በሕዋስ እና በማኅበር የተደራጁ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች የምሥራቅ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከትን እያናወጡ ነው

 • በአሰበ ተፈሪ በዓላማ የሚመስሏቸውንና በጥቅም የገዟቸውን የሀ/ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና ጸሐፊ በመያዝ የደ/ጽዮን ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት እና በዞኑ የማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤቶች እንዲታሸጉ አድርገዋል፡፡
 • ራሱን ‹‹ማኅበረ ናታኒም›› እያለ የሚጠራው በቅ/ሲኖዶስ ተወግዞ የተባረረው የሃይማኖተ አበው ርዝራዥ፣ የደ/ጽዮን ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤን ምርጫ በአባላቱ ብቻ ባቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ በኩል ለመቆጣጠርና አባላቱን በማስመረጥ በደብሩ ተጽዕኖውን ለማጠናከር ያደረገው ሙከራ በሰንበት ት/ቤቱ አባላት ጥረት ተጋልጧል፡፡
 • የምርጫው አፈጻጸም በቃለ ዐዋዲው መሠረት የሚካሄድና የሁሉም መብት የተጠበቀበት እንዲኾን በብርቱ በመቃወም የ‹‹ማኅበረ ናታኒም››ን ሤራ ካጋለጡት የሰንበት ት/ቤቱ አባላት መካከል አንዲት ወጣት ታረቀኝ በተባለው የማኅበሩ አባል ተደብድባለች፤ የከተማው ፖሊስ ጉዳዩን እንዲያውቅ የተደረገ ቢኾንም የወሰደው ርምጃ ባለመኖሩ ወጣቷ ለሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ለማመልከት ተገዳለች፡፡
 • የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ሓላፊዎች የሰንበት ት/ቤቱ እና ወረዳ ማእከሉ ጽ/ቤቶች የታሸጉት ‹‹የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምርጫ እስከሚካሄድና ሰንበት ት/ቤቱ በአዲስ መልክ እስኪቋቋም ድረስ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ይህም ዋነኛ ዓላማቸው ተወግዞ የተባረረውን ሃይማኖተ አበው አባላት በመመለስ ሰንበት ት/ቤቱን መቆጣጠር፣ የማእከሉ የማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት ለዘለቄታው እንዲዘጋ በማድረግ አገልግሎቱን ማቋረጥ /በእነርሱ አነጋገር ዘግቶ ለማስቀረት/ እንደኾነ ይጠቁማል፡፡ ለዚህም ‹‹የዞኑ ካቢኔ ተነጋግሮበት ወስኗል›› ሲል ታረቀኝ የተባለው የሁከቱ መሪ መናገሩ ተዘግቧል፡፡ 
 • የማኅበረ ቅዱሳን አሰበ ተፈሪ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላትና የማኅበሩ የምሥራቅ ኢትዮጵያ ማስተባበርያ ጽ/ቤት ሓላፊዎች የድሬዳዋ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን በድሬዳዋ አነጋግረዋል፤ ሊቀ ጳጳሱ ሰንበት ት/ቤቱም ይኹን የማኅበረ ቅዱሳን ማእከል እንዲታሸግ የሰጡት መመሪያ አለመኖሩን አስታውቀዋቸዋል፤ ቦታው ድረስ በመሄድም ችግሩን እንደሚፈቱ አረጋግጠውላቸዋል – ‹‹የቤተ ክርስቲያን ችግር በቤተ ክርስቲያን ይፈታል፡፡››
 • በዚያው በድሬዳዋ፣ በሕዋስ የተደራጁ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች መንበረ ጵጵስናው የሚገኝበትን የደብረ ምሕረት ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸው ነው የተሰማው፡፡ በዚህ ሳቢያ የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ የሰንበት ት/ቤቱን ጽ/ቤት የማሸግ ርምጃ ወስዷል፡፡ ይኹንና የሥራ አስፈጻሚው አባላት የሰበካ ጉባኤውን እግድ በመተላለፍ ጽ/ቤቱን በኀይል ገንጥለው ለመግባት ሞክረው በፖሊስ ርምጃ መገታታቸው ተዘግቧል፡
 • በጣም የሚያሳዝነው በድሬዳዋ ሀ/ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ክፍል ሓላፊው ከሀ/ስብከቱ የተሰጠውን የትምህርት ፈቃድ ተገን በማድረግ ‹‹በመቐለ ዩኒቨርስቲ ትምህርቴን እየተከታልኩ ነው፤›› በሚል በአዲስ አበባ አንድ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ሥልጠና እየወሰደ መኾኑ ነው፡፡ ሓላፊ ተብዬው በአዲስ አበባ በሚወስደው ሥልጠና ድሬዳዋ ላይ የኑፋቄ ሕዋስ እያደራጀ ነው፡፡ ለአብነት ያህል መንበረ ጵጵስናው የሚገኝበት የካቴድራሉ ሰንበት ት/ቤት ሰበካ ጉባኤ ውስጥ የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ ኾኖ የገባው ግለሰብ በሕዋሱ የታቀፈ ሲኾን በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ‹‹ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም የሚለው አነጋገር የማይሞች ነው›› በሚል ያሰፈረውንና ከሰበካ ጉባኤው አባላትና ከደብሩ ካህናት ጋራ ውዝግብ የቀሰቀሰውን ጽሑፍ ሁሉም የሰንበት ት/ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ‹‹መብቱ ነው፤ የእኛም አቋም ነው›› በማለት እንደደገፉት ተገልጧል፡፡
 • በተያያዘ ዜና ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ለሐምሌ ፲፱ ቀን የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ወደ ቁሉቢ ርእሰ አድባራት ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለማምራት ሲዘጋጁ ጥቂት ዕረፍት ባደረጉበት በድሬዳዋ ሀ/ስብከት መንበረ ጵጵስና /ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል/ ድረስ ለ‹‹አቤቱታ›› የመጡ በሐረር የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኞችና ጥቅመኞቻቸው አፍረው መመለሳቸው ተነግሯል፡፡
Advertisements

20 thoughts on “በሕዋስ እና በማኅበር የተደራጁ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች የምሥራቅ ኢትዮጵያ አህጉረ ስብከትን እያናወጡ ነው

 1. ገ/ሚካኤል July 31, 2013 at 6:36 am Reply

  If this report is realy true it needs wise management only by Curch Fathers not by some body else(Poletician, Association….etc).
  But Hara Tewhidowoch.
  ‹‹ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም የሚለው አነጋገር የማይሞች ነው››
  do you think this is Church Scholars’ Thinking. Don’t you think this is Heretics(ኑፋቄ).
  ሞት በምትለምን የሥጋ እናት ፋንታ በዮሐንስ እጅ በቀራንዮ የተሰጠችን አማላጅ ብሎ ማመን እውነት ነው፡፡
  የ መድኃኔዓለምን የማዳን ሥራን በአማላጅነት መተካት ግን እውነትም የክሕደት ክሕደት ነው፡፡
  I think you believe in

  የሉቃስ ወንጌል 2
  10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤

  11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

  የዮሐንስ ወንጌል 3
  14-15 ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።

  16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

  17 ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።

  18 በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል።

  የሐዋርያት ሥራ
  4፥12
  መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።

  or intensionally you want to use as Accusation means. if so the person may not be Protestant driven.
  please brothers and sisters. Let us be servants of the Truth not servants of association or glory of group.
  የማርቆስ ወንጌል 12
  14 መጥተውም። መምህር ሆይ፥ የሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለን
  if we are Christians pls pls pls let us be of Christ.

  May the Almighty cleaned our beloved EOTC from internal and external enemies and ignorants.

  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ማርያም መሓረነ ክርስቶስ
  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ

 2. ZMTA July 31, 2013 at 7:45 am Reply

  ‹‹ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም››

  ይኽ ከቅርብ ጊዜ ወዲኽ የመጣ አስተምህሮ እንጂ በምሥራቅም በምዕራብም የነበሩና ያሉ የቤተ ክርስቲያን አበው በየትኛውም መጽሐፋቸው እንዲኽ ብለው ሲያስተምሩ አልተገኘም፡፡ እመቤታችን በጸሎቷ፣ በልመናዋ ትራዳናለች ማለት አንድ ነገር ነው፡፡ “ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም!” ብሎ መናገር ደግሞ ፈጽሞ ሌላ ነገር ነው፡፡

  ክርስትናን ከእስልምና የለየው እስልምና በበጎ ሥራችንና በነቢያት ጸሎት እንድናለን ሲል ክርስትና ግን “መዳን በማንም በሌላ የለም፡፡ እንድንነበት ዘንድ የሚገባው ከሰማይ በታች የተሰጠን ስም ከኢየሱስ በቀር ሌላ ማንም የለም፡፡” (ሐዋ4፣2) ስለሚል ነው፡፡ በሰማይም ይኹን በምድር ያሉ የቅዱሳን ጸሎት በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንድንበረታና በጌታችን ያገኘነውን ድኅነት ከንቱ እንዳናደርግ ያግዘናል እንጂ በጌታችን የተፈጸመልንንና የሚፈጸምልንን የማዳን፣ የማማለድ፣ የማስታረቅ ሥራ የሚተካ ወይም በአቻነት የሚቆም አይደለም፡፡ “ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም፡፡” ብሎ ስብከት ጽንፈኝነት የወለደው፣ ካልተጠነቀቅንም ወደ አምልኮ ማርያም እየተወሰደ ሊተረጎምብን የሚችል ነገር ነው፡፡ ተናጋሪው ይኽን አባባል “ማይሞች የፈጠሩት አባባል ነው፡፡” ቢልም ስሕተት ኾኖ ሊያስነቅፈው አይገባም፡፡ ይኽን መፈክር ያውለበለቡት ሰዎች አባባሉ የሚያመጣውን ነገረ መለኮታዊ ተፋልሶ ወይም ውዥንብር ያስተዋሉ አይመስልምና፡፡

 3. Anonymous July 31, 2013 at 12:03 pm Reply

  እኚህ የሰይጣን ተላላኪዎች አይዟችሁ የሚላቸው አካል ስላለ እንጂ ቤተክርስቲያንን እንዲህ እንደዋዛ ባልደፈሯት ::
  እግዚአብሔር ኃይማኖታችንን ና ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን::

 4. mulushewa July 31, 2013 at 1:29 pm Reply

  ማህበረ ቅዱሳን ማለት በቤ/ክርስቲያን ስር ያለ የወጣት እና ቀናኢ ምሁራን ኦረቶዶክሳውያን ስብስብ ነው. ግን…ግን…ብቻውን ቤ/ክርስቲያን ነው ማለት አይደለም. ስለዚህ ማህበሩ በተነካ ቁጥር ቤ/ክርስቲያን እንደተናወጸች አታስመስሉ.
  1. እንኩዋን የማህበሩን አሰራር የሲኖዶስና የፓትርያርክ ዉሳኔም እየተቃወሙ ጥብቅ የኢኦተቤክ አባል መሆን ይቻላል
  2. የናንተ ምርጫ ሲሆን ርቱእ የሌላው ኦርቶዶክሳዊ ምርጫ ሁኖ በናንተ መንገድ ያልሄደ ሲሆን ሁልጊዜም ፍኖተ-ቃኤል ነው አትበሉ-ይህ አካሄድ የ1960ዎቹ ፖለቲከኞች አካሄድን ይመስላል
  3. ሚዛናችን የኢኦተቤክ ጥቅም እንጂ የማህበር ወዳጅ የመሆን እና ያለመሆን መሆን የለበትም
  4. ስለዚህ ራሳችውን እንዲከላክሉ እድል የማትሰጡዋቸውን ሰዎች ተሃድሶ፣መናፍቅ፣ሙሰኛ…እያሉ በድረ-ገፅ ሁዋላ ተደብቆ በሌለ ስልጣን ማውገዝ ጭፍን አማኝን ከመፍጠርና ከጲላጦስ ያነሰ ፍርድ ከመስጠት ውጭ ዘላቂ ጥቅም አይፈጥርም
  5. ፍረጃችሁን በልክ አድርጉት ያለበለዚያ ውሸታሙ እረኛ ሆናችሁ ራሳችሁንም ምእመኑንም ትጎዳላችሁ
  6. በዚህ አይነት አለመደማመጥ ከቀጠልን እንደሙስሊም ወንድሞቻችን ሰበካ-ጉባኤ በቀበሌ ይመረጥ እንዳይባል ያሰጋል
  7. ከመመረጣቸው በፊት ስለ ኑፋቄያቸው ትንፍሽ ሳትሉ ልክ ተመርጠው ወንበሩን ሲይዙ ደርሶ መናፍቅ-መናፍቅ ማለት ምንድነው!!!ወይስ ወንበር ስላልያዙ የጠፉ በጎች አይገዳችሁም!!!

  • Anonymous August 1, 2013 at 8:08 pm Reply

   ማቅ አሰበ ተፈሪ ላይ ተከሰተ ብሎ የጻፈዉ ሁሉ የተለመደ ዉሸቱ ነዉ፡፡ ስለዚህ ገና ቢሮዉ መታሸግ ብቻ አይደለም አዲስ አበባ ቤ/ክህነት ፊት ለፊት በምእመናን ገንዘብ የገነባዉ ህንጻ ታሽጎ ለባለቤቱ ለቤ/ክርስቲያን በቅርብ ተመላሽ ይሆናል፡፡

   • Dave August 2, 2013 at 4:27 pm

    +++

    ታላቅ ማስረጃ ፤ ማን በሃሰት የወንድሞች(የቤተክርስቲያን) ከሳሽ አንደሆነ የሚይሳይ ቪዲዪ

    የቤተክርስቲያን ጠባቂ ኢየሱስ ክርስቶስ የጌቶች ጌታ፤ የነገስታት ንጉስ ነው፤፤
    +++

 5. hiruy July 31, 2013 at 1:38 pm Reply

  thanks 2 GOD u start making responsible those irresponsible Sunday school mercenaries. go go Hara 2 rectify their multiple wrong-doings.

 6. Anonymous July 31, 2013 at 10:02 pm Reply

  Mulushewa mizanawi asteyayet sileseteh Egziabher yebelete libonahin yabralih

 7. Anonymous August 1, 2013 at 12:33 am Reply

  በለዉጥ ማመን መናፊቅ አያሰኝም ። ትክክል የሆነውን ያለጥርጥር እንቀበላለን ነገር ግን እርማት የምያስፈልገውን ነገር በቅንነት አምነን መቀበል አስፈላግ ነው።ሁላችን እንደምናዉቀው ብዙ መጽሐፊት መርካቶ በማንም ታትመው በቤተ ክርስቲያን ስም ይሸጣሉ፡፤ይህ አይነቱ ንግድ በቤተ ከርስቲያን ልቃዉነት መታየት ይገባል እንላለን። ለዉጥ ያስፈልጋል የተባለው በቤተ ከርስትያን ሊቃዉንት ያልተፃፈና ያልታየ የቤተ ክርስቲያን መጽሐፊት ታተምው ከነ አሰስገሰሱ በቅዱሳን ስም መሸጣቸው ጥፋትን አስከትሎዋል መታረም አለበት

 8. ገ/ሚካኤል August 1, 2013 at 7:57 am Reply

  Thank u hara tewahidowoch for postin these all comments

 9. Dave August 1, 2013 at 6:54 pm Reply

  please watch this http://www.youtube.com/watch?v=zu8BLzlQ82M

  የፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ የሃሰት ክስና ዘመቻ በኢትዪጵያ ክርስቲያኖች እና ቤተክርስቲያን ላይ እንዴት በፕሮቴስታንት ድርጅቶች እየተደገፈ እንደሚካሄድ ይህ ቪዲዮ ያሳያል። Ethiopian Orthodox የፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ዘመቻ በኢትዪጵያ ክርስቲያኖች ላይ

 10. Anonymous August 2, 2013 at 5:54 am Reply

  ‹‹ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም የሚለው አነጋገር የማይሞች ነው›› bedifret yehenin bemetechetu yasmeseginewal engi yehe eko mulu lemulu nufake new

 11. mulushewa August 2, 2013 at 9:52 am Reply

  የምን ጠጋ ጠጋ እኛ እንዲህ እናምናለን!!!FOR WHOM CONCERNED
  1.ሀራ ብሎግ የምግባር እንጅ ለወሬ የሚበቃ የሀይማኖት ህጸጽ የለበትም
  2.የተጠቀሱት ችግሮች በሁሉም ብሎጎች(ትክክለኛ ስማቸውን የብሎግ መጠሪያ ካደረጉት በቀር) ስላለ ችግሩ የሀራ ብቻ አይደለም
  3.ማህበረ-ቅዱሳን ሳይኖርም ቤ/ክ ኑራለች ብሎ አጉል ማህበሩን ማጣጣል ትናንት መብራት፣የቡዋንቡዋ ውሀ፣ስልክ፣መኪና.ወዘተ…..የቴክኖሎጂ ውጠየቶች ሳይኖሩም ስለኖርን አሁንም ዛሬን እንደትናንቱ እንኑር እንደማለት ወይም የራሳችን ፓትርያርክ ሳይኖረንም ክርስቲያን ነበርን አሁንም ባይኖርን ……..እንደማለት ነው. ማህበሩ ለቤ/ክርስቲያናችን ያስፈልጋታል.ችግር የሚሆነው ማህበሩ ቤ/ክ ታስፈልገኛለች ሲል ነው
  4.ከላይ የተጠቀሱት የአካሄድ ችግሮቹ እንዳሉ ሁነው ማህበሩ ባለፉት 21 አመታት:
  -በሐመር መጽሄት፣በስምዐ-ጽድቅ ጋዜጣ፣በድረ-ገጹ፣በሲዲና ካሴት በኤሌክትሮኒከስ ሚዲያዎች የሰጠው ወደር የለሽ አገልግሎት
  -የሚያወጣቸው የተመረጡ ወጥና ትርጉም መንፈሳዊ መጻህፍት
  -በሁሉም ክልሎች በሚገኙ የግልና የመንግስት የት/ት ተቁዋማት እና መ/ቤቶች የተዘረጉት የግቢ ጉባኤ የአገልግሎት ማእከላት
  -የሚያዘጋጃቸው አውደ-ርእዮች፣ጥናታዊ ምርምሮችና ዐውደ ጥናቶች
  -የሚባለውን ያህል ባይሆንም የገጠሪቱን ቤ/ክ ማእከል ያደረጉ በጎ አድራጎቶች
  -እንደ አቶ ተፈራ ዋልዋ አይነት ፖለቲከኞች ከሚናገሩት ሃላፊነት የጎደለው ንግግር አንስቶ እስከ ጅማና አርሲ የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ አባቶቻችን በፍርሃት በተሸበቡበት ወቅት ማህበሩ ድምጻችን ነበር
  -ባለፉት ጊዜያት በተሰራው ስራ በአሁን ሰዐት ማህበሩ ማናልባት በሀገሪቱ ትልቁ የምሁራን ስብስብ ይመስለኛል ስለዚህ የጽዋ ማህበር ብሎ ማጣጣል(የጽዋ ማህበርን ለማጣጣል ይመስላል)አጉዋጉል….
  5.የኢኦተቤክ’ንን እናድሳለን እያሉ በየብሎጉ የሚፎክሩት የውስጥ ዐርበኛ ነን ባዮች:
  -የኢኦተቤክ’ንን በሁሉም መልኩ ከመንቀፍ ባለፈ አቁዋማቸው ምን እንደሆነና ከሌሎች የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንዴት እንደሚለዩ አይገልጹም
  -የምግባር ህጸጽ በባሰ መልኩ ተጸናውቱዋቸዋል
  -መንግስት እና ሌሎች የሀይማኖት ተቁዋማት ሳይቀር የሚቀበሉዋቸውን የኢኦተቤክ ሀገራዊ አስተዋጽኦች እንኩዋ ለመግለጽ ልሳናቸው ይያዛል
  -በነዚህ ብሎጎች እንደ ቤ/ክ ጉድለት ተደርገው በተደጋጋሚ የሚለፈፉት ጽኁፎች ከጥንት ጀምሮ በየጉባኤ ቤቱ ይነሱ የነበሩ ጥቃቅን ጥያቄዎች እንጅ ጉባኤ የሚያስጠሩ የነገረ-ሀይማኖት ጥያቄዎች አይደሉም.ለምሳሌ ስለጾም፣በዐላት፣ቅ/ስዕላት፣…..
  -ለማህበረ-ቅዱሳን የተለየ እኩይ ገጸ-ባህርይ እየሰጡ የእሱ ወደረኛ ሁኖ ለመታየት ይሞክራሉ

  • Afework August 8, 2013 at 1:14 pm Reply

   Kalehiwot yaseman ! Yihew new iwnetu

 12. tedi August 2, 2013 at 9:56 am Reply

  ከንቱ የከንቱ ከንቱ ናችሁ ከእርግማን የዘለለ የማታውቁ በጣም ያሳዝናል

 13. Anonymous August 12, 2013 at 5:47 am Reply

  betam

 14. Abreham August 23, 2013 at 12:24 pm Reply

  Hara blog, It is shame…and insulting the work of Jesus at the cross….He is the only saviour.
  Everytime if somebody is against you..but right as per the WORD OF GOD….he is “MENAFIQ” as per your view……Let Godbe the light so that you go your journey clearly. Amen

 15. ደደ September 19, 2013 at 1:34 pm Reply

  ንንረፈ

 16. Anonymous March 23, 2014 at 3:56 am Reply

  ezaer hen maheber aferso yasyan babtekerstyan sem nagedbat esun mahebaer faerso ewnat kerstos yamasekaerbat bat tehonalch

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: