የቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ለፈተና ባለመቀመጥ የማስገደጃ ርምጃቸውን አጠናክረዋል

  • የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት እስኪፈጸም ድረስ ለፈተና ላለመቀመጥ ወስነዋል
  • የኮሌጁ ቦር በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ እየተወያየ ነው
  • ‹‹ቦርዱ ለአቡነ ጢሞቴዎስ ተጽዕኖ ያደረና እርሳቸው የሚሉትን ብቻ የሚሰማ ነው፤ በችግራችን ጠይቆንም ይኹን ሰብስቦን አያውቅም፡፡›› /ደቀ መዛሙርቱ/

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመደበኛው መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት ከዛሬ ሐምሌ ፩ – ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም እንደሚሰጥ በተገለጸው የኮሌጁ የፈተና አሰጣጥ ላይ ላለመቀመጥ በመስማማት በኮሌጁ አስተዳደር ላይ የጀመሩትን የማስገደድ ርምጃ አጠናክረው መዋላቸው ተዘገበ፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ባለፈው ሰኔ ፳ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም እንዳደረጉት በዛሬውም ዕለት የአስተዳደር ሕንጻውን መግቢያ በሮችና መተላለፊያዎች ከበውና ዘግተው ሠራተኞችና መምህራን ወደ ቢሮው እንዳይገቡ በማገድና በመከልከል የዋሉ ሲኾን ይኸው የማስገዳጃ ርምጃቸው በአጣሪ ኮሚቴው የቀረቡት የመፍትሔ ርምጃዎች በተግባር እስኪውሉ ድረስ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ከቀትር በኋላ በአጣሪው ኮሚቴ ሪፖርት ላይ ከኮሌጁ ቦርድ ጋራ መወያየቱ ተሰምቷል፡፡ የኮሌጁ ሊቀ ጳጳስ በፓትርያሪኩ ጭምር የማይጠየቁና የማይነኩ ተደርገው መወሰዳቸው በአጣሪ ኮሚቴው የቀረቡትን የመፍትሔ ሐሳቦች ተፈጻሚነት በማዘግየት በተስፋ ብቻ እንዲጠብቁ እንዳደረጋቸው የሚናገሩት ደቀ መዛሙርቱ፣ አቡነ ጢሞቴዎስ የሚሉትን ብቻ በመስማትና በመወሰን ስለ ችግራቸው ጠይቋቸውም ይኹን አወያይቷቸው የማያውቀው ቦርድ የችግሩ አካል ኾኖ ሳለ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋራ ለምክክር መቀመጡ እንዳስገረማቸው ገልጸዋል፤ ተቃውሟቸውም በ‹‹ፍራሽና እንጀራ›› ጥያቄ ተንኳስሶ በመታየት ብቻ እንዳይወሰንም አሳስበዋል፡፡

ወቅቱ የምረቃና ምደባ መኾኑን የጠቆሙት የደቀ መዛሙርቱ ተወካዮች፣ ጥያቄዎቻቸውንና አጣሪ ኮሚቴው ለውሳኔ ያቀረባቸውን መፍትሔዎች ግለሰባዊ ከማድረግ ጀምሮ ‹‹ቋሚ ሲኖዶስ በኮሌጁ ጉዳይ አይመለከተውም›› እስከማለት በደረሱት በኮሌጁ ሊቀ ጳጳስ አድልዎ ሊፈጸምብን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውም አልሸሸጉም፡፡

በዛሬው የተቃውሞ ውሎ÷ ደቀ መዛሙርቱን ለጠብ ለመገፋፋትና ሰላማዊ ርምጃዎቻቸውን ለማወክ፣ ኢትዮጵያ ጸጥታ የተባለችውና ከዘላለም ረድኤት ጋራ የቅርብ ግንኙነት ያላት የኮሌጁ ሊቀ ጳጳስ ጸሐፊ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ደደብ›› በሚል ኀይለ ቃል በመዝለፍ የቃጣችው ትንኮሳና የፖሊስ ኀይል ወደ ቅጽሩ በማስገባት ያደረገችው የማስፈራራት ሙከራ በደቀ መዛሙርቱ ትዕግሥት እንዳልተሳካላት ተገልጧል፡፡

ዘላለም ረድኤት÷ በቴዎሎጂ ሁለተኛ ዲግሪ አግኝቼበታለኹ የሚለውን የትምህርት ማስረጃ ለአጣሪ ኮሚቴው ለማቅረብ ፈቃደኛ ባለመኾን፣ የኮሌጁን ሊቀ ጳጳስ በክፉ ምክር እያሳተና በጥቅመኝነት እያባበለ በትምህርት አስተዳደሩና በተማሪው መብቶች ላይ በሚፈጽማቸው በደሎች እንዲሁም በእምነቱ በተጋለጠበት የመናፍቅነት ተግባር ከማስተማርና ሌሎች ሓላፊነቱ ተወግዶ በሚመለከተው አካል እንዲጠየቅ ሐሳብ የቀረበበት መስሐቲ እንደኾነ ቢገለጽም የኮሌጁ ዋና ዲን ወይም ምክትል አካዳሚክ ዲን አድርጎ ለመሾም በሊቀ ጳጳሱ መታቀዱ የደቀ መዛሙርቱን ተቃውሞ እንዳባባሰው፤ ኢትዮጵያ ጸጥታ የተባለችው የሊቀ ጳጳሱ ጸሐፊ ደግሞ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የደመወዝ አከፋፈል ስኬል የማይታወቅ ከፍተኛ ክፍያ ከሚፈጽምላቸው ሦስት የድጋፍ ሠራተኞች አንዷ መኾኗ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ለፈተና ባለመቀመጥ የማስገደጃ ርምጃቸውን አጠናክረዋል

  1. Anonymous July 11, 2013 at 4:27 pm Reply

    የምድረ መናፍቅ ና የምድረ ፖለቲኮኞች ስብስብ የሞላ ግቢ ስለሆነ ካሁን በውኋላ አዳዲስ ተማሪዎች ማንነታቸውን እየተጠኑ ቢገቡ መልካም ነው እላለሁ። ቤተ ክህነትም ጥሩ አስተዳደር ሊኖው ይገባል በህገ ልቦና መሄድ ይብቃው

  2. Anonymous July 14, 2013 at 4:20 pm Reply

    ምንድነው ይሄ ሁሉ?!! ለምን አይተውትም፡፡ አሁን እነዚህናቸው ደቀመዘምር እየተባሉ የሚሞካሹት? እነዚህ እኮ ናቸው ወደፊት በተለያየ እርከን የቤተክርስቲያኗን የአስተዳደር ሰንሰለት እንቆጣጠር የሚሉት፡፡መቼም ማስተዋሉ ነጥፎብን አስተሳሰባችን ሁሉ የሚገርም ሆኗል፡፡ ሲጀምር የቱንም ያህል በደል ቢፈጸም ዓመጽ፣አድማ ምናምን መንፈሳዊያን ነን ከሚሉ ሰዎች መሰማት የለበትም፡፡ በቃ ስጋውያን ስለሆኑ በመንፈስ ማሸነፍ ስለማይችሉ አቅማቸው ሥጋዊ ጉልበትን መጠቀም ነው፡፡ የሚገርም ዘመን ውስጥ እኮ ነው ያለንው! አዎ ችግር እንኳን ቢደርስባቸው ወደልዑል አምላክ ቢያመለክቱ ችግራቸው እንደሚወገድ አያምኑም፡፡ የማያምኑ “ደቀመዘምራን”! ይሄንን እንኳን ሳይረዱ መንፈሳዊ የኮሌጅ ተማሪዎች ሆኑ! እንዲሁ እነደለመዱት ሲወጡም ጥልቅ የሆነውን መንፈሳዊ አገልግሎት በስጋ ፍላጎታቸው ሊነዱት! ለእናንት የእግዚአብሔር ነገር ተረት ተረት ስለሆነባችሁ አይገባችሁም፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው ነው እኮ የሚለው! ቤተክርስቲያኗ እምነት ያለው እንጂ የቲዎሎጂ ዲግሪ ያላቸውን አትፈልግም፡፡ እምነት ካለ የተማረ ሞልቷል፡፡ ሌላም ሳይንስ ቢማር ሊመራት ይችላል! ምን ሁሉም ጋር ያው ነው፡፡ የቤተክርስቲያን ሚዲያ ተብዬዎቹም መንፈሳዊ ነገር ምን ማለት ይቅርና በአለማዊው አንኳን ሥነ-ምግባር የሚባለውን አታውቁትም፡፡ ዜናዎቻችጉ ሁሉ ጦርነትን እንጂ የምስራች ነጋሪዎች አይደሉም፡፡ ኧረ እባካችሁ መልካም ነገርን ተናገሩ! እከሌ ታገደ! አከሌ አስቸግሯል! አከሌ ጎጠኝነትን እያስፋፋ ነው! ……….. በቃ በውንጀላና ክስ የተሞላ ወሬ፡፡ እስኪ አለማዊ የዜና ዘገባዎችን እንኳን ተመልከቱ፡፡ ዜናውን በገለልተኛነት ለሕዝብ ከማቅረብ ውጭ የክስና የውንጀላ ቃላቶች አይታዩባቸውም፡፡ ለራሳችሁ አይደብራችሁም?! ምን ጉድ ነው የመጣብን!የለሌውየለሌው!የለሌው!ስነምግባርም የለሌው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: