው: ድምጹን ማውጣት ይቻላልና:: ልማት ልማት እያለ ጆሮአችንን ያደነቆረ መንግስት ስራ ላይ ለዋሉ ልማቶችና መሳሪያዎች ውድመት የሚወስደው እርምጃ የሚጮህለት ‘ልማት’ እውነተኛ መሆን አለመሆኑን ያሳያልና የሚወስደውን እርምጃ ብታሳውቁን መልካም ነው:: ለገዳማውያኑ: ለእምነታችንና: ለሰብአዊ መብት ምንም አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ይታወቃል ምክንያቱም መንግስት እራሱ እምነታችንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷልና: የእምነቱንና የገዳማውያኑን ጥቃት ለመከላከል ከመንግስት ምንም አይነት እርምጃ አንጠብቅም:: ሰብአዊ መብትም ያው እንደምናውቀው ነው:: ግን አሁን ማየት የምንፈልገው ለልማት ውድመት የሚወስደውን እርምጃ ነውና እባካችሁ ምን አይነት እርምጃ እና በምን ያክል ጊዜ ውስጥ እንደሚወስድ አሳውቁን:: አደራ!

  • Anonymous September 17, 2013 at 12:45 pm Reply

   Enezih dedeboch seytanoch silehonu ekonw yetekedesen bota ena ytebarwku yeteteru menkosatin yemyasadidu egzabher ygesistachew lengeru haylemariyam tbyew erasu.menafik aydel mn mefithe ystachewqlna embtie maryam hiy haymqnotachenen tebikilen

 2. Anonymous September 17, 2013 at 6:48 am Reply

  7) አቡነ ጎርቶርዮስ ካልዕ በሕይወት በነበሩበት እንዲህ ብለው ነበር

  ቤተክርስቲያን ስለ ሁሉ ሰላም ስለፀለየች ክፉዎች በእርሷ ላይ ተነሳሱባት ፤ ክብሯን ሲገፉባት ፡ አጥሯን ሲወዘውዙባት ፡ ክዳኗን ሲያነሱባት ክርስቶስ ይናገር ዘንድ እሷ ዝም ማለቷን ቢያዩ ይበልጥ ተበረታቱባት ፤ ስለክርስቶስ ሁሉን በማክበሯ ፡ ክፉ መሪ ደግ መሪ ሳትል ፡ መልካም ሰው ክፉ ሰው ሳትል ስለሁሉ በመፀለየዋ ፡ ስለሁሉ ምህረትን በማድረጓ ፡ ክፉወች ይቅር ባይነቷን ፡ ትእግስቷን መጠቀሚያ አደረጉት ፡ ሁሉ ተነሳሱባት ፡ የወላድ መካን እንደሆነች ፡ ጥቃቷን የሚመክትላት ልጅ እንደሌላት ሁሉ በሷ ላይ ተነሱ ፤ ልጆቿ ሁሉ አድር ባዮች መሰሉ ፡ ለሆዳቸው
  የሚጋደሉ ፡ ለስጋቸው የሚጨነቁ የመንፈስ ባይተዋሮች መሰሉ ፡ ስለዚህም ክፉወች ፡ የምድር ፈራጆች ፡ ጠላቶች የድፍረት እጃቸውን አነሱባት ፤ ይበልጥም በገዳም ያሉ አባቶቻችን ረሃብ ጥሙን ቻሉ ፡ የስጋ ስሜትን ቻሉ ፡ የአራዊትን ክፋት ቻሉ ፡ ሙቀት ቁሩን ቻሉ ፡ የሰይጣንን ተንኮል ቻሉ ፡ ሁሉን ቻሉ ፡ ሁሉን ስለክርስቶስ በክርስቶስ ቻሉ ፡ የቤተክርስቲያንን ነገር ግን እንደምን ይችላሉ? ስለክርስቶስ ሲሉ በዱር በገደል አለም እንዳልተገባቸው ተቅበዘበዙ ፡ አብዝቶ ስለመፆም ፡ ሳያቁርጡ ስለመፀለይ ፡ ለምስጋና ስለመቆም ፡ ደክመው ከስተው ባዩአቸው ጊዜ ገፍተው ይጥሏቸው ዘንድ ተነሳሱ ፤ መንፈሳውያን ናቸውና ጋሻና ጦር ፡ ወጥመድና ቀስት እንደሌላቸው ባዩ ጊዜ ክብራቸውን ያሳጧቸው ዘንድ ተበረታቱባቸው፡፡ ገዳማውያን አባቶቻችን ግን ምን አድረጉ ዘወትር ስለኢትዮጵያ ስለፀለዩ? ስለ ሐገር መሪው ፡ ስለ ወታደሩ ፡ ስለ ሁሉ ቀን ሳያስታጉሉ በባዶ ሆዳቸው ስለለመኑ? ደመወዝ ክፈሉን አላሉ ፡ ግለጡን ስበኩን አስተዋውቁን አላሉ ፡ ቤታችሁ ወስዳችሁ መግቡን አላሉ ፡ ምን አደረጉና ይናቁ? ምን አደረጉና ከቤታቸው ይባረሩ? ምን አደረጉና ትምክህታቸው ትፍረስ? ምን አድረጉና የአባቶቻቸው ክብር ይነካ? ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በሁሉ መገፋታችንን አስብ፡፡ ክርስቶስ ሆይ አባቶቻችን እንዳስተማሩን አንተ ትናገር ዘንድ እኛ ዝም ብለናልና ትእግስታችንን አፅናልን ፡ የቤተክርስቲያንንም ለቅሶ ሰምተህ ቸል አትበል፡፡ አሜን፡፡

 3. Geda Kumsa September 17, 2013 at 7:14 am Reply

  ለገዳማውያኑ: ለእምነታችንና: ለሰብአዊ መብት ምንም አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ይታወቃል ምክንያቱም መንግስት እራሱ እምነታችንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷልና: የእምነቱንና የገዳማውያኑን ጥቃት ለመከላከል ከመንግስት ምንም አይነት እርምጃ አንጠብቅም!!!!!!!!!!!!

 4. The Angry Ethiopian(ቆሽቱ የበገነው) September 17, 2013 at 8:07 am Reply

  መንግስት የምትሉት ይህ የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አገራችሁን ሲገዛ የነበረው ጴንጤና እስላም ነበር። ይኼንን ማገናዘብ ካልቻላችሁ፣መቼም ቢሆን ዋጋ የላችሁም።እዚጋ መስቀል ታየ፣ እዛጋ ተዐምር ተገለጠ ማለቱ ምንም ፋይዳ የለውም። እንደውም የወያኔ አገልጋይ ካድሬ ቄሶች የሚጠቀሙበት ማደናገሪያ ነው። ተዐምር የሚባለው፣ ሁለቱን ወረበሎች አባትና ልጅ ፀረ ኢትዮጵያውያን በአንድ ወር ውስጥ መልዓከ ሞት ቀስፎ የጣላቸው ጊዜ ነበር። ይኼው ከጫሩም አንድ ዓመት አለፈ – መለስንና ነፍስ አባቱን ማለቴ ነው። ለዛ እግዚአብሄርን አመሰገናችሁ ? ጧፍ አበራችሁ ? ወይስ በጅምላ አገር ዓቀፋዊ ለቅሶ ላይ ተገኝታችሁ እንባችሁን ስታዥጎደጉዱት ነበር ? ተዓምር የሚባለው አገራችሁን የወረራት የመጥፎ ባህል ወረርሽኝ ሲራቆት ነው። ተዓምር የሚባለው አገራችሁን የወረረው የቻይና ጎግ ማንጎግ ሠራዊት እግሬ አውጪኝ ብሎ ከአገራችሁ ሲፈረጥጥ ነው። እንደምንሰማው ከሆነማ እነዚህ ቻይኖች እንደገዢያችሁ ነው የሚታዩት።

 5. biruk September 17, 2013 at 10:39 am Reply

  ውድ የሐራ ተዋህዶ አዘጋጆች: መልካም ፈቃዳችሁ ከሆነ ይህንን ጉዳይ ተከታትላችሁ መንግስት የሚወስደውን እርምጃ አሳውቁን:: በጣም ከበቂ በላይ መረጃ ያለ በመሆኑ እርምጃ ለመውሰድ የቀናት ጊዜ በቂ ነው:: ገዳማውያኑ ስም አስቀድመው ከማሳወቃቸውና የቀበሌውና የወረዳው ሰዎች ከማወቃቸውም በላይ በስልክ ዛቻ አድርገውባቸዋል:: የስልክ ንግግር ደግሞ የተመዘገበ እጅ ከፍንጅ የሆነ መረጃ ነው: ድምጹን ማውጣት ይቻላልና:: ልማት ልማት እያለ ጆሮአችንን ያደነቆረ መንግስት ስራ ላይ ለዋሉ ልማቶችና መሳሪያዎች ውድመት የሚወስደው እርምጃ የሚጮህለት ‘ልማት’ እውነተኛ መሆን አለመሆኑን ያሳያልና የሚወስደውን እርምጃ ብታሳውቁን መልካም ነው:: ለገዳማውያኑ: ለእምነታችንና: ለሰብአዊ መብት ምንም አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ይታወቃል ምክንያቱም መንግስት እራሱ እምነታችንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷልና: የእምነቱንና የገዳማውያኑን ጥቃት ለመከላከል ከመንግስት ምንም አይነት እርምጃ አንጠብቅም:: ሰብአዊ መብትም ያው እንደምናውቀው ነው:: ግን አሁን ማየት የምንፈልገው ለልማት ውድመት የሚወስደውን እርምጃ ነውና እባካችሁ ምን አይነት እርምጃ እና በምን ያክል ጊዜ ውስጥ እንደሚወስድ አሳውቁን:: አደራ!

 6. Anonymous September 17, 2013 at 3:24 pm Reply

  ) አቡነ ጎርቶርዮስ ካልዕ በሕይወት በነበሩበት እንዲህ ብለው ነበር

  ቤተክርስቲያን ስለ ሁሉ ሰላም ስለፀለየች ክፉዎች በእርሷ ላይ ተነሳሱባት ፤ ክብሯን ሲገፉባት ፡ አጥሯን ሲወዘውዙባት ፡ ክዳኗን ሲያነሱባት ክርስቶስ ይናገር ዘንድ እሷ ዝም ማለቷን ቢያዩ ይበልጥ ተበረታቱባት ፤ ስለክርስቶስ ሁሉን በማክበሯ ፡ ክፉ መሪ ደግ መሪ ሳትል ፡ መልካም ሰው ክፉ ሰው ሳትል ስለሁሉ በመፀለየዋ ፡ ስለሁሉ ምህረትን በማድረጓ ፡ ክፉወች ይቅር ባይነቷን ፡ ትእግስቷን መጠቀሚያ አደረጉት ፡ ሁሉ ተነሳሱባት ፡ የወላድ መካን እንደሆነች ፡ ጥቃቷን የሚመክትላት ልጅ እንደሌላት ሁሉ በሷ ላይ ተነሱ ፤ ልጆቿ ሁሉ አድር ባዮች መሰሉ ፡ ለሆዳቸው
  የሚጋደሉ ፡ ለስጋቸው የሚጨነቁ የመንፈስ ባይተዋሮች መሰሉ ፡ ስለዚህም ክፉወች ፡ የምድር ፈራጆች ፡ ጠላቶች የድፍረት እጃቸውን አነሱባት ፤ ይበልጥም በገዳም ያሉ አባቶቻችን ረሃብ ጥሙን ቻሉ ፡ የስጋ ስሜትን ቻሉ ፡ የአራዊትን ክፋት ቻሉ ፡ ሙቀት ቁሩን ቻሉ ፡ የሰይጣንን ተንኮል ቻሉ ፡ ሁሉን ቻሉ ፡ ሁሉን ስለክርስቶስ በክርስቶስ ቻሉ ፡ የቤተክርስቲያንን ነገር ግን እንደምን ይችላሉ?

 7. ሳባይት September 17, 2013 at 4:01 pm Reply

  ከዚህ በላይ አሰተያይት የሰጣችሁ ሚዛናዊና መፍትሄ ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መንግስትን ለመስደብና ማንነታችሁን ለማሳወቅ የምትጥሩና ” በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ “ፈጣሪዎች መሆናችሁ ግልጽ ነው ። መፍትሄው እውነቱን አውቆ እና አሳውቆ እርምጃ እንዲወሰድ ጉዳዩን መከታተል ተገቢ ነው > ሌላው ቦምብ የሚያፈነዳ ፕሮቴስታንት ይኖራል ቢዬ ባልምንም ካለ ግን ብእርግጠኝነት ፕሮቴስታንት ነው ተብሎ ሊጠራ አይገባም ምክንያቱም የነሱ መመርያ “ቀኝህን ለሚመታ ግራ ጉንጭህን ስጠው'” ስለሆነ ምናልባት ሆን ተብሎ በሁለቱ መካከል ጠላትነትን ለመፍጠር የተደረገ የዘመኑ ተቃዋሚዎች ሴራ እንዳይሆን እጠረጥራለሁ ፣ ሁሌም ለኢትዮጵያ “ጦር አውርድ ” እያሉ የሚያሟርቱ እነሱ ስለሆኑ ማለቴ ነው

  • Anonymous September 19, 2013 at 12:09 pm Reply

   አንተ ሌባ መናፈቅ ፕሮቴታንቱና ካቶልኩ አይደለ እንዴ መፅሐፍ ቅዱስ ይዞ ህዝብን ሲያስጨፈጭፍና ሲጨፈጭፍ የነበረው ለዚህም ምስክር ይሆንህ ዘንድሁልግዜ በሀገሪቱ እየተቃጠሉ ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኖች ወይ በመናፍቃን አለበለዚያ በአክራሪ እስላሞች ነው ሌላ ደሞ የጣሊያን ወረራና የእንግሊዝ ወረራን አስታውስ እስቲ አንተ ንገረኝ በየትኛው አጋጣሚ ነው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በዓለም ታሪክ ወረራ ያደረገው ? አንተ ግን መናፍቅ በመሆንህ ብቻ የምታደርጉትን ለመደበቅ ትፈልጋላችሁ እኛ ግን በደንብ ማን ጠላታችን እንደሆነ እናውቃለን ወያኔም ቢሆን መናፈቅ ነው ስብስቡ ይመሰክራል

   እግዚአብሔር ጠላት ዲያብሎስን ያሳፍርልን

 8. Anonymous September 17, 2013 at 8:21 pm Reply

  ሳባይት you said የነሱ መመርያ “ቀኝህን ለሚመታ ግራ ጉንጭህን ስጠው’” ስለሆነ. I believe you have heard at least some of the inhumane actions in Ethiopia protestants did, such as burning a church, pretending to be a female monk and go to a monastery to defile nuns so as to spoil the image of monasticism. Frequently, insulting the orthodox, even using bad words that are not supposed to be used by those who claim to be Christians (rather by the devil). Even recently, a man in DC went to an orthodox church to create problems throwing the Virgin’s icon. More over, it is known that protestants have committed some of the most heinous war crimes in the world. It is easy to read history of protestantism. Any way, your comment implies you are a protestant or tehadiso, who are basically the same, and pretending to be not. Be your self!!

 9. selam September 18, 2013 at 12:41 am Reply

  በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። ( 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3 ቁጥር 12)
  ከቦምብ የባሰ ጥቃት ቢሰነዘር እንኳን ቁምነገሩ በጽድቅ መኖር መቻል ነው እንጂ ጉዳዩን የማንፈልገውን አካል ለመምታት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮፖጋንዳ ማዋል ክርስቲያናዊ መርህ አይደለም። ለእግዚአብሔር ቤት ከእግዚአብሔር በላይ መቆጨት ግብዝነት ቢሆንም ጥንቃቄ ይጠብቃል ማስተዋልም ይጋርዳል። ጥላቻና አካላዊ አፀፋ ፅዩፍ ናቸው። ያሁን ዘመን ጴንጤና ኦርቶዶክስ ከጭፈራቸው ውጪ አንድ ናቸው። የተመሰረቱበትን አለት ረስተው ለምድራዊ ጥቅማቸውና ክብራቸው የተጉ፣ ዘላለማዊ አጀንዳቸውን የረሱ፣ ንፁሁን ወንጌል ከማሰማት ይልቅ ተፈለጥኩኝና ተቆረጥኩኝን ብቻ የሚጮሁ፣ እርስ በርስ የሚነካከሱ፣ በአስተዳደር ላይ የፅድቅ ተፅእኖ ማምጣት ሲኖርባቸው የፖለቲካ ወጥመድ ታናቂዎች፣ ተረትና ፍልስፍና አንጋሾች፣ ከፍቅርና አንድነት ይልቅ ጥላቻና ልዩነትን ሰባኪዎች፣ የስህተት ትምህርትን ከመከላከልና ተኩላውን ከመመንጠር ይልቅ እርስ በእርስ መናፍቅ በመባባል ተወናያጆች፣ ከመንፈሳዊ እሴቶች ይልቅ ቁሳቁስንና ለፅድቅ የማይሆን ስርአቶችን ያስቀደሙበት ዘመን ነው።
  ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን
  የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። ( ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ቁጥር 18)
  አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን
  ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥
  አገልግሎትህን ፈጽም። ( 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4 ቁጥር 5)

 10. Anonymous September 18, 2013 at 6:01 am Reply

  ውድ የሐራ ተዋህዶ አዘጋጆች: መልካም ፈቃዳችሁ ከሆነ ይህንን ጉዳይ ተከታትላችሁ መንግስት የሚወስደውን እርምጃ አሳውቁን:: በጣም ከበቂ በላይ መረጃ ያለ በመሆኑ እርምጃ ለመውሰድ የቀናት ጊዜ በቂ ነው:: ገዳማውያኑ ስም አስቀድመው ከማሳወቃቸውና የቀበሌውና የወረዳው ሰዎች ከማወቃቸውም በላይ በስልክ ዛቻ አድርገውባቸዋል:: የስልክ ንግግር ደግሞ የተመዘገበ እጅ ከፍንጅ የሆነ መረጃ ነው: ድምጹን ማውጣት ይቻላልና:: ልማት ልማት እያለ ጆሮአችንን ያደነቆረ መንግስት ስራ ላይ ለዋሉ ልማቶችና መሳሪያዎች ውድመት የሚወስደው እርምጃ የሚጮህለት ‘ልማት’ እውነተኛ መሆን አለመሆኑን ያሳያልና የሚወስደውን እርምጃ ብታሳውቁን መልካም ነው:: ለገዳማውያኑ: ለእምነታችንና: ለሰብአዊ መብት ምንም አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ይታወቃል ምክንያቱም መንግስት እራሱ እምነታችንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷልና: የእምነቱንና የገዳማውያኑን ጥቃት ለመከላከል ከመንግስት ምንም አይነት እርምጃ አንጠብቅም:: ሰብአዊ መብትም ያው እንደምናውቀው ነው:: ግን አሁን ማየት የምንፈልገው ለልማት ውድመት የሚወስደውን እርምጃ ነውና እባካችሁ ምን አይነት እርምጃ እና በምን ያክል ጊዜ ውስጥ እንደሚወስድ አሳውቁን:: አደራ!

 11. Anonymous September 18, 2013 at 12:19 pm Reply

  እግዚአብሃር ገደዳማቶቻችንን ይጠብቅልን ያለእነሱ ምን የጸሎት ማማ አለንና!

 12. Anonymous September 18, 2013 at 2:48 pm Reply

  Protestants never and never and never do this!!!!

  • Anonymous September 18, 2013 at 7:58 pm Reply

   naive!!

  • Anonymous September 19, 2013 at 12:09 pm Reply

   አስመሳይ መናፍቅ

 13. Anonymous September 19, 2013 at 10:46 am Reply

  This is great lie !!!This is the interest of Orthodox.

 14. Asamenew September 20, 2013 at 10:27 am Reply

  This is completely unacceptable, if it is found really happened and happening. The monastery was there for centuries and no one has the right to displace them. I know there are some people who are politically motivated and want to destroy the relationship with in the church and the surrounding communities. And the government should investigate and take action on those who are responsible to this crime.
  We all are against this and we will follow up and respond any further updates on it. Shame of those who always work on sowing hatred!
  PEACE ON EARTH!

 15. Befekadu Endesrachew September 21, 2013 at 8:12 am Reply

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቃት!!!!

 16. crazy man December 17, 2013 at 7:32 am Reply

  Think globally not locally

 17. crazy man December 17, 2013 at 7:36 am Reply

  peoples who are openminded and civicminded donot do this

 18. teklemedhin March 1, 2014 at 11:45 am Reply

  ይህ ሀሉ ትክክል ከሆነ በቤ/ያኒቱ ከፍተኛ የስልጣን ቦታ ያሉ ሰዎች ኣባቶች ሳይሆኑ ጠላቶች ናቸው ማለት ነው፡፡ሰዎች ሳይበደሉ እንደተበደሉ መንግስትን ሲያጨናንቁ እነዚህ ደግሞ በጋሃድ የሚታይ የፍትህ መጉዋደል የማይታገሉ ሆድ ብቻ ናቸው ማለት ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: