ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም: በዋልድባ ገዳም እና በ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ የተፈጠሩ ዝንባሌዎችን ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ላሉት አክራሪነት/ጽንፈኝነት›› በጉልሕ ማሳያነት አቀረቡ

 • ‹‹በስደተኛው ሲኖዶስ የተሸፈኑና በማኅበረ ቅዱሳን የመሸጉ የትምክህት ኀይሎች የግንቦት ሰባትን ከበሮ ሲመቱ ከርመዋል››

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባዘጋጁትና ከነሐሴ ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በተካሄደው ‹‹አገር አቀፍ የሰላም እሴት ማጎልበቻ ጉባኤ›› ውይይት ከተካሄደባቸው ጽሑፎች መካከል የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ ያቀረቡት ጽሑፍ ይገኝበታል፡፡

Dr Shiferaw Teklemariam,Minster of Minstry of Federal Affairs

ፎቶ: ሽግግር ሃገራዊ መጽሔት

በሰባት ንኡሳን አርእስት ተከፋፍሎ በስፋት የቀረበው ጽሑፋቸው÷ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥት አንጻር እንዴት እንደሚታይ፣ በአገራችን ይታያሉ ያሏቸውን የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች፣ አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን የማስፋፊያ ስልቶችን፣ የአክራሪ/ጽንፈኛ ኃይሎች መነሻና መድረሻ ምስጢር፣ ሃይማኖትን ሽፋን ስላደረጉ የአክራሪነት አደጋዎች እና አክራሪነትን/ጽንፈኝነትን በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ መሠራት ይገባቸዋል ያሏቸው ስድስት የመፍትሔ ሐሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡

በሚኒስትሩ ጽሑፍ አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቃል የተበየነው በሦስት መንገዶች ነው፡፡ ይኸውም አክራሪነት/ጽንፈኝነት÷ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፯ ንኡስ አንቀጽ ፫ ዜጎች የፈለጉትን እምነት የመከተል መብት እንዳላቸው የተደነገገውን በመተላለፍ የሃይማኖትና እምነት ነጻነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፳፭ ስለ እኩልነት መብት በሚደነግጋቸው ንኡሳን አንቀጾች በሃይማኖቶች መካከል የማበላለጥ ጉዳይ እንደማይኖር የተቀመጠውን ድንጋጌ በመጣስ የሃይማኖት እኩልነትን በተግባር ለመናድ መንቀሳቀስ ነው፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ ስለ መንግሥትና ሃይማኖት መለያየት በግልጽ የተቀመጠውን ድንጋጌ በመፃረር መንግሥታዊ ሃይማኖት ወይም ሃይማኖታዊ መንግሥት ለመመሥረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡

አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል ደረጃው ይለያይ እንጂ በሁሉም ሃይማኖቶች ሽፋን እንደሚንቀሳቀስ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ዓለም አቀፋዊና ከባቢያዊ ገጽታም ያለውና የሚመጋገብ እንደኾነ ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህ እኔን የሚመለከተኝ አይደለም የሚል ሃይማኖትና አገር ይኖራል ተብሎ እንደማይታሰብ፣ እንደየአገሩ የሕዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ታሪክ፣ ከድህነትና ኋላቀርነት ተጋላጭነት የመላቀቅ፣ የሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት የብዝሃነት አያያዝ ጥበቃ ዋስትና ሊለያይ እንደሚችል ይናገራሉ፡፡

በአገራችን በሁሉም ሃይማኖቶች (በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን፣ በእስልምና ሃይማኖት ሽፋንና በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሽፋን) የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር አራማጆች ከሃይማኖቱ መሪዎች ያልተላኩና መነሻቸውም መድረሻቸውም ሃይማኖታዊ ሳይኾን ፖሊቲካዊ መኾኑን ይጠቁማሉ፡፡

ከዚህ በታች ሚኒስትሩ ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ለሚሉት ‹‹የአክራሪነት እና ጽንፈኝነት አስተሳሰብና ተግባር›› በማብራሪያነት የሰጡት ገለጻ ለሐራውያን ቀጥተኛ መረጃና ማገናዘቢያ ይኾን ዘንድ በጽሑፋቸው በሰፈረበት ይዘቱ ቀርቧል፡፡

*                       *                    *

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በንጉሡ ዘመን የመንግሥት ሃይማኖት እንደኾነች በ1948 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት የተደነገገና እስከ ንጉሡ ሥርዐት መውደቅ ድረስ የቀጠለ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ በዚያን ዘመን ንጉሡና የገዥ መደቡ አካላት ለሥልጣን ማራዘሚያ፣ የጥቅም ማካበቻና የሌሎች እምነት ተከታዮችን በማሸማቀቅ አንድ አገርና አንድ ሃይማኖት ፍልስፍና ለማራመድ ተጠቅመዋል፡፡

በሌላ በኩል ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንግሥት ሃይማኖት ገጽታ የተላበሰች ብትኾንም የውስጥ ነጻነት አልነበራትም፡፡ የጳጳሳትና የዲያቆናት ሹመት ሳይቀር በመንግሥት የሚወሰንና የሚጸድቅ ስለነበር መንፈሳዊም ይኹን አስተዳደራዊ ነጻነት ያልነበራት ነበረች፡፡ በሌላ በኩል የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ከገዥዎች አስተሳሰብ በተለየ ኹኔታ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ጋራ አብሮ በሰላም በመኖር የሺሕ ዓመታት ታሪክ የነበረው እንደኾነ ደጋግመን አውስተናል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ኾኖ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የተረጋገጠው የሃይማኖት/እምነት ነጻነት፣ የሃይማኖቶች እኩልነት እና መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚለው መርሕ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ክብርና ሞገስ፣ ታሪክና ጥቅም የነፈገ አድርገው የሚያስተጋቡ ግለሰቦችና ቡድኖች አሉ፡፡ እነዚህ ግለሰቦችና ቡድኖች የሃይማኖት/እምነት ነጻነትን፣ የሃይማኖት እኩልነትን፣ መንግሥታዊ ሃይማኖትም ይኹን ሃይማኖታዊ መንግሥት እንደማይኖር የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ይጥሳሉ፡፡

ከሃይማኖት/እምነት ነጻነት አኳያ ሲታይ የሌላውን እምነት ትክክል ነው ብሎ ለመውሰድ ማንም እንደማይገደድ ቢታወቅም የሌላውን ሃይማኖት የተለያዩ ስያሜዎችን እየሰጡ የማብጠልጠልና የማሳነስ አመለካከትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ይታያሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከሌሎች ሃይማኖት ጋራ እኩል ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፤ ይኽም ክብሯንና ታሪኳን የሚጎዳ ነው በሚል ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እንደማሳያም የአማኝ ቁጥራችን ብዙ ነው፤ ታሪካችን ረዥም ነው በሚል ለመከራከር ይሞክራሉ፡፡

ሃይማኖቶች እኩል ናቸው በሚል የተቀመጠው ድንጋጌ የአማኝ ቁጥርንና የሃይማኖቶችን ታሪክ የሚደፈጥጥ ሳይኾን የአገራችን ሕዝቦች እንደ ዜጋ በነጻ ፍላጎታቸውና ምርጫቸው የያዙት አመለካከት – ሃይማኖትና እምነት ከሌላኛው እንደማይበልጥና እንደማያንስ ብሎም ሁሉም ዜጎች የዴሞክራሲያዊ መብት ተጠቃሚ መኾናቸውን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ይህን ሕገ መንግሥታዊ መርሕ ዐውቀው በመጣስ በዙሪያው የትምክህት ኀይሎች የሚሰበሰቡበት ገጽታም የሚታይበት ኹኔታ አለ፡፡

በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን ከሚካሄዱት ቅስቀሳዎች ‹‹የበላይነትን አጥተናል፤ ይህንኑ መመለስ ይገባናል›› የሚል ሕገ መንግሥታችን የሻረውን አስተሳሰብ የሚደግፍ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች››፤ ‹‹አንድ አገር አንድ ሃይማኖት›› ወዘተ. . . ጉዳዮችን በማቅረብ በአንድ በኩል የአገራችንን የሃይማኖት ብዝሃነት የሚፃረር በሌላ በኩል ደግሞ አገራችን የሃይማኖቶች ብዝሃነት ነባራዊ መገለጫዋ መኾኗን የሚቃወም አካሄድ ነው፡፡

በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል አቋራጭ የፖሊቲካ መሣርያ ለማድረግም የሚንቀሳቀሱ አካላት ይታያሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት የሚታየው በተለያዩ የማኅበራት አደረጃጀት ውስጥ ራሳቸውን ደብቀው በሚሠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ነው፡፡ በእነዚህ ማኅበራት ውስጥ የመሸጉ አክራሪ ግለሰቦችና ቡድኖች በሚያሰራጭዋቸው የተለያዩ የኅትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የድረ ገጽ ውጤቶች በተከታታይ ሃይማኖትን ከሃይማኖት፣ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ሕዝብንና መንግሥትን የሚያጋጩ ዘገባዎችን በማስተጋባት የኢፌዴሪ መንግሥት የኦርቶዶክስ ክርስትናን ያሳነሰና ተገቢውን ክብርና ጥቅም የነፈጋት አድርገው ለምእመናን ያቀርባሉ፡፡

መንግሥት የሚያካሂዳቸው የልማት ሥራዎች መንግሥት የሚያሳያቸውን የገለልተኝነት ሚና. . .ወዘተ መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል በሚል ገሃድ ፍላጎትና ድብቅ አሠራር ካላቸው የውጭ ቡድኖች ጋራ በማበር ሰላምን አደጋ ውስጥ የማስገባትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሃይማኖት ሽፋን ለመናድ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በቅርቡ በነበረው የፓትርያርክ ምርጫና በዋልድባ ገዳም ዙሪያ የተፈጠረው ዝንባሌ የነዚህ ፍላጎቶች ጉልሕ ማሳያ ነው፡፡

*                       *                    *

የአክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል የማስፋፋት ስልቶች

 • የሃይማኖት ተቋማቱን የአመራር ዕርከኖች መቆጣጠር

አክራሪነትና ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት ከሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዱ በሃይማኖት ተቋማትም ይኹን በመንግሥት መዋቅር ሰርጎ በመግባትና ደጋፊ በመምሰል በድብቅ መሠረቱንና መረቡን ማስፋፋት ነው፡፡ ይህን መሠረት የማስፋፋትና መረብ የመዘርጋት ተግባር ውጤታማ በኾነና በአጭር ጊዜ ማከናወን የሚቻለው የመንግሥትንም ይኹን የሃይማኖቶች አደረጃጀቶችን በበቂ ደረጃ መቆጣጠር ከተቻለ ነው፡፡

በእስልምናም ይኹን በክርስትና ሃይማኖቶች ሽፋን የሚካሄደው የአክራሪነት/ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት እያነጣጠረ የሚገኘው የተቋማቱን የበላይ አመራር ዕርከኖች መቆጣጠር ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ማሳያ የሚኾነው በቅርቡ በተካሄደው የእስልምና ምክር ቤቶች ምርጫ ወቅት ለአክራሪው ኀይል ለራሱ በሚበጅ መንገድ ካልኾነ ምርጫው ትክክለኛ አይደለም በሚል የዑላማ ምክር ቤት ፋትዋ ጭምር በመቃወም ያደረገው ሙከራ ነው፡፡

ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራዊ ኾኖ ከ8 ሚልዮን በላይ ሕዝበ ሙስሊም ወጥቶ የፈለገውን አመራር ከመረጠ በኋላ እስከ ፍርድ ቤት የሚሄድ ክሥ የመመሥረት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ በራሱ ነጻ ፍላጎት መርጦ ያቋቋመውን መሪ ተቋም ማብጠልጠል የሚታይ የዘወትር ክሥተት አድርገዋል፡፡ አክራሪው ኀይል ‹‹የራሴ ብቻ ካልኾነ›› የሚለውን አመለካከት በግልጽ ያመላከተ ሂደት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡ ከምርጫ ሂደቱም በኋላ ከቀበሌ ጀምሮ የተመረጡ አመራሮችን በየዕርከኑ የራሱ ለማድረግ የሌት ተቀን ሥራውን በተለያዩ መደለያዎችና ማስፈራሪያዎች እየሠራ መኾኑ በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የ፮ው ፓትርያርክ ምርጫ ሲካሄድም በተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ከአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ተስተውለው እንደነበር ይታወቃል፡፡ የሚሾመው ፓትርያርክ ጉዳይ የራሱ የአማኙ መኾኑ እየታወቀና ራሱ ሲኖዶሱ አስመራጭ አካል ሠይሞ ከየሀገረ ስብከቱ በውክልና ከ800 በላይ መራጮች እንዲሳተፉ አድርጎ ያካሄደውን ሂደት በማብጠልጠል ‹‹መንግሥት ጣልቃ ገብቷል›› ስለዚህም የፍላጎታችንን መሾም አልቻልንም በሚል ለማስተጋባት ተሞክሯል፡፡

አክራሪው/ጽንፈኛው ኃይል የሃይማኖት ተቋማቱን የአመራር ዕርከኖች መቆጣጠር የሚፈልግበት ምክንያት ሕዝባችንን በተደራጀ መንገድ በበቂ ለማደናገርና ከዚያም ከሕገ መንግሥታዊ ሥርዐታችንና ከሕገ መንግሥት ጋራ ፊት ለፊት ለማፋጠጥ ነው፡፡ ‹‹በሃይማኖትኽ መንግሥት ጣልቃ ገብቷል›› የሚለውን መፈክራቸውን የሁሉም ሕዝብ መፈክር በማድረግ በሕገ መንግሥታችንና በዴሞክራዊ ሥርዐታችን ላይ በተሳሳተ መንገድ ሕዝብን ለማዝመት ነው፡፡ ተቋማዊ ቁመናና ትስስር ተጠቅመው ገንዘቡንም ሕዝቡንም ለአክራሪነት ግባቸው ለማሰለፍ ስለሚመቻቸው ነው፡፡ የሃይማኖቱ ተቆርቋሪ መስለው አክራሪነቱን ለማስፋፋት ምርጥ ዕድል ስለሚኾን ነው፡፡

በተቃራኒው ግን ሕዝበ ሙስሊሙም ይኹን ሕዝበ ክርስቲያኑ ለአፍራሽ ፍላጎት ተገዥ እንዳልኾነ፣ ለሰላምና ልማት የቆመ ሕዝብ መኾኑን ደጋግሞ በተግባር አሳይቷቸዋል፡፡ በእነርሱ እኩይ ዓላማና ፍላጎት እንደማይገዛ፣ ሕገ መንግሥታችንና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐትን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው ኃይል ጋራ እንደማይተባበር ፊት ለፊት በሰፋፊ ሰላማዊ ሰልፎች ጭምር ነግሯቸዋል፡፡

ስለዚህ አክራሪው ኃይል ቢቻል እነዚህን የአመራር ዕርከኖች ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ካልተቻለም ደረጃ በደረጃ እየሰረገና አቋሞቻቸውን እየሸረሸረ የራሱ ተቋም ለማድረግ ሰፊ ርብርብ ያደርጋል፡፡ ንጹሓን አማኞች ሁሌም ቢኾን ይህን አደጋ በንቃት በመጠበቅ ከመንግሥት ጋራ ተባብሮ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጉዳዩ ፀረ ሕገ መንግሥት አቋም እንደመኾኑ የሁሉም የሰላምና ልማት ኃይሎች ርብርብ የሚፈልግ ነው፡፡

Advertisements

20 thoughts on “ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም: በዋልድባ ገዳም እና በ፮ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ዙሪያ የተፈጠሩ ዝንባሌዎችን ‹‹በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሽፋን›› ይታያል ላሉት አክራሪነት/ጽንፈኝነት›› በጉልሕ ማሳያነት አቀረቡ

 1. Anonymous September 6, 2013 at 1:22 am Reply

  መናፍቃንና አሸባሪው መንግስት ገና መከራችን ብዙ መሆኑን እየነገሩን ነው እንደነሱ ሃሳብ ከሆነ ነገር ግን እንኩአን ከታሰበ ከተወረወረም የሚያድን አምላክ እንዳለ አልተረዱም ማለት ነው ::ይህ ምንም እንኩአን የመንግስት አቅዋም ቢሆንም ከየት እንደመጣ ምእመኑ በደንብ ያውቃል እንዲሁም ይገነዘባል የተለመደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የማጥፋት አባዜ የተጠናወታቸው ፋሺስቶች …. ::ከውስጥና ከውጭ ጠላቶቻችን (ቤተክርስቲያን ውስጥ ከመሸጉ መናፈቃንና ለይቶላቸው በየአዳራሹ ከምፎክሩ የግልፅ መናፍቃንመሆኑን ልብ ይሏል)
  እግዚአብሔር ጠላት ዲያብሎስን ያስታግስልን ::

  • King September 6, 2013 at 2:00 pm Reply

   አንተ ወረኛ …….አይደለም አዳራሽ ፤ ዛፍ ጥላ ስር ተሰብስበው ቢጠሩት…..አምላክ ይሰማቸዋል (ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ በስሜ ብትሰበሰቡ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ፡፡)
   ሌላው ሀገር ውስጥ ያለችውን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መንግስት እያጠፋት ነው ካልክ፤…….ውጪ ሀገር ያለችውን ማን ነው እያጠፋት/እየበጠበጣት ያለው ?
   የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነገር “ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል” እንደተባለው እየሆነ እኮ ነው……የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን ጴንጤ፣ መናፍቅ ፤ ተሃድሶ…..ወዘተ እያላችሁ ስታሳድዱ የነበራችሁ እናንተ፤…….አሁን ደግሞ ሊያጠፉን፣ ሊበትኑን ነው…..ወዘተ እያላችሁ የምታለቃቅሱት እናንተ……ይገርማል!
   የተዋህዶ ልጆች የዛሬ 20 ዓመት አካባቢ ጴንጤዎችን ለማጥፋት ስታባርሩ ነበር፤ አሁን ደግሞ ጴንጤዎች ሊያጠፉን ነው ብላችሁ ስትሸሹ በማየቴ ተገርሜያለሁ፡፡
   “ሰው የዘራውን ያጭዳል”
   ለነገሩ እኔም ኦርቶዶክስ ነኝ…….ግን ማንንም አልሰድብም/አልነቅፍም

   • Ben September 6, 2013 at 10:36 pm

    ወረኛ ደሞ ለነገሩ እኔም ኦርቶዶክስ ነኝ ትላለህ እንዴ? ውሸታም:: የመናፍቅ ሽታው ከሩቁ ያስታውቃል::

   • Anonymous September 6, 2013 at 11:21 pm

    እሺ የኔ ቱልቱላ ስም እንጂ ምግባር የለህም ሽፈራው የላከህ መናፈቅ መሆንህን ልነግርህ እወዳለው:ውሻስ በበላበት አይደለ የሚጮህው?!ወጣና እዛው አዳራሽ ፎክር እንጂ እዚህ ተደብቀህ መፎከር አትችልም እውነትን ማሸነፍ ስለማትችል

   • Anonymous September 10, 2013 at 10:13 am

    Mesloh new ethiopia wust enkuan pente temama enchet yemaytaybet gize eyekerebe new..

 2. Anonymous September 6, 2013 at 7:45 am Reply

  ከእውነት የራቀ የግል ጥቅማቸውን ለማራመድ የሚያደርጉት ጥረት አደጋ ነው ና መንግስት ቢያጤነው መልካም ነው በፖለቲካ ሽፋን አላማቸው ያሰተጋባሉ ።መለስ ዜናዊ የተናገረው ንግግር መሪዎች እኛ አደለንም መሪያችን ሕዝብ ነው።ታች ወርደው ቢያዩት ይማራሉ

 3. mulushewa September 6, 2013 at 10:05 am Reply

  ከዶ/ር ሽፈራው የማልቀበላቸው
  1.የ1948ቱ ህገ-መንግስት ኢኦተቤክ ብሄራዊ ሀይማኖት ናት የሚል ድንጋጌ ፈጽሞ የለውም. እርግጥ ነው የንጉሳዊ ቤተሰቡ አካል ለመሆን ሀይማኖቱ እንደመመዘኛ በአንቀጽ 16 ላይ ተቀምጡዋል. ሆኖም የሌላው የህብረተሰብ ክፍል የሃይማኖት ነጻነት ከአሁኑ የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 27 በሚመሳሰል መልኩ በ1948ቱ ህገመንግስት አንቀጽ40 ተደንግጉዋል. የሸሪአ ፍርድ ቤቶች በህግ የተቁዋቁሙት፣የሚሲዮናውያን ት/ቤቶች የተስፋፉት፣እንደነ ፊታውራሪ አመዴ ለማ አይነት ሙሰሊም የፓርላማ አባላት ፓርላማውን ያንቀጠቀጡት በንጉሱ ዘመን መሆኑም ዐገሪቱ አንድ አገር አንድ ሀይማኖት በሚል መርህ ትመራ ነበር የሚለውን ክርክር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው. በእንግሊዝ የንጉሳዊ ቤተሰቡና የአንግሊካን ቸርች ያላቸው ቅርርብ እንዲሁም በሌሎች የአውሮፓ የይስሙላ ንጉሳዊ አስተዳደሮች ከካቶሊክ ቤ/ክርስቲያን ጋር ያላቸው ትስስር ይታወቃል. ይህ ማለት ግን ዕነሱ የተከተሉት ሀይማኖት ሁሉ ብሄራዊ ነው ማለት አይደለም. ለኔ ኃ/ስላሴም እንደዛ ናቸው.በገቢር የንጉሱን ሀይማኖት በሚከተሉና በማይከተሉ መሀል ሊደርስ የሚችለው የስነ-ልቦና ጫና እንደተጠበቀ ሆኖ ቢያንስ በህግ፣በፖሊሲ የተለየ ከለላ የሚሰጠው ወይም የሚሳደድ ሀይማኖት አልነበረም.
  2.አንድ ሀገር አንድ ሀይማኖት የሚለውን አባባል ከባለስልጣናት ከመስማት ውጭ ከአንድም የቤ/አባል አልሰማሁም.በአጭሩ አባባሉ በማስረጃ ያልተደገፈ ነው.የክርስቲያን ደሴት ይላሉ ስለተባለውም በአሁን ጊዜ ቃሉ የቀረ ይመስለኛል.ደግሞስ ቢባል እኛ የክርስቲያን ብቻ አላልን. ስለዚህ ሙሰሊሙም፣ካቶሊኩም፣ፕሮቴስታንቱም፣ሌላውም የእኛም ደሴት ናት ይበልና ኢትዮጵያን የፍቅር ደሴት እናርጋት. ማነው ደሴትን የአንድ ዝርያ ብቻ መኖሪያ አድርጎ የሳለው. በሌላም በኩል ካለን የዐረቦች ጉርብትናና የጎረቤት ሀገሮች የሀይማኖት ተዋጽኦ አንጻር(ሙስሊሞች ይበዛሉ) ቃሉ ጥቅም ላይ ሲውል እንደነበር መረዳት ይገባል
  3.ሀይማኖታችን ከሌሎች ሀይማኖቶች ጋር ተነጻጽሮ በቀረበው ላይ- ብዙ አማኝና ረጅም ታሪክ ያለን መሆኑ እውነት ነው. በዚህ እንኮራለን!!!ግን ሌሎችን ለማጣጣል ፈልገን አላግባብ ጥቅም ላይ አናውለውም. ይሰድቡናል- ሁዋለቀር፣ኦሪታዊ፣የልማድ ዕስረኞች፣ከአለም ተነጥለን የቀረን ፣የግብጽ ኮፕቲክ ሎሌ አድርገው!!ስለዚህ ከግብጾች በፊት አማኞች እንደነበርንና የምጡቅ ግንባታዎች ባለቤቶች መሆናችንን እንዲያውቁ ስንል ከህገ ልቡና እስከ ህገ ወንጌል ያለ ታሪካችንን እንነግራቸዋለን. We are defending ourselves not offending anyone!!!
  4.መንግስትና ኢኦተቤክ- መንግስት ደጋግሞ ቤ/ክ ካለፉት ነገስታት ጋር ያላትን ትስስር ማውሳት ያለውን ትርፍና ኪሳራ ቢያስብበት ፣እንዲሁም ትክክለኛውን የታሪክ አሻራ በጥናት አስደግፎ ከዚያ በሁዋላ አቁዋም ቢይዝ.፣በየመድረኩ የሚናገሩ ባለስልጣናት የየራሳቸውን ተሞክሮ ልክ እንደቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ ማሳያ አድርገው ባያቀርቡ. የግል ተሞክሮ የግል ነው!!!ያለበለዚያ በአንድ ፕሮቴስታንት ካድሬ የግል ተሞክሮ የኢኦተቤክንን ታሪክ ለመበየን መሞከር የተአማኒነት ጥያቄ ያስነሳል. በተቃራኒውም እንደዚሁ. በደቡብና በኦረሚያ በተለይ ኦርቶዶክስና ነፍጠኛ የሚሉ ቃላትን በማስተሳሰር ሃይማኖቱን ለማስጠላት የሚካሄደው እንቅስቃሴ ሀላፊነት የጎደለው ነው. በተረፈ ጠንካራ ጎናችን ይወሳልን.
  5.መንግስት ገለልተኛ ነው????
  ከዶ/ር ሽፈራው በከፊል የምቀበላቸው
  ማህበሩ በዋልድባና በፓትርያርክ ምርጫው ላይ የተከተለው ግልጽነት የጎደለው አካሄድ በተለይ የአገር ውስጡና የውጩ አመራር የተለያየ አቁዋም ማራመድ ሊነቀፍ የሚገባው ነው
  በምርጫው መንግስት እጁን አስገብቱዋል እያሉ የራሳቸውን ዘውድ በመረጡት ጳጳስ ላይ ለመጫን እከሌን ምረጡ ሲሉ የነበሩትን እንዲህ ነው እንጂ የሲኖዶስን ውሳኔ ማክበር ብለን ታዝበናቸዋል!!መንግስት ቢሆኑ ኖሮ ምን ሊያደርጉ ነበር ብለን ተደንቀናል!!!!
  ማህበሩ ከአጥቢያ አመራር እስከሲኖዶስ ድረስ መመሪያን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት መሞከር(በተዘዋዋሪ መቆጣጠር)

 4. annonymus September 6, 2013 at 4:07 pm Reply

  ሙሉሸ፣

  በጣም ደስ የሚል የበሰለ ሰው አስተያየት ነው፡፡ ዶ/ር ሽፈራው እንዳሉት በቤተክርስቲያኗ ሽፋን ብዙ የየራሳቸውን ፍላጎት ሊያሳኩ ድብቆች እንዳሉ አንክድም፡፡ ይህ ቤተክርስቲያኗንም እየተፈታተናት ያለ ትልቅ ችግር ነው፡፡ በውስጧ ከተሰገሰጉት እነዚህ ግለሰቦች በተጨማሪ መንግስት ቤተክርስቲያኗን እንድትዳከም፣ ሌሎች በጥላቻ እንዲነሱባት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አድርጓል አሁንም እያደረገ ነው፡፡ ከላይ ሙሉሸዋ ያነሳው ቤተክርስቲያኗን በየክፍለአገሩ የቀደሙት ገዥዎች መሳሪያ ተደርጋ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እንዲዛመትባት ከሚያደርጉት የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዙት የመንግስተ ባለስልጣናት ናቸው (በየክፍለ ሀገሩ ያሉት)፡፡ መንግስትም ይሁን ሌላ አካል ሊረዳው የሚገባው ጉዳይ ግን ቤተክርስቲያኗና ተከታዮቿ በአገር ጉዳይ ላይ ከየትኛውም እምነትና ተከታዮቻቸው የበለጠ እንደሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ (መሠረቷ አገራዊ የሆነ) ሀማኖት እንደሆነች ማንም ሊክደው አይችልም፡፡ መሔጃም የላትም፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕልውና የቤተክርስቲያኗም ሕልውና ነው! ሌሎች አማራጭ አላቸው፡፡
  ኃይለስላሴ አሉ ሲባል የሰማሁት ግን ዶ/ር ሽፈራው ከሚሉት በተቃራኒ ነው፡፡ ሐይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው ያሉት ኃይለስላሴ መሰሉኝ፡፡

  • Anonymous September 6, 2013 at 11:24 pm Reply

   እሺ የኛ መናፍቅ ማነው የላከህ/ሽ ?

 5. Anonymous September 7, 2013 at 6:41 am Reply

  http://www.eotc-mkidusan.org/site/–mainmenu-2/47——
  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ክፍል አንድ

 6. Anonymous September 7, 2013 at 6:43 am Reply

  http://www.eotc-mkidusan.org/site/–mainmenu-2/35-l—–r–
  «ማኅበረ ቅዱሳን ለሁሉም ግልጽ አሠራር አለው» ክፍል ሁለት

 7. Anonymous September 7, 2013 at 6:44 am Reply

  http://www.eotc-mkidusan.org/site/–mainmenu-2/50——
  ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? ክፍል ሦስት

 8. Anonymous September 7, 2013 at 10:19 am Reply

  ሙሉሸ፣

  በጣም ደስ የሚል የበሰለ ሰው አስተያየት ነው፡፡ ዶ/ር ሽፈራው እንዳሉት በቤተክርስቲያኗ ሽፋን ብዙ የየራሳቸውን ፍላጎት ሊያሳኩ ድብቆች እንዳሉ አንክድም፡፡ ይህ ቤተክርስቲያኗንም እየተፈታተናት ያለ ትልቅ ችግር ነው፡፡ በውስጧ ከተሰገሰጉት እነዚህ ግለሰቦች በተጨማሪ መንግስት ቤተክርስቲያኗን እንድትዳከም፣ ሌሎች በጥላቻ እንዲነሱባት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አድርጓል አሁንም እያደረገ ነው፡፡ ከላይ ሙሉሸዋ ያነሳው ቤተክርስቲያኗን በየክፍለአገሩ የቀደሙት ገዥዎች መሳሪያ ተደርጋ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እንዲዛመትባት ከሚያደርጉት የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዙት የመንግስተ ባለስልጣናት ናቸው (በየክፍለ ሀገሩ ያሉት)፡፡ መንግስትም ይሁን ሌላ አካል ሊረዳው የሚገባው ጉዳይ ግን ቤተክርስቲያኗና ተከታዮቿ በአገር ጉዳይ ላይ ከየትኛውም እምነትና ተከታዮቻቸው የበለጠ እንደሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ (መሠረቷ አገራዊ የሆነ) ሀማኖት እንደሆነች ማንም ሊክደው አይችልም፡፡ መሔጃም የላትም፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕልውና የቤተክርስቲያኗም ሕልውና ነው!
  ኃይለስላሴ አሉ ሲባል የሰማሁት ግን ዶ/ር ሽፈራው ከሚሉት በተቃራኒ ነው፡፡ ሐይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው ያሉት ኃይለስላሴ መሰሉኝ፡፡

 9. Anonymous September 7, 2013 at 10:12 pm Reply

  መንግስትም እንደ መንግስትም ይዋሻል እንዴ?
  አሁን አሁን የኢትዮጵያ መንግስት ወይም ገዢው ፓርቲ ምንም እንኳ በየመድረኩ የሃይማኖት ነጻነት በአገሪቱ አረጋግጫለሁ በማለት በሚዲያ የሚናገር ቢሆንም ነጻነቱ ትርጉሙ እየቀየረ የመጣ ይመስላል፡፡ በየደረጃው ያሉ በመንግስት የሥልጣን ቦታ ያሉ አካላት ለራሳቸው ዕቅድ እና የግልም ይሁን የቡድን ፍላጎታቸው ያስፈጽምልናል ያሉትን ዕድል በመጠቀም የእነርሱ ሐሳብ የማይቀበልና እንደተሳሳቱና ማስተካከል እንደሚገባቸው የሚናገራቸው ሁሉ እንደተቃዋሚና ጸረ ልማት እንደሆነ በመፈረጅ የማያውቁትን እድሜያቸውን ለማራዘም ይጠቀሙበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን በተለይ ደግሞ በአማራና ትግራይ አከባቢ እየታየ ያለው በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካን ያራምዳሉ ተብለው የሚፈረጁትን ግለ ሰዎችም ሆነ ማኅበራትን የመቃወም፣ ስማቸውን የማጥፋትና ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ አቅጣጫውን የሳተና ሀገሪቱ ወደማትወጣው ብጥብጥና ሁከት የሚከት የሰላምና የነጻነት እጦት ችግር የሚከታት አካሄድ መሆኑን ማን በነገራቸው? ለነገሩ በአገራችን ሰመቶ የሚተገብር እንጂ የሚናገር መቼ ታጣና፡፡
  በሃይማኖት ስም ፖለቲካን ሊያራመዱ ስለሚሰጉት ያለ እና የሌለ ሲወራ፣ ሲዘገብ ሲዋሽ እና ለዚህ ማስፈጸሚያ የሚሆን በጀት ሲበጀት ምነው በፖለቲካ እና በሥልጣን ሽፋን ሃይማኖትን ስለሚያራምዱት ከቀበሌ እስከ ሚኒስቴር ከዋህዮ እስከ ከፍተኛ አመራር ያሉትን የመንግስት አካላት አንድ ነገር አለመባሉ ይገርማል፡፡ ከማስገረም አልፎ ትዝብት ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
  ጥፋት በሌለበት ጥፋት ካልተገኘ፣ ሁከት ለማይፈጥረው ለምን አታውክም፣ ለማያምጸው ይልቁንም ስለ ሰላም ለሚሰብከው ለምን አታምጽም ለሚል ሰው ምን ይባላል፡፡ መንግስት አሸባሪዎችን ለመዋጋት፣ አክራሪዎችን ለማስቀረት ማቀዱ፣ ለሕዝብ ማወያየቱ መልካም ሆኖ ሳለ፤ አሸባሪ ያልሆነውን ባልተጣራና በተዛባ መረጃ አንዳንዴም ሆን ተብሎ እስከሚመስል ድረስ አሸባሪ በማለት ሰላማዊውን ሰው ለሽብር የማነሳሳት አዝማሚያ ሲያከናውን ይታያል፡፡ መንግስት ስለ ልማት ሲያቅድና ሲጥር አስፈጻሚዎቹ ግን ባለፉት ዓመታት ተገኝቶ የነበረውን ነጻነትና ሰላም ያስደሰታቸው አይመስልም በገዛ መድረካቸው አመጽን ይቀሰቀሳሉና፡፡
  በሚኒስትር ደረጃ የተቀመጡት እነ አቶ ስብሐት ነጋ እና ደኩተር ሽፈራው በቅርብ ጊዜ በሃይማኖት ሸፋን የሚንቀሳቀሱ የከሰሩ ፖለቲከኞች ስላሏቸው አካላት በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ተቋቁሞ መንፈሳዊ አገለግሎትን እየሰጠ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረቡት ጉዳይ ነጩንና ንጹሁን ወረቀት ጥቁር ነው ብላችሁ ተቀበሉን ብሎ ሕዝቡን እንደማታለልና ማሞኘት የሚቆጠር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብን በእኛ ዐይን እዩ፣ በእኛ ጀሮ አድምጡ፣ በእኛ ጭንቅላት አስቡ ብሎ ሕዝቡ አንደማያይ፣ እንደማይሰማና እንደማያስብ አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሺ ብሎ በሰላም የተገዛውንና የመንግስት አቅጣጫ ይጠቅመኛል ብሎ የተቀበለውን ጨዋ ሕዘብ ከማስቀየም አልፎ ሳይወድ በመንግስት ላይ ለአመጽ ማነሳሳት ነው የሚሆነው፡፡ ምናለ እያደረጉት ስላለው ጉዳይ ቀም ብለው ብያስቡት፡፡ ስሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፋት ለሕዝቡ የሚናገሩት እነሱ በግልጽም በድብቅም በተግባር የሚፈጽሙት ከሆነ ምን ይባላል?
  ሕዝቡ እኮ ማንነው ጤነኛ ማንስ ነው ጤነኛ ያልሆነው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በየመንደሩ ያለፈቃድ ወጣቶቹንና አዛውንቱን የእኔ እምነት ተከተል የሚጠቅምህ ይህ ነው እኔ የማቀርብልህ አዲስ ነው አንተ የያዝከው አሮጌ ነው እያለ የሚያስቸግረው ማን መሆኑን ሕዝቡ በሚገባ ያውቃል፡፡ ስለ ሃይማኖት በሕገ መንግስት የተቀመጠው ያወቃል፡፡ ሕገ መንግስትና ሕገ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው የሚሄዱትን እነማን እንደሆኑ ይረዳል፡፡ መስጊድም ይሁን ቤተ ክርስቲያን ማን ነው የሚያቃጠለው ሕ/ሰቡ ያውቃል፡፡ ታዲያ ሕዝቡ በቤቱ እንደሚኖርና የሰው ቤት እንደማያንኳኳ ስለሚያውቀው ማኅበርም ሆነ ሃይማኖት ውጭ ነው ያለው ያምጻል ቢባል የሚቀበለው በየትኛው እይታ ነው፡፡ ይህ እኮ አይደለም በሃይማኖት አስተሳሰብ በፖለቲካዊ ፍልስፍናም ኪሳራ ነው፡፡
  እባካችሁ መንግስት ወይም አቅጣጫው ስቷል ገና በበረሀ እያሉ ያቀዱትና ደማቸውን ያፈሰሰሉት ጉዳይ ተዘንግቷል አልያም መንግስትን ሽፋን በማድረግ ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ሰዎች ገብተዋል፡፡ አንድ ሰው ሁለት ሰው ቢሳሳት እሺ መንግስት እንደ መንግስት ሲሳሳት፣ ባልተጣራ መረጃ ሲፈርጅና ያልሆነ ስም ሲሰጥ መመልከት እንደ ዜጋ ያሳፍራል፡፡ ግለ ሰው ቢዋሽ እንጂ መንስግት እንዴት ይዋሻል፡፡ እውነትን የሚመሰክር ስለ እውነት የቆመ ኢትዮጵያዊ በሚኒስቴር ደረጃ ማጣት ያሳፍራል፡፡ እርግቧን ቁራ ናት ብላችሁ ተቀበሉኝ የሚል የአገር መሪና ባለሥልጣኝ አገሪቱን ወዴት አቅጣጫ እንደሚመራት መገመት ቀላል ነው፡፡
  እንግዲህ አንድ ነገር ልበልና የማያልቅ ሀሳቤን ልቋጨው፡፡ ባለሥልጣናት ሆይ እናንተ ባላችሁበት የሥልጣን ወንበር ብዙዎች ከእናንተ በፊት ነበሩ ብዙዎችም ከእናንተ በኋላ ይከተላሉና በሐሰት ንግግርና ፕሮፓጋንዳ የማታውቁትን እድሜያችሁን ለማራዘም ከማሰብ እውነትን መስክራችሁ ለአገሪቱና ለልጆቻችሁ መልካም ዘር ተክላችሁ እለፉ፡፡ ስለ የዋሁና ጭዋው ሕዝብ ብሎ አስተዋይ አእምሮ ይስጣችሁ፡፡

 10. enew September 7, 2013 at 10:14 pm Reply

  መንግስትም እንደ መንግስትም ይዋሻል እንዴ?
  አሁን አሁን የኢትዮጵያ መንግስት ወይም ገዢው ፓርቲ ምንም እንኳ በየመድረኩ የሃይማኖት ነጻነት በአገሪቱ አረጋግጫለሁ በማለት በሚዲያ የሚናገር ቢሆንም ነጻነቱ ትርጉሙ እየቀየረ የመጣ ይመስላል፡፡ በየደረጃው ያሉ በመንግስት የሥልጣን ቦታ ያሉ አካላት ለራሳቸው ዕቅድ እና የግልም ይሁን የቡድን ፍላጎታቸው ያስፈጽምልናል ያሉትን ዕድል በመጠቀም የእነርሱ ሐሳብ የማይቀበልና እንደተሳሳቱና ማስተካከል እንደሚገባቸው የሚናገራቸው ሁሉ እንደተቃዋሚና ጸረ ልማት እንደሆነ በመፈረጅ የማያውቁትን እድሜያቸውን ለማራዘም ይጠቀሙበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን በተለይ ደግሞ በአማራና ትግራይ አከባቢ እየታየ ያለው በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካን ያራምዳሉ ተብለው የሚፈረጁትን ግለ ሰዎችም ሆነ ማኅበራትን የመቃወም፣ ስማቸውን የማጥፋትና ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ አቅጣጫውን የሳተና ሀገሪቱ ወደማትወጣው ብጥብጥና ሁከት የሚከት የሰላምና የነጻነት እጦት ችግር የሚከታት አካሄድ መሆኑን ማን በነገራቸው? ለነገሩ በአገራችን ሰመቶ የሚተገብር እንጂ የሚናገር መቼ ታጣና፡፡
  በሃይማኖት ስም ፖለቲካን ሊያራመዱ ስለሚሰጉት ያለ እና የሌለ ሲወራ፣ ሲዘገብ ሲዋሽ እና ለዚህ ማስፈጸሚያ የሚሆን በጀት ሲበጀት ምነው በፖለቲካ እና በሥልጣን ሽፋን ሃይማኖትን ስለሚያራምዱት ከቀበሌ እስከ ሚኒስቴር ከዋህዮ እስከ ከፍተኛ አመራር ያሉትን የመንግስት አካላት አንድ ነገር አለመባሉ ይገርማል፡፡ ከማስገረም አልፎ ትዝብት ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
  ጥፋት በሌለበት ጥፋት ካልተገኘ፣ ሁከት ለማይፈጥረው ለምን አታውክም፣ ለማያምጸው ይልቁንም ስለ ሰላም ለሚሰብከው ለምን አታምጽም ለሚል ሰው ምን ይባላል፡፡ መንግስት አሸባሪዎችን ለመዋጋት፣ አክራሪዎችን ለማስቀረት ማቀዱ፣ ለሕዝብ ማወያየቱ መልካም ሆኖ ሳለ፤ አሸባሪ ያልሆነውን ባልተጣራና በተዛባ መረጃ አንዳንዴም ሆን ተብሎ እስከሚመስል ድረስ አሸባሪ በማለት ሰላማዊውን ሰው ለሽብር የማነሳሳት አዝማሚያ ሲያከናውን ይታያል፡፡ መንግስት ስለ ልማት ሲያቅድና ሲጥር አስፈጻሚዎቹ ግን ባለፉት ዓመታት ተገኝቶ የነበረውን ነጻነትና ሰላም ያስደሰታቸው አይመስልም በገዛ መድረካቸው አመጽን ይቀሰቀሳሉና፡፡
  በሚኒስትር ደረጃ የተቀመጡት እነ አቶ ስብሐት ነጋ እና ደኩተር ሽፈራው በቅርብ ጊዜ በሃይማኖት ሸፋን የሚንቀሳቀሱ የከሰሩ ፖለቲከኞች ስላሏቸው አካላት በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ተቋቁሞ መንፈሳዊ አገለግሎትን እየሰጠ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረቡት ጉዳይ ነጩንና ንጹሁን ወረቀት ጥቁር ነው ብላችሁ ተቀበሉን ብሎ ሕዝቡን እንደማታለልና ማሞኘት የሚቆጠር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብን በእኛ ዐይን እዩ፣ በእኛ ጀሮ አድምጡ፣ በእኛ ጭንቅላት አስቡ ብሎ ሕዝቡ አንደማያይ፣ እንደማይሰማና እንደማያስብ አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ ይህ ደግሞ እሺ ብሎ በሰላም የተገዛውንና የመንግስት አቅጣጫ ይጠቅመኛል ብሎ የተቀበለውን ጨዋ ሕዘብ ከማስቀየም አልፎ ሳይወድ በመንግስት ላይ ለአመጽ ማነሳሳት ነው የሚሆነው፡፡ ምናለ እያደረጉት ስላለው ጉዳይ ቀም ብለው ብያስቡት፡፡ ስሌሎች ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፋት ለሕዝቡ የሚናገሩት እነሱ በግልጽም በድብቅም በተግባር የሚፈጽሙት ከሆነ ምን ይባላል?
  ሕዝቡ እኮ ማንነው ጤነኛ ማንስ ነው ጤነኛ ያልሆነው ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በየመንደሩ ያለፈቃድ ወጣቶቹንና አዛውንቱን የእኔ እምነት ተከተል የሚጠቅምህ ይህ ነው እኔ የማቀርብልህ አዲስ ነው አንተ የያዝከው አሮጌ ነው እያለ የሚያስቸግረው ማን መሆኑን ሕዝቡ በሚገባ ያውቃል፡፡ ስለ ሃይማኖት በሕገ መንግስት የተቀመጠው ያወቃል፡፡ ሕገ መንግስትና ሕገ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው የሚሄዱትን እነማን እንደሆኑ ይረዳል፡፡ መስጊድም ይሁን ቤተ ክርስቲያን ማን ነው የሚያቃጠለው ሕ/ሰቡ ያውቃል፡፡ ታዲያ ሕዝቡ በቤቱ እንደሚኖርና የሰው ቤት እንደማያንኳኳ ስለሚያውቀው ማኅበርም ሆነ ሃይማኖት ውጭ ነው ያለው ያምጻል ቢባል የሚቀበለው በየትኛው እይታ ነው፡፡ ይህ እኮ አይደለም በሃይማኖት አስተሳሰብ በፖለቲካዊ ፍልስፍናም ኪሳራ ነው፡፡
  እባካችሁ መንግስት ወይም አቅጣጫው ስቷል ገና በበረሀ እያሉ ያቀዱትና ደማቸውን ያፈሰሰሉት ጉዳይ ተዘንግቷል አልያም መንግስትን ሽፋን በማድረግ ሊጠቀሙበት የሚፈልጉ ሰዎች ገብተዋል፡፡ አንድ ሰው ሁለት ሰው ቢሳሳት እሺ መንግስት እንደ መንግስት ሲሳሳት፣ ባልተጣራ መረጃ ሲፈርጅና ያልሆነ ስም ሲሰጥ መመልከት እንደ ዜጋ ያሳፍራል፡፡ ግለ ሰው ቢዋሽ እንጂ መንስግት እንዴት ይዋሻል፡፡ እውነትን የሚመሰክር ስለ እውነት የቆመ ኢትዮጵያዊ በሚኒስቴር ደረጃ ማጣት ያሳፍራል፡፡ እርግቧን ቁራ ናት ብላችሁ ተቀበሉኝ የሚል የአገር መሪና ባለሥልጣኝ አገሪቱን ወዴት አቅጣጫ እንደሚመራት መገመት ቀላል ነው፡፡
  እንግዲህ አንድ ነገር ልበልና የማያልቅ ሀሳቤን ልቋጨው፡፡ ባለሥልጣናት ሆይ እናንተ ባላችሁበት የሥልጣን ወንበር ብዙዎች ከእናንተ በፊት ነበሩ ብዙዎችም ከእናንተ በኋላ ይከተላሉና በሐሰት ንግግርና ፕሮፓጋንዳ የማታውቁትን እድሜያችሁን ለማራዘም ከማሰብ እውነትን መስክራችሁ ለአገሪቱና ለልጆቻችሁ መልካም ዘር ተክላችሁ እለፉ፡፡ ስለ የዋሁና ጭዋው ሕዝብ ብሎ አስተዋይ አእምሮ ይስጣችሁ፡፡

 11. Anonymous September 8, 2013 at 2:59 pm Reply

  ay shiferawu

 12. ብላታ September 8, 2013 at 3:17 pm Reply

  ይድረስ ለግቡሳኑ

  እኔ የምለው ስለ ዛሬ ስንናገር ትናንትን መርሳት ያለብን ወይ? የዚህ ገጽ አዘጋጆችም ሆኑ አስተያየት ሰጪዎች የዘነጋነው ዐቢይ ጉዳይ አለ:: እስኪ ከሃያ ዓመታት በፊት ሊቃነ ጳጳሳቶቻችን በየንግሥ በዓሉና ዐውደ ጉባኤያት ላይ ምን ዓይነት ትምህርት ይሰጡ እንደነበር አስታውሱ? ልጆች ከነበራችሁ አባቶቻችሁን ጠይቁ:: በነጻ አውጪውና በመንግሥት መካከል የነበራቸው ሚና ምን ይመስል ነበር? እውነት ከአንድ መንፈሳዊ ተቋም የምንጠብቀውን ያህል እንኳ ባይሆን የምንጠቅስላቸው የአስታራቂነት ሚና የታለ? ከተልእኳቸው ውጪ ግን በተደጋጋሚ ሸንጋይ ገላጋይ እየሆኑ ትጥቅ ሊያስፈቱ በርሃ ሲላኩ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥትን የሚያውቁት አይመስሉም ነበር:: በምን ሙግት ትረቱታላችሁ ይህንን?

  አንድ ልጨምር በኢትዮጵያ “አንድነት” ስም የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ከካድሬዎቹ የደርግ አፈቀላጤዎች በላይ በኤርትራ የነጻነት ጥያቄና በኢትዮጵያ ሕዝቦች የነጻነት ትግል ላይ ዘምተዋል:: በዘመኑ በቤተ ክህነቱም በቤተ መንግሥቱም አንድ ዓይነት ድምጽ ይደመጥ ነበር:: ወያኔ፣ ሻቢያ፣ ገንጣይ፣ ወንበዴ ፥ ጭራሽ ሃይማኖታዊ መልክ ለመስጠትም ዐረብ ሊገዛህ ነው፣ ለየመን ልትሸጥነው፣ አንገት ተቆርጦ ምናምን ምናምን ስንት ነበር:: በአጠቃላይ ከሃገሪቱ ሚድያዎች በላይ እነርሱ ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው አፍራሽ ሚና ተጫውተዋል:: ይህንን ትረሳላችሁ ወይስ አታውቁም? ከዚህ መነሻ ስናየው ከፍተኛ ክትትል ጥበቃ የሚያስፈልገው ወረዳ ነው የሃይማኖት ጉዳይ::

  የዚህ ገጽ አሸጋጆችንም ተሳታፊዎችንም የምለምነው ወደ መስመር ኑና በግልጽ እናውራ መጻፍ መቻልና ለውጥ ማምጣት የተለያዩ ናቸውና:: ለለውጥ እንሰራለን ካላችሁ የት አላችሁ? እስከመቼ ግቡስ ሁናችሁ ትዘልቃላችሁ? የምፈራው አደባባይ ወድቃችሁ እስኪርብቶና ወረቀታችሁን ብቻ እንዳናገኘው ነው::

 13. ZMTA September 10, 2013 at 3:08 pm Reply

  As of my knowledge, when a flag is put on a religion, that religion is doomed to be politics. It will definitely become exclusive to that specific culture. Look at Islam. Islam is “a religion” (I would prefer to call it political ideology created to unite Arabs) created for Arabs. That is why where ever Islam goes, Arabic and the Arabic culture goes with it.

  Look also at the EOTC, where ever she goes she is Ethiopian. The Ethiopian culture, the Ethiopian language, the Ethiopian identity is always cherished. For instance, the EOTC is in Trinidad and Tobago, and Jamaica but have you ever seen any Jamaican bishop? The EOTC is in South Africa, but one can’t find any South African Bishop in the EOTC synod. One of the problems with the so called national churches is, they are burdened with their country’s culture and politics. Have a look at the Russian Orthodox Church, whether it is in corruption, or being subjugated to the ruling party it looks like the EOTC. I have never heard or read the synod of any national churches denouncing the corruption or the cruelty of their governments. In earlier Christianity there were not national churches. Instead, there were Churches in different countries. A national Church is doomed to be a church where politics uses religion to serve its needs (i.e. to brainwash people). That is why the Chinese government tries to create a National Catholic Church that rejects the authority of the pope. The Chinese communists are well aware that a church that claims to serve humanity- as opposed to a single nation- can cause a problem. Wherever you go except coutries under Sharia law like Saudi Arabia, governments do not seem to be worried about Pentecostal churches for they can never be united to criticize the anomalies in their governments.

  The power the early Christians had was their unity. They had no boundaries. Despite their cultural differences and misunderstandings they saw eachother as brothers and sisters. That is why our forefathers say: We Believe in the One Holy Catholic (Universal) Apostolic Church. For instance, the martyr St. Ignatius of Antioch was a bishop from Antioch but he died as a martyr (devoured by lions) in Rome. But, look at Christians of today particularly in Ethiopia. There are some Ethiopians who even try to make Jesus, Mary, St. Mark, Melchizedek… Ethiopians. They say their flag came from the rainbow of Noah. To me this is all farce for no one can put any historical evidence to this claims. I also think that these claims are results of inferiority complex, that in turn resulted superiority complex. Christ never was exclusivist. If this were the case we wouldn’t have had the billions of Christians in the whole world today. If it were to the terribly divided national churches we wouldn’t have had these thousands of cultures in the Christian world.

  Therefore, the church first and foremost should bring the gospel to the people of the world- not its culture. It should stop worrying about its culture instead of thinking about humanity. Only this will redeem her from being slave to politics or fanaticism.

 14. Anonymous September 12, 2013 at 2:11 pm Reply

  Shiferaw is nothing more than PARROT of TPLF

 15. temesgen September 24, 2013 at 8:02 am Reply

  Dear All,
  shiferaw t/mariam is very negativist for Ethiopian orthodox church. he has a complex i am not sure the reason i guess due to he is a protestant and lack of confidence. I know him very well. when he was state minster at the ministry of health(MOH) withTeyodros adhanom, he was even hiring people who are protestants and i was shamefull on him. And i was also shocked melese appointed him for federal afairs. Actually, he has been apointed for quata for SNNPR and he was not in a good relationship with former minster of MOH teyodros adhanom, i know not becuase of his skill or ability he was appointed as fullfillment of the quata. He is a man chracterazied by revange and that is why 100 times Mahiber Kidusan wust akirarinet al yemilew. For info!!!

  The current situation is bad for Ethiopia, the government try to creat a fight between muslim and orthodox in any way but still there were not successful and we have seen and heard different attempts but response from EOTC is praying to God and as God WON THE WORLD WE TOO . Any ways God awalys watch Ethiopia and removed them.

  For what it worths? Shiferaw is irrelevant for us AND ETHIOPIA.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: