የድሬዳዋ ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ሰ/ጉባኤ: ‹‹የሃይማኖት ጉዳይ በድምፅ ብልጫ አይወሰንም›› ሲል በኑፋቄ ውዝግብ የታሸገው ሰንበት ት/ቤት እንዲከፈትና በኑፋቄ የተጠለፈው አመራር እንዲቀጥል ሀ/ስብከቱ በድምፅ ብልጫ ያስተላለፈውን መመሪያ ተቃወመ

 • አመራሩ በታገደበት ቆይቶ የኑፋቄ ውዝግቡ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠይቋል
 • አመራሩ ኑፋቄው በአግባቡ እንዳይጣራ የተለያዩ ተጽዕኖዎችን ሲፈጥር ቆይቷል
 • ብዙኀኑ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አባላት በውሳኔው ቃለ ጉባኤ ላይ አልፈረሙም
 • ‹‹ከዚህ በኋላ ለሚፈጠረው ችግር ሓላፊነቱን የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ይወስዳል፡፡›› /ሰበካ ጉባኤው/

በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ሕዋስ በመጠለፉና በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት ለሰበካ ጉባኤው መመሪያ ባለመገዛቱ የመዘጋት ርምጃ የተወሰደበት የድሬዳዋ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት እንዲከፈትና ነባሩም አመራር እንዲቀጥል የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በድምፅ ብልጫ ወስኖ ያስተላለፈውን መመሪያ የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡

‹‹የሃይማኖት ጉዳይ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በሊቃውንትና ካህናት ጉባኤ እንጂ በአስተዳደራዊ መንገድና በድምፅ ብልጫ አይወሰንም›› ያሉት የሰበካ ጉባኤው አባላት፣ ውዝግቡ ከሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ውጭ በገለልተኛ ጉባኤ እንዲታይ አልያም ሰበካ ጉባኤውንና ማኅበረ ካህናቱን ከታገደው የሰንበት ት/ቤቱ አመራር ጋራ አቀራርቦ በማነጋገር፣ ጥፋተኛውን በመለየትና በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ በማድረግ እንዲፈታ አሳስበዋል፡፡

የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ ለሀ/ስብከቱ ውሳኔ ምላሽ ለመስጠት ነሐሴ ፲፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ እንደተገለጸው÷ ከግማሽ በላይ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ አባላት አጣሪም ወሳኝም ኾነው በተሳተፉበትና በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ሕዋስ የተጠለፈው የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አመራር ችግር በግልጽ በታወቀበት ኹኔታ በድምፅ ብልጫ የተላለፈው ውሳኔ ፍትሐዊነት ይጎድለዋል፤ የታገደውን አመራር የተሳሳቱ ሐሳቦችም የሚደግፍ ነው፡፡

Dire Dawa St Michael Church

የድሬዳዋ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

የሰበካ ጉባኤው የተቃውሞ ውሳኔ እንደሚያብራራው የሰንበት ት/ቤቱ አመራር÷ በኑፋቄ በመጠርጠሩ ከሓላፊነትና አባልነት ታግዶ ማጣራት እየተካሄደበት ለሚገኘው ሊቀ መንበሩ ጥብቅና በመቆም ማጣራቱ በአግባቡ እንዳይከናወንና እንዲድበሰበስ የሰንበት ት/ቤቱ የወቅቱ አባል ያልኾኑ የሌላ አጥቢያ ምእመናንን ጭምር ለዐድማና ዐመፅ በማንቀሳቀስና የሰንበት ት/ቤቱ አባላትም የዐውደ ምሕረት አገልግሎት እንዲያቆሙ ያለፈቃዳቸው በማስገደድ ጫና ፈጥሯል፤ በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት ከሰበካ ጉባኤው የሚሰጠውን መመሪያ ‹‹ሰበካ ጉባኤ አያዘንም›› በሚል አይቀበልም፤ በካቴድራሉ የሚደቡለትን መምህራን ይንቃል፤ ካህናቱን ያቃልላል፤ አባላቱም ከማኅበረ ካህናቱ ጋራ በአባትና ልጅ መንፈስ እንዳይተያዩ እየቀሰቀሰ በካቴድራሉ ከፍተኛ ብጥብጥና ንትርክ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

አመራሩ በዚህ አካሄዱ እንዲቀጥል ከተፈቀደለት የዐመፅና ብጥብጥ ተግባሩን እያሰፋ የሚሄድ በመኾኑ፣ በኑፋቄ በተጠረጠረው የሰንበት ት/ቤቱ ሊቀ መንበር ላይ በጉባኤ ካህናት የሚካሄደው ማጣራት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ጽ/ቤቱን የማሸግ፣ አመራሩንም ከሓላፊነት የማገድ ርምጃ መወሰዱ ተገልጧል፡፡ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በአጣሪ አካሉ አማካይነት ይህን የሰንበት ት/ቤቱን አመራር ችግርና ከመመሪያ ውጭ መኾን አረጋግጦ ሳለ ባለጉዳዮችን አቀራርቦ ለማነጋገር እንኳ ሳይሞክር የታሸገው ሰንበት ት/ቤት እንዲከፈትና የነበረው አመራር እንዲቀጥል መመሪያ መስጠቱ አግባብነት እንደሌለው የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ በተቃውሞ ውሳኔው ገልጧል፤ ከዚህ በኋላም ለሚፈጠረውም ችግር ሓላፊነቱ የሀ/ስብከቱ እንደሚኾን አሳስቧል፡፡

ሰበካ ጉባኤው በደረሰበት የጋራ አቋምና ስምምነት መሠረት የታገደው የሰንበት ት/ቤቱ አመራር የአስተዳደሩን መመሪያ ካለመቀበል ባሻገር ለካቴድራሉ አገልጋይ ካህናትና መምህራን ያለው አመለካከት ዝቅ ያለና ምንም እንደማያውቁ የሚቆጥር በመኾኑ፣ የሚመደቡለትንም መምህራን በቀናነት ስለማይመለከት እንዲቀጥል ሊፈቀድለት አይገባም፤ ሓላፊነቱን ማስረከብና በአዲስ ሥራ አመራር መተካት ይኖርበታል፡፡ በመኾኑም የሀ/ስብከቱን ውሳኔ ተቀብሎ ለማስፈጸም እንደሚቸገርና ጉዳዩ ከአስተዳደር ጉባኤው አባላት ውጭ በኾነ ገለልተኛ አካል ዳግመኛ እንዲታይ ጠይቋል፡፡

የሀ/ስብከቱ ምንጮች በበኩላቸው፣ በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አማካይነት ለካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ የተላለፈው መመሪያ ሰባት አባላት ያሉት የሀ/ስብከቱ አጣሪ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ የአስተዳደር ጉባኤው አባላት ተወያይተው ውሳኔ ያሳለፉበትን ቃለ ጉባኤ ተመልክተው ሳይፈርሙበት በችኮላ የወጣ ነው፤ በውሳኔያቸውና በተላለፈው መመሪያ መካከል ልዩነት በመኖሩ በድምፅ ብልጫ ተወስኖበታል በሚባለው መመሪያም አይስማሙም፡፡ ጉዳዩ በጉባኤ ካህናት/ጉባኤ ሊቃውንት እንጂ በአስተዳደራዊ መንገድ ብቻና በድምፅ ብልጫ ሊመረመር እንደማይገባ አክለው የሚያስረዱት ምንጮቹ÷ ከሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሰንበት ት/ቤቱን አመራር ከጠለፈው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ሕዋስ አንዱ ናቸው ተብለው ከሚጠረጠሩት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ሓላፊውና ሌሎች ሁለት ሓላፊዎች በቀር የሚበዙት ሓላፊዎች በቃለ ጉባኤው ላይ አለመፈረማቸውን አክለው ተናግረዋል፡፡

በርግጥ የሰበካ ጉባኤው የእገዳ ርምጃና በጉባኤ ካህናት የሚካሄደው ማጣራት በሊቀ መንበሩ ላይ የተወሰነ ኾኖ ሳለ ሁሉም የአመራር አባላት ከሊቀ መንበሩ ጋራ መወገናቸው፣ ከዚህም አልፈው መላው የሰንበት ት/ቤት አባላት እንዳያገለግሉ ማነሣሣታቸው አግባብ እንዳልኾነ የሀ/ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ለካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ በሰጠው መመሪያ ተችቷል፤ የሰንበት ት/ቤት ዋና ዓላማ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ መሄድና መመሪያን አክብሮ ማስከበር እና አገልግሎት መስጠት እንደመኾኑ መጠን ስሜታዊ ከመኾን ርቀው የአባቶችን ምክርና ትምህርት እንዲቀበሉም አሳስቧል፡፡ የታገደው የሰንበት ት/ቤቱ አመራር ወደ ሓላፊነቱ ተመልሶ ሰንበት ት/ቤቱን በቅርበት የሚከታተልና ምክር የሚሰጥ አባት ከብቁ መምህር ጋራ እንዲመደብ፣ አመራሩም ከሰበካ ጉባኤው ጽ/ቤት ጋራ ተቀራርቦ እንዲሠራ ማዘዙ ግን ከተመክሮና አመራሩ ከተጠለፈበት ባሕርዩ የተነሣ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋችና ተቀባይነት የሌለው መኾኑን የሰበካ ጉባኤው የተቃውሞ ምላሽ ይገልጻል፡፡

ሰንበት ት/ቤቱን ለመታሸግ፣ አመራሩን ለመታገድ ያበቃው የኑፋቄ ውዝግብ የተቀሰቀሰው የሰንበት ት/ቤቱ ሊቀ መንበርና በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በፌስቡክ ገጹ ላይ ‹‹ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም የሚለው አባባል የማይሞች ነው›› ብሎ ማስፈሩን ተከትሎ ነው፡፡ ተቃውሞው በዚያው በፌስቡክ ገጽ ላይ ትችታቸውን በሰነዘሩ የካቴድራሉና ሌሎች አጥቢያዎች ሰንበት ት/ቤት አባላት፣ ሰባክያንና ካህናት ተጀምሮ ሲስፋፋ ሊቀ መንበሩ በሰበካ ጉባኤው ውሳኔ ታግዶ ጽሑፉ የሰፈረበት ኹኔታ እንዲጣራ እየተደረገ ሳለ የሰንበት ት/ቤቱ አመራር አባላት በሙሉ ‹‹የእርሱ አቋም/ሐሳብ ሐሳባችን/አቋማችን ነው›› በማለታቸው ለውዝግቡ መጠናከር መንሥኤ ኾኗል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አስተያየት ሰጭዎች የውዝግቡ መንሥኤ ወይም አጋጣሚ ይህ ይኹን እንጂ የሰንበት ት/ቤቱ አመራር ከዚህም ሥር በሰደደ የጥርጥር ማዕበል የተመቱ መኾናቸውን ይመሰክራሉ፡፡ ለዚህም የቤተ ክርስቲያናችን ነገረ ማርያም እና የክብረ ቅዱሳን አስተምህሮ ‹‹የዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ሸክም ነው››፤ ‹‹በቀጥታ ኢየሱስን እንጂ ለምን ዙርያ ጥምጥም እየሄድን አስተርጓሚ እንፈልጋለን››፤ ‹‹ኦርቶዶክስ ባለሥልጣን እንጂ ሊቅ የላትም›› ማለታቸውን በአብነት ይጠቅሳሉ፡፡

His Grace Abune Enbakom Archbishop of Dire Dawa and West Haraghe

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም
የድሬዳዋ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

አስተያየት ሰጭዎቹ÷ የሰንበት ት/ቤቱን አገልግሎት በጊዜያዊ ኮሚቴ እንዲቀጥል አድርጎ በአመራሩ ሥር የሰደዱ ችግሮች ላይ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንና ቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ መሠረት ዙርያ መለስ ማጣራት ማካሄድ፣ አመራሩን የጠለፈውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሕዋስ ለማፍረስና የካቴድራሉን ሰላም ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ይላሉ፤ ለአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የደረሰው የካቴድራሉ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ ጥያቄና የተቃውሞ አቋም በዚሁ መንገድ ታይቶ መፍትሔ እንደሚያገኝም ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

በጥቅምት ፳፻፬ ዓ.ም የተካሄደው ፴፩ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስለ ሰንበት ት/ቤቶችና ሊደረግላቸው ስለሚገባ ጥበቃና ክብካቤ ያሳለፈው ውሳኔና ያወጣው የአቋም መግለጫ የሚከተለው ይላል፡-

 • ሰንበት ት/ቤቶች የቤተ ክርስቲያን ልጆችና ቅን አገልጋዮች፣ ተረካቢ አባላትና ተከላካይ ትኩስ ኀይል መገኛ እንዲኾኑ በአበው በጥልቅ ታስቦ የተመሠረተ ተቋም መኾኑ ይታወቃል፡፡ ስለኾነም መንፈሳውያን ወጣቶች በትምህርተ ሃይማኖት ታንጸው፣ በመልካም ሥነ ምግባር ተኮትኩተው ያድጉ ዘንድ ተገቢውን ቦታና ትኩረት በመስጠት የዕለት ከዕለት ክትትል እናደርጋለን፡፡ በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንም አስፈላጊውን ሁሉ እናሟላለን፡፡ ለሰንበት ት/ቤቶች መምህራን፣ አሳራጊዎችና ጠባቂዎች ካህናት እንዲኖራቸው የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን፡፡ ኾኖም መምሪያው በሁሉም በኩል ተጠናክሮ በበላይነት እንዲያበረታታን እንጠይቃለን፡፡

 

Advertisements

28 thoughts on “የድሬዳዋ ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ሰ/ጉባኤ: ‹‹የሃይማኖት ጉዳይ በድምፅ ብልጫ አይወሰንም›› ሲል በኑፋቄ ውዝግብ የታሸገው ሰንበት ት/ቤት እንዲከፈትና በኑፋቄ የተጠለፈው አመራር እንዲቀጥል ሀ/ስብከቱ በድምፅ ብልጫ ያስተላለፈውን መመሪያ ተቃወመ

 1. ZMTA September 2, 2013 at 1:14 pm Reply

  እስኪ በእነዚኽ በቀጥተኛ ጥቅስነት ባፈራችኋቸው ነጥቦች ላይ ጥቂት እንደተማረ ሰው እንወያይ፡፡ (እንሰዳደብ አላልኹም- ክርስቲያናዊ አይደለምና)

  1. “የዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ሸክም ነው››
  ክብረ ቅዱሳንም ኾነ ነገረ ማርያም ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ እንዳልወለዳቸው ማንም የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ የሚያነብ ሰው ይረዳዋል፡፡ አኹን በኑፋቄ ጠርጥረናቸዋል የተባሉት ሰዎችም እውነት አፋቸውን አውጥተው ነገረ ማርያምና ነገረ ቅዱሳን ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ የፈጠረው ነው ለማለታቸው አንድም ማስረጃ አላየኹም፡፡ ሰዎቹ “ያለማርያም አማላጅነት ዐለም አይድንም፡፡” የሚለውን ዐዲስና ልብ ወለድ ትምህርት አንስማማበትም በማለታቸው ክብረ ማርያምን ተፃረሩ የምትሉ ከኾነ ግን ክርክራችኹ ውድቅ ነው፡፡ ምክንያቱም እመቤታችንን ለማክበር በሚል ሰበብ ይኽንን በምሥራቅም፣ በምዕራብም ቤተ ክርስቲያን ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ መፈክር (አስተምህሮ እንዳልለው ከብዶኝ ነው፡፡) ካልተቀበላችኹ የምትሉ ከኾነ የሚያመጣውን የነገረ መለኮት ተፋልሶ አላስተዋላችኹትም ማለት ነው፡፡ ክርስትና ከእስልምና የሚለይበት እኮ ክርስትና “መዳን በሌላ በማንም የለም፡፡ እንድንበት ዘንድ የሚገባው ከሰማይ በታች የተሰጠ ስም ከኢየሱስ በስተቀር ሌላ ማንም የለም፡፡” “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚወጣ የለም፡፡” ሲል እስልምና ግን “በነቢያት፣ በቅዱሳን ጸሎት እንድናለን፡፡” ስለሚል ነው፡፡

  እመቤታችንን በማክበርና ስለ እመቤታችን የተጻፈውን ኹሉ በማክበር መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ እመቤታችን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ብሎ ለማክበር ተአምረ ማርያምን ማመን ሊጠበቅብን አይገባም፡፡ ተአምረ ማርያምን የጻፉት ሰዎች በዘመናቸው እንደነበራቸው ንቃተ ኅሊና ጽፈውታልና ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ ስንመዝናቸው አጨቃጫቂ የኾኑ ነገሮች ይገኙበታል- ለምሳሌ የእስጢፋኖስን ተከታዮች በአሰቃቂ ኹኔታ ስለ ገደላቸው እመቤታችን ብርሃን አወረደችልኝ የሚለውን፣ ተአምሯን የሰማ ሥጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይኾንለታል የሚለውን ክፍል መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይኹን እንጂ ይኽ መጽሐፍ የዶግማ መጽሐፍ ስላልኾነ “እርሱን ያላመናችኹ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተለዩ፡፡” ብሎ ማወጅ አይገባም፡፡ የሚወድድ ይቀበለው፡፡ ያልፈለገ አይቀበለው፡፡ ሊቃውንቱ በአድርባይነትና በቲፎዞ ብዛት ሳይኾን በነጻነት፣ በዕውቀትና በእምነት ሰፊ ጊዜ ሰጥተው ተከራክረው እስኪወስኑበት ድረስ መጽሐፉን ላለመቀበል ነጻነታችን የተከበረ መኾን አለበት፡፡ ከኹሉ አስቀድሞ፣ በክርስትና በጸሎተ ሃይማኖት ከተገለጠው ውጪ ያለ ነገር ትርፍ እንጂ ዋና ነገር ሊኾን አይችልም፡፡ እንዳስፈላጊነቱ በማስረጃ ላይ እየተመረኮዝን በዕውቀትነት ሊያከራክረን እንጂ በጥላቻ ተሞልተን እንድንጨቃጨቅ ሊያደርገን አይገባም፡፡

  2. ‹‹በቀጥታ ኢየሱስን እንጂ የምን ዙርያ ጥምጥም እንሄዳለን››
  ቤተ ክርስቲያንን በሰማይም በምድርም ያሉ የቅዱሳንን ቤተሰባዊ ጸሎት መጠየቅ የለብሽም እስካላሉ ድረስ “እኛ በቀጥታ ኢየሱስን እንጠይቃለን፡፡” ካሉ መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል፡፡ ቅዳሴው፣ ኪዳኑ የቅዱሳንን ስም ሳይጨምር የሚቀርብ ጸሎት አይደለምን? ለስሙ ክብር ይኹንለትና “ኢየሱስ” ሲባል ጥሩ ጠበል እንዳየ ጋኔን መበርገግ አይገባም- “ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላልና፡፡” ኢየሱስን በማናገር፣ በማፍቀር ሲያድጉ አካሉ ከኾኑት በሰማይም በምድርም ከሚኖሩ ቅዱሳን ጋር ኅብረታቸው መጠንከሩ አይቀርም፡፡ በመኾኑም ነጻነታቸው ሊከበርላቸው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች በክርስቶስ በመኾንና መቼም በማይጥለው፣ ለሚተማመኑበትም ነገሮችን ኹሉ ለበጎ በሚለውጠው ፍቅሩ በመታመን፣ እንዲኹም ሕይወታቸውን ኹሉ ለዚኽ አስተማማኝ ፍቅሩ ምላሽ የመስጠት ሕይወት አድርገው የመንፈስ ነጻነትን የሚቀዳጁባት ነጻ የምታወጣ የሰላም ከተማ እንጂ፣ ሰዎች በፍርኃት ታስረው፣ እግዚአብሔር ካኹን አኹን ምን መዓት ያወርድ ይኾን እያሉ ተሸማቅቀው የሚኖሩባት የኅሊና እስር ቤት መኾን የለባትም፡፡

  3. ‹‹ኦርቶዶክስ ባለሥልጣን እንጂ ሊቅ የላትም››
  ይኽ አባባላቸው (እውነት ብለውት ከኾነ) በተመለከቱት ነገር መቆጣታቸውን ያሳያል፡፡ ነገር ግን መናፍቅ የሚያሰኛቸው አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንዲት ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሊኖሯትም ላይኖሯትም ይችላሉ፡፡ ሊቃውንት ቢኖሯትና በየጊዜው የሚነሡ ነገሮችን ከሸመደዱት ሽምደዳ አኳያ ሳይኾን በጥንቃቄ በተጠናና ዘመኑን በዋጀ (ዘመኑን በሚራገም ወይም “አባቶቻችን ቅዱሳን ነበሩና እነርሱ ያሉት ነገር ኹሉ ትክክል ነው፡፡” በሚል ጭፍን አመለካከት አላልኹም) ዕውቀትና መንፈሳዊነት ከልዩ ልዩ አካላት ለሚነሡ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ብትችል ጥሩ ነው፡፡ ካልኾነ ደግሞ ዕውቀት ማለት ሽምደዳ የኾነባቸውን ወይም ዘመኑን በቅጡ ያልተረዱ ሰዎችን “ሊቃውንት” ብላ ሠይማ እርሷ ተሠቃይታ ልጆቿንም ከምታሠቃይ “ለዛሬው ሊቅ የለኝም ባይኾን ለነገ ሊቃውንት እንድትኾኑኝ ኑ፡፡ ተማሩልኝ፡፡” ብትል ወንጀል አይደለም- ክርስትና እውነትን መጋፈጥ እንጂ ከላይ ከላይ የገጽታ ግንባታ መሥራት ውስጥ ውስጡን ደግሞ በግብዝነት፣ በሐሰትና በሙስና መግማት አይደለምና፡፡ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጃትና የራሱ ያደረጋት ጌታ ኢየሱስ ነው እንጂ ሊቃውንት አይደሉም፡፡ ስለኾነም ሰዎቹ ጥያቄያቸውን አቅርበው ከማስፈራራትና ከመራገም የዘለለ አመርቂ መልስ የሚሰጥ ሰው ካላገኙ በብስጭት ይኽን ቢሉ ሊፈረድባቸው አይገባም፡፡ “ሊቅ አለ፡፡” ከተባለ ያ አለ የተባለው ሊቅ ተዘጋጅቶ፣ መልሱን አሰናድቶ በትሕትና ያናግራቸው፤ በጸሎት መንፈስ ያወያያቸው እንጂ ሰንበት ትምህርት ቤታቸውን ማሸግና መናፍቅ እያሉ ማብጠልጠል የታሪክ ተወቃሽ ያደርጋል፡፡ በአውሮፓ እነ ጋሊሌዮን ያሠቃየው የሃይማኖት ፍርድ ቤት (Inquisition) ይኸው ዛሬ ድረስ ሲወቀስ እንደሚኖር ታውቁ የለምን? ፍርድ ቤቱ ያንገላታቸው እነጋሊሌዮ ግን ዛሬ እነሆ ዓለም ያመሠግናቸዋል፡፡ እግዚአብሔር እንኳ የለኽም የሚሉትን ሰዎች በፍቅሩ ያቅፋቸዋል፤ በእንክብካቤው እያደሰ የእርሱ ተአምር ያልኾነ ነገር እንደሌለ ቀስ ብሎ ይጠቁማቸዋል እንጂ መች በመብረቅ ይቀጠቅጣቸዋል?

  አባታችን እግዚአብሔር ከኾነ በእኛ ዘንድ ያሉ ጠብና ክርክርን ከወዴት አመጣናቸው? በፍቅር ተነጋግሮ፣ በዕውቀት ተናንጾ፣ በትሕትና ተደጋግፎ መኖርስ ወዴት አሉ?

  • PM September 3, 2013 at 7:33 am Reply

   ZMTA እናመሰግናለን፤ በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው ያቀረቡት፡፡
   በእርግጥ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ ብዙ ሊቃውንት አሉን፤ ግን ስለ እውነት ለመመስከር ፈርተዋል፡፡
   እኔን የሚያሳዝነኝ ልጆቻችን ያልገባቸውን በጠየቁ ቁጥር እስከመቼ ድረስ ተሀድሶ/መናፍቃን እያልን እየሰደብናቸውና እያሳደድናቸው እንኖራለን ???
   ለተሃድሶ አቀንቃኞች ምላሹ ጠንካራ የሆነ፣ በስነ-ምግባር የታነጸ ትምህርት እንጂ ስድብ መልስ ሊሆን አይችልም፡፡
   ሐራ ዘተዋህዶ እባካችሁ እናንተም ተሃድሶ፣ መናፍቅ…..ወዘተ የሚል ቃል አትጠቀሙ፤…….ስለእነዚህ ሰዎች ጉዳይ ስትጽፉ ተጠራጣሪዎች፣ የጠፉት በጎች……ወዘተ እያላችሁ የፍቅር ቃላትን ብትጠቀሙ ይሻላል፡፡

  • ገ/ሚካኤል September 3, 2013 at 9:05 am Reply

   @ZMTA
   God bless you.This is intellectual thinking.
   May the Almighty blessed our beloved EOTC.
   G/mikael.

  • Anonymous September 4, 2013 at 2:22 pm Reply

   ይገርማል! እና መናፍቅነት ማለት ምን ማለት ነው? በትክክልም መናፍቅነት ማለት ያለወላዲት አምላክ ድህነት አለ ብሎ የሚል ትምህርትን ማስተማር ነው! በመጀመሪያ ደረጃ አልገባችሁ እነደሆነ ወላዲተ አምላክና ሌሎች ቅዱሳ፤ ቅዱሳን መላዕክትም ቢሆኑ በድህነት ጉዳይ ላይ ይለያያሉ፡፡ የብዙዎች ችግር መሠረታዊ ነገሮችን ካለመረዳት ከሆነ የወላዲተ አምላክ በድህነት ያላት ቦታ ዝም ብሎ የአማላጅነት ብቻም አይደለም፡፡ ጉዳዩ ከሚስጢረ ሥጋዌ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእርግጥም ያለ ወላዲተ አምላክ ድህነት የለም! የክርስቶስ ሥጋና ደም እኮ የእናቱ ነው እንጂ እሱ በመለኮታዊ ባሕሪው ስጋና ደም የለውም (አሁንም ማስተዋልን ይጠየቃል ጌታ ግን ሁሉም የእሱ ነው)፡፡ ሌላው ለመለኮት እናትነት ስትመረጥ በሰውኛ መስፈርተ አይደለም፡፡ አስቀድሞም ለዚህ የታሰበች የተፈጠረች ራሱ በማዳን ሂደት ውስጥ አንደ አካል እንድትሆን ሆና ነው እንጂ፡፡ ጥልቁን ሚስጢር መረዳት የሚቻለው በጉልበት ተንበርክኮ ሚስጢርን ሁሉ የሚገልጥ አምላክ በመጠየቅ እንጂ ይሄ የሆነው እንዲ ስለሆነ ነው እንዲህ ለመሆን እንዲህ መሆን አለበት በሚል ደፋር የስጋ ፍልስፍና አይደለም ፡፡ አስቀደሞ አዳም የፈለገውን አምላክነት (አምላክን ለመሆን ስለበላት ዕፅ) የቱንም ያህል የመከራ ራት ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን የፈለገውን ላይነሳው ነው የጌታ ሰው የመሆን ሚስጢር፡፡ አስቀድሞ አዳም ክፉንና ደጉን ያውቅ ዘንደ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለው ራሱ ጌታ ነው! አዎ በቃ ሰው እግዚአብሔርነትን ነው የተሰጠው! ይህ እግዚአብሔርነት ግን በእምነታችን ማነስና በስራችንም መክፋት አልተቻለንም፡፡ ለዚህ የበቃ ሕሊናን ለማስተናገድ የቻለች ግን እናቱ ድንግል ማሪያም ብቻ ነች፡፡ ያመነች ንፅሒት ናትና የእግዚአብሔር እናት ለመሆን በቅታለች! ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል ያለውም ለዚያ ነው! ምንም ነገር ቢሆን እግዚአበሔርን ከመውለድ በላይ የለም!! ያለ ድንግል ማርያም የመጣው “ኢየሱስ” ሀሰተኛው ነው፡፡ እውነተኛው ኢየሱስ በድንግል ማሪያም በኩል የመጣው ብቻ ነው! መዳን የሚቻለውም በድንግል ማርያም ልጅ፣ በእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ እናንተ በምትሉት ያለድንግል ማርያም በሆነው “ኢየሱስ” አይደለም፡፡ ሐሰተኛ “ኢየሱስ” አለ ወይ ካላችሁ ጌታ የተናገረውን አስተውሉ ሊያውም አንደ ሁለት ሳይሆን ብዙ “ኢየሱሶች” አሉ፡፡ በግልፅ “ኢየሱስ” ነኝ የሚሉትን በገዘፈ አካል የሚመጡትን አይደለም፡፡ እነሱስ ስለሚታዩ አይተናቸው እንወስናለን፡፡ ግን በስሙ ብቻ የተፈጠሩ ብዙ በአይን የማይታዩ “ኢየሱሶች” አሉ፡፡
   ታምረ ማርያምን በተመለከተ በጣም የማዝነው አለማስተዋላችንን ነው! ባለማወቅም ምክነያት በልቦናችንም ደንዳናነት ምክነያት ጠፍተናል፡፡ አለማመን መብቱ ነው ግን መንግስትን የመውረስ መብት ማንም አልተሰጠውም፡፡ ያ በልዑል አማላክ ውሳኔ የሚሆን ነው፡፡ እውነታው ግን ተዐምረ ማርያም ላይ ከተፃፈውም በላይ ዘሬም የምናየው ነው የሚፅፈው የለም እንጂ! ሲጀምር መቼ አመንና ነው ስለታምረ ማርያም የምናወራው! የኦርቶዶክስም ይሆን የሌላ ክርስቲያን ነኝ የሚል እስኪ ማን ነው ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራ ከዚህ ሂድ ብሎ ማፍረስ የሚችል እምነት ያለው፡፡ ለገዛ ሥጋችን ደዌ እነኳን ማመን እየተሳነን አይደል እንዴ የምንሰቃየው፡፡ ውሉ ጠፍቶብናል፡፡ ተዐምራት ለሁሉም ቅዱሳን ሊሆን የሚችል ክስተት ነው፡፡ የእግዚአበሔር እናትን ከመሆን በላይ ተዐምር ግን ሊኖር አይችልም!
   በመጨረሻ እንዲህ መሆን መብቱ ነው ይህንን አለመቀበል መብቱ ነው የሚባለው ጉዳዩ እኮ የዲሞክራሲ ጉዳይ አይደለም! ወደ አምላክ ዘንድ የምትወስደንን መንገድ ማወቅ ላይ እነጂ፡፡ ሌላ ጋር የተለማመድናቸውን ንግግሮች በእምነት ጉዳይ ላይ መፈላሰፍ አደጋው በገሀነም እሳትና በሕይወት መሀከል ያለውን ርቀት ነው፡፡ በአለማዊ አንኳን ከመብት በፊት የሚጠበቅ ነገር አለ፡፡ ሕግን ማወቅ! መጀመሪያ ግዴታን መብት የሚመጣው ከግዴታ በኋላ ነው፡፡ ማንም በይመስለኛል እንደፈለገ የሚያቦካው ነገር የለም! ለሁሉም ነገር ግን አንደ አስደንጋጭ የቅዱስ ጳውሎስ አባባል አለ፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን……….ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው! አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠን እንዴት ትክክለኛውን ማሰብ እንችላለን! አምላክ ሆይ ለማይረባ አእምሮ አሳልፈህ አትስጠን! አሜን!

  • annonymus September 4, 2013 at 2:39 pm Reply

   ይገርማል! እና መናፍቅነት ማለት ምን ማለት ነው? በትክክልም መናፍቅነት ማለት ያለወላዲት አምላክ ድህነት አለ ብሎ የሚል ትምህርትን ማስተማር ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እነደመጣ የማያምን ቢኖር እሱ መናፍቅ ነው! በመጀመሪያ ደረጃ አልገባችሁ እንደሆነ ወላዲተ አምላክና ሌሎች ቅዱሳን፤ ቅዱሳን መላዕክትም ቢሆኑ በድህነት ጉዳይ ላይ ይለያያሉ፡፡ የብዙዎች ችግር መሠረታዊ ነገሮችን ካለመረዳት ከሆነ ወላዲተ አምላክ በድህነት ያላት ቦታ ዝም ብሎ የአማላጅነት ብቻም አይደለም፡፡ ጉዳዩ ከሚስጢረ ሥጋዌ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእርግጥም ያለ ወላዲተ አምላክ ድህነት የለም! የክርስቶስ ሥጋና ደም እኮ የእናቱ ነው እንጂ እሱ በመለኮታዊ ባሕሪው ስጋና ደም የለውም (አሁንም ማስተዋልን ይጠየቃል ጌታ ግን ሁሉም የእሱ ነው)፡፡ ሌላው ለመለኮት እናትነት ስትመረጥ በሰውኛ መስፈርተ አይደለም፡፡ አስቀድሞም ለዚህ የታሰበች የተፈጠረች ራሱ በማዳን ሂደት ውስጥ አንድ አካል እንድትሆን ሰለፈቀደ ነው እንጂ፡፡ ጥልቁን ሚስጢር መረዳት የሚቻለው በጉልበት ተንበርክኮ ሚስጢርን ሁሉ የሚገልጥ አምላክ በመጠየቅ እንጂ ይሄ የሆነው እንዲህ ስለሆነ ነው እንዲህ ለመሆን እንዲህ መሆን አለበት በሚል ደፋር የስጋ ፍልስፍና አይደለም፡፡ አስቀደሞ አዳም የፈለገውን አምላክነት (አምላክን ለመሆን ስለበላት ዕፅ) የቱንም ያህል የመከራ ራት ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን የፈለገውን ላይነሳው ነው የጌታ ሰው የመሆን ሚስጢር፡፡ አስቀድሞ አዳም ክፉንና ደጉን ያውቅ ዘንደ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለው ራሱ ጌታ ነው! አዎ በቃ ሰው እግዚአብሔርነትን ነው የተሰጠው! ይህ እግዚአብሔርነት ግን በእምነታችን ማነስና በስራችንም መክፋት አልተቻለንም፡፡ ለዚህ የበቃ ሕሊናን ለማስተናገድ የቻለች ግን አንድ እናቱ ድንግል ማሪያም ብቻ ነች፡፡ ያመነች ንፅሒት ናትና የእግዚአብሔር እናት ለመሆን በቅታለች! ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል ያለውም ለዚያ ነው! ምንም ነገር ቢሆን እግዚአበሔርን ከመውለድ በላይ የለም!! ያለ ወላዲተ አምላክ የመጣው “ኢየሱስ” ሀሰተኛው ነው፡፡ እውነተኛው ኢየሱስ በድንግል ማሪያም በኩል የመጣው ብቻ ነው! መዳን የሚቻለውም በድንግል ማርያም ልጅ፣ በእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ እናንተ በምትሉት ያለድንግል ማርያም በሆነው “ኢየሱስ” አይደለም፡፡ ሐሰተኛ “ኢየሱስ” አለ ወይ ካላችሁ ጌታ የተናገረውን አስተውሉ ሊያውም አንድና ሁለት ሳይሆን ብዙ “ኢየሱሶች” አሉ፡፡ በግልፅ “ኢየሱስ” ነኝ የሚሉትን በገዘፈ አካል የሚመጡትን አይደለም፡፡ እነሱስ ስለሚታዩ አይተናቸው እንወስናለን፡፡ ግን በስሙ ብቻ የተፈጠሩ ብዙ በአይን የማይታዩ “ኢየሱሶች” አሉ፡፡
   ታምረ ማርያምን በተመለከተ በጣም የማዝነው አለማስተዋላችንን ነው! ባለማወቅም ምክነያት በልቦናችንም ደንዳናነት ምክነያት ጠፍተናል፡፡ አለማመን መብቱ ነው!? ግን መንግስትን የመውረስ መብት ማንም አልተሰጠውም፡፡ ያ በልዑል አማላክ ውሳኔ የሚሆን ነው፡፡ እውነታው ግን ተዐምረ ማርያም ላይ ከተፃፈውም በላይ ዘሬም የምናየው ነው የሚፅፈው የለም እንጂ! ሲጀምር መቼ አመንና ነው ስለታምረ ማርያም የምናወራው! የኦርቶዶክስም ይሆን የሌላ ክርስቲያን ነኝ የሚል እስኪ ማን ነው ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራ ከዚህ ሂድ ብሎ ማፍረስ የሚችል እምነት ያለው፡፡ ለገዛ ሥጋችን ደዌ እንኳን ማመን እየተሳነን አይደል እንዴ የምንሰቃየው፡፡ ውሉ ጠፍቶብናል፡፡ ተዐምራት ለሁሉም ቅዱሳን ሊሆን የሚችል ክስተት ነው፡፡ የእግዚአበሔር እናትን ከመሆን በላይ ተዐምር ግን ሊኖር አይችልም!
   በመጨረሻ እንዲህ መሆን መብቱ ነው ይህንን አለመቀበል መብቱ ነው የሚባለው ጉዳዩ እኮ የዲሞክራሲ ጉዳይ አይደለም! ወደ አምላክ ዘንድ የምትወስደንን መንገድ ማወቅ ላይ እነጂ፡፡ ሌላ ጋር የተለማመድናቸውን ንግግሮች በእምነት ጉዳይ ላይ መፈላሰፍ አደጋው በገሀነም እሳትና በሕይወት መሀከል ያለውን ርቀት ነው፡፡ በአለማዊ እንኳን ከመብት በፊት የሚጠበቅ ነገር አለ፡፡ ሕግን ማወቅ! ከዚያ ግዴታን ማወቅ፣ መብት የሚመጣው ከግዴታ በኋላ ነው፡፡ ማንም በይመስለኛል እንደፈለገ የሚያቦካው ነገር የለም! ለሁሉም ነገር ግን አንድ አስደንጋጭ የቅዱስ ጳውሎስ አባባል አለ፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን……….ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው! አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠን እንዴት ትክክለኛውን ማሰብ እንችላለን! አምላክ ሆይ ለማይረባ አእምሮ አሳልፈህ አትስጠን! አሜን!

  • annonymus September 5, 2013 at 5:58 am Reply

   What does this mean? እንድንበት ዘንድ የሚገባው ከሰማይ በታች የተሰጠ ስም ከኢየሱስ በስተቀር ሌላ ማንም የለም፡፡” “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚወጣ የለም፡፡” ሲል እስልምና ግን “በነቢያት፣ በቅዱሳን ጸሎት እንድናለን፡፡” ስለሚል ነው፡፡First of all go and learn language, then learn historical backgrounds of events, then acquire deep analytical then knee down and pray after getting the power from God try to say it out. Beqidusan amalaginet medan malet kekiristos wuchi yehone dihinet new? It is true no salivation without Jesus Christos! It is true too there is salivation through His saints! because He is in them! The one who is asking their help knows well who the King. Amalagi malet eko melemen malet new. Lik Abreham sile sodom ager tifat endelemnew, Muse sile Israel endelmenw, lelochim bizuwoch endaderegut. Yemigeremew zarem eko midire findata saiker litseliyilih litseliyilish yilal. Min malet new? End akimiti eko egziabiherin lamaldih new? So how come a proved God’s Saints can’t pray for us! Degimo enesu eko motewal litilim yihonal. Ewunataw yemotikew ensun motwal bileh yemitaminew neh. Sile demenefis bicha yemitasib, Ye Egziabiher estinfas yehonechiwun zelalmawit nefis yekadih! bedemawit nebsu manim maninim liamalid aychilim. demawit behonech nefsachin sewoch keleloch ensesate yetelyene aydelenim. Thence know that there are two life in a human being. The eternal soul and flesh life. The fleshy does but the eternal one will never die. But its destination for the good will be to paradise thence heaven for evils in hell thence eternal fire. That is the difference
   The other thing most of the christian say we believe only as per the bible only. But they have little knowledge about the bible and even what bible means. First the book ‘Bible’ is not as we see single book it is a compilation of many books written by different people in different time. The bible we have in hand now was first compiled as it appear here in era of Konstantine which was 300 years or more after Jesus Christos walked with us. Yet there were a lot of books left behind but that might have been part of the bible. Most people again try to stop the history of God’s work at the time of Jesus walked with us back 2000 years ago. But surprising that they did not realize that they are denying His works after that time. As a result they don’t want to accept books written after new testaments! How come Christianity has been there all along this periods but where is so evidence in books. Books written by different saints all through this periods too are bible. From the time of Adam to Christos was more or less documented but what about from the time of Christos to here? Kastwalin Metsahife Qidus yemilew qal lebiluy kidanina tiqit yeadis qidan tarikochin yeyazewe bicha ayidlem. Bizu qidusan metsahift kekiristos eskezare dires alu wedfitim yitsafalu. Lengeru ‘Metsahife Qidus’ yetebalewn metsahif enkuan mechi bewgu geban!

 2. peteros September 2, 2013 at 9:39 pm Reply

  ‹‹የዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ሸክም ነው››፤ ‹‹በቀጥታ ኢየሱስን እንጂ የምን ዙርያ ጥምጥም እንሄዳለን››፤ ‹‹ኦርቶዶክስ ባለሥልጣን እንጂ ሊቅ የላትም›› ማለታቸውን በአብነት ይጠቅሳሉ፡፡ yes, they right. My grand father his name is Ato Redi Geberwold built this church back in the day for the gospel, as my mother told me he was eager to see an Orthodox church in Diredawa keep the followers from visiting the Catholic church.

 3. ABCD September 3, 2013 at 8:16 am Reply

  Do you remember those two guys walking from Jerusalem to Emahuse , they were talking what had happened in Jerusalem. And our Lord Jesus Christ ask them what they were talking, but they were surprised and asked him whether he is from Jerusalem or not. What makes them surprised was that every thing they saw on him was a person from Jerusalem. His wearing, speaking and walking looks like a person from Jerusalem. But he did not seem he knows what happened in the city. After this preamble he told them what was written on the holy books about the event, this burns there heart and make them listeners. ZMTA what I see from your article is that you only know what the guys know at first. Because you did not start the journey you could not meet him. Every body in Jerusalem /the world / knows the name Jesus , but most of them did not know him. Saying his name could not make any body a follower of him it is only when you have what the holy books says about him and his works. Besides it is when you are back with thought to the mother church that you can say I have met him. As I see you are out of Jerusalem with out knowing what the holy books said to preach about him, that is why you did not still met him. But the guys were not out to preach, instead they were desperate , but they had had love for him. Any ways you need persons to know what the bible says about salivation and belief. Saying his name by it self is not the only sign for believe, most of the world knows that. What the world lacks is what it is and what it deserves.

  SAYING THE WORD JESUS ONLY MAKES A MAN A PERSON FROM JERUSALEM ONLY. WHAT MAKES A PERSON FROM ABOVE IS KNOWING HIM.

  • ZMTA September 4, 2013 at 8:48 am Reply

   Dear ABCD,

   Thank you for reading my comment. However I have some questions for you.

   First, can you please clarify your point?
   Second, what makes you sure that my arguments are not biblical?
   Third, you said, “you need persons to know what the bible says about salivation and belief.”
   I would really appreciate if you could tell me what Salvation means. Moreover, I want you to tell me where my argument went wrong or against Christianity.

   Additional questions:

   Do you think Zara’a Ya’qob was right in all what he did?

   Do you think there is nothing wrong with EOTC?

   Thank you,

 4. Anonymous September 3, 2013 at 1:58 pm Reply

  ለባ መናፈቅ ሁላ !መናፈቅ መናፈቅ መባል አለበት እንጂ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም መነገድ የለበትም በርግጥ እነዚህ “ሃሳቦችየዐጤ ዘርዐ ያዕቆብ ሸክም ነው››፤ ‹‹በቀጥታ ኢየሱስን እንጂ የምን ዙርያ ጥምጥም እንሄዳለን” የምንፍቅና መነሻ ሳይሆኑ ለዘመናት ውስጣቸው ተደበቆ የኖረ ነገር ግን ግዜ የደረሰ (ቤተክርስቲያንን የመናፈቃን ለማድረግ)መስሏቸው ነው የተናገሩት ::ሰዎቹ መናፍቅ ለመሆናቸው እንጂ ላለመሆናቸው ማስረጃ አልቀረበም ::ስለዚህ ህዝበ ክርስቲያኑን ሲያወናበዱት ሰበካ ጉባዬው የወሰደው እርምጃ ትክክል ነው ::ከላይ አስተያየት የሰጣቸሁ ብዙዎቻችሁ መናፈቃን ወይም በነሱ ቅዥት የተጠለፋችሁ (ምን አልባት ሳይገባችሁ ይህንንም እጠራጠራለሁ ታስቦበት ) ስለሆናችሁ በሃይማኖታችን እየገባችሁ ከመታውቁን እዛው የሰይጣን አዳራሻችሁ ሄዳችሁ ጩሁ ::

  • ገ/ሚካኤል September 4, 2013 at 5:28 am Reply

   Anonymous September 3, 2013 at 1:58 pm
   am sorry u said nothing but insulting.
   Do you have any evidence about the heresy of these guys.

  • ሚሚ September 4, 2013 at 6:28 am Reply

   ወንድማችን ለአንተ ቤተክርስቲያን ማለት ጣራ እና ግድግዳ ነው፡፡ ለእኛ ግን ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ስብስብ ናት (ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ ብትሰበሰቡ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ)፡፡ ስለዚህ በጎችን ለመሳደብና ለማባረር አትቾክል፤ ማን ያውቃል ከመካከላቸው ተጸጽተው የሚመለሱ ይኖሩ ይሆናል፡፡

 5. Anonymous September 3, 2013 at 2:51 pm Reply

  ሃገረ ስብከቱ እድር መሰለው እንዴ?በነገራችን ላይ የሃገረ ስብከቱ ፅ/ቤትም በመናፈቃን ላለመጠለፉ ማረጋገጫ የለም ስለመሆኑ እንጅ

 6. ሚሚ September 4, 2013 at 6:27 am Reply

  ወንድማችን ለአንተ ቤተክርስቲያን ማለት ጣራ እና ግድግዳ ነው፡፡ ለእኛ ግን ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ስብስብ ናት (ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ ብትሰበሰቡ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ)፡፡ ስለዚህ በጎችን ለመሳደብና ለማባረር አትቾክል፤ ማን ያውቃል ከመካከላቸው ተጸጽተው የሚመለሱ ይኖሩ ይሆናል፡፡

 7. annonymus September 4, 2013 at 2:38 pm Reply

  ይገርማል! እና መናፍቅነት ማለት ምን ማለት ነው? በትክክልም መናፍቅነት ማለት ያለወላዲት አምላክ ድህነት አለ ብሎ የሚል ትምህርትን ማስተማር ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እነደመጣ የማያምን ቢኖር እሱ መናፍቅ ነው! በመጀመሪያ ደረጃ አልገባችሁ እንደሆነ ወላዲተ አምላክና ሌሎች ቅዱሳን፤ ቅዱሳን መላዕክትም ቢሆኑ በድህነት ጉዳይ ላይ ይለያያሉ፡፡ የብዙዎች ችግር መሠረታዊ ነገሮችን ካለመረዳት ከሆነ ወላዲተ አምላክ በድህነት ያላት ቦታ ዝም ብሎ የአማላጅነት ብቻም አይደለም፡፡ ጉዳዩ ከሚስጢረ ሥጋዌ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በእርግጥም ያለ ወላዲተ አምላክ ድህነት የለም! የክርስቶስ ሥጋና ደም እኮ የእናቱ ነው እንጂ እሱ በመለኮታዊ ባሕሪው ስጋና ደም የለውም (አሁንም ማስተዋልን ይጠየቃል ጌታ ግን ሁሉም የእሱ ነው)፡፡ ሌላው ለመለኮት እናትነት ስትመረጥ በሰውኛ መስፈርተ አይደለም፡፡ አስቀድሞም ለዚህ የታሰበች የተፈጠረች ራሱ በማዳን ሂደት ውስጥ አንድ አካል እንድትሆን ሰለፈቀደ ነው እንጂ፡፡ ጥልቁን ሚስጢር መረዳት የሚቻለው በጉልበት ተንበርክኮ ሚስጢርን ሁሉ የሚገልጥ አምላክ በመጠየቅ እንጂ ይሄ የሆነው እንዲህ ስለሆነ ነው እንዲህ ለመሆን እንዲህ መሆን አለበት በሚል ደፋር የስጋ ፍልስፍና አይደለም፡፡ አስቀደሞ አዳም የፈለገውን አምላክነት (አምላክን ለመሆን ስለበላት ዕፅ) የቱንም ያህል የመከራ ራት ቢሆንም የኋላ ኋላ ግን የፈለገውን ላይነሳው ነው የጌታ ሰው የመሆን ሚስጢር፡፡ አስቀድሞ አዳም ክፉንና ደጉን ያውቅ ዘንደ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለው ራሱ ጌታ ነው! አዎ በቃ ሰው እግዚአብሔርነትን ነው የተሰጠው! ይህ እግዚአብሔርነት ግን በእምነታችን ማነስና በስራችንም መክፋት አልተቻለንም፡፡ ለዚህ የበቃ ሕሊናን ለማስተናገድ የቻለች ግን አንድ እናቱ ድንግል ማሪያም ብቻ ነች፡፡ ያመነች ንፅሒት ናትና የእግዚአብሔር እናት ለመሆን በቅታለች! ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል ያለውም ለዚያ ነው! ምንም ነገር ቢሆን እግዚአበሔርን ከመውለድ በላይ የለም!! ያለ ወላዲተ አምላክ የመጣው “ኢየሱስ” ሀሰተኛው ነው፡፡ እውነተኛው ኢየሱስ በድንግል ማሪያም በኩል የመጣው ብቻ ነው! መዳን የሚቻለውም በድንግል ማርያም ልጅ፣ በእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ እናንተ በምትሉት ያለድንግል ማርያም በሆነው “ኢየሱስ” አይደለም፡፡ ሐሰተኛ “ኢየሱስ” አለ ወይ ካላችሁ ጌታ የተናገረውን አስተውሉ ሊያውም አንድና ሁለት ሳይሆን ብዙ “ኢየሱሶች” አሉ፡፡ በግልፅ “ኢየሱስ” ነኝ የሚሉትን በገዘፈ አካል የሚመጡትን አይደለም፡፡ እነሱስ ስለሚታዩ አይተናቸው እንወስናለን፡፡ ግን በስሙ ብቻ የተፈጠሩ ብዙ በአይን የማይታዩ “ኢየሱሶች” አሉ፡፡
  ታምረ ማርያምን በተመለከተ በጣም የማዝነው አለማስተዋላችንን ነው! ባለማወቅም ምክነያት በልቦናችንም ደንዳናነት ምክነያት ጠፍተናል፡፡ አለማመን መብቱ ነው!? ግን መንግስትን የመውረስ መብት ማንም አልተሰጠውም፡፡ ያ በልዑል አማላክ ውሳኔ የሚሆን ነው፡፡ እውነታው ግን ተዐምረ ማርያም ላይ ከተፃፈውም በላይ ዘሬም የምናየው ነው የሚፅፈው የለም እንጂ! ሲጀምር መቼ አመንና ነው ስለታምረ ማርያም የምናወራው! የኦርቶዶክስም ይሆን የሌላ ክርስቲያን ነኝ የሚል እስኪ ማን ነው ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራ ከዚህ ሂድ ብሎ ማፍረስ የሚችል እምነት ያለው፡፡ ለገዛ ሥጋችን ደዌ እንኳን ማመን እየተሳነን አይደል እንዴ የምንሰቃየው፡፡ ውሉ ጠፍቶብናል፡፡ ተዐምራት ለሁሉም ቅዱሳን ሊሆን የሚችል ክስተት ነው፡፡ የእግዚአበሔር እናትን ከመሆን በላይ ተዐምር ግን ሊኖር አይችልም!
  በመጨረሻ እንዲህ መሆን መብቱ ነው ይህንን አለመቀበል መብቱ ነው የሚባለው ጉዳዩ እኮ የዲሞክራሲ ጉዳይ አይደለም! ወደ አምላክ ዘንድ የምትወስደንን መንገድ ማወቅ ላይ እነጂ፡፡ ሌላ ጋር የተለማመድናቸውን ንግግሮች በእምነት ጉዳይ ላይ መፈላሰፍ አደጋው በገሀነም እሳትና በሕይወት መሀከል ያለውን ርቀት ነው፡፡ በአለማዊ እንኳን ከመብት በፊት የሚጠበቅ ነገር አለ፡፡ ሕግን ማወቅ! ከዚያ ግዴታን ማወቅ፣ መብት የሚመጣው ከግዴታ በኋላ ነው፡፡ ማንም በይመስለኛል እንደፈለገ የሚያቦካው ነገር የለም! ለሁሉም ነገር ግን አንድ አስደንጋጭ የቅዱስ ጳውሎስ አባባል አለ፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን……….ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው! አንዴ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠን እንዴት ትክክለኛውን ማሰብ እንችላለን! አምላክ ሆይ ለማይረባ አእምሮ አሳልፈህ አትስጠን! አሜን!

 8. ababa September 5, 2013 at 8:13 am Reply

  betame yegeremal

 9. ababa September 5, 2013 at 8:37 am Reply

  እባካችሁ አንድን ፅሁህፍ ስታቀርቡ እውነት መሆኑን ለማስረዳት ትክክለኛ ማስረጃ አቅርቡ ያለምንም ማስረጃ የልጆቹን ስም አታጥፉ በእርግጥ ሰ/ት/ቤቱ በድሬዳዋ ውስጥ ካሉ ሰንበት ት/ቤቶች የተሸለ መሆኑ ይታወቃል ምን አልባት ማህበሩን ማለትም ማህበረ ቅዱሳንን ባለመደገፉ ሊጠላ ይችል ይሆናል ግን እንዲህ አይነቱን ወሬ ለእናንተ የሚያቀብሉት በሀገረ ስብከት ውስጥ ተቀጥረው የተቀጠሩበትን አላማ እረስተው ወሬ በማቀበል ላይ የተሰማሩ የማህበሩ አቀንቃኞች መሆኛቸው ይታወቃል ለማንኛውም እውነቱን ከጉዳዩ ባለቤቶች ብናጣራ የተሻለ ነው፡፡

 10. ababa September 9, 2013 at 5:42 am Reply

  በእጅ አዙር የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር መቆጣጠር የሚፈልገዉ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ጥርቅሙ ማህበረ ቅዱሳን በአሰበ ተፈሪ ድብቅ ሴራዉ ሲጋለጠ ደግሞ ወደ ድሬዳዋ ፊቱን ማዞሩ ይታወቃል ስለሆነም አንድም እውነታ የሌለው ወሬ ብቻ የሀነ ስለሆነ ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ ክርስቲያኖች ምንም አይነት መረበሽ እንዳይሰማችሁ ይህ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ጥርቅሙ ማህበረ ቅዱሳን ወሬ ስለሆነ፡፡

  • Anonymous September 9, 2013 at 2:08 pm Reply

   አስመሳይ መናፍቅ

   • Anonymous September 11, 2013 at 12:13 am

    To ZMTA
    All your writing is what protestants and tehadisos have been saying for a long time. From your writing I am 100% sure you are a protestant (= tehadisos)! So it is no wonder when you post anti-Orthodox. It will not be long before we clean our Holy Church the protestant heritics. You go to your dirty protestant church. You son of a devil. You wolde- Luther, wolde Bonkie. You would rather love Bonkie’s filthy teachings than our holy father’s!

 11. maru September 11, 2013 at 12:32 am Reply

  To ZMTA YOU dirty protestant get out of our holy church.

 12. maru September 11, 2013 at 1:10 am Reply

  ZMTA
  All your writings clearly point to the fact that you are a protestant(= tehadisos)! You would rather believe the fictional stories of Bonkie and Luther than our holy books. Take your hands off our Holy Church in general and our Eternal, Holy , Virgin , Mother of God. You would rather go to your dirty and satanic protestant ‘church’. You are trying to make closer our holy church to protestant teaching. Let me ask u this. Which angel told u that protestantism is the true faith? The world knows what protestantism looks like currently in the western world where it was born out of Luther’s mind. Your intention is to take the the Ethiopian holy church towards that stupidity. So do not disguise yourself as an Orthodox. We know you. We do not allow protestants reside in OUR CHURCH.

  • ZMTA September 12, 2013 at 11:59 am Reply

   Dear Maru,

   Which of my points are out of what our early church fathers taught?
   Don’t you think that Christians are one, despite their doctrinal differences, in Christ? Read, (Jn. 17: 20-23). That tells you how much our Lord wants us to be one, despite our pride and misunderstandings. I wonder if you have ever read anything written by another denomination. In addition, it is Jesus who saves, not Peter, or Paul, or Apolos. Only Jesus and no one else. A Church can call itself Orthodox while it has deviated from what our forefathers taught. But just because she calls herself that she will not be truly. A Church may call itself a Church of Christ while she has no time in defending the poor and the oppressed. (Remember what happened after 2005 election. History will remember what the EOTC press release was. The protestant churches also were totally silent. Everyone speaks righteous at the time of peace. Except the Catholic Church bishops not a single Church, as of my knowledge, stood with Christ who is always against bloodshed and oppression.)

   I am Christian.

   If believing in Christ is wrong, I don’t want to be right.

 13. AAA September 17, 2013 at 11:58 am Reply

  እናንተ ይሁዳዊያን ለመሆኑ መቼ ነው ስለገንዘብ መሰብሰብ ማሰብ የምታቆሙት ይህን ሁሉ የሚያስቀባጥራችሁ ሰው ባልዋለበት የምታውሉት እውነት የቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው? ወይስ እንደ ይሁዳ ቅ/ሚ/ቤ/ክ ብትቆጣጠሩት የምታገኙት ብር ስለቆጫችሁ ነው ትዝ ይላችኋል ይሁዳ ያንን ሽቶ ሸጦ የሚደርሰውን ብር አስቦ ተሸጦ ለድሆች ይካፈል ሲል 30 ብር ከሽያጩ ላይ እንደሚደርሰው ስላሰበ ነው ለድሆች እንዳሰበላቸው ሆኖ የተናገረው ማቅም እንዲሁ ነው እያደረገ ያለው ከዚህ ደብር ምንም አላስቀምስ ቢሏችሁ ይህን ሁሉ ያልተደረገ ተደረገ በማለት ቤ/ክርስቲያኑን ማመስ ጀመራችሁ አይ መመሳሰል በውነት በዚያ ዘመን የነበሩ ፈሪሳውያንንና ሰዱቃውያንን በመ/ቅዱስ እንዳነበብኩት ዛሬም የነሱን ስራ የሚሰሩ ማቆችን በማየቴ የመጨረሻው ዘመን አሁን እንደሆ ተረዳሁ እባካችሁ ከነሱ ተማሩ ማቆች ክርስቶስን በማሳደድ ምንም አላተረፉም ፍርድ እንጂ እናንተም የክርስቶስ ቤት የሆነውን የሰውን ልጅ /ታዳጊዎችን/ አታሳዱ ይብቃችሁ በቀረቻችሁ ጊዜ ንሰኃ ገብታችሁ የመንግስቱ ወራሾች ለመሆን ተዘጋጁ

 14. ababa September 18, 2013 at 7:15 am Reply

  kale hiwote yesema

 15. ababa September 18, 2013 at 7:21 am Reply

  እባካችሁ አንድን ፅሁህፍ ስታቀርቡ እውነት መሆኑን ለማስረዳት ትክክለኛ ማስረጃ አቅርቡ ያለምንም ማስረጃ የልጆቹን ስም አታጥፉ በእርግጥ ሰ/ት/ቤቱ በድሬዳዋ ውስጥ ካሉ ሰንበት ት/ቤቶች የተሸለ መሆኑ ይታወቃል ምን አልባት ማህበሩን ማለትም ማህበረ ቅዱሳንን ባለመደገፉ ሊጠላ ይችል ይሆናል ግን እንዲህ አይነቱን ወሬ ለእናንተ የሚያቀብሉት በሀገረ ስብከት ውስጥ ተቀጥረው የተቀጠሩበትን አላማ እረስተው አእምሮአቸውን ለገንዘብ ድቃቂና ለቸርቅ እላቂ አሳልፈው የሰጡ ክህነታቸውን ለሴት ማባለጊያነት የሚጠቀሙ ወሬ በማቀበል ላይ የተሰማሩ የማህበሩ አቀንቃኞች መሆኛቸው ይታወቃል ለማንኛውም እውነቱን ከጉዳዩ ባለቤቶች ብናጣራ የተሻለ ነው፡፡

 16. አባ ገብረ ማርያም ወልደሳሙኤል September 19, 2013 at 7:11 am Reply

  በነገራችን ላይ መናፍቅ ማለት ምን ማለት ነው? ያልገባውን የሚጠይቅ ነው በጣም ይገርማል ስለ እውነት ይምንኖር ከሆነ ለማንም ሳናደላ እንናገር ለእኔ ግን መናፍቅ ማለት ያልገባውን የሚጠይቅ ሳይሆን የአምልኮ መልክ ኖሮት ግን የእግሂአብሔርን ሀይል የካደ ነው; ቤ/ክ የሰጠችውን ሐላፊነት በአግባቡ የማይወጣ ነው; መንጋውን የሚበትን ነው ስለዚህ የመፅሐፍ መምህር ሰባኬ ወንጌል ተብሎ ተሰይሞ ድንገት ለሚነሱ ጉንጭ አልፋ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ያልቻለ መምህርም ሆነ ሰባኪ ምኑን መምህር ምኑን ሰባኪ ሆነ እውነት በድ/ዳ ሚካኤል ቤ/ክ የታየው ምንፍቅና ነው ውይስ የእውቀት መበላለጥ እንጃ ብቻ እግዚአብሔር እውነቱን በጊዜው ይግለጥ፡፡

 17. Anonymous July 7, 2014 at 4:49 pm Reply

  maryamen ymtamelku menafkan nachu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: