ቅ/ሲኖዶስ እና ፓትርያሪኩ የአቡነ ያዕቆብ የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት አስተዳደር እያስከተለ ለሚገኘው ጉዳት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ተጠየቀ

 • ለወራት በአ/አ የተቀመጡት ሊቀ ጳጳሱ ትላንት ምሽት ወደ ደ/አፍሪካ ተጉዘዋል
 • በሊቀ ጳጳሱ አስተዳደር የተማረሩና አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ አቤቱታዎች ለውጭ ግንኙነት መምሪያውና ለፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እየጎረፉ ነው
His Grace Abune Yacob, Archbishop of All African Diosces00

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ
የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ከዚህ በታች የምናቀርበውና ‹‹የአቡነ ያዕቆብ ሲሞናዊነት[ስምዖናዊነት] ሲገለጥ›› በሚል ርእስ የተጠናቀረው መልእክት የደረሰን በኬንያ – ናይሮቢ ከሚገኙ ምእመናን ነው፡፡ መልእክቱ÷ የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከትን የተመለከተ ዘገባ በጡመራ መድረኩ ለንባብ ከበቃበት ጊዜ ጀምሮ ከሚደርሱን በርካታ አስተያየቶች መካከል ለማለዘብ የተገደድናቸውንና በተለይ ሊቀ ጳጳሱን የሚመለከቱ ግልጽ የወጡ መረጃዎችንና ትችቶችን መልሰን እንድናጤናቸው፣ ደጋግመን እንድናጣራቸው አግዞናል፡፡

መልእክቱን መሠረት ያደረጉ ዋና ዋና ነጥቦችን በቅድሚያ ያስቀመጥን ሲኾን ምእመናኑ ከናይሮቢ ያደረሱን መልእክትም መጠነኛ ማለዘቢያ ተደርጎበት ተያይዞ ቀርቧል፡፡ ቁም ነገሩ÷ በቀደሙት ዘገባዎቻችን እንዳመለከትነው፣ ቤተ ክርስቲያናችን በብዙ በምትጠበቅበት የአፍሪቃ አህጉር ሐዋርያዊ ተልእኮዋ በምን ደረጃ እየተፈጸመ እንዳለ ለማሳየትና ከዚያም በመነሣት ለችግሮቹ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ፣ ለተግዳሮቱም የሚመጥን የአገልግሎት ዝግጁነት እንዲኖር ለማትጋት ነው፡

ዐበይት የትኩረት ነጥቦች

 • የማጥመቅ ሥርዐታቸውና የሚታሙበት ጥንቆላ ለምእመናን እምነት፣ ጤንነትና ማኅበራዊ ኑሮ ፈተና ኾኗል፤ ይህን የሚቃወሙ ካህናትም በደል ይፈጸምባቸዋል፡፡
 • በአብያተ ክርስቲያን ቅጽር ማረፊያ ቤት እያለ በቀን 150 የአሜሪካን ዶላር የሚከፈልበትን ‹ገስት ሃውስ› እና የግለሰብ ቤት ለማረፊያነት መምረጣቸው ከአዋኪው የማጥመቅ ሥርዐታቸውና ከሚታሙበት የጥንቆላ ተግባር ጋራ ተያይዞ ለከፋ ሐሜትና ትችት ዳርጓቸዋል
 • አዲስ አገልጋዮችን በመቅጠር አመካኝተው ገንዘብ ለመቀበል ሲሉ በአገልግሎት ላይ ያሉ ካህናት አገልግሎታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ይገፋፋሉ፤ የሚቃወሟቸውን ካህናት ከምእመናን ያጋጫሉ፤ ምእመናንን በካህናት ላይ ያነሣሣሉ፡፡
 • የውጭ ግንኙነት ጽ/ቤት ሳያውቀው በጎጠኝነትና ጥቅመኝነት ላይ ተመሥርተው ለሚፈጽሙት ቅጥር በአዲስ አበባ በደላላነት የሚያገለግሏቸው ቀሲስ ግሩም ታዬ ናቸው፡፡

*            *            *

 • በዑጋንዳ፣ ታንዛንያና ሌሎችም የአህጉሪቱ ክፍሎች አብያተ ክርስቲያን እንዲስፋፉ ለሚማፀኑ በጎ አድራጊ ምእመናን ቀናና አፋጣኝ ምላሽ አይሰጡም፤ ይልቁንም የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳደርን በመጋፋት ያለገደብ በሚጠይቁት የገንዘብ ወጪ አድባራቱን ለብኩንነት እየዳረጉ ማደኽየታቸው በፈጠረው ምሬት ከአንድነት መዋቅር የመለየት ስጋት የተጋረጠባቸው ነባር አድባራት አሉ፡፡
 • ይህ ምሬትና ስጋት ከተጋረጠባቸው አድባራት አንዱ የናይሮቢ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የደብሩን ይዞታ ንብረቷ ያደረገችው በሦስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አስተዳደር ወቅት ነው፡፡ የባዕለጸጎች መኖርያ ነው በሚባለው የከተማዪቱ ዕንብርት የሚገኘው ደብሩ ሁለት ዐበይት ችግሮች ተጋርጠውበታል፡፡
 • አንደኛው÷ የልማት ዕቅዶች ጅምር ቢኖሩትም ሊቀ ጳጳሱ በመስተንግዶና መጓጓዣ ስም የሚጠይቁት ያልተገባ ወጪ ፋይናንሳዊ አቅሙን እየተፈታተነው መኾኑ ነው፡፡ የኮፕት ቤተ ክርስቲያንና ካቶሊኮች ታላላቅ ገዳማትን በመመሥረት፣ ሆስፒታሎችንና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማትን በማስፋፋት የሚያካሂዱት ልማት መንፈሳዊ ቅንዐት የማይፈጥርባቸው ሊቀ ጳጳሱ የቀደሙት ሊቃነ ጳጳሳት (ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ) የፈጸሟቸውን ሐዋርያዊ ክንውኖች እንኳ ለማስጠበቅ ተነሣሽነቱም ብቃቱም የላቸውም፡፡
 • ሁለተኛው÷ ሊቀ ጳጳሱ በርቱዐ ሃይማኖት እና በሞያ ብቃት ሳይኾን በጎጥና ጥቅመኝነት ላይ ተመሥርተው በሚያካሂዱት ቅጥር አንድ ቀሳጢ ‹መነኩሴ› በቀዳሽነት ለማስቀጠር ከደብሩ አስተዳደር ጋራ ውዝግብ መፍጠራቸው ነው፡፡ በውጭ ግንኙነት ጽ/ቤትና በፓትርያሪኩ ዕውቅና የተላኩት ካህን በግፍ ቦታውን ጥለው እንዲሰደዱ ካደረጉ በኋላ ሊቀ ጳጳሱ በግል ውሳኔያቸው ሊያስቀጥሩት የነበረው ይህ የሃይማኖት ቀሳጢ ማንነቱ በማስረጃ ተጋልጦ ቅጥሩ ቢከሽፍም ሊቀ ጳጳሱን ተስፋ አድርጎ በዚያው የሚገኝ በመኾኑ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ስጋት ፈጥሯል፡፡ ውዝግቡ፣ በለቀቁት ባለሞያ ካህን ቦታ ተተኪ እንዳይቀጠርና ባሉት ጥቂት አገልጋዮች ላይ ጫና እንዲፈጠር አድርጓል፡፡

*            *            *

 • መላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ያላቸውን የምክትል ፕሬዝዳንትነት ሓላፊነት በአግባቡ እየተወጡ አይደለም፡፡ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባዎች መንፈሴ አላዘዘኝም እያሉ በተለያዩ ሰበቦች እንደሚቀሩት ሁሉ፣ መሳተፍ የሚገባቸውን የምክር ቤቱን ስብሰባዎችም ኾነ ብለው በማስተጓጎላቸው በአህጉር ደረጃ የተወከሉበትን የቤተ ክርስቲያናችንን ሚና ከሌሎች አብያተ እምነት መሪዎች ሚና አሳንሰዋል፡፡
 • ‹‹ለመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ርዳታ መስጠት››፣ ‹‹በደቡብ አፍሪካና በኢትዮጵያ የማሳድጋቸው ሕፃናት አሉ›› በሚሉ ሰበቦች መጠኑ ያልታወቀ የበጎ አድራጊ ምእመናንን ገንዘብ ለግላቸው አካብተዋል፡፡ ለዚህ ዓላማ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሠሩ ኢትዮጵያውያን ስታፎችንና ባዕለጸጋ ነጋድያንን በጥቅመኝነት በቀጠሯቸው አገልጋዮች ደላላነት ዒላማ አድርገዋቸዋል፡፡
 • ‹‹ኤርትራዊ ነኝ›› በሚል ከኤርትራውያን ምእመናን ገንዘብ ለግላቸው ይሰበስባሉ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ÷ ኤርትራዊ ተወላጅ ሲያገኙ ኤርትራዊ ነኝ፤ የኢሕአዴግ ደጋፊ ሲያገኙ ኢሕአዴግ ነኝ በሚል ጥቅም የሚያጋብሱበትን ኹኔታ በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትኩረት እየተከታተለው መኾኑ ተጠቁሟል፡፡

*            *          *

የአቡነ ያዕቆብ ስምዖናዊነት ሲጋለጥ

(ከናይሮቢ ምእመናን)

1)  ከአሜሪካ በዕፅ ማዘዋወርና መሰል ችግሮች ዲፖርት የተደረገን አንድ ወጣት ለስሙ ዲያቆን ብለው ሠይመው፣ ቤት ተከራይተው ለነውረኛ ተግባር እንደሚጠቀሙበት ይጠረጠራሉ፡፡

2)  በደብሩ ውስጥ ለአባቶች የሚኾን ማረፊያ ቤት እያለ በቀን 150 የአሜሪካን ዶላር ለኪራይ የሚከፈልበትን የእንግዳ ማረፊያ(ገስት ሃውስ) እንዲከፍሉላቸው በማድረግ የዋህ ምእመናን በዝብዘዋል፡፡

3)  በጣም የሚያሳዝነው በማጥመቅ ስም የሚፈጽሙት የጠንቋይነት ተግባራቸው ነው፡፡

 • ይኸውም የዋህ ምእመናን ኪራዩን በሚከፍሉላቸው ገስት ሃውስ ምእመናንን በተለይም ባለትዳር ሴቶችን በመጥራት ‹‹ባልሽ ሌላ ሴት ዘንድ ይሄዳል፤ እግዚአብሔር ነግሮኛል፤ የኾነ ነገር አይቼልሻለኹ›› በማለት ባለትዳር ሴቶችን ከባሎቻቸው በማጣላትና ከትዳራቸው በማፋታት ይታወቃሉ፡፡
 • በሚያጠምቁበት ወቅት የኬሚካል መርጫ ዕቃ በመጠቀም፣ ውኃ በመሙላት ወደተጠማቂው ሰውዬ ጉረሮ እና ዐይን በቀጥታ በመርጨትና በማጨናነቅ እንዲጮኽ ያደርጉታል፡፡ በእውነትና በእምነት ለቀረቡቱ በሚያድነው ጠበል ለመፈውስ ሽቶ የመጣው ሕመምተኛም ለተጨማሪ ችግር ይዳረጋል፡፡
 • ሲያጠምቁም የሚጠሩት ስመ እግዚአብሔርን አይደለም፡፡ የሚጠሯቸው ስሞች÷ ወሰን ጋላ፣ አዳል ሞቲ፣ ጠቋር፣ ከዘር የተላለፈ ሰይጣንና ምቀኛ ጎረቤት መድኃኒት ቀብሮብኻል ወዘተ የሚሉ ናቸው፡፡ እንደ ዲዲቲ መርጫ ባለ መሣርያ ተጠማቂው ላይ መርጨት ሲጀምሩም ‹‹ጠቋር ውጣ!››፣ ‹‹አዳል ሞቲ ውጣ!›› እያሉ በማስጨነቅ ሕሙሙ ተጨማሪ በሽታ ሸምቶ እንዲሄድ ያደርጉታል፡፡ በዚህም ምክንያት የእምነታቸውን ጥንካሬ የተፈታተኗቸው ምእመናን አሉ፡፡
 • ሌላው በአንዲት መበለት ቤት ከአንድ ወር በላይ ተቀምጠው ማሳለፋቸው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ርካሽ የጥንቆላ ተግባራቸውን እየሠሩ መቆየታቸው የብዙዎች መነጋገርያ የነበረ የዐደባባይ ምስጢር ነው፡፡

  4) ለግላቸው ገንዘብ ለመሰብሰብ የተጠቀሙበት ዘዴ

 • እ.አ.አ በ1963 ለተቋቋመው ለመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ መሥራች የኾነችው ቤተ ክርስቲያናችን በጉባኤው አማካይነት ለመላው አፍሪካ ትብብርና የሰላም ተልእኮ ጥሪ በማድረግ የበኩሏን እንደምትወጣ ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡ የጉባኤው ምክትል ፕሬዝዳንት ኾነው በቤተ ክርስቲያናችን ስም የተመረጡት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ግን ይህን በማጠናከር ፈንታ ‹‹ለመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያን ርዳታ ለማሰባሰብ›› በሚል ደብዳቤ ጽፈው በራሳቸው ቲተር ማኅተም አድርገው በተለያዩ የውጭ መሥሪያ ቤት የተሠማሩና ሀብታም ኢትዮጵያውያንን በደላሎቻቸው አማካይነት አስጠንተው መጠኑ ያልታወቀ የአሜሪካን ዶላርና የኬንያ ሽልንግ ሰብስበዋል፡፡
 • ኢትዮጵያ ውስጥና በደቡብ አፍሪቃ የምረዳቸውና የማስተምራቸው ሕፃናት አሉኝ በማለት አሉ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ባዕለጸጎችን በተናጠል በመጥራት ገንዘብ በመለመን ለግላቸው ሀብት ያደልባሉ፡፡
 • ቅዱስ ፓትርያርኩና የውጭ ግንኙነት ጽ/ቤት ሳያውቁት በጎጥና በገንዘብ ሰው መቅጠሩን ተያይዘውታል፡፡ ይህም በናይሮቢ ኬንያ ተፈጽሟል፡፡ የሚቀጥሩትም ሰው የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ያለው ሳይኾን እንዲሁ በመንደርና በገንዘብ ጥቅማጥቅም ነው፡፡ አዳዲስ ሰው በመቅጠር ገንዘብ ለመቀበል ሲሉም በመንበረ ፓትርያርኩ የተላኩ አገልጋይ ካህናትን በማሳደድ፣ ቦታውን ጥለው እንዲሄዱም ይገፋፋሉ፤ ባደረሱባቸው ግፍ ቦታውን ጥለው የሄዱም አሉ፡፡
 • ሌሎችም አገልጋይ ካህናት በእርሳቸው የጥንቆላ ዝንባሌና ተግባር ስላልተስማሙ በችግር ላይ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ፓትርያርኩና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይህን ተገንዝበው አስቸኳይ ርምጃ ካልወሰዱ ደብራችንን ከቤተ ክርስቲያናችን የአንድነት መዋቅር ለመለየት በቅርብ ርቀት ያሰፈሰፉ ወገኖች ሊሳካላቸው ይችላል፡፡
 • በሀገር ውስጥም ቄስ ግሩም ታዬ የተባሉ የረጅም ጊዜ ቀራቢያቸውን በሞያ ሳይኾን በገንዘብና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች ሰዎችን ለመቅጠር በደላላነት ይጠቀሙባቸዋል፡፡

5))  ባረጀና ባፈጀ የፖሊቲካ አካሄድ ሁሉን ይመስላሉ፤ ይጠቀማሉ

 • ለምሳሌ የኢሕአዴግ ደጋፊ ሲያገኙ ‹‹እኔ እኮ ኢሕአዴግ ነኝ›› ይላሉ፤ የኢሕአፓ ሰው ሲያገኙም ‹‹እኔም ኢሕአፓ ነበርኹ›› ይላሉ፡፡ እንዲያውም ‹‹እነ ኢጭአት፣ መኢሶን፣ ኢዲዩ ወዘተርፈ ሲመሠረቱ ሁሉ እኔም አንዱ ነበርኹ፤›› ይላሉ፡፡ በቀድሞው መንግሥት የባሕር ኃይል ወታደር እንደነበሩ በራሳቸው አንደበት የሚናገሩት ሊቀ ጳጳሱ ‹‹ጅንሳቸውን ጥለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መጠጋታቸውንም›› አይሸሽጉም፡፡
 • በተመሳሳይ ኹኔታ ኤርትራውያንን ሲያገኙ ‹‹እኔ እኮ ኤርትራዊ ነኝ›› ይላሉ፡፡ ለዚህም የባሕር ኃይል ወታደር በነበሩበት ወቅት በኤርትራ የሚያውቋቸውን አንዳንድ ቦታዎች በስም እየጠሩና የዚያ መንደር ተወላጅ መኾናቸውን እየጠቀሱ ገንዘብ ከእነርሱም ጭምር ይሰበስባሉ፡፡

ይህን ሁሉ ታድያ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት መምሪያው አጽንዖት ሰጥተው በጥብቅ ካልተከታተሉትና አስቸኳይ መፍትሔ ካልሰጡት የሚያስከትለው ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡

Advertisements

18 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ እና ፓትርያሪኩ የአቡነ ያዕቆብ የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት አስተዳደር እያስከተለ ለሚገኘው ጉዳት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጡ ተጠየቀ

 1. tesfa ze debub August 31, 2013 at 3:10 pm Reply

  Endemin alachu,
  Enante yezihin papas tikikilegna getsita alawetachum. Ende ewnetu kehone esachew ke seytanim belay neberu. silesachew yihinin tenagere yibekagnal, tenkara gonachew degmo yih new yemibal aydelem. betarik endezih aynet genzeb mewded, meseriyinet semiche alawkim. yihin betemelekete le dejeselam 15 page ye ej tsihufen like neber (April 2013), kechalachu yanin bitagegnu teru new. kalatoch yatrugnal. kifatachewun lemeglets alchalkum. ahun bezih weky enqwa silk meimenan bet eyetedewele ekele ena ekele tigre silehonu eysametsubign new, ekele ena ekele tebabrew liyatefugn new, wegene yelewum belew new ebakacu tesebasebuna and neger adrigu yemilu melect eyastelalefu new. bezihim aynet serachew dero jemiro wetetama neberu. bemanignawum menged yaltekefafele meimen lesachew menor yelebetim. betam yemaznew teklay betekinet gar yetebeke structural ginignunet yinuren bilen chuhen neber. beziyawum ye hisab aserarachin ena percent akefafelachin teklay betekinetu bemiyawkew deresegn yisera bilen neber. esachew gin altamachewum. yilikunim begilachew be ye atibiya ena gubaeatu eyemetu wede addis ababa lihed new, teklay batekinet min yizeh metah silemilugn 20% awatulign bilew sebsibew be cash yizew hedu. keziya deresegn bebal keyet yimta?
  yemiemenan genzebima bet yikuterew, yemasadigew eguwalemawtan alegn, yemiredaw ye geter betekirstian alegn, abune ekele tamewal lersachew hikimina, beteref eyetesera yalew betekirstian yihen yakil golotal etc yemibalu tedegagami tiyake yemimenun joro aselchitowal. betamnum batamnum and sew 700000.00R (seven hundred thousand rand) yesetebet gize neber. yihi be ethiopia wede 1.2 million birr new. yih engdih and sew new. beyebotaw endih aynet tarikoch sefi nachew.
  ye tinkola negerima asgerami new. esachew minim tinkola yemichilu aymeslegnim gin addis ababa weyim gojam yalutin debterawoch bemetekem yashebrunal. manignawum asteyayet keseteh zachaw neklehalew yemilew new. amed tihonaleh, betih yifersal…eneko kemelaect gar yemawera sew negn…eyetebale sewu yinegerewal..sintu tesededebat.
  haratewahido legnam mister yehonew yih hulu genzeb yet new hedo yemigebaw? bet eyeserubet new? nigd new? ebakachu yihin neger esti awtulin.
  lelaw lersachew demozina tikima tikim sinodosu endalsete tederego bemasewerat genzeb be wedajochachew endisebeseb madreg new. yih be mistir yemisebesebew new. mikniyatu degmo esachew kesemu esh aylum, silezih egna sebsiben ye gil chigrachewun enamwalalen yilalu. kkkkk?? yelakachew rasachew nachew. ahun beteyeku gin ene alawkim yilalu. mewashet man bilot abate?

  sewuyew lelaw yemitamubet sedomawniet new. le negeru ye sex film endemiyayu merejawoch alu. neger gin sile sedomawinetachew finch benorim yeteyaze mereja gin yelegnim. neger gin ye kirb redatachew bezih guday tekesew be nebere gize matatalachew ena alemegeremachew asdengitognal. gudayu yetekesetew siyatemku lijun yawakibutina taglew lemetal simokiru new tilowachew yewetaw. yihim le sebeka kerbo, sebekaw lersachew akribo neber. minim meftehe altesetem.

  yihin hulu sawera esachewun teliche aydelem. gibrachewun sasebew gin hiwot yastelagnal. yene netsuh mehon yesachew hatiyat aydelem gudayu. ene yemilew leteketerubet botachew ageligilot lemestet temetatagn aydelum. botaw yemifeligew abat abune petros, abune daniel, abune yisihak (yalefut) neberu. ye abune petros serama hiyaw new. dink new. abatinetachewun asmeskerewal. besachew yeteseraw zare le abune yaekonb report madregiya hone enji?
  lemehonu egnih sew yikeyeru bebalis yet new yemihedut? lesachew yemihon hegeresibket keyet yimetal. tikikilegn botachew kidist silasse college akebabi weyim teklay betekinet akebabi yimeslegnal.
  belu cher senbitu.
  silkachun bawk bedewelku neber.
  yasenbeten.
  endezih aynet gebiznet be geta zemenim altesemam.
  medhanialem cherinetun yilakilin.

 2. Anonymous September 1, 2013 at 5:09 am Reply

  ለውድ የሐራ ብሎገሮች,
  በኢ-ሜይልና በፖስታ መልእክት በሚደርሳችሁ ተመርኩዛችሁ ስለቤተክርስቲያን ጉዳዮች ዜና ባትሰሩ መልካም ነው:: በቦታው ተገኝታችሁ ያያችሁትን ወይም ደግሞ በትክክል ከምታውቁትና እውነተኛ የተዋህዶ አማኝ እንዲሁም ለቤተክርስቲያን ከሚቆረቆሩት ወገን መሆኑን ከምታውቁት ሰው ብቻ በተገኘ መረጃ ተመርኩዛችሁ ቢሆን መልካም:: ዋናው ምክንያቴ ብዙ ለቤተክርስቲያን የማይተኙና እንደዚህ አይነት ማደናገሪያዎችን ስራዬ ብለው የያዙ ስላሉ ነው:: ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ”አባ ሰላማ” በሚል እራሱን የሚጠራውን የተሃድሶን ብሎግ ማየቱ በቂ ነው:: የሚዘግቡት ሁሉ አንድም እውነትነት የሌለውና ግን እውነት አስመስሎ በመጻፍ ቤተ ክርስቲያንን የማፈራረስ ስራ ነው የተያያዙት:: ደግነቱ ቤተ ክርስቲያን በጴጥሮስ አለትነት ላይ የተመሰረተች ስለሆነች አትፈርስም እንጂ:: ባጭሩ በመልእክት በሚደርሳችሁ ላይ ተመርኩዛችሁ ዜና አትስሩ:: ተንኮል ያሰበ ሰው (መናፍቅ=ተሃድሶ) እዛ የሚገኝ ሰው ስም አፈላልጎ በዛ ሰው ስም ሊጽፍላችሁ ይችላልና::

 3. Anonymous September 1, 2013 at 9:25 am Reply

  south african priest and the member of the church wrote a letter to head office last week complaining about him .he cant be the administer of even one parish church . this bishop is dengerous mafia. this morning his speech in south africa for the congrigation that ‘menafikan’ are the one who wrote on the website.shame on you ante menafik papas gena kesouth africa beheg tekeseh tasereh new yemtewetaw . bank bet hedeh yeserahew sira banku bekirbu kis endemimeseretibeh ewek , acheberbari egziyabher yinkeleh .

  • Anonymous September 2, 2013 at 1:38 am Reply

   ውድ ሐራዎች፡- የደቡብ አፍሪካ ቤ/ክናት ችግርም ሆነ ምዕመኑም ብሶቱን ለበላይ ማሰማት የጀመረው አሁን አይደለም፡፡ በኬንያ እና በሱዳን አህት ቤ/ክናት ላይ ተፈፀመ የተባለውም በደል ሳይፈፀም በፊት ነው፡፡ ከ አንድ ዓመት ተኩል በፊት ብስለትና ትዕግስት በነበራቸው ወንድሞች ዕርቅ ይውረድ ተብሎ ነገሩ እንዲረጋጋ (ምንም እንኳ ለጳጳሱ ትምህርት አይሁን እንጂ) ስለተደረገ ነው እንጂ በወቅቱ የነበሩ የቤ/ክኗ እውነተኛ ተቆርቋሪ ወንድሞች አስከ ፓትሪያርኩ ፅ/ቤት ድረስ የደረሰባቸውን በደል አሰምተው ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ችግሩ እልባት አግኝቶ ቢሆን ኖሮ አሁን የደረሰው ደረጃ ላይ ባልደረሰ ነበር፡፡

   እንደተለመደው አሁንም ከጠፉበት መጥተው ይህንኑ ምስኪን መዕመን “መናፍቃኖች ናቸው ያሴሩብኝ” እያሉ ግራ የጋቡታል፡፡ እውነት ነው በዚህ ግርግር መሃል ድክመታችንን መናፍቃን ለፕሮፓጋንዳ መጠቀማቸው የማይቀር ስለሆነ በእጅጉ መጠንቀቅ ግድ ይላል፡፡
   አንድ ወንድም/እህት እንደጠቀሱት አንደማንኛውም የሚዲያ ማዕከል የመዘዋወር አቅምና ህጋዊ መብት ካላችሁ ወደ ደቡብ አፍሪካ የችግሩ ዋና መዕከል ወደ ሆነው የአህጉሩ ፅ/ቤት እንዲሁም እየተበደሉ ወዳሉት አጥቢያ ቤ/ክናት እና ጉባኤያት ተዘዋውራችሁ የሚካሄደውን እውነተኛውን ብትዘግቡ!

   አንዳንድ ወንድሞች/እህቶች ስለ አባቶችን መውቀስ የምትሰጡት አስተያየት በእውነት ሳይሰማን ቀርቶ አይደለም፡፡ በግሌ እኔም ከላይ የተጠቀሰው ትዕይንት ሲካሄድ ሳይገባኝ እግዚአብሔር ፈቅዶልኝ ተሳትፌ ነበር፡፡ አባት እንደማይከሰስና ያስታረቁ ወንድሞችንም ከልብ አመስግኜ ነበር፡፡ አሁን ታዲያ “በመንፈሳዊ ዕውቀት እንደ ፈጣሪ አምላክ ሆነህ ተሰማህ ወይ የምትተቸው” አንዳትሉኝ! ስለ ክርስትና የሌለኝን እውቀት ሳስበው ለራሴ ያሰፍረኛል፡፡ ነገር ግን ለ7 ዓመታት ያህል የተገለገልኩባትና እንደ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ገና ብዙ እውቀት አገኝባታለሁ የምላት ቤተ/ክ አደጋ ላይ ልትወድቅ መስሎ ሲሰማኝ በጣም ያሳስበኛል፡፡ ስለዚህም ነው የመንፈስ ቅዱስን ስራ ለባለቤቱ ትቼ ቢያንስ እንደ አለማዊ የማየውን አስተዳደራዊ ችግር በሚመለከተው ታይቶ እንዲፈታ ብሶቴን የማሰማው፡፡

   ቤተ ክርስቲያን ስትበደል ዝም ብሎ ማየት ባለብን ጉድፍ ላይ ተጨማሪ ጉድፍ የመበተን ያህል ነው!

   ቅዱስ አምላክ ሰላምን ያምጣልን፡፡

 4. Anonymous September 1, 2013 at 12:59 pm Reply

  Even so i do not know who this father is most of the blame does not look right dear brothers sand sisters please be God fearing. First look at your self are you real christian?

 5. Anonymous September 1, 2013 at 6:29 pm Reply

  My comment is more on Nationality. I always wonder about the role of Foreign nationals in our church administration. EOCT being independently Ethiopian church other sister orthodox church followers participation remains a very big question to me and many EOTC followers especially in diaspora. My comment doesn’t include in religious related matter participation, my focus is in administrative line. Many Eritrean nationals are administering our church in many ways such as in parish counsel and other representation. I feel like it is absolutely not legal and logical, what do you think about this issue?

  • christian September 8, 2013 at 3:00 am Reply

   Shame on u! U r not even christian u r poletician and racist.church is international and house of God.it is not poletical party.look at catholic church even the former cardinal for the whole ethiopea was eritrean.he passed away and burried in ethiopia. D u think when u go to heaven there is a nationality issue? Church is symbol of heaven so for God’s sake ask forgiveness from God for ur sick statement.

 6. Anonymous September 2, 2013 at 4:38 am Reply

  tiru sew kehonu manim ayinekfachewum ke mekawem kom bilo negerun matarat ena wusane mestet yishalal, le mirmera mezegyet tiru ayidelem, maregaget yichal yele.

 7. Anonymous September 2, 2013 at 7:13 pm Reply

  +++
  ሃራ ታሳዝናላችሁ::በሙ የጻፈው አሉ አሉ አሉ ባቻ ነው:: ይህ ደግሞ ከእውነት አርቆባችሁ የጥላቻ ዘገባ አስመስሎታል::

  ፍርዱን ለመድኃኒዓለም ::: እንደባለሙያ ዘገባው የወረደ ነው::

  +++

 8. Anonymous September 2, 2013 at 8:14 pm Reply

  what we call our self is it a real Christian please be God fearing. First let as look our self are we real christian? i don’t think so b/c if we are we are not point our finger the man of God .who we are ?PLEAS let as think about it.

 9. Anonymous September 2, 2013 at 8:45 pm Reply

  እባካችሁ፡ ወንድሞች፡ እህቶች፡ እኔ ፡ደቡብ አፍሪካ፡ ነዉ፡ ምኖረዉ፡ እግዝአብሄር፡ በቀባዉ፡ ላይ ፡ እጃችንን፡ ከምናነሳ ፡በጸሎት እንትጋ፡ ጌታ፡ ሁሉንም፡ ይቀይራል። እንዲህ ፡እንዲያ ፡ባልን ፡ቁጥር ፡ሃ ይማኖታችንን ፡ እያሰደብን ፡ነዉ።

 10. Anonymous September 4, 2013 at 10:34 pm Reply

  ምንም ጥርጥር የለውም ነውረኛ ጳጳስ ነው!!!

 11. Anonymous September 4, 2013 at 10:37 pm Reply

  mnem tereter yelewm neweregna papas new!!!

 12. Anonymous September 7, 2013 at 10:26 am Reply

  Shame on you, all news from Nairobi is so fake. It is a fabricated news.

 13. tesfamariam September 17, 2013 at 9:49 am Reply

  በጣም አሳፋሪ ፤ነዉረኛ የሆነ ፀረ ተዋሂዶ ጦማራችሁ እስከመች የአባቶችን ስምና የቤተክርስያንን ስም ማርከሱን ይቀጥል ይሆን
  መድሃኒዓለም የስራችሁን ይክፈላችሁ፡፡ በግልፅ ለምን የኢ/ኦ/ ቤተክርስቲያን በአለም ላ ይ ለምን ከፍ አለች ፤አማኟ ለምን በዛ አሁጉረስብከቱ በተ ለያየ አለማት እንደ ሰማይ ከዋ ክብት አበሩ ፣የሀዋሪያዊ ተልኮዉ መሳካት እረፍት ነሳን ብላችሁ ብትነግሩን
  ይሻላን፤ከዚህ በኋላ የኑፋቄ ልፈፋችሁን የሚሰማችሁ አማኝ የለም ፤፤እግዚአብሄር በቀባዉ ላይ አፋችሁን ለመክፈት የግብር አባታችሁ ዲያቢሎስ ያስተማራችሁ ስለሆነ ፤
  የቤተክርሰቲያን ራስ ራሱ መደሃኒዓለም ክርስቶስ ከመናዎፅ ያድነን

 14. daniel September 27, 2013 at 1:09 pm Reply

  yemisemaw neger asazinogal geta hizbun yitebik

 15. mesfkeb7@gmail.com October 26, 2015 at 1:28 pm Reply

  እግዚአብሄር በቀባዉ ላይ አፋችሁን ለመክፈት የግብር አባታችሁ ዲያቢሎስ ያስተማራችሁ ስለሆነ ፤
  የቤተክርሰቲያን ራስ ራሱ መደሃኒዓለም ክርስቶስ ከመናዎፅ ያድነን

 16. teddy February 6, 2016 at 10:16 pm Reply

  ብፁህ አባታችን በረከታቸው ይደርብን መች ይሆን ነገርን አጣርተን ሚዲያ የምናወጣው ስለማናውቀው እና ስላልገባን ነገር በአግባብ የምንጠይቀው ከምእመን ተስማተው የሚሰሩ እንደ ስልጣናቸው ሳይሆን በትህትና ወርደው ከአገልጋይ ከሰንበት ተማሪ ከምመን ጋር የሚወያዩ ሃላፊነታቸውን በአግባብ የሚወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይሾማቸዋል ይሸልማቸዋል ብለን ስናስብ እናንተ እና እናንተን የመሰሉ ክብራችሁ በነውራችሁ በሆኑ ጥቅም አይናቸው ያሳወራቸው ግለሰቦች አሉባልታ በሬ ወለደ ወሬ እየተሰማ ክብር ለሚገባው ክብርን ሳንሰጥ እየጠፋን ነው እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጃችንን እየዘረጋን እኔ ወድ 10ዓመት አባታችንን ሳውቃቸው ሰርተው የሚያሰሩ በሞራል በስነልቦና የሚያንፁ ለራሳቸው ስለሚበሉት የማይጨነቁ የማያማርጡ አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር የምዕመን መኖርያ ቤት የማይሄዱ አብዝተው የሚፀልዩ እንድፀልይ የሚገፋፉን በስራ የሚያምኑ በአለማዊውም በመንፈሳዊው ብቁ የሆኑ አባት ናቸው በዚህ በሳውዝ አፍሪካ እሳቸው ሲመጡ አንድ መድኃኒአለም ብቻ ነበር ምዕመኑን በፀሎት በሞራል እንዴት ገንዘብ ማጠራቀም እና ቤተክርስትያን መገንባት እንዳለብን በማሳየት ከድርድር ጀምሮ ግንባታ እና ምርቃት ደረጃ በማድረስ የፕሪቶርያ ኪዳነ ምህረት የብሉንፎንቴን ቅድስት ስላሴን እና ቅዱስ ያሬድ ገዳም የረስተንበርጉን የማርቆስ እናት ቤት እና ቅድስት አርሴማን የደርባኑን ቅድስት ማርያምን የኬፕታውኑን መድኃንያለምን የማፊኬን ቅዱስ ገብርኤልን ሌሎችንም ያሰሩ የሰሩ አባት እኮ ናቸው ስንቱ በአልጋ ቁራኛ ያለ የተጨነቀ ህመምተኛ ተፈወሰ ያሎለዱ መሀን ማህፀን ተፈታ የሳቸው በቪዲዬ ስላልተደገፈ ውዳሴውን አልፈልግም ብለው በየአንዳንዳችን ህልናውስጥ ቀረ እንጂ ብፅህ አባታችን አባት ሆነው ያአባትን ጠአም ያሳዩን የዘመኑ አባት ናቸው ግን ያሳዝናል ጌታ እኮ የፈወሳቸው ያበላቸው ሰዎች እኮ ናቸው ስቀለው ስቀለው ያሉት በአባታችንም ተመሳሳይ የአባታችንን እድሜ ያርዝምልን በረከታቸው ይድረሰን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: