በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከሰማይ ስለወረደው መስቀል

KeSemay Yeworedew Meskel

ከሰማይ ወረደ ተብሎ በጳጳሳት የተጎበኘው መስቀል ለሕዝብ ይታያል

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 13 ቁጥር 713፤ ቅዳሜ መስከረም ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም)

ዓለማየሁ አንበሴ

Addis Admas Logoበአቃቂ ቃሊቲ በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ፣ ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በቀስተ ደመና፣ በመብረቅ እና በነጎድጓድ ታጅቦ ከሰማይ እንደወረደ የተነገረው መስቀል፣ በጳጳሳት የተጎበኘ ሲኾን፣ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሕዝብ እይታ እንደሚቀርብ ተገለጸ፡፡

መስቀሉን ከወረደበት ለማንሣት የሞከረ ወጣት ተስፈንጥሮ ከወደቀበት ለአራት ቀን ራሱን እንደሳተ የሚናገሩ የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ፣ ከምሽቱ 9፡00 ከፍንዳታ ጋራ አካባቢው በብርሃን ተሞልቶ ስናይ የእሳት ቃጠሎ መስሎን ነበር ብለዋል፡፡ እያንጸባረቀ በኃይለኛ ግለት ያቃጥል ነበር የተባለው መስቀሉ፣ በጳጳሳት እና በማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች የተጎበኘ ሲኾን የኢየሱስን ስቅለት የሚያሳይ ወርቃማ ቅርጽ ያለው ነው፡፡

ወደ አቃቂ ከተማ ከሚያስገባው ዋናው የአስፋልት መንገድ በስተግራ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ገላን ጉራ በሚባለው ስፍራ የዛሬ አምስት ዓመት የተቋቋመው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም [የቅድስት] ክርስቶስ ሠምራ ክብረ በዓል እየተከናወነ ሳለ ከሌሊቱ 9፡00 የኾነው ክሥተት ነው የዚህ ሁሉ መነሻ፡፡ ከባድ የፍንዳታ ድምፅ የሰሙና የቀስተ ደመና ቀለማትን የተላበሰ ብርሃን የተመለከቱ ነገሩን ከዝናባማው የአየሩ ኹኔታ ጋራ በማያያዝ ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር የሚሉት የደብሩ መጋቢ፣ ‹‹በነጎድጓድና በኢትዮጵያ ባንዴራ የታጀበ መስቀል ከሰማይ ሲወርድ አይቻለኹ፤›› ብለዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ መስቀሉን ለማየት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የሚጎርፉ ምእመናን በርክተዋል፡፡

ባለፈው ኀሙስ ከአቃቂ ከተማ በማለዳ ተነሥተን ከሁለት ሰዓታት የእግር ጉዞ በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ ስንደርስ፣ ጥቂት ምእመናን በተገኙበት የዕለቱ ቅዳሴ እየተከናወነ ነበር፡፡ ከቆይታ በኋላ ቅጽሩ የመስቀሉን ታሪክ ሰምተው ከአቅጣጫው በሚመጡ ምእመናን ተሞላ፡፡ ‹‹መስቀሉ ከሰማይ ሲወርድ አይቻለኹ›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ ስለ መስቀሉ አወራረድ ገለጻ ማድረግ የጀመሩት ከጸሎተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ነው፡፡

በቅጽሩ ከሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ መስቀሉ ወርዶ ያረፈበትን ስፍራ እያመለከቱ ይናገራሉ፡- ቦታው በቆርቆሮ ታጥሮ ድንኳን ተተክሎበታል፡፡ መስቀሉ ዐርፎበታል ከተባለው ስፍራ ‹‹አፈር›› እየተቆነጠረ የሚቀርብላቸው ምእመናን፣ ‹‹አፈሩን›› እየተመለከቱ የመጋቤ ሐዲስን ገለጻ ያዳምጣሉ፡፡

ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓል ነሐሴ ፳፫ ቀን የጸሎት ሥርዐት ከምሽቱ 5፡00 አካባቢ እንደተጀመረ የሚያስታውሱት መጋቤ ሐዲስ፣ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ አካባቢው በቀስተ ደመና ብርሃን ደምቆ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ለዚህ ልዩ ክሥተት ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር፡፡ ከዝናባማው የአየር ጠባይ ጋራ አዛምደው አቅለለው ነው የተመለከቱት፤›› ብለዋል መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፡፡ የቀስተ ደመናው ብርሃን አንዴ ሲደምቅ፣ አንዴ ሲደበዝዝ መቆየቱን መጋቤ ሐዲስ ጠቅሰው፣ ‹‹ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ነፋስ ለማግኘት በካህናት መውጫ በር በኩል ስወጣ ግን ደብዛዛ የነበረው ብርሃን የበለጠ ደምቆ እንደ ቀን ብርሃን ወገግ ብሎ ታየኝ፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹አሻቅቤ ስመለከት ሰማዩ በነጭ ደመና ተከቦ ተመለከትኩ፡፡ አፍታም አልቆየ፣ በኢትዮጵያ ባንዴራ ቀለማት የተጠቀለለ አንዳች ነገር በዝግታ ከሰማይ እየተገለባበጠ ሲወርድ አየኹ፡፡››

ከቤተ ክርስቲያኑ ቤተ ልሔም አጠገብ ያለውን የአገር አቋራጭ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መሥመር ተሸካሚ ማማ እያመለከቱ፣ ‹‹ከሰማይ እየተጠቀለለ የሚወርደው ነገር ከማማው አካባቢ ሲደርስ ነጎድጎዳማ ድምፅ ማሰማት ጀመረ›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ፣ ‹‹መሬት ላይ ሲያርፍ በከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ አካባቢው የእሳት ንዳድ የመሰለ ብርሃን ሞላው፤›› ይላሉ፡፡ ‹‹ቤተ ልሔሙ ተቃጠለ እያልኹ ብጮኽም ድምፄን የሰማ ሰው አልነበረም፤ ለደቂቃዎች ያህል ለሰዎች እንዳይሰማ ኾኖ ታፍኖ ነበር፡፡ ድምፄ መሰማት ሲችል ግን፣ ካህናቱ ጩኸቱን ሰምተው ተደናግጠው ወደ ውጭ ወጡ፤›› ብለዋል፡፡ አንዳች አደጋ ደርሶ እሳት ተቀጣጥሎ ሊኾን ይችላል በሚል ድንጋጤ ሁሉም እሳቱን ለማጥፋት እንደተሯሯጠ ጠቅሰው፣ ነገር ግን ከአካባቢው ብርሃን በቀር የእሳት ቃጠሎ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል፡፡

‹‹አንድ የቤተ ክርስቲያናችን ወጣት አገልጋይ ወደ ደመቀው ብርሃን ተጠግቶ ለማየት ሞከረ፤ አንዳች ነገር ወደላይ አስፈንጥሮ መሬት ላይ ጣለው፤ ምእመናን ተደናገጡ፤ የኤሌክትሪክ መሥመር ተበጥሶ ኮንታክት ፈጥሮ ይኾናል የሚል ጥርጣሬ ነበር ያደረብን›› ሲሉም ተርከዋል፡፡ ‹‹የወደቀው ወጣት ምላሱ ተጎልጉሎ በወደቀበት ራሱን ስቶ ተዘርግቶ ነበር›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ ከወደቀበት በጥንቃቄ አንሥተን ጠበልና ቅብዐ ቅዱስ ብናደርግበትም አልተሻለውም ብለዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ካህናቱ እንደምንም ወደ ብርሃኑ ተጠግተው የተመለከቱት፡፡ እናም በብርሃን የታጀበ መስቀል መሬት ላይ ዐርፎ አዩ ብለዋል፡፡

ካህናቱና ምእመናኑ በአግራሞት ሲመለከቱ ቢቆዩም የእሳቱ ወላፈን ይፋጃል ያሉት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ በርቀት መጎናጸፊያ ተወርውሮበት እንዲለብስ እንደተደረገ ይገልጻሉ፡፡ የተቋረጠው ሥርዐተ ማሕሌት ከ10፡00 በኋላ የቀጠለ ሲኾን በካህናቱ ትእዛዝ መስቀሉ ወርዶ ካረፈበት ሥፍራ ላይ ማለዳ 12፡30 ድንኳን ተተከለ፤ ብፁዓን አባቶችም በስልክ እንዲያውቁ ተደረገ ብለዋል፡፡ ይኹን እንጂ በማግስቱ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ክብረ በዓል ስለነበር ብዙዎቹ ጳጳሳት ወደ ደብረ ሊባኖስ፣ ቀሪዎቹም ወደ የአድባራቱ ሄደው ስለነበር በዕለቱ መምጣት አልቻሉም ብለዋል፡፡

‹‹ከበላይ አካላት በተነገረን መሠረት ለወረዳው ፖሊስ ካሳወቅን በኋላ የፖሊስ ኃይል አካባቢውን ተቆጣጠረ፤›› የሚሉት መጋቤ ሐዲስ ቅዳሜ ዕለት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት መጥተው መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ለመምጣት ቀጠሮ የሰጡ ጳጳሳት ግን ከአንድ ሰዓት በላይ በረዶ የቀላቀለ ዝናም በመጣሉና ጭቃው የማያስገባ በመኾኑ ከመንገድ ተመልሰዋል፡፡ በማግሥቱ እሑድም አክራሪነትን ለመቃወም ሰልፍ የሚካሄድበት ቀን በመኾኑ መምጣት አልቻሉም፡፡

ሰኞ ዕለት፣ ነሐሴ ፳፯ ቀን በርካታ ጳጳሳት በቦታው ተገኝተው፣ መስቀሉ ዐርፎ ከቆየበት ስፍራ ተነሥቶና በበርካታ ምእመናን ታጅቦ ወደ መቅደስ እንዲገባ መደረጉን መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ ተናግረዋል፡፡ በደረሰበት አደጋ ራሱን ስቶ የቆየው አገልጋይ፣ በአራተኛው ቀን መንቃቱንና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ ወጣቱ ሲጠየቅም፡- ሊያነሣው እጁን ሲሰነዝር ከኋላው አንዳች ሕፃን ልጅ የመሰለ ነገር ጎትቶ መሬት ላይ እንደጣለውና ከዚያ በኋላ የኾነውን እንደማያውቅ መግለጹን መጋቤ ሐዲስ ተናግረዋል፡፡

መስቀሉ ከወደቀበት መሬት ተነሥቶ ሲገባ ከፍተኛ ግለት እንደነበረውና [ያከበሩት] አባት ‹‹እያቃጠለኝ ነው›› እያሉ ሲናገሩ እንደነበር ተገልጧል፡፡ መስቀሉ የሰው ሥራ እንዳይኾን የተጠራጠሩ መኖራቸውን የጠቀሱት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ፣ ‹‹መስቀሉ ከምን እንደመጣ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አቶ እንግዳው የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ፣ መስቀሉ ከሰማይ ሲወርድ እንዳልተመለከቱ ጠቅሰው፣ ‹‹በጳጳሳቱ ካረፈበት ተነሥቶ ወደ መቅደስ ሲገባ ወርቃማ ብርሃን ነበረው›› ብለዋል፡፡ አንዳንድ የአካባቢው ሰዎችም ሌሊቱን ነጎድጓዳማ ድምፅ መስማታቸውንና በማግሥቱም ስለ ክሥተቱ ከቤተ ክርስቲያኑ ካህናት እንደተነገራቸው ገልጸዋል፡፡ ለአካባቢው ጸጥታ በማሰብ መስቀሉ በየዕለቱ ለምእመናን እንዳይታይ ከቤተ ክህነት ትእዛዝ እንደተላለፈ ጠቅሰው፣ መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር መስቀሉን ለእይታ ለማወጣት ቀጠሮ መያዙን መጋቤ ሐዲስ አስታውቀዋል፡፡

*            *           *

 ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል ለማየት ብዙ ሕዝብ ወደ ቡልቡላ እየተመመ ነው

(ኢትዮ ቻናል፤ ቁጥር 416፤ መስከረም ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም)

ዮናስ አማረ

logo-transበአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 በተለምዶ ቡልቡላ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው ፈለገ ግዮን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከሰማይ በተኣምር ወረደ የተባለውን መስቀል ለማየት ሕዝቡ በብዛት እየተመመ ነው፡፡ ነሐሴ ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓል በቤተ ክርስቲያኑ በሚከበርበት ሳይታሰብ አካባቢው በብርሃን መሞላቱን ተከትሎ መስቀሉ ከሰማይ እንደወረደ የዐይን እማኝ ነን ያሉ ሰዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡

ኹኔታውን ለማጣራት ወደ ቦታው አምርተን በነበረበት ወቅት መስቀሉ ወደ ማረፊያው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መግባቱንና በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ማንም ለማየት እንደማይፈቀድለት ቢነገረንም የዐይን እማኝ ነን ያሉ ካህናት ስለ ኹኔታው በዝረዝር ነግረውናል፡- ‹‹ኹኔታው የጀመረው ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ነው›› ሲሉ ገለጻቸውን የጀመሩት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ አስረስ፣ በዚያ ምሽት ካህናቱ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ማሕሌት ቆመው እንደነበርና ከቤተ ክርስቲያኑ በስተምሥራቅ ባለው ቤተ ልሔም አካባቢ ከሰማይ ሰፊ ብርሃን መውረዱንና ነጎድጓድም መሰማቱን፣ ይህን ያዩ በደጅ የነበሩ ምእመናንም ቤተ ልሔሙ የተቃጠለ መስሏቸው ተደናግጠው በመጠራራት በአካባቢው መሰባሰባቸውን በመጥቀስ ያስረዳሉ፡፡

‹‹በቀስተ ደመና ብርሃን ተሞልቶ ከሰማይ እየተገለባበጠ ሲወርድና በቤተ ልሔሙ አካባቢ ሲያርፍ በዐይኔ አይቻለኹ›› ሲሉ የተናገሩት መጋቤ ሐዲስ ፍሥሓ ክሥተቱ ፍጹም የእግዚአብሔር ተኣምር እንደኾነ የገለጹት፡፡

ሌላው የዐይን ምስክር ነኝ ያሉን የደብሩ አለቃ መጋቤ ሃይማኖት ኃይሌ መዝገቡ ሲናገሩ፣ በክሥተቱ ወቅት ቤተ ልሔሙ ሲቃጠል ቆሜ አላይም ያለ ደብሩን የሚያገለግል አቶ ነጋልኝ የተባለ ምእመን በብርሃን ወደተጥለቀለቀው ቦታ መግባቱንና ድንገትም እንደ ኳስ ተወርውሮ መውደቁን ጠቅሰው ምእመኑ ለአራት ቀናት ራሱን ስቶ መቆየቱን ነግረውናል፡፡ ‹‹መስቀል የሰላም ምልክት ነው›› ያሉት ካህኑ እግዚአብሔር እንዲህ ዐይነት ተኣምር ያውም በአዲስ ዓመት መባቻ ላይ በዚህ ማውረዱ በጎ ምልክት እንደኾነ ነው የነገሩን፡፡

ወረደ የተባለው መስቀል በአካባቢው የፈጠረው ከፍተኛ ሙቀት ያለው ኃያል ብርሃን በረድ ሲል ራሳቸው በእጅ ስልካቸው ፎቶ እንዳነሡትና ከቤተ ክርስቲያን መጎናጸፊያ አምጥተው እንዳለበሱት መጋቤ ሃይማኖት ኃይሌ መዝገቡ ጨምረው ገልጸውልናል፡፡

ብርሃን የወረደበት የቤተ ልሔም አካባቢ በመታጠሩና ከካህናት ውጭ የተከለከለ ነው በመባሉ በቀስተ ደመና ተከቦ ከሰማይ ወረደ የተባለውን መስቀል በዐይናችን ለማየት ባይፈቀድልንም መስቀሉ በወረደ ሰዓት በሞባይል ካሜራ የተነሣ ፎቶ ግራፍ ነው ተብሎ በቤተ ክርስቲያኑ በ10 ብር ሲሸጥ ለመታዘብ ችለናል፡፡ ይህንኑ ፎቶ ግራፍ ሰሞኑን በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ሕዝቡ እየተቀባበለው የሚገኝ ሲኾን በርካቶች ክሥተቱን ፍጹም በማመን አስተያየት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

መስቀሉንና የተፈጠረውን ኹኔታ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና የአካባቢው ፖሊስ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ እንደጎበኙት ያነጋገርናቸው ካህናት ገልጸውልናል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ አስፈሪውን የቡልቡላ ወንዝ ድልድይ ተሻግሮ ጭቃው ሳይበግረው ሲተም አይተናል፡፡

Advertisements

48 thoughts on “በገላን ጉራ ፈለገ ግዮን ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከሰማይ ስለወረደው መስቀል

 1. Anonymous September 16, 2013 at 9:43 am Reply

  bewnet egziabher ethiopiyan ybark kemeskelu erdet bereket yasatfen …………………

 2. TADMK September 16, 2013 at 10:07 am Reply

  this is the mercy of God for those who believe in His Cross!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 3. Endale September 16, 2013 at 12:21 pm Reply

  I have not visited the place. I can not verify it! But, it is expected! Our Church in Ethiopia, Egypt and Syria has experienced such miracles. It is a recent memory that Painting of Virgin Mary was seen secreting pure olive oil. This same miracle was seen in Syria and Coptic Church in USA. Many received healing from the collected oil. In Ethiopia, in the 16th century, Light descended in a place called Debrebirhan in recognition to the Great virtues of Emperor Zera-Yacob. Our religion is accompanied by revelations! May God Bless Ethiopia and us all, Amen!

 4. aynalem September 16, 2013 at 12:48 pm Reply

  Alemawuyan dere getsoch eskemikerebut deres,eske zare yet neberachihu?betam yasazenal:enantem teteratrachihu new ende?

 5. Anonymous September 16, 2013 at 2:39 pm Reply

  The Absolute Miracle is the Shading of the Precious Blood of Jesus Christ for the atonement of the Sin of the world.

  We do not have place for your fairy stories. EPCO will soon give clarification about the thunder-Electric short-circuiting.

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:04 pm Reply

   መናፍቅ ዝም ብለህ ተቀመጥ

 6. Daniel September 16, 2013 at 2:56 pm Reply

  I think Jesus is re-telling this generation to believe in Him and then worship Him. Previously, He has said he is the only way to heaven; but many people are not exercising that. ክርስቶስ ግን አዛኝ አምላክ ነውና አሁንም በድጋሚ እየተናገረ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል::

 7. Anonymous September 16, 2013 at 3:27 pm Reply

  amen

 8. Anonymous September 16, 2013 at 5:43 pm Reply

  ይቺ ሀገር እኮ የዛሬ ገዢዎች እንደሚያናፉት አይደለችም እልፍ ግዜ ቢደክሙም እንደነሱ ምኞትም አትጠፋም እግዚአብሔር ይወዳታል እንዲሁም መርሳት የሌለብን የ ድንግል ማርያም የ አስራት ሀገር መሆኗንም ነው ::ዲያብሎስ ዛሬም በሰዎቹ ተሸሸጎ ቢያናፋም እግዚአብሔር ስለማይተወን ሁልግዜ ድል ይነሳል ::መወገድ ለጠላት ዲያብሎስና ለተባባሪዎቹ ይሁን::

  እግዚአብሔር ሁልግዜ እንዲህ በቸርነቱ ይጎብኘን ::

 9. Abera September 16, 2013 at 6:02 pm Reply

  yeminetachihun ewinetegnanet bemetsihaf kidusawi timihirit masireget siyakitachihu enide roman chatolicoch endich ayenet yemilikitoch chaweta jemerachihu???? yegerimal!!! orthodoxin egziabiher kedebiterawoch teret yefewisat!!!!

  • Anonymous September 16, 2013 at 9:25 pm Reply

   ቱልቱላ

  • Anonymous October 28, 2013 at 1:26 pm Reply

   lemamene eneji lemekade atefetene biyanese lematarate mokerena betawora teru newe ayehudaweyane enedanete nberu

 10. Araarsa (@araarsa) September 16, 2013 at 8:58 pm Reply

  AAAMMMEEENNN!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 11. maru September 16, 2013 at 10:10 pm Reply

  To anonymous on September 16, 2:39 pm
  You said fairy tale about Ethiopian orthodox Tewahido Church. Fairy tale is protestantism. How do you worship God while insulting His mother??? Your gang father Luther is burning in hell eternally together with your leader the devil!

 12. The truth September 16, 2013 at 10:10 pm Reply

  Let’s say it’s a miracle. If God wants to show us a miracle why the church hide it from the people?? It’s ridiculous. It’s always unclear why the church wants to make all stuffs secret. How someone beleives the presence of the Arc of the Coventant, the wing of the True Cross in Gishen, and other precious relics without seeing? Could you mention anything in the bible that orders to hide miracles. Show us all the relics, otherwise it’s codswallop!

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:20 pm Reply

   እሺ የኛ መናፈቅ ምስጢርን መካፈል ያለበት አማኙ እንጂ(አማኙም ቢሆን ማወቅ ያለበትና የሌለበት አለ የክህነትን ነገር ስለሚመለከት) ውሻው አይደለም ደሞ እኮ ምስጢር ለሁሉም አይደለም አስታውስ ካህን የነበሩት የ ሌዊ ወገኞች ነበሩ እንጂ ሁሉም እስራኤላውያን አልነበሩም ልክ እንደዚሁም ዛሬም ….. ::እግዚአበሔር የሚመለከው በ እምነት እንጂ በ እጅ ተዳሶ አይደለም ምን አልባት አላውቅም ያንተ የጥልቁ መንፈስ ግን ሲጫወትብህ በአካል እየተገለፀ ስለሆነ አልፈርድብህም ::
   ውሻ ከሰው ማዕድ አይካፈልም :ውስጥህ ያለው የተደበቀው መንፈስ እንዲወጣ ፀልይ ::

   በተረፈ ያልካው የሙሴ ፅላት ለዘመናት ብትመኘውም አታየውም አትልፋ እዛው አዳራሽህ ብትጮህ ይሻልሃል አትድከም ::ከንቱ የከንቱ ከንቱ

 13. sosi September 17, 2013 at 7:10 am Reply

  እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚስተምረውና በበረከት የሚገበኘው በወንጌል እንጂ በተአምራት አይደለም ከዮናስ በቀር ምልክትን እንደማያሳይ እራሱ ክርስቶስ ተናግሯል ጌታችን ደግሞ የተናገረውን የሚሽር አይደለምና እባካችሁ ምእመናን በወንጌል እንጂ በተአምራትና በምልክት የምታምኑ አትሁኑ በክርስቶ ያመነ ስለእርሱም በአፉ የመሰከረ ለመዳን ከዚህ የበለጠ ቀላል ነገር የለምና ሁሉም በላከው በአንድያ ልጁ ይመን

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:02 pm Reply

   እሺ የኛ መናፈቅ እግዚአብሔር ለምያደርገውም ቀናሽ ? ድብን ቅጥል በይ እግዚአብሔር ሁሌ በምህረት ይጎበኘናል ::

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:26 pm Reply

   ክርስትና የመገለጥ እንጂ የፉከራ እምነት አይደለም

  • Anonymous September 30, 2013 at 6:24 am Reply

   kyuhonas milikit beker lela atayum yalew sosit mealit ena sosit lelit bemekabir geta Eyesus Kirsitos Endemikoy lemegilets Yetenagerw new Engi lela milikit Atayum lemalet aydelem, Hawaryatochim bizumilikit siadergu neber. Buzu Gize Geta Milikit siaderig ke ayhudoch fit aydelem ke hawaryatoch fit Neber. Neger gin Bemekabir Sosit ken Yaderw gin lehulum Milikit hono Tayitol. silesih geta ayhudochin ke yuhonas milikit beker lea milikit Atayum Alachew.

 14. Misganaw Zerihun September 17, 2013 at 11:20 am Reply

  This is really a great miracle we have ever heard and as the same time a call to salivation to those who would have a broken heart for repentance. Ethiopia the land of God where very astonishing things have been happening since very ancient times to-date and will continue in this manner until the end of the universe. please praise the God Who is also doing great things to us and mother land. This is the most precious event you will never get anywhere you go and is thankful for he hasn’t neglected us because of our day to day sin and violation of His order. I am proud of being an orthodox christian and born in the holy land of Ethiopia even though I can’t dare to say I am a righteous man in the judgment of God. So,every body do not hesitate to stand on the side of the truth, the truth is just what you are now hearing and seeing, the Holy Cross is the sign and the symbol and the live testimony of our salivation and the road to eternal life. May every human being in the world get the opportunity to hear, to see and turn to repentance for salivation as Jesus Christ has devoted His Life to all the human beings and put his curable words up on the minds of them for ever. Our church and Mahebere kidusan should a say up on the event especially the Mahbere kidusan I am not clear for being silent, what is your mission, God is revealing the secret behind salivation, you have to shout loudly so as to testifying the redemption to the world and to human beings in general that God has been doing great things in the past,at present and in future. whom are you going to afraid of the earthly governors.I have been trying to open your website since I read the event from the facebook in order to have a brief explanation about the matter however you haven’t say any thing about it. that makes me very surprised, please try to be loyal to the truth.
  May the Holy light of the Cross shines to us all.

 15. Anonymous September 17, 2013 at 12:35 pm Reply

  @abera ante pinti menafk gena tqezefalachu

 16. AKLIL GEBRESELASSIE GEBREMARIAM September 17, 2013 at 2:50 pm Reply

  Yekidst dingl mariam lig yetemesegene yhun.

 17. Anonymous September 17, 2013 at 3:54 pm Reply

  abet weshet erebakachu eferu

 18. Anonymous September 17, 2013 at 4:18 pm Reply

  የሚገርም ውሸት የተለመደ ደራማ

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:21 pm Reply

   አሁን እግዚአብሔር ለሚያደርገው ምን አስቀናህ ?ዲያብሎስ

   • Anonymous September 18, 2013 at 6:44 am

    የሆነ ሰው እንዲህ አለ እኔም እስማማለሁ
    “በቦታው የሆነውን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ይኸ ሁሉ ቲያትር ‹‹ባሕታዊ›› ነኝ ባዩ ገንዘብ ለማግበስበስ ከካህናቱ ጋር የፈጠረው ሤራ መሆኑን ራሱም ሆነ አብረው የተሰለፉትም ያውቁታል፡፡ ለመሆኑ ብርሃኑ የታየው ፎቶ ላነሳውና አብሬ አይቸዋለሁ ለሚለው ሰው፣ ብርሃኑ ከሄደ በኋላ መስቀሉ አልነሳ አለ የሚለው ቲያትር እንዴት እንደተጠናቀቀ፣ ‹‹ባሕታዊ›› ነኝ ባዩ እንዴት እንዳቀናበረው እዚያ ያላችሁ ካህናት አታውቁትም? ካህናቱ አልነሳልን አለ ያላችሁትን መስቀል ያነሳውና የያዘው ዲያቆኑ አልነበር???… ማፈሪያዎች ናችሁ፡፡ በፎቶ የምታሳዩት ወርቅማ ቅብ ያለው ዘመናዊ መስቀል ነው… ተነሳ ተብሎ የታየው ደግሞ የእንጨት መስቀል ነው… ታዲያ ማምታታቱ ለምን ይሆን? ይህን ያልተረዳ ሕዝብ ገፈፋችሁት…. ዘራፊዎች፡፡”

 19. Anonymous September 17, 2013 at 7:02 pm Reply

  Teret teret. This is ridicules, ppl we are living in the 21st century. we should stop believing fairy tales like this. it is enough, it is an insult to the thinking mind. how come my ppl be fooled as they were 1000 years ago. We need to grow up, grow up and be more realistic and practical.This kind of thinking is one of the reasons why we are poor in the first place.

  I respect orthodox believers or any religion follower, for the matter of fact I respect human beings Irrespectable of their religion or race. but if they believe like this i have the right to ridicule and disrespect their ideas.

  Chaw

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:23 pm Reply

   እሺ መናፍቅ ለምን አዳራሽህ ዝም ብለህ አትቀመጥም

 20. Ade September 17, 2013 at 7:04 pm Reply

  Teret teret. This is ridicules, ppl we are living in the 21st century. we should stop believing fairy tales like this. it is enough, it is an insult to the thinking mind. how come my ppl be fooled as they were 1000 years ago. We need to grow up, grow up and be more realistic and practical.This kind of thinking is one of the reasons why we are poor in the first place.

  I respect orthodox believers or any religion follower, for the matter of fact I respect human beings Irrespectable of their religion or race. but if they believe like this i have the right to ridicule and disrespect their ideas.

  Chaw

  • Anonymous September 17, 2013 at 7:25 pm Reply

   እሺ የኛ የእውቀት ጥግ የደረስከው/ሽው !!!ቀናህ በዚህም ምን ታደርግዋለሽ ገና ብዙ ልትቃጠይ ትችያለሽ ሰለታወርሽ !!!

 21. Anonymous September 18, 2013 at 8:32 am Reply

  አባ ሕጻነ ማርያም (ከጅማ) እና መጋቤ ሐዲስ ፍስሐ (ከአቃቂ) ህዝብን በማጭበርበር ወንጀል ክስ እንመሰርትባቸዋለን:: እነ ታምራት ገለታ ከተከሰሱበት ጋር ተመሳሳይ ክስ ይገባል:: በሕግ ፊት ቀርበው እውነትቱን ካስረዱ መልካም:: አለበለዚያ ግን ሌሎች እንደእነርሱ አይነት ማጭበርበር እንዳይፈፅሙ መማርያ ጥሩ ይሆናሉ:: መስቀሉም ተአምራት በመስራት ከሰማይ የወረደ መሆኑን ካሳየ ይህም እንደመረጃ ይወሰዳል:: ከሕግ ባለሙያ

 22. Atnafu Nega September 18, 2013 at 1:48 pm Reply

  ይህ ሊገርም አይገባም መስቀሉ ቀርቶ የመስቀሉ ባለቤት በምድር ላይ ተመላልስ ምእመናንስ አስተምሮ የእኛን ሞት ሞቶ በመስቀል ላይ ውሎ ከሲኦል ወደ መንግስተ ሰመያት የመለሰን አምላካችን እግዛአብሔር ለሰው ልጆች ሲል መከራን የተቀበለ አምልክ ነው

  • maru September 18, 2013 at 10:17 pm Reply

   This is a holy church filled with miracles throughout its 2000 years of history. This holy church is unlike no other so called ‘churches’. It has no parallel. It is resided by God and his saints. I am sorry for you protestants. You don’t have place in GOD’s Kingdom. You are the enemies of God and His saints. Ethiopian protestants have the greatest degree of hate on God’s saints. You know who hates the holy church: your father the devil. you satanic protestants stop abusing and insulting our holy church. I am sure dirty protestantism will be wiped out of God’s country in a few years!

 23. Hiwot Gebreyes September 19, 2013 at 12:13 am Reply

  If this news comes bbc news or yahoo and other foreigner news agency you will be trust the news tamere aytayim ayhonem kalshe ya define yechelema astesaseb new. Yehe eras mitat yehonebacheue because of the miracle happen in side orthodox church. we invite to you come and learn. Don’t forget ye egiziabher sira dink endehone!!!

 24. gere ke Tigray September 19, 2013 at 5:44 am Reply

  ተናገሩ ድንቅ ተአምሩን መስክሩ ነውና ለ 19/01/2006 ዓ/ም ለሕዝብ እይታ ይቀርባል የተባለው የክፍለ ሀገር ልጆችም ማየትና አምላካችንን ማመስገን እንድንችል በቴሌቭዥን በቀጥታ ቢተላለፍ መልካም ነው፡፡

 25. ene September 19, 2013 at 5:46 am Reply

  Ere ebakachihu menafikan teamirun aytachihu enkuan atimelesun ende?

 26. getu September 19, 2013 at 12:49 pm Reply

  Do not put your pearls in front of Pigs ” Enquachihun be eriyawoch fit atanuru” because they do not deserve to know the deeds of the Holy Sprit. The protestants one time they shout about “miracle” ” revelation” etc. which is of course all fraudulent. When such true Miracles happen in the true Christian church, the orthodox, they tell us that miracle is not necessary. Let God give you the true wisdom that reveals the true way? Have you ever questioned why you say your sprit shivers and makes you shout in closed door and leaves you when you go out? The disciples of Jesus served life long with the grace of holy sprit they received on the festivity of the 50th day. Your evil sprit (The protestants) is the sprit of Lucifer. It leaves you naked, disturbed, filled with the sprit of insult, arrogance, fraud etc. Your sprit recharges you with such sprit.

 27. አሜን September 20, 2013 at 5:15 am Reply

  አሜን!!!

 28. Kibrom September 20, 2013 at 2:13 pm Reply

  ይህ የደብተራዎቹ ድራማ ነው:: እነሱኮ ለማሳመን ሲሞክሩ ፈጽሞ የክርስቶስና የክርስትያኖች ጠላት በመባል የሚታወቀውንም ዘንዶ አባታችን አባ አረጋዊን ተሸክሞ ወደ ደብሩ አወጣ ብለው የሚያምኑ መጽሐፉን ያልተረዱ ዕውሮች ናቸው:: መስቀሉ ወረደ ብንል እንኳ መጽሐፉ የሚነግረን የተሰቀለውን ክርስቶስ እንጂ የተሰቀለበትን መስቀል እንድናመልክ አልተፃፈም

  • keldoc September 21, 2013 at 4:54 am Reply

   yemigefater meskel ayche alawkm yeminisalemewn new yemawkew silezh ke 2 anu yewishet new lelaw bereket yehu kuta bemin awekachu ebakachu atasedibun

  • Anonymous September 21, 2013 at 6:15 pm Reply

   Dedeb nehe men tawkalhe degemo selabun argawy mewrte medferh dedeb menfke agelbete anbeb bezu kemawrthe befte trafe adis mety heymanot yege awky

 29. ነናተታታ September 21, 2013 at 7:13 am Reply

  አቤት ውሸት

 30. Awoke Kassa September 30, 2013 at 8:09 am Reply

  I believe more than this ,God is with us everything is possible this is great in my life !, I will give prize for God by moving to the place where the miracle takes place thanks glory to God !

 31. Anonymous October 22, 2013 at 10:20 am Reply

  yebetkereesteYane wqetawu hunyta masetlalfe Tere nw

 32. Gucci Sunglasses July 28, 2014 at 5:01 pm Reply

  Great post. I was checking continuously this blog and I’m impressed!
  Very useful information specially the last part 🙂 I care
  for such info a lot. I was seeking this certain information for a
  very long time. Thank you and good luck.

 33. Tsega Abebe February 11, 2015 at 8:26 pm Reply

  Amen!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: