የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ተካሄደ

 • መደበኛ ስብሰባው ነገ ከቀትር በኋላ እንደሚጀመር ይጠበቃል

Opening Prayer of the Synod Annual Meeting'05በዓለ ትንሣኤ በዋለ በኻያ አምስተኛው ቀን /በርክበ ካህናት/ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ጸሎት ተካሂዷል፡፡

ዛሬ፣ ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተከናወነው የዋዜማ መክፈቻ ጸሎት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ከኻያ አምስት ያላነሱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መገኘታቸው ተዘግቧል፡፡

‹‹በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የኾንህ አምላካችን መድኃኒታችን ሆይ÷ ስማን›› (መዝ.፷፬÷፮) የሚለውን የዕለቱን ምስባክ፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለሰጠችው ምስክርነት ከተነበበው ቃለ ወንጌል (ሉቃ.፩÷፴፱) ጋራ በማሰናኘት ያብራሩት የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ናቸው፡፡

ብፁዕነታቸው ከነገው የእመቤታችን ክብረ በዓል ጋራ በማያያዝ በአጭሩ ባቀረቡት ትምህርታቸው÷ በጽንፈ ምድር ላሉት ሁሉ ተስፋቸው፣ አለኝታቸው የኾነ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም÷ የተሰደደው ዓለም የተመለሰባት፣ የታሰረው ዓለም የተፈታባት፣ የረከሰው ዓለም የተቀደሰባት መኾኑን በአጽንዖት ገልጸዋል፡፡

ከአርባ ያላነሱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በርክበ ካህናት የሚያካሂደውን ሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ነገ፣ ግንቦት 21 ቀን ከቀትር በኋላ ጉባኤውን በርእሰ መንበርነት የሚመሩትን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩን የመክፈቻ ንግግር እንዲሁም የብፁዕ ዋና ጸሐፊውን ሪፖርት በመስማት እንደሚቀጥልና የመነጋገርያ አጀንዳ አርቃቂዎችን እንደሚሠይም ተመልክቷል፡፡

ከስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ፣ በወቅታዊና አንገብጋቢ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ በመምክር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተመልክቷል፡፡

ጉባኤው አጽንዖት እንደሚሰጥባቸው ከሚጠበቁት አንገብጋቢና ወቅታዊ ጉዳዮች መካከል፡-

 • የሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ቃለ ዐዋዲ ድንጋጌ ማሻሻ  ሂደ
 • የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር የመዋቅርና አሠራ ለውጥ ጥናት፣
 • የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የሦስትና አምስት ዓመት ስትራተጅክ ዕቅድ ዝግጅት ሂደት፣
 • በየአህጉረ ስብከቱ በተለይ በአ/አ አህጉረ ስብከት ከሙስናና ብልሹ አሠራር ጋራ የተያያዙ አስተዳደራዊ ችግሮችና ውዝግቦች፣
 • የፌዴራል ጉዳዮች ሚ/ር የሃይማኖት ተቋማትን ምዝገባ አስመልክቶ ስላወጣው መመሪያ ረቂቅ፣
 • የቀጣይ ሦስት ዓመታት የቅ/ሲኖዶስ ዋ/ጸሐፊ እና የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ዋ/ሥራ አስኪያጅ ምርጫና ሥያሜ
 • የፓትርያሪኩን ሀ/ስብከት – ኢየሩሳሌምን ጨምሮ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባና ዝውውር ጥያቄዎች፣
 • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደርና ደቀ መዛሙርት ውዝግብ በተመለከተ ከጠ/ቤ/ክህነትና ከመንግሥት የተውጣጣው አጥኚ ኮሚቴ ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ

የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

Advertisements

3 thoughts on “የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ተካሄደ

 1. O.T.Christian May 30, 2013 at 2:43 am Reply

  በዩ .ኤስ .ኤ . ውስጥ የሚገኙት የኢት/ ኦ/ ተ/ ቤ/ ክ/ የቅ ሴኖዶስን ፍርድ እየተጠባበቁ ናቸው። በአቡነ አብረኃም ስር የነብሩት ቤ/ ክርስቲያናት መንበራቸው እስካሁን ድረስ ክፍት ነው። የተላኩት ሊቀጳጳስ (አቡነ ፋኑኤል) እስካሁን አልተረከቡትም። ከገለልተኛ ቤ/ክ/ ውስጥ እንደገቡ ቀርተዋል። ኧረ ለመሆኑ አንድ አገረ ስብከት የሚያፈርስ ቅዱስ ሴኖዶስ ነው ውይስ አንድ ጳጳስ ነው ???
  እባካችሁ ቤተ ክርቲያናትን ታደጓቸው። ወይ ሌላ አባት መድቡላቸው ወይም ደግሞ ምእመናንን ለአባ መርቆሬዎስ አሳልፋችሁ እንደሰጣችሁ ሊሆን ነው።

 2. Anonymous May 30, 2013 at 7:33 am Reply

  Egziabher begowun yaserachihu!

  አይ ዶክትሬት ¡

  ‘ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’ እንደሚባለው አቡነ ጢሞቴዎስ የቅ/ሥ/መ/ኮሌጅ ዲን የሆኑበት ምክንያት ዶክትሬት ዲግሪ አላቸው ተብሎ ነበር፤ ነገር ግን የዶክትሬት ዲግሪ ቀርቶ የባችለር ዲግሪ የሌላቸው መሆኑ በቅርቡ የተቋቋመው ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ አረጋግጧል፡፡ በማጭበርበር ሥራቸው የሚታወቁት እኒህ ሰው ተማሪዎች ይነሱልን ያሏቸውን ሁለት መምህራን ‘አቻ የሌላቸው ናቸው’ ቢሏቸውም የማስተርስ ዲግሪ እንደሌላቸው በኮሚቴው ተጣርቷል፡፡ አባ ጢሞቴዎስ ዓለም አቀፍ በሆነው የትምህርት ሙያ ላይ ሁለቱን መ/ራን የማጭበርበር ወንጀላቸው ተባባሪ አድርገዋቸው ቢቆዩም በአዲሱ ትውልድ ቴክኖሎጂያዊ ስልት ሀገርን እና ትውልድን የመካድ ወንጀላቸው ተጋልጦ ወጥቷል፡፡ ይህንንም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተወካይ እና የፓትርያርኩ ተወካይ አጣሪ ኮሚቴዎች አረጋግጠዋል፡፡
  አባ ጢሞቴዎስ ከላይ የተጠቀሰው ወንጀላቸውን ለማፈን ሲሉ ለፋሲካ በዓል ብቻ ለተለያዩ ባለሥልጣናት ከ 20 በላይ በጎችን በስጦታ አበርክተዋል፡፡ ከባለሥልጣናቱ መካከልም በዋናነት አባይ ፀሐየ እና የወረዳ 09 የደህንነት ተጠሪው አቶ ሰሎሞን መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በ 20/09/2005 ዓ.ም. ደግሞ ወንጀልን የማይጠየፉት አባ ጢሞቴዎስ ሌሎች የወንጀላቸው ተባባሪዎችን አቡነ እጢፋኖስን፤የተሃድሶ ደጋፊ የሆኑትን አቡነ ሳዊሮስን እና አቡነ ፋኑኤልን፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተስፋየን እና የአስተዳደር መምሪያ ሐላፊ የሆኑትን አቶ ተስፋ ጊዮርጊስን በቤታቸው በመጥራት ሶስት በጎችን በማረድና ውስኪ በማውረድ ሲጋብዟቸው አምሽተዋል፡፡
  አቡነ ጢሞቴዎስ የ 21 ሚሊዮን ብር ዕዳቸውን፤ በአጣሪዎች የተጣራው የውሽት ዶክትሬት ዲግሪ ወንጀላቸውን እና ትውልድን ገድሎ ቤተ ክርስቲያኒቷን ጨፍልቆ ለመኖር ከላይ የተዘረዘሩትን ግለሰቦች በመጋበዝና በግብዣው ፕሮግራም ላይ ‘ ከተማሪዎች ውንጀላ ጠብቁኝ እኔም በያላችሁበት ሥልጣን እጠብቃችኋለሁ’ የሚል ቃል ኪዳን ፈጽመዋል፡፡ ሆኖም ፓትርያርኩ ከሌሎች አባቶች ጋር በመሆን የአባ ጢሞቴዎስን ሴራ ሳይቀበሉ ለስማቸው እና ለቤተ ክርስቲያናቸው ቢሰሩ መልካም ነው እንላለን፡፡

  የግብዣው አላማና ምክንያት
  አቡነ እስጢፋኖስን በሲኖዱስ አስመርጠው ጠቅላይ ሥራስኪያጅ ለማስደረግና በአጣሪዎች የተገለጠው ወንጀላቸውን ለማፈን ሲሆን ሌሎች ተጋባዦች ደግሞ ለአቡነ እስጢፋኖስ መመረጥ ተግባራዊነት እንዲሯሯጡ ማድረግና ቤተ ክርስቲያኒቷን ለመዝረፍ ነው፡፡
  ለመሆኑ አቡነ እስጢፋኖስ ማን ናቸው?
  በሁለቱ ዞኖች መካከል ያለውን የጤፍ ቂጣ የጋገሩት እርሶ እንደሆኑ ዘገባዎች ይገልጣሉ፤ ቂጣውስ ይጣፍጣል?¡
  ገንፎ ተመጋቢ እና ሥጋ በል እንስሳ መሆንዎን በየካቲት ወር የተመረመሩት የደም ውጤትዎ ያስገነዝባል፡፡
  እኒህ ሰው የጠ/ቤ/ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ ፈጽመው በአቡነ በርተሎሜዎስ፤ በአቡነ አረጋዊ እንዲሁም ከመንግስት በኩል አቶ አብርሃ ተጠምቀና ሌሎች ኮሚቴዎች በወቅቱ ባጣሩት መሠረት ከቤተ ክርስቲያኒቷ የኪራይ ቤቶች ብቻ ስድስት ሚሊየን ብር በጉድለት ተመዝግቦባቸዋል፤ ዳኛ በመጥፋቱም በእንጥልጠል ላይ ይገኛል፡፡ አዲሱ ፓትርያርክ ዳኝነት ይሰጡበት ይሆን ወይስ አብረው ተመሳስለው ይቀጥሉ? በሌላ በኩል አቡነ እስጢፋኖስ የአ/አ ሀገረ ስብከት ሥራአስኪያጅ በነበሩበት ወቅትም የድራፍት ቡድኖችን ያደራጁ፤ ሙስናን ያጠናከሩ፤ አለቆችን ሊጥ አቡኪና ኬክ ተሸካሚ ያደረጉና ለአስራ አምስት ዓመታት በአድርባይነት በሀ/ ስብከቱ ከፍተኛ ሴራ የፈጸሙና በአዲሱ ፓትርያርክ ምርጫ ወቅትም ሕዝቡንና ቅዱስ ሲኖዱስን ያታለሉ ዘላን አባት ናቸው፡፡ የማይድን የጭን ውስጥ ቁስላቸውን እናክምሎታለን በሚሏቸው የደህንነት ተጠሪው አቶ ሰሎሞን፤ የወረዳ 09 ኮማንደር አቶ ሐይሉና እነሱ የሚያዟቸው ተልከስካሽ ደህንነቶች ከመጥፎ ድርጊታቸው ሐኪም ሆነው ላያድኗቸው ዘላኑ ጳጳስ መውጣት ከማይችሉበት አዘቅት ለመግባት በዋዜማው ላይ ይገኛሉ፡፡ ስውር ምሽግዎ እንዳይሰበር፤ ከነ ጉድዎ በቴክኖሎጂው መስኮት እንዳይለቀቁ ይጠንቀቁ ተብለው ነበር ከዚህ በላይ እርሶ ያውቃሉ፡፡ ዶክተር ሳይሆን ዶክተር ነኝ ከሚል ማየት ከተሳነው ሰው ጋር የሚገምዱትን ቤተ ክርስቲያኒቷን ከማውደም ተግባር ቢታቀቡ መልካም ነው፡፡ የኮተቤውና የሲ ኤም ሲው ጉድዎ ይፋ ሊወጣ ትንሽ ቀርቶታል፡፡
  በ 21/09/2005 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት የምስራቅ ሸዋ ሀ/ስብከትን እንዳይድን አድርጎ የገደለው አቡነ ጎርጎርዮስ፤ የቅ/ሥ/መ/ኮሌጅን የገደለው አቡነ ጢሞቴዎስ እና ሥራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን ያወደመው ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ሆነው የሴራ ጥንስሳቸውን ሲጠነስሱ፤ ሲበጠብጡና ሲጠጡ ማምሸታቸው ታውቋል፡፡ ምናልባት ፓትርያርኩ ይልቁንም ደግሞ የሲኖዶሱ አባላት አይቀበሏቸውም እንጂ ከተቀበሏቸው የስድስት ሚሊዮን ብር ባለዳውን እና ብልሹ አሰራርን እንዲያንሰራራ ያደረገውን አቡነ እስጢፋኖስን የጠ/ቤ/ሥራ አስኪያጅ ለማድረግ የተደረገ ስብሰባ መሆኑ ተደርሶበታል፡፡ የቤተ ክህነት ጉድ መች ያልቅና ምናልባት ፓትርያርኩ ምን እንደሚያደርጉ ባይታወቅም እስካሁን የነበረው አሰራር ግን ሌባውን እና ዘራፊውን መሾም አጭበርባሪውንና አታላዩን መሸለም እንደነበር አይረሳም፡፡ ታዲያ አሁንስ ምን እንዲሆን ይጠበቃል? የቀድሞው ሌቦች የሀያ አንድ ሚሊዮን ባለዳውና የውሸት ዶክትሬት አለኝ የሚለው አባ ጢሞቴዎስ፤ የስድስት ሚሊዮን ባለዳው አቡነ እስጢፋኖስ የአዲስ አበባ ሀ/ ስብከትን ለከፍተኛ ምዝበራ ዳርጎት ያለፈው ንቡረ ዕድ ኤልያስ የፓትርያርኩ የቅርብ አማካሪ ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል የናዝሬትን ሀ/ስብከት ወደፊት እንዳይራመድ ያደረገው አቡነ ጎርጎርዮስ እና ሁለቱ አቶዎች አቶ ተስፋየ እና አቶ ተስፋ ጊዮርጊስ የመሳሰሉት ጭፍንና ለነገ የማያስቡ የጋማ ከብቶች በፓትርያርኩ ዙሪያ እያንዣበቡ መልካም የሚሰሩ በመምሰል ፓትርያርኩን እያፈኗቸው ነው፡፡ ስለዚህ ፓትርያርኩ ከእንደነዚህ ዓይነት ጭፍን ሰዎች ርቀው የተለያዩ ባለሙያዎችን ይዘው ካልሰሩ ሲኖዶስም ጠንካራ አባቶችን መርጦ አብረዋቸው እንዲሰሩ ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያ የፍየልና የእርያዎች መሰማርያ የምትሆንበት ጊዜው ሩቅ አይደለምና የሲኖዶሱ አባላትም በየሀ/ስብከታችሁ ያለው ሕዝብ ዓይናችሁን ላፈር እንዳይላችሁና መግቢያ እንዳታጡ ፤በትውልድም ተወቃሽ እንዳትሆኑ የማንንም ጣልቃገብነት ሳትቀበሉ ፍትሀዊና ሕጋዊ ሥራ እንድትሰሩ እንጠይቃለን፡፡አባቶቻችን በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ የተለያዩ ድርጅቶችን፤ ፋብሪካዎችን፤ ሆስፒታሎችን፤ ዩኒቨርሲቲዎችን፤ት/ቤቶችን እና የጤና ኬላዎችን ልትከፍቱልን ሲገባ ቤተ ክርስቲያኒቷን የዘረኝነት፤ የዝሙት፤ የውሸት ፤ የፖለቲካ፤ የጉቦኝነት፤ የአድማና የብልሹ አሰራር መጫወቻ ሜዳ ስላደረጋችኋት ከ 8 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከናንተስ ሌላው ይሻላል እያለ ኮብልሏል፤ አሁንም ሕዝቡ ከቤተ ክርስቲያኒቷ እየራቀ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን የወንጀል ሁኔታዎች በአጣሪዎች ሪፖርት መሠረት አስቸኳይ ውሳኔ እንድትሰጡና በሚሰጧችሁ አስተያየቶች መነሻነት ጉድለቶቻችሁን እያረማችሁ ወንጀለኞችን ለፍርድ እያቀረባችሁ እንድትሰሩ ሕዝባዊ አስተያየታችንን እናቀርባለን፡፡

 3. Anonymous May 30, 2013 at 9:38 am Reply

  የፕሮፌሰሩ ትዝብቶች
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አከርካሪቷ ተሰብሯል እየተሰበረም ነው/ አቦይ ስብሐት ነጋ/ ከኢህአዴግ ባለሥልጣን፡-
  ኢህአዴግ ለቤተክርስቲያኒቱ የሚመኘውን ውድቀት ለማፋጠንና ኢህአዴግ ያሰበው ይፈጸም ዘንድ ዳዊትና ሰሎሞን የተባሉ የኢህአዴግ ደህንነቶች የቅዱስ ሲኖዶሱ ተሰብሳቢ የሆኑትን እና ሐሳባችን አይቀበሉም ብለው የሚገምቷቸውን ሊቃነ ጳጳሳት የቤት በር እያንኳኩ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡
  ከኢህአዴግ ጐን በመሰለፍ ቤተክርስቲያኗን ተራ ተቋም ለማድረግና ጥንታዊነቷን፣ ታላቅነቷን፣ ባለውለታነቷን፣ ባለታሪክነቷን እና የቀደመ ክብሯን ለማሳጣት ሳይገባቸው በጭፍኑ እየሠሩ የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡፡
  1. በልከኝነታቸውና በጭፍን አስተሳሰባቸው የሚታወቁት አቡነ ጢሞቴዎስ አሁንም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን እየበጠበጡና እያበጣበጡ የሚገኙት ናቸው፡፡
  2. አቡነ እስጢፋኖስ ጅማ ሀገረ ስብከት ጉዴ ይወጣል በማለት ከተለያየ ባለሥልጣን ጋር ተሸጉጠው የሚኖሩት፡-
  3. በመሀይምነታቸው የሚታወቁት አቡነ ሳዊሮስ
  4. አቡነ ኤልያስ
  5. አቡነ ቀለሚንጦስ
  6. አቡነ ጎርጎሪዎስ ዝዋይ
  7. አቡነ ኤጲፋኒዎስ
  8. አቡነ ፋኑኤል
  9. አቡነ ማርቆስ ጐጃም
  10. አቡነ ሙሴ
  11. አቡነ ኢሳይያስ
  12. ሌሎችም መስማት፣ማየት እና ማሰብ ያቆሙ አረጋውያን ጳጳሳትም አሉበት፡፡ ለነዚህ ቀንደኛ ተባባሪና ጐንጓኝ የጢሞቴዎስ የቅርብ ወዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት አቶ ባያብል የሚባል ምዕመን አለበት፡፡
  የቤተክርስቲያንና የመንግሥት የመለያየት ጉዳይ
  (Separation of Church and State)
  የቤተክርስቲያንና የመንግሥት የመለያየት ነገር ሲነሳ ጽንሰ ሐሳቡ በአግባቡ መታየት ይኖርበታል፡፡ ቤተክርስቲያን መንግሥት አይደለችም የመንግሥት ተልዕኮም የላትም፡፡ መንግሥትም የቤተክርስቲያን ተልዕኮ የለውም መራጭም አይደለም ቀዳሽም አወዳሽም ሳይሆን እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ገብቼ ልዘዝ ልምራ ማለት በቀደሙት ከመንግሥታቸው ሲሶ በሰጡት እንኳ አልታየም በሌላው አቅጣጫ መንግሥት ቤተክርስቲያን አይደለም በተልዕኮውም ቤተክርስቲያንን ሊወክል አይችልም አይገባውምም፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ሁለት ተቋማት የሚገኙበት እና አንዱ በሌላው ተጽእኖ (Influence) የሚኖሩበት ሁኔታ በግልጽ በተግባር ይታያል፡፡ በዚህ ጉዳይ ወይም በዚህ ዙሪያ ሦስት አመለካከቶች ይንፀባረቃሉ፡፡ አንደኛው መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን አንዱ ሌላውን እየተካ በአሠራርም ይሁን በአመራር ያለመለያየት መሥራት ይችላሉ የሚል ሲሆን 2ኛው ደግሞ መንግሥትና ቤተክርስቲያን ምንም የሚገናኝ ሚና የሌላቸው የተለያዩ ግብና ዓላማ ያላቸው የተለያዩ ተቋማት ናቸው፡፡ በሕገመንግሥቱም መንግሥት በሃይማኖት ጣልቀ አይገባም አንቀጽ 11 የሚል አቋም ተደንግጓል፡፡ ሦስተኛው አመለካከት ግን እንደተቋማት የተለያዩ መሆናቸውን ተቀብሎ፣ ማህበራዊ በሆነ ዓላማቸው በተለይም ሞራላዊና ሥነምግባራዊ በሆኑ ጉዳዮች ግን ተወራራሽነት ሊኖር እንደሚችል ያወሳል እንጂ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን የፖለቲካ መጠቀሚያ ሊያደርጋት በፍፁም አይቻልም፡፡ ቃለ እግዚአብሔር የሚለውን እንመልከት
  • “ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር፡፡” ማር12፡-13-17 የሚለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ከአውዱ ውጭ እየተተረጐመ አግባብነት ለሌለው ዓለማዊ ሴኩላር (Secular) አስተምህሮ መንገድ እንዲከፍት ጥንቅቄ ማስፈለጉን በቅድሚያ ማስገንዘብ ይገባል፡፡ ስለሆነም የቃሉ ሥነ አፈታት በትክክል መታየት ይኖርበታል፡፡
  የወንጌሉ ክፍል በአግባቡ ስንመለከተው የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ለተጠየቀው ጥያቄ ከሚጠበቀው መልስ ባሻገር ሁለት ሥልጣናት እንዳሉ ያመለከትና ሰዎች ለሁለቱም ሥልጣናት መገዛት እንዳለባቸው ያስገነዝባል፡፡ የትኛው ሥልጣን የበላይ እንደሆነ ለሰሚዎቹ ግልጽ ነበር፡፡ ለእግዚብሔር መገዛት ለቄሳር ከመገዛት አይከለክልም፣ ቄሳር በስፍራው የተቀመጠው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ይህን ክፍል በመጥቀስ ብዙዎቹ እንደሚሉት መንግሥት ሴኩላር (Secular) ምድራዊ፣ የእግዚአብሔር ደግሞ መንፈሳዊ፣ ወይም ሰማያዊ እንደሆነ የሚያመለክት አነጋገር የለውም፡፡ የእግዚብሔር ሥልጣን በሁሉም ላይ ነው፡፡ ባለሥልጣናት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፡፡ ሮሜ.13፡4
  • በሁለቱም ተቋማት ተልዕኳቸውን፣ ዓላማቸውንና ኃላፊነታቸውን ሳይዘነጉ፣ ከተወሰነላቸው ድንበርም ሳይዘሉ አንዱ ከሌላው ጋር ሳይጣረስ፣ በውስጥ አስተዳደራቸው ጣልቃ ሳይግባቡ ተደጋጋፊ በሆነ መልኩ ግን ለማኀበረሰብ ጥቅምና በጐነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን እና ሰውን ማገልገል የክርስቲያን መብት ነው፡፡ ዘኁል 3፡6፣ ማር 1ዐ፡44
  • ጣልቃ አለመግባት ማለት ግን ቁጥጥርና ሚዛናዊነትን (Check and balance) በህብረተሰብ ዘንድ ለማስገኘት አለመጣር ማለት አይደለም፡፡ በዚህም ረገድ አንዱ ተቋም የሌላውን በጐ ጐን እየደገፈ በጐደለበት ወገን ደግሞ እያስተካከለ እና እርምት እያደረገ ለማህበረሰብ መልካም አስተዳደር በትብብር መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በማንኛውም ተቋማዊ አሠራር ቁጥጥርና ሚዛናዊነት መጠቀም ይከተላል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ሁለት ተቋማት አንዱ የሌላውን አሠራር የሚመለከትበትና የሚቆጣጠርበት አሠራር መዘርጋት አስፈላጊነቱ የጐላ ነው፡፡
  • ማንነቷን በመረዳት በተክርስቲያን እራሷን ለማንኛውም ፖለቲካና አስተሳሰብ ዘይቤ ሳትገዛ ይልቁንም ሁሉም አገልጋዮቿ፣ አስተሳሰቦች እና ዘይቤዎች የሚመዘኑበት መመዘኛ በቅዱስ ቃሉ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ይህንንም ለማጽናት እምነቷን በተግባሯ በመግለጽ በንጽህና በቅድስና እራስንም በመግዛት ምሳሌያዊ ሕይወት እንዲኖራት ያስፈልጋል፡፡
  • ከማንነቷ የተነሳ በውስጧ ያሉትን ወገኖች ባላቸው ግለሰባዊም ሆነ ማህበረሰባዊ አቋም ሳትለያይ ሁሉን እኩል በማየት ልታገለግል ይጠበቅባታልለ፡፡ ድምጽ አልባ የሆኑትን ስውር ደባዎች የራሷን አገልጋዮች ሌላው አካል መሣሪያነት እንዳይጠቀምባቸው ልትከላከል ይገባል፡፡ የተጠቁትን ልትታደጋቸው፣ ለተቸገሩት እጆችዋን ልትዘረጋ በአጠቃላይ ማህበረሰባዊ ተልዕኮዋንም ልታስብ ከእግዚአብሐር የተሰጣት ኃላፊነት ነው፡፡
  • ከህብረተሰቡ ዘንድ የመልካም አስተዳደር እሴቶች እንዲዳብሩ ብሎም ሰዎች ሁሉ መብቶቻቸውንና ግዴታዎቻቸውን አውቀው በመቻቻልና በመተባበር ለጋራ ጥቅም መሥራት እንዲችሉ እንጂ አንዱ አንዱን የጥፋት መሣሪያ አድርጐ መጠቀም ፍፁም ክህደት ነው፡፡ የተለያዩ መድረኮችም ሆነ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮችን በመጠቀም የታላቋን ቤተክርስቲያን ገጽታ ማበላሸት ሌላው የታሪክ ስህተት ነው፡፡
  ያረጀ አስተሳሰብ በዕድገትና በለውጥ ላይ ያለው ተጽእኖ፡-
  እርጅና /እርግና/ አረጀ /አረገ፣ አሪግ/ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም አሮጌ ሆነ፣ ሸመገለ፣ አፈጀ፣ ኢሳ.46፡4 ማለት ነው፡፡ በሌላም በኩል አሮጌነት፣ ሽምግልና የሚል ትረጉም ይሰጣል፡፡ ኢዮ.21፡7፡፡ (ደስታ ተክለ ወልድ አዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ አርቲስቲክ ማተሚያቤት፣ አዲስ አበባ 1962 ዓ/ም ገጽ 131)
  እርጅና በሁለት የሚከፈል ሲሆን የመጀመሪያው በእድሜም አነስተኛ፣ መካከለኛም ሆነ ትልቅ ቢሆንም ካሮጌ አስተሳሰብ አለመላቀቅን የሚያመለክት ነው፡፡ ሁለተኛው ከእድሜ ትልቅነት ጋር የተያያዘ እና የውጫዊ አካል መድከምን የሚያመለክት ሆኖ በመዝገበ ቃላቱ እንደ ተመለከተው ከ7ዐ ዓመት በላይ እንደሚከሰት ይገልጻል፡፡ ይህ ግን ከአዕምሮ ወይም ከሌላ የውስጥ ሰውነት ጋር ተያያዞ ችግር ካልተፈጠረ ወይም ቅንነት ከማጣት ጋር ካልተቆራኘ በስተቀር የአስተሳሰብ ማርጀትን አያመለክትም፡፡
  በእርጅና ወቅት ከቅንነት ማጣት ጋር በሥራ ላይ ያውም በአስተዳደር ስራ ላይ መሆን የራሱ ተጽዕኖ አለው፡፡
  እርጅና እና ሽምግልና አንዳንዴ የሚመሳሰሉበት ጊዜ አለ በእርጅና ወይም በሽምግልና እድሜ ላይ ማስተዋልና ጥበብ የታከለበት ከሆነ ግን ይህ የውጭ አካልን እርጅና እንጂ የውስጡን በተለይም የአስተሳሰብን የሚመለከት አይደለም፡፡ ይልቁንም መጽሐፍ “ በሽምግልና ጊዜ ጥበብ፣ በዘመን ርዝመት ማስተዋል ይገኛል” መጽ.ኢዮ.12፡12 እንደሚለው በዕድሜ የበለጸገ ሰው በተለይም በኢኮኖሚ ባደጉ ሀገራት እስከ ሀገር ማስተዳደር የሚደርስ፣ የሁሉም አባትነት ወይም እናትነት ፀጋን የተላበሰ በመሆኑ ትውልዱን ለመምራት እና በመልካም ሁኔታ ለመቅረጽ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡ በእርጅና እድሜ ላይ የሚገኝ ሰው በተለይ እግዚአብሔርን የሚፈራ እና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚያከብር ከሆነ፣ “ ቢሰሙ ቢያገለግሉትም፣ እድሚያቸውን በልማት፣ ዘመናቸውን በተድላ ይፈጽማሉ፡፡” መጽ.ኢዮ.36፡11 እንዲል እንዲህ አይነት ሰው ወገኑንም ሆነ ራሱንም ይጠቅማል፡፡ በተዋህዶ ሃይማኖቱ ፀንቶ እለተ ሞቱን እየዘከረ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖር ከሆነ ከሌላው ይልቅ ቅዱስ ዳዊት እንዳለው እንኳን በወጣትነት እና በጐልማሳነት ጊዜው ይቅርና በሽምግልናው ወቅትም ቢሆን መልካም ፍሬን ያፈራል ቀሪውንም እድሜ በተድላ በደስታ ይኖራል፡፡
  መዝ.92፡14
  ብዙውን ጊዜ ቅንነት ለጐደላቸውና በንግግራቸው እንጂ በተግባራቸው ሥራንና እግዚአብሔርን በማያውቁት፣ እድሚያቸው በእርጅና ላይ በሚገኝ ሰዎች በእጅጉ መጐዳት ነው፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚለው “ በእድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፣ ሽማግሌዎችም ፍርድን አያስተውሉም፡፡” መጽ.ኢዮ 32፡9 የዚህ ዋናው ምክንያት አምላካቸው እግዚአብሔርን አይሰሙትም፣ ቃለ እግዚአብሔርንም አያስተውሉም፣ በተለይም በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ እየኖሩና በዘመናዊ እውቀት የገፉ ሆነው በእውቀታቸው ማህበረሰቡን ማገልገል እንደሚገባቸው ካልተረዱ ማስተዋል የተሳናቸው በመሆኑ የዘወትር ተግባራቸው ለትውልዱ በተግባር ሊተረጐም የሚችል ነገር ግን ከተለያዩ አሉባልታዎች በመነሳት ራስ በሚያደነዝዝ ውሸት ላይ ተመሥርቶ ምቅኝነትና ቅናት ላይ ተመሥርቶ ተቋምንና ሀገርን የሚጐዳ መልዕክት ማስተላለፍ ብቻ ላይ ያተኰረ ይሆናል፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች እንደምእራባውያን አነጋገር “ Triangulate፣ ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች” የማየት ችግር ያለባቸው ስለሆኑ ማስረጃ ሳይዙ በመረጃ መሰል ወሬ ብቻ ተመርኩዘው “ አልተማረም “ እንደሚባል ሰው ወደ አሉታዊ ድምዳሜ ይደርሳሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸው “ አበረከትነው” በሚሉት ውሸት ላይ አስተዋጽኦ ስለመጣው ለውጥ ሣይሆን ስለሠሩት ሥራ፣ የቱን ያህል በቤተ ክርስቲያኗ የደረሰው ጉዳት ምስክር ነው፡፡ ሠራነው ከሚሉትም ሥራ ይልቅ እራሳቸውን ማጋነን ከኛ ወዲያ ላሳር የሚሉ ናቸው፡፡ መቼም አንድ ሰው ህፃን ልጁን ቆሞ አያጫውትም፣ እንደ እድሜው ሁኔታ በማየት ወደ መሬት ዝቅ ብሎ እንደ ህጻኑ አስተሳሰብ ሆኖ ከጨዋታ ባለፈ ቁም ነገርን ያጋራዋል እንጂ፡፡ አሁን የምንለው አይነት ሰዎች ከላይ የተጠቀሰው አይነት ስለሆኑ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫም ቢሆን እራሱን መምራት ብቻ እንጂ ቤተሰብም ሆነ ከቤተሰብ ከፍ ያለ ተቋም መምራት ቢያስብም ይከብደዋል፡፡ እንደእነዚህ አይነት ሰዎች ያለባቸው የግለኝነት ጸባይ እየባሰባቸው ስለሚሄድ እራሳቸውንም አይለውጡም፣ ያሉበት ተቋምም ወደለውጥ እና መሻሻል እንዲያመራ ፈቀደኞች አይደሉም፡፡ ታዋቂው የአየርላንድ ተወላጅ ደራሲና ኢኮኖሚስቱ ጆርጅ በርናንድ ሸው ስለመሻሻል እና ለውጥ ሲናገር፡- “Progress is impossible without change, and those who cannot change their minds cannot change anything”፣ ለውጥ ከሌለ መሻሻል የሚታሰብ አይሆንም፣ የራሳቸውን አስተሳሰብ የማይለውጡ ሰዎችም ምንም ነገር መለወጥ አይችሉም ማለቱ በዓለማችን ይልቁንም በሀገራችን ከዚያም ዝቅ ባለ በመሥሪያ ቤታችን መሻሻል ከለውጥ ጋር የሚሄድ እና አስፈላጊ እንደሆነ የሚጠቁም እና ራሳቸውን ለለውጥ ያላዘጋጁ ለተቋሙ መሻሻል የማይፈይዱ መሆኑን ጠቋሚ ነው፡፡
  ከዚህም ጋር በተያያዘ ቅን አስተሳሰብ የሌላቸው እድሜአቸው ሳይሆን አስተሳሰባቸው ያረጅ ሰዎችም ለለውጥ ዝግጁ አይደሉም፡፡ ለራሳቸው የተሻሻሉ እና እያሻሻሉ ያሉ ቢመስላቸውም ቅንነት የሚባል ነገር እንኳን በውስጣቸው ሊኖር ቀርቶ በላያቸውም ላይ ስላላለፈ ለውጥን እጅግ ይፈሩታል፡፡ እነዚህ ሰዎች መ/ቤታቸውን እንደ አንድ ግል ሀብት የያዙት ስለሆነ ወደ ሌላ መሥሪያ ቤት እንኳ ቢሄዱ ውስጣቸው ያለው ጠማማነት ካልለመዱት ሰው ጋር በቀላሉ እንደማይቀላቀላቸው ስለሚያውቁ እና ስለሚረዱ ያው የፈረደበት ጡረታ መጥቶ (በቅንነትና በትክክለኛ አመራር የሚያስተዳድር ሲኖር) ሲገለሉ ወይም በማይቀረው ሞት ሲገላገሉ ብቻ በግድ የሚለቁ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ለሀገር በተለይም ለተቋሙ መሞት ተጠያቁ መሆን የሚገባቸው ይልቁንም በፈጸሙት እኩይ ተግባር እግዚአብሔር በሰጣቸው ጊዜ ተጠቅሞ ንስሐ ካልገቡ ከመሞታቸው በኋላ በነፍሳቸው ዘለዓለማዊ ቅጣት እስኪያገኙ ድረስ ሰቆ.ኤር.3፡64፣ አግባብ ባለው ፍርድ ቤት መቅረብ ይገባቸዋል፡፡ ለወደፊት ባለው ጊዜ ግን አንድ መሥሪያ ቤት ተቋማዊና ግለሰባዊ ተጠያቂነት ያለበት አሠራርን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ይህን ፈጣን የመዋቅር ለውጥ ማካሄድ እና ሠራተኛው ውጤትን መሠረት አድርጐ በሥራው የሚመዘንበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፡፡ በየጊዜው ወቅቱን የጠበቀ ስራንና የመሥሪያ ቤቱን ተልዕኮ ከማስፈጸም አኳያ ወቅታዊ የሥራ ግምገማ ማካሄድ እጅግ ወሳኝ እና ተቋሙን ወደእድገት ጐዳና እንዲያመራ ያግዛል፡፡
  እንደ እነ አቡነ ጢሞቴዎስ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ለመቃብር እንደዳረጉ ቤተክርስቲያንስ?
  ቤተክርስቲያኗን ከወንበዴዎች ማን ይታደግ ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: