የአክራሪነት ውንጀላ የተሰነዘረበት ማኅበረ ቅዱሳን ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተቃውሞ ሪፖርት/ክሥ ማቅረቡ ተጠቆመ

 • የአክራሪነት ውንጀላው በ‹‹አገር አቀፍ የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ወቅት ማኅበሩንና አገልግሎቱን ከተቀበረ ፈንጂ ጋራ ያመሳሰለውና በአቶ ስብሓት ነጋ አጽንዖት የተሰጠው የአባ ዮናስ ጥቆማ ነው፤ ጥቆማው የተሰማው ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሑፍ ተከትሎ አቶ በረከት ስምዖን በመሩት የውይይት መድረክ ነው፡፡ 
ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን

 • ከሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ተወክለው የመጡት አባ ዮናስ÷ ማኅበሩን በስም ለይተው ባይጠቅሱም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ለቤተ ክርስቲያን ልጆች የሚሰጠው ሥልጠና ትውልዱን ‹አክራሪ ያደርጋል› በማለት፣ በእነርሱም በኩል የመንግሥትንና የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ለመቆጣጠር ይካሄዳል ያሉት እንቅስቃሴ ‹‹በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረ ትልቁ የአክራሪነት ፈንጂ›› እንደኾነ ጠቅሰው ማኅበሩን ቅ/ሲኖዶስ አጽድቆ በሰጠው የአገልግሎት ድርሻው በመጠቆም በከፍተኛ ደረጃ ወንጅለዋል፡
 • ለአባ ዮናስ በቂምና ጥላቻ የተሞላ ውንጀላ ምላሽ ለመስጠት ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው ያላገኙ የውይይቱ ተሳታፊ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከስብሰባው በኋላ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከፍተኛ ሓላፊዎች በተለይ ከሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ጋራ ከፍተኛ ሙግት ገጥመው ታይተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና የሰጠችውና በመዋቅሯ የምትቆጣጠረው ማኅበርና አገልግሎቱ ከአክራሪነት ጋራ መያያዙና ትርጉሙ በቀላሉ እንደማይታይ ያመለከቱት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ሚኒስቴሩ ማኅበሩን ጠርቶ ለማነጋገርና ለመመካከር ሞክሮ እንደኾነ ጠይቀዋል፤ ጉዳዩንም መንበረ ፓትርያርኩ በጥብቅ ይዞ እንደሚነጋገርበት አሳስበዋቸዋል ተብሏል፡፡
 • የአባ ዮናስን ውንጀላና አቶ ስብሃት በውንጀላው ላይ ተመሥርተው ለሚኒስትሩ የሰጡትን አስተያየት ያጸደቁ የሚመስሉት ዶ/ር ሽፈራው ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ማሳሰቢያ በሰጡት ምላሽ ‹‹ማስረጃ›› እንዳላቸው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ የዜና ምንጩ እንዳመለከተው ዶ/ር ሽፈራው በማስረጃነት የጠቀሱት ማኅበረ ቅዱሳን እንደተቋም ሳይኾን የማኅበሩ አባላትና አገልጋዮች ናቸው የተባሉ ግለሰቦች በግል ፕሬሶች፣ በኢሳት ቴሊቪዥንና በቪ.ኦ.ኤ ሬዲዮ ከዋልድባ ገዳም፣ ከዕርቀ ሰላም እና ከ፮ው ፓትርያርክ ምርጫ ጋራ በተያያዘ ያሰፈሯቸውን ጽሑፎችና የሰጧቸውን ቃለ ምልልሶች ነው፡፡
 • በዚህ ሳምንት ከወጣው ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ ጋራ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶ/ር ሽፈራው ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ያሉት አክራሪነትና ጽንፈኝነት ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰጡትን ምላሽ ያጠናከረ ነው – ‹‹አክራሪነትና ሽብርተኝነት በፍልስፍና መንገድ ተፈልጎ የሚታይ ሳይኾን በየዐደባባዩ በግላጭ የሚታይ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው የሚሄዱ ግለሰቦችና ቡድኖች ይህን ድርጊታቸውን በአካል ይፈጽማሉ፤ በመጽሔታቸው፣ በጋዜጣቸው፣ በድረ ገጾቻቸው ያስነብባሉ፡፡ አንዳንድ ጋዜጦች በየቀኑ ከሚተላለፉ የአሸባሪ ጣቢያዎች ናቸው ተብለው ከሚታወቁ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋራ መግለጫ ሲሰጡ ነው የሚውሉት፡፡ ብዙ የተደበቀ ነገር አይደለም፡፡ ከኢሳት ቴሌቪዥን፣ ከመጽሔቶችና ሬዲዮኖች ጋራ አብረው ነው የሚሠሩት፡፡ በዚህ ዙሪያ ወጣቶች እና ሴቶችንም አደራጅተው የሚንቀሳቀሱበት ኹኔታ አለ፡፡ ስለዚህ የተደበቀ ነገር የለም፡፡››
 • ማኅበረ ቅዱሳን መንበረ ፓትርያሪኩን በመወከል በስብሰባው ከተካፈሉ ኀምሳ ያህል ልኡካን መካከል እንደ ጽ/ቤት አልተጋበዘም፡፡ በአክራሪነት ከመፈረጁ ጋራ በተገናኘ ምክንያት አልያም ለልኡካኑ ጥሪውን ያሰራጨው የምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት ችግር ሊኾን እንደሚችል አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ ያም ኾነ ይህ የማኅበሩ ጽ/ቤት በስብሰባው ከተሳተፉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ ከተነጋገረ በኋላ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተቃውሞ ክሥ/ሪፖርት ማቅረቡ ተጠቁሟል፡፡ ጽ/ቤቱ ጉዳዩን ለቋሚ ሲኖዶስ በአጀንዳነት አቅርቦ የበኩሉን አቋምና ርምጃ እንደሚወስድ ተመልክቷል፡፡ 
 • በሌላ በኩል ‹‹የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታ እና ቀጣይ አቅጣጫዎ ›› በሚል ርእስ በግንቦት ወር ፳፻፭ ዓ.ም በመንግሥት አካል መዘጋጀቱ የተገለጸ አንድ ሰነድ በማኅበረ ቅዱሳን መሽገዋል ያላቸው የትምክህት ኀይሎች፣ ‹‹ጽንፈኛ የፖሊቲካ ኀይሎች አካል በመኾን በጋዜጣና በመጽሔት ሕዝቡን ለዐመፅና ሁከት ለማነሣሣት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፤ በስደተኛው ሲኖዶስ በመሸፈንም እያንዳንዱ ሌላ ቀን ኢትዮጵያ የምትባል አገር የሌለች አስመስለው የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል›› በማለት መተቸቱ ተገልጧል፡፡ 
 • ይኸው ሰነድ ‹‹በ፮ው የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ምርጫ ወቅት የታዩ አንዳንድ ዝንባሌዎች ከውስጥም ይኹን ከአገር ውጭ ያሉትን የአክራሪነት አሰላለፎች በግልጽ ያመለከተ ነበር›› በማለት ከገለጸ በኋላ በኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ሽፋን ይንቀሳቀሳሉ ያላቸው ማኅበራት ‹‹የአክራሪነትና የከሰሩ ፖሊቲከኞች ምሽግ ኾነው ማገልገል ከጀመሩ ውለው አድረዋል›› ሲል ይከሣቸዋል፡፡
 • ሰነዱ በቁጥር አብዝቶ የሚጠራቸውና በስም ዘርዝሮ ያልገለጻቸው እኒህ ማኅበራት በፓትርያርክ ምርጫው ‹‹የየራሳቸውን ፍላጎት የሚያሳኩ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍና አሜሪካ ከሚገኘው ስደተኛው ሲኖዶስ ከሚባለው ቡድን ጋራ የዕርቅ ኹኔታ በሚል እንቅስቃሴዎችን እንደሚያደርጉ›› ጠቅሷል፡፡ አያይዞም ‹‹ራሳቸው በፈጠሩት ትርምስ መንግሥት እጁን አስገብቷል ወዘተ እያሉ ኦርቶዶክስ አማኞችን ለማወናበድ ይሞክራሉ፡፡ ‹‹በራሳችንም እንደሌላው ኃይል ሰልፍ ልንወጣ ይገባል›› በሚል የዐመፅና የሁከት ቅስቀሳ ለማድረግ እንደሚፈልጉ ገልጧል፡
 • በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው የአሜሪካ ሲኖዶስ የ፮ውን ፓትርያርክ ምርጫ በማውገዝ መግለጫ መስጠቱን ያስታወሰው ሰነዱ፣ ‹‹[ሕዝቡ] ይህ ኀይል ሰላም እንዳልኾነ፣ የሰላም ጥረቶችን በሙሉ ሲያሰናክል የሰነበተ፣ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ሳይኾን የከሰሩ ፖሊቲከኞች እንቅስቃሴ መኾኑን ግንዛቤ ይዟል፤›› ብሏል፡፡ የ፮ው ፓትርያርክ ምርጫ ‹‹ሰላማዊ፣ አሳታፊና ግልጽ›› ኾኖ መካሄዱን የሚገልጸው ጽሑፉ ‹‹የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሕዝብ ራሱን ስደተኛው ሲኖዶስ ብሎ ለሚጠራው አካል ተከታታይ የውግዘት መግለጫ ጆሮ ሳይሰጥ አልፏል›› ሲል ውግዘቱን አጣጥሏል፡፡ 
 • ለጉዳዩ የቅርብ ክትትል ባላቸው ወገኖች ግንዛቤ መሠረት በማኅበሩ ውስጥ መሽገዋል የተባሉ የትምክህት ኀይሎችን ለማጋለጥና በሕግ ለመፋረድ ይካሄዳል የተባለው የ‹ፀረ አክራሪነት› እንቅስቃሴ የማኅበሩን ሕዝባዊ ተቀባይነት ለማሳጣትና የድጋፍ መሠረቱን ለማሸሽ የተወጠነ ሊኾን እንደሚች ተጠርጥሯልእኒህ ወገኖች እንደሚገምቱት በእንቅስቃሴው÷ ማኅበሩን በአባታዊ ቡራኬ የሚጠብቁትን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች አስተዳደራዊ እገዛ ለማሳጣት፣ አባላቱንም ከማኅበረ ካህናት፣ አጥቢያ ሰበካ ጉባኤያት እና ሰንበት ት/ቤቶች ለመለየትና ለማጥራት ሊሞከር፣ በአንዳንድ ሚዲያዎችም በማጋለጥ ስም መጠነ ሰፊ የስም የማጥፋት ዘመቻዎች ሊካሄድ ይችላል፡
 • መንግሥት፡- የመንፈሳውያን ማኅበራት የፋይናንስ ዝውውርና አጠቃቀም ሥርዐትና ግልጽነት የሰፈነበት ስለመኾኑ በምዝገባ ሕግ ከመቆጣጠር ጀምሮ ‹‹በማኅበራት ውስጥ ያሉኝን አባሎቼን [ኢሕአዴግ] በማንቀሳቀስ ቅኝታቸውን አስተካክላለኹ›› የሚል ዕቅድ መያዙ ተሰምቷል፡፡
 • በመንፈሳውያን ማኅበራቱ ውስጥ ያሉ የኢሕአዴግ አባሎችን በማንቀሳቀስ ‹‹የማኅበራቱን ቅኝት የማስተካከል›› እንቅስቃሴ በሁሉም ክልሎች የሚፈጸም ሲኾን በትግራይና በአማራ ክልሎች የግንባሩ አመራሮችና አባላት ላይ ልዩ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡ በተለይ በክልል ትግራይ የማኅበረ ቅዱሳን ማእከላት የመንግሥት ሠራተኞች የኾኑ የማኅበሩ አባላት ከሥራቸው ወይ ከአገልግሎታቸው እንዲመርጡ እየተገደዱ ስለመኾኑ ተጠቁሟ፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን ከሰሞኑ ‹‹የሰላም ዕሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ሁለት ሳምንት በፊት ‹‹የአክራሪዎችና ትምክህተኞች ምሽግ›› በሚል ስለተፈረጀበት ኹኔታ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ጋራ ለመወያየት በተለያዩ መንገዶች ያቀረበው ጥያቄ በሚኒስቴሩ ፈቃደኝነት ማጣት ተቀባይነት አለማግኘቱ ተገልጧል፡፡ ከዚህ ቀደም የማኅበሩ አመራር በተጠቀሱት የዋልድባ ገዳም፣ የዕርቀ ሰላም እና የፓትርያርክ ምርጫ ጉዳዮች ከሚኒስቴሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ጋራ ለአራት ጊዜ ያህል በመወያየት በጉዳዮቹ ላይ ያሉትን አቋሞች ሚኒስቴሩ የሚሰነዝርበትን ክሥና ወቀሳ ለማስተባበል በሚያስችል ደረጃ ማስረዳቱ ታውቋል፡፡
 • መንግሥት አካሂደዋለኹ የሚለው የፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴ አሁን በሚታየው ስፋት ከመጀመሩ በፊት ማኅበሩ በኅትመት ውጤቶቹ የአክራሪነትንና አሸባሪነትን አደጋ የሚተነትኑ፣ ተከባብሮ የመኖር ባህላችን ጎልብቶ እንዲቀጥል የሚመክሩና የሚያሳስቡ ጽሑፎችን በተደጋጋሚና በጥልቀት ማቅረቡን የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጭዎች÷ በፀረ – አክራሪነት/ጽንፈኝነት ሰበብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከአገራዊ ሰላም አንጻር ብቻ ሳይኾን የቤተ ክርስቲያናችንን ኦርቶዶክሳዊ ማንነት፣ ተቋማዊ ህልውናና ነጻነት ከማስጠበቅ አንጻር በጥንቃቄ እንዲታይ በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡

 Mahibere Kidusan Statement

Advertisements

30 thoughts on “የአክራሪነት ውንጀላ የተሰነዘረበት ማኅበረ ቅዱሳን ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተቃውሞ ሪፖርት/ክሥ ማቅረቡ ተጠቆመ

 1. geezonline September 6, 2013 at 10:33 pm Reply

  ቀጭን ጊዜ። አኹን የምሰጋው፦ የለየላቸው የፖለቲካው ታማኞች ብቻ ሳይኾኑ፤ አጕል ዐዋቆች ነን ባዮች ስሜተ ቀዝቃዞቹም ጭምር፤ ወንድሞቻቸው እና እኅቶቻቸውን አሳልፈው እንዳይሰጡ፤ ወይ ደግሞ ማንም ድንበር ዘሎ ሲወስዳቸው በቸልታ እንዳያልፉ ነው። ለቤተ ክሲያኗም ኾነ ላገሪቱ የማሰባቸው ነገርማ ከተቀበረ ሰንብቷል…

  አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር
  ወውሕድ ሃይማኖት እምእጓለመሕያው!

 2. Anonymous September 7, 2013 at 7:01 am Reply

  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?
  http://www.eotc-mkidusan.org/site/–mainmenu-2/47——
  «ማኅበረ ቅዱሳን ለሁሉም ግልጽ አሠራር አለው»
  http://www.eotc-mkidusan.org/site/–mainmenu-2/35-l—–r–

  http://www.eotc-mkidusan.org/site/–mainmenu-2/50——

 3. Anonymous September 7, 2013 at 9:44 am Reply

  አሁንስ ኸዬ መንግስት አበዛሁ ቃሉ ራሱ ያሰጠላል አክራሪነት ጽንፈኝነት ፡፡ የሃሳብ ልይነት አክራሪነት አይደለም፡፡ መንግስት በምሰራሁ ሥራ ሊሳሳት ይችላል፡፡ ሰህተት ከሆነ ሰህተት ነው ልባል ይገባል፡፡ ማህበረ ቅድሳን የሃይማኖት እንጂ የፖለቲካ ፖርቲ
  አይደለም፡፡

 4. Anonymous September 8, 2013 at 6:43 am Reply

  We have to prying to God to bring peace to Ethiopian people and to change his mind and to think to his remaining life how to back to God or to be Die like his two evil leaders died last year. All this words come from the only and only peoples like SIBIHAT NEGA the enemy of ORTHODOX and AMAHRA if he asks would u like ur job or Mahbere kdusan?
  I’m telling u Old man you will be the next one to be panish u better not to play with Orthodox.

 5. ብላታ September 8, 2013 at 4:35 pm Reply

  መንግሥት፣ ቤተ ክህነትና ማኅበሩ የተሰፉባቸው ቀጭን ክሮች

  ማናችንም ልብ ልንለው ያልቻልነው ቢመስልም ለመቀበል የሚቸግረን ብዙ ነገር አለ:: እንደ አውሮፓ እግር ኳስ ተጫዋች በሁለት ማሊያ የሚጫወተው ማኅበረ ቅዱሳን በርግጠኝነት ሀገር ውስጥ ለብሔራዊ ቡድን ብቻ ሲጫወት በሌላው ዓለም እንደወደደ ብዙ ለከፈለው የሚሰለፍ ነው:: የሚያስገርማችሁ ሀገር ውስጥ ይህ ቡድን በሲኖዶስ ሕግ የሚመራ፣ ሕገ መንግሥት የሚያከብር፣ ተደምሮ በሚመጣ ውጤትም መንፈሳዊ ተቋም ቢባል አይከፋም:: ችግሩ ከሀገር ሲወጡ ነው:: አባላቱ በሁለቱም ሲኖዶስ ውስጥ ከላይ መዋቅር እስከ ምእመን ድረስ አሉ:: አንዳንዴም ቀሳውስቶቻቸውን ጨምሮ ገለልተኛ ናቸው:: ለዚህ ማሳያ በፓትርያርኩ እረፍት ወራት የታየው ውዥንብር በቂ ነው:: ይህ ልዩነት ለምን መጣ ግርታ እንዳይፈጥርባችሁ:: ሆን ተብሎ ግልጽ አሰራር አለን ስሜት ለመፍጠር የሚያገለግል ነው:: መዋቅሩ ግን ተመጋግቦ የሚያድር በመንግሥት ጀሌዎች የተሞላ የገዛ አባላቱንም ሲሰልል የሚኖር ደንበኛ ሲአይኤ ነው:: ለዚህ የተሠራ ለመንግሥት አካላት ሹክ የሚልበት ቀጭን ክር አለው::

  ለመንግሥት የተጫወተውን ሚና ቀላል አድርጋችሁ የምትገምቱ ካላችሁ ትሳሳታላችሁ:: የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉባኤያት የተቋማቱን የወጣቶች እንቅስቃሴ አከርካሪ በመንፈሳዊነት ስም ሰብሮለታል:: የትምህርት ተቋማቱ ጉባኤያት ዛሬ ዛሬ ፎርም ማስሞላት ብቻ እስኪቀራቸው በመንግሥት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ወጣቶቹ እንዲሳተፉ ተግተው ይሰራሉ:: በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ያሉ አባላቱ በቤተ ክርስቲያን ስም የማያምኑበትን አቋም እንዲያራምዱ በአመራሮቻቸው በኩል መልእክት ይደርሳቸዋል:: ይህ ማኅበር ለማን እየሠራ ነው? በየ ሚዲያው ስሙ ገኖ የሚወራው ፈልጎ ባመጣው ሳይሆን ከተሰፋበት ቀጭን ክር የተነሳ ነው::

  በየመሀሉ ለምን የሚል ሕሊናዊ ሙግታቸው እያቀረቡ መንፈሳዊነታቸውንና የግል አቋማቸውን ጠብቀው የሚጓዙ አባላቱን የኔ አይደሉም አላውቃቸውም እስከ ማለት የሚደርሰው ከተሰፋበት ክር እንጂ ሌላ አይደለም:: ቤተ ክህነትና ማኅበሩ አንዳንዴም በሕጻን ጸብ እስኪካሰሱ ይደርሳሉ:: ይህ ከሰው ለሰው የረዘመ ድራማ ለሃያ ዓመታት ሲታይ ማኅበሩ አንዳች ተዓምር ፈጥሮ ለውጥ የሚያመጣ ይምሰለን እንጂ ተመጋግበው ሊኖሩ የተሰፉ መሆናቸው መች ተገለጸልን:: ታዲያ ማኅበሩን መንግሥት ስሙን ቢያነሳ ማኅበሩም ተቃውሞም ሆነ ክስ ለቤተ ክህነት ቢያስገባ ስንተኘው ክፍል እንደሆነ ባናውቅም ጡዘት ላይ መሆናቸውን ግንልንሸሽገው አንችልም:: እንዴት ይጠናቀቅ ይሆን ከደራሲው በቀር ማን ያውቃል? ለማንኛውም ልብ ማንጠልጠሉን ወደነዋል:: የተሰፋችሁበትን ክር ግን አንዘነጋውም::

  • Anonymous September 9, 2013 at 1:32 am Reply

   እሺ አንተ መናፍቅ ቱልቱላ ውስጥህ የተደበቀው ስይጣን ሳይወጣልህ በዚህ ዓለምም በወዲያኛውም ተመሳሳይ ኑሮ መግፋትህ ትንሽ እንኩዋን አያሳስብህም?ከንቱ

 6. Anonymous September 8, 2013 at 7:53 pm Reply

  ምነው ብላታ
  እንዲህ አይነት ደምሳሳ አስተያየት መስጠትህ ማህበሩ ፖለቲከኛ ነው ለማለት ፈልገህ ይመስለኛል ኢህአዴግ አላማውን የሚያሳካለትን አካል እንዴት እንደዚህ ይከሳል በጭራሽ!

  መንግስት እንዲህ አይነቱን ነገር ከ ማህበሩ ጋር የጀመረው ዛሬ አይደለም አስቀድሞም በነ አቶ አባይ ጸሐዬ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር
  መንግስት ማህበሩን ለምን ይከሳል
  1. የማህበሩ አባላት የተማሩ እና በሳል አመራሮች መሆናቸውን ስለሚያውቅ በማንኛውም አጋጣሚ ይህ ሃይል ለመንግስት ስጋት ሊሆን ይችላል
  2. ማህበሩ መንግስት በዋልድባ የፈጸመውን ግፍ እንዲያስተባብል ቢፈለግም ማህበሩ ግን በመረጃ የተደገፈ ሰነድ በማቅረቡ መጥፎ እይታ ውስጥ እንዲገባ ሆናል
  3.በየዩኒቨርስቲው ያለው የግቢ ጉባኤ ተማሪ የማህበሩን አላማ ተገንዝቦ ማህበሩን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው በቤ/ክ የበላይ አካላት(ቅ.ሲኖዶስ) ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ና የ ግቢ ጉባኤያቱን ከማህበሩ ለመንጠቅ የታለመ ነው
  4 ከቀድሞ ፓትርያሪክ ዜና ዕረፍት በሃላ የ ቤ/ክ አንድነት እንዲመጣ በማሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጎ ነበር ይህ ነገር ፈጽሞ ለኢህአዴግ የማይዋጥ ና ለእርሱ የሚመቸውን ለመምረጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከማህበሩ ጋር ስላልተጣጣሙ በመሆኑ

  በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህንን ማህበሩን የመጣል ስራ እንደሚሰራ በቀላሉ መገመት ይቻላል

  ነገር ግን ማህበሩ እንደ ማህበር(አንዳንድ ከማህበሩ አላማ ጋር የማይጣጣም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አባላት እንዳሉ ከግምት መባስገባት) ከፖለቲካ ጋር የማይገናኝ የሃይማኖት ማህበር እንደሆነ የሚያውቀው ያውቀዋል!!!

 7. dalol September 8, 2013 at 7:59 pm Reply

  ምነው ብላታ
  እንዲህ አይነት ደምሳሳ አስተያየት መስጠትህ ማህበሩ ፖለቲከኛ ነው ለማለት ፈልገህ ይመስለኛል ኢህአዴግ አላማውን የሚያሳካለትን አካል እንዴት እንደዚህ ይከሳል በጭራሽ!

  መንግስት እንዲህ አይነቱን ነገር ከ ማህበሩ ጋር የጀመረው ዛሬ አይደለም አስቀድሞም በነ አቶ አባይ ጸሐዬ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር
  መንግስት ማህበሩን ለምን ይከሳል
  1. የማህበሩ አባላት የተማሩ እና በሳል አመራሮች መሆናቸውን ስለሚያውቅ በማንኛውም አጋጣሚ ይህ ሃይል ለመንግስት ስጋት ሊሆን ይችላል
  2. ማህበሩ መንግስት በዋልድባ የፈጸመውን ግፍ እንዲያስተባብል ቢፈለግም ማህበሩ ግን በመረጃ የተደገፈ ሰነድ በማቅረቡ መጥፎ እይታ ውስጥ እንዲገባ ሆናል
  3.በየዩኒቨርስቲው ያለው የግቢ ጉባኤ ተማሪ የማህበሩን አላማ ተገንዝቦ ማህበሩን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው በቤ/ክ የበላይ አካላት(ቅ.ሲኖዶስ) ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ና የ ግቢ ጉባኤያቱን ከማህበሩ ለመንጠቅ የታለመ ነው
  4 ከቀድሞ ፓትርያሪክ ዜና ዕረፍት በሃላ የ ቤ/ክ አንድነት እንዲመጣ በማሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጎ ነበር ይህ ነገር ፈጽሞ ለኢህአዴግ የማይዋጥ ና ለእርሱ የሚመቸውን ለመምረጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከማህበሩ ጋር ስላልተጣጣሙ በመሆኑ

  በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህንን ማህበሩን የመጣል ስራ እንደሚሰራ በቀላሉ መገመት ይቻላል

  ነገር ግን ማህበሩ እንደ ማህበር(አንዳንድ ከማህበሩ አላማ ጋር የማይጣጣም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አባላት እንዳሉ ከግምት መባስገባት) ከፖለቲካ ጋር የማይገናኝ የሃይማኖት ማህበር እንደሆነ የሚያውቀው ያውቀዋል!!!

 8. Anonymous September 8, 2013 at 11:10 pm Reply

  Aye Egziabher Ante Tsadik Amlak neh Be ewinet… Yehe Devil Maheber Yesintun Likawint dem afesese Yezer Politica akahede (Abune Merehan, Abune Paulosin..ena .Megabi Biluy Seifeselassien bemedihanit yegedele kifu mahiber new) yabatochachin geday mahiber new. Ashebari yemilew yansewal keshibir balefe bizu nefisat silegedele ….Geday libal yigebawal betelom litefa yigebal). Yihen yatsafihut ageligay endemehone abalatu yigedelu alilim neger gin lefird yikirebu ena lehizib yasiredu mahiberu gin betelo yizega elalehuuuuuuuu

 9. Anonymous September 9, 2013 at 5:39 am Reply

  Absolutely! MK is pro tplf association. It has never voiced its opposition when the Church’s canon,legal rights and assets were violated by the ruling junta many times in the past 20 years and now too. See, the allegations that the association is implicated to be extremist are just and true except that they exposing the government’s interference in the affairs of the Church. if so, why is that MK says it was not promoting those causes,but it is some members here and there ? This now reaffirms that MK is with the government saying that those who opposed the election of the six patriarch and support peace and reconciliation to take first are terrorists. As a true Church institution, MK had to say: yes we support peace and unity for our Church. instead of agreeing with the government in its labeling of its opposition as terrorist just for they aspire peace and unity for their Church. Come on MK! Is voicing the destruction of Waldiba monastery extremism? If you had not been the servant of tplf, you would have voiced this senseless destruction of historical and religious site.

 10. Anonymous September 9, 2013 at 8:07 am Reply

  As my knowledge of MK and the EOTC is concerned , there is no problem. The church as an organization and MK as one of the association working under the rule and regulation of God, and with rule and the regulation of the Country constitution, never have any hidden agenda. If we critically read all the magazines and news papers of Mk besides religious issue they have some many valuable information to any citizen. On my understanding the government must think a lot before saying unnecessary information on the media. I believe God never let down MK, because all most all members of MK are serving the church.

  Let us Pray on it !

 11. Anonymous September 9, 2013 at 10:16 am Reply

  ምነው ብላታ
  እንዲህ አይነት ደምሳሳ አስተያየት መስጠትህ ማህበሩ ፖለቲከኛ ነው ለማለት ፈልገህ ይመስለኛል ኢህአዴግ አላማውን የሚያሳካለትን አካል እንዴት እንደዚህ ይከሳል በጭራሽ!

  መንግስት እንዲህ አይነቱን ነገር ከ ማህበሩ ጋር የጀመረው ዛሬ አይደለም አስቀድሞም በነ አቶ አባይ ጸሐዬ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር
  መንግስት ማህበሩን ለምን ይከሳል
  1. የማህበሩ አባላት የተማሩ እና በሳል አመራሮች መሆናቸውን ስለሚያውቅ በማንኛውም አጋጣሚ ይህ ሃይል ለመንግስት ስጋት ሊሆን ይችላል
  2. ማህበሩ መንግስት በዋልድባ የፈጸመውን ግፍ እንዲያስተባብል ቢፈለግም ማህበሩ ግን በመረጃ የተደገፈ ሰነድ በማቅረቡ መጥፎ እይታ ውስጥ እንዲገባ ሆናል
  3.በየዩኒቨርስቲው ያለው የግቢ ጉባኤ ተማሪ የማህበሩን አላማ ተገንዝቦ ማህበሩን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው በቤ/ክ የበላይ አካላት(ቅ.ሲኖዶስ) ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ና የ ግቢ ጉባኤያቱን ከማህበሩ ለመንጠቅ የታለመ ነው
  4 ከቀድሞ ፓትርያሪክ ዜና ዕረፍት በሃላ የ ቤ/ክ አንድነት እንዲመጣ በማሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጎ ነበር ይህ ነገር ፈጽሞ ለኢህአዴግ የማይዋጥ ና ለእርሱ የሚመቸውን ለመምረጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከማህበሩ ጋር ስላልተጣጣሙ በመሆኑ

  በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህንን ማህበሩን የመጣል ስራ እንደሚሰራ በቀላሉ መገመት ይቻላል

  ነገር ግን ማህበሩ እንደ ማህበር(አንዳንድ ከማህበሩ አላማ ጋር የማይጣጣም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አባላት እንዳሉ ከግምት መባስገባት) ከፖለቲካ ጋር የማይገናኝ የሃይማኖት ማህበር እንደሆነ የሚያውቀው ያውቀዋል!!!

 12. መነው ብላታ? September 9, 2013 at 10:17 am Reply

  ምነው ብላታ
  እንዲህ አይነት ደምሳሳ አስተያየት መስጠትህ ማህበሩ ፖለቲከኛ ነው ለማለት ፈልገህ ይመስለኛል ኢህአዴግ አላማውን የሚያሳካለትን አካል እንዴት እንደዚህ ይከሳል በጭራሽ!

  መንግስት እንዲህ አይነቱን ነገር ከ ማህበሩ ጋር የጀመረው ዛሬ አይደለም አስቀድሞም በነ አቶ አባይ ጸሐዬ ጉዳዩ ተነስቶ ነበር
  መንግስት ማህበሩን ለምን ይከሳል
  1. የማህበሩ አባላት የተማሩ እና በሳል አመራሮች መሆናቸውን ስለሚያውቅ በማንኛውም አጋጣሚ ይህ ሃይል ለመንግስት ስጋት ሊሆን ይችላል
  2. ማህበሩ መንግስት በዋልድባ የፈጸመውን ግፍ እንዲያስተባብል ቢፈለግም ማህበሩ ግን በመረጃ የተደገፈ ሰነድ በማቅረቡ መጥፎ እይታ ውስጥ እንዲገባ ሆናል
  3.በየዩኒቨርስቲው ያለው የግቢ ጉባኤ ተማሪ የማህበሩን አላማ ተገንዝቦ ማህበሩን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ከፍተኛ ድርሻ ስላለው በቤ/ክ የበላይ አካላት(ቅ.ሲኖዶስ) ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ና የ ግቢ ጉባኤያቱን ከማህበሩ ለመንጠቅ የታለመ ነው
  4 ከቀድሞ ፓትርያሪክ ዜና ዕረፍት በሃላ የ ቤ/ክ አንድነት እንዲመጣ በማሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርጎ ነበር ይህ ነገር ፈጽሞ ለኢህአዴግ የማይዋጥ ና ለእርሱ የሚመቸውን ለመምረጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ከማህበሩ ጋር ስላልተጣጣሙ በመሆኑ

  በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ይህንን ማህበሩን የመጣል ስራ እንደሚሰራ በቀላሉ መገመት ይቻላል

  ነገር ግን ማህበሩ እንደ ማህበር(አንዳንድ ከማህበሩ አላማ ጋር የማይጣጣም እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አባላት እንዳሉ ከግምት መባስገባት) ከፖለቲካ ጋር የማይገናኝ የሃይማኖት ማህበር እንደሆነ የሚያውቀው ያውቀዋል!!!

 13. ብላታ September 9, 2013 at 12:01 pm Reply

  ክቡር DALOL ምነው እርስዎ ራስዎ?
  ስውር ስፌቱን
  ገልብጠው ይመልከቱ

  የዋህነት ነው ለማለት በሚያስቸግር ስልት ላቀረቧቸው ነጥቦች መከተሪያ ላብጅለት ሳይገባ አይቀርም::
  * የማኅበሩ ሰዎች እንደሚሉት በፍጹም ስጋት ሊሆን አይችልም::
  እርስ በርስ መካሰስ የዘመናችን የወዳጅነት መገለጫ መሆኑን በፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና በመንግሥት መካከል የነበሩትን ሰጣገባዎች ማስታወስ በቂ ነው:: ድራማው አልቆ እንደ እንትና የተወነልን እየተባለ ካልተዋወቀ አላምንም ማለት ይችላሉ:: ደግሞስ የማኅበሩ ስጋት መሆን እውን ሆኖ መንግሥት እንቅልፍ ሊወስደው ነበር? እንደ እውነት መንግሥት የሌለበት የሰፈር ዕቁብስ አለ እንዴ በዚህ ምድር?

  * በዋልድባም ጉዳይ ማኅበሩ ከመንግሥት የተለየ አቋም ይዟል ብለው እንዳያስቡ::
  የተለየ አቋም ከነበረም ሰሜን አሜሪካ እንደተባለው “የግንቦት ሰባትን ከበሮ” ሲመቱ የከረሙት ሰዎች ካልሆኑ ልዩነት አልነበረም:: ይልቁንም በኩርፊያና በንትርክ ከሀገር ውስጥ መሪዎቹ ጋር መኳረፋቸው ይሰማል:: የአንዳንድ ግለሰቦች አድርገው ካልወሰዱትም ሞግተው የነበሩ ባለ አቋም የማኅበሩ ሰዎችም እዚሁ ማእከል ላይ እንደነበሩ አይዘንጋዎ:: የማኅበሩ የምንለው ግን ግለሰቦች ያራመዱትን ሳይሆን በመጨረሻ የተደረሰበትን ድምዳሜ ነው:: በዚህ ድምዳሜ ማኅበሩ ምን አለ? ያለው ነገር ከመንግሥት ጋር እንዴት ተለያየቦ? እንደ መርካቶ ነጋዴ በሁለት ሰነድ ሪፖርት ማቅረብ እንደጀመርን ማን በነገርዎ::

  * የግቢጉባኤያቱን በራሱ ጊዜ ማኅበሩ በንዝህላልነት ቸል እያለ ካላስወሰዳቸው በቀር ማንም እንደማይነጥቀው የታወቀ ነው::
  መንግሥት እንዴት እንደሚጠቀምባቸው ካላወቁ እርስዎ ወይ በግቢ አላለፉም አልያም በጣም ሰንብተዋል:: የማኅበሩ አብዛኛው ተመዝጋቢ የኢሀዴግ አባል መሆኑን ያረጋገጠልን ማን ነው? ትናንት መንፈሳዊነት አይደለም የተባለው ባለሥልጣንነት ዛሬ ምን እየተባለ እንደሚሰበክ አልሰሙም ሌሎች ቤተ እምነቶች ሥልጣኑን ይዘው ቤተ ክርስቲያንን እያጠቁ ነውና ተሰለፉ ተብሏል:: አሁን እያወራን ያለነው እውነታው ላይ አይደለም:: ይህ ስብከት ከማኅበሩ መተዳደሪያና የትላንት አስተምህሮ ጋር ለምን ተለየ? የአቋም ለውጥ አድርጓል አልያም የውስጥ ስፌቱ መገለጥ ጀምሯል::

  * በፓትርያርክ ምርጫ ማኅበሩ ስለነበረው አቋም እርስዎ የተጠቃ አድርገው ገልጸዋል::
  ይህንን ግን የማኅበሩ ሰዎች አይሉትም፣ አያስተባብሉትምም:: ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ዓይነት አቋም አራምዶ አልተሳካለትም ሊሉት በማይችሉበት መልኩ፥ የተማረ ኃይል ተብሎ ከሚታሰብና ቤተ ክርስቲያኒቱን በቅርበት ያውቃታል ተብሎ ከሚገመት ክፍል የማይጠበቅና ያልተሰፈረ አቋም አራምዶ የተሸነፈበት ታሪክ የቅርብ መሆኑን አይዘንጉ:: ይህ ሁሉ ግን አስቀድሜ እንደነገርኮ ከተሰፋበት የማንነት ክር የተነሳ ነው::

  ልጆች እያለን አባታችን ተቆጥቶ ወይም ገርፎን እናታችን ጋር ያለቀስነው ዓይነት ልቅሶ የከሰስነው ዓይነት ክስ ነው ማኅበሩ መንግሥትን ለቤተ ክህነት የከሰሰበት ክስ ያላዘነበት ማላዘን:: ታዲያ እንዴት ይፈታ ይመስልዎታል? ቤተ ክህነት ምን ብሎ ይመልስልኛል ብሎ ነው ክስ ያቀረበው? ሳይታለም የተፈታ አቤቱታ ይልዎታል ይሄ ነው:: ወደ ሕግ አካል ይሄዳል ብለው ይገምታሉ? ወይስ ቤተ ክህነት ማስጠንቀቂያ ትሰጥለታለች? እናንተ ቤት ይህ ሲገጥም እናትዎ አባትዎን ይቆጡልዎት ነበር? ሊሆን አይችልም:: ያያሉ የተወራው ተወርቶ ተራግቦና ተጩሆ ሲያበቃ ሁሉ ይረሳል:: የፖለቲካውን አጀንዳ መቀየሪያ ለትኩረት መሳቢያነት ካልሆነ ፋይዳ የሌለው የሲኒ ላይ ማዕበል ነው::
  ክቡር DALOL ይህንን ስፌት ገልብጠው ካላዩት ሁሌም ይሳሳታሉ::

  • Anonymous September 9, 2013 at 2:03 pm Reply

   አስመሳይ መናፈቅ ዝም ብለህ አታውራ ካድሬ

   • Anonymous September 18, 2013 at 1:38 pm

    ለዘንዶውም የስድብ አፍ ተሰጠው የሚለውን አንብብው ይሆንን

 14. Anonymous September 9, 2013 at 12:45 pm Reply

  ሐራውያን፡- ማኀበረ ቅዱሳን ለማዳን በሚል ሽፋን ወንድሞችን መስዕዋት ለማድረግ የተያዛቹት መንገድ ብዙም አልተመቸኘም፡፡

  • Anonymous September 9, 2013 at 2:00 pm Reply

   ማነው መሰዕዋት የሚሆነው ከ እግዚአብሔር የሆነ ነገር ሲፈርስ አይተህ ታውቃለህ ::

 15. Anonymous September 9, 2013 at 1:18 pm Reply

  አህያውን ፈርቶ ዳውላውን

 16. Anonymous September 9, 2013 at 1:37 pm Reply

  ሰው የመሰለውን ሊናገር ይችላል፡፡ ሲናገርም ደግሞ የራሱን ጥቅም እና ዓላማ ከማሳካት አኳያ ሁኔታውን አመቻችቶ ነው፡፡ ሰው ሁሉ ሊረዳው የሚገባ አንድ አብይ ጉዳይ አለ፡፡ እንደሚባለው ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው የተነሱ ፖለቲከኞች እንዳሉ ሁሉ ለብዙዎች ግልፅ የሆነ ነገር ግን በይፋ ያልተነገረ ፖለቲካን ሽፋን አድርገው ወደ መንግስታችን የፖለቲካ መድረክ የገቡ የሃይማት ሰዎች መኖራቸው እንዲህ ላለው ውዥንብር መፈጠር ምክንያት ሆነዋል፡፡ እነሱ እንደሚሉት ማኅበረ ቅዱሳን የጽንፈኞች/የአክራሪዎች ምሽግ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ዶግማና ቀኖና መጠበቅ፣ለቤተ ክርሰቲያኒቱ በሁለንተናዊ ልማት የወደፊት እመርታ ማምጣት፣ሀገር ወዳድና ለሀገራዊም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ልማትና ዕድገት የሚተጋ ወጣት በመቅረፅ ከቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር በመሆን የታዘዘውን የሚፈፅም የቤተ ክርስቲያን ልጆች ስብስብ እንደሆነ እራሳቸው ከሳሾቹ ያውቃሉ፡፡ ይሄ ደግሞ እነርሱ ፖለቲካን ሽፋን አድርገው ለቆሙለት ስውር ዓላማ የማይስማማ በመሆኑ ያለ በቂ መረጃ ማኅበሩን ይከሱታል፤የተለያየ ስምም ይሰጡታል፡፡ይህ ደግሞ የዲያብሎስ ስራ ነው፡፡ እርሱም የታጠቀው ዝናር ጥይት እስኪልቅ የእግዚአብሔርን ልጆች ከመዋጋት አያቆምም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሆነ ግን ያሻንፋል፡፡የመንግስት አካላቱ ራሳቸውን በጥልቅ ቢመረምሩ መልካም ነው፡፡

 17. newyemariam September 9, 2013 at 3:05 pm Reply

  Betam yasazinal ayit yelelebetin dawa kememeniter sebilachin eyetebela yalew beyet bekul new yemilewin atarito memeliket lehagerim lewegenim yemitekim yimesilegnal endyaw le balance yakil weinim degimo letedebeke alama sibal meferej lemengistim bihon yemitekim ayimesilegnim. Degimom eko kim lemekiref yimesilal Dr shiferaw be EOT betechrstian lay eyaramedu yalut akuwam ejig gimit wust yemiket new kand halafinet kalebetina ketemare sew ayitebekim ehe gundan belelebet esat manided ejig adegegna new selamawiwin selamun atintekut atirtachihu eyu enji ende menajo yemayimeleketewin akal atanekaku.

 18. mebrate regasa September 9, 2013 at 5:50 pm Reply

  Yh mahber endayfers berttachhu sruEGZEAEBHER KENANTE GAR YHUN

 19. Anonymous September 10, 2013 at 9:46 am Reply

  This is not new thing. Remember the past history, the same problem was happens, may be it also happens in the future. The key is free from the agenda of this thing.

 20. Anonymous September 10, 2013 at 11:28 am Reply

  In view of the history of the church, christianity was not preached through violence and war. It was through the blood and sacrifice of Jesus Christ. According to the Revealtion of John, the extent through which Chritstians experience because of who we are unavoiadable. In my view what is most important is to live according to the teachings of Juses Christ and leave the rest to Him. DearChristian brothersand sisters let us pray.

 21. Anonymous September 10, 2013 at 11:53 am Reply

  Ashebarinet be EOTC bota yelewum! Sew megidel beEOTC ayatsedikim (Yasikoninal). Wuguz Keme Arios Shiferahu Be Siltane Abew Hauariat.

 22. Bezabih September 10, 2013 at 11:58 am Reply

  Wuguz Keme Arios Shiferaw. Ashebarinet EOTC bet Yasikoninal.

 23. Anonymous September 11, 2013 at 11:48 am Reply

  egziabhre slamun yamta mk ybtkerstyan andu akle nwena menem ayhonem (tore kftawe wra yftawe >endmibalwe mk huneme zime belo serawen yesera balbtu dgemo hulunem yawqebtal |||

 24. Anonymous September 17, 2013 at 8:29 am Reply

  wore bicha

 25. Anonymous October 3, 2013 at 1:19 am Reply

  no matter what we say all of us who follow mahberkedusan are in shame and scared because what they say is not what they do. Their top representatives are look discent out side but are like snake inside. They even can’t say one wedase mariam but they try to undermind our respected church fathers, try to kick them out from church as possible , creat different church and bring division in the church we all now that we all ask God to give you mind or someting. mahberkedusan all of your orginal followers and backed now they don’t say good about you. you need to learn to be a childrens not like you know every thing. As the same time I respect true christan brothers and sisters who work hard in truth thinking this mahber will help the orthodox church.

 26. Elbethel October 3, 2013 at 2:33 am Reply

  Ewunet Botawan Atelekim, manachinem binehone tsenten megegnete newu yemiyawatan.
  Yenigus liji Ayerebeshim Ayerebetebetem , Egna christyanochi Degimo Ye negestat nigus yehonewu Abatachin Nigusachin yemiyaderegewun hulu betsega enekebelalen, betesefam entebekalen.
  Egzeabhere kehulachin Gar yehun!
  Amen

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: