የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የለውጥ ግንዛቤን የሚያስጨብጡ የምክክር እና ሥልጠና ጉባኤዎችን ማካሄድ ጀመረ

 • የምክክር ጉባኤውን ተከትሎ በሀ/ስብከቱ እና በክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ ይካሄዳ
 • የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶችን በቢሮ ዕቃዎች ለማደራጀት የ1.6 ሚልዮን ብር በጀት ተመድቧ
 • በ1.6 ሚልዮን ብሩ ጽ/ቤቶቹን ለማደራጀት የተቋቋመው የዕቃ ግዥ ኮሚቴ÷ ረዳት ሊቀ ጳጳሱን በሙስና ቀለበት ውስጥ በማስገባት የለውጥ ሂደቱን ለመቆጣጠር በሚያልሙ የለየላቸው ሙሰኞች የሚንቀሳቀስ መኾኑ ሀ/ስብከቱን ለከፋ ትችት እየዳረገው ነው

 

የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በመልካም አስተዳደር፣ በፋይናንስ አያያዝና በሰው ኀይል አመዳደብ እንዲሁም በስብከተ ወንጌል አሰጣጥ የሕግ የበላይነትን አክብሮ እንዲሠራ በቋሚ ሲኖዶሱና በመንበረ ፓትርያሪኩ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡ ይህም የመንበረ ፓትርያሪኩ መቀመጫ የኾነው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ለሁሉም አህጉረ ስብከት በሞዴልነት መጠቀስ ይገባዋል ከሚል እምነት የመነጨ መኾኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአድባራትና ገዳማት የሚገኙ መሪዎችንና አገልጋዮችን የመሪነትና የሥራ ብቃት ደረጃ ከፍ በማድረግ ስለታሰበው የአሠራር ለውጥ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የታቀደበት ወርክሾፕ፣ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አዳራሽ ተጀምሯል፡፡His Grace Abune Estifanos

በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ስለ ምክክር እና ሥልጠና ጉባኤው ዓላማ አስመልክቶ ሲናገሩ፣ ሀ/ስብከቱ በአስተዳደር፣ በፍትሕ መንፈሳዊ፣ በማኅበራዊ አገልግሎትና በምጣኔ ሀብት በኩል በሕግና ሥርዐት በመመላለስና በመደራጀት ውጤታማ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡ በርካታ ዕቅዶቹን ተግባራዊ ለማድረግ በሀ/ስብከቱ የሚገኙ የሥራ ሓላፊዎችና ሠራተኞች በለውጡ አጀንዳዎች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በዘርፉ የላቀ ክህሎትና ዕውቀት ባላቸው ባለሞያዎች የሥልጠናና ምክክር መርሐ ግብሩን ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

ከሀ/ስብከቱ የሥራ ግዝፈትና ካለው ሰፊ የፋይናንስ ፍሰት አንጻር ሲመዘን ችግሩ የተጋነነና የገዘፈ እንዳልኾነ የሚያምኑት ብፁዕነታቸው፣ ተጠቃሽ ጉድለቶችን ሲዘረዝሩ፡-

 • የመልካም አስተደር ግድፈትና ማሽቆልቆል፣
 • ዘመኑን የዋጀ የምጣኔ ሀብት አስተዳደርና ዘመናዊ የሒሳብ አሠራር ክፍተት፣
 • የእርስ በርስ አለመናበብና የጎጠኝነት ስሜት፣
 • ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዐት አለመዘርጋት
 • የተአምኖ ግብርና እና የሥነ ምግባር ደረጃ ዝቅ ብሎ መገኘትና የመሳሰሉትን

እንደኾኑ ጠቁመዋል፡፡

በሀ/ስብከቱ እና በሥሩ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት የመልካም አስተዳደር ትርጉሙ በአብዛኛው ተዛብቷል፡፡ ብፁዕነታቸው እንዳብራሩት፣ መልካም አስተዳደር÷ ከእግዚአብሔር በተሰጠን ሥልጣንና ሓላፊነት የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት በሁሉም መስክ በጎ አርኣያነት ያለው መልካም እረኛ መኾን ማለት ነው፡፡ በመልካም አስተዳደር መርሕ መሠረት ‹‹ሓላፊ ነኝ፤ አዛዥ ነኝ›› ከሚል መኮፈስ ይልቅ የአገልጋይነትና የመሪነት ስሜት መላበስ ተገቢ ነው፡፡

‹‹የምንመራትና የምናገለግላት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር በደሙ የዋጃት እንደመኾኗ መጠን የተቀበልነው አደራ እጅግ ታላቅና በልዑል እግዚአብሔር ፊት ቀርበን ዋናውን ከትርፍ ጋራ የምንጠየቅበት ነው፤›› ያሉት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ፣ የምንመራቸው ሰዎችና የምናስተዳድረው ሀብት የእግዚአብሔር ሀብት ነውና ሓላፊነታችን እጅግ ከባድ እንደኾነና አገልግሎታችንም በዚሁ አቅዋምና መንፈስ ሊቃኝ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

ከትላንት በስቲያ በተጀመረውና በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የሥልጠናና ምክክር ጉባኤ፡-

 • መልካም አስተዳደር እና ጠቀሜታ
 • የግዥ ሥርዐት፣ ተያያዥ ችግሮቹና የመፍት አቅጣጫ

 • ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራር፣ አያያዝና ተጠያቂነት
 • የዕቅድ፣ ቁጥጥር፣ ክትትል እና ግምገማ ሥርዐት
 • ውጤታማ መሪነት ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት
 • ሙስናና ተያያዥ ችግሮች
 • የግጭት መንሥኤ እና አፈታት

የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች የተካተቱ ሲኾን የዘርፉ ባለሞያዎችና ምሁራን ከቤተ ክርስቲያናችን ተጨባጭ ችግሮች ጋራ በማዛመድ በሚያቀርቧቸው መነሻዎች ተሳታፊዎቹ ውይይት እያካሄዱባቸው ይገኛሉ፡፡ ለዚሁ መርሐ ግብር ከተመረጡ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችና ሠራተኞች ባሻገር ከ82 አድባራትና ገዳማት የተውጣጡ 574 ያህል አስተዳዳሪዎች፣ ምክትል የሰበካ ጉባኤ ሊቃነ መናብርት፣ ጸሐፊዎች፣ የቁጥጥር ሓላፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ ገንዘብ ያዦች እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች የመርሐ ግብሩ ዋነኞቹ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የአሁኑን ጨምሮ በሁለት ዙሮች ከሚካሄደው የሥልጠናና ምክክር ጉባኤ ጋራ በተያያዘ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአዲስ መልክ በተሠራው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በሚቋቋሙት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ እንደሚካሄድ ተዘግቧል፡፡ ምደባው የተካሄደው ለዚሁ ዓላማ በተቋቋመው መዳቢ ግብረ ኀይል በተሰበሰበ የሠራተኞች የትምህርት ዝግጅትና የአገልግሎት ልምድ ማስረጃ መሠረት መኾኑ ታውቋል፡፡

በአዲሱ አደረጃጀት ሀ/ስብከቱ ለመልካም አስተዳደር በሚያመቹ ሰባት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲኾን በቋሚ ሲኖዶሱ ተሻሽሎ በጸደቀለት ልዩ መተዳደርያ ደንብ መሠረት በሥልጣንና ሓላፊነት ለመሥራት እንደሚያስችለው ተመልክቷል፡፡ እስከ ጥቅምት ወር ፳፻፮ ዓ.ም ብቻ በጊዜያዊነት እንደሚያገለግል የተነገረው ይኸው ምደባ፣ የሓላፊዎችን የትምህርት ዝግጅትና የአገልግሎት ልምድ ለየሥራ ዐይነቱና ደረጃ በሚያስፈልገው ትክክለኛ የሰው ኀይል ትመና/ምጠና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጧል፡፡

ይህን በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ሥራንና ሠራተኛን በማገናኘት ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ በማስቀመጥ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለው የአሠራር ሂደት በቁርጠኝነት እንደሚከተል የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የምክክርና ሥልጠና መርሐ ግብሩን ዓላማ ባብራሩበት ንግግራቸው አስታውቀዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ይህን ይበሉ እንጂ በአሁኑ ወቅት ሀ/ስብከቱ የገባበትን ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለበት የአሠራር ሂደት በቁርጠኝነት እንዳይከተል ማነቆ የኾኑበት ሰዋዊ የአመለካከትና የተግባር ችግሮች እንዳሉበት በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ ከሰሞኑ የሐላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ ጋራ በተገናኘ ተበራክቷል የሚባለው የተጭበረበሩ የትምህርትና የአገልግሎት ልምድ ማስረጃዎች ማቅረብ (forgery) የችግሩ ጉልሕ ማሳያ ነው፤ ነገሩ የሚባለውን ያህል እውነት ከኾነ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ በመመደብ ሥራን ከሠራተኛው ለማሰናኘት የሚደረገውን ጥረት ያኮላሻል፤ የመልካም አስተዳደር ተስፋውን በወሬ ያስቀራል፡፡ ስለኾነም ለትምህርትና ልምድ ማስረጃዎቹ አንዳች ዐይነት የማረጋገጫ ሥርዐት የግድ ሳያስፈልግ አይቀርም – ለአሁኑ ምደባ ባይደርስ በሂደት!

ሌላው ማነቆ ሰባቱን የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች ለማደራጀት የታቀደውን የቢሮ ዕቃዎች ግዥ ለማከናወን ለተቋቋመው ኮሚቴ የተመረጡት ሰዎች ማንነት ነው፡፡

Advertisements

3 thoughts on “የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የለውጥ ግንዛቤን የሚያስጨብጡ የምክክር እና ሥልጠና ጉባኤዎችን ማካሄድ ጀመረ

 1. Xxx July 18, 2013 at 7:53 am Reply

  Adis abeba hagre sebket lewdfit yeyazew eked melkam new

 2. Xxy July 18, 2013 at 7:54 am Reply

  Gimarow tiru naw fethamewun yasamereln

 3. adugna August 6, 2013 at 2:34 pm Reply

  የተጭበረበሩ የትምህርትና የአገልግሎት ልምድ ማስረጃዎች ማቅረብ..why? Yawum be Egziabher bet?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: