በቅድስት ሥላሴ መ/ኮሌጅ ጉዳይ ቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

 • ደቀ መዛሙርቱ ጉዳያቸው በቅ/ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ እንዲታይ ጠይቀዋል፤ ቅ/ሲኖዶሱ ከመንግሥ ጋራ በመነጋገር የደኅንነት ጥበቃ እንዲደረግላቸው አመልክተዋ
 • የልዩ ጽ/ቤቱን ለቃችኹ ውጡ ትእዛዝ ‹‹ሕግን የጣሰና ለከሳሽ ያደላ›› በሚል ተቃውመውታል
 • የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና የጠ/ቤ/ክህነቱ ዋ/ሥራ አስኪያጅ ደቀ መዛሙርቱን እያረጋጉ ነው
 • የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ ከደቀ መዛሙርቱ ጎን ቆመዋል ተብሏል
 • ኹኔታው ያሳሰባቸው የማታ ተማሪዎች ተወካዮች ከቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጋራ ተወያይተዋል
 • የኮሌጁ መምህራን አቡነ ጢሞቴዎስ ከበላይ ሓላፊነታቸው እንዲነሡ መጠየቃቸው ተሰምቷል
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያን ኮሌጁን በበላይነት የመቆጣጠር ሥልጣን የዋ/ሥ/አስኪያጁ ነው
 • የኮሌጁ ቦርድ እና አስተዳደሩ ብቃት ባላቸው ባለሞያዎች እንዲደራጅ የጠየቀው አጣሪ ኮሚቴው ቦርዱ ተጠሪነት ከቅ/ሲኖዶስ ይልቅ ለጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንዲኾን በሪፖርቱ መክሯል
 • ‹‹ኮሌጁ እንደ ሀ/ስብከቴ ነው፤ በኮሌጁ ጉዳይ ጣልቃ አትግቡብኝ!›› /አቡነ ጢሞቴዎስ/
 • ‹‹የኮሌጁን ጉዳይ ለኔ ተዉት!›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/

 

EOTC_HeadQuarterየቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር እስከ መጪው ፳፻፮ ዓ.ም መስከረም ወር አጋማሽ ድረስ እንደተዘጋና ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን እስከ ዛሬ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በትላንትናው ዕለት በይፋ ያወጣውን ማስታወቂያ የተቃወሙ የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ቅ/ሲኖዶሱ ለአስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

ሐራዊ ምንጮች ከመንበረ ፓትርያሪኩና ውዝግቡ አፋጣኝ እልባት እንዲያገኝ በበጎ ፈቃድ ከሚንቀሳቀሱ አካላት እንደተረዱት÷ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና አራቱ ተተኪ/ተለዋጭ የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔና ያወጣውን ማስታወቂያ በመቃወም በኮሌጁ ወቅታዊ ኹኔታ ላይ ለመወያየት አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ለቅ/ሲኖዶሱ አባላት አድርገዋል፡፡ ስብሰባው እስከ መጪው ዐርብ፣ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ድረስ ሊጀመር እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ቅ/ሲኖዶሱ በአስቸኳይ ስብሰባው÷ ልዩ ጽ/ቤቱ በደቀ መዛሙርቱ ላይ ያሳለፈው ውሳኔና ያወጣው ማስታወቂያ ከሕገ ቤተ ክርስቲያንና ውዝግቡን ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ካቀረባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች አንጻር ያለው አግባብነት ይፈተሻል፤ ኮሚቴው ከአጭርና ከረጅም ጊዜ አኳያ የዘረዘራቸውን የማስተካከያ ርምጃዎች መርምሮ ተፈጻሚ እንዲኾኑ መመሪያ ይሰጣል፤ ከዚህም ባሻገር አካላዊ ጤንነታቸው ለያዙት ሓላፊነት ብቁ አያደርጋቸውም የተባሉትን የኮሌጁን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ የማንሣት ርምጃም ሊወሰድ ይችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

የቋሚ ሲኖዶሱ ሰብሳቢ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ቢኾኑም በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፲/፪/ሀ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶሱ አስቸኳይና ድንገተኛ ጉባኤ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ወይም ቋሚ ሲኖዶሱ በሚያደርጉት ጥሪ ሊካሄድ ይችላል፡፡ በሕመምና በልዩ ልዩ ከአቅም በላይ በኾነ ምክንያት አንዳንድ አባላት ባይገኙ እንደ አጀንዳው ዐይነት /የሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ወይም የአስተዳደር መኾኑ/ ተለይቶ ከዚህ አኳያ የምልአተ ጉባኤው መሟላት ተወስኖ ስብሰባው ሊደረግ እንደሚችል በዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ ፫/ሀ እና ለ ላይ ተደንግጓል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ከሐምሌ ፰ – ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ኮሌጁን እንዲለቁ በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ ፊርማ በወጣ ደብዳቤ የተላለፈው ትእዛዝ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ግዳጁን ሲፈጽም አልታየም፡፡ በምትኩ በመማክርታቸው ሰብሳቢነት በቀጣይ ርምጃቸው ላይ ሲወያዩ ያደሩት ደቀ መዛሙርቱ ‹‹እንደ ወንጀለኛ አይቶናል›› ያሉት የልዩ ጽ/ቤቱ ትእዛዝ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው በመግለጽ በዐሥር ነጥቦች ያህል የተከፈሉ ጥያቄዎችን የያዘ ደብዳቤ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት አድርሰዋል፡፡

የደቀ መዛሙርቱ ደብዳቤ÷ ፓትርያሪኩ ከኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ጋራ በመስማማት በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል ያስተላለፉት ትእዛዝ ‹‹ሕግን መሠረት ያላደረገ፣ ሚዛናዊነት የጎደለውና ለተከሳሽ ወገን ያደላ›› እንደኾነ ተችተዋል፡፡ ትእዛዙን በፊርማቸው ያወጡት የልዩ ጽ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ እንደ ኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ አባልነታቸው ተከሳሽ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡ ከጥያቄዎቻቸውም መካከል፡-

 • ምልአተ ጉባኤ እንዲጠራና ጉዳዩ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ታይቶ እንዲወሰንበት፣
 • ለችግሩ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የቆየው ቦርዱ ሓላፊነቱን ባለመወጣቱ ተጠያቂ እንዲኾን፣
 • ሓላፊነቱን ያልተወጣው ቦርዱ ተሟልተው ባልተገኙ አባላቱ ለፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እንዲቋረጥ የሰጠው የውሳኔ መነሻ ሕገ ወጥ እንደኾነ፣
 • በኮሌጁ የቀን መደበኛና የማታ ተከታታይ መርሐ ግብር ተማሪዎች መካከል ልዩነት በማድረግ የቀኑ መርሐ ግብር እንዲቋረጥ መወሰኑ አግባብነት እንደሌለው፣
 • የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት እንዲገለጽልን፣
 • ፓትርያሪኩ እስከ አሁን ስላላነጋገሩን እንዲያነጋግሩን፣
 • የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ከመንግሥት ጋራ ተነጋግሮ የደኅንነት ጥበቃ እንዲያደርግልን

የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡

ዛሬ ማምሻውን ከኮሌጁ እንደተሰማው የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስና የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራሮች አማካይነት ተማሪዎቹን የማረጋጊያ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በደቀ መዛሙርቱ ለቀረቡት ጥያቄዎችም ኹነኛ ምላሽ ለመስጠት ጥረት እንደሚደረግ መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡

ኹኔታው ካሳሰባቸውና በበጎ ፈቃድ ተነሣስተው ለመፍትሔው ግፊት ከሚያደርጉ አካላት መካከል በማታው መርሐ ግብር ተማሪዎች የተመረጡ ተወካዮች ከቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊው ጋራ በዛሬው ዕለት መወያየታቸው ተነግሯል፡፡

በተመሳሳይ አኳኋን የችግሩን ስዕበት ለማስገንዘብ በሌሎች አገልጋዮችና ምእመናን በተደረገ ጥረት በፓትርያሪኩ አቋሞች ላይ ወሳኝ ተጽዕኖ አላቸው የሚባሉት በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩንና የኮሌጁን ሊቀ ጳጳስ መልሶ ከማግባባት ጀምሮ የአጣሪ ኮሚቴው የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲተገበሩ አቋም ከያዙት የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ጎን መቆማቸው ተገልጧል፡፡

ከኮሌጁ ተማሪዎችና አንጋፋው ተቋም የሰነበትበት ውዝግብ ከሚያሳስባቸው አገልጋዮችና ምእመናን በጠነከረ አኳኋን የኮሌጁ መምህራን ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት አቀረቡት የተባለው የፊርማ አቤቱታ ደግሞ የበላይ ሓላፊው ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ከሥልጣናቸው እንዲነሡ የሚጠይቅ ነው፡፡ ላለፉት 14 ዓመታት ኮሌጁን በበላይ ሓላፊነት (ዋና ዲን?) የመሩት ሊቀ ጳጳሱ÷ ከዕርግናም ከጤንነትም የተነሣ በአሁኑ ወቅት አጥርተው ለማየት ለመስማትም የሚሳናቸው መኾኑና ለረጅም ጊዜ የቆዩትን ያህል ከግለሰቦች ጋራ ያዳበሩት የጥቅመኝነት ግንኙነት በአንድ በኩል፣ የኮሌጁ ያለበት ትውልዳዊ ተቋማዊ ተልእኮ ክብደት በሌላ በኩል ከሓላፊነት የመገለላቸውን ጥያቄ አግባብነት ለክርክር ሊያቀርበው እንደማይገባ ይታመናል፡፡

በዚህ ረገድ ወሳኝ አቋም ለመውሰድ በእጅጉ የተቸገሩ መስለው የሚታዩት ከበላይ ሓላፊው ጋራ የቆየና የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው የሚባሉት ፓትርያሪኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብቻ ናቸው፡፡

ወዳጅነቱ፣ ቅዱስነታቸው በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት በቀረበላቸውና ለተፈጻሚነቱም እንደተስማሙበት የተዘገበው የአጭርና የረጅም ጊዜ የማስተካከያ ርምጃዎች ተግባራዊ እንዳይኾን ማነቆ ኾኗል፡፡

ወዳጅነቱ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፴ ንኡስ አንቀጽ ፲፬ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የቤተ ክርስቲያኒቱን የትምህርት ተቋማት በበላይነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ የተሰጣቸው ሥልጣንና ተግባር በአቡነ ጢሞቴዎስ እልክ ሲናድ በዝምታ የታለፈበት ነው፡፡

ወዳጅነቱ÷ ቋሚ ሲኖዶሱ ለኮሌጁ በዲንነት የመደባቸውን ሓላፊ ለአቡነ ጢሞቴዎስ ምቾት እስከ ማስለወጥ የተደረሰበት ነው፡፡

የወዳጅነቱ ገጽታ ሲከፋ÷ በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ‹‹መ/ር ዘላለም ከላይ እርሳቸውን በሚመለከት በተዘረዘሩት ምክንያቶች ከኮሌጁ ተነሥተው ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሚመድባቸው ቦታ እንዲመደቡ ቢደረግ፣ የቀረበባቸው የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ በሚመለከት እንዲጣራ ቢደረግ›› /ገጽ 17/ የሚል የመፍትሔ ሐሳብ የቀረበበት ዘላለም ረድኤት፣ ቋሚ ሲኖዶሱ ከመደባቸው ሓላፊ ይልቅ ለዲንነት ሲታጭ በጽናት ከመቃወም ይልቅ የመጎናበስ ዝንባሌ የታየበት ነው፡፡

ኮሚቴው በዘላለም ረድኤት ላይ ላቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መነሻ ያደረጋቸው ምክንያቶች፡-

 • ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ኮርሶችን ያለሞያቸው ይዞ ማስተማ
 • ለሚያስተምሩት ኮርስ ብቁ ኾኖ አለመገኘት
 • የቅንነት ጉድለት
 • በሥራ መለገም
 • አለመግባባቶችን ወይም ነገሮችን ማባባስ
 • ከሁሉም በላይ የሃይማኖት ሕጸጽያስተምራሉ /ገጽ 14/

የሚሉ፣ ቅዱስነታቸውና ቤተ ክህነታችን ከገቡበት የመዋቅርና አሠራር ለውጥ ምዕራፍ ጋራ ከቶም የማይጣጣሙ መኾናቸው ይሄ ወዳጅነት በተቋማዊ መሻሻል ተስፋችን ላይ የጋረጠውን አደጋ በጉልሕ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህም አንጻር በብዙዎች ዘንድ የመንበረ ፓትርያሪኩ በተለይም የቅዱስነታቸው ቁርጠኝነት የተመዘነበትና በአንዳንዶችም ዘንድ በድክመት የተገመገመበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡

በመንፈሳዊ ኮሌጁ መደበኛ ደቀ መዛሙርት እና በአስተዳደሩ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት በማጣራቱ ሂደት አጣሪ ኮሚቴው ሁሉንም የኮሌጁን ባለድርሻ አካላት /የተማሪዎች ካውንስል፣ ደቀ መዛሙርት በየክፍላቸው፣ መምህራን፣ የኮሌጁ አስተዳደር አባላት፣ የኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት/ ማወያየቱንና የኮሌጁን ሕንጻዎች በአካል ተዘዋውሮ መጎብኘቱን በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ በአስተዳደርና በአካዳሚክ ዘርፎች ድክመቶችንና ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት አኳያ እየለየ ዘርዝሯል፡፡

የኮሌጁ አስተዳደር በአጣሪ ኮሚቴው የቀረበለትን የአጭር ጊዜ ሥራዎች በሙሉ ፈቃደኝነት ተቀብያለኹ ካለ በኋላ ወደ ሥራ አለመግባቱ አጣሪ ኮሚቴው የኮሌጁ አስተዳደር ራሱን ለማረም ዝግጁ አለመኾኑን አስገንዝቦታል /ገጽ 8/፡፡ ለመፍትሔውም የአስተዳደሩ አደረጃጀት ተፈትሾ ብቃት ባላቸው ባለሞያዎች /የኮሌጅ ዲን፣ ምክትል አካዳሚክ ዲን እና ምክትል አስተዳደር ዲን/ እንዲደራጅ፣ በመስኩ የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ ያለው ሰው ተፈልጎ እንዲሾም መክሯል፡፡

Board members of the college

የኮሌጁ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት

ኮሌጁን በበላይነት የሚመራው በቅዱስ ፓትርያሪኩ የሚሠየም ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ የኾነው ሥራ አመራር ቦርድ÷ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሃይማኖታቸውና በምግባራቸው የታወቁ ኦርቶዶክሳውያን ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች እንዲገኙበት ነበር የሚታሰበው፡፡ ነገር ግን ሪፖርቱ እንደሚያትተው፣ የቦርዱ አባላት የኾኑት ሊቃነ ጳጳሳት በስብሰባ አዘውትረው አይገኙም፤ በመደበኛ ስብሰባ የሚገኙት ከምእመናን የተመረጡ አባላት ሲኾኑ ስብሰባውን የሚመሩትም ምክትል ሰብሳቢው ዶ/ር ተጠምቀ መሐሪ ናቸው፡፡ ይህም ሃይማኖት ነክ የኾኑ ጉዳዮች ለውሳኔ ሲቀርቡ ለመወሰን አዳጋች እንደሚያደርግባቸው ገልጸዋል /ገጽ6/፡፡

ቦርዱ ለኮሌጁ የሚጠቅሙ ስትራተጅዎችና ፖሊሲዎች ከማውጣት ይልቅ በየዐሥራ አምስት ቀኑ እየተገናኘ አስተዳደሩ ሊሠራ የሚገባውን ሥራ ሠርቶ የሚለያይ ነው፡፡ የኮሌጁ ደንብ እንደሚያስረዳው ኮሌጁ አንድ ዋና ዲንና በሥሩ አካዳሚክ እና የአስተዳደር ም/ዲኖች እንደሚኖሩ ቢገለጽም ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጢሞቴዎስ የኮሌጁ ዋና ዲን ወይ የበላይ ሓላፊ ሊ ጳጳስ መኾናቸው በግልጽ እንደማይታወቅ መነገሩ በሪፖርቱ ተዘግቧል፡፡

ለመፍትሔውም በኮሌጁ ውስጥ ጠንካራና ውሳኔ የሚሰጡ የአስተዳደር ሰዎች እንዲኖሩ፣ የቦርዱ ተጠሪነት ለቅ/ሲኖዶስ ከሚኾን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንዲኾን፣ ቦርዱ ኮሌጁን በባለቤትነት የሚያስተዳድር በመኾኑ በግቢው ውስጥ ችግር ሲከሠት ከሩቅ ኾኖ የሚያይ ብቻ ሳይኾን በቅርበት እየተከታተለ አቅጣጫ የሚሰጥ ኾኖ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ፣ በቋሚ የጊዜ ሰሌዳ ከኮሌጁ ማኅበረሰብ ጋራ እየተገናኘ የታዩ ችግሮችን በመፈተሽ ምላሽ እየሰጠ የተሻለ የሥራ ግንኙነት እንዲኖር እንዲያደርግ የሚሉ የመፍትሔ ሐሳቦች በኮሚቴው ተሰጥተዋል፡፡

በዚህና በመሳሰለው መልኩ በየዘርፎቹ/የደቀ መዛሙርቱን አመላመልና ዲስፕሊን ጨምሮ/ የተነቀሱት የአሠራር ክፍተቶች ተስተካክለው የኮሌጁ የመማር ማስተማር ሥራ ቤተ ክርስቲያኒቱ በምትፈልገው ኹኔታ ይካሄድ ዘንድ በአጭርና በረጅም ጊዜ ተለይተው የቀረቡት የማስተካከያ ርምጃዎች ከሞላ ጎደል ተገቢነት ያላቸውና ለአፈጻጸማቸውም የበላይ አካልን አስቸኳይ መመሪያ የሚጠብቁ ናቸውና ከአስቸኳይ ስብሰባው ዐቢይ ውሳኔ እንደሚተላለፍ ተስፋ ይደረጋል፡፡

Advertisements

10 thoughts on “በቅድስት ሥላሴ መ/ኮሌጅ ጉዳይ ቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

 1. Anonymous July 17, 2013 at 8:07 am Reply

  Des yilal cher were yaseman!

  • Tigabu July 18, 2013 at 1:04 pm Reply

   firde gemdel banhon tiru new aseteyayet senesetim krstina asasebon kehon melkam new semetachin bemekotater bihon tiru new! kalhon gin yegil kursho ayidelim bekrstinaw balemum yemiyawata ayimeselegnm!!

 2. antoni July 17, 2013 at 10:34 am Reply

  betam asfelagi new
  enen yegeremegn gen yeqedus patriyariku zemeta new malete lechegeroch afatagn yemeftehe ermeja liwesdu yegeba neber degmom bezih aynet chela kalu ketayu yebetekerstiyan guday endet lihon new?
  musenan endemiwagu begelts eyetenageru neber tadya musena malet yehew alneberem?
  …………………………….lehulum kom belew biyasbubet betam melkam new

 3. kibru July 17, 2013 at 1:20 pm Reply

  እኔ የሚገርመኝ የፓትርያርኩ ነገር ነው በጣም ያሳዝናል፡ ተማሪዎቹ ያናግሩአቸው ዘንድ በተደጋጋሚ ሲሄዱ አሁን ተኝተዋል ይባልና ሲጠብቁ ሲጠብቁ ውለው በረሃብ ላይ ድካም በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ይመለሳሉ የልጆቹ ረሃብ የማይገደው አባት ብሎ ለመጥራት ያስቸግራል፡፡ በሚቀጥለው ደግሞ ሲሄዱ አምባሳደር እያነጋገሩ ነው ይባላል እርሱም ይሄዳል ደክሟቸዋል ይባላል ተማሪዎቹ ይመለሳሉ፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያን አምባሳደር የሆኑትን ደቀ መዛሙርት አላናግርም ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ችግር እያዩ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለት ምን ማለት ነው? የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በጓደኝነት መለወጥ ፍርድ ማጓደል ይህ ዓይነት አስተሳሰብ ለፖትርያርክነት ቀርቶ ለአንድ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት አይመጥንምና ቢያስቡበት ይሻላል በዙሪያዎችዎ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሙዳየ ምጽዋት ገልብጥ ሁሉ ይፈትሹ እርስዎም እራስዎን ይፈትሹ ምን እያደረግሁ ነው ብለው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ዓይነት ሰው አይደለም የምትፈልገው የነበረው ተቅበዝብዞ የኖረው በግ የሚሰበስበው ነበር የሚፈልገው ነገር ግን እርስዎ ውጡ እያሉ ደቀ መዛውርቱን ያባራሉ የቤተ ክርስቲያንን ዓይን ለማጥፋት፣ አንድ ፖትርያርክ ቀኑን ሙሉ እንቅልፍ መተኛት ምንድን ነው አረ እባካችሁ ምከሯቸው፡፡እግዚአብሔር ይሁናቸው፡፡

 4. asraw July 17, 2013 at 2:45 pm Reply

  የፓትርያርኩ ነገር በጣም ያሳዝናል አረ እባካችሁ ምከሯቸው፡፡እግዚአብሔር ይሁናቸው፡፡

 5. kiros July 17, 2013 at 5:02 pm Reply

  patriyarku yale enklf lela ayawkum musna ewagalehu mallet tegnito new ende tim bcha lela minm yelem iy mathis

 6. kiros July 17, 2013 at 5:05 pm Reply

  kihaa

 7. Anonymous July 17, 2013 at 5:24 pm Reply

  ?

 8. Anonymous July 18, 2013 at 12:16 pm Reply

  ፓትርያርኩ እንደተመረጡ ሰሞን የምንሰማቸው ውሳኔዎች እና ጥቃቅን ማስተከከያዎች ሁሉ እንድናመሰግናቸው ያደረገን መስሎን ነበር። ለካ ገና ነው። መጽሐፉም – ኢትነዐዶ ለሰብእ ዘእንበለ ትርአይ ተፍጻሜቱ – ይላል እኮ!!!
  ስለቤ/ክ ብለው ምናለ ወንዘኛነቱን ትተው የምስኪኖቹን ተማሪዎች ጩኽት ቢሰሙ??? ልብ ይስጥልን!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: