በከፍተኛ ሙስና የተጠረጠሩት የደብሩ ዋና ጸሐፊ በኀምሳ ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

 • የደብሩ ምእመናን በፍ/ቤቱ ውሳኔ ግራ ተጋብተዋል
 • ዋና ጸሐፊው ከሥራቸው ታግደዋል፤ በምትካቸው ሌላ እንዲመደብ ተጠይቋል
Dn Mirutse Tikue of St Urael Church under police arrest

ተጠርጣሪው ዲ/ን ምሩፅ በፍ/ቤት

በሰነድ ማጭበርበር እና ሰነድ ማሸሽ በተፈጸመ ከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዲያቆን ምሩፅ ትኵዕ በኀምሳ ሺሕ ብር ዋስትና መለቀቃቸው ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የደብሩ ዋና ጸሐፊ በኀምሳ ሺሕ ብር ዋስትናቸው ተጠብቆ እንዲወጡ ትእዛዙን የሰጠው ከጊዜ ቀጠሮ በፊት በተጠርጣሪው ጠበቃ ለችሎቱ በቀረበ አቤቱታ መኾኑ ተገልጧል፡፡

ችሎቱ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ለተጠርጣሪው የፈቀደው የዋስትና መብት፣ ዋና ጸሐፊው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ በዋናነት እና በተባባሪነት እንደፈጸሟቸው የተጠረጠሩባቸውን ሕገ ወጥ ድርጊቶች የሚያስረዱ ሰነዶች ከቢሯቸውና ሌሎች ቦታዎች በፖሊስ ፍተሻ መሰብሰባቸውን በምክንያት የተጠቀሰበት መኾኑ ተዘግቧል፡፡

ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ምሩፅ ከተያዙበት ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ከቆዩበት ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በአጀብ ወደ ቢሯቸው እየመጡ በተካሄደው ፍተሻ ሊያሸሿቸው አስበዋል የተባሉ የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎችን ጨምሮ ለምርመራ ሥራ የሚጠቅሙ ሰነዶች መሰብሰባቸው ተነግሯል፡፡

ይህም ሐምሌ ፲፮ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ተጠርጣሪው በችሎቱ በቀረቡበት ወቅት ፖሊስ ‹‹ማስረጃ ያጠፋሉ፤ ምስክር ያባብላሉ›› በሚል የዋስትና ማመልከቻቸውን በመቃወም የጠየቀባቸውና ፍ/ቤቱ የፈቀደለት የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተሠብሮ ከጊዜው ቀጠሮ በፊት በዋስትና እንዲወጡ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡

ዲያቆን ምሩፅ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ይውጡ እንጂ፣ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤልን የፋይናንስ እንቅስቃሴና አሠራር በመመርመር ላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እና የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ልኡካን የማጣራት ሥራቸውን ከሚሠሩበት ቢሯቸው ትውር እንዳይሉ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ መወሰኑ ታውቋል፤ ውሳኔውንም እንዲያስፈጽሙ ለደብሩ ጠቅላላ አገልግሎትና የጥበቃ ሓላፊ የቃል መመሪያ መተላለፉ ተገልጧል፡፡ ከዚሁ በማከታተል አስተዳደሩ የደብሩ ጽ/ቤት ሥራዎች እንዳይስተጓጎሉ ተተኪ ዋና ጸሐፊ እንዲመድብለት ሀ/ስብከቱን በደብዳቤ መጠየቁ ነው የተሰማው፡፡

St Urael Church

የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን

በዲያቆን ምሩፅ ላይ የተላለፈው እግድ ከፖሊስ የምርመራ ሂደትና የፋይናንስ እንቅስቃሴውን ከሚያጣሩት ልኡካን ሥራ ጋራ የተያያዘ እንደኾን የጠቀሱ የደብሩ ምንጮች፣ በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ መሠረት እግዱ ከአንድ ወር በላይ ሊዘልቅ ስለማይችል የምርመራው መዳረሻና የማጣራቱ ውጤት በደብሩ ሀብት መመዝበር ተቆርቁረው አቤቱታ ሲያቀርቡ በቆዩ ወገኖች ሁሉ ዘንድ በተስፋ የሚጠበቅ ያደርገዋል ይላሉ፡፡

ሌሎች አስተያየት ሰጭዎች ሙስናን ከመዋጋት አንጻር ከመንግሥትም ይኹን ከቤተ ክህነት የወጡትን መግለጫዎች በመጥቀስ፣ ዋና ጸሐፊው በተጭበረበረ ሰነድ በፈጸሙት የኪራይ ውል ደብሩን ያሳጡትን የሦስት ሚልዮን ብር ገቢ እና የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቆጠራ ቃለ ጉባኤዎችን በማሸሽ ከጥቅመኞቻቸው ጋራ ሊያካብቱ የሚችሉትን ከፍተኛ ገንዘብ በማስላት ፍ/ቤቱ የዋስትና መብት መፍቀዱ ግራ እንዳጋባቸው ይናገራሉ፡፡ ተጠርጣሪው ‹‹ይረጫሉ›› ከሚሉት የገንዘብ መጠንና ይነግዱባቸዋል ከሚሏቸው አንዳንድ ድሉል የጸጥታ አባላት አንጻርም በምርመራው/ማጣራቱ ሂደት ላይ ተጽዕኖ ሊያደርጉ፣ የሰው ምስክሮችንም ሊያባብሉ አልያም ሊያስፈራሩ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ይገልጻሉ፡፡

Advertisements

10 thoughts on “በከፍተኛ ሙስና የተጠረጠሩት የደብሩ ዋና ጸሐፊ በኀምሳ ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

 1. Anonymous July 28, 2013 at 9:19 pm Reply

  harawech mechem weshet ayselechum enante ye betkerstian nekrsawch nachu. mahebre aganent bekedusan sem atacheberberu.
  .

 2. maty July 29, 2013 at 6:15 am Reply

  ere ebakachu hara newswoch be addis ababa hagere sibket mestengdo balemenoru miknyat eyetegulalan new 1 belulin plz

 3. Anonymous July 29, 2013 at 9:15 am Reply

  It is the continuation of the corrupted system. They leave him because they want him to go abroad with the money and consequently they can cover their own crime. As he, himself once said it is impossible to account him since the corruption chain includes many clergy men and government officials. At this time, he departs with the dollar to his fellows.

  May God keep Ethiopia and our beloved church

  • Anonymous July 31, 2013 at 9:33 am Reply

   I know this guy; he used to be in the former army. when I heard as he is serving in church as a teacher I became shocked. I know ehtiopian orthodox dying but he does not deserve for St. Lalibela Debir.

 4. Anonymous July 29, 2013 at 1:04 pm Reply

  ምን እየተሰራ ነው ጌታ እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ እንጂ ሁሉም ተረባርቦ ለማጥፋት ተነስቷል::

  ቤተክርስትያንን ይጠብቅ!!!

 5. Anonymous July 29, 2013 at 8:07 pm Reply

  እኔ የምለው እነዚያ እሳት የላሱ የዑራኤል ወጣቶች የት ገብተው ነው ይሄ መናፍቅና ግብረሰዶማዊ እንዲህ የጠገበው ?! እንደነ
  በጋሻው ቢያረጉት ጥሩ ነበረ ። ለነዚህ ውሾች መድሀኒቶቹ እንደ ዑራኤል ወጣቶች አይነቶቹ ናቸው ።

 6. Anonymous July 31, 2013 at 1:41 pm Reply

  ante kefelegik tedebadeb egnan lekek adirgen! ante **** neh meselegn

 7. Anonymous July 31, 2013 at 11:06 pm Reply

  @ tedbababiw…who r u ma friend ? are u ortodox or islam chrstian etics not prech this kind of stubid things

 8. Anonymous August 1, 2013 at 3:04 pm Reply

  Egezeo meharene kerstose ! sewen behaset eyekonenahu yet tegebu yehon ? melkam sebena behaset kal ayegodefem. kenanete belay diyakon miruthn bedenb lemenakew lega lesera balederebohu edel setun enenager! zemenu yesetan honewal teru sew metelabet metefo sew mewededebet ! E/r meheretun yelakelen endenanete ayenet setanohen yatefalen !!! Amen.

 9. Anonymous August 14, 2013 at 1:21 pm Reply

  amennnnnnnnnnnnnnnnnnnnn

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: