የቅድስት ሥላሴ መ/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በነገው ክብረ በዓል ችግራቸውን ለምእመኑ ያሰማሉ፤ የቋሚ ሲኖዶሱ አብዛኞቹ አባላት ያለምእመናን ንቅናቄ ችግሩ መፍትሔ እንደማያገኝ ያምናሉ

St Trinity Cathedral, Addis Abeba

 • ደቀ መዛሙርቱ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን የኮሌጁን የምግብ ቤት አገልግሎት ተከልክለዋልበጉዳዩ ላይ ሲመክር የቆየው የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር ፓትርያሪኩን ያነጋግራል
 • የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ደቀ መዛሙርቱ ወደ ክረምት ዕረፍት ከመሄዳቸው በፊት የማጠቃለያ ፈተና እንዲወስዱና ተመራቂዎቹ እንዲሸኙ ጥረት እያደረገ ነው፤ በፓትርያሪኩ የመወሰን አቅም ላይ ጥርጣሬ የገባቸው የሚኒስቴሩ ሓላፊዎች ልዩ ጽ/ቤ ደቀ መዛሙርቱን በኀይል ከኮሌጁ ለማስወጣት ያቀረበውን የድጋፍ ጥያቄ ውድቅ ባደረጉበት አቋማቸው ጸንተዋል
 • ፓትርያሪኩ በሚይዟቸው አቋሞች ረዳት ሊቀ ጳጳሱ አቡነ እስጢፋኖስ ከአቡነ ጢሞቴዎስ ጋራ የእንደራሴነት ሚና እየተጫወቱ መኾኑ እየተነገረ ነው
 • አቡነ ጢሞቴዎስ በኮሌጁ ያላቸው ሥልጣን በግልጽ እንደማይታወቅ ለአጣሪ ኮሚቴው የተናገሩት የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ኮሌጁ ‹‹ጠንካራና ውሳኔ የሚሰጡ የአስተዳደር ሰዎች›› እንደሚያስፈልጉት ጠቁመዋል
 • አጣሪ ኮሚቴው÷ የኮሌጁ አስተዳደር ራሱን ለማረም ዝግጁ እንዳልኾነ ተገንዝቧል፤ ኮሚቴው በየዘርፉ ለታዩ የአሠራር ክፍተቶች በሪፖርቱ ያቀረባቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ የማስተካከያ ርምጃዎች በአስቸኳይ ይፈጸሙ ዘንድ የሚመለከተው የበላይ አካል መመሪያ እንዲሰጥበት ጠይቋል
Advertisements

5 thoughts on “የቅድስት ሥላሴ መ/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በነገው ክብረ በዓል ችግራቸውን ለምእመኑ ያሰማሉ፤ የቋሚ ሲኖዶሱ አብዛኞቹ አባላት ያለምእመናን ንቅናቄ ችግሩ መፍትሔ እንደማያገኝ ያምናሉ

 1. kebere July 14, 2013 at 1:01 pm Reply

  አቡነ ማትያስ ከሥላሴ ዘንድ ፕትርክናህ ዛሬ ተቀደደ

  “ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ፓትርያርክ እንዳትሆን ናቀህ አለ። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በኢትዮጵያ ላይ ፓትርያርክ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም አለው። ነቢዩም። እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ፕትርክና ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት የኢትዮጵያ ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው።”1ኛ ሳሙ 15፡23 ፣ 26-29

 2. geezonline July 14, 2013 at 1:58 pm Reply

  “ያለምእመናን ንቅናቄ” አላችኍ? እንደ ምእመን ለመነቃነቅ’ኮ ካንድ ወይም ሌላ አፋኝ መኅበር አባልነት በፊት የቤተ ክሲያኗ አባል–ምእመን–እንደኾኑ በምር መገንዘብን ይጠይቃል! አይደለም’ንዴ? ለማበር ስም ሳይኾን ለማተቡ የሚቆም ትውልድ ሳንፈጥር ከቲፎዞ ጫጫታ ያለፈ ትርጕም ያለው የምእመናን ንቅናቄ መጠበቅ አንችልም። ተማሮቹን እሱ ባለቤቱ ይኹናቸው። ተዋሕዶንም። ኢትዮጵያንም።

 3. Anonymous July 15, 2013 at 4:01 am Reply

  ምንድነው ይሄ ሁሉ?!! ለምን አይተውትም፡፡ አሁን እነዚህናቸው ደቀመዘምር እየተባሉ የሚሞካሹት? እነዚህ እኮ ናቸው ወደፊት በተለያየ እርከን የቤተክርስቲያኗን የአስተዳደር ሰንሰለት እንቆጣጠር የሚሉት፡፡መቼም ማስተዋሉ ነጥፎብን አስተሳሰባችን ሁሉ የሚገርም ሆኗል፡፡ ሲጀምር የቱንም ያህል በደል ቢፈጸም ዓመጽ፣አድማ ምናምን መንፈሳዊያን ነን ከሚሉ ሰዎች መሰማት የለበትም፡፡ በቃ ስጋውያን ስለሆኑ በመንፈስ ማሸነፍ ስለማይችሉ አቅማቸው ሥጋዊ ጉልበትን መጠቀም ነው፡፡ የሚገርም ዘመን ውስጥ እኮ ነው ያለንው! አዎ ችግር እንኳን ቢደርስባቸው ወደልዑል አምላክ ቢያመለክቱ ችግራቸው እንደሚወገድ አያምኑም፡፡ የማያምኑ “ደቀመዘምራን”! ይሄንን እንኳን ሳይረዱ መንፈሳዊ የኮሌጅ ተማሪዎች ሆኑ! እንዲሁ እነደለመዱት ሲወጡም ጥልቅ የሆነውን መንፈሳዊ አገልግሎት በስጋ ፍላጎታቸው ሊነዱት! ለእናንት የእግዚአብሔር ነገር ተረት ተረት ስለሆነባችሁ አይገባችሁም፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ነው እኮ የሚለው! ቤተክርስቲያኗ እምነት ያለው እንጂ የቲዎሎጂ ዲግሪ ያላቸውን አትፈልግም፡፡ እምነት ካለ የተማረ ሞልቷል፡፡ ሌላም ሳይንስ ቢማር ሊመራት ይችላል! ምን ሁሉም ጋር ያው ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ሚዲያ ተብዬዎቹም መንፈሳዊ ነገር ምን ማለት ይቅርና በአለማዊው አንኳን ሥነ-ምግባር የሚባለውን አታውቁትም፡፡ ዜናዎቻችጉ ሁሉ ጦርነትን እንጂ የምስራች ነጋሪዎች አይደሉም፡፡ ኧረ እባካችሁ መልካም ነገርን ተናገሩ! እከሌ ታገደ! አከሌ አስቸግሯል! አከሌ ጎጠኝነትን እያስፋፋ ነው! ……….. በቃ በውንጀላና ክስ የተሞላ ወሬ፡፡ እስኪ አለማዊ የዜና ዘገባዎችን እንኳን ተመልከቱ፡፡ ዜናውን በገለልተኛነት ለሕዝብ ከማቅረብ ውጭ የክስና የውንጀላ ቃላቶች አይታዩባቸውም፡፡ ለራሳችሁ አይደብራችሁም?! ምን ጉድ ነው የመጣብን!የለሌው!የለሌው! የለሌውየለሌው!የለሌው!ስነምግባርም የለሌው!

 4. Mistilal July 16, 2013 at 12:39 am Reply

  የሚገርማችሁ ይህ የተከሳሹ የዘላለም ረድኤት ሃሳብ ነው፡፡ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ፡፡

  አንተ መናፍቅ በክ የእመቤታችንን ሥዕል እንደረገጥክ ገና ትረገጣለህ ደቀ መዛሙርቱን ማንም እንዲህ አይላቸውም ዘላለም ረድኤት የአንተ ሃሳብ እንደሆነ ይታወቃል ሰይጣን ሊወጣ ሲል ይፈራገጣል፡፡ ኮሌጁን ለአንዴና ለመረሻ ለቅቀህ ትሄዳለህ እስካሁን የተጫወትክበት ይበቃሃል አሁን ግን ጊዜው አልቋል ሁሉም ነቅቶብሃል፡፡ እስካሁን ማንም ያላወቀ እንዳይመስልህ ከአባ ጢሞቴዎስ ጋር በኮሌጁ ስም በቤተ ክርስቲያኗ ስም ከመናፍቃን የተቀበላችሁትን በሚልዮን የሚቆጠር ብር ገና ትተፉታላችሁ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ተነስቷል የትም አትደርስም ዝም ቢል የሌለ መሰለህ እንዴ፡፡ ደቀ መዛሙርት ሆይ አይዟችሁ “አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም።ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው። 2ኛ ቆሮ 6፡2-1ዐ

 5. በቀለ July 16, 2013 at 9:35 am Reply

  እነዚህ ደቀ መዛሙርት ተብዬዎች፣ በአቢይ ጾም ወቅት እንጀራው ተበላሸብን ብለው ለአመጽ የተነሳሱ ሆዳም፣ የዝንጀሮ መንጋ…..ማፈሪያዎች፤ የነገዪቱ ቤተክርስቲያን እነዚህን በመሳሰሉ ደቀ መዛሙርት ስትመራ ማየት በጣም ያሳዝናል፡፡
  እነዚህ ተማሪዎች ተበድለው ከሆነ ጥያቄዎቻቸውን እንደ ክርስቲያን በአግባቡ ማቅረብ አለባቸው፤ ለጥያቄያቸው ምላሽ ካጡ ከተማሪዎቹ የሚጠበቀው በደልን ሁሉ በትእግስትና በጽናት ለማሳለፍ ጥረት ማድረግ ነው እንጂ ……አመጽ፣ ያውም በመንፈሳዊ አባቶቻቸው ላይ ለአመጽና ስም ማጥፋት ዘመቻ መነሳሳት ተገቢ አይደለም……ነውር ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: