የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ዛሬ ይጠናቀቃል፤ መግለጫም ይሰጣል

 • ብፁዕ አቡነ ዳንኤል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመድበዋል፡፡ በኬንያ፣ ሱዳን፣ ዝምባቡዌ – ሐራሬ፣ በደቡብ አፍሪቃ፣ በአሜሪካ ቴክሳስ እና በሚኔሶታ አብያተ ክርስቲያናትን በማቋቋም የማገልገል ዓለም አቀፍ ልምድ እንዳላቸው የተመለከተው ብፁዕነታቸው÷ የግብጽ ቆብጥ ቤተ ክርስቲያን ሳይገባት ባነሣችው የይገባኛል ጥያቄና በ‹‹ስታተስኮ›› ሕግ ሳቢያ ጥገናው ተከልክሎ በመፈራረስ ላይ የሚገኘውን የታሪክና ቅድስና ይዞታችንን ጉዳይ የበለጠ በማራመድ፣ የሀ/ስብከቱን ተጨማሪ ይዞታዎች በማጠናከር፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚጥሱ የምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አፈጻጸሞችን መልክ በማስያዝ፣ በጉዞ ወኪልነትና ተሳላሚነት ስም ሕገ ወጥ ስምሪት በሚያደርጉ አካላት ላይ የእርምት ርምጃ በመውሰድ የተሻለ አገልግሎት መፈጸም ይጠበቅባቸዋል፡ ብፁዕነታቸው ይህን አዲስ ምደባ ከማግኘታቸው አስቀድሞ የቀድሞው የሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

  His Grace Abune Daniel Archbishop of Jerusalem

  ብፁዕ አቡነ ዳንኤል
  በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ

 • ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከማእከላዊ ዞን አክሱም ሀ/ስብከት ተነሥተው የታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳማት የበላይ ጠባቂ ተደርገዋል፤ ‹‹ከፓትርያሪኩ ሌላ ሊቀ ጳጳስ አንፈልግም፤ የምንተዳደረው በንቡረ እድ ነው፤›› የሚሉ ተቃዋሚዎች ለብፁዕነታቸው መነሣት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል፡
 • ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ከዓዲ ግራት እና ሽሬ አህጉረ ስብከት ጋራ ማእከላዊ ዞን አክሱም ሀ/ስብከትን ደርበው ይመራሉ፡፡
 • ወደ አንድነቱ የተመለሰው የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አስተዳደር በዐሥር ያህል የወረዳ ቤ/ክህነት መዋቅሮች ይጠናከራል፤ በአዲሱ አወቃቀር በመልካም አስተዳደር፣ በፋይናንስ አያያዝና በሰው ኀይል አመዳደብ ረገድ ሕግ ተከብሮ እንዲሠራ በቋሚ ሲኖዶስና በፓትርያሪኩ ጥብቅ ክትትል ይደረግበታል፤ የመዋቅር ለውጡ 130 ያህል ለሚኾኑ የሀ/ስብከቱ ሠራተኞች ስጋት አሳድሯል፡
 • በሰሜን አሜሪካ የቀድሞው የካሊፎርንያና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በዐሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ በአካል ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉና ስለተሰነዘረባቸው ክሥ እንዲጠየቁ መወሰኑ ተገልጧል፡፡

 

የቅ/ሲኖዶሱን መግለጫ ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ዛሬ ይጠናቀቃል፤ መግለጫም ይሰጣል

 1. maty June 10, 2013 at 10:14 am Reply

  pls tall me ur email addres txs

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: