ስብሓት ነጋ ጥፋቷን ስለሚመኙላት ቤተ ክርስቲያንና መግደያ ብትር ሊያደርጉት ስለሞከሩት ማኅበረ ቅዱሳን ይወተውታሉ

 • ስብሓት የንግግራቸው መነሻ ያደረጓቸውና ወጣት ሲሉ የጠሯቸው መነኩሴ ማን ናቸው?

 

Ethio-Mihdar Flag of the day

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚያስተኛ አይደለም

/አቶ ስብሓት ነጋ/

(ኢትዮ-ምኅዳር ቅጽ 01 ቁጥር 34፤ ረቡዕ ነሐሴ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋራ በመተባበር በአዲስ አበባ በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ከነሐሴ ፳፩ – ፳፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. ‹‹የሃይማኖቶች በሰላም አብሮ የመኖር እሴት በማጎልበትና ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በማክበር የሀገራችንን የሕዳሴ ጉዞ ለማሳካት እንረባረባለን›› በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ጉባኤ ላይ ‹አቦይ› ስብሐት ነጋ በመገኘት አነጋጋሪ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡ አንጋፋው የህወሓት/ኢሕአዴግ መሥራችና የጀርባ ሰው የሚገልጹት ሐሳብ የመንግሥትን ቀጣይ ርምጃ ያመላክታል በሚል በአጭሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

Sebhat Negaአክራሪነት ይዘቱ ሃይማኖታዊ እንዳልኾነ ሕዝቡም የተገነዘበው ጉዳይ መኾኑ ተደጋግሞ ተገልጧል፡፡ ሃይማኖትን የፖሊቲካ መድረክ የሚያደርጉት የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈጸም መኾኑ ግልጽ የኾነልን ይመስለኛል፡፡

አክራሪነትና ጽንፈኝነት በሃይማኖት ውስጥ ማስገባት የመጀመሪያው አደጋ ሲኾን በዚህ ኹኔታ ሃይማኖቱም ሃይማኖት አይኾንም፡፡ አማኞች፣ አክራሪነትና ጽንፈኝነት በየሃይማኖታቸው ውስጥ ሲታይ ሃይማኖታቸው አደጋ ላይ እንደወደቀ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን (የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ) እንዳለውም፣ በጣም አስደናቂ የኾነውን የኢትዮጵያ ዕድገት ማደናቀፍ ከማንኛውም ወንጀል በላይ በሕዝብ ላይ ከባድ ወንጀል መፈጸም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለብዙ ዓመታት ሲሠቃይ የነበረ በመኾኑ አሁንም ሕዝቡን ለሥቃይ መዳረግ ተወዳዳሪ የሌለው ወንጀል ነው፡፡

በማንኛውም ሃይማኖታዊ አክራሪነት እና ጽንፈኝነት፣ በምንም ዐይነት ኹኔታ አንድም ሰው ለአንድ ደቂቃ እንኳ ተዘናግቶ መተኛት የሌለበት ሲኾን በተለይ ይህን ነገር በጥብቅ በሁሉም መንገድ መታገል አለብን፡፡

አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ዕድገት የሚቀናቀነው የውጭ ተቀናቃኝ ነው፡፡ የእነዚህን ተቀናቃኞች ዓላማ በመያዝ በአክራሪነትና በጽንፈኝነት መልክ ታላቅ ክሕደት መፈጸም ከባድ አገራዊ ክሕደት ነው፡፡ የውጭ ጠላት ቀላል ስላልኾነ አንድም ሰው ሳይቀር በጣም ተጠናክረን መመከት ይገባል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት ያደረገ የፖሊቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ ሕገ መንግሥቱን የመጣስ ዝንባሌ ግን እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ መንግሥቱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያጸደቀው የራሱ ሕገ መንግሥት ስለኾነ ሕዝብ በመራራ ትግል ያጸደቀውን ሕገ መንግሥት መጣስ የወንጀሎች ሁሉ ወንጀል ነው፡፡

በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ግንዛቤ መያዙ በጣም የሚያስደስት ነው፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ ተስፋ ነው፡፡ ለውጭ ጠላት ደግሞ ሲጠብቀው የነበረ ብጥብጥ መቅረቱ ሕዝብን የሚያስደስት፣ ጠላትን ደግሞ የሚያሳፍር ነው፡፡

ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነሣ ነበር፡፡ አንድ አባታችን ካነሧቸው ብዙ ነገሮች አንዱ፣ ‹‹መንግሥት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን ያስገባል›› የሚል ነው፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ በእስልምናም ይኹን በኦርቶዶክስ እጁን አያስገባም፡፡ በዚህ ጉዳይ የመጀመሪያ ተጠያቂው እምነቱ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም? ሁለተኛው ተጠያቂ ደግሞ መንግሥት ይኾናል፡፡

ስለዚህ በሩን ከፍቶ ሲያንቀላፋ መንግሥት እጁን ካስገባበት እምነቱ ይጠየቃል፡፡ ይኹን እንጂ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት እጁን እንዳላስገባ መቶ በመቶ አምናለኹ፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ሰዎች ግን እጃቸውን አስገብተው ሊኾን ይችላል፡፡ ስለዚህ እነዚህን መመከት ነበረበት፡፡ በመጀመሪያ ተጠያቂው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ራሱ ሲኾን እጃቸውን ያስገቡ ሰዎች ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጠያቂ ይኾናሉ፡፡

ሁለተኛ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ወጣት*የተነሣ ሐሳብ አለ፡፡ አክራሪነት አደጋ ነው ብሏል፡፡ በኋላ በእስልምና ሃይማኖት አካባቢ በአንዳንድ ሰዎች የሚታየው አክራሪነት አደጋ ነው፤ ዋናው ግን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተቀበረው ፈንጅ ነው ትልቁ የአክራሪነት አደጋ ብሏል፡፡ አክራሪነት ማለት እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ማዋል፣ እምነቱን ለፖሊቲካ ጥቅም ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ማኅበራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖሊቲካ መድረክ እያደረጓት ነው፤ ማኅበሩ** እንኳ ባይኾን አንዳንድ ሰዎች ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህን ተጠንቅቆ ያቀረበው ይመስለኛል፡፡ ማኅበሩ ነው አክራሪ ወይስ በማኅበሩ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ናቸው? መጣራት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅበር ያሉ አንዳንድ ሰዎች ማኅበሩ ጤናው የተበከለ እንዳይኾን ማጣራት፣ ተጠንቅቆ መያዙ፣ እንደተባለው ፈንጅ ከኾነ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወጣቱ* እና ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር) ሁለቱም ከባድ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደተባለው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በእውነት የፖሊቲካ መድረክ እየኾነች ከኾነ፣ በዚህ አገር የትኛው አክራሪነት ነው ከተባለ፣ ትልቁ አደጋ ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው የተባለው ትክክል ነው ወይስ ትክክል አይደለም የሚለው መጣራት የሚኖርበት ቢኾንም በሁለቱ ሰዎች የተጠቆመው ግን የሚያስተኛ አይደለም፡፡ ከእምነቱ ቦታ የኾንም መተኛት የለብንም፤ የሌሎች እምነት አማኞችም መተኛት የለባቸውም፡፡

 *                    *                 *

ሐራዊ ማስታወሻ፡-

*አቶ ስብሓት ወጣቱ ሲሉ የጠሯቸው የስብሰባው ተሳታፊ ከከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ከሚገኘው ሃላባ ወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመጡ አባ ዮናስ የተባሉ መነኩሴን ነው፡፡ እኒህ ስመ መነኮስ እንደ በጋሻው ደሳለኝ ላሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን ዐውደ ምሕረት በመፍቀድና ምእመኑን ሰላም በመንሳት በወረዳው የማኅበሩ ጽ/ቤት እንዲዘጋ ያደረጉ፣ ከትምህርቱም ከግብረ ገቡም የሌሉበት ግለሰብ ናቸው፡፡

መንግሥት አካሂደዋለኹ በሚለው የፀረ አክራሪነት ትግል አጋር መስለው የተጠጉ ግለሰቦች [የደብር አስተዳዳሪ ለማሾም 60,000 ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው 60 ጎራሽ የተባሉትንና ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተነሥተው ወደ መ/ፓ/ጠ/ቤተ ክህነት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ምክትል ሓላፊነት የተዛወሩትን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢን ርእሰ ደብር በሪሁ አርኣያን ይጨምራል]  ያላቸውን አግባብነትና የሚሰጡትን መረጃ ትክክለኛነት (ቅንነት) ማጤን ይገባዋል፡፡

አቶ ስብሓት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያራምዱትና በልዩ ልዩ ዘገባዎች ሲገለጽ የቆየው አቋማቸው በተለይ ከ፳፻፩ ዓ.ም ጀምሮ በሚገባ ይታወቃል፡፡ ‹‹ሕገ መንግሥት የሰጠው መብት ሲጣስ፣ መንግሥት እጁን ሲያስገባ ለምን ዝም አለ? ለሕገ መንግሥታዊ መብቱ ለምን አልታገለም?›› ማለታቸው በአባባል ደረጃ ተገቢ ቢኾንም እርሳቸው የጠቀሱትን ሕገ መንግሥታዊ መብት ለማስከበር ቢያንስ በግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም በመጠኑ የሞከሩ ብፁዓን አባቶች ምን እንደደረሰባቸው የሚታወቅ ነው፡፡ ይህን የምንለው ሊቃነ ጳጳሳቱን ልናመሰግናቸው ፈልገን ወይም አቶ ስብሓት እንዳሉት ‹‹በሩን ከፍቶ ያንቀላፋ የለም›› ለማለት አይደለም፡፡ በሌላ መድረክ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ ኹኔታው ምሬታቸውን በገለጹበት ወቅት ‹‹ብትሰየፉስ!›› ያሏቸው የመከራቸው ፍጻሜ ገና መኾኑን ስለሚያሳይ፡፡

አቶ ስብሓት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ ለውጥ በቅ/ሲኖዶሱና በቀድሞው ፓትርያርክ መካከል የተደረገው የውስጥ ትግል በተጧጧፈበት ወራትና ከዚያም ወዲህ በእጅጉ ይጠሏቸው ነበር የሚባሉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው ለማስወገድ ማኅበሩ በቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ካገኘበት የአገልግሎት ዓላማና ስልት ውጭ ሚና ለመስጠትና መሣርያ ለማድረግ የገፋፉበት ኹኔታ በማኅበሩ ቀጣይ ህልውና ላይ ያላቸውን ፍላጎት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ እንደነበር ይነገራል፡፡

ግፊታቸው በወቅቱ በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች መካከል ልዩነት ፈጥሮ እንደነበር የሚገለጽ ቢኾንም ተቀባይነት ያገኘ ግን አልነበረም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹የቤተ ክህነት ዕዳ ነው›› በማለት ‹‹የተቃዋሚ ፖሊቲካ መድረክነት›› እንደሚታይበት ወዘተ ባለፈው ዓመት የፍትሕ ጋዜጣ ጽሑፋቸው የሰነዘሩበት ሒስም የዚያ ማወራረጃ እንደኾነ ይታሰባል፡፡

ማኅበሩ ከተመሠረተበት ዓላማና ከሚፈለግበት አገልግሎት አኳያ በድክመት የሚተችበትና ገና ብዙ እንደሚቀረው የብዙዎች እምነት ቢኾንም በሰሞኑ ስብሰባ አቶ ስብሓት ወጣቱ  ባሏቸው አባ ዮናስ ጥቆማ በኩል አልፈውና የአባ ዮናስን ንግግር አጉነው ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሰጡት አስተያየት ወይ አቅጣጫ መነሻው ጥላቻ የወለደውና ቅንነት የጎደለው መረጃ እንደኾነ የመረጃው ጠቋሚ ሰው ስለ ማኅበሩ ባላቸው አቋምና በወረዳቸው ከማኅበሩ አባላት ጋራ ባላቸው ግንኙነት መረዳት አያዳግትም፡፡

መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡

አባ ዮናስ ከእውነት የራቀ ጥቆማቸውን፣ አቶ ስብሓትም በዚሁ ላይ የተመሠረተ አስተያየታቸውን/አቅጣጫቸውን በሰጡበት መድረክ ሊቃነ ጳጳሳቱ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ናትናአል ፣ አቡነ ኄኖክ፣ አቡነ ጎርጎሬዎስ በአጸፋ የመናገርና ምላሽ የመስጠት ዕድል ተነፍገዋል፡፡ ይኸው የስብሰባው አካሄድ ከአዳራሹ ውጭ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች መካከል በከፍተኛ ደረጃ አጠያይቆ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ በውይይቱ ቤተ ክርስቲያን ከአክራሪነት አንጻር የተገለጸችበትንና ማኅበሩን አስመልክቶ የተሰነዘሩ ሐሳቦችን መንበረ ፓትርያርኩ በቀላሉ እንደማይመለከተውና በጥብቅ እንደሚነጋገርበት ሊቃነ ጳጳሳቱ ለሚኒስቴሩ ሓላፊዎች እንዳሳሰቧቸውም ተገልጧል፡፡

21 thoughts on “ስብሓት ነጋ ጥፋቷን ስለሚመኙላት ቤተ ክርስቲያንና መግደያ ብትር ሊያደርጉት ስለሞከሩት ማኅበረ ቅዱሳን ይወተውታሉ

 1. ABEBE September 5, 2013 at 2:00 am Reply

  Bzuwoch ychin betekrsiyan lematfat leshih ametat taglewal betekrstiyan gn eskahun alech enesu terestewal.Ahunm betbeb betekrstiyann yemiyatequ yemimeslachew tebebachewn tlew nege ke egrua sr ywedqalu.yefq bet gn qimegna slalonech lenebsachew yqrta eyeteyeqech askerenahewnm bekbr tasarfalech.yhe demo yeqrb gize twstachn now.

  And mahberekdusann lemafres bitru Egziabher bzu mahberekdusann yasnesal.Yblagn enji lekesash tehadsowoch.Mgbarachhu keseytan yekefa now.Seytan eko bemanm lay behaset almesekerem bayhon teketayu lemadreg ytral enji.Behaset yemtterut geta ytazebal.frdum eruq ayhonm.

 2. Anonymous September 5, 2013 at 6:17 am Reply

  egna eyamelekin yalenew Egziabhern new manin seyf lay biwedik yemigodaw seyfu aydelem.

 3. Anonymous September 5, 2013 at 8:09 am Reply

  ምንም ይባል ምን ማኅበሩ አንደሚባለውአክራሪ ሳይሆን የቤተክርስቲያኑዋ አገልግሎት አንዲፋጠን አጋዥ አካል ነው:: ይህንንም ቀርበው ማየት ይቻላል:: አለበለዚያ ወረድ በሉለት አገልግሎቱን ያገልግልበት::

 4. Anonymous September 5, 2013 at 10:38 am Reply

  Aboy esat baychiru yishalal . It is sucidal for the EPRDF led government . Be haymanotachin keld yelem endihum bemahiberachin !

 5. Anonymous September 5, 2013 at 1:38 pm Reply

  An old man is considered as wise in our culture, because he will analyse and speak based on the fact. Father Sebhat should know he was used (dis-informed) by Abba Yonas for his secterain mission.

 6. Nigat September 5, 2013 at 2:16 pm Reply

  ወጣቱም ሆነ ስብሐት ነጋ ያሉት ትክክል ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ ከማሕበራት ወከባ ራስዋን ልትጠብቅ ይገባታል።

 7. Anonymous September 5, 2013 at 2:25 pm Reply

  ጭንቅላቱ የበሰበሰ ሽማግሌ በመሞቻው እንኩአን የማይማር አሁን ምን ቀረኝ ብሎ ነው ደሞ ከቤተክርስቲያን አናት ላይ የማይወርደው እግዚአብሔርን ይፈዳል የሽማግሌው ተራ ደርሷል መሰለኝ::ለነገሩ በጣም የምያሳምመው ነገ ሲሞት አሸቃባጮች በሀገር ደረጃ ፍታት ይደረግለት ማለታቸው የማይቀር ነው ::በተረፈ ውስጧ ተሸጉጠው የሚገኙ መናፈቃንን አስተዳደሩ (የቤተክርስቲያ) መመንጠር ቢያቅተው በየስብሰባው እየወከለ ቤተክርስቲያንን እንዲያደሟት መፍቀድ ግን የግፍ ግፍ ነው ::ቤተክህነቱም ቢሆን በአስቸኳይ ከመናፈቃን መፅዳት አለበት ::ይህም በቤተክርስቲያን የበላይ አካል (ቅዱስ ሲኖዶስ) ሊታሰብበት ይገባል ::እግዚአብሔር የቤተክርስቲያን ጠላቶችን ድባቅ እንደሚመታ አያውቁም እንዴ?ማንም ስይፍ ላይ ቢወድቅ ሰይፉ ሳይሆን የወደቀው ይቆረጣል::ከእግዚአብሔር ጋ ትግል ለመቆረጥ ነውና ተራህን በቅርቡ እናየዋለን::

  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን ::

 8. mulushewa September 5, 2013 at 3:32 pm Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ላለፉት ሀያ ምናምን አመታት ከስሙ ይልቅ ስራው የገነነ የኢኦተቤክ አጋዥ ሆኖ ቆይቱአል አሁንም እንዲቀጥል ምኞቴ ነው. ሆኖም አሁን አሁን ከስራው ይልቅ ስሙ መግነኑ እና አንዳንድ ነገሮቹ አልተመቹም. በተለይ
  1.ሁለት አይነት የሚዲያ አጠቃቀም-ይፋዊ እና ይፋዊ ያልሆነ(ደጀሰላም፣አንድ አድርገን፣ሀራ ተዋህዶ). በተለይ ይፋ ያልሆኑቱ አርአያ የሚሆኑ በህይወት ያሉና የሌሉ አባቶችን ህይወት ከመተረክ ይልቅ ባንድ ወገን ቆመው ለማህበሩ አስጊ ናቸው ባሉዋቸው ሁሉ በጭፍን ይተኩሳሉ. በነዚህ ሚዲያዎች የቤ/ክ አመራሮች ኢላማ በመደረጋቸው የማህበሩን አባላት እንደልጅ አቅርቦ መምከሩንና መገሰጹን ትተው ስማቸው እንዳይጠፋ በመፍራት ብቻ እያዩ ዕንዳላዩ እየሆኑ ነው.ማህበሩ በስሙ ከመፈራት ይልቅ በስራው ለመወደድ ብዙ ይስራ በ..ተ..ለ..ይ በማህበረ ካህናት ዘንድ ማህበሩ የሚታይበት የጥርጣሬ አይን
  2.ተገቢ ያልሆነ ቡድናዊ መዋቅር-በአሁን ሰአት ሰ/ጉባኤና ሰ/ት/ቤቶች ተጠሪነታቸው ለአጥቢያ አብ/ክርስቲያናት ሳይሆን ለማህበሩ የሆነ ይመስላል.በዚህም አጥቢያውን ዘለው የኦዲት ሪፖርት የምናቀርበው ለማህበሩ ነው የሚሉ ሰ/ት/ቤቶችን ማየት ከለመድን ቆየን
  3.ፖለቲካ- መንግስት ኢኦተቤክንን ካለፉት ስርኣቶች ጋር ለመደመር የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መቃወም ፖለቲካ ካልተባለ በቀር በሀገር ውስጥ ያለው የማህበሩ እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን ከፖለቲካ የጸዳ ይመስለኛል.ባህር ማዶ ያለው የማህበሩ ክንፍ ግን ያጠራጥራል.ይህን ደግሞ የማህበሩን የአሜሪካ እንቅስቃሴ ሲያsተጋባ የቆየው ደጀሰላም በተደጋጋሚ ከሚያወጣቸው ገዥውን ፓርቲ የሚወቅሱና አንዳንዴም ቢሆን ተቃዋሚን የሚወግኑ በኢሳት እስከመጠቀስ የደረሱ ዘገባዎች መረዳት ይቻላል
  4.ካህናትን እንደጥቅመኛ ፈርጆ ራስን ብቸኛ የቤ/ክ ተቆርቁዋሪ ማድረግ-ይህ አቁዋም በተለይ በተራ አባላት ላይ ስር እየሰደደ መጥቱዋል. እኔ(እኛ) ብቻ የሚሉ ደግሞ በሀገራችን ምን ያህል ጥፋት(ሽብር) እንደሰሩ ታሪክ ምስክር ነው.ስለዚህ ስለአቦይ ስብሃት፣ስለአባ ዮናስ፣ስለሚኒስቴሩ እና ስለመንግስት ከማውራታችን በፊት ንግግራቸውን አጢነን ራሳችንን እንመርምር.ማን ተናገረ ሳይሆን ምን ተናገረ የሚለው ላይ እናተኩር.የለበለዚያ ያው የፈረደበት የፍረጃ አዙሪት ውስጥ መውደቃችን ነው.
  5.በሰ/ት/ቤቶች አመራር አካባቢ ያሉትን የስነ-ምግባር ችግሮች ለመቅረፍ አለመሞከርና መተካካትን አለማበረታታት-የማህበሩ ዲሞልራሳዊ የውስጥ አሰራርና የአመራር መተካካት ሂደት ምርጥ የሚባል ቢሆንም ይህ ልምድ ለሰ/ት/ቤቶች ባለመትረፉ 20 እና 30 አመታት ከክፍል ክፍል ሲዘዋወሩ ቆይተው በስንት ትግል የሚወርዱ የሰ/ት/ቤት አባላት ጉዳይ ሽብር ባይሆንም ሼም ነው
  6.ካህን መርጦ መሳለም-የማህበሩ አባላት የሲኖዶስን ውሳኔ ሳይጠብቁ ካህናትን በየሰበብ አስባቡ እየፈረጁ መርጦ መሳለም ፋሽን ኁኗል.አስተውሉ ከማህበሩ ኔትወርክ አንጻር በዚህ መልኩ የተፈረጀ ካህን በማህበረ ምእመናኑ ምን ያህል ሊገለል እንደሚችል.
  7.ከመንግስት የተቀራረበ የመሰለውን ሁሉ መፈረጅ-አንዱ መንግስት ማህበሩን እንዲጠራጠር የሚያደርገው ምክንያት ይህ ይመስለኛል.ይህ ደግሞ በአቡነ ጳውሎስ፣በአባሰረቀ፣በንቡረዕድ፣በዲ/ባያብል፣በዲ/ዳንኤል ታይቱዋል.ቢታረም!!!

 9. Anonymous September 5, 2013 at 4:32 pm Reply

  “መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘ”
  እኔ ከላይ ስለተዘረዘረው ጉዳይ ወይም እንደ ስብሃት ስላሉ የዲያቢሎስ ግብረ አበሮች ሳይሆን ሃሳብ የምሰጠው ከላይ ስላስቀመጥኩት ሃሳባችሁ ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ በቤተ ክርስትያን ስር ብዙ አካላት አሉ እንደ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ሊቃውንት ጉባኤ፣ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤት የመሳሰሉት፡፡ታዲያ ማህበረ ቅዱሳን በሰንበት ት/ቤት ስር ሆኖ ሳለ፣ ሌሎችም ብዙ ማህበራት በሰንበት ት/ቤት ስር እንዳሉ እየታወቀ፣ ለምንድነው ማህበረ ቅዱሳን በማህበር ደረጃ ቤተ ክርስትያንን መወከል አለብኝ ብሎ የሚታበየው፡፡ ይህ ዓይነቱ አካሄድ ለማንም አያዋጣም፡፡ቤተ ክርስትያን ተወካዮች ላኪ ስትባል አስፈላጊ መስሎ ከታያት እና ተወካዮች ከማህበረ ቅዱሳን ተወክለው ይሂዱ ብላ ከወሰነች ትሄዳላችሁ እንጂ የምን ትዕቢት ነው “ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘ” የምትሉት፡፡ አስቡበት ራስን ከቤተ ክርስትያን በላይ ማድረግ ምን ሊያመጣ እንደሚችል፡፡

  • Anonymous September 6, 2013 at 5:35 am Reply

   ማኅበሩ መንበረ ፓትርያርኩ ወክሎ ልኮት አልወከልም አልሄድም አለ የሚል ነገር የለም።መቼም መንበረ ፓትርያርኩ 50 ተሳታፊዎችን ሲወክል በቃል ሳይሆን በደብዳቤ መሆን አለበት እንደ አንድ ተቋም።ተወካዮቹም ቢሆኑም እኮ የተወከሉበትን ደብዳቤ ካልያዙ በቀር ዘው ብለው ስብሰባውን መካፈል አይችሉም።ታዲያ ማኀበሩ እንደ ማህበር ካልተጋበዘ እንዴት አድርጎ በስብሰባው ላይ መሳተፍ ይችላል።
   መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡ምናልባትም እኮ ለሚነሱበት ጥያቄዎች ቀጥተኛ መልስ እዳይሰጥ ተፈልጎስ ቢሆን።

 10. Anonymous September 6, 2013 at 5:36 am Reply

  ማኅበሩ መንበረ ፓትርያርኩ ወክሎ ልኮት አልወከልም አልሄድም አለ የሚል ነገር የለም።መቼም መንበረ ፓትርያርኩ 50 ተሳታፊዎችን ሲወክል በቃል ሳይሆን በደብዳቤ መሆን አለበት እንደ አንድ ተቋም።ተወካዮቹም ቢሆኑም እኮ የተወከሉበትን ደብዳቤ ካልያዙ በቀር ዘው ብለው ስብሰባውን መካፈል አይችሉም።ታዲያ ማኀበሩ እንደ ማህበር ካልተጋበዘ እንዴት አድርጎ በስብሰባው ላይ መሳተፍ ይችላል።
  መንበረ ፓትርያርኩን በመወከል በስብሰባው እንዲገኙ ጥሪ ከተደረገላቸው 50 ተሳታፊዎች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን በዋና ጽ/ቤቱ ደረጃ እንደማኅበር እንዳልተጋበዘና ይህም በአክራሪነት ከተካሄደው ፍረጃ ጀምሮ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡ምናልባትም እኮ ለሚነሱበት ጥያቄዎች ቀጥተኛ መልስ እዳይሰጥ ተፈልጎስ ቢሆን።

 11. anteneh yes September 6, 2013 at 9:26 am Reply

  ማቅ እየተነገረለት ያለውን ያክል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አላገለገለም፡፡፡፡፡ ባይሆን አባላቱ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ማኅበሩን አስበልጠው እንዲያዩ በማድረግ አደንዝዟቸዋል ይህ ደግሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገለገለ ለማለት አያስደፍርም፡፡
  ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ አዘጋጆችና አንባባያን ከላይ የተባሉት ችግሮች ከሌሉበት ታዲያ ምን ያስፈራዋል

  • anteneh yes September 6, 2013 at 9:29 am Reply

   ማቅ እየተነገረለት ያለውን ያክል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አላገለገለም፡፡፡፡፡ ባይሆን አባላቱ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይልቅ ማኅበሩን አስበልጠው እንዲያዩ በማድረግ አደንዝዟቸዋል ይህ ደግሞ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገለገለ ለማለት አያስደፍርም፡፡
   ጥያቄ ለዚህ ጽሁፍ አዘጋጆችና አንባባያን ከላይ የተባሉት ችግሮች ከሌሉበት ታዲያ ምን ያስፈራዋል

 12. getu September 19, 2013 at 1:07 pm Reply

  How can you expect Sibihat Nega and his Surrogate children to Praise Mahibere Kidusan. I am not Member of this association but I feel that Sibhat Nega and his surrogate children Like Dr Shiferaw Tekle Mariam do not have any common ground MK. Their play ground are 100% different and polarized not because of politics rather because of ideology. Dirty politics of the earth and Holy sprit from heaven.

 13. Annonyname September 24, 2013 at 11:46 am Reply

  Ahun tigle yejemerachihut betechrstiyanitun kemeseretat ke Egziabhare gar newu. Yeman kind yitenekir yihon yenante/Yefetari? tiyakewun kenante wuchi eminet/haymanot yalewu hulu yawukewal.ke Egziabhare gar yemitalu yidekalu

 14. MINILIK SALSAWI March 28, 2014 at 2:40 pm Reply
 15. Anonymous April 1, 2014 at 6:59 am Reply

  ለመሆኑ ሽማግሊዉ ስለነፍሳቸዉ ከመጸለይ ለምን ድነዉ ስለቢተ-ክርስቲያን ጥፋት የሚመኙት ማህበሩ-እንደዉ ስለእዉነትየኮመነዉ በአጠካላይ ኢሀድግ እጁን ከቢተክርስቲያን ያን ሳልን በህግ-አምላክ

 16. Anonymous August 21, 2016 at 4:24 am Reply

  ስራ በልብ ነው።

 17. Anonymous August 21, 2016 at 4:27 am Reply

  ማህበሩ እስከ አሁን ድረስ እያለቀሰ እንባ እየረጨ ነው የታገሳቹህ። ወደፊትም መፍትሔውን እስከቀበራችሁት ድረስ ይቀጥላል። አዛኝ መሳይ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: