‹‹የአቡነ ጳውሎስ ፋውንዴሽን›› ለማቋቋም ታስቧል

 • የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዐት ነገ ይካሄዳል
 • የቤተዎቻቸውንብረት ይገባናል ጥያቄ ውሳኔ አላገኘም
 • 1.5 ሚልዮን ብር ጨረታ የተሰጠ የመቃብር ሐውልታቸው አልተሠራም
 • ለ፳ ዓመት በዓለ ሢመታቸው “የካንሰር፣ ቲቢና ኤድስ የሕክምናና ማገገሚያ ማእከል” ግንባታን እንደ ስጦታ ያበረከተው ‹‹ራእይ ለትውልድ›› እና በዓል አድማቂዎቹ ‹‹ዉሉደ ጳውሎስ›› የት ናቸው?

The Late Patriarch Abune Paulos 1st Anniv.

አምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ነገ፣ ነሐሴ ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በማሕሌት፣ በጸሎተ ፍትሐት እና በቅዳሴ ታስቦ ይውላል፡፡

በመታሰቢያ ሥነ ሥርዐቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና መዘምራን እንደሚገኙ ተገልጧል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “‹‹የአቡነ ጳውሎስ ፋውንዴሽን›› ለማቋቋም ታስቧል

 1. Anonymous August 16, 2013 at 3:20 pm Reply

  ለዘመናት ቤተክርስቲያንን ሲያጠፉና ሲበድሉ የኖሩ ሰው በቤተክርስቲያን ወጪ ምን የሚሉት መታሰቢያ ነው የሚደረግላቸው?ከግራኝ መሐመድና ከ ዮዲት ጉዲት በምን ይለያሉ ?መታሰቢያ የሚደረግለት እኮ መልካም ለሰራ ነው የሰራውን መልካም ነገር እያሰብን የተሻለ ለመስራት እሳቸው እኮ ቤተክርስቲያንን ያጠፉ ምዕመናንን ያስገደሉ የቤተክርስቲያንን ክብር ያዋረዱ መናፈቃንን አስርገው በማስገባት ለመበታተን የሞከሩ ቤተክርስቲያንን ለሁለት እንዲከፈል ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ (ውጭ ያሉት በ ጥፋታቸው ተባባሪ መሆናቸው ሳይረሳ ) ገዳማትን በዕቅድ ታስቦበት እንዲጠፉ ያደረጉ …እረ ስንቱ

  ከጠላት ዲያብሎስ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ ::አሁን ያሉትን አባቶቻችንን በ ሃይማኖታቸው ጠንካራ ሆነው ለቤተክርስቲያን መብት የሚሟገቱ ለእምነታቸው የሚሞቱ ያድርግልን ::

 2. Aba Gerima August 30, 2013 at 8:48 am Reply

  የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ፡- በፌስ ቡክ፣ በትዊተር… ‹‹የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ተከታዮች ነን›› የሚሉ የተለያዩ ቅዱሳንን ‹‹ፎቶግራፍ›› የለጠፉ ብዙ ‹‹ወዳጆችና›› ‹‹ተከታዮች›› ያላቸው የሚመስሉ የ‹‹ነፍስ አባት፣ ቄስ፣ ጳጳስ፣ ፓትርያርክ፣ ሐዋርያ፣ ነቢይ፣ ሰማዕት፣ ጻድቅ›› መሆን የሚዳዳቸው ሰዎችን መመልከታችን የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡
  ይህን ተከትሎም ክርስቲያናዊ አስተምህሮን፣ ኦርቶዶክሳዊ ትውፊትን፣ ኢትዮጵያዊ ባሕልን የሚቃረኑ ነገርን፣ ሁናቴን፣ ታሪክን በርጋታ፣ በትዕግሥትና በክርስቲያናዊነት ከመገምገም ይልቅ ፈራጅነት (ትንሽነት፣ አባካኝነት፣ …) ባለበት አካሄዳቸው የተነሳ ሌላውን የሚያረጋጋ፣ ፍቅርና ትሕትናን የተላበሰ መልእክት ለማስተላለፍ የተሳናቸው ደፋር የዕውር መሪዎች ቁጥራቸው ጥቂት አለመሆኑን ስንመለከት – ክርስቲያን ስለ መሆናቸው ጥያቄ እንድናነሳ ያስገድደናል፡፡
  እነዚህ ሰዎች ዳዊትን የኦርዮን ደም አፍስሰሃል፣ በላዔ ሰብን ሰባ ነፍስ ፈጅተሃል፣ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ስለ ሰይጣን ምሕረት እንዲደረግ ጸሎት አቅርበሻል ብለው የፈራጁን ወንበር ፈንግለው ዳኝነቱን በመንጠቅ ፍርድ የሚለዋውጡ ‹‹የራሳችንን ኃጢአት በንስሐ የወንድሞቻችንንም በትዕግሥት የማንሸፍን›› – ነገር ግን ‹‹በጎች ጻድቃን›› ነን ማለት የሚደፍር ግሳት ያላቸው ሆነው የሚታዩ ናቸው፡፡ ይህም የክርስትና ሃይማኖትን ረቂቅ የእግዚአብሔር ስጦታነት የሚቃረን አካሄድ ከመሆንም በላይ – እንደ ይሁዳ አባት ይህ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተቀምጧል ብሎ ስለ ተተኪዎቻቸው ለመተንበይም የሚያደፋፍር ነው፡፡
  ይህን ለማለት ያነሳሳኝ ሃይማኖቴን ወደ ጠባቡ መንደርተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ምን ሰብሳቢነት ነው የሚባለው መንገድ ያስገባ የሚመስለው ‹‹የኦርቶዶክስ አርበኞች፣ የማርያም ወዳጆች፣ …›› ባይ ዓይነት ሰዎች የሽሙጥ አካሄድ ነው፡፡
  ለምሳሌ የአቡነ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ ‹‹ሐውልት ተሠራ፣ ቢዮንሴ መጣች፣ መንግሥትን ደገፉ፣ ባሕታዊ ተገደለ…›› ባይ ጩኸትን ከሰፈራቸው ሲያሰሙ የዚያው የሰፈራቸው ገደል ማሚቶ ወደ አቡነ ባስልዮስ ሐውልት፣ ተፈራርመው ወዳስገደሏቸው የአቡነ ቴዎፍሎስ አጽም፣ ባሕታዊው ወደ ያዘው ጎራዴ አስተጋብቶ እንደሚያሰማባቸው የዘነጋ የ‹‹አቡነ ያሬድ ፕሮቴስታንት ሆኑ›› ዓይነት ጩኸት ያስጮሃል፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ‹‹ሰውነት›› ክርክር እንዲነሳ የምጋብዝ አይደለሁም፤ ፍጹም ጻድቅም ፍጹም ኃጥእም ያልሆኑ ስለ ኃጢአታቸው ያስቀደሱት ቅዳሴ፣ የጸለዩት ጸሎት፣ የጾሙት ጾም ምሕረት ያሰጣቸዋል ብዬ ከማመን ባለፈ ለአገልግሎት በተቀበሉት ኃላፊነት ያለፉበትን መንገድ መንቀፍም መደገፍም ገደብ ሊኖረው ይገባል የምል ነኝ፤ ሁሉን ያደረጉበት ምክንያት ይነፐራቸዋልና፡፡ ስለ አቡነ ሲኖዳ ያለኝም አስተያየት እንዲሁ ነውና፡፡ አቡነ ሲኖዳ – የሁስኒ ሙባረክ ቀንደኛ ደጋፊ በመሆናቸው በብዙዎች የኮፕት(ቅብጥ) ክርስቲያኖች (በተለይ በወጣቶቹ) ሲወገዙ፣ ጋብቻን አስመልክቶ ከሃይማኖት በወጣ መልኩ ያሳዩት አቋም ሚዛኑን ሳይስት እንደ አባትነታቸው በጎው ጎናቸው ጎልቶ ድካማቸው ለእርሳቸው፣ ለእግዚአብሔርና ለምንጸልይላቸው ጸሎት ተትቶ መሆኑ ከአንዳንድ የሀገሬ ክርስቲያኖች የተሰለበ መሆኑ አካሄዶቻችን አሁንም ክርስቲያንና ኦርቶዶክሳዊ አለመሆናቸውን የሚያሳብቅ ነው፡፡ አቡነ ሲኖዳ ድካም ቢኖርባቸውም ትናጋችን እስኪጣበቅ ስለድካማቸው አንጽፍም፣ አናዋርዳቸውም፣ አንከሳቸውምም… ክርስቲኖች – ኦርቶዶክሳውያን ነንና.. እስኪ ለማንኛውም እነዚህን ገጾች ተመልከቱልኝ፡-
  http://english.ahram.org.eg/NewsContent/1/64/5097/Egypt/Politics-/Pope-Shenouda-III-supports-Mubarak,-Egyptian-state.aspx
  http://search.wikileaks.org/gifiles/?viewemailid=1910637
  http://search.wikileaks.org/gifiles/?viewemailid=156141
  http://search.wikileaks.org/gifiles/?viewemailid=1909583
  http://www.wikileaks.org/plusd/cables/05CAIRO2722_a.html
  ታዲያ ዓይናችንን ውበትን ለማድነቅ እንጂ ለወቀሳ፣ ለክስ፣ ለፍርድ… ወዘተ መጠቀሙ ከማስወቀስ ያለፈ ፋይዳ የለውምና ከየገጻችሁ ላይ ይኸን መሰል ነውር እያነሳችሁ የሚያንጸውን ብትሰቅሉበት ይሻላል ስል የወደዳችሁትን ማድረጋችሁ በምላሹ ማንነታችሁን የሚያሳይ መነጽር ከመሆን ያለፈ ፈይዳ እንደሌለው ከማስታወስ ጋር ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: