በሊቀ ጳጳሱ ዳተኝነት፡ በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ከመንግሥት የተሰጣቸውን ዕውቅና የመነጠቅ ስጋት እንደተጋረጠባቸው ተጠቆመ

 • ችግሩ የውጭ ግንኙነት መምሪያውን አፋጣኝ ትኩረት ይሻል

የመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኾኑት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አስተዳደር ላይ በወጣው ዘገባ ዙርያ ከሚደርሱን አስተያየቶችና ትችቶች የሚበዙት ከደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን ምእመናንና አገልጋዮች የሚላኩልን ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙበት ፲፱፻፺፯ ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ለስምንት ዓመታት የቆዩበት ደቡብ አፍሪቃ መንበረ ሊቀ ጵጵስናው እና የአህጉረ ስብከቱ ጽ/ቤት ከበርካታ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ጋራ የሚገኝበት ነው፡፡

‹‹ማንነቴን የተቸኋቸው ሰዎች ሁሉ ያውቃሉ›› ያሉ አስተያየት ሰጭ፣ በደቡብ አፍሪቃ አብያተ ክርስቲያን በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱና እርሳቸው በግል ዕውቅና ብቻ በሚመድቧቸው አለቆችና ካህናት ይፈጸማል ያሏቸውን በደሎች በዝርዝር አስፍረዋል፡፡

ከያዙት ሓላፊነት አኳያ የተጣለባቸውን መንፈሳዊና አባታዊ አደራ ከመወጣት ይልቅ ‹‹እርሳቸው[ሊቀ ጳጳሱ] ናቸው እንጀራዬ›› የሚሉ የደብር አለቆች ያለባቸው የአስተዳደር ብቃት ማነስ በምደባ ረገድ የተገለጸውን የጥቅመኝነት ግንኙነት የሚያረጋግጥ ነው፡፡

በዚህ መልኩ በተመደቡና በተቀጠሩ አለቆችና ካህናት ላይ ደግሞ ኑፋቄና ከፍተኛ የእምነት ማጉደል ወንጀልን የሚያቋቁሙ የምግባር ችግሮች  ሲጨመሩበት አስተያየት ሰጭው እንዳሉት ‹‹የዋህና አባቶቹን አክባሪ የኾነውን ክርስቲያን እምነትና አንድነት የሚፈታተን›› ነው፤ ከፋፋይና በታኝ ነው፡፡

የአስተያየት ሰጭው ትችት ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ስለ ደቡብ አፍሪቃ አብያተ ክርስቲያን የልማት እንቅስቃሴ ያቀረቧቸውንና በመንበረ ፓትርያሪክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የተዘገበውን ሪፖርት የሚያስተባብልም ነው፡፡ ከዚያም በላይ አስተያየት ሰጭው ስጋታቸውን ሲገልጹ፣ በአህጉረ ስብከቱ ጽ/ቤት ዳተኝነት ምክንያት የአህጉረ ስብከቱ አሠራር የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት ዕውቅና ከሰጠበት አገራዊ ሕግ አኳያ እንዲጣጣም ባለመደረጉ ‹‹የተሰጠን  ዕውቅና  እንደሚነጠቅና ሕዝበ ክርስቲያኑም እንደሚበተን አጠያያቂ አይደለም፤››ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በመላው አፍሪቃ አህጉረ ስብከት የብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አስተዳደር ላይ በጥቅሉ የተጠቆሙት ችግሮች÷ ሐዋርያዊቷና ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን ለዘመናት እጃቸውን ዘርግተው ለሚጠብቋት ጥቁር ሕዝቦችና ለመላው ዓለም ለመድረስ በዓለም አቀፋዊ ተልእኮዋ ረገድ ያሉባት በርካታ ውስንነቶች አነስተኛው መገለጫና ከዚህም አንጻር ገና ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባት ጠቋሚዎች ናቸው፡፡ ለማንኛውም ሐራዊው አስተያየት ሰጭ ‹‹ለሚመለከተው አካል በቀጥታ መድረስ ያለበትና አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው›› ያሉት መልእክታቸው ከሚያስፈልገው ልዩ ትኩረት አንጻር እንዳለ አቅርበነዋል፡፡

*            *            *

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 /ማንነቴን የተቸኋቸው ሰዎች ሁሉ ያውቃሉ/

በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት ላይ በግለሰቦች እየተሠራ ያለው በደል በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ይህ ከዚህ በታች የምተነትነው መልዕክት በቀጥታ ለቤተ ክርስቲያንዋ እውነተኛ ተቆርቋሪዎች ይደርስ እንደሆነ አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው፡፡

የማይታየውንና ሰማያዊውን ነገር መንፈስ ቅዱስ ይመርምር!!! የሚታየውንና በግልጽ የማውቀውን ግን በድፍረት ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ስል እመሰክራለሁ፡፡

በደሉም በሰፊው እየተፈጸመ ያለው በአቡነ ያዕቆብና በየአጥቢያው በየግል እውቅና ብቻ በመደቧቸው አስተዳዳሪዎች ነው፡፡ ይህን በደል እንዲያቆሙ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እውነተኛ ለቤተ ክርስቲያናችን የምንቀና ግለሰቦች ፊት ለፊት በግልጽ ልንመክራቸው ሞክረናል፡፡ እርሳቸው ግን በማን አለብኝነት የዋህና አባቶች አክባሪውን ሕዝበ ክርስቲያን በማታለልና በመከፋፈል የክርስትና አንድነታችንን በሚፈታተን መልኩ እየበተኑን ነው፡፡

ወደ ደቡብ አፍሪካ ተመድበው ሲመጡ ለነበሩበት መንበር ሰበካ አባላት ዕንቆቅልሽ በሆነ መልኩ ስብከተ ወንጌል እንዳይስፋፋ የነበረውም አሠራር እንዲዳከም አደረጉ፡፡ በመቀጠልም የማይገባቸውን “የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት” አስተዳዳሪነት ከፓትሪያርኩ ጽ/ቤት ተሰጥቶኛል የሚሉትን ደብዳቤ ይዘው መጥተው ለአገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በማሳወቅ የጥፋት ዘመቻቸውን ጀመሩ፡፡

በመጀመሪያ ለሌሎች አርኣያ የነበረውንና ለሌሎችም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት መመሥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተውን የደርባንን ጉባኤ ከእናት ቤተ ክርስቲያን እንዲለይ አደረጉ ወይም እንደ አባት ያጠፋውን ክፍል ገሥጸው መመለስ ሲችሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው እስከ አሁን መፍትሔ ሳይሰጡ ቆይተዋል፡፡

በመቀጠልም በጆሐንስበርግ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለመግለጽ ለአእምሮ የሚከብድ ጥፋት ሲጠፋ እየሰሙ እንዳልሰሙና በሐላፊነት ብዛት ልፈታው ጊዜ የለኝም በማለት እያደባበሱ መንበረ ጵጵስናቸውንም ችላ በማለት በሌሎች “የአህጉረ ስብከቱ” አባል አገሮች በተለያየ ቦታዎች “ሥራ እየሠራኹ ነው” በማለት በጽ/ቤታቸው ላለመገኘት ምክንያት እየሰጡ ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተለያዩ ግንባታዎች እንዲካሄዱ አድርጌያለሁ ብለው የሰጡትን ሪፖርት በሚመለከት፡- አንድ እና አንድ ግልጽ ነው – የሚመለከተው የበላይ አካል መጥቶ ይመልከት!! የተደረጉትም ጥቂት ልማቶች በጠንካራ የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን እንጂ በርሳቸው የአመራር ብቃት ወይም ፍላጎት አይደለም፡፡ እንዲያውም በተለያዩ አጋጣሚዎች ለግንባታ መሰናክል ሲሆኑ ነው የሚታዩት፡፡

በመጨረሻም አሁን በፕሪቶርያ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት የተፈጠረው ችግር ያልተፈታው እርሳቸውን በመጠባበቅ ነው፡፡ ከላይ አንደተገለጸው በየአጥቢያው የሚመደቡትን አስተዳዳሪዎች የሚመድቡት እርሳቸው ናቸው፡፡ እኝህም የችግሩ መንሥኤ የኾኑት መነኩሴ የተመደቡት በርሳቸው ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ደብሩን ያስተዳደሩት መነኩሴ ሰበካው ያወጣውን የአስተዳደርና ሌሎችንም የቅጥር መስፈርቶች ያላሟሉና ተመድበው ከመጡበት ጌዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ የደብሩ ካህናትንና ዲያቆናትን ጨምሮ በተለያዩ ግለሰቦች በምንፍቅና፣ በገንዘብ ማታለልና እንዲሁም በወሲብ ክሶች ሲከሰሱ የቆዩ ነበሩ፡፡ ሰበካው በመደበው ንኡስ ኮሚቴ ጉዳዩ ለረጅም ጊዜ ተመርምሮ በምንፍቅና እና በገንዘብ ማታለል የተከሰሱበትን በግልጽ ተነግሯቸው እንዲታረሙ ተደርገው፣ በወሲብ ምክንያት የተከሰሱበትን ክስ ግን በቂ ማረጋገጫ ስላልተገኘ ውድቅ ኾኖ ነበር፡፡

መነኩሴው እሳቸው ናቸው አንጀራዬ ብለው በግልጽ እየተናገሩ ለአቡነ ያዕቆብ ወሬ አቀባይ ከመኾንና ሰበካውን ከምእመኑና ከካህናት ጋር ከማጋጨት በስተቀር ምንም ለቤተ ክርስቲያኑ ያበረከቱት ነገር የለም፡፡ በመጨረሻም ከደብሩ የተባረሩበት በግልጽ በተረጋገጠ የወሲብ ትንኮሳ ክስ ከሰበካው አባላት በተጨማሪ ዐሥር ያህል ገለልተኛ ምእመናን በተገኙበት በሙሉ ድምፅ የተወሰነ ውሳኔ እርሳቸውም በወቅቱ አምነው የፈረሙበት ነው፡፡

ይህ ከላይ የተገለጸው ታሪክ ምናልባት እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አሠራር ይቅር በመባባል እንዲሁም እንደተለመደው አንድ ደብር ያጠፋውን አስተዳዳሪ ወደ ሌላ ደብር መመደብ ቀላል ሊኾን ይችላል፡፡ ነገሩ ግን ከዚህም በጣም የከፋ ገጽታ አለው፡፡
ይኸውም አሁን ጠቅላላ መስተዳደሩ ላይ ያለው አካል ላለንበት አገር (ደቡብ አፍሪካ) መንግሥት ቤተ ክርስቲያንዋ የተሰጣትን ዕውቅና ላለማጣት ዓመታዊ የሒሳብና የተለያዩ ሪፖርቶችን ለሁለት የመንግሥት አካላት (Social Development እና South African Revenue Service) ማቅረብ ግዴታ አለባት፡፡ ይህም ደግሞ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ጽ/ቤታችን “የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት” ጽ/ቤት ተብሎ እስከተሰየመ ድረስ ጽ/ቤቱ ላለበት አገር ጠቅላላ የውስጡንም ኾነ የውጪውን በሥሩ ያሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ገንዘብ ነክ የሆኑና ያልሆኑ የሥራ እንቅስቃሴዎች ሪፖርት ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን እንኳን የውጪውን አገሮች የውስጡንና የመንበረ ጵጵስና ደብራቸውን የተሟላ ተቀባይነት የለው የሒሳብ አሠራር እንዲዘረጋ ጳጳሱ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ለ(Social Development) እንዲሁም ለአራት ዓመታት ለ(South African Revenue Service) ሪፖርቶች ያልቀረቡ ሲኾን በቅርቡ የሚያስፈልገው ወሳኝ ሥራ ካልተሠራ የተሰጠን ዕውቅና እንደሚነጠቅና ሕዝበ ክርስቲያኑም እንደሚበተን አጠያያቂ አይደለም፡፡

እንግዲህ ይህን የሚያህል ሐላፊነት አደጋ ላይ ጥለው ነው አቡነ ያዕቆብ ለግል ጥቅማቸው/ስማቸው ብቻ ላይ ታች የሚሉት፡፡ የሚገርመው መንግሥት ለኦዲት ቢመጣ ሌላው ይቅርና ላለፉት አምስት ዓመታት 50,000 ራንድ በላይ በግል የታክስ ዕዳ የመጀመሪያ ተጠያቂ የሚሆኑት አቡነ ያዕቆብ እና እንደማንኛውም ግለሰብ በሥራ የመንግሥት ፈቃድ እየታደሰላቸው የተመደቡት መሰሎቻቸው የየደብሩ አስተዳዳሪዎች ናቸው፡፡

ይህ ነገር በግልጽ ቢነገራቸውም አቡነ ያዕቆብ አሻፈረኝ ብለዋል፡፡

ተ ክርስቲያን ስትበደል አይቶ ዝም ማለት ባለብን ጉድፍ ላይ ተጨማሪ ጉድፍ የመበተን ያህል ነው!

እግዚአብሔር ተሰባስቦ ከመበተን ይጠብቀን!!!

Advertisements

11 thoughts on “በሊቀ ጳጳሱ ዳተኝነት፡ በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ከመንግሥት የተሰጣቸውን ዕውቅና የመነጠቅ ስጋት እንደተጋረጠባቸው ተጠቆመ

 1. ባልቻ August 28, 2013 at 8:45 am Reply

  አሁን በቅርቡ የፌድራል ጉዳዮች ሚንስትር መ/ቤት የሐይማኖት ተቋማት ምዝገባና በፈቃድ አሰጣጥ ዙሪያ የወጣውን ደንብና መመሪያ ረቂቅ ተመልክተው……እኛ እንዴት እንመዘገባለን አማናዊት፣ ታሪካዊት፣ ጥንታዊት….ወዘተ እያሉ ሲያጨበጭቡ የነበሩ ሁሉ ደቡብ አፍሪካ ላይ ግን ምዝገባ ብቻ አይደለም የሒሳብ ሪፖርታቸውን ጭምር እንዲያቀርቡ ይገደዳሉ፡፡
  እውነቱን ለመናገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቢያንስ ቢያንስ የምስራቅ አፍሪቃ ህዝቦች ሐይማኖት የመሆን ዕድልና አጋጣሚ ነበራት ግን ምን ያደርጋል ተዋህዶ ልጆችሽ አይረቡም፤ ዘረኝነት፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ ስም ማጥፋት፣ ግለኝነት፣ ትምክህት፣ አድማ፣ ፖለቲካ፣ስግብግብነት……….ኧረ ስንቱ ይጠራል
  እኔ የሚገርመኝ በዓለም ላይ በጥቂቱ የምናየው ነውርና ኃጢያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በስፋት መታየቱ ነው፡፡
  ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የጥቁር ህዝቦች ይቅርና የኢትዮጵያውያን ሐይማኖት ለማድረግ እንኳ አቅማችን፣ ችሎታችን፣ እውቀታችን፣ በተለይ ደግሞ ስነ ምግባራችን አይፈቅድም፡፡
  አሁን አሁንማ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንም መልካም ነገር አይሰማም………..ያሳዝናል!

  • ንጹህ August 29, 2013 at 6:20 am Reply

   አትዘን፤
   ካልደፈረሰ አይጠራም፡፡

 2. hanna August 28, 2013 at 10:49 am Reply

  selam hara tewahdo 8 amet mulu akoselun enkwan yemela Africa papas tera mimen enkwan sile betekiristian yikochal yasbal melkam sinemigbar yitayibetal fitsum menfesawinet yegodelachew abat be ewnet ye south Africa mimen tenkara new esachew bemiadersut bedelina gif sew hulu betefa neber bizu sewm bemitayew yastedader bilishunet ke betekiristian yekere beki yewengel agelglot bemekuwaretu hizbu menafik eyehone new lelawm ke betekiristian eyetefa new ahunim sinodosu yihn teredto enihn abat marem yitebekibetal ye betekiristian shekim nachew esti be Mariam ke erkebe kahnat sibseba bewala 4 wer mulu Addis abeba min yiseralu Agere sibketachew ezih debub Africa new le sint guday sitebeku hagere sibketachew tenawto eyemetahu new erob emetalew eyalu sint ye erob samint alefe yasazinal amlake kidusa yifared yetm astedadrew sayawku astedadariy teblew be 1995 metu wedyaw mastedaderun sayilemamedu be 2 amet papas honu teshomu wulude pawlos yebetekiristian yebetekiristia ewket yelachew kidase enkwan le south Atrica medhanialem betekiristian bemetenu ashashlewal be gubo hayil ezih yederesu migbare bilishu nachew Amlak libona setto yimelsachew legnam yeseranewn hatyat yikir bilo melkam abat yisten silesachew bizu malet yichalan nger gin yibkan

 3. Anonymous August 28, 2013 at 11:47 am Reply

  ትክክል! ቃለ ሕይወት ያሰማልን

 4. Anonymous August 28, 2013 at 3:38 pm Reply

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አሃዱ ምላከ
  አሜን፤፤

  በመጀመርያ ይህን ጽሑፍ አቀናብራችሁ ውሸትም ቢሆንም ቅሉ ላቀረባችሁልን ለማህበረ ቅዱሳንና ለደብሩ ስበካ ጉባኤ አባላቶች ከልብ እናመሰግናለን፤፤
  በመቀጠል ‹‹የዓሣ ግማቱ ከኣናቱ ››እንዲሉ የሊቀጳጳሱ ነገር ተነግሮ አያልቅም ለምሳሌ ካለባቸው መጥፎ ስነ ምግባር እንደ እስስት ጠባይን መቀያየር ውሸታምነት ዘረኝነት የተማረ ሰውን አለመውደድ እኔ አቃለሁ ማለት በአጠቃላይ የትምህርትና የአስተዳደር ብቃት ማነስ ብዙ ሙሁራን ካህናት ጊዚያቸው ስውተው የወሰኑትን ውሳኔ በተልካሻ ምክንያት ማፍረስ በቅርቡ ደርባን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ምዕመናኑ ለ3 ወር ያህል መፍትሄ አጥተውከ600ኪሎሜትር በላይ ተጉዘው ተንከራትተው ሲመጡ እሳቸው ግን ቤታቸው ተኝተው ከባለስልጣናት ጋር ስብሰባ ነኝ አይመቸኝም ….እያሉ ሲያጉላሉዋቸው መፍትሄ አጥተው ከእናት ቤተክርስቲያን ተገንጥሉ ፤፤ ይህ ሁሉ የሳቸው ስራ መሆኑ ኢያወቁ ና እየሰሙ ማህበረ ቅዱሳን ግን እነሱ ስላልተነኩ ብቻ ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው ጸጥ ብለው ከርመዋል፤፤
  አሁን ግን በማህበረ ቅዱሳን ጉርፕ ሲመራ የነበረውን የሃመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነምህረት ቡተከርስቲያን ሰበካ ጉባኤው ህዝቡ በተደጋጋሚ የሂሳብ ሪፖርት አቅርቡልን ሲላቸው በገንዘብ ጉድለት ምክንያት ባለማቅረባቸው የትምህርት ማነስና የፖለቲካና የስልጣን ጥመኝነት ስላላቸው እንዲውርዱልን ስላሉ አስተዳዳሪውም በእሁድ ቀን ለህዝቡ ግልጽ ድርገው አናውንስ ስላደረጉ ማክሰኞ ሰበካጉባኤውና ማህበረቅዱሳን ሆን ብለው ተቀናጅተውበምነኩሴው ላይ ድራማ ስሩ ድራመውም አነሱ በየጥጉ ተደብቀው ቅድሚያ ተደርጎ የማያውቅ በቤተክርስቲየንዋ ላይ ትልቅ ድፍረት ፖሊስና ጋዜጠኛ አዘጋጅተው ሴት ቤታቸው ገብታ እንድትጮህ አድርጉ ለአስተዳዳሬው አናሳስረዎታለን ዲፖርት እናደርገዎታለን ብለው በማስፈራራትና በማስገደድ ራሳቸው በውሸት ያቀናበሩት ደብዳቤ እንዲፈርሙ አድረግዋቸው ፤፤
  ለምን ቢባል ትልቁ ምስጢር 1ኛ የማህበሩ ጥቅማ ጥቅም ስለተነካ በየጊዜው ከደብሩ ያለ አግባብ የሚዛቅና የሚሰጣቸው ብር ሊቀርባቸው ነው፤
  2ኛ ስበካ ጉባኤዎቹ አባላቶች በቂ የሆነ የራሳቸው ገቢ የሌላቸው ከመሁኑም በላይ በየጊዜው በጸባይናበደብሩ ገንዘብ ጉድለት የሚታሙ ስለሆኑ ከሰበካ ጉባኤ ከወረዱ ከሙዳየ ምጽዋት ውጪ ምንም አይነት ገቢ ስለሌላቸው እንደ ርስት ጉልት መውረድ አይፈልጉም፤፤ምስጢሩ ይሄው ብቻ ነው፤፤፤፤፤፤

 5. teshe August 29, 2013 at 6:38 am Reply

  Hara tewahido endemin keremachu? ene silegnih sewiye sera zim malet betekirstianin mebedel meslo tayegn. be tarik (sinksar the tahisas) endemitayew simonawuyan pipisina teshumew betekirtianin yawekubet agatami neber. genzeb be zemenachin yalgebabet bota yelem. andin yesenbet temari kemis albiso, distun tido papas bilo be berari wereket silak tazibenal. ye zemenu senbet temari enqwan betam yeseletene new. ewket alew. ahun gebeya lay yalutin simonawiyan menekosat ena papasatin temelketu. tensiou, tseliu, bilew semon sayizu/sayawku eko new fitihat the weld bicha atnitew yeminorut. hulachihum altazebachum? ke papasat abune yaekob, abune fanuel, abune sawiros yitekesalu. ke menekosatis…bet yikterew.
  alememarachew be haymanot menorin kelkilowachewal. hulem zemawiyan, genzeb ena tikim asadojoch honu, ye menafikan telalakiwochim enersu nachew. yih hulu yehonew betekirstian wustachew sile lech new. endew hule kemaznew neger and bicha litikes. abune yaecob ke akwakwam mihur menekuse (melake mihret aba teklemariyam) gar tegachu. bewektu menekusew esachewun be sim bayteksim dirgitachewun be tinish metsihaf melk tsifo neber (ye metsihafun copy magignet yichalal), fes yalebet ziliya aychilim newuna, sile ene new yetsafkew yilutina kebetekirstian yaswetutal. keziyam lemastarek enem shimagle hugne bezu dekemin. menekusewum atifichalew yikir belugn alachew. mecheresha yikirtan ke abune yaekob magignet altechalem. bezih yetebesachew komos kobun tilo protestant hone. yene hasab mewedekiya bayasatut nuro biyance ye niseha edilu sefi neber. mechereshaw gin tifat hone. kezih belay aremenent min ale? yikir yemayil yebetekirtian abat man neber? yohanis? hiriyakos? …sintun abatochen litkes? lemehonu keman teweledu abune yaekob?
  ene bezu malet echil neber silebetekirtian kebir yibkagn. ye nesiha gize yistachew.
  ke kahinat wegen negn

 6. እኔም የምለው አለኝ August 29, 2013 at 7:43 pm Reply

  በስመ አብ ወወልድ ወምንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
  ይህ ዜና ከወጣበት እለት ጀምሮ እያንዳንዱን አስተያየት እየተከታተልኩ የቆየሁ ቢሆንም ዛሬ ደግሞ እንደማንኛውም የቤተክርሰቲያን ተቆርቋሪ ምእመን የሚሰማኝን ለመተንፈስ ወሰንኩ፡፡
  በቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ሰአት እንደቀድሞው እግዚአብሄር አምላክ ሳይሆን እግዚአብሄር በአምሳያው የፈጠራቸውና እሱን አንዲያገለግሉ የተሾሙ ሰዎች እየተመለኩ እንደሆነ ለመታዘብ ይቻላል፡፡ በእርግጥ እኔ ተራ ሰው ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የመናገር ብቃቱ ባይኖረኝም የእግዚአብሄር ቤት ግን መገበያያ ሲሆን እያዩ ፀጥ ማለት የሚያስችል መንፈስ ስላልተሰጠኝ እናገራለሁ፡፡ ይህን ማለት ደግሞ የራሴን ግንድ ሳልነቅል የባልንጀራዮን ጉድፍ መመልከት የሚሆንብኝ ከሆነ መጽፉን ወይ እኔ ወይ ደግሞ ነቃፊዮ በትክክል አልተረዳነውም ማለት ነው፡፡
  ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት አንድ ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ….ለመሆኑ አባታችን አቡነ የዕቆብ የት ሄዱ? አንድ አለማዊ አስተዳዳሪ አንኳን በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ከቀናት ባለፈ በማይወስድበት ጊዜ ላይ እያለን ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን የቤተክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ብቃቱም ሆነ ስልጣኑ እንዳላቸው የምናስባቸው አባት ወዴት ተሰወሩ?
  የዝሙት ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በይፋ መሰማት ከጀመረ ውሎ ቢያድርም(ባለፈው አመት በጆሀንስበርግ የዛሬ ሁለት ወር ደግሞ በፕሪቶሪያ)ለጉዳዩ የመጨረሻውን መልስ መስጠት ያለባችው አባት ግን የሉም፡፡ መንጋው አንድ በአንድ በተኩላ እየተነጠቀ ባለበት በአሁኑ ሰአት የእረኞች ማንቀላፋት አግባብነት ያለው አይመስለኝም፡፡ ባለፈው በጆሀንስበርግ የተነሳው የዚሁ ጉዳይ ቢፈታ ኖሮ ዛሬ ደግሞ በኪዳነምህረት ባልተደገመ ነበር፡፡
  ከምንም በላይ ደግሞ የሚገርመው በጉዳዩ የተከሰሱት ቆሞስ ሰበካውና ማህበረ-ቅዱሳን ተመሳጥረው ( ሰበካው ሂሳብ ስለጎደለበት በሚል ሰበብ ማለት ነው)እንዲባረሩ እንዳደረጉ በሰፊው እንዲወራ ማድረጋቸው ነው፡፡ እኔ የምለው የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ እሳቸው አልነበሩም እንዴ? ገንዘብ ሲወጣም ሆነ ሲገባ እንዲሁም ሙዳየ ምፅዋት ሲቆጠር እና ገንዘብ ነክ የሆኑ ውሳኔዎች ሲወሰኑ የሚፈርሙት ዋናው እሳቸው አይደሉም እንዴ? ገንዘብ ጎደለ የሚሉ ከሆነማ በዚህም እንከሳቸዋለን ማለት እኮ ነው፡፡
  ሌላው የገረመኝ ነገር ደግሞ የሀገረ ስብከቱ ሰበካው ያገዳቸውን አባት ተቀብሎ ስለታገዱበት ቤተክርስቲያን ጉዳይ ውሳኔ እንዲሰጡ ለማስቻል ጉዳዩ ሳይፈታ በአህጉረ-ስብከቱ ስብሰባ ላይ ማስቀመጡ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለሰሩት መልካም ስራ ‘ሽልማት’ መስጠት እንደማለት ነው፣በጣም ያሳፍራል፣ያሳዝናልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሰበካውንና ከጉዳዩ ጋር ይያያዛሉ ብሎ ያሰባቸውን አካላት የአህጉረ ስብከቱ ስራ አስፈጻሚ የሆነው ‘ምሁር’ ሲያነጋግር የጉዳዩ ባለቤትና ተጎጂ የሆነችውን ግለሰብ ግን ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ሊያነጋግራት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ይህንን ከባለ ጉዳዋ አንደበት ከጉኝጮቿ ከሚፈልቁት እንባ ጋር መስማቴን እመሰክራለሁ፡፡ ቆሞሱ ሲሰሙ በሳቸው በደል የደረሰባት ግለሰብ ግን የመሰማት መብት አላገኘችም፡፡ በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ አንዱ ልጅ አንዱ የእንጀራ ልጅ ነው እንዴ?
  በተጨማሪ ከዚህ በላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ አስተያየት በተመለከተ ነው፡፡ ዜናውን በተመለከተ የማህበረ ቅዱሳን እና የሰበካው እጅ እንዳለበት የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ፣ የሰበካው አባላት በቂ መተዳደሪያ የሌላቸውና የገቢያቸው መሰረት የሆነውን የሙዳየ ምፅዋት እንዳይቀርባቸው….ወዘተ ያሉት አስተያየት ሰጪው ስለ አባላቱ ማንነት በቂ ግንዛቤ እንደሌላቸው የሚያስረዳ ነው፡፡ እኔ የሰበካው አባለት ተቆርቋሪ ወይም ወኪል ባልሆንም፣ ስለአባላቱ የኑሮ ደረጃ ግን ለመመስከር እችላለሁ፡፡ በመጀመሪያ አባላቱ አንቱ የተባለ የቢዝነስ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቷ ከጉባኤነት ወደ ቤተክርስቲያነት እንድትሸጋገር ቀን ከለሊት ጊዜአቸውን ሰውተው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ እንደጠቀስኩት የሂሳብ ጉድለት ካለ በዋነኝነት መጠየቅ ያለባቸው የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ቆሞስ ናቸው፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት የሂሳብ ጉድለት እንደሌለ ደግሞ እሳቸውን አስጠልሎ ያስቀመጠ የአሕጉረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የባለፈው እሁድ ሳምንት ከስርአት ቅዳሴው በኋላ ለምእመኑ ይፋ አድርጓል፡፡በእኔ አመለካከት በሰበካው ጥያቄ እንዲመጡ የተደረጉ አስተዳዳሪ፣ በሰበካው ሴራ የባረራሉ ብዮ አላስብም ምክንያቱም እንዲመጡ ጥያቄ ያቀረበው እራሱ ሰበካው በመሆኑ፡፡በእርግጥ የሁሉም ፈራጅና የልብ መርማሪ እግዚአብሄር ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ምዕመን ደገሞ በዙ የምንታዘበው ነገር አለ፡፡ አንድም ቀን ቆሞሱ የመንፈሳዊነት እይታ ታይቶባቸው አያውቅም፡፡ ባለፈው የደርባን ምዕመን ሊበተን ነውና ምሕላ እና ጸሎት ለምን እንዲደረግ አታደርጉም ብሎ የተወሰነ ምዕመን በግል ሲያናግራቸው የሰጡት ምላሽ ‘ሰውዬው(ጳጳሱ) የምን አድማ ነው የምታስደርገው ብሎ እንዲጮህብኝ ልታደርጉ ነው እንዴ?’ የሚል ነው፡፡ ለዚህ ነው ከላይ በተክርሰቲያ ኒቱ ውስጥ እግዚአብሄር ሳይሆን ነገ ወደ አፈር የሚገባው ሰው ነው ለማለት የደፈርኩት፡፡
  ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት ብዙ በዙ ስለ ጳጳሱም ሆነ እሳቸው ስላመጧቸው ሰዎች መናገር ቢቻልም፣ አንባቢውን ከማሳዘን ውጪ ያንጻል ብይ ስለማላስብ ዝም ማለት ይሻላል፡፡ ነገር ግን የሚመለከተው አካል የህንን በደል ተመልክቶ እርምጃ ቢወስድ የተሸለ ይመስለኛል፡፡ ካልሆነ ደግሞ ክርስቶስ በደሙ ስለገዛት ቤተክርስቲያን ጉዳይ እሱ ባለቤቱ ይፍረድ፡፡ ሆኖም ግን የእግዚአብሄርን ትዕግስትና ምህረት ከሞኝነት ባንቆጥር መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡
  እንግዲህ እግዚአብሄር ፊቱን ይመልስልን፣ይራራልንም ይቅርም ይበለን፡፡ እኔንም የማይገባኝን ከዘባረኩ ይቅር ይበለኝ፡፡አሜን፡፡

 7. እኔም የምለው አለኝ August 29, 2013 at 7:51 pm Reply

  በስመ አብ ወወልድ ወምንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

  ይህ ዜና ከወጣበት እለት ጀምሮ እያንዳንዱን አስተያየት እየተከታተልኩ የቆየሁ ቢሆንም ዛሬ ደግሞ እንደማንኛውም የቤተክርሰቲያን ተቆርቋሪ ምእመን የሚሰማኝን ለመተንፈስ ወሰንኩ፡፡

  በቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ሰአት እንደቀድሞው እግዚአብሄር አምላክ ሳይሆን እግዚአብሄር በአምሳያው የፈጠራቸውና እሱን አንዲያገለግሉ የተሾሙ ሰዎች እየተመለኩ እንደሆነ ለመታዘብ ይቻላል፡፡ በእርግጥ እኔ ተራ ሰው ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የመናገር ብቃቱ ባይኖረኝም የእግዚአብሄር ቤት ግን መገበያያ ሲሆን እያዩ ፀጥ ማለት የሚያስችል መንፈስ ስላልተሰጠኝ እናገራለሁ፡፡ ይህን ማለት ደግሞ የራሴን ግንድ ሳልነቅል የባልንጀራዮን ጉድፍ መመልከት የሚሆንብኝ ከሆነ መጽፉን ወይ እኔ ወይ ደግሞ ነቃፊዮ በትክክል አልተረዳነውም ማለት ነው፡፡

  ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባቴ በፊት አንድ ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ….ለመሆኑ አባታችን አቡነ የዕቆብ የት ሄዱ? አንድ አለማዊ አስተዳዳሪ አንኳን በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ከቀናት ባለፈ በማይወስድበት ጊዜ ላይ እያለን ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን የቤተክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ብቃቱም ሆነ ስልጣኑ እንዳላቸው የምናስባቸው አባት ወዴት ተሰወሩ?

  የዝሙት ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በይፋ መሰማት ከጀመረ ውሎ ቢያድርም(ባለፈው አመት በጆሀንስበርግ የዛሬ ሁለት ወር ደግሞ በፕሪቶሪያ)ለጉዳዩ የመጨረሻውን መልስ መስጠት ያለባችው አባት ግን የሉም፡፡ መንጋው አንድ በአንድ በተኩላ እየተነጠቀ ባለበት በአሁኑ ሰአት የእረኞች ማንቀላፋት አግባብነት ያለው አይመስለኝም፡፡ ባለፈው በጆሀንስበርግ የተነሳው የዚሁ ጉዳይ ቢፈታ ኖሮ ዛሬ ደግሞ በኪዳነምህረት ባልተደገመ ነበር፡፡

  ከምንም በላይ ደግሞ የሚገርመው በጉዳዩ የተከሰሱት ቆሞስ ሰበካውና ማህበረ-ቅዱሳን ተመሳጥረው ( ሰበካው ሂሳብ ስለጎደለበት በሚል ሰበብ ማለት ነው)እንዲባረሩ እንዳደረጉ በሰፊው እንዲወራ ማድረጋቸው ነው፡፡ እኔ የምለው የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ እሳቸው አልነበሩም እንዴ? ገንዘብ ሲወጣም ሆነ ሲገባ እንዲሁም ሙዳየ ምፅዋት ሲቆጠር እና ገንዘብ ነክ የሆኑ ውሳኔዎች ሲወሰኑ የሚፈርሙት ዋናው እሳቸው አይደሉም እንዴ? ገንዘብ ጎደለ የሚሉ ከሆነማ በዚህም እንከሳቸዋለን ማለት እኮ ነው፡፡

  ሌላው የገረመኝ ነገር ደግሞ የሀገረ ስብከቱ ሰበካው ያገዳቸውን አባት ተቀብሎ ስለታገዱበት ቤተክርስቲያን ጉዳይ ውሳኔ እንዲሰጡ ለማስቻል ጉዳዩ ሳይፈታ በአህጉረ-ስብከቱ ስብሰባ ላይ ማስቀመጡ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለሰሩት መልካም ስራ ‘ሽልማት’ መስጠት እንደማለት ነው፣በጣም ያሳፍራል፣ያሳዝናልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሰበካውንና ከጉዳዩ ጋር ይያያዛሉ ብሎ ያሰባቸውን አካላት የአህጉረ ስብከቱ ስራ አስፈጻሚ የሆነው ‘ምሁር’ ሲያነጋግር የጉዳዩ ባለቤትና ተጎጂ የሆነችውን ግለሰብ ግን ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ሊያነጋግራት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ይህንን ከባለ ጉዳዋ አንደበት ከጉኝጮቿ ከሚፈልቁት እንባ ጋር መስማቴን እመሰክራለሁ፡፡ ቆሞሱ ሲሰሙ በሳቸው በደል የደረሰባት ግለሰብ ግን የመሰማት መብት አላገኘችም፡፡ በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ አንዱ ልጅ አንዱ የእንጀራ ልጅ ነው እንዴ?

  በተጨማሪ ከዚህ በላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ አስተያየት በተመለከተ ነው፡፡ ዜናውን በተመለከተ የማህበረ ቅዱሳን እና የሰበካው እጅ እንዳለበት የጠቆሙት አስተያየት ሰጪ፣ የሰበካው አባላት በቂ መተዳደሪያ የሌላቸውና የገቢያቸው መሰረት የሆነውን የሙዳየ ምፅዋት እንዳይቀርባቸው….ወዘተ ያሉት አስተያየት ሰጪው ስለ አባላቱ ማንነት በቂ ግንዛቤ እንደሌላቸው የሚያስረዳ ነው፡፡ እኔ የሰበካው አባለት ተቆርቋሪ ወይም ወኪል ባልሆንም፣ ስለአባላቱ የኑሮ ደረጃ ግን ለመመስከር እችላለሁ፡፡ በመጀመሪያ አባላቱ አንቱ የተባለ የቢዝነስ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቷ ከጉባኤነት ወደ ቤተክርስቲያነት እንድትሸጋገር ቀን ከለሊት ጊዜአቸውን ሰውተው ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ እንደጠቀስኩት የሂሳብ ጉድለት ካለ በዋነኝነት መጠየቅ ያለባቸው የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ቆሞስ ናቸው፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት የሂሳብ ጉድለት እንደሌለ ደግሞ እሳቸውን አስጠልሎ ያስቀመጠ የአሕጉረ ስብከት ስራ አስኪያጅ የባለፈው እሁድ ሳምንት ከስርአት ቅዳሴው በኋላ ለምእመኑ ይፋ አድርጓል፡፡በእኔ አመለካከት በሰበካው ጥያቄ እንዲመጡ የተደረጉ አስተዳዳሪ፣ በሰበካው ሴራ የባረራሉ ብዮ አላስብም ምክንያቱም እንዲመጡ ጥያቄ ያቀረበው እራሱ ሰበካው በመሆኑ፡፡በእርግጥ የሁሉም ፈራጅና የልብ መርማሪ እግዚአብሄር ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ምዕመን ደገሞ በዙ የምንታዘበው ነገር አለ፡፡ አንድም ቀን ቆሞሱ የመንፈሳዊነት እይታ ታይቶባቸው አያውቅም፡፡ ባለፈው የደርባን ምዕመን ሊበተን ነውና ምሕላ እና ጸሎት ለምን እንዲደረግ አታደርጉም ብሎ የተወሰነ ምዕመን በግል ሲያናግራቸው የሰጡት ምላሽ ‘ሰውዬው(ጳጳሱ) የምን አድማ ነው የምታስደርገው ብሎ እንዲጮህብኝ ልታደርጉ ነው እንዴ?’ የሚል ነው፡፡ ለዚህ ነው ከላይ በተክርሰቲያኒቱ ውስጥ የሚመለከው እግዚአብሄር ሳይሆን ነገ ወደ አፈር የሚገባው ሰው ነው ለማለት የደፈርኩት፡፡

  ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት ብዙ በዙ ስለ ጳጳሱም ሆነ እሳቸው ስላመጧቸው ሰዎች መናገር ቢቻልም፣ አንባቢውን ከማሳዘን ውጪ ያንጻል ብይ ስለማላስብ ዝም ማለት ይሻላል፡፡ ነገር ግን የሚመለከተው አካል የህንን በደል ተመልክቶ እርምጃ ቢወስድ የተሸለ ይመስለኛል፡፡ ካልሆነ ደግሞ ክርስቶስ በደሙ ስለገዛት ቤተክርስቲያን ጉዳይ እሱ ባለቤቱ ይፍረድ፡፡ ሆኖም ግን የእግዚአብሄርን ትዕግስትና ምህረት ከሞኝነት ባንቆጥር መልካም ነው ባይ ነኝ፡፡

  እንግዲህ እግዚአብሄር ፊቱን ይመልስልን፣ይራራልንም ይቅርም ይበለን፡፡ እኔንም የማይገባኝን ከዘባረኩ ይቅር ይበለኝ፡፡አሜን፡፡

 8. bogale August 30, 2013 at 9:10 am Reply

  አስገራሚው ጉዳይ ደስታ ባለመመደቡ ምክንያት ኦርቶዶክሳዊ ብሎጎቻችን ጳጳስ እየሰደቡ የሚያወጡ ከሆነ ማንን እንዴት አድርገን ወደፊትስ ሌሎች እውነቶችን ማመን እንችላለን ፡፡ ውድ ሀራ ዎች በእጅጉ አክባሪያችሁና እናተ ምታወጡትን እውነትም የምደግፍ ነኝ ይሁንና በአቡነ ያዕቆብ ላይ ስለተከፈተው ዘመቻ ግን ማለት ምፈልገው ነገር ቢኖር ሱዳን ካርቱም ለሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ሰሎሞን ቶልቻ የተባለው ወይ ከትምህርት አልያም ከቡተ ክርስቲን ሞያ የእለት ውዳሴ ማርያም የማያውቀውና ባሌ ጎባ ሳለ በግብርና ቢሮ በጥበቃ ሰረተኝነት ሲሰራ የነበረ ሰው ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ የቅርስ ሃላፊ ሆኗል ; ሱዳን ሔዶ የደብሩ ዋና ጸሀፊ ለመሆንና ደስታን ደግሞ በሂሳብ ሹምነት ለመውሰድ ይስማማሉ ፡፡ ነገሩ ያላማረው ደስታ ማቅ በሚያውቃቸው ሰዎች አማካኝነት ስለሱዳን ሲያስጠና ሒሳብ ሹምና ጸሐፊ አንድ ሰው መሆናቸውን ይረዳና ቶልቻን ፈንግሎ የፓትርያሪኩ ልዩ ጸሐፊን በነተስፋዬ ዩፎ አማካኝነት በማስለመን ለመሔድ ሥር ጉድ የበዛል የፎርጅድ ውሳኔም ገሱዳን ያመጣል ቶልቻ ደግሞ ይህን ሲሰሰማ ደስታ መሃይምነው መቀደስ አይችልም ብሎ ማስወረጥ ይጀምራል በዚህ ሒደት ውስጥ አቡነ ያዕቆብ ወጥ ቀቃያቸውን ቄስ ግሩምን ሱዳንም ወጥ አንዲቀቅልላቸው እንደሆን እንጃ እርሱ እንዲመደብ ያቀርባሉ በዚህ ግዜ ደስታ የተለመደውን ፉከራ ፎክሮ በእናተ ብሎግ ስለፓጳሱ አጥፎ የሀሰት ወሬውን ጀመረ እውነቱ ይህ ነው ፡፡

 9. Anonymous August 30, 2013 at 2:06 pm Reply

  እባካችሁ እግዚአብሔር ከዚህ የጥፋት ማዕበል እንዲታደገን እንፀልይ፡፡ በጣም የሚያሳፍር ድርጊት ነው፡፡ ለነገሩ በእምነቱ ውስጥ የሌሉ ሰዎች ስለ እምነቱ ተቆርቋሪ ይሆናሉ ማለት ያስቸግራል፡፡ የነርሱ አላማ ቤተክርስቲያኒቱን ብዕል ተካፋፍለው ምዕመኑንም በትነው ሳይበቁ የተቀበሉትን ምንኩስና ጥለው ወደ ሚፈልጉት ዓለምና የምንፍቅና አዳራሽ መኮብለል ስለሆነ ዝም ከተባሉ እዚህ ሳይደርሱ አይቆሙም፡፡ ነገር ግን እኛ ባንችል እግዚአብሔር ክንዱን የነሳ ጊዜ እን ትቢያ ተነው ይጠፋሉ፡

 10. Anonymous September 3, 2013 at 2:22 pm Reply

  እጅግ የሚያሳዝነኝ የአንዳንድ የዋህ ምእመናን አስተያየት ነው።”እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጅህን አታንሳ” “እኛ ማን ነን” ወዘተ ይህ ለማን እና ለምን እንደተጠቀሰ የማያውቁ “ሰነፎች” ቤታቸው በእሳት ሲቀጣጠል አያዩ ለማጥፋት የማይሞክሩ አሊያም የድረሱልኝ ጩኸት የማያሰሙ የሰነፍ ሰነፎች,,,,,,,,,,,

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: