በአቡነ ያዕቆብ የአፍሪቃ አህጉረ ስብከት አስተዳደር ላይ የሚቀርበው አቤቱታ እየተጠናከረ ነው

 • በጥቅመኝነት ላይ የተመሠረተ የአገልጋዮች ምደባና ስምሪት፣ ለምእመናን ወቅታዊ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ አለመስጠት፣ በዕቅበተ እምነት ሊቀ ጳጳሱ ይታይባቸዋል የሚባለው ቸልተኝነት እና የጎጠኝነት ዝንባሌ በዋናነት ተጠቅሰዋል፡፡

*       *      *

 • ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሥራች አባል
  His Grace Abune Yacob

  ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ
  የአፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

  ለኾነችበት ለመላው አፍሪቃ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በቅርቡ በምክትል ፕሬዝዳንትነት መመረጣቸው ለውጭ ግንኙነታችን መልካም ዜና ነው፡፡ ከጉባኤው ዓላማና ዋና ዋና ተግባራት መካከል÷ አብያተ ክርስቲያናት የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት ማገዝ፣ በመካከላቸውም የባለሞያ ወይም የሰው ኃይል ተራድኦ እንዲኖር ማበረታታት፣ የጋራ ጥናትና ምርምር ማካሄድ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

 • አህጉር አቀፍ ጉባኤው ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ አገልግሎቷን እንድታጠናክርና በተስፋ በምትጠበቅበት የጥቁሩ ዓለም ዕውቅናዋን እንድታስፋፋ ዕድል የሚሰጥ ከፍተኛ መድረክም ነው፡፡ ለውጭ ግንኙነት መሠረት የኾነውንና ወሳኝ ሚና የሚጫወተውን የውስጥ አስተዳደር ጥንካሬ የሚጠቅሱ ወገኖች÷ ብፁዕነታቸው መንበረ ሊቀ ጵጵስናቸው በሚገኝበት በጆሐንስበርግ መድኃኔዓለም የተወሰኑና በሌሎች አህጉር (ሱዳን፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ) የሚገኙ አብያተ ክርስቲያንን በቅርበት እንደማይከታተሉ በመጥቀስ ክፉኛ ይተቿቸዋል፡፡
 • ሊቀ ጳጳሱ የአብያተ ክርስቲያኑን ተጨባጭ ኹኔታ ሳያገናዝቡ፣ የአብያተ ክርስቲያኑን አስተዳደርና ምእመናን ጥያቄ ችላ በማለት የሚያካሂዷቸው የአለቆች፣ ካህናትና ሰባክያነ ወንጌል ምደባና ስምሪት÷ ለክህነትና ስብከተ ወንጌል ሞያዊ ብቃት እንዲሁም ለቋንቋ ክህሎት ትኩረት የማይሰጥ በምትኩ የጥቅመኝነት ዝንባሌ የሚታይበት፣ የዝምድናና ጎጠኝነት ተጽዕኖ ያየለበት እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

*       *      *

 • በአገልጋዮች ምደባና ስምሪት በተፈጠረ ችግር ከመንበረ ሊቀ ጵጵስናው የተለየው የካርቱም ጻድቁ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን በራስ አገዝ አስተዳደር እየተመራ ነው፤ የአስተዳደር ሓላፊዎችን፣ ካህናትንና ሰባክያነ ወንጌል ስምሪትና ምደባ በራሱ እያካሄደ ነው፡፡
 • ከአህጉረ ስብከቱ ጋራ ያለውን ግንኙነት ያቋረጠው የካርቱም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ከመንበረ ፓትርያሪኩ ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነት እያደረገ ነው፡፡ ወደ አዲስ አበባ በተዘዋወሩት የቀድሞው አስተዳዳሪ ቦታ ይተኩ ዘንድ ሰበካ ጉባኤው ከካህናቱ ጋራ በአንድ ድምፅ በመወሰን ‹‹በሥነ ምግባራቸው፣ ዕውቀታቸው፣ የአገልግሎት ዘመናቸውና ብቃታቸው መርጫቸዋለኹ›› የሚላቸውን አባት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አለመቀበላቸው ነው የአለመግባባቱ መንሥኤ፡፡
 • እልቅናውን ከሚሹ ሌሎች ግለሰቦች እስከ ብር 47,000 እጅ መንሻ ቀርቦበታል ከተባለው ከዚህ ሹመት ጋራ ስማቸው ተያይዞ የሚነሣውና ለሊቀ ጳጳሱ ቅርበት ያላቸው ቀሲስ ግሩም ታዬ አንዱ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በመንበረ ፓትርያሪክ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር በአስጎብኚነት የሚሠሩት ቀሲስ ግሩም ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ ያስተሳሰራቸው የቀደመ ዕውቂያቸው ‹‹አጥማቂነታቸው›› መኾኑ ይነገራል፡፡
 • በ‹‹አጥማቂነት›› ስም በሚፈሟቸው ነውረኛ ተግባራት ክሥና ወቀሳ የቀረበባቸው ቀሲስ ግሩም ከዚህ ቀደም በድጋፍ ሰጭነትና በሓላፊነት ሲሠሩባቸው በቆዩዋቸው ቦታዎች (መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፣ ፈረንሳይ ኤምባሲ፣ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት) በሥራ አጋጣሚ በእጃቸውን የገባውን ገንዘብና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል እምነት ማጉደል ርምጃ ሲወሰድባቸው የቆዩ ናቸው፡፡
 • ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ጽ/ቤት ጋራ በቀጥታ እየተጻጻፈ የሚገኘው የካርቱም ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ያቀረበውን ማመልከቻ ማጤኑ የተነገረው በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ አለመግባባቱ በካህናቱና ምእመናኑ ጥያቄ መሠረት መፈታቱ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ወሳኝነት እንዳለው ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ጽፎታል በተባለው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡
 • በግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ርዳታ በሱዳን ካርቱም የተመሠረተው ቤተ ክርስቲያኑ ሁለንተናዊ አገልግሎቱን ለማጠናከር ት/ቤት ከፍቶ በሱዳን የሚወለዱ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት የሀገራቸውን ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ እንዲማሩ እየሠራ ይገኛል፡፡ የውጭ ግንኙነት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት የቀድሞው ፓትርያሪክ ባደረጉት ጥረት ደብሩ የሱዳን መንግሥትን ድጋፍ አግኝቷል፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ከቤተ ክርስቲያናችን ጋራ በቅርበት እንዲሠራ አድርገዋል፡፡

*       *      *

 • የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅድመ ክርስትና ዘመን አንሥቶ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የነበራትን የውጭ ግንኙነትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ታሪክ የሚከተለው የአፍሪቃ አህጉር እንቅስቃሴዋ ነው፡፡ መላዋ ኢትዮጵያ እንደ አንድ የቆብጥ ሀ/ስብከት ትቆጠር የነበረበት የ1600 ዓመት ሞግዚትነት ታሪክ የራስዋን መንበረ ፕትርክና በመቀዳጀት ካከተመ በኋላ ዓለም አቀፋዊ ልዕልናን ካገኘችባቸው 11 አህጉረ ስብከቷ አንዱ ነው – የአፍሪቃ አህጉረ ስብከት፡፡
 • በግንቦት ፳፻፫ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ በአንድ መንበረ ሊቀ ጵጵስና እንዲመራ በተደረገው የአፍሪቃ አህጉረ ስብከት አስተዳደር ውስጥ፣ በ፲፰፻፺፪ ዓ.ም የተጀመረው በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከፍተኛ ዕድገት በማሳየት ላይ እንዳለ ተዘግቧል፡፡
 • የሀገሪቱ መንግሥት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሰጠው ክብር ለቤተ ክርስቲያናችን ሰፋፊ መሬቶች  ተዋል፡፡ በጆሐንስበርግ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን 200 ተማሪዎችን የሚያስተናግድ ት/ቤት፣ በፕሪቶርያ ኪዳነ ምሕረት ከ100 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚረዳ የቤተ ክርስቲያኗ የትምህርት ተቋማት ተገንብተዋል፡፡ በብሎምፎንቴን ለኢትዮጵያውያንና ለደቡብ አፍሪቃ ተወላጆች የሚኾን የቅዱስ ያሬድ የካህናት ማሠልጠኛ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴና የቅዱስ ያሬድ ገዳም በ20,100 ካሬ ሜትር ስፍራ ላይ የተመሠረተ ሲኾን ለግንባታው ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አድባራትና ገዳማት ከት ሚልዮን ብር በላይ መለገሱ ተገልጧል፡፡

  South Africa Pretoria St Kidane Miheret Church

  Photo: Ethiopian Orthodox Tewahido Church South Africaa

 • ከአህጉረ ስብከቱ የአስተዳደር ችግሮች ጋራ ተያይዞ ስሙ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው በደቡብ አፍሪቃ የመንበረ ሊቀ ጵጵስናው ጸሐፊ በካቶሊካዊነት በስፋት ይታማል፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ሥርዐትንና ሥነ ምግባርን በማቃለል የሚታወቀው ጸሐፊው በሚፈጽመው አስተዳደራዊ ጫና [በደርባን ቅድስት ማርያም] የቤተ ክርስቲያን አንድነት ለአደጋ እየተጋለጠ መኾኑ ተነግሯል፡፡
 • በፕሪቶርያ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በተቀሰቀሰው ውዝግብ የደብሩ አስተዳዳሪ ከሓላፊነታቸው ለቀዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ ከሄዱ የሰነበቱት ሊቀ ጳጳሱ ለሦስት ወራት የዘለቀውን ይህንኑ ውዝግብ፣ ‹‹አስተዳዳሪውን ከምእመኑ በማስታረቅ እፈታዋለኹ›› ቢሉም ወደ ደብሩ በእልቅና ተመድበው ለመሄድ የጠየቁ አመልካቾች እስከ ብር 70,000 እጅ መንሻ መጠየቃቸውን በስሞታ መልክ ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡

*       *      *

 • የቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ ማንነት በሐዋርያዊ ተልእኮ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የውጭ ግንኘነቷ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን የምታስፈጽምበት አንድ መሣርያ ነው፡፡ በውጭ ግንኙነት ተልእኮዋ እንደ ጥንታዊነቷና ዓለም እንደሚጠብቃት ለመንቀሳቀስ ምእመናን በጎችን ሳይተኙ ነቅተው፣ ሳይሰንፉ ተግተው የሚጠብቁ፣ ባለርእይ የኾኑ፣ የውጩን ቋንቋ፣ ባህልና የኑሮ ዘይቤ በኦርቶዶክሳዊነት ሊዋጁ የሚችሉ አባቶችን፣ ካህናትንና ሰባክያነ ወንጌልን በመመደብ በብቃት ልታከናውን ይገባል፡፡
 • በዚህ ረገድ የውጭ ግንኙነት መምሪያው በሰው ኃይል ተጠናክሮና በበቂ በጀት እንዲደገፍ፣ በአፍሪቃ፣ በአውሮጳ፣ በአሜሪካና በሌሎችም አህጉር አገናኝ ዴስክ እንዲቋቋም፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን እንቅስቃሴ የሚዳስስ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋ የሚዘጋጅ ወርኃዊ መጽሔት እንዲጀመር ቅ/ሲኖዶስ በጥቅምት ፳፻፭ ዓ.ም ያስተላለፈውና አፈጻጸሙ በእጅጉ የዘገየው ውሳኔ በትውውቅ ከሚፈጸም ቅጥር በራቀ፣ ለሥራው ጥራት ከሚቆረቆርና ብቃት ላይ በተመሠረተ ጥንቃቄ ሊፈጸም ይገባል፡፡
 • በዘመናችን ዝርወት ማለትም ዲዮስጶራነት የትውልዱ ባህል ቢኾንም ቤተ ክርስቲያን ከቀዬአቸው፣ ከወገናቸውና ካደጉበት ባህል ርቀው በባዕዳን መካከል የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን በማረጋጋት፣ ኢትዮጵያውያኑንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑን በመልካም ሰብእናና በመንፈሳዊ ሕይወት በማነፅ የኖረችበትን የመሰብሰቢያ፣ የመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ማእከልነት ማጠናከር ያስፈልጋታል፡፡
 • ከዚህም ጋራ ለቤተ ክርስቲያናችን መስፋፋትበአህጉረ ስብከት ደረጃ መደራጀት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ምእመናን ጥያቄና አቤቱታ ተገቢው ትኩረት አግኝቶ ወቅታዊ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል – ቤተ ክርስቲያናችን በስደትም፣ በመከራም፣ በእስራትም ጊዜ ከመንጋው የማትለይና ስለሕዝቧ በነገር ሁሉ የምትቀድም መኾኑን የምታረጋግጥበት አጋጣሚ ነውና፡፡
Advertisements

36 thoughts on “በአቡነ ያዕቆብ የአፍሪቃ አህጉረ ስብከት አስተዳደር ላይ የሚቀርበው አቤቱታ እየተጠናከረ ነው

 1. tare August 25, 2013 at 9:02 pm Reply

  bemejemeria sile zenaw ameseginalew. Engidih yih zena yeteseraw abune yaekob be gilachew yazegajutin report teketilo yimeslegnal. Abune yaekob le teklay betekinet yakerebut report be fitsum be debub africa yelele, ena yaltesera neber. Lemisale pretoria lay yetebalew wushet new, johanesburg layim wushet new. enqwan timrt bet linkeft yikirena ye hisab audit enqwa endaysera esachew ye bank ferami, asgebi yehonubet hidet berasu eskahun yawezagibal. ke addis ababa 2 million birr yetebalew be fitsum wede botaw yaltelakem bich sayhon, ye blue fontein maseltegn yetebalew be sim bich desasa gojo teserto bezu tikim yasgegnelachew neber. Ye johanesbur ena pretoria be atekalay be debub africa yalewun yihudawi aserar mereja ke felegachu enakerbalen. beterefe amlak betekirstianin yitebik!

 2. tina, pretoria August 26, 2013 at 3:55 am Reply

  በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ አስተዳዳሪው ከካህኑ ሚስት ጋር በተያያዘ በምእመናኑ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነው የተባረሩት፡፡ የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ ግን መመለስ አለባቸው አለ፡፡ ሊቀ ጳጳሱም ሁኔታውን እየሰሙ ሌላ ሥራ አለብኝ ብለው ዝም አሉ፡፡ የአስተዳዳሪው መባረር ከቤተ ክርስቲያን ግዥ ጋር አይያያዝም፡፡ ከተገኘባቸው የምግባር ሕፀፅ ጋር እንጂ፡፡ ችግሩ በአስቸኳይ ካልተፈታ ፕሪቶርያ መገንጠል ወይም መከፋፈል የማይቀር ነው፡፡

 3. Gebre Kidan August 26, 2013 at 4:22 am Reply

  Selam Wondimoch. The current problem in Pretoria is not related to the purchasing process of the church. The church has been bought 4 years ago and it was the most peaceful spiritual place in South Africa till recently. It runs its own kindergarten to generate funds for the activity of the church. Please let’s all pray for restoration of peace to all our churches.

 4. Anonymous August 26, 2013 at 5:00 am Reply

  Mahibere Kidusanoch hulum gar lamasil alachu! Genezeb asabesachu! Endenante achberbari gubognas yinor yihon? lemayawkachu tatenu. Ene dawit yenante gubo akebabay aydelum ende? be 2000 bir demoz menoriya fok yemigeneba endenante ale? betekristianin yenigd bet yaregachu shekachoch!

 5. Anonymous August 26, 2013 at 11:11 am Reply

  ሐራ ስለ አቡነ ያዕቆብ ክስ አቀረበ ማለት፣ እርሳቸው ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ተቃቅረዋል ማለት ነው፡፡

  • tiblet August 27, 2013 at 12:16 am Reply

   mahibere seytan silu be joroye semichalew. tadiya min yidenkal…

 6. Anonymous August 26, 2013 at 4:19 pm Reply

  የማህበረ ቅዱሳን ጠላት እንደሆኑ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው

  • Anonymous August 27, 2013 at 6:50 am Reply

   ስለዚህ ከአንተ/አንቺ በፊት የሰጠሁት አስተያየት ትክክል ነው ማለት ነው፡፡ ዋናው መታወቅ ያለበት እርሳቸው የማኅበረ ቅዱሳን ጠላት ሳይሆኑ፣ የማኅበረ ቅዱሳንን እኩይ ሰይጣናዊ ድርጊት የማይደግፉ ናቸው ማለት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት እርሳቸው ትክክለኛው ኦርቶዶክሳዊ አባት ናቸው ማለት ነው፡፡ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያራዝምልን፡፡ እግዚአብሔር በፀጋውና በበረከቱ ይጠብቃቸው፡፡ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከማኅበረ ቅዱሳን እሥራት ያውጣልን፡፡ አሜን!!!

   • Anonymous August 27, 2013 at 10:15 pm

    ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ ቆዳ አንጥዠፉልኝ አለ”።የተባለው ነገር ነው የሆነብን የአባቶቻችን ነገር በደቡብ አፍሪካ

  • teshe August 29, 2013 at 6:42 am Reply

   mahiberu endehone ye egzer tat alebet. kersu gar mewagat ye michal aymeslegnim. bihonima abune yaekobina gibreaberochachew tint baferesut neber. egzer gin kelkelowachewal. ahunim egzer kalfelegew endalneber yaregewal. ante degmo akimihin awkeh menor teru new. gidgida betigefa tidekim kalehone besteker …

 7. Anonymous August 26, 2013 at 5:00 pm Reply

  abune yacob malet yebete kiristian nekeresa , minim aynet yeastedader chilota yelelachew ,hizbun eras berasu yemiyatalu , beyememenu bet silk eyedewelu sewn siyamu yemiweluna yemiyadru ejig lebetekiristyanachin yemayigebu sew nachew . egziyabher becherenetu yinkelilin amin. thank u hara tewahido.

 8. Anonymous August 26, 2013 at 5:06 pm Reply

  Yes, there are rumors that the general secretary of the diocese is not to the side of the church. Though the article has some facts what we need from Haratewahido is proof.

 9. Anonymous August 26, 2013 at 8:24 pm Reply

  ወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለ ምን ታያለህ፥ በራስህ ዓይን ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን። ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።
  የሉቃስ ወንጌል 6:41-42

  • Anonymous August 28, 2013 at 12:10 pm Reply

   ይህ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የሚደረግ ትግል እንጂ በሰው ከመፍረድ ጋር የሚይያያዝ ኃጢአት አይደለም። ስለዚህ ወንድሜ! ቤተ ክርስቲያን እንደተበደለችው አንተ ብትበደል ኖሮ እንዲህ እንደማትል እርግጥ ነው። እውነተኞች መስለው ከሚያዳክሙን አስመሳዯች ጌታ ይጠብቀን!!!

 10. wedajeneh August 27, 2013 at 12:15 am Reply

  yersachew chigir:
  1. zeregnnet ; yihim be kifu sinemigbar yetewawekutin ena yehagere yalutin be meyaz lelochin lemarak memoker. ezih lay lesew lij yalachew niket tikuret yashal. e.g yehagerachewun lij tsehafi adrgew shumew siyabeku huwala esir bet gebtowal
  2. be atmakinetachew ye memihr girma wendim nachew. debtirina awkalew betihin afersalew yemilew zacha le meimenan sineger mesmat tseyafi new
  3. genzeb mewded, eskahun ye sera enkifat yehonubet tiliku mikniyat kaznachew endaynetif new. e.g ke addis ababa adbarat yetelegesse genzeb be man audit tederege? hagersibketus meche new yeteklay betekinetun carni yemitekemew?
  4. ye rasin zina ena alawakinetin ke magulat balefe andim ken ewnet menager yemayhonilachew. ke ewnet gar yetetalu. tilikunim tinishunim mewashet, matalel, mamtatat
  5. memenin mekefafel, sewun besew maselel, ye silela mewakir maskemet. andu andun eyeselele report endiyaderg. yih le miemenim, le kahinatim new
  6. kidasewn, mahiletun, seatatun metlat. ye debtera new malet
  7. ye serate betekirstian ewket yelelew sew tenesto papas mehonu bezih zemen orthodox min yahil be aftim endetedefach misikir new
  8. ke betekirtian tikim yilik addis ababa balachew yaltegeba ginugninet ene gorfun yemeselu menafikan gar mewedajet, ekekegn likekekilih…
  9. arada lemehon weyim ye zihin zemen wetat mamognet weyim alibale mehon lesachew tilik dil new
  10. yanin libs lebso be tibit kemeweter balefe andim melkam astesaseb ena akuwam yelelachew
  sintu yizerezeral….yeferesewun betun egzer gin yitegnal..lesachewum ye ejachewun!!!

  • Anonymous August 28, 2013 at 6:18 am Reply

   ለወዳጄነህ
   ‘be atmakinetachew ye memihr girma wendim nachew. debtirina awkalew betihin afersalew yemilew zacha le meimenan sineger mesmat tseyafi new’ ምን ለማለት ነው፡፡ የመውጊያውን ብረት ብትመታ ለአንተው ይብስብሀል!!! ከአምስቱ ውሾች አንዱ ልትሆን እንደምትችል ገምት፡፡ አንተው የጠቋይና ደብተራ ተገልጋይ ሆነህ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚያገለግለውን ሰው ምላስህን ልታረዝምበት የምትሞክር አንተ ማን ነህ፡፡ ስለ መምህር ግርማ እንዳንተ ያለው የእርግማን ዘር ሊናገር የሕሊና ብቃቱ የለውም፡፡ አንተና መሰሎችህ ብዙ ብላችኋል፡፡ አሁን ሁለት ጽንፍ ላይ በክርስትና ስም የተቀመጥን ወገኖች እንዳለን ተረድተናል፡፡ ባለማወቅ ከሚያጠፉት ግን አውቀው ብዙ የራሳቸውን የጥፋት አባላት ለማብዛት የሚጥሩት በዝተዋል፡፡ ዛሬ ስለ መምህር ግርማ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይነት ለማወቅ የማይፈልጉት እንጂ ባለመረዳት በእሳቸው ላይ አንዳች ክፉ ለመናገር አቅም ያለው የለም፡፡ ሁሉንም በተግባርና በእውነተኛ ምስክርነት ስለሚያስተምሩት ትምህርት አእምሮው በትክክል የሚሰራ ሁሉ የሀይማኖትን ነገር ተረድቶታል፡፡ አንተ ራስህ የደብተራ ልጅ ሆነህ ውስጥህ እያስጨነቀህ መሰሎችን ለማፍራት አትዳክር፡፡ ከቻልክ ወደሕሊናህ ተመለስ፡፡ ሕሊናህን አትበድል፡፡ ሐጥያት ሁሉ ሊሰረይ ይችላል በሕሊናው ግን እምቢ ያለ እንዴት ሊድን ይችላል! ይሁዳ የጌታ ደቀመዘሙር እንደነበር አስተውል ጳውሎስ ደግሞ የጌታ አሳዳጅ፤ በቀኝ የተሰቀለው ሽፈታም ዘመኑን ሁሉ በዝርፊያና ሰው በመግደል ያሳለፈ እንደሆነም አስተውል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከመጀመሪያውም (አሳዳጅ ሆኖ ራሱ) ስለሕሊናው ነጻ እንደነበር አስተውል እውቀቱ ስህተት ነበር እንጂ፡፡ እውነቱን እንዲያውቅ አደርጎ ለራሱ አገልጋይ ያደረገው ስለሕሊናው ንፅህና እንደሆን አስተውል፡፡ ሽፍታውም ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሁዳ ግን የእነዚህ ተቃራኒ ነበር፡፡ ሌባ ነበርና፡፡ ሌባ ሰውን ያታለለ ይመስለዋል ግን መጀመሪያ ያታለለው ሕሊናውን ነው፡፡ ሕሊና ደግሞ የእግዚአብሔር እንደራሴ ነው፡፡ ሕሊናውን ያታለለ ንስሀ የለውም፡፡ በምን ይቅርታ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ስለ መምህር ግርማ ብዙ ብላችኋል፡፡ ቀደም ብሎ ብዙዎች ካለማወቅ ነበር አሁን ያላችሁት ግን የእርግማን ዘሮቹ እንደሆናችሁ እንገነዘባለን፡፡ አንተና መሰሎችህ በሰይጣን የመተትና የምትሐት አሰራር ታምናላችሁ የእግዚአብሔርን ኃይል ግን ክዳችኋል፡፡ የእርግማን ዘሮች!!!

   • teshe August 29, 2013 at 6:50 am

    amenzira tiwlid milikitin yishal. wendime be girma yemitamin kehone minew ke debub africa be tv yemitelalefewun ye fewus sereat (yawum bekal bicha, mekuteriya yelem) atamnachewum. pasterochim eko dink neger liyadergu yichilalu. ene yemamnew be orthodox haymanot dogma ena kenona enji, ende girma aynet bale mekuteriya aydelem. ayzoh yedank mesloh bezu awerah enji, bezu beshita new yegebabih. ende megdelawit mariya 7 sayhon 777 new ante lay yeseferebih. ye ato girma lij engidih min tihon? memhir? girma becha sayhonu, abune yaekob, kesis girma ..bezuwochu and aynet technology tetekamiwoch nachew. ante degmo yenersu seleba neh. egzer fewsun yilakilih. ye kifu tiwlid lij

   • Anonymous August 29, 2013 at 2:52 pm

    Wedaje/Teshe,

    First please use your name the same. I can trace same person using different name. Any way, that does not matter. I better know the secrete now. the reality is as I have mentioned to you in my above message. I find the Habesha land where the holy and curse live together. I exactly surface you where you are? Thanks to God now many of us able to discriminate the evil from the good! It happened only through Memehir Girma. He is the one who is unveiling the curse inside the Habesha land. True most Habesh Orthodox are practically not Christians. For example Gojam is statistically near even more than 90% nominally christian. Unfortunately, Gojam happened to be the most evil eyed, metetegna, miqegna and other practices of the devil. You can’t deny this! At least you hear ‘Gojame Buda’. That all is due to the exercises of the society towards evil spirit which mostly is by their Debtera. That is true for most other north Ethiopia which is said to be christian dominant too. In the south and other part the country is with dominance of other versions of devils usually witches, qalicha or other that looks traditions. This is the reality. Memehir Girma has enabled us to learn more deep. Forget about the healing he is doing? many are today doing by their own following his teachings! Believe or not that is the reality going on! We understand this has disturbed many others like you. In the near future you will find us even to confront the centuries years old confusions in science too. We have today hand full of evidences to withstand the wrong postulates and thoughts of the so called modern science particularly, the life science. You believe in Metet but not in power of God! That is your problem. I now know both! Your Debeteras Metet will have nothing to do on me here after! Thanks to Memehir, he showed us the unfolded power God which destroys all your Metets and other doings of your father, the devil. I don’t think you can teach me about the Dogma and canon a of Ethiopian Orthodox. ‘Amenzirana tiwlid milikitin yishal?’. Long ago I read bible but hardly had understood most part. Now I understand what I read. Know first why Jesus said that. And read in most other parts how people were believing in miracles. That too happened in His disciples. Quote not good words towards your hell! This has happened to be the way most so called orthodox preachers have so far been using to dread and confuse people. He God, Son God, Son of Holy Virgin Mary, Jesus Christos confirmed for those believes in Him those signs of the Holy Spirit to follow him/her. Among others are casting out devil, healing ills etc! We believe in GOD that is all!

 11. ማንነቴን የተቸኋቸው ሰዎች በሙሉ ያውቃሉ August 27, 2013 at 1:04 am Reply

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

  በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ቤተክርስቲያናት ላይ በግለሰቦች እየተሰራ ያለው በደል በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡
  ይህ ከዚህ በታች የምተነትነው መልዕክት በቀጥታ ለቤተክርስቲያንዋ እውነተኛ ተቆርቋሪዎች ይደርስ እንደሆነ አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው፡፡

  የማይታየውንና ሰማያዊውን ነገር መንፈስ ቅዱስ ይመርምር!!! የሚታየውንና በግልፅ የማውቀውን ግን በድፍረት ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ደህንነት ስል እመሰከራለሁ፡፡

  በደሉም በሰፊው እየተፈፀመ ያለው በአቡነ የዕቆብ እና በየአጥቢያው በየግል እውቅና ብቻ በመደቡዋቸው አስተዳዳሪዎች ነው፡፡
  ይህንን በደል እንዲያቆሙ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እውነተኛ ለቤተ ክርስቲያናችን የምንቀና ግለሰቦች ፊት ለፊት በግልፅ ልንመክራቸው ሞክረናል፡፡ እርሳቸው ግን በማን አለብኝነት የዋህና አባቶች አክባሪውን ህዝበ ክርስቲያን በማታለልና በመከፋፈል የክርስትና አንድነታችንን በሚፈታተን መልኩ እየበተኑን ነው፡፡

  ወደ ደቡብ አፍሪካ ተመድበው ሲመጡ ለነበሩበት መንበር ሰበካ አባላት ዕንቆቅልሽ በሆነ መልኩ ስብከተ ወንጌል እንዳይስፋፋ የነበረውም አሰራር እንዲዳከም አደረጉ፡፡ በመቀጠልም የማይገባቸውን “የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት” አስተዳዳሪነት ከፓትሪያርኩ ፅ/ቤት ተሰጥቶኛል የሚሉትን ደብዳቤ ይዘው መጥተው ለአገረ ስብከቱ ፅ/ቤት በማሳወቅ የጥፋት ዘመቻቸውን ጀመሩ፡፡

  በመጀመሪያ ለሌች አርአያ የነበረውንና ለሌችም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት መመስረት ከፍተኛ አስተወፅኦ ያበረከተውን የደርባንን ጉበኤ ከእናት ቤተ ክርስቲያን እንዲለይ አደረጉ ወይም እንደ አባት ያጠፋውን ክፍል ገስፀው መመለስ ሲችሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው አስካሁን መፍተሄ ሳይሰጡ ቆይተዋል፡፡

  በመቀጠልም በጆ/በርግ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለመግለፅ ለአእምሮ የሚከብድ ጥፋት ሲጠፋ እየሰሙ እንዳለሰማ እና “በሃላፊነት ብዛት ልፈታው ጊዜ የለኝም በማለት” እያደባበሱ መንበረ ጵጵስናቸውንም ችላ በማለት በሌሎች “የአህጉረ ስብከቱ” አባል አገሮች በተለያየ ቦታዎች “ ስራ እየሰራሁ ነው” በማለት በፅ/ቤታቸው ላለመገኘት ምክንያት እየሰጡ ነው፡፡

  በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተለያዩ ግንባታዎች አንዲካሄዱ አድርጌያለሁ ብለው የሰጡትን ሪፖርት በሚመለከት፡- አንድ እና አንድ ግልፅ ነው – የሚመለከተው የበላይ አካል መጥቶ ይመልከት፡፡ የተደረጉትም ጥቂት ልማቶች በጠንካራ የቤተ ክርስቲያኑ ምዕመን እንጂ በርሳቸው የአመራር ብቃት ወይም ፍላጎት አይደለም፡፡ አንዲያውም በተለያዩ አጋጣሚዎች ለግንባታ መሰናክል ሲሆኑ ነው የሚታዩት፡፡

  በመጨረሻም አሁን በፕሪቶሪያ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት የተፈጠረው ችግር ያልተፈታው እርሳቸውን በመጠባበቅ ነው፡፡ ከላይ አንደተገለፀው በየአጥቢያው የሚመደቡትን አስተዳዳሪዎች የሚመድቡት እርሳቸው ናቸው፡፡ እኝህም የችግሩ መንስዔ የሆኑት መነኩሴ የተመደቡት በርሳቸው ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ለሶስት ተከታታይ አመታት ደብሩን ያስተዳደሩት መነኩሴ ሰበካው ያወጣውን የአስተዳደርና ሌሎችንም የቅጥር መስፈርቶች ያላሟሉና ተመድበው ከመጡበት ጌዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ የደብሩ ካህናትንና ዲያቆናትን ጨምሮ በተለያዩ ግለሰቦች በምንፍቅና፣ በገንዘብ ማታለልና እንዲ ሁም በወሲብ ክሶች ሲከሰሱ የቆዩ ነበሩ፡፡ ሰበካው በመደበው ነዑስ ኮሚቴ ጉዳዩ ለረጅም ጊዜ ተመርምሮ በምንፍቅና እና በገንዘብ ማታለል የተከሰሱበትን በግልፅ ተነግሮአቸው እንዲታረሙ ተደርገው፤ በወሲብ ምክንያት የተከሰሱበትን ክስ ግን በቂ ማረጋገጫ ስላልተገኘ ውድቅ ሆኖ ነበር፡፡

  መነኩሴው “አሳቸው ናቸው አንጀራዬ” ብለው በግልፅ እየተናገሩ ለአቡነ የዕቆብ ወሬ አቀባይ ከመሆንና ሰበካውን ከምዕመኑ እና ከካህናት ጋር ከማጋጨት በስተቀር ምንም ለቤተ ክርስተያኑ የበረከቱት ነገር የለም፡፡
  በመጨረሻም ከደብሩ የተባረሩበት በግልፅ በተረጋገጠ የወሲብ ትንኮሳ ክስ ከሰበካው አባላት በተጨማሪ አስር ያህል ገለልተኛ መዕመናን በተገኙበት በሙሉ ድምፅ የተወሰነ ውሳኔ እርሳቸውም በወቅቱ አምነው የፈረሙበት ነው፡፡

  ……… ይህ ከላይ የተገለፀው ታሪክ ምናልባት አንደ ቤተ ክርስቲያናችን አሰራር ይቅር በመባባል እንዲሁም እንደተለመደው አንድ ደብር ያጠፋውን አስተዳዳሪ ወደ ሌላ ደብር መመደብ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሩ ግን ከዚህም በጣም የከፋ ገፅታ አለው፡-
  አሁን ጠቅላላ መስተዳደሩ ላይ ያለው አካል ላለንበት አገር (ደቡብ አፍሪካ) መንግስት ቤተ ክርስቲያንዋ የተሰጣትን አውቅና ላለማጣት ዓመታዊ የሂሳብና የተለያዩ ሪፖርቶችን ለሁለት የመንግስት አካላት (Social Development እና South African Revenue Service) ማቅረብ ግዴታ አለባት፡፡ ይህም ደግሞ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ፅ/ቤታችን “የመላው አፍሪካ አህጉረ ስብከት” ፅ/ቤት ተብሎ እስከተሰየመ ድረስ ፅ/ቤቱ ላለበት አገር ጠቅላላ የውስጡንም ሆነ የውጪውን በስሩ ያሉ አጥቢያ ቤተ/ክናት ገንዘብ ነክ የሆኑና ያልሆኑ የስራ እንቅስቃሴዎች ሪፖርት ማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን እንኳን የውጪውን አገራት የውስጡንና የመንበረ ጵጵስና ደብራቸውን የተሟላ ተቀባይነት የለው የሒሳብ አሰራር እንዲዘረጋ ጳጳሱ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

  ላለፉት ሁለት አመታት ለ Social Development እንዲሁም ለአራት ዓመታት ለ South African Revenue Service ሪፖርቶች ያልቀረቡ ሲሆን በቅርቡ የሚያስፈልገው ወሳኝ ስራ ካልተሰራ የተሰጠን ዕውቅና እንደሚነጠቅ እና ህዝበ ክርስቲያኑም እንደሚበተን አጠያያቂ አይደለም፡፡

  አንግዲህ ይህንን የሚያህል ኃላፊነት አደጋ ላይ ጥለው ነው አቡነ ያዕቆብ ለግል ጥቅማቸው/ስማቸው ብቻ ላይ ታች የሚሉት፡፡ የሚገርመው መንግስት ለኦዲት ቢመጣ ሌላው ይቅርና ላለፉት አምስት ዓመታት ከ50 000 ራንድ በላይ በግል የታክስ ዕዳ የመጀመሪያ ተጠያቂ የሚሆኑት አቡነ የእቆብ እና እንደማንኛውም ግለሰብ በስራ የመንግስት ፈቃድ እየታደሰላቸው የተመደቡት መሰሎቻቸው የየደብሩ አስተዳዳሪዎች ናቸው፡፡

  ይህ ነገር በግልፅ ቢነገራቸውም አቡነ ያዕቆብ አሻፈረኝ ብለዋል፡፡

  ቤ/ክ ስትበደል አይቶ ዝም ማለት ባለብን ጉድፍ ላይ ተጨማሪ ጉድፍ የመበተን ያህል ነው!

  እግዚአብሔር ተሰባስቦ ከመበተን ይጠብቀን!!!

 12. Anonymous August 27, 2013 at 6:04 am Reply

  አኔ የምለው ይህን ያህል በሊቀ ጳጳሳትና ሰባክያን ላይ የጥፋ መዓት ስታወርዱ “እኛ ንጹህ ነን” እያላችሁ ነው ማለት ነው፤ ሌላው ቢቀር እንዲህ ብላችሁ በመጻፋችሁ ብቻ ማለት የአባቶቻችንን ድካም ባለመደበቃችሁ አደባባይ ላይ በማውራታችሁ ጥፋ አለባችሁ፡፡ “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ” አይደል የሚለው መጽሐፉ፡፡ እንደ እኔ እንደ እኔ እነርሱ በእዚህ ምንም አይጎዱም ግን ጽሑፋችሁን የሚያነብ ሰው ግን ለቤተ ክርስቲያኑ እኩል መረዳት ሰለሌለው የማይጠቅመውን ነገር በመስማቱ ተጎጂ ነው ባይ ነኝ፡፡
  ልብ ይስጣችሁ!

 13. Anonymous August 27, 2013 at 8:54 am Reply

  yasazenal manen enemen tadiya?

 14. Anonymous August 27, 2013 at 11:45 am Reply

  በስመ አብ፣ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን!

  ውድ ሐራዎች በደቡብ አፍሪቃ ስላለው ችግር ያቀረባችሁት አጠር ያለ ዘገባና ያለውን መንፈሳዊ ቀውስና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እናንተ ካላችሁትም በላይ ነው፡፡ ይህ ችግር ደግሞ በተናጠል በደቡብ አፍሪካ ወይም በአፍሪካ አህጉረ ስብከት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ጥንታዊቷና ሐዋርያዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ወይም ከዓመት ወደ ዓመት እየተባባሰ የሔደውን ችግሮቿና ቀውሶቿ መገለጫዎች ይመስሉኛል፡፡ በአውሮጳ፣ በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያ፣ በካናዳና በካረቢያንም እንደየኹኔታው ችግሮች አሉ፡፡ ለዘመናት የጥቁር ሕዝቦች ተስፋና የከነዓን ምድር ተደርጋ የምትታየው ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአፍሪካ፣ በመላው ጥቁር ሕዝቦችና በተቀረው ዓለም ያላትን ታሪካዊ ቦታ የሚገባትን ያህል ጠብቃ ለማስቀጠል እንዳልቻለች እሙን ነው፡፡

  ለዚህ ደግሞ ከሐዋርያት የተቀበለችውን ወንጌል፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን የአምልኮ ሥርዓቷን፣ ትውፊቶቿን፣ ዜማዎቿንና ቅርሶቿ ለአፍሪካ ሕዝቦችና ለመላው ዓለም በማዳረስ ረገድ በፍቅርና በሰቀቀን እጆቿን ዘርግተው ይጠብቋት የነበረውን ያህል፣ ሐዋርያዊቷና ጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን እጆቿን ዘርግተው ለሚጠብቋት ሕዝቦች ለመድረስ አልቻለችም፡፡ እናም የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለበት ደረጃ ከሚጠበቀው በታች መሆኑን ምሥክር መቁጠር የሚያሻ አይመስለኝም፡፡

  ቤተ ክርስቲያኒቱ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያላትን ረጅምና ታሪካዊ ግንኙነት መሠረት በማድረግ ብዙ ሥራ መሥራት የሚቻልበት ዕድል ቢኖርም ለዚህ ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ራሳቸውን የሠጡ፣ ባለ ርእይና ብቁ የሆኑ አባቶችና አገልጋዮችን ግን በስፋትና በብቃት ማግኘት ወይም ማምረት እንዳልተቻለ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገር ውስጥም ኾነ በውጭ አገር እየተባባሱ ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ ኁልቆ መሣፍርት ሌላቸው ችግሮቿና ቀውሶቿ እየጠቆሙ ናቸው፡፡

  ስለሆነም በቤተ ክርስቲያኒቱ ባሉ አገልጋዮች ዘንድ ያለው ባለ ርእይ ያለመሆን፣ የመንፈሳዊ ሕይወት እጦት ድርቅ መመታት፣ በአገልጋዮች ዘንድ ያለው ብቁ የኾነ የመንፈሳዊ እውቀት እጦትና ከፍተኛ የኾነ የቋንቋ ችግር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፋዊና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ትልቅ መሰናክል መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ይመስለኛል፡፡ የሚበዙት አገልጋዮቻችን የምዕራቡን ዓለም የኑሮና ሕይወት ዘይቤ ናፋቂዎች እንጂ የአገራቸውን ታሪክ፣ ቅርስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንታዊ አስተምህሮና ትውፊት ከዘመኑ ጋር በማቀናጀት ያላቸውን መንፈሳዊ ሀብትና ግዙፍ ታሪክ በማስተማር ሌሎችን ለመማረክ እውቀቱ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱም በእጅጉ የሚያንሳቸው መኾኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

  ከዚህም የተነሣ የአንዳንድ አገልጋዮችን የመጨረሻ ዕድገትም መስሎ የሚታያቸው ምዕራባዊነትንና የጵሮቴስታንት አስተምህሮንና ቅራቅንቦን ማስተናገድ፣ በዘመናዊነት ስም ታሪካቸውን ማጣጣልና የማንነት ቀውስ ውስጥ መዘፈቅ እየኾነ እንደመጣ እየታዘብን ነው፡፡ እናም መንፈሳዊ ፍቅር፣ ትሕትና፣ የጸሎትና የአርምሞ ሕይወት በአገልጋዮቻችን መዝገበ ቃላት ውስጥ ቀስ በቀስ እየተፋቁ እየሔዱ ናቸው ናቸው፡፡

  ብቸኛና አንድ ለእናቱ የኾነው የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ኮሌጅም ከሃምሳ ዓመታት በኋላ እንኳን ደረጃውን የጠበቀ የሥነ መለኮት ዩኒቨርስቲነትና የምርምርና የልቀት ማዕከልነት ወደ መኾን ማደግ የሚችልበት መንገዶቹ ሸካራና ጎርበጥባጣ እየኾኑበት፣ ጉዞው የዔሊ ጉዞ እንደኾነበት የዛን ሰሞኑ አስጥ አገባ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

  የቤተ ክርስቲያን ጠባቂና አጽናኝ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!! አሜን!!!

 15. Anonymous August 27, 2013 at 6:37 pm Reply

  Harawoch endemin keremachhu bergit hulachnim ye rasachin bizu hatyat alebn bihonm gin enkwan ke 1 ye Africa papas ke 1 mimen yemanayewun yesinemigbar bilishunet new yayenew yesemanew 7 ametachn ke Abune yakob gar yenornew fitsum menfesawinet yetefabachew ushetam asmesay mikir yemaysemu le mimenan yemayasibu be musina na bewushet siltan yagegnu be south Africa mimenan yekeledubet achberbary abat nachew tenkuay debtera ekuy abat nachew mahbere kidusanin mahbere seitan silu bejoroye semichalew Amlak bemiawkew ene mahbere kidusan hogne aydelem neger gin ye betekiristian lig yehone mahberun endih yale sim aysetewm menfesawinetu min yahil endetefabachew yamelekital ke erkebe kahnat bewala 4 wer mulu Be Mariam Addis Abeba min yiseralu ye Africa like papas teblew hageresibketachew ezih new enih sew alamachew min endehone aytawekim lelaw ewnet new yemilachhu ezih medhaniyalem betekiristian Johansburg papasm honew eske kirb gize ye atbia betekirisian ferami neberu be kirb new 3-4 wer keferaminet ye lekekut silesachew biwera ayalikim Amlak ewnetegna Abatochn yassnesalin lib yistachew yikoyen

  • Anonymous August 28, 2013 at 7:07 am Reply

   ማንነቴን የተቸኋቸው ሰዎች በሙሉ ያውቃሉ, G*** and many of the anonymous posts here are from same person who would like to trigger things on purpose. I also realized in many of the other posts you are the one who is flooding much raising completely opposite views. Please that is not ethical! Stop doing that! This is gambling!

   • welete mariam August 29, 2013 at 8:22 pm

    So it means that you are one of those the commenter has criticized! thank u for exposing urself…….

    and it woowed me you talking about ethics! this is not politics or game…this is about religion, about someone’s identity. No matter how long it takes, God will pass His judgment. Lets pray to be forgiven!

 16. durban August 27, 2013 at 8:43 pm Reply

  Sile Betsuentachew yametsafew taganene beya masab yekebedagnal. meknyatum egna beDederban yalenew memenan seleteftsemben bedel tenagren anchersewum. Be Debub Sudan enedehum Keneya lederes yemechlewn asebu. Yehn hulu eyesemu zem malet beBetekrstiyan lay telat mehon new.

 17. gudukasagojam August 28, 2013 at 3:42 pm Reply

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱሰ አሃዱ ምላከ
  አሜን፤፤

  በመጀመርያ ይህን ጽሑፍ አቀናብራችሁ ውሸትም ቢሆንም ቅሉ ላቀረባችሁልን ለማህበረ ቅዱሳንና ለደብሩ ስበካ ጉባኤ አባላቶች ከልብ እናመሰግናለን፤፤
  በመቀጠል ‹‹የዓሣ ግማቱ ከኣናቱ ››እንዲሉ የሊቀጳጳሱ ነገር ተነግሮ አያልቅም ለምሳሌ ካለባቸው መጥፎ ስነ ምግባር እንደ እስስት ጠባይን መቀያየር ውሸታምነት ዘረኝነት የተማረ ሰውን አለመውደድ እኔ አቃለሁ ማለት በአጠቃላይ የትምህርትና የአስተዳደር ብቃት ማነስ ብዙ ሙሁራን ካህናት ጊዚያቸው ስውተው የወሰኑትን ውሳኔ በተልካሻ ምክንያት ማፍረስ በቅርቡ ደርባን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ምዕመናኑ ለ3 ወር ያህል መፍትሄ አጥተውከ600ኪሎሜትር በላይ ተጉዘው ተንከራትተው ሲመጡ እሳቸው ግን ቤታቸው ተኝተው ከባለስልጣናት ጋር ስብሰባ ነኝ አይመቸኝም ….እያሉ ሲያጉላሉዋቸው መፍትሄ አጥተው ከእናት ቤተክርስቲያን ተገንጥሉ ፤፤ ይህ ሁሉ የሳቸው ስራ መሆኑ ኢያወቁ ና እየሰሙ ማህበረ ቅዱሳን ግን እነሱ ስላልተነኩ ብቻ ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው ጸጥ ብለው ከርመዋል፤፤
  አሁን ግን በማህበረ ቅዱሳን ጉርፕ ሲመራ የነበረውን የሃመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነምህረት ቡተከርስቲያን ሰበካ ጉባኤው ህዝቡ በተደጋጋሚ የሂሳብ ሪፖርት አቅርቡልን ሲላቸው በገንዘብ ጉድለት ምክንያት ባለማቅረባቸው የትምህርት ማነስና የፖለቲካና የስልጣን ጥመኝነት ስላላቸው እንዲውርዱልን ስላሉ አስተዳዳሪውም በእሁድ ቀን ለህዝቡ ግልጽ ድርገው አናውንስ ስላደረጉ ማክሰኞ ሰበካጉባኤውና ማህበረቅዱሳን ሆን ብለው ተቀናጅተውበምነኩሴው ላይ ድራማ ስሩ ድራመውም አነሱ በየጥጉ ተደብቀው ቅድሚያ ተደርጎ የማያውቅ በቤተክርስቲየንዋ ላይ ትልቅ ድፍረት ፖሊስና ጋዜጠኛ አዘጋጅተው ሴት ቤታቸው ገብታ እንድትጮህ አድርጉ ለአስተዳዳሬው አናሳስረዎታለን ዲፖርት እናደርገዎታለን ብለው በማስፈራራትና በማስገደድ ራሳቸው በውሸት ያቀናበሩት ደብዳቤ እንዲፈርሙ አድረግዋቸው ፤፤
  ለምን ቢባል ትልቁ ምስጢር 1ኛ የማህበሩ ጥቅማ ጥቅም ስለተነካ በየጊዜው ከደብሩ ያለ አግባብ የሚዛቅና የሚሰጣቸው ብር ሊቀርባቸው ነው፤
  2ኛ ስበካ ጉባኤዎቹ በቂ የሆነ የራሳቸው ገቢ የሌላቸው ከመሁኑም በላይ በየጊዜው በጸባይና በደብሩ ገንዘብ ጉድለት የሚታሙ ስለሆኑ ከሰበካ ጉባኤ ከወረዱ ከሙዳየ ምጽዋት ውጪ ምንም አይነት ገቢ ስለሌላቸው እንደ ርስት ጉልት መውረድ አይፈልጉም፤፤ ምስጢሩ ይሄው ብቻ ነው፤፤፤፤፤፤

  • welete mariam August 29, 2013 at 8:54 pm Reply

   2ኛ ስበካ ጉባኤዎቹ በቂ የሆነ የራሳቸው ገቢ የሌላቸው ከመሁኑም በላይ በየጊዜው በጸባይና በደብሩ ገንዘብ ጉድለት የሚታሙ ስለሆኑ ከሰበካ ጉባኤ ከወረዱ ከሙዳየ ምጽዋት ውጪ ምንም አይነት ገቢ ስለሌላቸው እንደ ርስት ጉልት መውረድ አይፈልጉም፤፤ ምስጢሩ ይሄው ብቻ ነው፤፤፤፤፤፤

   shame on you that you said this! I do respect your opinion though. however, I don’t think you know any thing about our church and its management. do you have any idea who the members are? I also am not their representative but let the Lord give them their reward! i dont think they serve the church to be honored by u or any flesh being. so let Him forgive u for what you just have said and help His people to calm down and worship Him without these whole mess!

 18. gudukasagojam August 28, 2013 at 4:39 pm Reply

  ምዕመናን የደቡብ አፍሪካ ጸሐፊ ማህበረ ቅዱሳን ለምን በእምነት ነቀፉት
  ብንል በእውቀት ስለሚበልጣቸው ክፍ ስነ ምግባራቸው ስላወቃቸውና በአስተዳደር ላይ አላሳልፍ ስላላቸው ነው ብዙ ጊዜ አነሱን የነኩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተሃድሶ መናፍቅ ሌላም ብዙ ነገር ተብለው ተገፍተው ተንካራትተዋል አሁንም ይህም ጸሐፊ ትልቁ ጥፋቱ ብሔሩ ደቡባ ህዝብ/ሆሳእና/ስለሆነ ነው በእውነት ከደቡብ ክርስቲያን አይወጣም እንዴ

  • ማንነቴን የተቸኋቸው ሰዎች በሙሉ ያውቃሉ August 29, 2013 at 9:43 am Reply

   ወንድሜ ያላየኸውን አትተች፡፡ እውነተኛ አማኝ ክርስቲያን ከሆንክ ፍርዱን የምንወቅሳቸውን አባቶቻችንን፣ አንተን እና እኔንም አይቶ ለሚፈርደው አምላክ ተወው! ብትችል የበላይ አካል ባለው ስልጣን መጥቶ ሁሉን መርምሮ እንዲዳኝ ብሶትህን አሰማ፡፡ ያለው ውዥንብር በሰላም እንዲፈታ ፀሎት እናድርግ!

  • Anonymous August 29, 2013 at 9:54 am Reply

   የተበዳይዋ ሴት ባለቤት ካህንም ቤተ ክርስቲያንዋን ከ7 ኣመት በላይ ያገለገሉ የደቡብ ሰው ናቸው፡፡

  • welete mariam August 29, 2013 at 8:41 pm Reply

   @gudukasagojam,

   well about the secretary of the diocese, 1st he is studying at the expense of the humble congregants. it is us who pay for his college. so if we were jealous of his level of education, we would never have allow the church to sponsor for his PHD or whatever. 2nd, in the House of God, we all are equal, no intellectual, no slave or lord. we all are sinners and almost invisible. As a result, being an intellectual, if he really is, not a criteria for salivation. don’t fool yourself….
   3rd you don’t need to be his agent to witness his leadership skill, let the congregants of Durban and people from his birth place talk about him….and of all, he knows why he is here…just to finish his education at any cost! let God judge him again.
   Any way, don’t try to change the subject, we are talking about the problem of the church and how to solve it. let the Almighty protect our churches.

 19. Anonymous August 30, 2013 at 7:59 pm Reply

  እውነት እንነጋገር ከተባለ ሲጀመር የቄስ ሚስት ምን ልታረግ መነኩሴ ቤት ትገባለች ሌላው የአንድ የካህን ሚስት አለባበሷን ማስተካከል አለባት የሧ ግን ክዚህ የተለየ ነው ይሄ ነገር ራሱ የተቀነባበረ ይመስላል

 20. Anonymous August 31, 2013 at 10:18 am Reply

  ha ha yepretoryaw yetekenebabere new yalkew asafari sew neh . ayzoh nege yante mist weym ehitih lay simeta tichohaleh. ayzoh yegziyabeher gize dersowal eyendandu astedadare eyetegalete new. hulum yikir yedebub africa zegenet yalachew kahinat lemindenew yihn yahil kitat yemidersebachew .they have been fought for 100 years to join our church and lerarn more since abayacob came in this country they didn’t get any lesson about 7 years still they are crying . but we remebere when the church stablished abune petros brought 4 teachers to teach them about 7 month ,at least he did something .but when we compare the current bishop aba yacob he make them cry why?any one who conform this u can ask them and they will tell u and last time they had written a ltter to head office and they are waiting for the answer . silezih ebakwo aba yakob chilotaw yelotim kezih bota yihidu yecoptic betekiristyanin enkwan aytew aykenum daru gin erso were bicha new yemichilut kesati menafik , yewengel telat , mekedes yemayichil mebarek yemayichil yeaganint maderya ,egzyabher yinkelew yerson menfes kezih bota .

 21. Anonymous September 5, 2013 at 9:08 pm Reply

  hulachehum menafican nachew anteh man hone new sile abun yakob yemetaweraw,yerasehen gemena debekeh sele batekersiteian(sele abatoch)yemetawera laba hula yegezehabehar genezeb ayegegnem zeme belehe meregem belyelay tekemeraleh.

 22. Anonymous September 30, 2014 at 10:26 am Reply

  አባታችን ቡራኬዎት ይድረሰን ከጉልላት ቤተሰብ (እሙሽ)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: