ሰበር ዜና – ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ

 • የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እስከ መስከረም አጋማሽ ፳፻፮ ዓ.ም ድረስ እንዲቋረጥ ተወስኗል
 • ደቀ መዛሙርቱ በቀጣ ርምጃዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው

Letter from the special office of the Patriarchየቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ፡፡

ልዩ ጽ/ቤቱ ዛሬ፣ ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከቀትር በኋላ በኮሌጁ የለጠፈው ማስታወቂያ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ማስታወቂያው ከወጣበት ከዛሬ ሐምሌ ፰ እስከ ነገ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

‹‹የቀኑ ትምህርት የተቋረጠ መኾኑን ስለማሳወቅ›› በሚል በቁጥር ል/ጽ/445/339/05 በቀን 8/11/05 ዓ.ም በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ ተፈርሞ በአድራሻ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተላከው ይኸው ደብዳቤ፣ የቀኑ መርሐ ግብር የተዘጋው ከኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ከተመረመረ በኋላ መኾኑን አስታውቋል፡፡

ከመጋቢት ፬ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ጀምሮ የኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ሲስተጓጎል መቆየቱን የልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ ጠቅሶ፣ ከሐምሌ ፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ የኮሌጁን ቢሮ በመዝጋትና የመንፈቅ ዓመቱን የማጠቃለያ ፈተና ለመፈተን የመጡ መምህራን ወደ ቢሮ እንዳይገቡ በመከልከል በፈቃዳቸው መፈተን እንደማይፈልጉ ማረጋገጣቸውን ገልጧል፡፡

የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እና የቅድስት ሥላሴ ሥራ አመራር ቦርድ ደብዳቤው በግልባጭ እንዲደርሳቸው የተደረጉ አካላት ሲኾኑ ውሳኔውን በጽኑ የተቃወመው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በዝርዝሩ ውስጥ አልተጠቀሰም፡፡

እንደ መንበረ ፓትርያሪኩ ምንጮች፣ ከቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ሰባት አባላት መካከል የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እንዲዘጋ የሥራ አመራር ቦርዱ አቅርቦታል በተባለው የውሳኔ ሐሳብ በተለይ የተስማሙትና የወሰኑት ከኮሌጁ ‹‹የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ›› ጋራ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው ፓትርያሪኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብቻ ናቸው፡፡ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊውን ብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ የወቅቱ የቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ አባላት – ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ – ኮሌጁን መዝጋት የፓትርያሪኩ ሥልጣን እንዳልኾነ በግልጽ ከማሳሰብ ጀምሮ የአጣሪ ኮሚቴው የመፍትሔ ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲደረጉ የተሟገቱ ናቸው፡፡

የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ እንደ ቀድሞው ዘመነ ፕትርክና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚጥሱ ውሳኔዎችን በጎማ ማኅተም በመሸኘት የጥፋት ተባባሪነታቸውን መቀጠላቸውን ያስረዱት ምንጮቹ፣ በዚህና ሌሎች የፓትርያሪኩ አቋሞች የእንደራሴነት ሚና እየተጫወቱ ናቸው ያሏቸውን በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስንም በትችት እየሸነቋጧቸው ነው፡፡ ከረዳት ሊቀ ጳጳስነት ባለፈ ፓትርያሪኩን ከብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ጋራ በወሳኝ ጉዳዮች ላይ በማማከር የእንደራሴነት ሚና ይጫወታሉ የሚባሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የደቀ መዛሙርቱ ችግር ዘልቆ የተሰማቸውና ለኮሌጁ የሚቆረቆሩ አገልጋዮችና ምእመናንን ተማኅፅኖ/ሽምግልና ለመቀበልም ጭምር ሲቸገሩ መታየታቸው ነው የተዘገበው፡፡

በቃለ ዐዋዲው መሠረት እያንዳንዱ አህጉረ ስብከት ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ፈሰስ ከሚደረገለት ፳% እና ከሌሎች ምንጮች ከሚያገኘው አጠቃላይ ገቢ 5% የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ድርሻ ነው፡፡ ይህን ድንጋጌ በመመርኮዝ ኮሌጁ የሕዝብ መኾኑን በትላንትናው የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል ላይ ለምእመኑ ሲያብራሩ የዋሉት የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ምእመኑ ገንዘብ ከመስጠት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ በመጠየቅ በቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ በባለቤትነት ስሜት ቀጥተኛ ተሳታፊ በመኾን ከጎናቸው እንዲቆም ሲጠይቁ ውለዋል፡፡

Dekemezamuret demonstarating on EOTC Patriarchateበዛሬው ዕለት ጠዋትም ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዘንባባ በመያዝ አመርተው ሙስናን በሚያጋልጡና የኮሌጁን አላግባብ መዘጋት በሚቃወሙ ኀይለ ቃሎች እንዲሁም በመዝሙርና በስብከት አቋማቸውን ሲገልጹ ውለዋል፡፡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የደቀ መዛሙርት ማፍርያ እንጂ የሙሰኞች መሸሸጊያ አይኾንም›› ያሉት ደቀ መዛሙርቱ እንዳሰቡት ምእመኑ በአካል ከጎናቸው ባይቆምም በተለያዩ መንገዶች ድጋፉን ገልጦላቸዋል፤ በገንዘብም ደረጃ እስከ ብር 30 ሺሕ ድጋፍ መሰብሰቡ ነው የተዘገበው፡፡

በዛሬው የተቃውሞ ውሎ ፓትርያሪኩ የደቀ መዛሙርቱን አምስት ተወካዮች እንደሚያነጋግሩ ቀትር ላይ ተገልጾ ተወካዮቹን በብዙ አስጠብቀዋቸው ሲያበቁ ‹‹አምባሳደር እያነጋገሩ ነው›› በሚል እንደወትሮው ያለውጤት ወደ ግቢያቸው ከተመለሱ በኋላ ነው ከልዩ ጽ/ቤቱ ወጥቶ በግቢያቸው ስለተለጠፈው ማስታወቂያ የተረዱት፡፡

‹‹ይህ ዐይነቱ ማስታወቂያ የእብደት እንጂ ከጤነኛ አእምሮ አይመነጭም፤ መሄድ እስከምንችለው ድረስ በተቃውሟችን እንቀጥላለን›› ያሉት ደቀ መዛሙርቱ፣ ቀጣይ ርምጃዎችን በተመለከቱ የትግል አማራጮች ላይ እየተወያዩ መኾኑ ታውቋል፡፡

Advertisements

7 thoughts on “ሰበር ዜና – ደቀ መዛሙርቱ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ

  • yeneneh July 16, 2013 at 11:13 am Reply

   it is a shame that the only one church’s spiritual college is closed down for irrelevant reasons. sad to hear it..

 1. Berhanu Melaku July 16, 2013 at 3:28 am Reply

  ይህ ኮሌጅ የምእመናን ነው፤ በምእመናን አስራት የታነጸና ምእመናኑ እምነቱ እንዲጠበቅና እንዲጎለብት ልጆቹን የሚያሰለጥንበት ነው። ስለሆነም ምእመኑ ገንዘብ ከመስጠት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ በመጠየቅ በቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ በባለቤትነት ስሜት ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ኮሌጁን መዝጋት ማለት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን ላይ ጦርነት ማወጅ ነው።
  ይህን ጉዳይ ብጹዕነታቸው አቡነ ማተታስ አጥብቀውና አርቀው ቢመለከቱት ምልካም ነው።
  አወ ‹‹ይህ ዐይነቱ ማስታወቂያ የእብደት እንጂ ከጤነኛ አእምሮ አይመነጭም፤ መሄድ እስከምንችለው ድረስ በተቃውሟችን እንቀጥላለን››። ኮሌጁን መዝጋት የፓትርያሪኩ ሥልጣን አይደለም። ከቀን ቀን ይህንን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን የሚሸረሽሩ ድርጊቶች በታላላቅ አባቶቻችን እየተፈጸሙ ናቸው።
  ዛሬ በውስጥም በውጭም አገር የሚገኙት ምእመናን እንባቸው እንደጎርፍ እየወረደ፥ ልባቸው እየነደደ ወደ እግዚአብሔር ስለ ታላላቅ አባቶችቻችው እየጸለዩ ነው፤ እግዚአብሔርም ቁጣው እየቀረበ ነው።
  ይህ ኮሌጅ በምንም ምክንያት መዘጋት የለበትም፤ ሕዝብን ያስቆጣል።

  እንበል እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ 1,000,000,000,000 ጊዜ፥ ብእነተ ማርያም መሃረነ ክርስቶስ ጊዜ 1,000,000,000,000 ።

 2. Anonymous July 16, 2013 at 3:31 am Reply

  እንበል እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ 1,000,000,000,000 ጊዜ፥ ብእነተ ማርያም መሃረነ ክርስቶስ 1,000,000,000,000 ጊዜ ።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።

 3. anoni July 16, 2013 at 7:37 am Reply

  ይህ ዐይነቱ ማስታወቂያ የእብደት እንጂ ከጤነኛ አእምሮ አይመነጭም፤

 4. Anonymous July 16, 2013 at 12:39 pm Reply

  ይድረስ ለ ————–
  በትናንትናው ዕለት በኮሌጃችን ቦርድ ላይ የተለጠፈውን ኮሌጁ ተዘግቷልና በሁለት ቀናት ውስጥ ኮሌጁን “በሰላማዊ መንገድ ለቃችሁ እንድትወጡ” የሚለውን የደብዳቤ ሃሳብ እያስላሰልኩ ነው፡፡ ወዲያው “ሐራ ዘተዋሕዶ” ን ዋቤ አድርጎ የዘገበ አንድ ጋዜጣ በአንድ ደቀ መዝሙር አማካኝነት በእጄ ገባ፡፡ እኔም የተማሪውን አቋምና የራሴን ሃሳብ አዋህጄ ወደዚህ የመረጃ ቋት የሆነ ነገር ለማለት ወሰንኩ፡፡
  በቦርዱ ላይ የተለጠፈ ደብዳቤ በጥቂት ሕሊናቸውን በሸጡ ሴረኞች ተሸርቦ በማን አለብኝነት በአየር ተረማምዶ በግድየለሽነት የተከናወነ ነው፡፡
  ይህ ደብዳቤ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት፤ ቅዱስ ሲኖዶስና ቋሚ ሲኖዶስ በግልባጭ እንኳን ሳያሳውቅ መፈጸሙ ሴራውን ግልጽ ያደርገዋል፡፡ በደብዳቤው ተከሳሽ የሆነው የቦርድ አባል አቡነ “ገሪባ” ዶክተር¡ በሚል የስድብና የዘለፋ ማኅተም ምስል አቁሞበታል፡፡ በደብዳቤውም ሙሰኞችን ሸልሞ ንጹሐንን ኮንኗል፡፡
  ይህም መላው ደቀመዛሙርት ዓመቱን ሙሉ የይስተካከሉልን ድምፁን እያሰማ እየተራበ፣ እየተጠማ፣ ጥንብ እንዳየ አሞራ ግቢውን በድንገት በሚወሩ አፋኞ እየተዋከበ የተጓዘበተን የታሪክ ምዕራፍ ከምንም ሳይቋጥር በፌደራል ግቢውን እንዲለቁ ማዘዙን ደቀ መዛሙርቱን አስተዳድሩ ከቦርድ አባላት ጋር በመሆን ምን ያህል በመረረ ጥላቻ እየተመለከታቸው እንደሆነ በግልፅ የሚያሳይ ማስረጃ ነው፡፡ ፓትሪያርኩና ቦርዱም የሙሰኛና የመናፍቅ ከለላ መሆናቸውን የገለጸበት ነው፡፡
  ሚዛናዊነት በጎደለው በተከሳሽ አካል ይህ ደብዳቤ ሲጻፍ “ቅዱስ” ፓትሪያርኩ ዝም ማለትዎ ከአቡነ ጢሞቴዎች ጋር ያለዎትን ግንኙነት ጥርጥር ውስጥ ይከተዋል፡፡ በዘንድሮው ዓመት በምሴተ ሐሙስና በበዓለ ትንሳኤ ቅዳሴ ሲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ፣ የካቴድራሉ የበላይ ጠባቂ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊቃነ ጳጳሳት ባሉበት የቅዳሴ የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ጸሎት ሲያሳርጉ ተኝተው ሰለነበር አልሰማዎትም እንጂ አቡነ ጤሞቴዎስ በማለት በተደጋጋሚ በመጀመሪያ መግለፅዎም በአደባባይ የገለፁት ወዳጅነትዎን ነው፡፡
  እኔ የምለው አባ “ገሪባ” ሥራ በቆመበት ኮሌጅ ውስጥ ነጻ ወረቀት/clearance/ ሳይሞላና ንብረት ሳያስረክብ ደብዳቤ ሳይወስድ ይወጣል እንዴ? ነው ወይስ እኔ የማውቀው ንጹሐን በረሃብ የሚቀጡበት እስር ቤት እንጂ ኮሌጅ እነደሆነ አይደለም ብለው ነው፡፡
  አሁንም የበተናችሁትን መሠብሰብ እንዳያቅታችሁ፣ ቁጭ ብላችሁ የሰቀላችሁት ቆሞ ማውረድ እንዳያቅታችሁ፣ ማጣፊያው አጥሮ ብርዱ እንዳይመታችሁ ዞር ብላችሁ ብታስቡ ጥሩ ነው፡፡ ለብዙኃን ጥያቄ መልስ መስጠትና አጣሪ ኮሚቴ ያስቀመጣቸውን የመፍትሔ ነጥቦችን ተግባራዊ እንዲሆን ብትጥሩ ጉዳዩ እንደ ኤርታሌ በተደጋጋሚ ነገሩ ባልፈነዳ ነበር፡፡
  ቀላሉንና ተስፋ ያላቸውን አማራጮች ወደ ኋላ ገሸሽ አድርጋችሁ ብትተውት ግን “ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ” ነውና የቤት ሥራውን ያበዛባችኋል፡፡ ላቅማችሁም የማይመጥን አደጋው ሌላ አደጋን የሚጠራ የሕዝቡንም ሥር ነቀል ወቅታዊ ምላሽ ሊያካትት ስለሚችል የትውልዱን ሃሳብ ቸል ባትሉ መልካም ነው እንላለን፡፡
  ለዚህም በኛ የተጀመረው በቀጣዩ ትውልድ ምላሽ እንደሚያገኝ ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ ከግቢ ማስወጣት ትችሉ ይሆናል በብራችሁና በእከክልኝ ልከክልህ የያዛችኋቸው ባለስልጣናት አሉና፡፡
  ይህ ብታደርጉም ልትገነዘቡት የሚገባው
  – ደቀ መዛሙርቱን ከኮሌጅ እንጂ ከቤተክርስቲያን ልታስወጡትና እምነቱን ልታስተውት እንዳይናገርም አፉን ልትዘጉት አትችሉም፡፡ በአዲስ መንፈስ በአንድነት ፈጅም ጉዞን ለመጓዝ አቅዷል፡፡
  – ስህተታችሁን እስክታርሙና ጀሮአችሁን እስከምትኮረኩሩ ግን የእኛም ሆነ የሕዝቡ ጩኸት አያርፍላችሁም፡፡
  አባቶቻችን የዘመነኞችን ወይም ዓለማውያን /secularist/ ዓላማ የተረዳችሁ አይመስለኝም አብዛኛው ዓለምና የኛ መንግሥት ወደዚህ ጎራ ለመቀላቀል ተፍተፍ የሚልበት ሰዓት ነው፡፡ እናም የሃይማኖት ለዘብተኛነትን በእጅጉ ይፈልገዋል፡፡ ወደ መሥሪያ ቤት ለጉዳይ የመጣ ሰው መስቀል በኪሱ ይዞ ሲገባ ተፈትሾ አስቀምጦት ቢገባ ደስ ይለዋል፣ ቆብ አድርጎ ከሆነ ያቆብ ወልቆ ተመርምሮ ቢገባ ደስ ይለዋል፡፡ ዕለተ ሰንበት በበዓልነት ባይፈረጅ ደስ ይለዋል፡፡ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ሃይማኖታቸው መመሪያ እንዲጓዙ ሳይሆን ለመንግሥት በሚመች ሁኔታ እንዲኖሩ ይፈልጋል፡፡ እርሱ ምን ያደርግ የዘመነኞች ዓለም/secular world/ ዓላማ ነው፡፡
  ተጻፈ ምንም እንኳን እርግማናችሁ የበለዓም ቢሆንም (ዘኁ 22)
  5 ዓመት ተረግሞ አንድ ቀን ይመረቅ ከነበረ አንድ ደቀ መዝሙር !!!

 5. my church July 16, 2013 at 5:52 pm Reply

  Dear Hara, I just want to thank you for this news. But, I have a very serious question. in the first place I don’t have that much problem a devout being asked to participate in their church affairs. However, don’t these guys know that our church is not like other Protestant churches to be lead by the laity? Our church is led by Holy Spirit that dwells in our holy fathers. Otherwise, our church will be torn apart thousand places just like menafikan. Let’s pray and ask God to help our holy fathers to decided the right thing. otherwise we are not Protestants to ask believers to interfere in the bigger issues of the leadership.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: