ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተመርጠዋል፤ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ኾነው ተሠይመዋል

  • ለዋ/ሥ/አስኪያጅነት በዕጩነት የቀረቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አንዳችም የድጋፍ ድምፅ አላገኙም 
  • ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ራሳቸውን ከዋ/ሥ/አስኪያጅ ዕጩነት አግልለው ነበር

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ግንቦት ፳፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም አምስተኛ ቀን ጥዋት የስብሰባ ውሎው የሰቲት ሁመራ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስን የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ኾነው እንዲሠሩ ሠይሟል፤ የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስን ደግሞ የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መርጧል፡፡

His Grace Abune Lukas

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ
የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፳፭ ንኡስ አንቀጽ ፩ እና ፬ መሠረት÷ ቅ/ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤውና በቋሚ ሲኖዶስ በየጊዜው በሚያደርገው ስብሰባ ላይ ሁሉ የሚነጋገርባቸውን ርእሰ ጉዳዮች የማዘጋጀት፣ ውሳኔዎቹን ሁሉ በተግባር ላይ መዋላቸውን የመከታተል ሥልጣንና ተግባር የብፁዕ ዋና ጸሐፊው ነው፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፴ ንኡስ አንቀጽ ፱ መሠረት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ÷ ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔዎየማስፈጸም ሥልጣነ ክህነት፣ በቂ የትምህርት ደረጃና ችሎታ ያላቸውን ሦስት ሰዎች ለም/ሥራ አስኪያጅነት በዕጩነት ለቋሚ ሲኖዶስ አስቀርበው ቅ/ሲኖዶስ ሲስማማበት የማስመረጥና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ የማሾም ሥልጣን አላቸው፡፡ በዚሁ አንቀጽ ንኡስ ቁጥር ፲ መሠረት የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎችን እያጠኑና እያስመረጡ ፓትርያሪኩን በማስፈቀድ ይሾማሉ፡፡

His Grace Abune Mathewos

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ
የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ

ከብፁዕ አቡነ ሉቃስ ጋራ ለቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት በዕጩነት የቀረቡት ብፁዓን አባቶች÷ አቡነ ኄኖክ እና አቡነ ዲዮስቆሮስ ናቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከፍተኛ ድምፅ አግኝተው በመመረጣቸው ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ቅ/ሲኖዶሱን በዋና ጸሐፊነት እንዲያገለግሉ መሠየማቸው ታውቋል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ከፍተኛ የአስፈጻሚ አካል በዋና ሥራ አስኪያጅነት ለመምራት ከብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጋራ በዕጩነት የተወዳደሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው፡፡ በምርጫ ውድድሩ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት ማገልገላቸውን በመጥቀስ ራሳቸውን ማግለላቸው ቢያሳውቁም በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ በምርጫው እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡

በዚህ መሠረት ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ጽ/ቤቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመራውን አባት ለመለየት በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የቀድሞውን ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በሁለት ድምፅ በመብለጥ መመረጣቸው ተዘግቧል፡፡

ሌላኛው ዕጩ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ግን አንዳችም የምልአተ ጉባኤውን ተሳታፊዎች ድምፅ አለማግኘታቸው ብዙዎችን አስደምሟል፡፡ በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እስከ አሁን ድረስ መንበራቸውን በሊቀ ጳጳስነት ለመደባቸው ቅ/ሲኖዶስ በማይታዘዘው ‹‹ገለልተኛ›› ቤተ ክርስቲያን አድርገው መቀመጣቸውና የለየለት ፕሮቴስታንት የኾነውን ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንን በአህጉረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅነት መሾማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ እንደቀሰቀሰባቸው ይታወቃል፡፡

በሙሰኛና ጎጠኛ ቡድኖች ሤራ የምክነት ስጋት ያንዣበበት የተቋማዊ ለውጥ ዕቅዱ በሁለቱ ብፁዓን አባቶች አመራር የመስጠት ክሂልና የማስፈጸም ትጋት ከፍጻሜ ደርሶ የቤተ ክህነታችንን ትንሣኤ እንደሚያሳየን እናምናለን፡፡

ሁለቱ ብፁዓን አባቶች ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት መጽናትና መስፋፋት፣ ለቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት መጠበቅና መልማት፣ ለተቋማዊ ነጻነቷ መከበርለአንድነቷ መረጋገጥ እስከሠሩ ድረስ ሐራ ዘተዋሕዶ ከጎናቸው እንደምትቆም ትገልጻለች፡፡ለሁለቱ ብፁዓን አባቶቻችን መልካም የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን!!

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ  

Advertisements

2 thoughts on “ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተመርጠዋል፤ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ኾነው ተሠይመዋል

  1. elohe elohe lamasebektani June 4, 2013 at 12:31 pm Reply

    Engdih bete krstian yemiberalat ymeslal

  2. korabanchi April 4, 2016 at 4:55 pm Reply

    በድንብ ብሉ ስለተባሉ ይብሉ፤ ሃይ ባይ የሌለው ገብስ ውፍ ይጨርስዋል!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: