የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተጠናክሯል

 • ·         በአጣሪ ኮሚቴው የቀረቡት የመፍትሔ ሐሳቦች እንዲተገበሩ ጠይቀዋል
 • ·         የአቡነ ጢሞቴዎስን የሹመት ሐሳብ በማውገዝ ርምጃ ለመውሰድ ዝተዋ

 • ·         ነገ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ ይወያያሉ

Theology College Buildingየቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የተቃውሞ እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው ውለዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ረፋድ ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በከፍተኛ ቁጥር በማምራት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስን ለማነጋገር ያደረጉት ሙከራ ወደ ግቢው እንዳይገቡ በጥበቃ በመከልከላቸው ምክንያት አለመሳካቱ ተነግሯል፡፡

የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ታምሩ አበራ ከጥቂት የደቀ መዛሙርቱ ተወካዮች ጋራ የተገናኙ ሲኾን፣ ደቀ መዛሙርቱ÷ ከአምስት ወራት በፊት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች በአጣሪ ኮሚቴ ከታዩ በኋላ የተሰጡት የመፍትሔ ሐሳቦች በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረጉ፣ ከኮሌጁ እንዲባረር በአጣሪ ኮሚቴው የተጠቆመበትን የቀን መርሐ ግብር ሓላፊ ዘላለም ረድኤትን የኮሌጁ ሊቀ ጳጳስ በዋና ዲንነት ለማሾም ማሰባቸውን በመስማታቸው ይህን ከማስፈጸም እንዲታቀቡ ለልዩ ጽ/ቤት ሓላፊው ማሳሰባቸው ተዘግቧል፡፡

በልዩ ጸሐፊያቸው አማካይነት መልእክት ያስተላለፉት ፓትርያሪኩ፣ በነገው ዕለት ሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ኮሌጁ እንደሚልኩና በጉዳዩ ላይ ከእነርሱ ጋራ እንዲወያዩ እንደሚያደርጉ ለደቀ መዛሙርቱ ነግረዋቸዋል ተብሏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ትላንት ሌሊት በኮሌጁ አዳራሽ ተሰብስበው ለጥያቄያቸው በአጭር ጊዜ ምላሽ እንደሚያገኙ በተሰጣቸው ተስፋና ውሎ አድሮ በታየው ኹኔታ ላይ በስፋት መወያየታቸው የተዘገበ ሲኾን ቀጣይ አካሄዳቸው የኮሌጁን መግቢያና መውጫ ከመቆጣጠር ጀምሮ በሓላፊዎች ላይ የሚወሰድን አስገዳጅ ርምጃ ሊያካትት እንደሚችል ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተመልክቷል፡፡

አጣሪ ኮሚቴው ሲያካሂድ በቆየው ማጣራት÷ ለኮሌጁ ሙሉ ሥልጣን ያለው ዋና ዲን እንዲሾምና ምክትል ዋና ዲን የሚለው ስማዊ ሥልጣን እንዲቀር፣ አካዳሚክ ምክትል ዲኑ ከሓላፊነታቸው ተነሥተው በማስተማር እንዲወሰኑና በምትካቸው አግባብነት ያለው ሰው እንዲተካ፣ የቀን መርሐ ግብር ሓላፊው ዘላለም ረድኤት ከኮሌጁ እንዲወገዱና ከነገረ ክርስቶስ እና ክብረ ቅዱሳን ጋራ በተያያዘ በቀረበባቸው የሃይማኖት ሕጸጽ እንዲጠየቁ በደረሰበት የመፍትሔ ሐሳብ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ጋራ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ እንዲፈጸም መወሰኑ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

Advertisements

6 thoughts on “የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተጠናክሯል

 1. Anonymous June 27, 2013 at 6:40 am Reply

  ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት:-

  የቅድሰት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የግል ባለ ሃብት ነው ወይስ የቤተ ክርስቲያን?
  ቅዱስ ፓትርያሪኩስ ለምን ነው ደቀ መዛሙርቱን ለማነጋገር ያልቻሉት? አቡነ ጢሞቴዎስን በመፍራት ወይስ…….?
  ደቀ መዛሙርቱስ እንደዚህ ብለው ተምረው የቤተ ክርስቲንን ተልእኮ ያስፈፅማሉን?….
  ’’እባካችሁ አስቡበት’’!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

 2. Anonymous June 27, 2013 at 7:05 am Reply

  እንጠይቃችሁ!
  ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱሰ ሲኖዶስ አባላት

  ብዙ የራሱ አጀንዳ ያለው ዓለም የተነጋገረበትን ጉዳይ መፍትሔ እንኳን ባታመጡ የራሳችሁን ጉዳይ ባጀንዳ እንኳን መያዝ እንዴት ከበዳችሁ?
  ደህናውን ሰው ከቦታ ቦታ ስታቀያይሩ ይቀየሩ የተባሉትን ሁለት መምህራን እንዴት መቀየሩን አላሰባችሁም?

  ለብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ

  የተራበን አብላ የሚለውን የወንጌል ቃል አላነበበቡም ይሆን ፤ ነቢዩ ኤልሳዕን ጠላቶችህን እንዴት አበላህ ብለው እስኪ ይጠይቁት? እረ ጠላትን ማብላት ይቅር እቴ ልጆቼ ብለው ባደራ የተቀበሏቸውን ማስራብ ማን አስተማሮት?
  ትውልዱ ውስጥ ምን እንዲቀረጽ አስበው ይሆን? ተማሪው የእርሶን የአምባገነንነት ፈለግ ቢከተል ኖሮ እኮ በገዛ በጀቱ እየተራበ ዝም ይሎት ነበርን? የተማረው ትምህርት አግዶት እንጂ!
  በዓለም መገናኛ ብዙሃን አግባብ ያለው ማስተር እንኳን የሌላቸውን ‘አቻ የሌላቸው’ ማለት የኢትዮጵያን ሊቃውንትን መስደብ አይሆንቦትም?

  ለመንግስት አካላት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

  የሚያጣራ ኮሚቴ እናዋቅራለን እንጂ እንዲሁ አንወስንም ብላችሁ ሕግን እንደሚያከብር ተማሪው በማይፈልጋቸው መምህራን እንዲማር ለምን አስገደደዳችሁ ኮሌጁ የቋቋመው ለምሁራን ማፍርያ ወይስ ለዘመድ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ? ሁሉም ይሁን ብለን ብንቀበለው እንኳን ኮሚቴው አጣርቶ ያቀረበላችሁን ውጤት ለመግለጽ ለምን ከበዳችሁ?
  ለሁለት ሰዎች ተብሎ በ 180 አገር ተረካቢዎች ላይ ይህ ሁሉ ችግር ሲከሰት የብዙሃን መብት የሚለው እዚህ አይሰራም እንዴ? እንኳን ጥፋታቸው የታወቀ፤ ተጠርጣሪዎች እንኳን እስኪጣራ በሕግ ቁጥጥር ሥር ይውሉ የል እንዴ?
  ሰላማዊ ጥያቄ የጠየቀን ሰው ነፍስ ያጠፋ እንኳን በማይቀጣበት ምግብ መከልከል እንደጥፋት ስለማይታይ ይሆን እንዴ በእጀ ረጅሞች ጥቅም ተደልላችሁ ደቀ መዛሙርቱን የምታስፈራሪ?

  የሁሉም መልስ የታወቀ ነው በጎ ሕሊና አለመኖር እና በጥቅም መያዝ የሚል ነው ፡፡ ለማንኛውም ልቡና ይስጣችሁ!

 3. Somson June 27, 2013 at 7:37 am Reply

  ይህ ሁሉ ግፍ የሚደረገው ደቀ መዛሙርቱ ያሳዩት ትእግስት ነው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከመንግሥትም ሆነ ከአባቶች መፍትሔ የሚሰጣቸው ሰው አላገኙም፡፡ ግፍና መከራቸው በዛ ወደ አሰቡት የኃይል እርምጃ ቢገቡ ማነው ተጠያቂው እስካሁን ያሳዩትን ክርስቲያናዊ ትእግስት እናደንቃለን ዝንቱ ጋኔነ ዘመድ ኢይወጽእ እንበለ ……. እንዳለ ጌታችን ከማሁ ግበሩ

 4. Anonymous June 27, 2013 at 2:55 pm Reply

  lemneden new enante marageb yefelgachut

 5. Anonymous June 27, 2013 at 3:21 pm Reply

  zeregna temari hula

 6. nitsuh miskire July 1, 2013 at 3:34 am Reply

  ይህ ሁሉ ሲደረግ ራሳቸውን ለቤተክርስቲያን አሳልፈው በሰጡ፣ ለእምነታቸው በሞቱ ቅዱሳን ስም ራሳቸውን የጠሩ ‘ማኅበረ ቅዱሳን’ የተባሉት ወዴት ናቸው? ቤተክርስቲያን ካሏት ሁለት/ሦስት መንፈሳዊ ኮሌጆች ውስጥ ትልቁ የሰባኪያን ማፍሪያ በደንታቢሶች በፖለቲካ ሹመኞች ሲዘጋ ማኅበረ ቅዱሳን ወዴት አለ? ይህ ማኅበር የሚጮኸው ራሱ ሲነካ ጥቅሙ ሲጎድል ብቻ ነው እንዴ? ቤተክርስቲያን ስትጠቃ፣ ገዳማቶቿ ሲደፈሩ ሲታረሱ ማኅበረ ቅዱሳን ወዴት አለ? ወይ እንደስክንድር ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ! የኛ ቅዱሳን ወራሪን፣ ኃይማኖት ለዋጮችንና አላውያንን እምቢ ያሉ ናቸው እንጂ እንደማኅበረ ቅዱሳን አድርባዮች አይደሉምና በቅዱሳን ስም መነገዳችሁን አቁሙና በግልጽ ለቆማችሁለት የዘረኛ ‘መንግስት’ ድጋፍ ስጡ። ከሰውም ከእግዚአብሔርም ፍርድ ግን አታመልጡም! አድርባዮች!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: