ሰበር ዜና – የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የ14 አድባራት አስተዳዳሪዎችን ከሓላፊነት አነሣ

 • ዐሥራ አንዱ የተነሡት በዝውውር ነው፤ ቀሪዎቹ ሦስቱ ከአስተዳዳር ሥራ ውጭ ተደርገዋል
 • ከአስተዳደር ሥራ ውጭ ከተደረጉት ውስጥ የደ/ጽጌ ቅ/ዑራኤል እና የደ/ሰላም ቅ/እስጢፋኖስ አስተዳዳሪዎች ይገኙበታል

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶስ ቀርቦ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት ሙስናና ብልሹ አሠራር የገነገነባቸውን፣ የካህናትና ምእመናን አቤቱታ የበረታባቸውን የ14 አድባራት አስተዳዳሪዎች የማዘዋወር፣ ከአስተዳዳሪነት ሓላፊነት የማራቅ እና በጡረታ የማግለል ርምጃ መውሰዱ ተገለጸ፡፡

የአስተዳዳሪዎች ዝውውር የተካሄደባቸው አድባራት፡- የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የደብረ ነጎድጓ ቅዱስ ዮሐንስ፣ የደብረ ሰላም ቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ የደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የደብረ ገሊላ ቅ/ዐማኑኤል፣ የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ የመንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም፣ የሰሚት ኪዳነ ምሕረት፣ የመካኒሳ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና የመካኒሳ ቅ/ሚካኤል ናቸው፡፡

የደብረ ሰላም ቅ/እስጢፋኖስ አስተዳዳሪ ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዛውረው በሕግ አገልግሎት መምሪያ እንዲሠሩ፣ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ወደ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተዛውረው በጸሎተ ቅዳሴ አሳራጊነት እንዲያገለግሉ እና በእርሳቸው ቦታ የደብረ ነጎድጓድ ቅ/ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዲተኳቸው ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን እስከ 800 የደብረ ገሊላ ቅ/ዐማኑኤል ካቴድራል ምእመን አቤቱታ ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት የተሰለፈባቸው የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ወደ ደብረ ነጎድጓድ ቅ/ዮሐንስ ተዛውረዋል፡፡

የመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ በጡረታ ተገልለዋል፡፡

Advertisements

4 thoughts on “ሰበር ዜና – የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የ14 አድባራት አስተዳዳሪዎችን ከሓላፊነት አነሣ

 1. Anonymous August 3, 2013 at 8:39 am Reply

  ere lemehonu yemenbere mengst st.gebreal church astedadari silasse memedeb neberebachew? ye hitsan lij chewata new yeteyazew ejig yasaznal

 2. Anonymous August 5, 2013 at 8:46 am Reply

  “የደብረ ሰላም ቅ/እስጢፋኖስ አስተዳዳሪ ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተዛውረው በሕግ አገልግሎት መምሪያ እንዲሠሩ”
  ቀልድ ነው የተያዘው አንድ ቦታ ሲያጭበረብር የነበረ ሰው አንስቶ ሌላ ቦታ መመደብ፣ ስራ እየሰሩ ነው ብለን እንድናጨበጭብላቸው ነው፡፡አሁንስ አበዛችሁት እሱ ቤቱን ማጽዳት ሲጀምር እናንተን አያድርገኝ፡፡እዚህ ይበቃሃል እዛ ሄደህ ዝረፍ የሚል መመሪያ የሚሰጡ አባት የሚባሉ ፌዘኞች መቀለጃ ትሁን ቤተ ክርስትያን እግዚኦ እንበል እባካችሁ፡፡

 3. Yoseph November 15, 2014 at 4:12 pm Reply

  Keep on going ahead!

 4. Anonymous December 9, 2017 at 8:45 pm Reply

  የእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅ/ስለሴን ዝርፊያ የሚመለከት ዓይን እንዴት ይጥፋ? ጥቂት ግለሰቦች እንዲበለፅጉ ብዙሃኑ ማህበረ ካህናት እንዲራቡስ የፈቀደው ምን አይነት መሪ ይሆን? ስለደብሩ ሰላምስ የሚቆረቆር አንድ የበላይ ሰውስ እንዴት ይጥፋ? ምዕመናን እንዲበተኑ ደብሩም በዘራፊዎች እጅ እንዲወድቅ መደረጉስ እውን ተገቢ ነውን? እረ ስለፈጣሪ ብላችሁ የሚመለከታቸሁ አካላት የሰው ህይወት በዘራፊ ቡድኖች ሳይጠፋ አፋጣኝና ዘላቂ መፍትሄ ስጡ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: