አቡነ ጢሞቴዎስ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊነት ተገለሉ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ኮሌጁን በጊዜያዊ ሓላፊነት እንዲመሩ ተመድበዋል

 • አቡነ ጢሞቴዎስ ጉዳያቸው ከሚታይበት ስብሰባ ላለመውጣት ሲለመኑ ውለዋ
 • ፓትርያሪኩ ስለ አቡነ ጢሞቴዎስ ብዙ ከመናገር ተጠንቅቀዋል፤ ተቆጥበዋል
 • ደቀ መዛሙርቱና መምህራኑ ደስታቸውን በቅኔ፣ ወረብና መዝሙር እየገለጹ ነው
 • የቦርድ አባላቱ በሲኖዶሱ ፊት ያሰሙት ያልተጠበቀ ምስክርነት አስተዳደሩን አጋልጧል
 • የአጣሪ ኮሚቴው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲተገበሩ ቅ/ሲኖዶሱ መመሪያ ሰጥቷል
 • የንቡረ እድ ኤልያስ ምደባ ከሚያስነሣው ግዙፍ ጥያቄ ጋራ የምረቃው ቅድመ ዝግጅት ይቀጥላል..
His Grace Abune Timothy

ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ

ላለፉት 14 ዓመታት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን በበላይ ሓላፊነት ሲመሩ የቆዩት ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ ከሥልጣናቸው እንዲገለሉ ቅዱስ ሲኖዶስ መስማማቱ ተገለጸ፡፡

ቅ/ሲኖዶሱ ዛሬ፣ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በደረሰበት ስምምነት መሠረት÷ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት እና መምህራን ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሣባቸው ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በበላይ ሓላፊነት ከያዙት ሥልጣን ይገለላሉ፤ ለኮሌጁ አዲስ ሊቀ ጳጳስ እስከሚመድብ ድረስም የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ‹‹የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ›› ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በጊዜያዊ ሓላፊነት እየሠሩ እንዲቆዩ ተመድበዋል፡፡

በቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት እና በኮሌጁ አስተዳደር መካከል በተፈጠረውና ላለፉት ስድስት ወራት ሲባባስ ለቆየው አለመግባባት እልባት ለመስጠት በተጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ከ18 ያላነሱ የቅ/ሲኖዶስ አባላት ተገኝተዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ የኮሌጁን አስተዳደራዊ እና አካዳሚያዊ ኹኔታ፣ የቦርዱን አሠራር፣ የመምህራኑንና ደቀ መዛሙርቱን አያያዝ በተመለከተ የተፈጸሙ ስሕተቶችን በመዘርዘር የበላይ ሓላፊው ችግሩን ለመፍታት የተከተሉትን አካሄድ ተችተዋል፡፡ አቡነ ጢሞቴዎስ ከሚገኙበት የዕርግናና የጤንነት አቋም በመነሣት የችግሩ አያያዛቸው ሊቀ ጳጳሱንና በዙሪያቸው የተሰለፉ ግለሰቦችን ከመጥቀም በቀር የኮሌጁን መብት የማያስጠብቅ፣ ሀብቱን ለብክነት የሚዳርግና ተቋማዊ ተልእኮ የሚያሰናክል እንደኾነ በመግለጽ ለውዝግቡ መባባስ የበላይ ሓላፊውን ዋነኛ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

በስብሰባው የተወሱት ጉዳዮች አለመግባባቱን ያጣራው ኮሚቴ በ18 ገጾችና በስምንት ዋና ዋና ክፍሎች ካቀረበው ሪፖርት ጋራ ተቀራራቢ እንደኾነ የገለጹት የስብሰባው ምንጮች መፍትሔውም ኮሚቴው ከአጭርና ከረጅም ጊዜ አንጻር በመከፋፈል ባቀረባቸው የማስተካከያ ርምጃዎች መሠረት ተፈጻሚ እንዲኾን ከስምምነት ላይ መደረሱ ተዘግቧል፡፡ ስለኾነም በቀደመው ዜና ብሥራታችን እንደገለጽነው፣ የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር ሓላፊ ዘላለም ረድኤት ከኮሌጅ ሓላፊነቱ ከመነሣቱም በላይ ከኮሌጁ ይወገዳል፤ አካዳሚክ ዲኑ መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ ከአካዳሚክ ምክትል ዲን ሓላፊነታቸው ተነሥተው የያዟቸው ተደራራቢ ኮርሶች ተቀንሰው በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ፡፡

ቀድሞ እንደተጠበቀው የዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ ያሰማን ዐቢይ ውሳኔ፣ የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ከሥልጣናቸው ገለል እንዲሉ መደረጋቸው ነው፡፡ ስብሰባው የተጀመረው ሌሎች ወቅታዊ አጀንዳዎችን በመመልከት እንደነበር የተገለጸ ሲኾን በኮሌጁ ዙሪያ መወያየቱን ለመቀጠል በሕገ ቤተ ክርስቲያን በተደነገገው መሠረት የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ከስብሰባው መውጣት የግድ ነበር፤ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተደነገገው የሕጉ አንቀጽ ፰ ንኡስ አንቀጽ ፯ እንደሚሠራው፣ አንድ የሲኖዶስ አባል ስለራሱ ጉዳይ በሚታይበት ስብሰባ ላይ በአባልነት መገኘት አይችልምና፡፡

የሕጉን የስብሰባ ሥርዐት በመጥቀስ ጭምር ከስብሰባው እንዲወጡ የተጠየቁት ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ግን ፈቃደኛ ባለመኾናቸው በተሳታፊዎቹ ሲለመኑ ውለዋል፤ ከዚህም አልፈው ቅ/ሲኖዶስ የኮሌጁን ወቅታዊ ኹኔታ አጀንዳ በማድረግ ለአስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡን ሳይቀር ነቅፈዋል፤ ስብሰባውንም ‹‹ሕገ ወጥ ነው›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ ቅ/ሲኖዶሱ ‹‹አስኬማዬን ይረከበኝ›› ሲሉም አሻፈረኝ ብለዋል፡፡ ምንጮቹ እንደገለጹት ልመናው በመጨረሻ ሠምሮ ስብሰባው ባለጉዳዩ በሌሉበት የቀጠለው የጉባኤው ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ሲጨመሩበት ነው፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጣዊ ጉዳይ የማይመለከታቸው ወገኖች ሁሉ እጃቸውን በችግሩ ሰበብ እንዲያስገቡ ምክንያት መኾኑን ያወሱት ርእሰ መንበሩ፣ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ብዙኀን መገናኛ ርእሰ ጉዳይ እየተደረገች መተቸቷ እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ጉባኤው መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቀዋል፤ ከዚህ በቀር አቡነ ጢሞቴዎስን በሚመለከት ሌሎች ተሰብሳቢዎች በሰፊው ከተናገሩት በአንጻሩ ጥንቃቄና ቁጥብነት መርጠው መታየታቸው ተስተውሏል፡፡ እንዲያውም ቤቱ በጉዳዩ ላይ መሠረታዊ አቋም እየያዘ መሄዱ ሲረጋገጥ ‹‹ይህ ሁሉ ነገር መኖሩን መች ዐወቅኁትና!›› በሚል ጸጸት ስሜታቸውን መግለጻቸው ነው የተሰማው፡

አቡነ ጢሞቴዎስ በሌሉበት ውይይቱ ቀጠለ፡፡ በቀደሙት ቀናት መምህራኑና የደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራሮች በቋሚ ሲኖዶሱ ፊት በየራሳቸው ቀርበው አስረድተው ነበር፡፡ በዛሬው ስብሰባ ደግሞ በቅ/ሲኖዶሱ የተጠሩት አቡነ ጢሞቴዎስ የሚመኩባቸው የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ነበሩ፡፡ ኮሌጁ እንዲዘጋ ደቀ መዛሙርቱም ለቀው እንዲወጡ ለፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የውሳኔ መነሻ ሰጥተዋል የተባሉት የቦርድ አባላት በቅ/ሲኖዶሱ ፊት የሰጡት ምስክርነት ግን እንደወትሮው አቡነ ጢሞቴዎስን የሚደግፍ አልያም ድክመታቸውን የሚሸፍን አልነበረም፡፡

ይልቁንም እንደ ቦርድ የመሥራትና የመወሰን ነጻነት እንደሌላቸውና ኮሌጁን እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመምራት እንዳልቻሉ አጋለጡ፤ በተለይ በየ15 ቀኑ እየተገናኘ ሻይ ቡና ጠጥቶ፣ አበሉን ሰብስቦ ብቻ ከመለያየት በቀር መምህራኑን ይኹን ደቀ መዛሙርቱን አናግሮ እንደማያውቅ የተተቸውን የቦርዱን ስብሰባ አያስታጉሉም የሚባሉት ምክትል ሰብሳቢው ዶ/ር ተጠምቀ መሐሪ ኮሌጁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው የሚያሰኝ አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ቁመና ይኹን የተሟላ ሎጅስትክ እንደሌለው በአጽንዖት ተናገሩ፡፡

በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ገጽ 4 እና 5 ላይ በተመዘገበው ቃላቸው አራት የሥራ አመራር ቦርዱ አባላት የጠቀሷቸው ችግሮችም ይህንኑ በሌላ ገጽ የሚያብራሩ ናቸው፡-

 • የኮሌጁ ቦርድ ከሌሎች ተመሳሳይ ቦርዶች የተለየ መኾኑ፤ ማለትም ለኮሌጁ የሚጠቅሙ ፖሊሲዎችንና ስትራተጅዎችን በማውጣት ሳይኾን በየዐሥራ አምስት ቀኑ እየተገናኘን የኮሌጁ አስተዳደር ሊሠራ የሚገባውን እየሠራ መኾኑን ይህንንም እንዲያደርግ ደንቡ የሚደነግግ መኾኑን፣
 • የኮሌጁ አስተዳደር የአመራር ድክመት ያለበት መኾኑ፣
 • የደቀ መዛሙርቱ አመላመልና አቀባበል ችግር እንዳለበት፣
 • የሥራ አመራር ቦርድ አባላት የኾኑት በተለይም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በስብሰባው ላይ አዘውትረው አለመገኘት፤ በመደበኛ ስብሰባ የሚገኙት ከምእመናን የተመረጡ አባላት ሲኾኑ ስብሰባውን የሚመሩትም ም/ሰብሳቢው ዶ/ር ተጠምቀ መሐሪ ናቸው፡፡ ይህም ሃይማኖት ነክ የኾኑ ጉዳዮች በአጀንዳነት ሲቀርቡ ለመወሰን እንደሚቸገሩ ገልጸዋል፡፡ ለምሳሌ በተከለሰው ሥርዐተ ትምህርት የአምስት ዓመቱ የዲግሪ መርሐ ግብር ወደ አራት ዓመት ሲቀየር የብሉይ እና የሐዲስ ኮዳን ትምህርቶች ተገቢው ትኩረት አልተሰጣቸውም ተብሎ በመምህራኑ ለቀረበው ጥያቄ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይህ ካሪኩለም ሲጸድቅ ቢገኙ ኑሮ ቅሬታ ላይፈጠር ይችል እንደነበር ተናግረዋል፡፡
 • ኮሌጁ የበጀት ችግር ያለበት መኾኑ፤ ምንም እንኳን የኮሌጁን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ በኮሌጁ ግቢ ግዙፍ ሕንጻ ቢገነባም በሕንጻው ገቢ ኮሌጁ እንደማይጠቀም፣ በባለሞያ ተጠንቶ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚቀርበው በጀት እየተቀነሰ በየዓመቱ ተመሳሳይ በጀት መላኩ፤
 • ለኮሌጁ መምህራን፣ ደቀ መዛሙርትና አስተዳደር የወጡ ደንቦች ክፍተት ያለባቸው መኾኑ፤ ለምሳሌ የኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት እና አስተዳደር አባላት ተመሳሳይ ኾኖ እንዲዋቀር ደንቡ መፍቀዱ አንዱ ያጠፋውን ሌላው እንዲያርም መንገድ አለመመቻቸቱ የሚሉ ሐሳቦች ይገኙበታል፡፡

ለእኒህ ችግሮች የቦርዱ አባላት የሰጧቸው ተነጻጻሪ የመፍትሔ ሐሳቦች እንደሚከተለው ሰፍረዋል፡-

 • የኮሌጁ በጀት ለይቶና ተስተካክሎ እንዲሁም ተመጥኖ እንዲሰጠው ቢደረግ፣
 • ከውስጥ ገቢ ማለትም ከካፌ፣ ከመማሪያ ክፍሎች፣ ከአዳራሽ ኪራዮች፣ ከማታ፣ ከማስተርስና ከርቀት ትምህርት ፕሮግራም የሚገኘው ገቢ በትክክል ታውቆ ቀሪው ከቤተ ክህነት የሚሸፈንበት መንገድ ቢመቻች ወይም ከሕንጻው ገቢ ላይ ተጠንቶ የተወሰነ ፐርሰንት ለኮሌጁ ቢሰጥ፤
 • ደቀ መዛሙርቱ በኮሌጁ ውስጥ በወጣላቸው መተዳደሪያ ደንብ እንዲተዳደሩ ቢደረግ፤
 • በኮሌጁ ውስጥ ጠንካራና ውሳኔ የሚሰጡ የአስተዳደር ሰዎች ቢኖሩ፡፡ በዚህ ውስጥ የኮሌጁ ደንብ እንደሚያስረዳው፣ ኮሌጁ አንድ ዋና ዲንና በሥሩ የአካዳሚክና የአስተዳደር ም/ዲኖች እንደሚኖሩ ቢገለጽም ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ የኮሌጁ ዋና ዲን ወይስ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ መኾናቸው በግልጽ አለመታወቁ እና ዶ/ር አባ ኀይለ ማርያም መለሰ በሌለ መዋቅር ም/ዋና ዲን ተብለው መመደብ ከዚህም የተነሣ የአስተዳደር ም/ዲን የሚባለው መዋቅር በሥራ አለመዋሉ ናቸው፡፡
 • ኮሌጁ የተሟሉ የቦርድ አባላት ቢኖሩት፤ በተለይ ለቦርዱ አባልነት የተመደቡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በስብሰባ ላይ እንዲገኙ ቢደረግ፤ በቦርድ አባልነትም የትምህርተ መለኰት ዕውቀት ያላቸው የቤተ ክርስቲያን ምሁራን እንዲሳተፉ ቢደረግ፤

በዚህና በመሳሰለው መልክ የቀረበው የቦርዱ አባላት ምስክርነት የእውነታው ማረጋጋጫ ኾኖ ቅ/ሲኖዶሱን ወደ አንድ ውሳኔ አደረሰው – ላለፉት 14 ዓመታት ኮሌጁን በበላይ ሓላፊነት ሲመሩ የነበሩት አቡነ ጢሞቴዎስ ከበላይ ሓላፊነታቸው እንዲገለሉ፣ በአስተዳደሩ ጣልቃ እንዳይገቡና ምናልባትም እስከ መጪው ዓመት ጥቅምት ድረስ እንደ በላይ ጠባቂ እንዲቆዩ!

እንደ ስብሰባው ምንጮች መረጃ ግን ይህን የቅ/ሲኖዶሱን የስምምነት ውሳኔ ባለጉዳዩ አቡነ ጢሞቴዎስ ባሉበት ለማሳወቅ ጭንቅ ኾኖ ነበር፡፡ ከመምህራኑ፣ ከደቀ መዛሙርቱ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ እና በተለይም እንደ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ካሉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በ‹‹እንተያያለን›› እልክ ተጋብተው የሰነበቱት አቡነ ጢሞቴዎስ ውሳኔውን እንዲቀበሉት ለማግባባት በወዳጅነታቸው የሚጠቀሱት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ፀጋይ በርሄ ሚና እንደተጫወቱ በስፋት እየተወራ ቢኾንም መረጃውን ከገለልተኛ ምንጭ ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ሚኒስትሩ ለብፁዕነታቸው ‹‹እርስዎን ዘመን ነው የገደብዎ፤›› በማለት ዕረፍት ማድረግ እንዳለባቸው አስተያየት መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡

የአቡነ ጢሞቴዎስ ከሥልጣን መገለል እንደተሰማ መምህራኑና ደቀ መዛሙርቱ በአንድነት በኮሌጁ ቅጽር ተሰብስበው ደስታቸውን በቅኔ፣ ወረብና መዝሙር የገለጹ ሲኾን ይህ ዜና በሚጠናቀርበት ሰዓት ሐሤት ማድረጉ ቀጥሎ እስከ መንፈቀ ሌሊት ዘልቋል፡፡ በይበልጥም የውሳኔው የምሥራች የተሰማበት ሐምሌ ፲፪ ቀን የአምስተኛ ዓመት ዕጩ ተመራቂዎች ተራ ገብተው የሚዘክሩት የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወርኀዊ በዓል ጋራ በመገጣጠሙ በመዝሙርና በዝማሬ ሐሤት ማድረጉ ከመንፈቀ ሌሊትም በኋላ በድምቀት ቀጥሎ እንደነበር ታውቋል፡፡ ‹‹ላለፉት 14 ዓመታት የወረደው እንባ በዛሬው ዕለት ግፈኞችን ከኮሌጁ አጽድቷቸዋል›› ብለዋል በዓለ ትፍሥሕቱን አስመልክተው ትምህርት የሰጡት ሊቀ ማእምር፡፡

NebureEd Elias Abreha

ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ

ንቡረ እድ ኤልያስ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ከማይታወቀው ‹‹የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት›› ጋራ በመደረብ የያዙት የጊዜያዊ ሓላፊነት ምደባ እስከ ቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር እንደሚቆይ ተመልክቷል፤ ኮሌጁ አዲስ ሊቀ ጳጳስ እስኪመደብለት፣ አስተዳደሩና ቦርዱ በአዲስ መልክ እስኪዋቀር ድረስም ከድጋፍ ሰጭ ሠራተኞችና መምህራን ጋራ እየተመካከሩ መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ንቡረ እዱ ባለፈው ዓመት ለአጭር ጊዜ የኮሌጁ የአስተዳደር ዲን ኾነው መሥራታቸውን ያስታወሱ ወገኖች የአሁኑ አለመግባባት በተባባሰበት ባለፉት ስድስት ወራት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ጽ/ቤት ከነበራቸው ቅርበት አንጻር የተጫወቱት ሚና ገንቢ እንዳልነበር ተችተዋል፡፡

ቀደም ባሉት ዘገባዎቻችን ሲገለጹ ከቆዩት የከፋ የሙሰኝነት፣ ቡድንተኝነትና ጎጠኝነት ችግሮቻቸውም በመነሣት ከፍተኛ የሀብት ምንጮች ላሉት አንጋፋ የትምህርት ተቋም ባለአደራነት አለመብቃታቸውን ብቻ ሳይኾን የምደባውን አርኣያነትንም አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡ የቤተ ክህነታችንን የተቋማዊ ለውጥ ርምጃዎች ለማምከን ከማይቦዝኑ ፅልመታዊ ቡድኖች ጋራ ያላቸው ያልተቋረጠ መስተጋብርም ከተቋሙ ተልእኮ አንጻር የሚደቅናቸው ስጋቶች አሉት፤ ምንም እንኳ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች የምደባውን ጊዜያዊነት በመጥቀስ ቢጽናኑም!

Advertisements

40 thoughts on “አቡነ ጢሞቴዎስ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊነት ተገለሉ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ኮሌጁን በጊዜያዊ ሓላፊነት እንዲመሩ ተመድበዋል

 1. mebrat July 20, 2013 at 1:02 am Reply

  እረ ይሔ ምንም የሚያስወርብና ቅኔ የሚያስዘርፍ አይደለም:: ይህን ያክል ዘመን ቤተክርስቲያን ውስጥ እየኖሩ ስለ ንቡረ-እድ ኤልያስ አያውቁም ማለት ነው ቅኔ ዘራፊዎቹ? ቤተክርስቲያን ስንት ሰው እያላት የቤተክርስቲያን ጠላት ይመድባሉ አባቶች? የዘላለም መነሳት ሲያስደስተን በፊት ከነበረው በስንት እጅ የከፋ ሰው ተመደበበት በአስተዳደር ክፍሉ? ንቡረ-እድ ኤልያስ ደግሞ ኢሃዲግ ለዚህ አላማው የመረጠው ሰውና ቤተክርስቲያንን ለመመዝበር በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካስቀመጣቸው ሰዎች አንዱና ዋናው ነው:: ንቡረ-እድ ኤልያስ ተሾሙ ማለት ኢሃዲግ ኮሌጁን ተቆጣጠረው ማለት ነው:: ከዚህ ቦሃላ ሙስናው ድሮ ከነበረው እጅግ ይጨምራል ማንም ግን ጥያቄ ማንሳት አይችልም: ለምን ብሎ መጠየቅ አይችልም:: በጣም ያሳዝናል:: እንደዚህ አይነት ሰው ከሚመደብ አቡነ ጢሞቴዎስ ባይነሱ እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ይሻል ነበር:: የንቡረ-እድ በሳቸው ቦታ መተካት ማቅ ያስለብሳል: ታላቅ ሀዘንም ልናዝን ይገባናል:: ቤተክርስቲያን ያለ ፖለቲከኞቹ ጣልቃ ገብነት ስራ መስራት አትችልም ማለት ነው? እኔ በበኩሌ እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት:: ትላንት የዘላለም መነሳት አስደስቶኝ ነበር አሁን ግን ከዛ ደስታ እጅግ በከፋ መልኩ አዘንኩ:: የተማሪዎቹ ጥያቄ እጅግ በጣም ቀላልና በጣም በቀላሉ የሚፈታ ነበር:: ከላይ በሃላፊነት ላይ እንደ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያሉት ሰዎች ግን አውቀው አወሳስበውት አሁን የፈለጉትን የኢሃዲግን ካድሬና ሙሰኛውን ንቡረ-እድ ኤልያስን አስቀመጡበት:: በየሴሚስተሩ መጨረሻ መምህራን በተማሪዎች ይገመገማሉ:: እንኳን እንደዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ተነስቶበት ቀርቶ በግምገማው መሰረት ብቻ አስተማሪን ከስራው ማባረር እኮ ኮሌጁ ሙሉ መብት አለው:: መምህሩ የቤተክርስቲያን ስለሆነ የሱም ጉዳይ ያሳስበኛል ካለች ቤተክርስቲያን ሌላ ከተማሪ ጋር የማያገናኘውና መድረክ ላይ መስበክ በማይችልበት የስራ መደብ መመደብ ይቻል ነበር (መናፍቅነት አለው ስለተባለ ያ እስኪረጋገጥ):: አቡነ ጢሞቴዎስንም እንዲሁ በሌላ አባት መተካት ይቻል ነበር:: ግን አውቀው አወሳሰቡት:: ወደዳችሁም ጠላችሁም ለጉዳዩ በጊዜ መፍትሔ ያልሰጡት ይኸው አላማ ስለነበራቸው ነው (ኮሌጁን በኢሃዲግ ካድሬ የማስያዝ አላማ)::

  • mebrat July 20, 2013 at 12:08 pm Reply

   min aynet sew neh tinish atafirim lenegeru yeterabinew egna ante min alebih leteqmach semay kirbu new bakih wendime nisha giba yemenafiku yezelalemin hasab meyazih yasazinal

   • axumit July 20, 2013 at 10:45 pm

    ወንድሜ ሞክሼ መብራት: ለመሆኑ ስንተኛ አመት ተማሪ ነህ? አማርኛ ጽሁፍ አንብበህ መረዳት ካለመቻልህ አንጻር አንተን የኮሌጁ ተማሪ ነህ ማለት ይቀብዳል:: የኮሌጅ ተማሪዎች አይደለም እንደዚህ ፊት ለፊት የቀረበን ጽሁፍ ቀርቶ በጣም ውስብስብ የሆኑ አረፍተነገሮችን ተረድተው መፍታት የሚችሉ ናቸው:: የተዋህዶ ቤተክርስቲያን ኮሌጅ ውስጥ የሚማሩት ተማሪዎች ደግሞ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ ተማሪዎች የበለጠ ውስብስብ ጽሁፎችን የመፍታት አቅሙ አላቸው ምክንያቱም የሚማሩት ትምህርትና ድሮም ከልጅነታቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ የተማሩት ትምህርት በጣም ያመራምራል:: በየትኛው አረፍተ ነገር ነው የዘላለምን ሃሳብ የያዝኩት? ለመሆኑ የጻፍኩትን በትክክል አንብበኸዋል? ወይስ የአይን ችግር አለብህ?

  • wesen seged July 20, 2013 at 12:11 pm Reply

   Enie hulachum tazebkuwahcu kegna belay legna enkwklachiwalen eyalachun new kezih behal kolleju yehaymanot chdri yeminegebet sayhon chgri yemifatabet gzie deres enante gin ye MK alama mantsebarek yetetemedachu gizie meshebachu sew hulu cristian kehon dres sew new gotognoch athunu e4nday meshbachu keza berha lay endatdru

  • Anonymous July 27, 2013 at 9:33 am Reply

   ‹‹ትሻልን ትቼ ትብስን አገባሁ ማለት ይሄ ነው››
   ‹‹የቀን ጅብ ይሉሃል ንቡረ ዕድ ኤልያስ ነው››
   ንቡረ ዕድ ኤልያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት ከአንዱ ደብር ወደ አንዱ ደብር ወደሌላው ለመቀየርና ለመቀጠር ከ 15,000ሺ ብር በላይ ጉቦ እንደሚጠይቅ አቀባዮቹ የአዲስ አበባ አድባራት ፀሃፊዎችና ቁጥጥሮች ያውቃሉ ምስክርነታቸውን ቢጠየቁ ለሆዳቸው ካላደሩ ሊመሰክሩ ይችላሉ፡፡
   ንቡረ ዕድ ኤልያስ የበላይ ኃላፊ የሚሆንበት መንፈሳዊ ኮሌጅ ምን ዓይነት ኮሌጅ ሊሆን ነው?? ምክንያቱም ግለሰቡ መንፈሳዊውንም ሆነ ለኮሌጅ የሚመጥን ችሎታ የሌለው በዓለማዊ ጥቅም የታወረ ነው፡፡

 2. Anonymous July 20, 2013 at 2:29 am Reply

  ምን እየሆነ ነው ያለው ?ያሉት አስቸጋሪ ሰው ገለል ሲደረጉ ሌላ የባሰበት ሌባ(ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ) ይመደባል ? ፓትርያርኩ ምን ነካቸው የስውሩ እጅ ሰለባ ሆኑ እንዴ?

  እግዚአብሔር ሃይማኖታችንን ይጠብቅ

 3. Sintayhu Haele Gebreil July 20, 2013 at 2:58 am Reply

  የመልካም አስተዳደር ትልቁ መሳሪያ *ዉሳኔ ሰጭነት * ነዉ፡፡ ቤተ ክርሰቲያንን በሁለት መንታ መንገድ
  ዉስጥ ከከተታት ዉጥንቅጥ ዉስጥ ያወጣታል፡፡

  ግን ንቡረ እድ ኤልያስ በምን መስፈርት ተመደቡ…??? ይሔም ትኩረት ያሻዋል….

 4. sintayhu Evangadi July 20, 2013 at 3:34 am Reply

  የመልካም አስተዳደር ትልቁ መሳሪያ ዉሳኔ ሰጭነት ነዉ፡፡ ቤተ ክርሰቲያንን በሁለት መንታ መንገድ ዉስጥ ከከተታት ዉጥንቅጥ ዉስጥ ያወጣታል፡፡
  ግን ንቡረ እድ ኤልያስ በምን መስፈርት ተመደቡ…??? ይሔም ትኩረት ያሻዋል…. ንቡረ እዱ ምን ይሰሩ እንደነበር እየታወቀ…. ደቀ መዛሙርቱ ሌላ ፈተና እንደ ሚጠብቃችሁ አትዘንጉ….
  ይህ የቅዱስ ሲኖዶስ ዉሳኔ ወደ ሀገረ ስብከቶችም መዉረድ አለበት ፡፡ በተለይም ምስራቅ ሸዋ ሐገረ ስብከት መታየት አለበት፡፡
  አንድ ሊመለስ የሚገባዉ ጥያቄ አለ “ሊቃነ ጻጻሳት ቤተ ክርስቲያንን ለማን ሊያስረክቡዋት ነዉ … በዘረኝነት፤በሙስና፤በኑፋቄ ተተብትበዉ ለዳኛ የሚያስቸግሩት… ምንኩስና አልገባቸዉም ማለት ነዉ…?

 5. axumit July 20, 2013 at 6:52 am Reply

  ንቡረ-እድ ኤልያስ? hahahahaha
  ቀልደኞች ናቸው! ስለዚህ የተማሪው ጥያቄ ተመለሰ ማለት ነው? ንቡረ-እድ ኤልያስ….የሰው ስጋ ለብሶ ሰው መስሎ የሚንቀሳቀስ ሰይጣን እንዴት ይመደባል? በአቡነ ጢሞቴዎስ ምትክ ሆነኛ ሰው ወይም አባት እስኪመደብ ድረስ ተቋሙ በሳቸው ስር መቆየት ነበረበት ወይም አሁኑኑ ሌላ ሁነኛ አባት/ሰው መመደብ ነበረበት:: አቡነ ጢሞቴዎስ እነ ዘላለም እያሳሳቷቸው እንጂ በራሳቸው ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸው እናውቃለን:: እነ ዘላለም እሳቸውን በመሸወድ በውስጥ ሙስና ይሰራሉ: አቡነ ጢሞቴዎስም የዘላለምን ምክር ሰሙ እልህም ገቡ::እልከኝነት በጣም መጥፎ ነው:: በዛ ላይ ደግሞ እርጅናም አለ:: ሙስናው ውስጥ ግን እሳቸው እንዳማይሳተፉ 100% እርግጠኞች ነን:: የሆነው ሆኖ መነሳታቸው ምንም አያጠያይቅም ትክክል ነው የአስተዳደር ችግር ስላለ:: ግን ደግሞ ንቡረ-እድ ኤልያስ ለአንድ ቀንም ቢሆን ከሚመደብ አቡነ ጢሞቴዎስ ከስራቸው ያሉት የስተዳደር ሰዎች ተቀይረውላቸው ቢቆዩ በጣም የተሻለ ነው:: ወይ ይህች ቤተክርስቲያን! ለሃገራችን ባለውለታ እንዳልሆነች ሁሉ: ፊደል ከነሙሉ ምልክቱ በማበርከት ከድንቁርና እንዳላወጣችን ሁሉ: ሀገራችን ነጻነቷን እንደተጎናጽፈች እንድትኖር እንዳላደረገችና የጥቁር ሁሉ ኩራት እንድንሆን እንዳላበቃችን ሁሉ ዛሬ እንዲህ ይጫወቱባት?

 6. Anonymus July 20, 2013 at 11:22 am Reply

  እባካችሁ የምንናገረው እንወቅ እንደ ክርስቲያኖችም እናስብ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ መተቸት አይገባም፡፡ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳልጠረው ሰው የምናዋርድበት መድረክ አናድርገው፡፡ ንቡረ እድ ኤልያስ በጊዚያዊነት ካስቀመጣቸው ምን እንርዳዎ ብሎ ምክር መስጠት አስተያየት መለገስ ይገባል እንጂ ሰው በሚሰራው ሥራ እንጂ በዘሩና ባለው ርዕዮት ባንፈርድበት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ

  • guest July 21, 2013 at 7:36 am Reply

   ይህች ነች ጭዋታ! ኤልያስ ሥጋ የለበሰ ጋኔን ነው! በጣም ያሳዝናል! እንዴት ይህን ወስላታ ሌባ ይወክሉታል!

 7. Anonymus July 20, 2013 at 11:30 am Reply

  እባካችሁ የምንናገረው እንወቅ እንደ ክርስቲያኖችም እናስብ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ መተቸት አይገባም፡፡ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረው ሰው የምናዋርድበት መድረክ አናድርገው፡፡ ንቡረ እድ ኤልያስ በጊዚያዊነት ካስቀመጣቸው ምን እንርዳዎ ብሎ ምክር መስጠት አስተያየት መለገስ ይገባል፡፡ ሰው በሚሰራው ሥራ እንጂ በዘሩና ባለው ርዕዮት ባንፈርድበት መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ

  • guest1 July 21, 2013 at 7:25 am Reply

   መቼም በቀጣም ባይሆን በተዘዋዋሪ ትምህርትበቱም ሆነ ደቀምዝሙርቱ ሰላም እንዲያገኙ የተፈለገ አይመስልም:: ንቡረእድ ኤልያስ ከአባ ጢሞቴዎስ የከፋ እንጅ ያነሰ ጉዳት በተማሮቹ ከማድረስ አይመለስም:: ችግሩን ለመፍታት ከሆነ አሁን ንቡረድ ኤልያስን ለዚሁ ኃላፊነት የሚያስመርጥ ምን ችልታ አለው? እነዚህ ሰዎች ምኑን ያህል ለጥፋትና ስርቆት ቆርጠዉ ቢነሱ ነው? ይህን ንግዳቸዉንና ስርቆታቸዉን ለመግታት ትግሉ መቀጠል አለበት!

 8. mebrat July 20, 2013 at 12:06 pm Reply

  mebrat letebalikew sew እንደዚህ አይነት ሰው ከሚመደብ አቡነ ጢሞቴዎስ ባይነሱ እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ይሻል ነበር:endt ante rasih min eyalik new betam tasazinaleh tiomotewos malet haymanot yelelew kehadi new ante rasih yesu akatari neh ewneten new eske ahun yekoyenew eko berehab betimoty mikiniyat new

 9. Anonymous July 20, 2013 at 12:22 pm Reply

  ያሳዝናል….. የቤተ ክርስቲያን ፈተና….አንዱ ሲፈታ ሌላ ትልቅ ፈተና ብቅ
  እግዚአብሔር ሆይ አንተው ጠብቃት

 10. Yekolow temari July 20, 2013 at 12:44 pm Reply

  Kidus abatachin wsanewn lebchachew alastelalefum mastelalefm aychlum endeza kehone YEBEFITU TEMELESE MALET NEW EGZIABHER MENGEDUN SIYAMECHACHLN BIHONS NIBURE eid wst hono man yagaltew dinget ende zelalem Hoo bibalbet man yawkal ene LEBEGO NEW ELALEW

 11. Anonymous July 20, 2013 at 1:48 pm Reply

  Let we think more about our church than individuals.

 12. Anonymous July 20, 2013 at 4:30 pm Reply

  way????????????????? nebure-ed Eliyas!!!!!! yihenen zarewnu mekawm alebachew:: werebu bikoy,,,, betekirstiyanachin bizu Abatoch aluwat!!!!!Way?????? nebure-ed eliyas!!

 13. Anonymous July 20, 2013 at 5:36 pm Reply

  ye isayas abate timotiws tewarede

 14. kiros July 20, 2013 at 7:01 pm Reply

  des ylal enkon weredu

 15. Anonymous July 20, 2013 at 11:13 pm Reply

  kedtu wedematu

 16. nitsuh miskire July 21, 2013 at 3:54 am Reply

  ተሰማ ቢሔድ ተተካ ባልቻ መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ አለ ያገሬ ሰው። ይትነግር ዘኢይገርም ይላል የኔ ብጤ ጨዋ። አንዴ ከተዘጋ እንዳይከፈት አድረጎ እንዲዘጋው ብለው ነው ‘ንቡረእድን’ የሾሙት? የጳጳሳቱን እርቅና ሰላሙን ጥረት ያከሸፈ አንዱ እርሱ ስለሆነ ማፍረስ ያውቅበታል ብለው ነው የሾሙት መሰለኝ። ጉድ ነው ዘንፍሮ አይሰማው የለ ጆሮ። ይህም ያልፋል።

 17. Anonymous July 21, 2013 at 7:22 am Reply

  መቼም በቀጣም ባይሆን በተዘዋዋሪ ትምህርትበቱም ሆነ ደቀምዝሙርቱ ሰላም እንዲያገኙ የተፈለገ አይመስልም:: ንቡረእድ ኤልያስ ከአባ ጢሞቴዎስ የከፋ እንጅ ያነሰ ጉዳት በተማሮቹ ከማድረስ አይመለስም:: ችግሩን ለመፍታት ከሆነ አሁን ንቡረድ ኤልያስን ለዚሁ ኃላፊነት የሚያስመርጥ ምን ችልታ አለው? እነዚህ ሰዎች ምኑን ያህል ለጥፋትና ስርቆት ቆርጠዉ ቢነሱ ነው? ይህን ንግዳቸዉንና ስርቆታቸዉን ለመግታት ትግሉ መቀጠል አለበት!

 18. yemeserach July 21, 2013 at 2:05 pm Reply

  ምን እየሆነ ነው ያለው ?ያሉት አስቸጋሪ ሰው ገለል ሲደረጉ ሌላ የባሰበት ሌባ(ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ) ይመደባል ? ፓትርያርኩ ምን ነካቸው የስውሩ እጅ ሰለባ ሆኑ እንዴ?

  እግዚአብሔር ሃይማኖታችንን ይጠብቅ ያሳዝናል….. የቤተ ክርስቲያን ፈተና….አንዱ ሲፈታ ሌላ ትልቅ ፈተና ብቅ
  እግዚአብሔር ሆይ አንተው ጠብቃት እንደዚህ አይነት ሰው ከሚመደብ አቡነ ጢሞቴዎስ ባይነሱ እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ይሻል ነበርቀልደኞች ናቸው! ስለዚህ የተማሪው ጥያቄ ተመለሰ ማለት ነው? ንቡረ-እድ ኤልያስ….የሰው ስጋ ለብሶ ሰው መስሎ የሚንቀሳቀስ ሰይጣን እንዴት ይመደባል? በአቡነ ጢሞቴዎስ ምትክ ሆነኛ ሰው ወይም አባት እስኪመደብ ድረስ ተቋሙ በሳቸው ስር መቆየት ነበረበት ወይም አሁኑኑ ሌላ ሁነኛ አባት/ሰው መመደብ ነበረበት:: አቡነ ጢሞቴዎስ እነ ዘላለም እያሳሳቷቸው እንጂ በራሳቸው ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸው እናውቃለን:

 19. yegermal????????????? July 21, 2013 at 2:41 pm Reply

  መቼም በቀጣም ባይሆን በተዘዋዋሪ ትምህርትበቱም ሆነ ደቀምዝሙርቱ ሰላም እንዲያገኙ የተፈለገ አይመስልም:: ንቡረእድ ኤልያስ ከአባ ጢሞቴዎስ የከፋ እንጅ ያነሰ ጉዳት በተማሮቹ ከማድረስ አይመለስም:: ችግሩን ለመፍታት ከሆነ አሁን ንቡረድ ኤልያስን ለዚሁ ኃላፊነት የሚያስመርጥ ምን ችልታ አለው? እነዚህ ሰዎች ምኑን ያህል ለጥፋትና ስርቆት ቆርጠዉ ቢነሱ ነው? ይህን ንግዳቸዉንና ስርቆታቸዉን ለመግታት ትግሉ መቀጠል አለበት!

 20. ARAYA July 22, 2013 at 7:15 am Reply

  ስለንቡረ ዕድ በትንሹ አውቃለሁ. በዓለማዊም ሆነ በመንፈሳዊ ት/ት የበለጸጉ ስለመሆናቸው ግላዊ ባህሪያቸውን በሚመለከት ግን ከድረገጾች ጭምጭምታ ባለፈ የማውቀው ነገር የለም. So,I give him the bemefit of dout. ካልሆኑ ሰዎች ጋር ይገጥማሉ ስለሚባለው እኛ ለሳቸው ጉዋደኛ የመምረጥ መብት ስለሌለን ብንተወው. ከቻልን ስርዐት(system) እንፍጠር ያለበለዚያ በሰው እስከተመራን ድረስ ሁሉን የሚያስደስት ተግባር አናከናውንም.ተመልከቱ ቅዳሴውን፣ማህሌቱን፣ሰዐታቱን….ምን ሰው ቢቀያየር በስርዐተ መንፈስቅዱስ ስለሚመሩ ላለመግባባት መነሻ እየሆኑ አይደለም. አስተዳደሩ ግን እንደምታዩት ነው. ሀላፊነት የሚጎላቸው ቡድናዊ ድረገጾች፣ራዲዎኖች፣መጽሄቶች እና ጋዜጦች ወሬ ማሞቂያ ሆኖ ቀረ.

 21. yegermal????????????? July 22, 2013 at 8:03 am Reply

  ይህች ነች ጭዋታ! ኤልያስ ሥጋ የለበሰ ጋኔን ነው! በጣም ያሳዝናል! እንዴት ይህን ወስላታ ሌባ ይወክሉታል!መቼም በቀጣም ባይሆን በተዘዋዋሪ ትምህርትበቱም ሆነ ደቀምዝሙርቱ ሰላም እንዲያገኙ የተፈለገ አይመስልም ችግሩን ለመፍታት ከሆነ አሁን ንቡረድ ኤልያስን ለዚሁ ኃላፊነት የሚያስመርጥ ምን ችልታ አለው?

  • hiruy July 22, 2013 at 2:16 pm Reply

   ንቡረዕድ ኤልያስ ማለት
   የአቁዋቁዋምና የዝማሬ መዋስእት መምህር፣የአደራረስ ይትብሃል ያሳተሙ፣ቅኔና ዜማ የሚያውቁ፣ዘመናዊ የተማሩ፣ሀሜቱ እንዳለ ሁኖ የረጅም ጊዜ የአስተዳደር ልምድ ያላቸውና የልጆች አባት በመሆናቸው ሀላፊነት ይሰማቸዋል ተብለው የሚጠበቁ……..በጥቅሉ በቤተ ክህነቱ ዙሪያ ካሉት ሰዎች የተሻለ CV ያላቸው ናቸው. ሲኖዶሱም አምኖባቸዋል. ለዘሀለፈ ስርየት ወለዘይመፅእ እቅበት ብለን እንያቸው. አሉባልታ ይቁም!!ለቡድን ሳይሆን ለእውነት እንቁም!!ይቅር ባይ እንሁን!!ንጹህ ልብ ይኑረን!!ለልበ-ንጹህ ነገሮች ሁሉ ንጹህ ሆነው ይታዩታል!!

 22. Anonymous July 22, 2013 at 8:39 am Reply

  llkkkl;l

 23. mulushewa July 22, 2013 at 2:54 pm Reply

  እንደ አልባሌ ባህታዊ ስብከት ምንድነው ሁሌ መጣልህ ማለት??? ካለእናንተ (ቅ/ሲኖዶስም ቢሆን) ለቤ/ክርስቲያን የሚያስብ የለም ማለታችሁ ነው??? የጠላችሁትን ሲያወርድ ታመሰግኑታላችሁ -ያመነበትን ሆኖም ግን እናንተ ያልወደዳችሁትን ሲሾም ታሙታላችሁ what a twist using of double standard!!!!እባካችሁ በሀይማኖት ህፀፅ እንደሌለባችሁ እናውቃለን. ግን የስነ-ምግባር ህፀፅ ያሠጋችሁአል. ምንድን ነው ሰውን ይህን ያህል ማሳደድ-ማውገዝ!! ወደፊት ውግዘት በሁለት ይከፈላል፤በድረገፅ እና በቅ/ሲኖዱስ እንዳይባል እሰጋለሁ!! U r not doing enough to create an ardent, well informed and reasonable EOTC follower, rather u r incubating a backbiting group who shot blindly hiding in z cave of ur blog towards any ur-labeled person.

 24. guest July 22, 2013 at 9:05 pm Reply

  አቶ ሂሩይ

  ለኤልያስ ምን ችሎታና ብቃት እንዳለው የፈለከውን ያህል መቀባትና ማምካሸት መብትህ ነው:: እውነታው ግን ግልብና ግልፍጥ ባልጌ ነው:: የኤልያስ ችሎታ ክፋትና ጥላቻና ተንኮል ብቻ ነው::

  በተለይም እሱን ለኮለጁ ኃላፊ ማድረግ ድፍረት ብቻ ሳይሆን ስድብና ምጸት በተለይም ተማሮቹን በበልረጠ ለመጉዳት ታስቦ መሆን አለበት!

 25. Anonymous July 23, 2013 at 1:16 pm Reply

  Abune Timotewosin awurdo Eliyas Abrihan meshom “Ke ditu wede matu” ayihonim???

 26. Anonymous July 23, 2013 at 2:23 pm Reply

  Dear Haras,

  I advice you to monitor comments given to news you are producing. You are also not producing standard news which is neutral. You always post completely a one sided message. Please don’t abuse and confuse the people. I don’t know why people around the church are this much against some thing good. Why such insolent words are posted. We are morally dead when we are insulting our church fathers. Yes, they might be wrong and we may not also be please with what they are doing. We may question and react for their doing but it should not at all be with our rude act. Most of them at least are older than us. They should at least be respected with their age. Forget about their being religious fathers. For what they are doing wrong there God who judge them. Why we are taking their Sin if they do any thing wrong? Emotions are driving us in a more wrong way. People in this forum are simply with Id behavior. Things in the church are not as easy as we talk. We must be careful. We must knee down and pray instead. The problem is people in this forum misunderstand people who are calmly see things. Last time it was me who suggested praying instead of mob. But most qoted me as if I were who they call him ‘Zelalem’. The entire move in the process does not seem good for me since things were more of force that in a calm and justifiable actions. Please still there is time and the solution give also is already stated to be temporary. Let’s do for lasting solution and fruitful output. Please Egziabiher sile afachin endayqesifen. Manim Kahin kifu bisera Egziabiher yidagnewal egna gin be andebetachin mikineyat teteyaqiwoch anihun. Mekari hasaboch kalu kesidib betsedu kalatoch memeker, meqawemim yichalal.

 27. Taddese July 23, 2013 at 3:18 pm Reply

  በሀሳብ፣ በንግግር እና በድርጊት ከሚሠራ ኃጢአት እግዚአብሔር ይፍታ ሚል ካህን ኑዛዜ አለ፤ እነዚህ ሰዋች፣ በሀሳብ ክፋትን አስበው በአፋቸው ስድብን የሚናገሩ ኢ-ክርስቲያን ናቸው፡፡ መልአኩ ስድብ ቃል አልተናገረም፡፡ እግዚአብሄር ይገስጻው፡፡ ከውሾች የስድብ ጩሐት እንጅ ምርቃት አይገኝም፡፡

 28. Anonymous July 23, 2013 at 4:11 pm Reply

  thanks God for everything

 29. yegermal????????????? July 23, 2013 at 4:25 pm Reply

  yetebalew hulu weshet hone aygermem
  ????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????

 30. Anonymous July 24, 2013 at 5:37 am Reply

  Egziabher bicha yihen gize asalifo selamun gize yamtaw

  • Esemelealem Meheretu July 27, 2013 at 9:38 am Reply

   ‹‹ትሻልን ትቼ ትብስን አገባሁ ማለት ይሄ ነው››
   ‹‹የቀን ጅብ ይሉሃል ንቡረ ዕድ ኤልያስ ነው››
   ንቡረ ዕድ ኤልያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት ከአንዱ ደብር ወደ አንዱ ደብር ወደሌላው ለመቀየርና ለመቀጠር ከ 15,000ሺ ብር በላይ ጉቦ እንደሚጠይቅ አቀባዮቹ የአዲስ አበባ አድባራት ፀሃፊዎችና ቁጥጥሮች ያውቃሉ ምስክርነታቸውን ቢጠየቁ ለሆዳቸው ካላደሩ ሊመሰክሩ ይችላሉ፡፡
   ንቡረ ዕድ ኤልያስ የበላይ ኃላፊ የሚሆንበት መንፈሳዊ ኮሌጅ ምን ዓይነት ኮሌጅ ሊሆን ነው፡፡ ምክንያቱም ግለሰቡ መንፈሳዊውንም ሆነ ለኮሌጅ የሚመጥን ችሎታ የሌለው በዓለማዊ ጥቅም የታወረ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: